እንኳን ለ 1443 ኛው አመተ ሂጅሪያ በሰላም አደረሳችሁ።

كل عام وانتم بألف خير

***********************************
-------------------------------------------------------------

https://www.tg-me.com/joinchat-1Vr67jA3DZU3ZGI0
የአላህ መልዕክተኛ(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል

☞ የሰላት ቁልፍ ንጽህና ነው።

☞ የሐጅ ቁልፍ ኢህራም ነው።

☞ የመልካም ስራ ቁልፍ እውነት መናገር ነው።

☞ የጀነት ቁልፍ አላህን አንድ አድርጐ መገዛት ነው

☞ የእውቀት ቁልፍ ጥሩ ጥያቄና ጥሩ ማዳመጥ ነው።

☞ የልዕልና ቁልፍ አላህን ማስታወስ ነው።

☞ የነጻነት ቁልፍ አላህን መፍራት ነው።

☞ የመልስ ቁልፍ ዱዓእ ነው።

☞ የመጪው አለም ናፍቆት ቁልፍ
በምድር ላይ መተናነስ ነው።

☞ የኢማን ቁልፍ አላህ ባሪያዎቹን እንዲያስተውሉ ወዳዘዘው ነገሮች ላይ አስተውሎ ማድረግ ነው።

☞ የልቦና ሕይወት ቁልፍ ቁርዓንን በተመሰጥኦ ማንበብ(መቅራት) ለሊት ተነስቶ አላህን ከልብ መለመንና ኃጢያቶችን መተው ናቸው።

Good Night😘

@bekri2 👈👈👈
#የዐሹራእ_ቀን


የዐሹራእ ቀን ሚባለው ከሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ነው። በዚህ ቀን #የተከሰቱ ድንቅ ነገሮች ⇩

አሏህ ነቢዩሏህ ኑሕንና በሰፊናው የነበሩትን ከውሃ መጥለቅለቅ አድኗቸዋል።

ነቢዩሏህ አደም ከዛች ትንሽ ስህተት አሏህ ይቀር ብሏቸዋል።

ነቢዩሏህ ሙሳንና ተከታዮቻቸን አሏህ በውሃ ከመስመጥ አድኖ ፊርዓውንና ተከታዮቹን በማስመጥ አጥፍቷቸዋል።

አሏህ ነቢዩሏህ ዩኑስን ከአሳ ነባሪ ሆድ አድኗቸዋል።
_
ነቢዩሏህ ዒሳ ወደ ሰማይ አርገዋል።

ነቢዩሏህ ዩሱፍ ከነቢዩሏህ የዕቁብ ጋር ተገናኝተዋል።

ነቢዩሏህ አዩብ ከህመማቸው ሽረው ችግሮች ተነስተውላቸዋል።

ሰይዱና ሑሰይን [ረዲየሏሁ ዐንሁ] ከርበላእ በተባለ ቦታ ላይ ተግድለዋል። ሲገደሉም ኮኮቦች በቀን ታይተዋል፤ በሰማይ ያሉ መላኢካዎች አልቅሰዋል፤ በምድር ያሉትም ደጋጎች አልቅሰዋል።

**የዐሹራእ ቀንን መፆም ሱና ነው። ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ መዲና በገቡ ጊዜ የሁዶች የዐሹራእ ቀንን ፆመው አገኟቸው ...
#መልዕክተኛውም_ﷺ የምን ፆም ነው ምትፆሙት ? ብለው ጠየቋቸው ...
#እነሱም፦ በዚህ ቀን አሏህ ሙሳንና ህዝቦቹን በውሃ ከመስመጥ አድኖ ፊርዓውንና ህዝቦቹን አስምጧቸዋል። እናም ሙሳ አሏህን ለማመስገን ይህን ቀን ጹመውታል አሉ ...

#መልዕክተኛውም_ﷺ ለመፆም ባለቤቶችም በላጮችም እኛ ነን አሉ። ከዛም ነቢዩ ﷺ 10ኛውን ቀን ፆሙ ሱሓበቶችንም እንዲፆሙ አዘዙ።

#ሙስሊም እንደዘገቡት መልዕክተኛው ﷺ እንዲህ አሉ« ከረመዷን ቀጥሎ በላጩ ፆም ከአሏህ ዘንድ የተላቀው የሙሐረም ወር ነው ከግዴታ ሶላቶች በላጩ የለይል ሶላት ነው።»

የሙሐረምን 9ነኛውን ቀን መፆም ሱና ነው ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ « እሰከ ሚመጣው አመት ከቆየሁ ዘጠነኛውን ቀን እፆማለሁ» ብለዋል። #ሙስሊም እንደዘገቡት።

ኢማሙና #አሽሻፊዒይ [ረዲየሏሁ ዑንሁ] እንዲህ አሉ ፦“ ከሙሐረም ወር #9 #10 #11 እንዚህን ሶስት ቀናቶች መፆም ይወደዳል ብለዋል።

@bekri2 👈👈👈
🔴የአሹራ ፆም የፊታችን ሐሙስ ሙሐረም 10 ነው:: 9ኛውን እና 10ኛውን ቀን ለመፆም የፈለገ እሮብ እና ሐሙስ መፆም ይችላል!በካላንደሩ ላይ ያለው ቀን ማስተካከያ እንዲደረግበት የሳኡዲ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አዟል።
#ሙሀመድዬ 💚

⇛ በዚች ምድር ላይ እንደ ረሱል ﷺ ያፈቀረ እንደሳቸውም የተፈቀረ የለም ወደፊትም አይኖርም!!

⇛ በዚህች ላይ እንደ ረሱል ሙሉ ታሪካቸው የኑሮ ምድርእና እያንዳንዶ እንቅስቃሴ የተከተበ ሰው የለም።

⇛ ቢዚህች ምድር ላይ እንደ መሀመድ የሚለው ስም መጠሪያ ያማረ የለም በስም ብዛትም አንደኛ ነው።

⇛ ከ1400 ዓመት በፊት አንድ ሰው ይወድህ ነበር! ያኔ አንተ አልተወለድክም ነገር ግን አንድ ሰው ስለአንተ ያለቀስ ነበር። ስለአንተ የአላህን ምህረት ይለምን ነበር።

⇛ ከ1400 አመት በፊት ከጀነት ያላነሰ ነገር አልተመኙልንም።

⇛ የሚወዱት የሚያፈቅሩት የሚሳሱለት ቤተሰብ ሰዎች ለአንድ ሴኮንንድ እንኮን እንዲለዩት የማይፈልጉ አያሌ ሰዎች ነበሩት ነገር ግን እኛን በመናፈቅ ትክዝ ብለው ወንድሞቼ ናፈቁኝ ብለዋል።

⇛ በቀን ውስጥ መሀመድ የሚለው ቃል ተደጋግሞ በመጠራት ከአለም አንደኛ ነው።

⇛ የነብዩ መሀመድ ስም ከፍ ተደርጎ በመጠራት አሁንም ከአለም አንደኛ ነው። በአዛን ወቅት።

⇛ አሁንም በውስጥ ወይም በልብ መሀመድ የሚለው ቃል ተደጋግሞ በመጠራት ከአለም አንደኛ ነው። በተሽሁድ ግዜ።

⇛ በአለም በተውሂድ ባንድራ ላይ የሚውለበለበው ስም የሰፈረ ብቸኛው ሰው ነብይ መሀመድ ነው።

⇛ አንድ ግዜ ብቻ በሳቸው ላይ ሰለዋት በማድረግ አስር ግዜ አላህ በኛ ላይ የሚያወርድብን ኡመት ነን።

⇛ እንደ እሳቸው አይነት ሠው ሠማይ አላንጣለለችም ፤ ምድር አልተሸከመችም ፤ ሀቢቢ ነብዩ ሙሀመድ ( ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)

Join us👇👇👇
@bekri2
@bekri2

اللهم صلي و سلم على نبينا محمد
‏”صلوا على من جلس على ركبتيه... يواسي طفلاً مات عصفوره"... ﷺ

እርግቡ የሞተችበትን ህፃን ሊያፅናና፤ በጉልበቶቹ የተንበረከከው ነብይ ላይ ሰላዋት አውርዱ!!

#صلوا_على_النبي_ #ﷺ
--------------------
🔹
🔹 #ሼር_ያድርጉት
🔹 @bekri2
ፈጅርን_አለመስገድ_ያለው_አደጋ !
እና ከዚህ አደጋ_ለመዳን_መጠቀም ያለባቹ መፍትሄዎች!
1) የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት
መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!!
[ቡኻሪና ሙስሊም]
2) የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡
በአንድ ወቅት ነብዩ
(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው
ተወራ፡፡ ይህኔ
እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው
ነው!” አሉ፡፡
3) የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ
ሲሳይ ትሆናለህ፡፡
ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ
ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ_ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና
እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡
[ቡኻሪና ሙስሊም]
4) ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ
እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ
ወሰለም
እንደተላለፈው አንድ ሰው
ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን
ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ
እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ
መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡
ቂያማ_እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ
መልኩ የሚሰቃየውን
ሰውየ ምንነት ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ
ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡
ወንድም እህቶች ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጉ፡፡
ወቅቱን_ጠብቃቹ_እንድትሰግድ_የሚያግዛቹሁን_ብልሃትም ተጠቀሙ!
1) በጊዜ ተኛ! የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከዒሻ
በፊት እንቅልፍ፣
(ከዒሻ) ቡኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
2) ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር
ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ
የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ
ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡
3) ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ
ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ
ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለ አላርም
እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለ እውነት ከባድ
የሞራል ልሽቀት ነው፡፡
4) ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት
ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ
ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡
5) በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ
ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን
አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50
ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ
ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ_ፀጋ_ሁሉ_በላጭ
እንደሆነች እራስህን አስታውስ!
6) በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር
ካለህም እሰየው!
ይህን መልእክት ለእህት ወንድሞች በማስተላለፍ ከዚህ አደጋ ይታደጓቸው።

ይቀላቀሉን

👇👇👇👇👇
@bekri2
አጂብ ልብ የሚነካ ታሪክ እባከወን ካነበቡ ቡሓላ እርሶወጋ እንዲቀር አይፍቀዱ!

የገንዘብ_ደሀ እውቀትን ፈላጊና አላህን ፈሪ የሆነ ወጣት ነበር

አንድ ቀን በጣም ስለራበው ረሀቡን የሚያስታግስለት ነገር ፍለጋ ከቤቱ ወጣ ነገርግን ምንም አላገኘም በመንዱ ላይ እያለ አንድ የአትክልት ቦታ አገኘ ቦታው በapple 🍎 ፍሬዎች የተሞላ ነበር አንዷ ዛፍ ወደመንገዱ ወጣ ብላ ስለነበር አንዷን በልቶ ረሀቡን ማስታገስ ፈለገ አንድ apple 🍎 ቆርጦ በላ ወደቤቱ ከተመለሰ በኃላ ግን ነፍሱ ትወቅሰው ጀመር _ ከነፍስም ራሷን የምትወቀስ ጥሩ ነፍስ አለችና_ እንዴት የኔ ሀቅ ያለሆነን ወይም ባለቤቱን ሳላስፈቅድ እበላለሁ ? አለ። ተመልሶ የአትክልቱን ባለቤት ፈልጎ ካገኘው በኃላ በጣም ራበኝና ከአትክልት ቦታህ ሳታውቅ ሳላስፈቅድህ አንድ apple 🍎 በልቻለሁና አሁን ላስፈቅድህ _ ይቅር እንድትለኝ መጥቻለሁ _ አለው ። ባለቤቱ ግን ይቅርታ አላደርግልህም እንደወም የቂያማ ቀን እተሳሰበሀለው አለው ወጣቱ ያለቅስ ይቅርታ እንዲያደርግለትም ይማፀነው ጀመር ባለቤቱ ጥሎት ሄደ ለዐስር ሰላት ሲወጣ አሁንም ወጣቱ እያለቀሰ ያገኘዋል ወጣቱ ይቅርታ እንድታደርግልኝ የፈለከውን አደርጋለሁ ቀሪ እድሜየን ለአትክልት ቦታህ አገልጋይ ልሁን አለው ባለቤቱ ይቅርታ ላደርግልህ ዝግጁ ነኝ ግን በመስፈርት ነው አለው መስፈርቱም ልጄን ልታገባ ነው ~ ወጣቱ በመስፈርቱ ተደነቀ ባለቤቱ ቀጠለና ልጄ ግን አታይም ፣ አትሰማም ፣ አትናገርም አትንቀሳቀስም እሷን ታገባለህ ! መስፈርቷን አምኖ የሚቀበልኝ ስፈልግ ጊዚያት አልፈዋል አለው ወጣቱ እንዴት መኖር እንደሚችል አሰበ የአትክልቱ ባለቤትም ቀጠሮህ ሀሙስ ነው የመህር እና ለግብዣ የሚሆን ነገር በኔ ነው አታስብ አለው የቀጠሮው ቀን ደርሶ ወደ ሙሽራዋ ገባ ••• አሰላሙ ዐለይኩም ባሌ አለችው ወጣቱ በጣም ደነገጠ የሚያየውን ነገር ማመን ከበደው በጣም የተዋበች ናት ወጣቷ ነገሩ ስለገባት ፦ አባቷ ለሱ ያለውን አስረዳችው
• አዎ ! አይኔ የታወረ ነው ሀራም አይቼ አላውቅም
• ምላሴ ሀራምን አልተናገርም
• ጀሮየም ሀራምን አልሰማም
• እግሮቼም ወደ ሀራም ቦታ አልሄዱም
አባቴ ሷሊህ የሆነ ባል ፍለጋ አመታትን ቆይቷል በአንድ ፍሬ apple አላህን የፈራ በልጄ ላይም አላህን ይፈራል ብሎ ነው የመረጠህ እንኳን ደስ አለህ ! አለችው ከነዚህ ምርጥ ጥንዶች ምርጥና የታወቁ ኢማም ተወለዱ _ ኢማም አቡ ሀኒፋ➊።
__________
➊ ኢማም አቡሀኒፋ ( አቡ ሀኒፋ ኑዕማን እብን ሳቢት አል_ኩፍይ ) ከ80 እስከ 150ኛው ሂጅራ ድረስ የነበሩ የተወሰኑ ሰሀቦች ጋር የተገናኙ የሀነፍይ መዝሀብ ባለቤት ናቸው ።

Share share
👇👇👇👇
@bekri2
@bekri2
አንድ ከአላህ መንገድ የራቀ ዱንያውን በአኺራው የገዛ ወጣት ነበር። ወጣቱ የሚኖረው አላህን ሱብሃነሁ ወተዓላ ከሚፈሩ ሰዎች መንደር ሲሎን ሰዉ ሁሉ እንዲስተካከል እንዲሁም የታላቅ ወንድሙን ፈለግ እንዲከተል ይመክሩታል። ይህ ልጅ ግን የሚሰማ አይደለም። ስለ ታላቅ ወንድሙ ካነሳን አይቀር የዚህ አስቸጋሪ ወጣት የ4አመት ታላቁ ነው። ቁርዓንን ከመጨረስም አልፎ በቃሉ ሃፍዟል። እንደ ዘመኑ ሃፊዞችም ሃፍዞ ከሃፈዘው ቁርዓን ተቃራኒ አይተገብርም። ባይሆን አላህ እንዲሸመድድ በወፈቀው ቃሉ ውስጥ ያሉትን ትዕዛዛቶች እንዲሁም ክልከላዎች በጥንቃቄ ያከናውናል።

ከእለታት አንድ ቀን ይህ አስቸጋሪ ወጣት ከዚያ አላህን ከሚፈራው ከታላቅ ወንድሙ ይማር ዘንድ አባት ሁለቱን ለጉዞ ያሰናዱ ጀመር። ለታላቅ ወንድሙ የጉዞውን አላማ በደንብ ያወጉት ሲሆን ለታናሽ ወንድሙ ግን አልነገሩትም። ታናሹ አስቸጋሪ ወንድም ይህን ጉዞ ባይቀበልም አባት እናት እንዲሁም ወንድሙ እንደምንም ብለው አሳምነውታል። እነሆ በጉዟቸው ቢያንስ የታላቅ ወንድሙን ባህሪ ይላበስ በማለት ከቤት ወጥተው መጓዝ ጀምረዋል።

ከቤት የተነሱት የሱብሂን ሰላት ሰግደው ሲሆን ከረጅም ጉዞ በኋላ ወደ ረፋድ አካባቢ የሆነ ጫካ ውስጥ ይገባሉ። ይሄና ታላቅ ወንድሙ የለመደውን #የዱሃ ሰላት ለመስገድ ውዱዕ ማድረግ ጀመረ። ታናሹም እኔ አሁን መስከድ ስለማልፈልግ ሽንቴን ሸንቼ መጣሁ በማለት ከወንድሙ ተለይቶ ይጓዛል። ይሄኔ አላህ ይህን ወጣት ሊያስተካክለው ይመስል አንድ አይቶት የማያውቀውን #ፍጡር ይልክበታል። ፍጡሩን ሲመለከቱት ያስፈራል። ሰውነቱ ሙሉ በሙሉ ጥቁር ነው።አብዛሃኛው የሰውነቱ ክፍል በፀጉር የተሸፈነ ሲሆን ከድፍን ጥቁርነቱ ጋር ተዳምሮ ላየው ሰው እጅክ ያስፈራል።

ወጣቱ ይህን አላስተዋለውም ነበር። ድንገት ይህ ፍጡር ከዛፍ ላይ በመዝለል ፊት ለፊቱ ድቅን አለበት። የሚያደርገውን አጣ ተርበተበት እየሮጠም ለማምለጥ ሞከረ። ነገር ግን ሊሳካለት አልቻለም። ምክንያቱም ይህ ፍጡር በጣም ፈጣን ስለነበር ዞሮ እፊት ለፊቱ ድቅን አለበት። አንዳንዴ ስንደነግጥ ለማያወራን ነገር እንደምናወራው ወጣቱም ለዚህ ፍጡር ያወራ ይመስል "አንተ ማን ነህ?" በማለት እየተርበደበደ የተቆራረጡ ሲቃ የተናነቃቸው ቃላቶቹን ሰነዘረ።

ዳሩ ግን እንስሳ መናገር አይችልምና የዚህ #አስፈሪ #ፍጡር ምላሽ ዝምታ ነበር። ላጩን እያንጠባጠበ ከቀጭ ወደ ግራ ይዟዟራል። አንዳንዴ አፋን በሃይል ይከፍተዋል። የሚያጉረመረም ድምፁ ከርቀት ለሰማው ልብ ይሰብራል። ወጣቱ የሚሆነው አጣ። መሬት ጠበበችበት። ይሄኔ ያኔ ከአላህ መንገድ ርቆ ሲከውናቸው የነበሩትን እኩይ ተግባሮች ማስታወስ ጀመረ። እያንዳንዱ ስራው እንደ መፅሐፍ ፊቱ ላይ ይገለጥ ጀመር። የሰፈሩ ሰው፣ እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድሙ ሲመክረው እንቢ ማለቱ ቆጨው። በውስጡም እንዲህ ሲል ተናዘዘ። 'አላህዬ !! ከዚህ ጭንቅ ገላግለኝ እንጂ ዳግም አንተን ላለማመፅ ቃል እገባለሁ"

ይህንን ንግግሩን ሳይጨርስ ታላቅ ወንድሙ ከሩቅ ትልቅ ዱላ ይዞ ወደ እንስሳው መሮጥ ጀመረ።ይህም ወጣት ወንድሙን እንዲመለስ ተማፀነው። ነገር ግን ያኛውም ጀግና ስለነበር በያዘው ዱላ አስፈሪውን ፍጡር ይነርተው ገባ። እንስሳ ቢጎዳ ሳይጎዳ አይተውም እንዲሉት አንድ ተሳክቶለት ያ አደገኛ ፍጡር ታላቅ ወንድሙን አንድ ግዜ በሃይል ነከሰው። ይሄኔ በታላቅ ወንድሙ መነከስ የተማረረው ወጣት እንስሳብጅውን በሃይል ባገኘው ዱላ ቀጥቅጦ ገደለው።

ወዲያውኑ አይኑ በእንባ እንደተሞላች ወደ ታላቅ ወንድሙ በመዞር ሲመለከተው ታላቅ ወንድሙ ጣቱን ወደ ሰማይ ቀስሮ እያጣጣረ ነው። ወንድሜ!! ወንድሜ!! እያለ ቢጮህም ማንም ሊደርስለት አልቻለም። ብዙ ደም ስለፈሰሰው ወደ ቀጣዩ አለም አኺራ ሸሃዳን ብሎ በሰላም ተሰናበት።

ይሄኔ ኑበር ያ ወጣት የወንድሙን ጀናዛ አጥቦ፣እራሱን ከዚህ በፊት ጀናዛ እንደነበር በማሰብ ንፁህ በሆነ መልኩ ገላውን ታጥቦ ወደ አላህ መንገድ ተመለሰ። ከዚያም በኋላ ወደ ተለያዩ ሃገራት እየዞረ ኢልም በማካበት ሃገሪቱ ውስጥ አለ የተባለ ታዋቂ ዓሉም ለመባል በቃ።

ከዚህ አጭር ልብ-ወለድ የምንማረው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ማንኛውንም ሰው በፈለገው መንገድ ያቀናል። የፈለገውንም ያጠማል። እኛ ግን ጥሪ አድራሾች ሆነን ተሹመናል።

Share it to ur friends
👇Join our best channel👇

@bekri2
@bekri2
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
▪️ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ

🔻የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። (ሙስሊም ዘግቦታል).

اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
     ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

@bekri2 👈👈👈
🌹 ጥያቄ 🌹

👉 የወመል ቂያማ አንገታቸው ረጃጅም ሆኖው የሚቀሰቀሱት እነማን ናቸው?

💚 ነብያቶች

❤️ ሸሂዶች

🌺 ሙአዚኖች

🌸 ፆመኞች


#ሊላሂ_ተአላ_ብላችሁ ተሳተፉ😊
#መልስ

🌺 ሙአዚኖች
#ቀልብህን

≈•° በሶላት አድሳት

≈•° በዚክር አርጥባት

≈•° በቀደር አሳምናት

≈•° በቁርዓን አክማት

≈•° በየቂን አጠንክር

≈•° በኢማን አበልፅግ

≈•° በሞት አለስልሳት

≈|° በቀብር አስፈራራት

≈•° በጀሀነም አስጠንቅቃት

≈•° በጀነት አበሽራት

Share
👇👇👇
@bekri2
🌴ጂብሪል ዐ.ሰ አንድ ቀን ወደ ረሱል ሰለላሀ አለይሂ ወሰለም መጣና እንዲህ አላቸው
" አላህ ሱ.ወ ምድር ላይ የሚገኙትን እያንዳንዱን ቅጠል ባህር ውስጥ ያሉትን አሳዎች ሰማይ ላይ ያሉትን ከዋክብት ብዛት እንዲሁም የእያንዳንዷን የአፈር ብናኝን የመቁጠርን እውቀትን ሠጥቶኛል
ግና አንድ መቁጠር የማይቻለኝ ነገር አለ"

ረሱልም ሰ.ዐ.ወ ምን እንደሆነ ጠየቁት።

ጂብሪልም ዐ.ሰ መለሰ
" ከአንተ ኡመት አንድ ሰው በአንተ ላይ ሰላትና ሰላምን ሲያወርድ አላህ ሱ.ወ የሚቸረውን በረከት መቁጠር ይሳነኛል"

📚ቲርሚዚ

 💚اللهمَّ صلِّ على سيدنا ومولانا محمدٍ مِدادَ كلماتِكَ ، اللهمَّ صلِّ على سيدنا ومولانا محمدٍ مِلْءَ سَمَاوَاتِكَ وأرْضِكَ

@bekri2
ጂብሪል (አለይሂ ሰላም)አንድ ቀን ያለወትሮው ረሱል ሰዐወ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ
መጣ።
ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንት ጅብሪል ምነው ፊትህ
እኮ ተቀየሯል?" አሉት። ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁት
ሰዐት የጀሀነም አቀጣጣዮችን አላህ እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት
ነው። ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣እሳትም እውነት መሆኗን
ላወቀ፣የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣የአላህ ቅጣት ትልቅ
መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለባትም"
ብሎ መለሰላቸው።
ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም ንገረኝ" አሉት።
ጅብሪልም (አለይሂ ሰላም)"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ቀይ
እስክትሆን ድረስ
ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ነጭ እስክትሆን ድረስ ከዚያም
1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ጥቁር እስክትሆን ድረስ.....አሁን /ጀሀነም
ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ. የመርፌ ቀዳዳ
ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት
ይቃጠል ነበር።
ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.ከጀሀነም ሰዎች
ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከል ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ
ምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር። ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ
በላከህ አላህ እምላለሁ...አላህ ቁርአን ላይ የጠቀሰው የጀሀነም
ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው
መሬት ድረስ ይቀልጣል።
ያ በዕውነት በላከህ አላህ እምላለሁ. በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም
ቢቀጣ ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር።
ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት
ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ
ነው።
7 በሮች አሏት።
ለያንዳንዱ በር የተለያዩ በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም" ብሎ
መለሰላቸው።
ረሱልም [ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም]"እኛ እንደምንጠቀመው አይነት በር ነው?" ብለው
ሲጠይቁት
ጅብሪልም (አለይሂ ሰላም)" አይ አይደለም ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር
ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር ያለው ርቀት 70 አመት
ያስኬዳል።
እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል። የአላህ
ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ
የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው
አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል።
ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ
ይታሰራል።
እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል። ከዚያም
በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ
ይመቷቸዋል።
ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎ
መለሰላቸው።
ነቢያችንም (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)"በነዚህ በሮች የሚገቡት እነማን ናቸው?" ብለው
ጠየቁት።
ጅብሪልም ( አለይሂ ሰላም)
"በታችኛው በር የሚገቡት
1፦ሙናፊቆች
2፦በዒሳ ( አለይሂ ሰላም) ማዕድ የካዱት
3፦"የፊርዐውን ቤተሰቦች...ሲሆኑ የበሩ ስም ሀዊያ ይባለል። √ሁለተኛው
በር ስሙ ጀሂም ሲሆን በሱ የሚገቡት ሙሽሪኮች ናቸው።
√ሶስተኛው በር ሳብያኖች ነው የሚገቡበት ስሙም ሰቀር ይባላል።
√በአራተኛው በር ኢብሊስ እና ተከታዮቹ መጁሶችም ይገቡበታል ስሙም
ለዟ ይባላል።
√አምስተኛው በር የሁዶች የሚገቡበት ሲሆን ስሙም ሁጠማ ይባላል።
√ስድስተኛው በር ስሙ ዐዚዝ ሲሆን የሚገቡበት ክርስቲያኖች
ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ √ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት
ያዘው።
ነቢያችንም (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?" ብለው
ሲጠይቁት
'ጂብሪልም ( አለይሂ ሰላም)"በሱ በር የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ
ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ የሞቱ ናቸው" ብሎ
ሲመልስላቸው ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ራሳቸዉን ስተው ወደቁ። ከዚያም
ጅብሪልም የረሱልን (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ
ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት
ጀሀነም ሚገባ አለ እንዴ?" ብለው ሲጠይቁት
ጅብሪልም ( አለይሂ ሰላም) አዎን ካንተ ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች
ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣ የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ
አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ይሄን ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ
ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ።
/ፊዳከ አቢ ውኡሚ ያ ረሱለላህ/
ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)"ያጅብሪል አንተም ታለቅሳለክ?" አሉት ።
ጅብሪልም፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ መጨረሻ በምን አውቃለሁ?
እብሊስ እኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው ።

😍እስቲ በውዱ ነብይ ሰለዋት እናውርድ (አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ነቢይና ሙሀመድ)❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
___
🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
🎓
🎓 join us @bekri2
🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 29 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 18 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 19 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 10 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
2024/05/10 00:33:17
Back to Top
HTML Embed Code: