አሮጌውን ሰው አስወግዱ
“ከእንግዲኽ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥራ ይሽር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋል" /ሮሜ.6፥6/ የሚለውን የሐዋርያው ቃል ሳስብና የእኛን ሕይወት ስመለከተው ምን ያኽልም ከዚያ እንደራቅን ሳስብ ውስጤ ይቃትታል፡፡ ዐይኔ በእንባ ይመላል፡፡ ምንም እንኳን በጥምቀት አዲሱን ሰብእናችን ብንለብሰውም እኛ ግን ወደ ቀደመ አሮጌ ሰብእናችን ወደ አሕዛባዊውም ኑሮ ተመልሰናልና፡፡ አማናዊውን መና ትተን በግብጽ እንበላው የነበረውን ዓሣ፣ ዱባና ሽንኩርት እናስባለንና /ዘኁ.11፥5/፡፡ አንድ ሳምንት እንኳን ሳይሞላን በየጊዜው ጥለነው ወደመጣን ትፋታችን እንመለሳለንና፡፡ በአዲሱ ሰዋችን ላይ የኃጢአት ሕንፃ እየገነባን እመለከታለሁና አለቅሳለሁ፡፡ የዘፈን፣ የስካር፣ ጣዖትን የመውደድ ሕንፃ በመገንባት አዲሱን ሰዋችን እያበላሸነው ነውና አነባለሁ፡፡ አሮጌውና ውራጁ ሊጠፋ ሲገባው በየጊዜው ስናድሰው እየተመለከትኩ አለቅሳለሁ፡፡
ፍቁራን ሆይ! ሽማግሌዎችን አይታችኋልን? አዎ! ሽማግሌ ቆዳው የተሸበሸበ ነው፤ ድምጹ ይቆራረጣል፤ መጋጥሞቹ በሪህና በቁርጥማት የሚሰቃዩ ናቸው፤ ብዙውን ጊዜ የሚናገረውን ስለማያውቅ ይዘባርቃል፤ ይረሳል፤ ዓይኑ በሞራ የተጋረደ ነው፤ ደም ግባት የለውም፤ ጉልበቱ የተዳከመ ነው፡፡ የአሮጌ ሰው ነፍስም እንዲኽ የተጐሳቆለች ናት፡፡ የአዲሱ ሰው ነፍስ ግን ወጣትን ትመስላለች፡፡ ወጣት ደም ግባት አለው፤ ርሷም ውብ ነች፡፡ ወጣት ኹል ጊዜ ዝግጁ ነው፤ ርሷም የሚመጣባትን ፈተና ለመዋጋት ዘወትር ዝግጁ ናት፡፡
የአሮጌው ሰው ነፍስ እንዲኽ ዓቅም ስለሌላት በቀላሉ ትወድቃለች፡፡ መዝሙረኛው “ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ" እንዳለ የአሮጌ ሰው ነፍስ ኃጢአት እንዳሻው ወደ ፊትና ወደ ኋላ ስለሚያወዛውዛት ኹል ጊዜ ለአደጋ የተጋለጠች ናት /መዝ.1፥4/፡፡
በዕድሜ የሸመገሉ ሰዎች አስቀድመን ከተናገርነው በተጫማሪ ብዙውን ጊዜ ጤና ስለሌላቸው ያስላቸዋል፤ ዓቅም ስሌላቸው አክታቸውን እንኳን መትፋት ይሳናቸዋል፤ በብዙ ጥረትም በእጃቸው ይጠርጉታል፡፡ ያነጫንጫቸዋል፤ ትንሽ ነገር ያበሳጫቸዋል፤ ትንፋሽ ያጥራቸዋል፡፡ ከእኛ መካከል ምናልባት እንዲኽ በጠና የታመመ ሰው ካለ እነዚኽን ምልክቶች በቀላሉ ያውቃቸዋል፡፡ እነዚኽ ኹሉ በሥጋ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡ ወዮ! ወዮ! የአሮጌው ሰው ነፍስ እንደምን ከዚኽ የባሰች ትኾን?
በሉቃስ ወንጌል ላይ የምናገኘው የጠፋው ልጅ እንዲኽ ኾኖ ታሞ የገረጣ የከሳ ልጅ ነበር፡፡ ሲወስንና ሲጸጸት ግን ወድያው እንደ ቀድሞ ወጣት ኾነ፡፡ “ተነሥቼም ወደ አባቴ እሔዳለሁ” ባለ ጊዜ አሮጌው ሰውነቱ እየከሰመለት... እየጠፋለት... አዲሱ ሰውነቱ ደግሞ እየፋፋለት... መጣ /ሉቃ.15፥17/፡፡ በሐሳቡና በቃሉ ላይ ተግባር እየጨመረበት ሲመጣ ደግሞ የበለጠ እየወፈረ... እያገገመ… መጣ፡፡ “ተነሥቼ ወደ አባቴ እሔዳለሁ፡፡ አባቴ አንተንም ፈጣሪዬንም በደልኩ፡፡ ከእንግዲኽ ወዲኽ ልጅህ ልባል አይገባኝም፡፡ ከባሮችህ እንደ አንዱ ቁጥረኝ እንጂ እለዋለኁ" ብሎ እዚያ የቆየ አይደለም፤ ፈጥኖ ድሮ የሔደበትን መንገድ እየተወ ወደ ቤቱ ተመለሰ እንጂ፡፡
ይቀጥላል....
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች ገጽ 66-69 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)

❤80🙏12🕊7
ሁለቱን ሐሳቦች ተረዷቸውና ተጠንቀቋቸው አንደኛው "አንተ ቅዱስ ነህ" የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "መቼም ቢሆን ልትድን አትችልም" የሚለው ነው፡፡
ሁለቱም ሐሳቦች ከጠላት ናቸው፤ በትዕቢትና ተስፋ በመቁረጥ የተሞሉ እውነት የሌላቸው ናቸው፡፡
አንተ ግን ለራስህ ይህን በለው "እኔ ታላቅ ኃጢአተኛ ነኝ ስራዬ በፊቴ ነው ግን አምላክ መሐሪ ነው! ሰዎችንም በጣም ይወዳል፤ ስለዚህ ኃጢአቴን ይቅር ይለኛል፡፡"
አባ ስልዋኖስ ዘአምድ

❤90🙏22🕊3👍1
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ! ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም። ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም 11/2018…
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 12 የቻናላችን ቤተሰቦች 24,500 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ27 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 53 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ

❤24👍1
፪
አሮጌውን ሰው አስወግዱ
ተወዳጆች ሆይ! ከአባታችን ቤት ብዙ ርቀን በአሕዛብ ሀገር ገብተን ቢኾንም ፀሐይዋ ገና አልጠለቀችምና አኹንኑ ወስነን እንመለስ፡፡ የመንገዱን ርዝማኔ እየታሰበን በዚያ የምንዘገይ አንኹን፡፡ እኛ ፈቃደኞች ከኾንን የሔድንበት መንገድ ለመመለስ ከቀድሞ ይልቅ ቀላል ደግሞ የፈጠነ ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው የሔድንበትን የእንግድነት ሀገር ወስኖ መልቀቅ ብቻ ነው፡፡ ስለዚኸ ከሔድንበት የኃጢአት ሀገር ተመልሰን ከአባታችን ከጽድቅ ቤት እንግባ፡፡ አባታችን እኛን ለመቀበል ፍሪዳውን አርዶ (ቅዱስ ሥጋዉን ክቡር ደሙን አዘጋጅቶ) ቤቱንም አሰናድቶ እየጠበቀን ነውና ከዚያ የኃጢአት ሀገር ፈጥነን እንውጣ፡፡ ጤናን ከማጣት የተነሣ የገረጣውን ሰውነታችን በእንግድነት ሀገር ሳይሞት ፈጥነን እንመለሰው፡፡
ተወዳጆች ሆይ! ሓኪሞች አንድ የታመመን ሰው “ከአልጋህ ተነሥና ተመላለስ" ሲሉት መዠመርያ እንደሚፈራ ወደ አባታችን ቤት መመለሱን የምንፈራ አንኹን፡፡ ይኸ ከአልጋ የሚነሣ ታማሚ የሚያበረታቱት ሐኪሞችና ቤተሰቦች በዙርያው እንዳሉ ኹሉ ከእኛ ጋርም መንፈስ ቅዱስና እልፍ አእላፍ ወትእልፊት ቅዱሳን መላእክት አሉ፡፡ ታማሚው አንዴ ከተነሣ በኋላ ዓቅምና ብርታት እያገኘ እንደሚሔድ ኹሉ እኛም አንድ ቀንና ኹለት ቀን መመለስን ስንዠምር በሦስተኛው ቀን የበለጠ እየበረታንና እየፈጠንን እንሔዳለን፡፡ የበለጠ በመጣን ቁጥር የአባታችንን ቤት አሻግረን እናያታለን፤ ጉልበትም እናገኛለን፡፡ የተዘጋጀልንን ድግስ በሩቅ ስናይም የበለጠ ብርታት እየተሰማን እንመጣለን፡፡
የጠፋው ልጅ ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ስላባከነው ገንዘብ አባቱ አንዳች ስንኳ የጠየቀው አይደለም፡፡ አንዲት የወቀሳ ቃል ስንኳ አልሰነዘረበትም፡፡ ፊቱን አላጠቆረበትም፡፡ ከዚያ ይልቅ አዘነለት፤ ፈጥኖም አንገቱን አቅፎ ሳመው እንጂ፡፡ ባሮቹን ፈጥነው ያማረውን ልብስ እንዲያለብሱት፣ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ እንዲያስገቡለት አዘዛቸው እንጂ፡፡ ማለፊያውን ፍሪዳ አምጥተው እንዲያርዱለት አዘዛቸው እንጂ። ፍቁራን ሆይ! አባታችንም እንዲኽ አዘጋጅቶ እየጠበቀን ነውና እንመለስ፡፡ በእንግድነት ሀገር ስለምን እየተራብን እንቆያለን? አባታችን እኮ ለገዛ ልጁ ስንኳ ያልራራለት ይልቁንም ስለኹላችን ቤዛነት ለሕማም ለሞት አሳልፎ የሰጠው አፍቃሪያችን ነው /ሮሜ.8፥32/! እንዲኽ አሮጌው ሰብእናችንን አውልቀን ስንመለስ'ማ አባታችን እንዴት በእጅጉ አይደሰት?! እንኳንስ ርሱ የሰማይ መላእክትም በእኛ መመለስ ምክንያት ሐሴት ያደርጋሉ፡፡
ስለዚኽ እንምጣና የተጨማደደውን አሮጌ ሰውነታችንን እናድሰው፡፡ እንምጣና በበሽታ የተጠቃው አሮጌ ሰውነታችንን አውልቀን በሽታን የመቋቋም ዓቅም ያለው አዲሱን ሰውነታችን እንልበስ፡፡ እንምጣና ለይስሙላ ሳይኾን ለእውነት በሚኾኑ የጽድቅና የቅድስና ልብስ እናጊጥ፡፡ እንምጣና አክሊልን እንደለበሰ ሙሽራ በጌጥ ሽልማትም እንዳጌጠች ሙሽሪት የመዳንን ልብስ እንልበስ /ኢሳ.61፥10/፡፡

❤77🙏15👍2👌1🏆1
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ! ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም። ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም 11/2018…
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 13 የቻናላችን ቤተሰቦች 25,500 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ28 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 52 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 13 የቻናላችን ቤተሰቦች 25,500 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ28 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 52 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
❤28👍3
Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

❤30👍3
መልካም አድርግና እርሳው!
ስላደርግኸው ስለዚህ ነገር ማንኛውንም ዓይነት ውዳሴም ሆነ ሙገሳ አትሻ። መልካም ያደረግህለት ሰው አንተ እንዳደረግህለት ለአንተ መልካም የሆነውን አጸፋ እንዲመልስልህ ወይም አንተ አንደተንከባከብከው እርሱም እንዲንከባከብህ አትጠብቅ።
መልካም ስታደርግ በምላሹ መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን! መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን። መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን። መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገር ይሁን።
እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል። መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

❤129🙏15👍4🤩1
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 14 የቻናላችን ቤተሰቦች 25,800 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ28 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 52 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 14 የቻናላችን ቤተሰቦች 25,800 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ28 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 52 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
❤52👍2
በእንተ ስማ ለማርያም
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 15 የቻናላችን ቤተሰቦች 26,300 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ29 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 51 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።

❤24🙏5👍2
“እምነት አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡
ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡
ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡
እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

❤104🙏19
ኑሮየን ንገረኝ
ታላቁ ቅዱስ አርሳንዮስ ቤተ መንግሥትን ለቆ ወደ በረሃ ለምናኔ ሲገባ ጌታን የለመነበት ትልቅ ጸሎት ነበር። "ጌታ ሆይ" አለው። ጌታም "አርሳኒ ምን ትሻለህ" አለው። ቅዱስ አርሳንዮስም "ጌታ ሆይ ኑሮየን ንገረኝ" ሲል ጠየቀ። ዳግመኛም "ጌታ ሆይ" ሲል ጮኸ። ጌታም "አርሳኒ ምን ትሻለህ" አለው። እርሱም "ጌታይ ሆይ ኑሮዬን ንገረኝ" አለው። ሦስተኛም አለ "ጌታ ሆይ" አለ። ጌታም "አርሳኒ ምን ትሻለህ?" አርሳኒም "ጌታ ሆይ ኑሮየን ንገረኝ" አለ ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ፦ጌታም መለሰ። ቦታ ምረጥ፣ ከሰው ተለይ፣ ዝም በል አለው። አርሳኒም ገዳም ገብቶ ለፍጹምነት በቃ።
ሰው መንገድ ሲሄድ በሁለት መንገድ ሊወድቅ ይችላል። አንደኛ በጠማማ መንገድ በመሄድ። ሁለተኛ በቅን መንገድ ሳያስተውሉ በመሄድ ነው። በጠማማ መንገድ በመሄድ መውደቅ ማለት በጠማማ ሃይማኖት መኖር ነው። በቅን መንገድ ሳያስተውሉ መጓዝ ማለት ደግሞ በቀናች ሃይማኖት እየኖሩ አካሄድን አለማወቅ ነው። መንገዱ የቀና ቢሆንም አረማመዱ ባለማየት ከሆነ እግሮቹ ተጣልፈውም ቢሆን ይወድቃል። አካሄዱ ካላማረ በክርስቶስ ማመንም ያስኮንናል። የምናውቀው ክርስትና በማናውቀው መንገድ ከኖርነው ያጠፋል።
አውቀን ለምናደርጋቸው እንኳ ቢሆን እንዴት ላድርገው እያልን መጠየቅ በየዕለቱ እናደርገው ዘንድ ይገባል። በየጊዜውና በየሰዓቱ ወደ ክርስቶስ የምንጓዝ ነንና ጥያቄያችን የዘወትር ነው። ጸሎት አይቋረጥም መባሉ ስለዚህ ነው። ቅዱስ አርሳንዮስ ኑሮው ምንኩስና እንዲሆን ወስኖ ነበር። ግን መነኩሴ መሆን እንዳለበት እያወቀ ኑሮየን ንገረኝ ይል ነበር። ለምን ቢሉ ኑሮውን ብናውቀውም አኗኗሩን ግን ካልጠየቅን የሚጠቅመውን በማይጠቅም መንገድ ልንኖረው እንችላለን።
ለምሳሌ ከቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ጳውሎስን እንይ። ቅዲስ ጳውሎስ ምሑረ ኦሪት ነበር። 46ቱን የኦሪት መጻሕፍት ተምሯል። መጻሕፍቱ ግን የሚተረጎሙት በክርስቶስ መገለጥ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ግን ጌታን ያሳድድ ነበር። የሚያሳደደውም ለሕግ የተቆረቆርሁ መስሎት ነበር። ጌታም ቅንነቱን አይቷልና ጌታን እያገለገለ መስሎት ጌታን ያሳድድ የነበረውን አልተወውም። መንገዱን ያቀናለት ዘንድ መንገገድ ላይ በመብረቅ ተገለጠለት። ሊያሳድድበት የሄደውን መንገድ ወደ ክርስቶስ እንዲደርስበት መራው። እውቀትን ቅንነት ይመራዋል፤ ቅንነትን እውቀት ያበራዋል። ስለዚህ ስለምናደርገው ነገር በቂ እውቀት ቢኖረንም ያንን ግን እንደ መርከብ የሚመራው ረድኤተ እግዚአብሔር ነውና አዘውትረን ኑሮየን ንገረኝ እንበል!
(ርዕሰ ሊቃውን አባ ገብረ ኪዳን ግርማ )

❤184🙏36😍6💯4🏆1
በእንተ ስማ ለማርያም
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 15 የቻናላችን ቤተሰቦች 26,300 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ29 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 51 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 15 የቻናላችን ቤተሰቦች 26,300 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ29 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 51 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
❤24🙏20🕊1🏆1
በእንተ ስማ ለማርያም
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 16 የቻናላችን ቤተሰቦች 35,300 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ39 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 41 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።

❤23🙏4💯2
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በእንተ ስማ ለማርያም መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት “ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36 እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 16 የቻናላችን ቤተሰቦች 35,300 ብር አግኝተናል። እግዚአብሔር…
የቀሩትን 41 መጻሕፍት እናሟላ እና እሁድ መስከረም 11/2018 ወልድያ በሰሜን ወሎ ማረሚያ ቤት ለታራሚዎች እናስረክብ!
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
❤16
፩
ተግሣጽ በእንተ ቅንዓት
ቅንዓት ፍትሕ እንዲዛባ ያደርጋል፡፡ ቅንዓት አንድ ሰውን ማየት ከሚፈልገው ውጪ እንዲያይ አይፈቅድለትም፡፡ በዚህ አንዴ የተጠመደ ሰው የነፍሱን ዓይኖች ለዘለዓለም ያሳውራቸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ስው እንዴት ትሕትና ማስተማር ይቻለዋል? ቀኝ ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውን አዙርለት ብሎ ትእዛዝን ሊሰጥ ይችላልን? መከራም ሲገጥመን እንድንታገሥ ይመክረናልን? መከራን ከመታገሥ ይልቅ እንድንበቀል የሚያስተምር አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ እነዚህ ወገኖች በደልን የሚያበረታቱ እንጂ ግፍን የሚያርቁ ናቸውን?
ነገር ግን አስቀድሜ እንደተናገርሁት ከሁሉ የከፋው ተንኮል ነው፡፡ ተንኮል ሰውን ግብዝ ያደርገዋል፤ ዓለምንም ቊጥር በሌለው ኀጢአት እንድትሞላ ያደርጋታል፡፡ ይህ ኀጢአት ፍርድ ቤቶችን የሞላ ሲሆን ከዚህም ኀጢአት ከንቱ ውዳሴ፣ ገንዘብንና ሥልጣንን መውደድ እንዲሁም ድፍረት ይወጣሉ፡፡
በዚህ ኀጢአት የተያዙ ሰዎች ርኅራኄ የሌላቸው ዘራፊዎችና የባሕር ላይ ወንበዴዎች ይሆናሉ፡፡ ከዚህ ኀጢአት ነፍሰ ገዳዮች ተወልደው ወደ ዓለም ሁሉ ይበተናሉ፡፡ ሰዎችን በዘር ምክንያት ይከፋፍሏቸዋል፤ ስለዚህ ተንኮል የኀጢአቶች ሁሉ ምንጭ መሆኑን በእነዚህ እንረዳለን፡፡
ይህ ኀጢአት ወደ ቤተ ክርስቲያንም ስርጎ ገብቶአል፡፡ በዚህም ምክንያት ከመጀመሪያው ጀምሮ ብዙ ሺህ ክፉ ጥፋቶች መጥተውብናል፡፡ ቅንዓትም የስስት እናቱ ነው፤ ይህ ደዌ አኗኗራችንን የሚያመሰቃቅልና ፍትሕን የሚያዛባ ነው፡፡ ይህ ቅንዓት፡- “እጅ መንሻ መማለጃ ዐዋቆች ስዎችን ዓይነ ልቡናቸውን ይሰውራቸዋል፤ አፋቸውን ይዘጋዋል ቃላቸውንም ያስለውጣቸዋል፡፡” (ሲራክ ፳፥፳፱) እንዲል ነጻ የሆኑትን ሰዎች ባሮች የሚያደርጋቸው ነው:: ስለዚህ ይህን በተመለከተ ሳንታክት እናስተምራችኋለን፡፡
ከዚህ ኀጢአት ምንም በጎ ነገር አይወጣም፤ በዚህ ክፋት ውስጥ ካለን ከዱር አራዊት ይልቅ የከፋን እንሆናለን፡፡ ወላጅ አልባዎችን እንበዘብዛለን፣ መበለቶችን እንገፋለን፣ በደሃው ላይ እንጨክናለን፡፡ ይህ ኀጢአት በወዮታ ላይ ወዮታን የሚደራርብ ነው፡፡ ነቢዩም፡- “ደግ ሰው ከምድር ጠፍቶአል፥ በሰውም መካከል ቅን የለም፤ ሁሉ ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥ ሰውም ሁሉ ወንድሙን በመረብ ለመያዝ ይከታተለዋል።" (ሚክ.፯፥፪) እንዲል ከዚህ በኋላ በዚህ ጉዳይ ከመናገር ይልቅ የማዘኑ ተራው የእኛ ነው፡፡
ይቀጥላል...
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ዮሐንስ ወንጌልን በተረጎመበት ድርሳኑ ቅጽ 2 ገጽ 156-159 በዲያቆን ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)

❤64🙏18
#መጽሐፍ_ቅዱስ_ለታራሚዎች
“ታምሜ ጠይቃችኹኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” (ማቴዎስ 25፥36)
መስከረም 11/2018 ዓ/ም በሕግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሒደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎትና በእለቱ ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ የቻሉትን ታግዙን ዘንድ እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲኾን የ40 ተሸፍኖልናል፤ ቀሪ 40 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ማነው 40 መጽሐፍ ቅዱስ የሚያግዘን!
በእመቤቴ ዛሬንና ነገን እጨርስ ፈቃደኛ የሆናችሁ በውስጥ መስመር አናግሩን!
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
“ታምሜ ጠይቃችኹኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” (ማቴዎስ 25፥36)
መስከረም 11/2018 ዓ/ም በሕግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሒደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎትና በእለቱ ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ የቻሉትን ታግዙን ዘንድ እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲኾን የ40 ተሸፍኖልናል፤ ቀሪ 40 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ማነው 40 መጽሐፍ ቅዱስ የሚያግዘን!
በእመቤቴ ዛሬንና ነገን እጨርስ ፈቃደኛ የሆናችሁ በውስጥ መስመር አናግሩን!
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
❤34🙏5
፪
ተግሣጽ በእንተ ቅንዓት
...በጸሎታችን ወይም በምክራችን ወይም በተግሣጻችን ምንም አላተረፍንምና፤ ለእኛ የቀረልን ልቅሶ ብቻ ሆኖአል፡፡ ክርስቶስም ያደረገው እንዲህ ነበር፤ እርሱ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ብዙ ጊዜ የገሠጻቸው ቢሆንም፤ ምንም ትርፍ ስላላገኘባቸው ስለ ድንዳኔያቸው አልቅሶላቸዋል። ነቢያትም ለእስራኤላውያን አንብተውላቸዋል፡፡ እኛም እንዲሁ ስለ እናንተ እያነባን እንገኛለን፡፡ አሁን እኛ የምናዝንበትና የምናለቅስበት እንዲሁም ወዮ የምንልበት ወቅት ላይ ደርሰናል። “እንዲመጡ አልቃሾች ሴቶችን ጥሩ፤ እንዲመጡም ወደ ብልሃተኞች ሴቶች ላኩ" የምንልበት ወቅት አሁን ነው። (ኤር ፱፥፲፯)
በእርግጥ የሚያማምሩ ቤቶችን ለመገንባት የሚሹትን ሰዎች ስንመለከት የቅንዓት ደዌ ምን ያህል ጽኑ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ እነዚህ ሰዎች ከሰዎች በነጠቋቸው መሬቶች የተከበቡ ናቸው፡፡ አዎን ለማዘን አሁን ወቅቱ ነው፤ እናንተ መሬታችሁ የተነጠቀባችሁ በእነርሱም የተጎዳችሁ ኑ ከእኔ ጋር በአንድነት እዘኑ። ኀዘናችሁንም ተካፍዬ እንባዬን አፈስ ዘንድ ፍቀዱልኝ፡፡ ኀዘናችን ግን ለእኛ ሳይሆን ለእነርሱ ነው፡፡ እኛ ብንጎዳ በምድር ነው፣ የእነርሱ ጥፋት ግን ዘለዓለማዊ ነው፡፡ እናንተ ግን በእናንተ ላይ የተፈጸመባችሁ ግፍ ዋጋ ሆኖአችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ትወርሳላችሁ፡፡ ነጣቂዎቻችሁ ግን ገሃነምን ይወርሳሉ፡፡ ከመጉዳት መጎዳት አይሻልምን? ስለዚህ ስለ እነርሱ ማቅ ለብሰን እናልቅስላቸው! በሰዎች ዘንድ ባለው የልቅሶ ሥርዓት ግን አይደለም፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈው ነቢያት ያዘኑትን ኀዘን ዓይነት እንዘንላቸው። ከነቢዩ ኢሳይያስ ጋርም “ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጆሮዬ እንዲህ አለ፦ በእውነት ብዙ ታላቅና መልካም ቤት ባድማ ይሆናል የሚቀመጥበትም አይገኝም" በማለት አምርረን እናልቅስላቸው፡፡ (ኢሳ ፭፡፰-፱)
ኤርሚያስም “ቤቱን በግፍ ሰገነቱንም በዓመፅ ለሚሠራ፥ ባልንጀራውንም እንዲያው በከንቱ ለሚያሠራ፥ ዋጋውንም ለማይሰጠው፤ ለራሴ ሰፊ ቤት ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፥ መስኮትንም ለሚያወጣ በዝግባም ሥራ ለሚያሳጌጥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት!' ብለን እናልቅስላቸው፡፡ (ኤር.፳፪፥፲፬) ወይም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ለነበሩት “ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና፡፡ ብሎ እንዳዘነ እንዘንላቸው፡፡
ይቀጥላል.....
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ዮሐንስ ወንጌልን በተረጎመበት ድርሳኑ ቅጽ 2 ገጽ 156-159 - በዲያቆን ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)

❤57🙏4💯4🏆3
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚዎች 40 ይቀረኛል!
“ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” (ማቴዎስ 25፥36)
እሑድ መስከረም 11/2018 ዓ/ም በሕግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሒደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎትና በእለቱ ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ የቻሉትን ታግዙን ዘንድ እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲኾን የ40 ተሸፍኖልናል፤ ቀሪ 40 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ማነው ከ40 መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአቅሙን የሚያግዘን!
በእመቤቴ ዛሬንና ነገን እጨርስ ፈቃደኛ የሆናችሁ በውስጥ መስመር አናግሩን!
በዚህ @natansolo አናግሩን!

❤41👌2
፫ (የመጨረሻ)
ተግሣጽ በእንተ ቅንዓት
.....ወንድሞች ሆይ! ለእነርሱ ማዘናችሁን እንዳትተው እለምናችኋለሁ፤ ይህ የማይሆን ለመሰላቸውም ከዚህ እንዲርቁ ደረታችንን እየደቃን እናልቅስላቸው። በሥጋ ለተለዩን ሳይሆን በሕይወት ላሉት ለስስታሞቹ፤ ለነጣቂዎቹ፣ ለቀናተቹ፤ ለሆዳሞቹ እናልቅስላቸው፡፡
ስለሞተው ስለ ምን እናለቅሳለን? እነርሱን በተመለከተ የምናመጣው አንዳች ነገር የለምና፡፡ ከዚህ ድርጊታቸው ሊመለሱ ጊዜው ለተሰጣቸው ኀጢአተኞች ግን እናልቅስላቸው። ለእነርሱ በማዘናችን ግን ሊሳለቁብን ይችላሉ፡፡ ይህ በራሱ ስለ እነርሱ ለማንባት በቂ ምክንያት ይሆነናል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ኀጢአታቸው ማቅ ለብሰው ሊያዝኑ እንጂ ሊስቁ ባልተገባቸው ነበርና፡፡ በእኛ ኀዘን ተነክተው ከዚህ ኀጢአታቸው ለመመለስ ከፈቀዱ ግን ማዘናችንን እናቆማለን፡፡
ነገር ግን ይህን ባለማስተዋል የሚመላለሱ ከሆነ ስለ እነርሱ ማንባታችንን አናቋርጥም፡፡ ለባለጠጎቹ ብቻ አይደለም፣ በፍቅረ ንዋይ ለወደቁ፣ በስስት ለተያዙ ለስግብግቦችም እናለቅስላቸዋለን፡፡ ገንዘብ በራሱ መጥፎ ሆኖ ግን አይደለም፡፡ ገንዘብን በአግባቡ ከተጠቀምንበትና ለሚገባ ነገር የተገለገልንበት በራሱ ክፋት የለበትም፡፡ ነገር ግን ስስት ክፉ ነው፤ እርሱም ዘለዓለማዊ ሞትን ያመጣብናል፡፡
ስለሆነም የንስሐ ዕድሜ ቀርቶላቸዋልና እንዲህ ላሉ ሰዎች እንዘንላቸው ወይም በዚህ ኀጢአት ወድቀው ማምለጥ ላልቻሉ እናልቅስላቸው፡፡ ሌሎችም በዚህ ኀጢአት ተሰነካክለው እንዳይወደቁ ከዚህም ይጠብቃቸው ዘንድ በእንባ በመሆን ለሰው ሁሉ እንጸልይ፡፡ በሚመጣው ዓለም ከዚህ ኀጢአት ባርነት ነጻ ወጥተው ከእኛም መካከል አንዱ ስንኳ በዚህ በኀጢአት ሳይያዝ ተስፋ የተሰጠንን መንግሥቱን እንወርስ ዘንድ የበቃን ያድርገን፡፡

❤60🙏14