Telegram Web Link
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሰላም ተወዳጆች ለአንዲት በጉባላፍቶ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ለምትገኝ ዝርጋ ማርያም እየተባለች ለምትጠራ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድስት (መጻሕፍት፣ ልብሰ ተክህኖ፣ እጣን፣ ዘቢብ፣ ጧፍ፣ ሻማ....) ያስፈልጋልና ወደጆቼ አለን በሉኝ። @natansolo
እስከ አሁን አንዲት እህት ለቤተክርስቲያኗ የሚያስፈልጉ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደምትሸፍን ቃል ገብታልናለች ለልብሰ ተክህኖው ከ10 የቻናላችን ቤተሰቦች 30,550 ብር ደርሰናል ቀሪውን የሚሞላ ያስፈልጋል።

በተጨማሪ እግዚአብሔር ቢፈቅድ መስከረም 4/2018 ዓም አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በማረሚያ ቤት ከሚገኙ የህግ ታራሚዎች ጋር ጉባኤ አዘጋጅተናል በዚሁ መርሐግብር ለህግ ታራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ ገዝተን ለመስጠት አስበናል ለዚህም የተቀደሰ ተግባር ትብብራችሁ እንዳይለየን።

ለታራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ ከ4 የቻናላችን ቤተሰቦች 8500 አግኝተናል ቀሪው በጎ አድራጊዎችን ይጠብቃል።

@natansolo
👍7

አዲሱ ዓመት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው
)

ትዳራችን እንኳን ለእግዚአብሔር ክብር ልናደርገው ይገባናል፡፡ መኝታችን (በትዳር ውስጥ የሚደረገው ሩካቤ) ንጹሕ ማድረግ፣ ትዳርን ለብር ወይም ሌላ ምድራዊ ነገርን ለማግኘት ሳይኾን ነፍሳችንን ለማዳን፣ እግዚአብሔርን ለማግኘት የሚደረግ ከኾነ ለእግዚአብሔር ክብር አደረግነው ይባላል፡፡ የትዳር አጋራችንን ከዘለዓለማዊ ሕይወት አንጻር እንጂ ከውበት፣ ከሃብት፣ ወይም ከሌላ ጊዜአዊ ጥቅም አንጻር የማንመለከት ከኾነ ትዳራችን ለእግዚአብሔር ክብር የተደረገ ነው ይባላል፡፡ በአዲሱ ዓመት ይኽን ልንለማመድ ይገባናል፡፡ እግዚአብሔር የሚወዳችኁ እናንተም የሚምትወዱት ልጆቼ! ይኽን ኹሉ በዝርዝር የምነግራችኁ ለምን ይመስላችኋል? ይኽን ኹሉ በዝርዝር መናገሬ በዘዴ ኹላችንም የምናደርገውን ማናቸውም እንቅስቃሴያችን ለእግዚአብሔር ክብር እናደርገው ዘንድ ስለምሻ ነው፡፡ በባሕር የሚነግዱ ነጋዴዎች ንብረታቸውን ወደ ከተማ ዳር መልሕቅ ካመጡ በኋላ መዠመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር በቀጥታ ወደ ገበያ ሥፍራ መሔድ አይደለም፡፡ ወደ ገበያ ሥፍራ ከመሔዳቸው በፊት ስለ ትርፋቸው ያስባሉ እንጂ፡፡ እኛም በምናደርገው ኹሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ የምናገኘውን ጥቅም ማሰብ አለብን፡፡

ከእናንተ መካከል፡- “ኹሉንም ነገር ስለ እግዚአብሔር ክብር ብሎ ማድረግ ግን የሚቻል አይደለም” የሚል ፈጽሞ አይገኝ፡፡ ጫማችንን ብንጫማ፣ ፀጕራችንን ብናስተካክል፣ ልብሳችንን ብንለብስ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ብንጓጓዝ፣ የቁመናችን አኳኋን፣ ንግግራችን፣ ስብስባችን፣ መግባታችን፣ መውጣታችን፣ መገሠፃችን፣ ማመስገናችን፣ መውቀሳችን፣ አለ መውቀሳችን፣ ሰውን ወዳጅ ወይም ጠላት ማድረጋችን ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ የሚቻለን ከኾነ እኛ ከፈቀድን ለእግዚአብሔር ክብር ተብሎ የማይደረግ ምን ይቀራል? የወኅኒ አለቃ ከመኾን ምን የከፋ አለ? የወኅኒ ጠባቂ ሕይወት እጅግ የምትከብድ አትመስልምን? ነገር ግን የልቡና ፈቃደኝነት ካለን የወኅኒ አለቃም ተኩኖ ኹሉንም ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ ይቻላል፡፡ እስረኞችን ማዳን ይቻላል፡፡ ያለ አግባብ የታሰሩትን መንከባከብ ይቻላል፡፡ ንጹሐን ሰዎችን አለ አግባብ ከሚያሰቃዩ ክፉዎች ጋር አለመተባበር ይቻላል፡፡ እስረኞችን እንደ አለቃ ሳይኾን እንደ ወንድምና እኅት ማገልገል ይቻላል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሃይማኖት የመለሰውን የወኅኒ ጠባቂ ስንመለከት እንደዚኽ ዓይነት ሰው ነበር /ሐዋ.16፡25-40/፡፡ ስለዚኽ በአዲሱ ዓመት ኹሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር እናድርገው ብንል ይቻለናል ማለት ነው፡፡

እስኪ ንገሩኝ! ከነፍሰ ግድያ በላይ ምን የከፋ ነገር አለ? ነገር ግን በዚኽ የነፍስ ግድያ እንኳን የጽድቅን ሥራ መሥራት ይቻላል፡፡ አትደንግጡ! ግድያ እንኳን ለእግዚአብሔር ክብር ተብሎ ሊደረግ ይችላል፡፡ ከእናንተ መካከል “ነፍሰ ገዳይ ሰው እንዴት አድርጐ ነው በነፍሰ ገዳይነቱ ጽድቅ ሠራ ተብሎ ሊነገርለት የሚችለው?” የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ የተመዘገበውን አንድ ታሪክ አንሥቼ ልነግራችኁ እወዳለኹ፡፡ አንድ ጊዜ ምድያማውያን ከእስራኤል ጋር ጦርነት ይገጥሙ ዘንድ እግዚአብሔርን ለቁጣ ቀስቅሰዉት ነበር፡፡ በጦርነቱም ልዕልናቸውን በማሳየት፥ የእግዚአብሔርን መልካም ፈቃድ ለማስቀረት አስበው ሴቶቻቸውን በማሳመር በድንኳኑ ፊት ቆመው ነበር፡፡ በዚኽም እስራኤላውያንን በዝሙት እስከ መሳብና ለጣዖት እንዲሰግዱ እስከ ማታለል ደርሰው ነበር፡፡ ይኽም ብቻ ሳይኾን እስራኤላውያን ሃይማኖት የለሽ እንዲኾኑ ፈልገው ነበር፡፡ ፊንሐስ ግን ይኽን ባየ ጊዜ በእጁ ሰይፍ ይዞ ኹለት ሲያመነዝሩ የተገኙትን ሰዎች ሆዳቸውን በሰይፍ ወግቶ ገድሏቸዋል፡፡ በዚኽም የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደኾነ አረጋግጧል፡፡ ፊንሐስ ያደረገው ነገር ሰውን መግደል ነው፡፡ የዚኹ ግድያ ዓላማ ግን እስራኤልን በጠቅላላ ማዳን ነበር፡፡ በመኾኑም ከግድያ እንኳን ጽድቅን ማፍራት ይቻላል ማለት ነው /ዘኅ.25/፡፡

ፊንሐስ በፈጸመው ግድያ እጁ አልረከሰም፡፡ ይልቁንም ያ “ነፍሰ ገዳዩ” ፊንሐስ እስራኤላውያንን ከዝሙት ጠንቅ ጠብቆ ንጹሐን አደረጋቸው እንጂ፡፡ ፊንሐስ እነዚያ ኹለቱንም የገደላቸው ጠልቷቸው አልነበረም፤ የተቀሩትን የእስራኤል ሰዎች ለማዳን እንጂ፡፡ ኹለቱንም ብቻ በመግደል እልፍ እስራኤልን በነፍስ በሥጋ ከመሞት ለመታደግ እንጂ፡፡ ይኸውም ሐኪሞች እንደሚያደርጉት ነው፡፡ ሐኪሞች አንድ በቁስል መበስበስ (በጋንግሪን) የተጠቃን የሰውነት ክፍል ቈርጠው ቢያስወግዱት የተቀረውን ሰውነት ለማዳን ነው፡፡ ፊንሐስም ያደረገው እንደዚኹ ነው፡፡ መዝሙረኛው ክቡር ዳዊት ይኽንን በተመለከተ ሲናገር፡- “ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፤ ቸነፈሩም ተወ፡፡ ያም እስከ ዘለዓለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ኾኖ ተቈጠረለት” ብሏል /መዝ.106፡30-31/፡፡ ፊንሐስ ያደረገው ነገር ትክክል ነው ተብሎ እስከ ዘለዓለም ሲነገርለት ይኖራል፡፡ (በነገራችን ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አልመለስ ያሉትን መናፍቃን ከቤተ ክርስቲያን አውግዛ የምትለያቸው ቀሪውን ምእመን እንዳይበክሉ እንጂ ጠልታቸው አይደለም፡፡ በቅርብ ጊዜ የተወገዙት የተሐድሶ አራማጆች የተወገዙትም ከዚኹ አንጻር ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ውግዘቱ ለእግዚአብሔር ክብር የተደረገ ነው፡፡)

ይቀጥላል.....

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ- ሰማዕትነት አያምለጣችሁ እና ሌሎች ገጽ 13-36)
45🙏3
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሰላም ተወዳጆች ለአንዲት በጉባላፍቶ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ለምትገኝ ዝርጋ ማርያም እየተባለች ለምትጠራ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድስት (መጻሕፍት፣ ልብሰ ተክህኖ፣ እጣን፣ ዘቢብ፣ ጧፍ፣ ሻማ....) ያስፈልጋልና ወደጆቼ አለን በሉኝ። @natansolo
እስከ አሁን አንዲት እህት ለቤተክርስቲያኗ የሚያስፈልጉ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደምትሸፍን ቃል ገብታልናለች ለልብሰ ተክህኖው ከ10 የቻናላችን ቤተሰቦች 30,550 ብር ደርሰናል ቀሪውን የሚሞላ ያስፈልጋል።

በተጨማሪ እግዚአብሔር ቢፈቅድ መስከረም 4/2018 ዓም አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በማረሚያ ቤት ከሚገኙ የህግ ታራሚዎች ጋር ጉባኤ አዘጋጅተናል በዚሁ መርሐግብር ለህግ ታራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ ገዝተን ለመስጠት አስበናል ለዚህም የተቀደሰ ተግባር ትብብራችሁ እንዳይለየን።

ለታራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ ከ4 የቻናላችን ቤተሰቦች 8500 አግኝተናል ቀሪው በጎ አድራጊዎችን ይጠብቃል።

@natansolo
18👍4
፰ (የመጨረሻ)
አዲሱ ዓመት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

ዳግመኛም አንድ ሰው በመጸለዩ ምክንያት እግዚአብሔርን አስቈጥቷል፡፡ ምክንያቱም ጸሎቱ ለእግዚአብሔር ክብር የተደረገ አልነበረም፤ ርሱም ፈሪሳዊው ነው /ሉቃ.18/፡፡ ፊንሐስ ግድያን ስለ ፈጸመ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አገኘ፤ ፈሪሳዊው ደግሞ በአንጻሩ ስለ ጸለየ እግዚአብሔርን አስቈጣ፡፡ ስለዚኽ ማናቸውም የምናደርገው ነገር ምንም መንፈሳዊ ቢኾንም ለእግዚአብሔር ክብር እስካልተደረገ ድረስ ትርፉ ጉዳት ነው፡፡ ሥጋዊ ሥራም ብንሠራ ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ ይቻለናል፡፡ ሰውን ከመግደል በላይ እጅግ ክፉና ዘግናኝ ነገር ምን አለ? ነገር ግን ይኽ ለእግዚአብሔር ክብር የሚደረግ ከኾነ ከዚኹ ግድያ እንኳን ጽድቅን ማግኘት ይቻላል፡፡

እንግዲኽ ከነፍሰ ገዳይ እንኳን እንዲኽ ዓይነት ጽድቅ ከተገኘ እያንዳንዱ ግብራችን ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ አይቻለንም እንደምን ማለት ይቻለናል? የልቡና ፈቃደኝነት ካለን ግን ኹሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ ይቻለናል፡፡ ብንገዛም ብንሸጥም ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ ይቻለናል፡፡ ከአግባብ በላይ ዋጋን በመጨመር ሸማቹን ማኅበረ ሰብ ባለ ማስቸገር ንግዳችን ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ ይቻለናል፡፡ አንድን ዕቃ በመደበቅ (አኹን ባለው የአገራችን ተጨባጭ ኹኔታ ዘይትንና ስኳርን ማለት እንችላለን) አለአግባብ ለመክበር ብለን የምንደብቀው ከኾነ “እኽልን የሚያስቀር ሰው በሕዝቡ ዘንድ የተረገመ ነው” እንደተባለ /ምሳ.11፥26/ ንግዳችን እግዚአብሔር የከበረበት ንግድ አይደለም፡፡

ከእናንተ መካከል፡- “አባታችን! አንድ ምሳሌ መስለኽ ልታስተምረን ስትችል ወደዚኽ ኹሉ ዝርዝር መግባት ለምን አስፈለገኽ?” የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ አንድ የሕንፃ ተቋራጭ አንድን ሕንፃ ለመገንባት የሚዠምረው መሠረት በመጣል ነው፡፡ ከዚያም ደረጃ በደረጃ የተቀረውን የሕንፃን ክፍል ይገነባል፡፡ በመጨረሻም ሕንፃው እጅግ የሚያምር እንዲኾን የቅብ (finishing) ሥራን ይሠራል፡፡ እኛም ይኽን ኹሉ በዝርዝር ማየታችን በክፍል 2 ትምህርታችን፡- ወዳጄ ሆይ! ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለኽ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋኽን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለኽ? አስቀድመኽ ቤቱን (ነፍስኽን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመኽ ለነፍስኽ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለኽ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለኽ አስብ እንጂ እንዲኹ ከአኹን (ከአዲሱ ዓመት) በኋላ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለኁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲኽ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚኹ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ /1ኛ ቆሮ.10፡31/፤” የሚለውን መሠረት ይዘን ነው፡፡

ከእንግዲኽ ወዲኽ ብንጸልይም፣ ብንጦምም፣ ብንገሥፅም፣ ይቅር ብንልም፣ ብናመሰግንም፣ ብንወቅስም፣ ብንገባም፣ ብንወጣም፣ ብንሸጥም፣ ብንገዛም፣ ብንናገርም፣ ዝም ብንልም፣ ማናቸውን ነገር ብናደርግ ለእግዚአብሔር ክብር ልናደርጋቸው ይገባናል፡፡ ይኽን ያልዠመርን ካለንም አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ እንዠምረው፡፡ ለእግዚአብሔር ክብር የማናደርገው ከኾነ ግን አንሥራው፤ በማኅበር መካከል እንድንናገር ብንገፋፋም አንናገር፡፡ የትም ብንሔድ ይኽቺውን የሐዋርያው ቃል በልቡናችን ጽላት ጽፈን ይዘናት እንሒድ፡፡ ርሷም (ኃይለ ቃልዋ) የምናደርገው ኹሉ ለእግዚአብሔር ክብር እንድናደርገው ታሳስበናለች፡፡ የምናደርገው ኹሉ ለእግዚአብሔር ክብር የምናደርገው ከኾነም “ያከበሩኝን አከብራለኹ” ብሏልና /1ኛ ሳሙ. 2፥30/ ከሰው እጅ ሳይኾን ከራሱ ከክብር ባለቤት ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ክብርን እንጐናጸፋለን፡፡

እንኪያስ ከእንግዲኽ ወዲኽ ክብር የክብር ክብር፣ አምልኮና ውዳሴ ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ይገባዋልና በቃል ብቻ ሳይኾን በገቢር ጽድቅ በምግባር በትሩፋት ዘወትር እናክብረው፡፡ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ- ሰማዕትነት አያምለጣችሁ እና ሌሎች ገጽ 13-36)
62🙏6🏆3
ዘመን ማን ነው? ዘመን ማለት እኛ ነን..ስንከፋ የሚከፋ ደግ ስንሆን ደግ የሚሆን የእኛው ነጸብራቅ ነው ዘመን። ለዚህ ነው አበው በአንጋረ ፈላስፋ "ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሰላማዊ ስትሆን ሰላማዊ ትሆናለች፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች፡፡" በማለት የተናገሩት።

እናም ዘመን እኛ እኛም ዘመን ነንና ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው በዕሜያችን ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰብን ራሳችንን እንዲህ ብልን እንጠይቅ፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፣ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፣ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፤ ታዲያ ምን በጎ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፤ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ (ዘመኔ) መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፤ ታዲያ ዕድሜዬ (ዘመኔ) ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውን የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንደ አቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችንን እንጠይቅ።"

“አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።” ሰቆ.ኤር 5፥21
117🙏34👍10
መስከረም 1 - ርዕሰ አውደ ዓመት

በግዕዝ አውደ ዓመት ይባላል - ርዕሰ አውደ ዓመት - የበዓላት ሁሉ የበላይ፣ ራስ ማለት ነው፡፡ በዓመቱ ውስጥ የሚውሉት በዓላትና አጽዋማት የሚወጡት መስከረም አንድን መነሻ አድርጎ ስለሆነ ርዕሰ አውደ ዓመት ተባለ። በአማርኛ ደግሞ እንቁጣጣሽ፣ የዘመን መለወጫ ወይም ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል፡፡ የዘመን መለወጫ የሚለው ግልፅ ስለሆነ ሁለቱን ስያሜዎች ለየብቻ እንመልከታቸው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ የተሰየመው በነቢዩ ዘካሪያስ ልጅ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንጂ በሐዋርያው/ ወንጌላዊው ዮሐንስ አለመሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ በብሉይና አዲስ ኪዳን መካከል የነበረ እና "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ የኖረ፣ በመጨረሻም በሔሮድስ ትዕዛዝ ራሱን የተቆረጠ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡

በዚህም ምክንያት የቤተክርስቲያን አባቶች የበዓላትን ስርአት ሲሰሩ፣ ይህ በዓል ለመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ መታሰቢያ እንዲሆንና በእሱ ስምም እንዲጠራ በመወሰናቸው ነው፡፡

ዕንቁጣጣሽ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘራሉና ተራ በተራ እንያቸው፡፡

አንደኛው በኖህ እና በልጆቹ ዙሪያ የሚያጠነጥን፡፡ ሴም፣ ካምና ያፌት ሶስቱ የኖህ ልጆች ናቸው፡፡ ኖህ አህጉራትን ለሶስቱ ልጆች አከፋፍሎ ሲሰጥ ለካም አፍሪካ ደረሰው፡፡ ካም ወደ አፍሪካ የገባው እና መጀመሪያ የረገጠው ኢትዮጵያን ሲሆን ወሩም ምድሪቱ በአደይ አበባ ያሸበረቀችበት የመስከረም ወር ነበር፡፡ በምድሪቱ ውበት በመደመሙና ይህ ዕጣም ለእሱ ስለደረሰው ተደስቶ “ዕንቁ ዕጣ ወጣልኝ” አለ፡፡ እንግዲህ እንቁጣጣሽ ለሚለው ቃል አንዱ የየት መጣ ሀሳብ /Etymology/ እንዲህ የሚል ነው፡፡

ሁለተኛው ምድሪቱ በአደይ ፈክታ ሲመለከት “ዕንቁ ዕፅ አወጣሽ” ከሚል ነው እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ የመጣ የሚል ነው፡፡

በዚህኛው አካሄድ “ዕንቁ” ከኦይስተር ቅርፊት /pearl/ ውስጥ የሚገኝ ትንሽ ድቡልቡል፤ ጠንካራ አንጸባራቂ፤ ነጭ ውድ ጌጥ/ ለጌጥነት የሚያገለግል ነገር/ ሲሆን “ዕፅ” ደግሞ በግዕዝ የአማርኛው “ተክል” አቻ ነው፡፡ ስለዚህ የተክሉን መልክ ከዕንቁ ጋር በማነጻጸር የምድሪቱን ውበት ለመግለጽ የተጠቀሙበት ነው፡፡

ሶስተኛው ደግሞ የቀዳማዊ ምኒሊክ እናት ንግስት ሳባ ሰሎሞንን ለመጎብኘት በሄደችበት ጊዜ ንጉሱ “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ” ብሎ መስጠቱን መሰረት አድርጎ የሚነሳ ሃሳብ ሲሆን ወሩም ወርሃ መስከረም ነበር።

#ቀሲስ_ንዋይ_ካሳሁን
66😍5🙏3
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ!

ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም።

ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም በማረሚያ ቤት (በእስር) ከሚገኙ ወገኖች ጋር አዲስ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በጉባኤ እናከብራለን። በዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ይዘን እንሄዳለንና እርስዎ ለጌታ ጥያቄ መልስ የሚሆንዎት ተግባር ላይ ከአንድ ሰው ጀምረው እስከፈቀዱ መጽሐፍ ቅዱስን ማበርከት ይችላሉ። እስከ ሰማኒያ ሰው ለመስጠት አስበናል የአንዱ ዋጋ 900 ብር ነው። ዓመቱን በዚህ የተቀደሰ ተግባር ይጀምሩና ነፍስዎን ያስባርኩ።

ይህን ስጦታ ልዩ የሚያደርገው ለማያውቁት ሰው ከእግዚአብሔር ብቻ የሚጠብቁትን በረከት ለመቀበል የሚደረግ ፍጹም ስጦታ በመሆኑና የሚሰጡት የሕይወት ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ ነው።

ለዚህ በረከት ተሻሙ!
የንስሐ ዘመን ይሁንልን!

@natansolo
65🙏6😍4🕊1
#የአዲስ_ዓመት_ጸሎት_በአቡነ_ሺኖዳ

አቤቱ ጌታ ሆይ፦ ዓመቱን የተባረከ አድርገው። አንተን ደስ የሚያሰኝ ንጹሕ ዓመት ይሁን። መንፈስ የሚገለጥበት ዘመን ይሁን፣ ከእኛ ጋራም ይሥራ፤ እጆቻችንን ያዝና አሳቦቻችንን ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ማብቂያው ድረስ አንተ ምራቸው። አንተ ደስ ያሰኝህ ዘንድ ይህ ዓመት የአንተ ይሁን፡፡ ይህ አመት አዲስ ዓመት ስለሆነ በኃጢአታችንና በበደላችን አናርክሰው።

እግዚአብሔር ሆይ፦ በዚህ ዓመት ልንሠራው ባቀድነው በማንኛውም ሥራ ውስጥ አንተ ከእኛ ጋር ሁን፤ እኛ ዝም እንላለን አንተ ሁሉንም ነገር ታደርጋለህ፡፡

አቤቱ ጌታ ሆይ፦ ይህ ዓመት መልካም ይሁን።
በእያንዳንዳችን ላይ ፈገግታን ግለጥ፤ የሁላችንንም ልብ አስደስት፤ በችግራችን ውስጥ ጸጋህ ይገለጥ፤ የተፈተኑትንም አንተ እርዳቸው፤ የአሳብ ሰላምንና ጸጥታን አድለን፡፡ ለተቸገሩት ስጣቸው፤ የታመሙትን ፈውሳቸው፣ ያዘኑትን አጽናናቸው፡፡

ጌታችን ሆይ፦ ለራሳችን ብቻ አንጠይቅህም ያንተ ስለሆኑት ስለሁሉም እንጠይቃለን የፈጠርኻቸው ባንተ ደስ እንዲሰኙ ነው ይህ ከሆነ በአንተ ደስ እንዲሰኙ አድርጋቸው ቃልህ ለሁሉም ልብ ይደርስ ዘንድ ስለ ወንጌል አገልግሎትና ስለ ቤተ-ክርስቲያናችን እንጠይቅሃለን፤ ስለሃገራችንም እንጠይቅሃለን፡፡

መንግሥትህ በሁሉ ስፍራ እንድትመጣም ስለ ዓለም ሰላም እንጠይቅሃለን፡፡ ዓመቱ ፍሬያማና በመልካም ነገሮች የተሞላ ይሁን፡፡ እያንዳንዱ ቀንና ሰዓት የራሱ የሆነ ስራ አለው አንተ የሚባክን ጊዜ ይኖርህ ዘንድ አትፍቀድ፡፡ ሕይወታችንን በእንቅስቃሴ በሥራና በምርት የተሞላ አድርግ፤ ለምርታማና ለተቀደሰ ልፋታችን በረከትህን አድለን፡፡ በተግባራችን ውስጥ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት ከእኛ ጋር ይሁን።

አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ እስከዚች ሰዓት ድረስ ጠብቀህ ስላቆየኸንና ይህንን ዓመት ስላደልከን እናመሰግንሃለን፣ እንባርክህማለን፡፡
91🙏16🕊2
48🙏7🕊4💯3
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ!

ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም።

ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም በማረሚያ ቤት (በእስር) ከሚገኙ ወገኖች ጋር አዲስ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በጉባኤ እናከብራለን። በዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ይዘን እንሄዳለንና እርስዎ ለጌታ ጥያቄ መልስ የሚሆንዎት ተግባር ላይ ከአንድ ሰው ጀምረው እስከፈቀዱ መጽሐፍ ቅዱስን ማበርከት ይችላሉ። እስከ ሰማኒያ ሰው ለመስጠት አስበናል የአንዱ ዋጋ 900 ብር ነው። ዓመቱን በዚህ የተቀደሰ ተግባር ይጀምሩና ነፍስዎን ያስባርኩ።

ይህን ስጦታ ልዩ የሚያደርገው ለማያውቁት ሰው ከእግዚአብሔር ብቻ የሚጠብቁትን በረከት ለመቀበል የሚደረግ ፍጹም ስጦታ በመሆኑና የሚሰጡት የሕይወት ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ ነው።

ለዚህ በረከት ተሻሙ!
የንስሐ ዘመን ይሁንልን!

@natansolo
66🙏16👍5😍4👌2💯1
“በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ” መዝ 65፥11

ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን እንደ ኃጥአታችን ያይደለ እንደቸርነቱ የንስሃ ጊዜ የፍሬ ጊዜ ሰጥቶናልና እናመሰግነው ዘንድ ይገባናል፡፡ ምስጋናችንም ይህን የተወዳጅ ሐዋርያ የቅዱስ ጳውሎስን ቃል በመተግበር እንግለፅ፡፡

“ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌ 4፥22

መልካም አዲስ አመት!
95🙏14🏆1
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ!

ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም።

ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም በማረሚያ ቤት (በእስር) ከሚገኙ ወገኖች ጋር አዲስ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በጉባኤ እናከብራለን። በዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ይዘን እንሄዳለንና እርስዎ ለጌታ ጥያቄ መልስ የሚሆንዎት ተግባር ላይ ከአንድ ሰው ጀምረው እስከፈቀዱ መጽሐፍ ቅዱስን ማበርከት ይችላሉ። እስከ ሰማኒያ ሰው ለመስጠት አስበናል የአንዱ ዋጋ 900 ብር ነው። ዓመቱን በዚህ የተቀደሰ ተግባር ይጀምሩና ነፍስዎን ያስባርኩ።

ይህን ስጦታ ልዩ የሚያደርገው ለማያውቁት ሰው ከእግዚአብሔር ብቻ የሚጠብቁትን በረከት ለመቀበል የሚደረግ ፍጹም ስጦታ በመሆኑና የሚሰጡት የሕይወት ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ ነው።

ለዚህ በረከት ተሻሙ!
የንስሐ ዘመን ይሁንልን!

@natansolo
40🙏3👍1💯1🏆1
እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?”

ተወዳጆች ሆይ! አዲስ ዓመት ሲመጣ እነዚህን ነገሮች በጥንቃቄ ልናስብባቸው ይገባናል፡፡ ይህን እያደረግንም ስለ ቀጣዩ ዓመት እናስብ፡፡ ይህን የምናደርግ ከኾነ “ቀኖቻቸውም በከንቱ አለቁ፤ ዓመቶቻቸውም በችኰላ” አይባልብንም (መዝ.78፡3)፡፡ ዕለት ዕለት በዓልን እናድርግ ብዬ የገለጥኩላችሁም ይኸው ነው፡፡ የእኛ በዓል ዘወትር መኾን ይገባዋል፡፡ የክርስቲያኖች በዓል በዓመታትና በቀናት ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ ቤተ ክርስቲያንም በሳምንት፣ በወር፣ በዓመት የሚከበሩ በዓላት እንዲኖሩ ማድረጓ ዘወትር ከዚሁ ልንርቅ እንደማይገባ ማሳሰቧ እንጂ ሌላ አይደለምና፡፡ ይህን በዓል በየዕለቱ ማድረግም ለኹሉም ይቻላል፤ ለድኻውም ለባለጸጋውም ይቻላል፡፡ በዓልን ለማድረግ (የጽድቅ ሥራን ሠርቶ ሐሴት ለማድረግ) የሚያስፈልገው ቅን ልቡና እንጂ ገንዘብ አይደለምና፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰማዕትነት አያምለጣችሁ ገጽ 13-19 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመው)
82🙏14💯4
እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እኅቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡

እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡

ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡

የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንኾናለን፡፡”

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ- የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች ገጽ 27)
70🙏9
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ!

ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም።

ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም 11/2018 ዓ.ም በማረሚያ ቤት (በእስር) ከሚገኙ ወገኖች ጋር አዲስ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በጉባኤ እናከብራለን። በዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ይዘን እንሄዳለንና እርስዎ ለጌታ ጥያቄ መልስ የሚሆንዎት ተግባር ላይ ከአንድ ሰው ጀምረው እስከፈቀዱ መጽሐፍ ቅዱስን ማበርከት ይችላሉ። እስከ ሰማኒያ ሰው ለመስጠት አስበናል የአንዱ ዋጋ 900 ብር ነው። ዓመቱን በዚህ የተቀደሰ ተግባር ይጀምሩና ነፍስዎን ያስባርኩ።

ይህን ስጦታ ልዩ የሚያደርገው ለማያውቁት ሰው ከእግዚአብሔር ብቻ የሚጠብቁትን በረከት ለመቀበል የሚደረግ ፍጹም ስጦታ በመሆኑና የሚሰጡት የሕይወት ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ ነው።

ለዚህ በረከት ተሻሙ!
የንስሐ ዘመን ይሁንልን!

@natansolo

እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 10 የቻናላችን ቤተሰቦች 20,900 ብር አግኝተናል።

እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ23 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 57 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።

በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
34🙏11👍1
"እናንተ ደካሞች…"

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-“እናንተ ኃጢአት ሸክም የሆነችባችሁ፣ እናንተ ጭንቀት አላኖር አላስቀምጥ ያላችሁ፣ እናንተ ሐዘን የደቆሳችሁ፣ እናንተ ትእዛዛቴን በመተላለፍ ቅስማችሁን የተሰበራችሁ፣ እናንተ በሐፍረት ካባ ተከናንባችሁ የምትቆዝሙ፣ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ አበቃልኝ በቃኝ ብላችሁ ያንገሸገሻችሁ፣ እናንተ ለመናገር እንኳን ድፍረት ያጣችሁ… ምንም እንኳን ዝሙት ብትሠሩም፣ ምንም እንኳን ዋሽታችሁ ቢሆንም፣ ምንም እንኳን ሰርቃችሁ ቢሆንም፣ ምንም እንኳን መናገር የማትችሉት ከባድ የምትሉት ኃጢአት ብትሠሩም፣ ምንም እንኳን “ከእንግዲህ ወዲህ በቃ እግዚአብሔር ይቅር አይለኝም” ብትሉም የእኔ ፍቅር የእኔ ቸርነት ይህን ሁሉ ኃጢአታችሁን፣ ይህን ሁሉ ሸክማችሁን፣ ይህን ሁሉ ሐዘናችሁን፣ ይህን ሁሉ ከባድ የምትሉትን ነገራችሁን መደምሰስ የሚችል ነውና ኑ፡፡

ኑና ላሳርፋችሁ፤ ኑና ስለ እናንተ የቆሰለውን እጄ ተደገፉ፤ ኑና ፍቅሬን ቅመሱ፤ ኑና ቸርነቴን አጣጥሙ፤ ኑና ሸክማችሁን ሁሉ በእኔ ላይ አራግፉ፡፡ ብቻ እናንተ ፈቅዳችሁ ኑ እንጂ ከእኔ አቅም በላይ የሆነ ሸክም የለባችሁምና አትስጉ፡፡

ኑና ሥርየተ ኃጢአትን ልስጣችሁ፤ ኑና ዕረፍተ ነፍስን ሰጥቼ ላሳርፋችሁ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንኳ እንደ አመዳይ አነጻላችኋለሁ፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ አጠራላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ ኃጢአታችሁን እየቆጠራችሁ ከምትቆዝሙ ቀና በሉና ወደ እኔ ኑ፡፡ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና ልጆቼ ወደ እኔ ቅረቡ፡፡ እኔም ልቅረባችሁ፡፡ “ቀንበሬን ተሸከሙ” ስላችሁ በሩቁ አትፍሩኝ፡፡ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና፡፡ ደግሞም ይህ ቀንበር አንገታችሁን ለማለዘብ (ለመላጥ) ሳይሆን በቀጭኒቱ መንገድ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳትሉ እኔ ወዳዘጋጀሁላችሁ ርስት መንግሥት የምታደርስ ናትና በሩቁ አትፍሯት፡፡

ስለዚህ እናንተ ደካሞች፣ እናንተ ዓቅመ ቢሶች፣ እናንተ ከእኔ ውጪ ምንም ማድረግ የማትችሉ በገዛ ደሜም የገዛኋችሁ ልጆቼ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ማዳን ብቻ ሳይሆን አሳርፋችኋለሁ፡፡”

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
116🙏23👍1🏆1
2025/10/26 07:30:30
Back to Top
HTML Embed Code: