Telegram Web Link
"ልጆቼ! የሚያሳፍር ነገር፣ የስንፍና ንግግር ወይም ዋዛ ፈዛዛ የማይገቡ ናቸውና በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ ከቶ አይሰሙ፡፡ እስኪ ንገሩኝ! የዋዛ ፈዛዛ ንግግር ጥቅሙ ምንድን ነው? እስኪ ንገሩኝ፤ አንድ ጫማ ሰፊ፣ ጫማ እየሰፋ በአንድ ጊዜ ሌላ ሥራ መሥራት ይችላልን? አይችልም፡፡ ከዋዛ ፈዛዛ የሚያሳፍር ንግግር ይወለዳል፡፡ የአሁኑ ጊዜ ደግሞ ለእኛ ለክርስቲያኖች ዋዛ ፈዛዛ የምንናገርበት ሳይኾን የንስሐችን ጊዜ ነው፡፡ እስኪ አሁንም ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! አንድ ቦክስ የሚጫወት ሰው ውድድሩን ችላ ብሎ ዋዛ ፈዛዛን ይናገራልን? እንዲህ የሚያደርግ ከኾነስ በተጋጣሚው በቀላሉ የሚሸነፍ አይደለምን? ታዲያ ባለጋራችን ዲያብሎስ‘ኮ የሚውጠውን ፈልጐ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙርያችን ቁሟል፡፡ ጥርሱን እያንቀጫቀጨብን ነው፡፡ እኛን የሚጥልበት ወጥመድ በማዘጋጀት ላይ ነው፡፡ የደኅንነታችን መንገድ ላይ እሳት እየተነፈሰ ነው፡፡ ታዲያ ዲያብሎስ እንዲህ እኛን ለመጣል ሲተጋ እኛ ዋዛ ፈዛዛን፣ የሚያሳፍር ነገርን፣ የስንፍናንም ንግግር ስንናገር ቁጭ ልንል ይገባናልን?

የምወዳችሁ ልጆቼ! ጊዜው የምንተኛበት ጊዜ አይደለም፡፡ የተጋድሎ ጊዜ ነው እንጂ፡፡ ቅዱሳን ጊዜያቸውን እንደ ምን እንደሚያሳልፉት ማወቅ ትፈልጋላችሁን? እስኪ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስን አብረን እንስማው፤ እንዲህ ያለውን፡- “ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ”፤ … “በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችኋለሁ…”፡፡ … “የሚደክም ማን ነው፤ እኔ አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፤ እኔም አልናደድምን?”፤ “… በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን”፡፡ ታዲያ እነ ቅዱስ ጳውሎስ ጊዜያቸውን እንዲህ ካሳለፉ፣ ኃጥአን የምንኾን እኛ ጊዜያችንን በሳቅና ስላቅ ልናጠፋ ይገባናልን? በክርስቶስ ፍቅር የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በንግግሬ አትማረሩ፡፡

ጊዜው የተጋድሎ ጊዜ ነው፤ ታዲያ ስለ ምንድን ነው የዘፋኞችን መሣርያ አንሥተን ከዓለም ጋር የምንዘፍነው? በጦር ግንባር ያለ ወታደር ከጠላት ሊመጣ የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል ከመዘጋጀት ይልቅ ጊዜውን በዋዛ ፈዛዛ ያጠፋልን? አያጠፋም፡፡ ታዲያ እኛም‘ኮ የክርስቶስ በጎ ወታደሮች ነን፡፡ ..."

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
161🙏43💯8💔7👌5
"ቤተ ክርስቲያናችን እየተፈተነች ያለችው ከውጭ ብቻ ሳይሆን ከውስጥም ጭምር እንደሆነ መካድ የለብንም፤ ንጽህትና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥር የሰደደ የቅድስና ሕይወትና በፈሪሐ እግዚአብሔር የተቃኘ ሥነ ምግባር ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፤ በአሁኑ ጊዜ ግን እነዚህ ሁሉ ቦታቸውን እየለቀቁ ያሉ መስለዋል፤

ቤተ ክርስቲያን በረጅሙ ታሪኳ ሲያስተምሩም ሆነ ሲማሩ፣ ሲመንኑም ሆነ ሲመነኲሱ፣ ሲቀድሱም ሆነ ሲያስቀድሱ ያለምንም ደመወዝ በራሳቸው ዓቅም በግብርና እየተዳደሩ ቤተ ክርስቲያንን በጥሩ ሰብእና በንጽህና እና በቅድስና ጠብቀው ያስረከቡ እልፍ አእላፍ አበው እንዳልነበሯት ዛሬ የተሻለ ኑሮና ደመወዝ እያገኘን እግዚአብሔርን እንደቀኖናው በጥንቃቄ ማገልገል አቅቶናል፤ ምእመናንም በዚህ ምክንያት እየተሰናከሉ እንደሆነ እየተስተዋለ ነው፡፡

ሚድያውም ስሕተቶችን ወደ ውጭ በማውጣት ሰድቦ ለሰዳቢ እየዳረገን ነው፤ ይህ ሊሆን የቻለው የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት በአግባቡ በመያዝ ለታለመለት ዓላማ ማዋል አለመቻላችን ነው፤ ይህ ችግር ባለበት ከቀጠለ ሌላ ጦስ ይዞብን እንዳይመጣ ሁነኛ ለከት ማኖር የግድ ይሆናል፡፡ "

(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በ፵፬ ኛው የሰበካ ጉባኤ ዓለም አቀፍ መደበኛ ስብሰባ የመክፈቻ ንግግር።)
123🙏46💯9😍6💔6
ልጆቼ፦ እግዚአብሔርን በእምነት በጸሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሔር ልናቀርብ ይገባናል፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን?

እንዲህ ከሆነ መሐሪ እግዚአብሔርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሔርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እግዚአብሔርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
137🙏24🏆1
እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ  እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
157🙏33👌4
ትንሿ ቤተክርስቲያን በኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ

ባለትዳሮች በቤታቸው ውስጥ ማድረግ ያለባቸው ቤተ ክርስቲያን መጥተው ያዩትን ነው፡፡ ለምሳሌ፦

👉 ቤተክርስቲያን ውስጥ የጠዋትና የሰርክ ጸሎት እንዳለ ኹሉ እነዚህ ባለ ትዳሮችም የጠዋትና የሰርክ ጸሎት በቤታቸው ውስጥ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ያለው የኅብረትና የአንድነት ጸሎት እንደ ኾነ ኹሉ፥ ባልና ሚስት ልጆችም ሳይለያዩ አብረው መጸለይ አለባቸው፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ ከቅዳሴ በኋላ ትምህርተ ወንጌል እንዳለ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም እራት ከበሉ በኋላ ቃለ እግዚአብሔር ሊማማሩ ይገባቸዋል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ ራሳቸውን ገዝተው የሚኖሩ ትጉሃን መነኰሳት እንዳሉ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ይህን ትግሃትና ምስጋና ወደ ቤታቸው ይዘዉት ሊኼዱ ይገባቸዋል፡፡

👉 ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማታ ላይ ኅብስቱን አበርክቶ ሕዝቡን ከመገባቸው በኋላ ወዲያው ወደ መኝታ እንዲኼዱ እንዳላደረገ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ወደ መኝታቸው ከመኼዳቸው በፊት የቀን ውሎአቸውን መገምገም አለባቸው፡፡

👉 ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሊት ሌሊት ሲጸልይ ያድር እንደ ነበረ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ሌሊት ላይ ነቅተው መጸለይ ይገባቸዋል፡፡ ሕፃናት ካሉም አብረዋቸው እንዲነሡ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ጾም እንደሚታወጅ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም በቤተ ክርስቲያን ከሚታወጀው ጾም በተጨማሪ ከንስሐ አባቶቻቸው ጋር ተመካክረው በፈቃዳቸው ሊጾሙ ይገባቸዋል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳለው፥ ባልና ሚስትም የቤታቸውን ግድግዳ፣ መስኮትና በር በመስቀል ሊያስጌጡት ይገባቸዋል፡፡ ማማተብ በማይችሉ ልጆቻቸው ግንባርም አድገው ራሳቸው ማማተብ እስኪችሉ ድረስ እነርሱ ያማትቡላቸው፡፡ ቅዱሳት ሥዕላትም በቤታቸው ውስጥ ሊኖሩ ይገባል፡፡

ቤታቸው ትንሿ ቤተ ክርስቲያን የምትኾነው በዚህ መንገድ ነው፡፡

(ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 60 - 61)
159🙏20👍3
"ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ብርቱ (ጠንካራ) ምንም የለም። ይህችውም ከሰማይ ከፍ ያለች ከምድርም ይልቅ የሰፋች ናት። አታረጅም ነገር ግን ዘወትር ታበራለች።"…

"ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ሁሉ ትሰፋለች። መታሰቢያዋም የሚጠፋ (የሚሞት) አይደለም።"…

"ቤተ ክርስቲያን በስንቶች ውጊያ ተደርጎባት ነበር? አልተሸነፈችም እንጂ። የተዋጓት አላውያን፣ የጦር መሪዎች፣ ነገሥታቱስ ምን ያህል ናቸው? የተማሩና ኃይልን የተሞሉ ጎበዞች ሐዲሲቷን ቤተ ክርስቲያን በብዙ ጎዳናዎች ተዋግተዋት ነበር። ሊነቅሏት ግን አልቻሉም። ነገር ግን እርሷን የተዋጉ ጥቂቶች ለዝምታና ቶሎም ለመረሳት ተላልፈው ተሰጥተዋል። የወጓት ቤተ ክርስቲያን ግን ከሰማይ በላይ ከፍ ከፍ ብላለች። ቤተ ክርስቲያንን ድል ከማድረግስ ፀሐይን ማጥፋት (ማጨለም) ይቀላል። ሰው ሆይ! ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ኃያል ምንም የለም። ከሰው ብትጣላ ወይ ታሸንፋለህ አልያም ትሸነፋለህ። ቤተ ክርቲያንን ግን ብትጣላ፣ ታሸነፍ ዘንድ የሚቻልህ አይደለም። እግዚአብሔር ከሁሉ ይልቅ ኃያል ነውና። እግዚአብሔር መስርቷታል፣ እንግዲህ ማን ሊነቀንቃት ይችላል? "

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(በዲያቆን አቤል ካሳሁን የተተረጎመ)
115🙏11👌2
48👍2🕊2💔2
እመቤቴ የተመረጥሽ ድንግል ማርያም ሆይ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ አምላክ ካንቺ ጋራ በመሰደዱ በግብፅ መከራሽ እማልድሻለሁ፡፡ መንገድ በመሄድ የድካምሽ አሳብ በልጅሽ ፊት ይቁም ስለ ኃጢአቴ መማለጃ ይሆን ዘንድ፡፡

በምድረ ግብፅ ያገኘሽ የረኃብና የጽምዕ ሐሳብ በበኩር ልጅሽ ፊት ይቁም ስለ ኃጢአቴ ማቃለያ ይሆን ዘንድ፡፡ ካይንሽ የፈሰሰው የዕንባ ጎርፍ በፊትሽ የተንጠባጠበው በልጅሽ በወዳጀሽ ፊትም የወረደው፡፡ አሁንም ደግሞ በልጅሽ በወዳጅሽ ፊት ይቁም ስለ ኃጢአቴ ማዘከሪያ ይሆን ዘንድ፡፡

የሠራሁትን ኃጢአት ባስበው ልቡናዬ እጅግ ደነገጠብኝ፡፡ አእምሮ ሳለኝ አለል ዘለል እያልኩ በጽርዓት መኖሬን ባሰብሁት ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ፡፡ የኃጢአቴን ብዛት በተቆጣጠርሁ ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ አንድ ሰዓት ስንኳን ኃጢአት ለመስራት አላቋረጥኩም፡፡

በሰውና መላእክት ጉባኤ መካከል ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ፡፡ በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስሁ፡፡ ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ፡፡ ከዚህ እጅግ የሚያስፈራው ከሠራሁት ኃጢአት ፍዳ የተነሣ ምናልባት የሚዋሰኝ ባገኝ ብዬ፡፡ ነገር ግን በማማለድ እኔን ለማዳን የምትቸይውን አንቺን አማላጅ አገኘሁ፡፡ ዘወትርም ከኔ እንዳትርቂ ዐወቅሁ፡፡

እንዲህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቼ አይደለም በሃይማኖት ያዝሁሽ በመዳሰስ አይደለም በእደ ሕሊና ያዝሁሽ በእደ ሥጋ አይደለም፡፡ እደ ሕሊናየን ግን የሰው ኃይለኝነት ሊያስተወው አይችልምና፡፡ የሰይፍ ስለትም ሊቆርጠው አይችልም፡፡

ልትደገፊኝ ያዝሁሽ ልትጥይኝ ግን አይደለም ወደ ላይ ከፍ ከፍ ልታደርጊኝ ያዝሁሽ ወደ ታች ልታወርጅኝ ግን አይደለም፡፡ ለዘለዓለሙ ያዝሁሽ ለዕድሜ ልክ ብቻ አይደለም፡፡ እናቴ ሆይ ነፍሴ ባንቺ ዘንድ ትክበር ስለቸርነትሽም እመቤቴ ነሽ፡፡ ስለ ፍቅርሽ የታመንሽ ስለ ልጅሽም የመድኃኒት ቀንድ ሆይ አስቢኝ እንደ ወደቅሁም እቀር ዘንድ አትርሺኝ፡፡

(በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ - የማክሰኞ አርጋኖን)
167🙏29🏆4🕊2👍1
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፥አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፥
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፥ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፥ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።”

ትርጉም፦
ነጭና ቀይ አበባ የሚመስል ልጅሽን ታቅፈሽ፥በመንጻት ወራት በተዓምርም ቀን ወደቤተ መቅደስ ስትገቢ፥ከኀዘኔ ታረጋጊኝ/ታጽናኚኝ ዘንድ ርግቤ ኾይ ነይ፥መልካም እናቴ ኾይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፥እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከኾነ ከሚካኤል ጋር ነይ።”

               (አባ ጽጌ ድንግል)

ለማኅሌተ ጽጌ የተፈጥሮ አበቦችን ተባብራችሁ ግዙልን

@natansolo
165🙏14
"ልጅሽ ደጅ ላይ ቆሟል"

ከመስከረም 26 እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደ የካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው...መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ። ‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡ ‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤ ‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ፣ ‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት....

ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡ ‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ

ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው...በሲጋራና በመጠጥ ሽታ የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤

‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ። መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት

‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት...ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን...ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት...ለረጅም ዓመታት...አክሊለ ጽጌ ብዬ...ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ

‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ...በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ...አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ...ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ...ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል

‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም...ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ...ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ...ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ...መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣...የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ...ማልቀስ እጀምራለሁ...ፍቅሯን አስባለሁ....የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው....ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል....በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ››

አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤
‹‹ወደ ውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ ‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤
‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣

‹‹ማን....እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ....እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ

ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ። ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ›› አልኩ አምላኬን፣ በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት

(ዲያቆን አብርሃም ይኄይስ እንደጻፈው)
172💔31😍27🙏7
ምጽዋት ብዛት ወይስ ጥራት?

የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ። የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ።

አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው። የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፤ ታድያ ለወንድምህስ የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነውን? መሆን የለበትም። ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው። ከምትለብሳቸው ሁለቱ ልብሶች አንዱን ስጠው። የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው። ለአንተ የምትመኝውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ። "እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40 ያለውን ቃል መለስ ብለህ አስብና የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ።

አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋእት እንዴት እንደነበረ አሰብ። "አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋእቱ ተመለከተ።"ዘፍ 4፥4 ለምን መረጠለት? ብትል አቤል ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርጎ ስላቀረበ ነው። በሐዋርያት ሥራ 4፥34-35 ላይ ሰፍሮ የሚገኝውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ።

"እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40

#ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
95🙏10
#ጥቅምት_8

#ቅዱስ_አባ_አጋቶን_ባህታዊ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ዳግመኛም በዚህ ቀን ታላቁ አባት አባ አጋቶን መታሰቢያው እንደሆነ ስንክሳሩ በስም ጠቅሶ ያልፈዋል፡፡ ይህን ቅዱስ ታላቅ ጻድቅ ገዳማዊና የእግዚአብሔር ሰው ሲሆን አንደበቱን ከክፋት ይከለክል ዘንድ ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሶ ኖሯል። ይህንን ቅዱስ ሊቃውንት ሲገልጹት "ክምረ ክምር ጽድቁ እስከ አስተርአየ" ይሉታል። ትእግስቱ ደግነቱ አርምሞው ትሩፋቱ ከመነገር በላይ ነው። በነበረበት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም እንደ ኮከብ ያበራ ታላቅ አባት ነው።

ታላቁ ገዳማዊ አባት አጋቶን የታላቁ መቃርዮስ የመንፈስ ልጅ ነው። ገዳመ አስቄጥስ እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን ስታፈራ ይህ አባት ቅድሚያውን ይይዛል። ምንም በብዛት የሚታወቀው በአርምሞው (በዝምታው) ቢሆንም ባለ ብዙ ትሩፋት አባት ነው። የሚገርመው የቀደሙ አባቶቻችን የፈለገውን ያህል መናኝ ቢሆኑም የሰው ጥገኛ መሆንን አይፈልጉም። "ሊሠራ የማይወድ አይብላ" የሚለውን መለኮታዊ ትዕዛዝ መሠረት አድርገው ከተጋድሎ በተረፈቻቸው ሰዓት ሥራ ይሠራሉ። አንዳንዶቹ እንደሚመስላቸው ምናኔ ሥራ መፍታት አይደለምና ሰሌን ዕንቅብ ሠፌድ የመሳሰለውን ይሠፋሉ። ታላቁ አባ አጋቶንም በአንደበቱ ድንጋይ ጐርሶ በእግሮቹ ቀጥ ብሎ ቆሞ እንቅቦችን ይሠፋ ነበር። ቅዱሱ የሰፋውን ወደ ገበያ ይወጣል በጠየቁትም ዋጋ ሽጦት አንዲት ቂጣ ይገዛል። የተረፈውን ገንዘብ ግን እዚያው ለነዳያን አካፍሎት ይመጣል እንጂ ወደ ገዳሙ አይመልሰውም።

አንድ ቀን እንደልማዱ የሠፋቸውን እንቅቦች ተሸክሞ ወደ ገበያ ሲሔድ መንገድ ላይ አንድ የኔ ቢጤ ወድቆ ያገኛል። እንደ ደረሰም ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ ይለምነዋል። አባ አጋቶን ከእንቅቦቹ ውጪ ምንም ነገር አልነበረውምና "እንቅቡን እንካ" አለው። ነዳዩ ግን ወይ የሚበላ ካልሆነም ገንዘብ እንደሚፈልግ ይነግረዋል። ወዲያው ደግሞ "የምትሠጠኝ ነገር ከሌለህ ለምን ወደ ገበያ ተሸክመህ አትወስደኝም?" አለው። የነዳዩ አካል እጅግ የቆሳሰለ በመሆኑ እንኩዋን ሊሸከሙት ሊያዩትም የሚከብድ ነበር። ጻድቁ ግን ደስ እያለው ያለማመንታት አንስቶ ተሸከመው። ከረጅም መንገድ በኋላ ከገበያ በመድረሳቸው አውርዶ ከጐኑ አስቀመጠው። ያ ነዳይ አላፊ አግዳሚውን ሁሉ ቢለምንም የሚዘከረው አጣ። አባ አጋቶን አንዷን እንቅብ ሲሸጥ "ስጠኝ?" ይለዋል። ጻድቁም ይሠጠዋል። እንዲህ "ስጠኝ" እያለ የእንቅቦችን ዋጋ ያ ነዳይ ወሰደበት። አባ አጋቶን ግን ምንም ቂጣ ባይገዛም በሆነው ነገር አልተከፋምና ሊሔድ ሲነሳ ነዳዩ "ወደ ቦታየ ተሸክመህ መልሰኝ" አለው። አባቶቻችን ትእግስታቸው ጥግ የለውምና ጐንበስ ብሎ በፍቅር አንስቶት አዘሎት ሔደ። ካነሳበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ይወርድለት ዘንድ ጻድቁ ቆመ። ነዳዩ ግን አልወርድም አለ። ትንሽ ቆይቶ ግን ለቀቀው ሊያየው ዞር ቢል መሬት ላይ የለም። ቀና ሲል ግን ያየውን ነገር ማመን አልቻለምና ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ነዳይ መስሎ እንዲያ ሲፈትነው የነበረው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነበርና ክንፎቹን ዘርግቶ በብርሃን ተከቦ በግርማ ታየው ከወደቀበትም አነሳው። "ወዳጄ አጋቶን ፍሬህ ትእግስትህ ደግነትህ ግሩም ነውና ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎት ተሰወረው፤ ጻድቁም በደስታ ወደ በዓቱ ሔደ። አባ አጋቶን ተረፈ ዘመኑን በአርምሞ ኑሮ ዐርፏል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ጥቅምት እና #ከገድላት_አንደበት)
99🙏10💯2
450 አበቦች ለዛሬ ለሁለተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ደርሶልናል እናመሠግናለን!

ለሦስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ የተፈጥሮ አበቦችን የምትተባበሩን በውስጥ አናግሩኝ

@natansolo
82😍3
2025/10/20 03:28:19
Back to Top
HTML Embed Code: