Telegram Web Link
በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!'

መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም 'ለሰው ፊት የማያዳላ' እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም። (ሐዋ 10፥34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡

'የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ' ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው።

(ዲያቆን አቤል ካሳሁን)
184🙏32🕊5🏆2👍1
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለኦሎምፒያስ የተላከ መልእክት

(ቅዱሱ ይህንን መልእክት ሲልክ በሕመም ላይ እያለ መሆኑን ልብ ይሏል።)

ተወዳጂት ሆይ! የገጠመሽ ነገር እንግዳ ወይም ያልተለመደ ነገር አይደለም፤ ያው የተለመደውና ለሕሊና ተስማሚ የኾነ ነው እንጂ፡፡ ይኸውም ኹልጊዜ አዘውትሮ በሚያገኝሽ መከራ የነፍስሽ ጅማቶች ይበልጥ ይጠነክሩ ዘንድ፣ ጉጉትሽና ኃይልሽ ለተጋድሎ ይጨምር ዘንድ፣ ከዚያም ታላቅ የኾነ ደስታን ታገኚ ዘንድ ነው፡፡ የመከራ ጠባይዋ እንደዚህ ነውና፡- ብርቱና ንጹህ ነፍስን ስታገኝ እነዚህ ከላይ የገለጽኩልሽን ነገሮች ታስገኛለች፡፡

እሳት በእርሷ ላይ የተጨመረችን የወርቅ ቅንጣት ንጹህ እንደምታደርጋት ኹሉ መከራም ወርቃማ ነፍሳትን ስታገኝ ይበልጥ ንጹሃንና ብሩሃን ታደርጋቸዋለች። ስለኾነም የተወደደው ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- "መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም አመክሮን" /ሮሜ.5፥3-4/፡፡ ስለ እነዚህ ምክንያቶች እኔም ደስ እሰኛለሁ፤ ሐሴት አደርጋለሁ፤ የአንቺን ብርታት እያሰብሁ እዚህ በብቸኝቴ እጽናናለሁ፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ስፍር ቊጥር የሌላቸው ተኩላዎች ቢከቡሽም፣ ምንም እንኳን የክፉዎች ማኅበር በዙሪያሽ ቢኖሩም አንዳችም ቢኾን አልፈራም፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ፈተና እንዳንገባ እንድንጸልይ እንዳዘዘን አሁን ያሉት ፈተናዎቸች እንዲያልፉ፣ ለወደፊቱም ሌሎች እንዳይኖሩ እጸልያለሁ እንጂ፡፡

እግዚአብሔር ፈቃዱ ኾኖ ፈተናዎች የሚኖሩ ከኾነ ግን ከዚያ ፈተና ብዙ ሀብታትን በምታገኝ በወርቃማው ነፍስሽ እተማመናለሁ፡፡ ታዲያ እነርሱ ራሳቸው እጠፋ እጠፋ የሚሉ ኾነው ሳለ አንቺን የሚያስፈሩሽ እንዴት ነው? ሀብትሽንና ንብረትሽን በማሳጣት ነውን? እነዚህስ በአንቺ ዘንድ ከአፈርና ከትቢያ ይልቅ የተናቁ እንደኾኑ ዐውቃለሁ፡፡ ከአገርሽና ከቤትሽ እንድትሰደጂ ስለሚያደርጉሽ ነውን? ይህስ በታላላቅና ሕዝብ በበዛባቸው ከተሞች ላይ ምንም ሰው እንደሌለባቸው በመቊጠር እንዲሁም ዓለማዊ ፍላጎቶችን ከእግርሽ በታች በመርገጥ እንዴት በአርምሞና በዕረፍት መኖር እንዲቻል ታውቂዋለሽ፡፡ እንደሚገድሉሽ በመዛት ነውን? ይህም ቢኾን በየጊዜው ይህን እየጠበቅሽ ተለማምደሸዋል፡፡ ወደ መታረድ ቢጎትቱሽም ሰውነትሽ አስቀድሞ ለዚህ ዓለም የሞተ ነውና፡፡ ከዚህ በላይስ ምን እንድነግርሽ ትፈልጊያለሽ? አንቺ ራስሽ ወደሽና ፈቅደሽ አብዝተሽ ያላደረግሽውን ነገር በአንቺ ሊፈጽም የሚችል አንድ ሰውስ እንኳን የለም፡፡ ምክንያቱም አስቀድመሽ በጠባቢቱና በቀናይቱ መንገድ በመጓዝ በእነዚህ ኹሉም ነገሮች ራስሽን ስታለማምጂ ኖረሻል፡፡

በሕይወትሽ ኹሉ ይህን አስደናቂ ጥበብ ስትለማመጂ ስለነበርሽም አሁን በፈተናው ውስጥ እንኳን ከፍ ከፍ ብለሽ ታየሽ፡፡ በሚደርሱት መከራዎች መደናገጥስ ይቅርና ጭራሽ በእነርሱ ምክንያት በፍስሐ ወሐሴት ዘልለሻል፡፡ በመንፈሳዊ ልምምድሽ ውስጥ ስትጠብቂያቸው የነበሩ ፈተናዎች ምንም እንኳን ሰውነትሽ ከሸረሪት ድር ይልቅ ደካማ ቢኾንም አሁን በቀላለ ድል የምታደርጊያቸው ኾነሻል፡፡ ምንም እንኳን ሴት ብትኾኚም፥ ካዘጋጁልሽ መከራ ይልቅ ሌላም ቢኾን ለመቀበል ዝግጁ ኾነሽ ጥርሳቸውን እያንቀጫቀጩና በቊጣ ነድደው የሚመጡ ወንዶች፥ ፌዛቸውን ከእግርሽ በታች ረግጠሸዋል፡፡ በምትቀዳጂው አክሊል ሽልማት እጅግ በጣም ደስተኛ ነሽ፤ በዚህ ብቻም ሳይኾን በፈተናው በራሱ እጅግ ደስተኛ ነሽ፡፡

የእንደዚህ ዓይነት ተጋድሎ ጠባዩ እንደዚህ ነውና፦ አክሊል ሽልማቶቹ ከመሰጠታቸው በፊት በፈተናው ውስጥ ዋጋቸውና ብድራታቸው አለ፡፡ ይኸውም አንቺ አሁን ያገኘሽው ደስታ፤ ሐሴት፤ መንፈስ ጠንካራነት፣ ጽናት፣ ትዕግሥት፣ ኹሉንም ነገር ድል አድርጎ የሚያሳይ ከፍ ያለ ኃይል፣ በማንኛውም እጅ የሚመጣውን ዛቻ እንደ ቁም ነገር እንዳትቈጥሪው ያደረገሽ ፍጹም ልምምድ፣ በብዙ የመከራ ሞጎዶች ውስጥ እንደ ዓለት ጸንቶ መቆም፣ ባሕሩ በዙሪያሽ ኾነ የፈለገውን ያኽል ስርግርግ ቢልም እንኳን አንቺ ታላቅ በኾነ ጽሞና ውስጥ መግባት ነው፡፡ እነዚህ ኹሉ ርስት መንግሥተ ሰማያት ከመውረስሽ በፊት በዚህ ዓለም የምታገኚያቸው የመከራ ሽልማቶች ናቸው፡፡ ይህን በዚህ ዓለም እንኳን ቢኾን በደስታ ተሞልተሸ፣ ሥጋ እንደ ለበሰ ሰው ሳትኾኚ ከዚህ የከፋ ነገር ቢመጣ እንኳን ለመቀበል ዝግጁ እንደኾንሽ በደንብ አድርጌ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ደስ ይበልሽ! በራስሽና በአልጋቸው፤ ወይም በቤታቸው ሳይኾን በወኅኒ ቤት፤ በእግረ ሙቅ፣ በግርፋት ቅዱስ ሞትን በሞቱ ኹሉ ሐሴት አድርጊ፡፡ ማዘን የሚገባሽ እነዚህን ኹሉ ስቃያት ለሚያደርሱት ነው፡፡

ስለ ሥጋዊ ጤንነቴ ማወቅ ስላለብሽ በቅርብ ጊዜ ሲያሰቃየኝ ከነበረው ሕመም አሁን ደኅና መኾኔን ልንገርሽ፡፡ አሁን ጥሩ ኹኔታ ላይ ነው ያለሁት፡፡ ጥቂት የምፈራው ክረምቱ ሲመጣ ምናልባት የጨጓራ በሽታዬ እንዳይቀሰቀስብኝ ነው፡፡ ከአይሳውሪያናውያን ጋር በተያያዘ ግን አሁን በጣም ሰላም ነን፡፡

(ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ኦሎምፒያስ የተላኩ መልዕክቶች ገጽ 104-105 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
96🙏13
በእመቤቴ 5 መጽሐፍ ቅዱስ ግዙልኝ 🙏 ፈልጌው ነው 🙏
የአንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ዋጋ 1350 ብር ነው።

@natansolo በውስጥ ኑ!
33💯5🙏1
#የሕፃኑን_ሕይወት_እንታደግ

ሕፃን ተመስገን ደስታው ይባላል የ13 ዓመት ልጅ ሲሆን የሚተዳደረዉ ሱቅ በደረቴ በመሥራትና ማደሪያዉን ዘበኛ ጋር አድርጎ ነበር። እናትና አባቱ ላልይበላ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ሁለቱም በሽተኞች በመሆናቸዉ ከሚያገኘዉ ገንዘብ በመቆጠብ በመጠኑ ይረዳቸዉ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ ከፍተኛ የደም ማነስ ተብሎ የሰዉ ደም ቢወስድም በአፉና በአፍንጫዉ ደም እየፈሰሰ ስላስቸገረው ከወልድያ ሆስፒታል ወደ ደሴ ሆስፒታል ከዚያም ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄዶ እንዲታከም ሪፈር የተፃፈለት ሲሆን፤ ይህን ህጻን የሚያሳክመው አቅም ያለው ቤተሰብ ባለመኖሩ በበጎ አድራጊዎች እርዳታ አዲስ አበባ ቢሄድም የህክምና ዉጤቱ የደም ካንሰር ያሳያል ስለተባለና ህክምናዉም ለረዝም ጊዜ የሚቆይ ስለሆነ የምትችሉትን እንድትረዱት ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ባህሩ ዋሴ ➛ 1000327114895
ለበለጠ መረጃ ➛ 0975121276
💔12329👍2😍1🏆1
የመስቀል በዓል ስጦታ ስጡኝ

በእመቤቴ 5 መጽሐፍ ቅዱስ ግዙልኝ 🙏 አዲስ ለተመሠረተ ሰነሰበት ት/ቤት ፈልጌው ነው 🙏

የአንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ዋጋ 1350 ብር ነው።

@natansolo በውስጥ ኑ!
🙏2415💯3
እነሆ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ በእግዚአብሔር ማመንም ተመልሷል፤ እውነትም [ወንጌልም] ወደ ዓለም ኹሉ ደርሷል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ ሰማዕታትም [ከመስቀል በኋላ ሞት ሞት መኾኑ እንደ ቀረና የሹመት የሽልማት ማሳ መኾኑን ዐውቀው አብረው] ተገልጠዋል፤ በክርስቶስ ማመንም በኹሉም ዘንድ ተሰራጭቷል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ [በእርሱም ሞት ራሱ ሞቷልና] ትንሣኤ ሙታንም ተገልጧል፤ ሕይወትም ታይታለች፤ መንግሥተ እግዚአብሔርም እንደዚሁ እርግጥ ኾናለች፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ለእነዚህ ኹሉ ነገሮች ምክንያት ኾኗል፡፡ በመስቀሉ እግዚአብሔርን ማመስገን ተማርን፡፡ እንግዲህ ከቅዱስ መስቀሉ ይልቅ ሌላ የተወደደ ምን አለ? እኮ ከቅዱስ መስቀሉ በላይ ለነፍሳችን የሚረባት [የረባት፣ የጠቀማት] ሌላ ምን አለ? ስለዚህ በሙሉ ልባችን ይህን እንመስክር እንጂ ስለ ቅዱስ መስቀሉ ለመናገር ቅንጣት ታህልስ እንኳን አንፈር፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)

ሞታችንን በሞቱ ለሻረበት ለሰላማችን መገኛ፤ ኃይላችን፣ መድኃኒታችን፣ መመኪያችንና መጠጊያችን ለሆነን በዓለ መስቀል እንኳን አደረሰን።
72🙏11
"ወንዶች እንደ ቆስጠንጢኖስ፥ ሴቶች እን እሌኒ"

መጋቤ ጥበባት አክሊለ ብርሃን መስከረም 2018 ዓም

https://youtube.com/watch?v=jzvc8muh6KA&si=PxzRBDKfl2RkTHsp

መጋቤ ጥበባት ስለ ነገረ መስቀል ምን አሉ?
ሊንኩን ተጭነው ያድምጡ!
👍128🙏4
የመስቀል በዓል ስጦታ ስጡኝ

በእመቤቴ 5 መጽሐፍ ቅዱስ ግዙልኝ 🙏 አዲስ ለተመሠረተ ሰነሰበት ት/ቤት ፈልጌው ነው 🙏

የአንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ዋጋ 1350 ብር ነው።

@natansolo በውስጥ ኑ!
18💔8👍5
መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው።
መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው።
መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው።
መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው።

መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው።

መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው።

መስቀል ማኅተመ ሥላሴ የሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው።

መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው።

መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው።
መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው።

መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው።
መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው።

መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው።

መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው።

(ውዳሴ መስቀል - በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
88🙏10😍6🏆2👍1
በሐሰት ወሬ አትሸበሩ

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስና የሀገረ ስብከቱ አመራሮች "ከተማዋ ሰላም ናት" በሚል ፕሮፓጋንዳ እንዲሠሩ መመሪያ ወርዷል የሚል መረጃ በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር ተመልክተናል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስና የሚመሩት ሀገረ ስብከት ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸውን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ከመወጣት ያለፈ ያስተላለፉት መልእክትም ሆነ የተላለፈላቸው መመሪያ የለም።

ብፁዕነታቸው የኹሉም አባት በመሆናቸው የፖለቲካ፣ የሃይማኖት፣ የዘር ወዘተ ልዩነት ሳያደርጉ እኩል አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ አሁንም እያገለገሉ የሚገኙ ሃይማኖታቸውን በምግባር የገለጡ አባት ናቸው።

የመንግሥትም ሆነ የፋኖ ታጣቂዎች ባሉበት ኹሉ የማስተማርና የመመገብ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን ከመስጠት የተቆጠቡበትጊዜ የለም።

በማኅበራዊ ትስስር ገጾች በሚሰነዘሩ አሉባልታዎች አገልግሎታቸውን ማስቆም አይቻልም።

በፈጠራ ወሬ አባትን መክሰስ ምን ለማትረፍ? የት ለመድረስ? እንደሆነ የሚያውቁት የሀሰት መረጃውን ያሠራጩት ሰዎች ብቻ ናቸው።

(የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት)
66🙏19💔4
ቅዱስ መስቀል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በመስቀል ከጠላትነት ድነናል፤ በመስቀል ወደ እግዚአብሔር አንድነት ተመልሰናል፡፡ በመስቀል ዲያብሎስ አርነት ወጥተናል፤ በመስቀል ከሞትና ከጥፋት ድነናል፡፡

ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን በሞት ጥላ ሥር ተይዘን ነበር፤ አሁን ብሥራተ መስቀል በተገለጠበት ጊዜ ግን ህልውና እንኳን እንደሌለው አድርገን ቈጥረን የዘለዓለም ሕይወትን እየናፈቅን ሞትን ንቀነዋል፡፡ ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን ለገነት እንግዶች ነበርን፤ መስቀል በተገለጠ ጊዜ ግን ወንበዴስ እንኳን ለገነት የተገባ ሆኖ ተገኘ፡፡

የሰው ልጅ እንደዚህ ካለ ጨለማ መጠን ወደ ሌለው ብርሃን፣ ከሞት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት፣ ከመዋቲነት ወደ ኢመዋቲነት ታድሶ ተሸጋገረ፡፡ ዓይነ ልቡና ባለማወቅ ጽልመት ከመታወር ድኖ በመስቀል የዕውቀት ብርሃን ተጥለቀለቀ፡፡ እዝነ ልቡና ካለማመን ድንቁርና ወጥቶ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ መስማት ተመለሰ፤ ዕውራንም ብርሃናቸው ተመልሶላቸው የእግዚአብሔርን ክብር ማየት ተችሎአቸዋል፡፡ በቅዱስ መስቀሉ የተሰጡን ሀብታት እነዚህ ናቸው፡፡ በቅዱስ መስቀሉ ያልተሰጡን በረከቶችስ ምን አሉ?

እነሆ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ በእግዚአብሔር ማመንም ተመልሷል፤ የእውነት ወንጌልም ወደ ዓለም ሁሉ ደርሷል፡፡

ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ ሰማዕታትም ከመስቀል በኋላ ሞት ሞት መኾኑ እንደ ቀረና የሹመት የሽልማት ማሳ መኾኑን ዐውቀው አብረው ተገልጠዋል፤ በክርስቶስ ማመንም በሁሉም ዘንድ ተሰራጭቷል፡፡

ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ በእርሱም ሞት ራሱ ሞቷልና ትንሣኤ ሙታንም ተገልጧል፤ ሕይወትም ታይታለች፤ መንግሥተ እግዚአብሔርም እንደዚሁ እርግጥ ኾናለች፡፡

ቅዱስ መስቀሉ ለእነዚህ ኹሉ ነገሮች ምክንያት ኾኗል፡፡ በመስቀሉ እግዚአብሔርን ማመስገን ተማርን፡፡ እንግዲህ ከቅዱስ መስቀሉ ይልቅ ሌላ የተወደደ ምን አለ? እኮ ከቅዱስ መስቀሉ በላይ ለነፍሳችን የሚረባት ወይም የረባትና የጠቀማት ሌላ ምን አለ? ስለዚህ በሙሉ ልባችን ይህን እንመስክር እንጂ ስለ ቅዱስ መስቀሉ ለመናገር ቅንጣት ታህልስ እንኳን አንፈር፡
73🙏13👍5💯1🏆1

በእንተ ንስሐ በቅዱስ ኤፍሬም

እርሱ ለገበሬው ዝናብና ጠልን በነፃ ስለ ሰጠ ገበሬው ማረስና መዝራት ትቶ አይተኛም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ኃጢአተኞችን የሚያድን መድኃኒት (ንስሐ) በእጃችን ስላለ ለኃጢአት ሥርየት መለመንን አንተው፡፡ ዘወትር መጸለይንም አንስነፍ፡፡

አንድ ገበሬ ዘር ባይዘራ ዝናቡ መዝነቡ ምንም ጥቅም እንደማይሰጠው ሁሉ ኃጢአተኛም ስለ ኃጢአቱ ተጸጽቶ ምሕረትን ካልለመነ ንስሐም ካልገባ ንስሐ መኖሩ ብቻ አያድነውም። ይልቅስ እርሱ ‹‹ቊስላችሁን አሳዩኝ እኔም አድናችኋለሁ›› ይላልና እንለምነው ዘንድ ይገባል፡፡ ከዚያ በኋላ እርሱ በምሕረቱ ይጎበኘናል፤ በቸርነቱም ያድነናል፡፡

እንግዲህ በወዳጅነት መጸጸታችሁን ንገሩት፡፡ እርሱም ይቀበላችኋል፡፡ ‹‹ወደኔ ተመለሱ እኔም ወደእናንተ እመለሳለሁ›› ብሎ በነቢዩ ነግሮናልና፡፡ እንዲህ ልቡናችሁን ወደ ጸሎት መልሱ፤ ቸርነቱም ሊቀበላችሁ ወደ እናንተ ይመለከታል፡፡ በንስሓ መንገድ ተመላለሱ ያን ጊዜ ቸርነቱ ያበራላችኋል፡፡

ነገር ግን አንድ ቀን ተጸጽታችሁ በሌላ ቀን ደግሞ ኃጢአተኞች አትሁኑ፤ አንድ ቀን የኃጢአተኞች ተባባሪ ሌላ ቀን ደግሞ ተነሳሒ አትሁኑ፡፡ ለቅሶአቸሁና ጸጸታችሁ አንድ ቀን ብቻ አይሁን፡፡ አንድ ቀን ‹‹በድያለሁ፣ ወድቄአለሁ› ብላችሁ ሌላ ቀን ደግሞ ‹‹ነገ እንሞታለንና ዛሬ እንብላ እንጠጣም›› አትበሉ፡፡

ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ እንጂ ሁል ጊዜ በጥፋት መንገድ አትመላለሱ፤ ሞት ሳታስቡት በድንገት ይመጣባችኋልና፡፡ የሥጋ ምቾትም ንስሓን አይፈልግምና ለጥፋት ይዳርጋል፡፡

የመጨረሻው ቀን መጥቶ ሳያገኘን በንስሓ መንገድ እንመላለስ፡፡ የማይቀረው ሞት ሲመጣ ሁለተኛው ሞት እንዳያገኘን በቅድስና ሆነን እንጠብቅ፡፡ በሃይማኖት መጽናትም የድካማችንን ፍሬ እናግኝ። በዚህች ዓለም መልካሙን ሥራ ሠርተው ካለፉ ቅዱሳን ጋር የክብር አክሊል እንቀዳጅ ዘንድ፡፡ ሰው ታይቶ የሚጠፋውን የዚህን ዓለም አክሊል ለመቀዳጀት በወታደር እና በሠረገላ ጦርነት ይከፍታሉ፤ ጊዜአዊ የሆነ የዚህን ዓለም ደስታና ሐዘን ለመቅመስ ነው፡፡

ይቀጥላል....

(ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ - በእንተ ንስሐ በዲያቆን መዝገቡ የተተረጎመ - ገጽ 31-34)
47🙏29💯2

በእንተ ንስሐ በቅዱስ ኤፍሬም

እንግዲህ የዚህን ዓለም ዘውድ ለመቀዳጀት ሩጫው ይህን ያህል ከሆነ ዘላለማዊውን ክብር፣ ሰማያዊውን አክሊል ለመቀዳጀት ውድድሩ ምንኛ ታላቅ ይሆን? ስለዚህ ሐዋርያው ‹‹የሚታገል ሁሉ በሁሉ ነገር ይታገሣል፤ እነርሱስ የሚጠፋውንና የሚያልፈውን አክሊል ያገኙ ዘንድ ይበረታሉ፤ እኛ ግን የማያልፈውን አክሊል ለማግኘት እንታገሣለን›› (1ቆሮ. 9፥25-26) አለን፡፡

እንግዲህ እርጉም በሆነው ጠላታችን ላይ ድል እስክናገኝ ድረስ ከተንኮል ሥራውም እስክናመልጥ ድረስ የተጋድሎአችንን መሣርያ ንጽሕና ማድረግ ይገባናል፡፡ ክፉ የሆነው ጠላታችን እኛ ትኁታን ስንሆን ይቀናብናልና ይዋጋናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ከጠላት ቀስት የምንድንበት የበለሳን መድኃኒት ሰጠን፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር ያስተማረን የንስሓ መድኃኒት ነው፡፡

በእውነት ለቀረበ፣ ከልቡም ተጸጽቶ ለተመለሰ ይህ መድኃኒት ፍጹም የሚያድን ነው፡፡ ነገር ግን መድኃኒቱ የተሰረቀ በደል ያለበትን ገንዘብ በእጃቸው ይዘው፣ የረከሰ ሰውነታቸውን እየወደዱ በአፋቸው ብቻ ‹‹አድነን›› ለሚሉት አይደለም፡፡

ዳግመኛ በቀደመ ርኵሰታቸው የሚወቀሱትን የወቀሳ ድምፅ ስሙ፡፡ እንደዚሁም በመተላለፋቸው እራሳቸውን እየወቀሱ ዳግመኛ ወደ ጥፋት እንዳይመለሱ የሚጠነቀቁትን ስሙ፤ በግብርም እነርሱን ምሰሉ፡፡ ሕሊናን ሁሉ ወደሚመረምረው ወደ እርሱ ሁለት ልብ ሆናችሁ አትቅረቡ፡፡ የተሰወረውን ሁሉ ያውቃልና በሁለት መንገድ አትመላለሱ፡፡

እንግዲህ ንስሓ ለመግባት ፍጠኑ እንጂ ወደ አረንቋ አትመለሱ፡፡ በቸርነቱ ፍቅር ታጥባችሁ ንጹሐን ሁኑ እንጂ ዕዳችሁ ከተሰረዘላችሁ በኋላ ገንዘቡ እንደ ወደመበት ሰው ዳግመኛ ወደ ዕዳ አትግቡ፡፡

ከምርኮ የተለቀቀ ሰው በምንም መልኩ ዳግመኛ መማረክ፣ ወደ ምርኮው ቦታ ተመልሶ መሔድ አይፈልግም፡፡ ወይም ከግዞት ሥቃይ ከወጣ በኋላ ዳግመኛ መገዛት አይፈልግም፡፡ ነገር ግን ዳግመኛ ወደ ግዞት እንዳይገባ ይጸልያል፡፡ እንግዲህ እናንተም ከገዳይ ቀንበር ከወጣችሁ በኋላ ዳግመኛ እንዳትገዙ ጸልዩ፤ በጥልፍልፉ ወጥመድም እንዳትያዙ ትጉ፡፡

(ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ - በእንተ ንስሐ በዲያቆን መዝገቡ የተተረጎመ - ገጽ 31-34)
72🙏12👍6
2025/10/20 09:48:28
Back to Top
HTML Embed Code: