Forwarded from የኪዳን ልጅ
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

#እምነት_እግዚአብሔር የምፈልገውን ያደርጋል ብሎ #ማመን አይደለም። #እምነት_እግዚአብሔር ትክክል የሆነውን ያደርጋል ብሎ #ማመን ነው።
     
     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

#ማክስ_ሉካዶ
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

ስትሞት መቃብርህ ላይ ለረጅም ጊዜ የሚመላለሰው ማን ይመስልሃል

ስሙን የምትጠራው ሰው ካለ ማመን ከሚገባህ በላይ ታምነዋለህ ማለት ነው❗️

የምትጠራው ምንም ሰው ከሌለህ ደግሞ አንተ የምታምነው ሰው የሌለህ ብቸኛ ሰው ነህ ማለት ነው❗️

     
     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

#ማሰብ_የማንፈልገው
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

"በህይወታችሁ ለመለወጥ ስትወስኑ ብዙ ቻው የምትሏቸው ሰዎች አሉና ተዘጋጁበት"
     
     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Hiskelboy
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

ይቺህ አለም መኖር እየናፈቁ በሚሞቱ ፥ መሞት እየናፈቁ በሚኖሩ ሰዎችም የተሞላች ናት❗️

ደግሞም ይቺህ አለም.....

የሚኖሩለት ነገር ያላቸው በሞት የተቀደሙ ፥ የሚኖሩለት ነገር በጠፋባቸው በእድሜ የተንበሸበሹ ሰዎችም ይኖሩባታል❗️

ይቺህ አለም የተሸከመችው ይህ ብቻ መሰለህ .....

ይቅር ማለት በተሳናቸው በደለኞች ፥
መልካምነት በጎደላቸው ክፉዎች ፥
ቅንነት ባጡ ጠማሞች ፥
የሰው ስኬት በሚጠሉ ቀናተኞች ፥
የሰው ሳቅ በሚያስጨንቃቸው ገዳዮችም የተሞላች ዓለም ናት❗️


ይቺ አለም እነዚህም አሏት.....

የሰው ደስታ በሚናፍቁ ቅኖች
የሰው ሰላም በሚሹ ትሁቶች
የሰው ስኬት በሚወዱ ሩሩሆች
የሰው ሙላት በሚያስደስታቸው አፍቃሪዎች
የሰው ተድላ በሚያረካቸው አማኞች
የሰው ከፍታ በሚያዩ ተስፈኞችም የተሞላች ዓለም ናት❗️

አንተስ እራስህን ከየትኞቹ  ጎራ ትመድባለህ
     
     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Hiskelboy
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

ለምን ብለን ብንጠይቅ እንኳን መልስ የማናገኝላቸው የህይወት ሚስጥሮች አሉን❗️

ምክኒያታቸው ሳይገባን  የምናልፍባቸው አስቸጋሪ የህይወት ጎዳናዎች አሉን❗️

ከህሊናችን ጋር እየታገልን የምንሆናቸው ብዙ ነገሮች አሉን❗️

ያለምናቸው ትልልቅ ህልሞች ፥ ያሰብናቸው ትልልቅ አሳቦች ፥ አርቀን ያየናቸው ትልልቅ አላማዎች ፥ ጊዜ ወስነን ልናሳካ ያቀድናቸው አስደሳች እቅዶች ፥ የህይወታችንን መንገድ ይቀይሩ ይሆን ብለን የናፈቅናቸው አጓጊ እድሎች ፥ በክብር ከፍታ በተራራው ጫፍ ላይ ለመቆም የወጠናቸው ብሩህ ተስፋዎች

ጥርሳችንን ነክሰን የተፋለምናቸው ክፉ ጭለማዎች ፥ ወገባችንን አስረን የታገልናቸው ተስፋ አስቆራጭ ትግሎች ፥ በህይወት እንዳንቀጥል የሚያደርጉን እልህ አስጨራሽ የህይወት ምዕራፎች ፥

እንዳንናገር አፋችንን የያዙ ፥ እንዳናይ አይናችንን የሸፈኑ ፥ እንዳንሮጥ እግራችንን ያሰሩ ፥ እንዳናምን ልባችንን ያራዱ  ፥ የህይወት ውጣ ውረዶች ፥

አልቅሰን እንዳይወጣልን ፥
አዝነን እንዳንጽናና ፥
ጮህን እንዳናርፍ ፥
ስቀን እንዳንደሰት ፥

ብቻ ሁላችንም ዘርዝረን ብንናገራቸው ቃላት በማይገልጣቸው በህይወት እንቆቅልሾች የተሞላን ፍጥረት ነን❗️

እንዲህም ቢሆን እውነታው የሰው ሰሪው ፈጣሪው #እግዚአብሔር ሲሰራው ሰው በልብ መኖር የሚናፍቅ ፥ ነገን ለማየት እንዲጓጓ ፣ በድካሙ ደስ እንዲለው ፥ በተስፋና በእምነት እንዲሁም በፍቅር ፥ ነፍስና መንፈሱን ስጋውንም ጭምር  አዋህዶ ነው❗️

ምንም ይሁን ምን በህይወት መኖር ካለመኖር እጅግ የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ❗️

     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Hiskelboy
Channel @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

"ህልማችንን ለማሳካት አንዳንድ ጊዜ ብርቱ የሆኑ ፍላጎቶቻችንን ጭምር መስዋዕት ማድረግ ይኖርብናል።"
     
     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Hiskelboy
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

አንዳንድ ሰዎች በራሳቸው የአሳብ አለም እስርቤት ውስጥ ይኖራሉ።

ሌላን አሳብ ለመቀበልም ሆነ ለማስተናገድ የልቦቻቸውን በሮች ይዘጋሉ።

አለም በእነርሱ የአስተሳሰብ ምዕዋር ስር ብቻ እንደምትዞር ያምናሉ።

አሁን ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር መታረቅ ይሳናቸዋል።

አሁን ያሉበትን ሁኔታ እንደ ድል ይቆጥራሉ እንጂ ፈጽሞ በእነርሱ ስህተት የሆነ ምንም ነገር እንደሌለ ያስባሉ።

እራሳቸውን በሙገሳ ካቦ ሲሞሽሩ ይውላሉ እንጂ ሌሎችን ፈጽመው ለማመስገን ብቁ አይደሉም።

እውር አይናማዎች ፥ ዲዳ ተናጋሪዎች ፥ ደንቆሮ ሰሚዎች ፥ ሽባ እሯጮች ፥ ለጋሽ ነፋጊዎች ናቸው።

ይናገራሉ እንጂ አይሰሙም ፥ እንድታደርግ ያዙሃል እንጂ አድርገው አያሳዩህም።

እነዚህ ሰዎች በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ከኛ ጋር የጠበቀ የህይወት ትስስር አላቸው❗️

     
     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Hiskelboy
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

እንግዳ ነገሮች በህይወትህ መሆን የሚጀምሩት ባልጠበከው ጊዜ ነው።

የጠበካቸው ነገሮች መሆን ያቆሙና ያልጠበካቸው ነገሮች መሆን ይጀምራሉ።

የህይወትን መልክ አስደናቂ ከሚያደርጓት ነገሮች መካከል የምትሆነውን እንድትሆን ምርጫው ያንተ አለመሆኑ እና ባልመረጥካቸው ነገሮች አንኳን ቢሆን አንተነትህን ሆነህ መቀጠል እንድትችል የምርጫው ባለቤት ግን አንተ መሆንህ ነው።

የምናልፍባቸው እና ያሳለፍናቸው ነገሮች ሁሉ ሚስጥር ይገቡናል ማለት አይደለም። ነገር ግን ጥቂቱ ከገባን የመኖር ምክኒያት እናገኛለን❗️

የመኖር ምክኒያት ያገኘ ሰው የመሞት ምክኒያት ካገኘ ሰው ይልቅ ወደፊት አንድ እርምጃ መራመድ ይቻለዋል❗️

     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Hiskelboy
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

ህይወት እጅግ በሚያስደስቱ ነገሮች የተሞላች ብትሆንም ፥ በውድቀትና በጉድለት የታጀበች ፥ የፍጹምነትን ካባ እንድናወልቅ በሚያስገድድ ፥ በእውነተኛ ውጣውረድ ማዕበል የምትናጥ በታላቁ ውቅያኖስ የምትጓዝን መርከብ ትመስላለች።

     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Hiskelboy
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

መዝሙር 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፤ ልጆቻቸው ብዙ ናቸው የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
¹⁵ እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።
     

     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Hiskelboy
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

       #አራቱ_ስህተቶቻችን

1 •  መናገር በሚገባን ጊዜና ሁኔታ ላይ ዝም ማለታችን፣ ዝም ማለት በሚገባን ጊዜና ሁኔታ ላይ መናገራችን!!! 

2 •  የማይፈልጉንንና የማይጠቅሙንን ሰዎች መከታተላችን፣ የሚፈልጉንንና የሚጠቅሙንን ሰዎች ችላ ማለታችን!!! 
   
3 •  አጥብቀን መያዝ ያለብንን ነገር በቀላሉ መልቀቃችን፣ በቶሎ መልቀቅ የሚገባንን ነገር ደግሞ አጥብቀን መያዛችን!!!

4 •  ሰርተን ማግኘት የሚገባንን ነገር በነጻ መጠበቃችን፣ በነጻ የተሰጠንን ነገር ሰርተን አለማሳደጋችን!!!

     

     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

#መለሰ_መንገሻ_ማሞ
Channel @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
Forwarded from Christsbelievers (🇭 🇮 🇸 🇰 🇪 🇱)
. #አእምሮን_ማንቃት
👇

ብዙ ጊዜ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ነገሮች ቅድሚያ መስጠትን ዘንግተን ፤ ቅድሚያ ለማይሰጣቸው ነገሮች ቅድሚ ስንሰጥ እንገኛለን።

በዚህ ምክኒያት ህይወት ምስቅልቅሏ ወጥቶ ፥ የመኖራችን ትርጉም ጠፍቶብን ፥ በብዙ መከራ መካከል ፥ ለመኖርና ፥ ነገን ጨልሞ ማየት እስኪሳነን ድረስ በሐዘን ተውጠን ፥ የምንኖር ብዙዎች ነን።

ከሁሉም በላይ በዚህ ምድር ላይ በህይወት መኖር ትልቁ ነገር ሆኖ ሳለ ፤ እኛ ግን የሚያስጨንቀን በምን አይነት ሀገር እና ቤት ውስጥ እየኖርን እንዳለን ነው።

ከሁሉ በፊት በምድር ላይ ለመኖር ትልቁ ነገር የሚጠጣ ውሀ ሆኖ ሳለ ፤ እኛን የሚያስጨንቀን ትልቅ የተባለ መዝናኛ ገብተን ዋና አለመዋኘታችን እና ሙቅና ቀዝቃዛ የሚያደርግ ሻዎር ቤት አለመስራታችን ነው።

ከሁሉ በፊት በዚህ ምድር ላይ ለመኖር ምግብ መመገብ ሆኖ ሳለ ፤ እኛን የሚያስጨንቀን በአለማችን የሚወደዱ ፥ ጣፋጭ እና ውድ የሆኑ ምግቦችን መመገብ መቼ እንደምንጀምር ነው።

ከሁሉ በላይ በምድር ላይ ለመኖር የሚያስፈልገን ልብስ ሆኖ ሳለ ፤ እኛን የሚያስጨንቀን በየወቅቱ የሚመረቱ ፋሽን የሆኑ ልብሶችን እየቀያየርን መልበስ ነው።

ከሁሉ በላይ ወደምድር ስትመጣ የተፈጠርህለት አላማ ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነህ ፥ የእግዚያብሔር ልጅ ሆነህ ፥ ዳግም በመወለድ የመንግስቱ ወራሽ መሆን ሳለ ፤ በየትኛው አገር እንደተወለድክ ፥ የማንኛው ብሔር እንደሆንክ ፥ የብሔርህ ቋንቋ መቼ ከሌሎች በላይ እንደሚሆን ፥ ሌሎቹ ሲፈናቀሉ እና ሲሞቱ ፥ ዘሬ የምትላቸው ሲገሉና ሲያፈናቅሉ ማየት ነው የሚያስጨንቅህ።

ከሁሉ በላይ ወደምድር ስትመጣ ራቁትህን ነበርክ ፥ ይቺን ምድር ስትለይ እራቁትህን እንደምትሄድ እወቅ።

@Hiskelboy
Channel @christsbelievers
2025/06/27 03:24:32
Back to Top
HTML Embed Code: