Telegram Web Link
Unfinished thoughts...
Forwarded from Tuyaaa
ወንድማችንን እናሳክም🙏

ደግነት ዳንኤል ባሳ ይባላል፤ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 5ኛ ዓመት (Clinical ll) የሕክምና ተማሪ ነው። ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት  ባጋጠመዉ የአንገት አከባቢ ህብለ ሰረሰር እጢ በሽታ (C2 –C3 intramedullary spinal cord tumor) ክፉኛ እየታመመ ይገኛል፤ ለዚህም በአስቸኳይ ሕክምናን የማያገኝ ከሆነ በሽታዉ የመተንፈሻ ጡንቻዎችን በመጉዳት ሕይወቱን አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ ሕክምናዉም ሀገር ዉስጥ ስለሌለ በአስቸኳይ ወደ ዉጪ ሀገር ሄዶ እንድታከም  የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ እና ኮምብርሄንሲቨ ሆስፒታል ሕክምና ቦርድ የወሰነ ሲሆን ለዚህም ብያንስ 1.5 ሚሊዬን ብር እንደሚያስፈልገዉ ተነግሮታል፡፡ ይህም ከቤተሰቡ አቅም በላይ ስለሆነ ሁላችውም የአቅማችሁን ትብብር እንድታደርጉ ይጠይቃል።

ለትብብራቹ እናመሰግናለን።
CBE
1000205065478
Deginet Daniel Bassa

Dashen Bank
5049110500011
Deginet Daniel Bassa

+251949613179 ደግነት ዳንኤል

በተጨማሪ
0941047406 ሳምሶን መስቀሌ
0904761931 ናፓሊዮን ፈ/ሥላሴ
0909896878 ዘሪሁን ዛና
0965497319 ተሻገር ብርሃኑ
0916280514 ሙሴ ደምሴ
0924654040 ኢማን ወለላ
0961530200 የሺወርቅ ሀይሉ
እኩለሌሊት የማያቆማቸው ዟሪ እግሮቹ፣ ፀሐይ ሳትጠልቅ ጅማወርቅ (ሚስቱ) ረከቦት ዙሪያ መሰብሰብ ጀመሩ።
(የስንብት ቀለማት)
I love these days. The sun rises early and sets late. And I feel like everyone is patient with me.
And there are few people who make you say this but this is so true. To love a person is to be acutely aware of time and place’s chains. Especially time. Oh time!
@coffeeandscribblings
ደግሞ ይሄ ዘፈን አለ። ደስ ደስ ይበልሽ፣ ፈገግ በይ፣ ሳቅ ሳቅ በይ፣ አይ ሰዎቹ እያዩ ትከሻሽ ይቅር የሚል የመሰለ።

ሰይ።

ሰይ።

ቢለኝ ሰው የማልወጣው ተራራ ይኖራል ወይ።

ይሄ ዘፈን እና edith piaf በተደበረ ድምጿ heureux heureux heureux ስትል ደስስስስስስስ ይለኛል።
መሞት በጣም ይገርማል። ብሞት ለራሴ በጣም አዝናለሁ። መኖር ከባድ ነው። መሞት ግን ቀላል ነው። እንደቀልድ በአንድ የሚሆን ነገር ነው። አስበው ይሄን ሁሉ አመት ስኖር ቆይቼ ብሞት። ስበላ፣ ስጠጣ፣ ሳነብ፣ ስማር፣ ስጽፍ፣ ስወድ፣ ስጠላ፣ ሳስብ፣ ስጸልይ፣ ስጨነቅ ቆይቼ death on arrival ብሆን።

አሁን እዚህ አጠገቤ የተቀመጠው ፖሊስ ጠብመንጃው ቢባርቅበት እና transection of the great vessel ምናምን በሚል ሰበብ አስባብ ብሞትስ።

ጭንቅላቴን የሞላው ሁሉ ሲፈስ። በልቤ የያዝኹት ያሰብኹት ሁሉ ማንም ሳያውቅልኝ።

ኪሲርት ትላለች አንዲት ጓደኛዬ። ኪሲርት። ሌላው ቢቀር የቅድሙ ቡና ከሰረ ማለት አይደለም? በጀበናው ፈልሰስ ማለት ሲችል?
@coffeeandscribblings
I want to be a person who gives out candies. <<Hey you look a little down here is candy for you. It is even heart shaped and tastes like mangoes>>.

And I know candies are not good for your teeth and all that health related things... but it makes people smile. A different kind of smile. And it makes the world a little just for a fraction of a second better.
@coffeeandscribblings
ኧረ ተይ አንቺ ልጅ ያዝ ያዝ ጠበቅ አድርጊኝ ይላል በጠዋት።

ሳሙናን ያዝ ሊያደርጉት ይችላሉ? ቅርጸ ቢስስ ጠበቅ ይደረጋል?
@coffeeandscribblings
New writing ☝️☝️
ሰው ማመን ምኑ ይከብዳል? መታወቂያ አለው። መታወቂያ ባይኖረው መልክ አለው። እናውቀዋለን የሚሉ አንድም ሁለትም ሰዎች አይጠፉም።

ከባዱ ቁምነገር፣ ህይወትን ማመን ነው። በዚህ አለፈች የሚልህ በሌለበት። አይ እሷ ልማዷ ነው ደግሞ ትመጣለች የሚልህ በሌለበት።

አሁን ለእኔ ከመቀመጫው ተነስቶ የሚያጨበጭብ አዳራሽ ሙሉ ህዝብ አይገባኝም ወይ? በዚህች አጭር እድሜ፣ ይህችን ህይወት የምትባል መታወቂያ የሌላት፣ መልክ የሌላት፣ ምስክር የሌላትን ነገር ደግሜ ደግሜ ሳምን?
@coffeeandscribblings
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
https://youtu.be/lWengrlMpok


This is not just acting. It sends something down my spine. I know I have shared it before but here it is again
ጭንቀት ቁልቁለት እንደመንደርደር ነው። መቆሚያ የሌለው። ዲዲዲዲዲዲዲ ወደታች። ኧረ አቁሙኝ! ኧረ መልሱኝ! እያሉ። አይመልሱህም። አይቆምም እንዴ ምን አባቱ ይሉኃል። ሄደህ ሄደህ ከአንዱ ተላትመህ ትቆማለህ። የምትቆም ባይመስልህ አትደንግጥ። ትቆማለህ። ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች አትሁን። አጆኻ።
@coffeeandscribblings
የሚያውቀኝ የስንብት ቀለማትን ያላነበብኹበት ጊዜ እንዳልነበር ያውቃል። ሁሌ የስንብት ቀለማትን እያነበብኹ ነው። ሰዎች ጨርሰው ሲወያዩበት ሳይ ይገርመኛል። እኔ ስጀምረው፣ ከዛ ሳልጨርሰው አንድ ነገር ሲፈጠር፣ ያን የሚያህል መጽሐፍ ተሸክሜ መዞር ስለማልችል ወይ ፎቶ እያነሳሁ ልውሰድ እንዴ ስል.. ስተወው... ደግሞ ድጋሚ ስጀምረው... የተኮላን፣ የጅማ ወርቅና የቤላን ታሪክ ልሸመድደው ምን ቀረኝ? ደግሞ ደግሞ በመጀመር።

ብቻ... የስንብት ቀለማት ላይ የሚጠቀስ ስዕል ነው ይሄ።

Death and the maiden by Schiole.

እና ሳየው አያምርም?

እና ስለዚህ መጻፍ ነበር አልኹ። ሞትን እንደፍቅረኛዋ የምትጠመጠምበት ወጣት ሴት ምን ሆና ነው?

ከዛ ለካ ጽፌያለሁ። እነኚህ ሞትና አለሚቱ አይደሉም ወይ?
@coffeeandscribblings
(ከማህደር)

የፊትህ ላይ ፈገግታ በልቤ ፋሲካ ነው ትላለች ዘፋኟ። (የውርስ ትርጉም)
ይገርመኛል። አፌን እያንሸራፈፍሁ ከማዳምጠው ውጪ ልቤ ላይ የሚያስፈስከኝ ባለመኖሩ። @amadonart የሰውለሰው ድራማን ድሮ እንደጠበቃችሁት የምትጠብቁት ነገር አለን ይላል?

የሚያስፈስከኝን እጠብቃለሁ። የኔ ሁዳዴ መቼ ነው የሚያልቀው?
@coffeeandscribblings
2025/07/05 06:29:17
Back to Top
HTML Embed Code: