Telegram Web Link
You may now leave your thoughts and comments @lozacas
Coffee and Scribblings pinned «You may now leave your thoughts and comments @lozacas»
በእንዲህ ያሉ ቀናት ብትከፍተኝ አንጀቴ የጠቆረ ይመስለኛል። ተቆርጦ የሚጣል ያለው።

በእንዲህ ያሉ ቀናት ጨለማ ውስጥ ተቀምጦ መብራት እንደሚጠብቅ ሰው ነኝ።

በእንዲህ ያሉ ቀናት እንደነፍሰጡር ነኝ። እስኪገላግሏት እንደምትጠብቅ።

በእንዲህ ያሉ ቀናት የከበዱ ነገሮች አሉ። እንደሚያልፉ ግን አውቃለሁ።

@coffeeandscribblings
Coffee and Scribblings is interested in conducting interviews for creative purposes, without disclosing any names, and using a standardized set of questions. If interested DM @lozacas
የበላኹበትን ወጭት ላለመስበር...

ብዙ ጊዜ በመመገቢያ ሰዐቶች በተለይ ምሳ ሰዐት የመቀመጫ ቦታ የለም። የራት ሰዐት እንኳን የተለጠጠ እና መጀመሪያ እና መጨረሻው የማይታወቅ ነው። እኔ ኮሌጅ በነበርኹበት ጊዜ ከቀኑ 11 ሰዐት እስከ ምሽቱ 5 ሰዐት ድረስ ነበር የራት ሰዐት። ምሳ ሰዐት ግን ከ6-8 ብቻ ነው።

እና መቀመጫ የለም።

ተማሪም፣ ሀኪምም፣ ነርስም፣ ታካሚም፣ አስታማሚም ይመጣባቸዋል እነዚህን ቤቶች። እነዚህን ማዘር ቤቶች። እኛ ማዘር ቤት ብለናቸው አናውቅም። በከተማዋ ግን እንዲያ ነው የሚጠሩት አሉ። ዋጋቸው አነስተኛ ሆኖ፣ ምግቦቻቸው ጣፋጭ ስለሆኑ ይሆናል። በሸራ የተሸፈኑ ቤቶች ናቸው።

ትናንሽ ቤቶች ናቸው። በቃ ትናንሽ። እየተሰናሰሉ ተደርድረዋል። ሰማያዊ ወይ ብርቱካናማ ሸራ ለብሰዋል። የላስቲክ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች ተደርድረውባቸዋል። ከሁሉም ፊት ለፊት የሚታየው ትላልቅ ረከቦት ነው።

በብዛት የምንጠራቸው በሚያስተናግዱት ልጆች ነው።  አንዳንዴ በምግብ ሰሪዎቹ። ሳቤላ። ሚሚ። መስቀሌ። ፋናዬ። ባርች። ኤፍራታ። በቃ በሴቶች ስም ከላይ እስከታች ተደርድረው።

የማይሸጡት ምግብ የለም። ዱለት። (ዱለት አይደለም ግን በቃ ደቅቆ የተከተፈ የበሬ ስጋ ነው።) በየአይነት። ፓስታ በአትክልት ወይ በስጎ ወይ በስጋ። (መኮረኒ የለም። መኮረኒ ለምን የተገፋ ምግብ ሆነ? ዮናስ የሰነፍ ምግብ ይመስለኛል ይላል። ጠቅ ጠቅ ስለሚደረግ። እንደፓስታ ጠቅልሉኝ አይልም።) ፍርፍር በቀይ ወይም በአልጫ ወይ በስጋ። ቲማቲም ለብለብ። ቲማቲም ስልስ። እንቁላል ብትፈልግ ሳንድዊች ብትፈልግ ፍርፍር ብትፈልግ ስልስ። (ስወድ እንቁላል ስልስ ስወድ።) ሽሮ ፈሰስ። ተጋቢኖ።
ደግሞ እርጥብ። እርጥብ ሁሉም ጣዕሙ የተለያየ ይሰራሉ። ሀሳቡ አንድ ሆኖ። ሁሉ የሳቤላን ይወዳል። እኔ ግን የሳቤላ እርጥብ አይገባኝም።

ዝም ብሎ እህል ውሃ የማይል ምግብ እንዳይመስልህ። ቆንጆ ምግብ በቃ። የሚጣፍጥ። አሁን የናፈቀኝ።

አሁን እዚህ ቁጭ ብዬ ነገሩን እንዴት እንደሚያስኼዱት ይገርመኛል። በስልክ ትዕዛዝ ይቀበላሉ። አዘህ መጥተህ በፌስታል አንጠልጥለህ መሄድ። (ከፌስታል እንበላ ነበር። አቤት እናቴ ይህን ብታይ ምን ትላለች እላለሁ አንዳንዴ።) አዘህ ደግሞ ቁጭ ብለህ መብላት። ከደወልህ ቶሎ ይደርሳል ምግብህ። አንዳንዴ አይደርስም። ግን መከራከርያ ነጥብ አለህ። ደውዬ ነበር እኮ። ደግሞ መጥቶ አዝዞ መጠበቅ።

የሚያደንቃቸው የለም። ከጠዋት እስከማታ ነው የሚሰሩት። ከስር ከስር እቃ ማጠቡ፣ ምግቡን መስራቱ፣ ትዕዛዝ መቀበሉ፣ የሰውን ንጭንጭ ማስተናገዱ። ሁሌ ንጭንጭ አለ። አረፈድሽብኝ። ቀድሜ ነው ያዘዝኹት ምናምን።

ከጠዋት 1:30 አካባቢ ነው የሚጀምሩት መስራት እስከ 4 ሰዐት ማታ አሉ። ሴቶች በቃ። ምድጃ ላይ አጎንብሰው፤ ከስንቱ እየተነታረኩ፤ መዐት ትዕዛዝ እየተቀበሉ።

ደግሞ ቡናና ሻይ በተጨማሪ ስፕሪስ ያቀርባሉ። የተለየ ለማድረግ የሚሞካክሩት ነገር አይጠፋም። ሁሉም ሌላው የማይሰራው አንድ የተለየ ነገር አላቸው። አንዷ ምስር ትሰራለች። በቃ ምስር እና ሰላጣ። ሌላዋም ሌላ።

ግብግብ ነው የያዙት ከኑሮ ጋር። ልንጨርስ ሰሞን የከተማ አስተዳደር ሸራዎቻቸውን ሁሉ አነሳባቸው። መች እጅ ይሰጣሉ? ግቢያቸው ውስጥ በረንዳቸው ላይ ሳሎናቸው ድረስ ሰው ያስተናግዳሉ።

በጣም ጀግኖች ናቸው። መልሼ ሳስባቸው ስላገኘኋቸው እኮራለሁ። የትም ብሄድ ባልረሳቸው እመርጣለሁ። ጠንካራ ሰዎች ናቸው። ትላልቅ ምግብ ቤቶች ቢኖሯቸው በቃ ከተማዋን ይወዘውዟታል እነዚህ። ደግሞ አንደኛዋ የትምህርት ቤት ዩኒፎም ለብሳ አየኋት። በቃ በጣም ገረመኝ። ህክምና ስማር የተማርኹት የሰውን መንፈስ ጥንካሬ ነው። በጣም ጠንካራ ነው በቃ። ይገርማል።

@coffeeandscribblings
ስለ ልጆች መናገር አልችልም። በጣም የሚከብደኝ ዲፓርትመንት የህጻናት ህክምና ነበር። በልጆች ጉዳይ ደካማ ነኝ የምር። አንጀቴ ክፉኛ ይላወሳል። ያየናቸውን ነገሮች Harry Potter ላይ Dumbledore ከጭንቅላቱ ትዝታ እየጎተተ እንደሚያወጣው ላወጣቸው እወዳለሁ።

ህጻናት የተለዩ ፍጡራን ናቸው። የሰው ፍጡር አይመስሉኝም። ህጻን ብዙ ሳዋራ፣ ጸልይልኝ ያመልጠኛል።

እና መልካም ነገር ሁሉ ብታደርግላቸው ያንስባቸዋል። ጫፋቸው ላይ አይደርስም።

ታካች አለም፣ ከላይ ታች በጦርነት ስትታረስ እነዚህን ደካማ ፍጡራን ማሰብ ግድ ይላል። በማይገባቸው እና በማያገባቸው ነገር ይቸገራሉ፣ ልጆችዬ። ይራባሉ። ይጠማሉ። ይታመማሉ። ይፈራሉ። ይቆስላሉ። የሚጠብቃቸው ያጣሉ።

ያየኹትን አይቻለሁ።

ስለጦርነት ዜና ስትሰሙ፣ በየትም ቦታ... በማንኛውም ጊዜ... በምንም ሁኔታ... እነዚህን ንጹኃን በጎች እያሰባችኹ ተቃወሙ።

እና ይህን ፊልም እዩት።

በጦርነት ዙሪያ የሚሰሩ የጥበብ ስራዎች ታላቁ ምጸታቸው ፊታችንን ስናዞር ወደ ሰላም ማዞራችን ነው።

Ah quelle l'art.

ብለህ ማኪያቶህን ትጠጣለህ። ይህን ፊልም አይቼ ምናምን ትላለህ።

ጥፋተኝነት ስለተሰማኝ ነው። በሀገሬም በሌላም ቦታ ሁሉ በጦርነት ስለሚገኙ ህጻናት።

@coffeeandscribblings
Someone in here asked for book recommendations. Here are some books which revolutionized the way I saw things and life.

- To kill a mocking bird (Harper Lee)
- Crime and punishment (Fyodor Dostoyevsky)
- The fall (Albert Camus)
- Tower in the sky (ማማ በሰማይ) (ህይወት ተፈራ)
- ትኩሳት (ስብሐት ገብረእግዚአብሔር)
- The happiest man on earth (Eddie Jaku)

Pic: New books
I owe the pleasure of knowing Albert Camus to a dear friend. (I owe many pleasures to friends actually).

'Albert Camus was awarded the Nobel Prize in Literature in 1957 for his significant contributions to literature, particularly for his influential works that explored the human condition and its moral and philosophical challenges'.

What a thing to say, right? Explored human condition and its moral and philosophical challenges?

Camus brought interesting ideas into our lives. He tried to answer few questions and asked many more.

It is indeed a pleasure to live in a time after Camus'. It is indeed a pleasure that he is born.

He said, 'To create is to live twice'. And he lives multiple lives in each one of us through his works.

My favorite script of his is in the plague. And I mention this quite often; he talked about maintaining faith in difficult times like a plague... it is an overwhelmingly good argument.

Ah... well... he is awesome.

Joyeux anniversaire à Albert Camus.

Et mon amie est ici et elle sait que je parle d'elle, merci mon ami.

@coffeeandscribblings
Forwarded from Zeraf Books
"ደስታንም እንደቆሎ ቅሜአለሁ።
ፍስሃ ደጋግማ የተባረከውን የቤቴን በር አንኳኩታለች።
ችግርም በፈንታው የተለያየ ክብደት ባለው ኮቴው ወጥቶብኛል፣ ወርዶብኛል።
በአዲስ አበባም ራስ ወዳድ ጎዳናዎች ላይ እስኪሳቅብኝ ቼ ቼ ብሎኛል።
አንዳንዴም የአለም ችሎታዋ መቆንጠጥ ብቻ እስኪመስለኝ ተቆንጥጫለሁ።
እንዲህ ሲሆን እንደ ጌታዬ 'ተፈፀመ' አላልኩም።
የተሳሳትኩትን አረምኩ።
ከአሳሳቾችም ራቅኩ።
ጥንካሬዬንም አየሁ።
ስህተት የማይፈፅም የሰው ልጅ የለም።
ዛሬ የለበስነው ንፁህ ነገር ከትላንት ወዲያ ቆሽሾ ትላንት የታጠበ ቢሆን እኮ ነው።
"ወእምሐበ ወረደ አንብዑ ነቅዓ ማይ ፀዓዳ--- ዕንባው ከፈሰሰበት ቦታ ፅሩ ውሐ
ወጣ" ይላል ገድለ ተክለሃይማኖት።
ታዲያ ቆሻሻው ወጥቶልን ነፍሳችን የምትፀዳው ሒስ ወይ ግለ ሒስ ስናደርግ ነው።
ከሁሉ ከሁሉ ግን እልሃለሁ
ራስን ማጠብ ይመረጣል።"
***
መረቅ
(አዳም ረታ)
እንደgoogle map:- in 300 metres turn right then in 100 metres turn left እያለ በህይወቴ የሚመራኝ ሰው እፈልጋለሁ።

@coffeeandscribblings
* የድሮ ካፌ ሽታ ያለው የድሮ ወንበሮች ያሉት ካፌ... የጠላኹት ዘፈን በሬዲዮ... ሳንቡሶች... ዛሬ ሳንቡሳ ይከተለኛል። በሬዲዮ ራሱ ስለሳንቡሳ ስሰማ ነው የመጣኹት። አልበላት። ችግር ካልመጣ ሳንቡሳ መብላት አልወድም። አዲስ ካፌ ውስጥ በገባሁ እና ሰው አፍጥጦ ባየኝ ቁጥር፣ የሰው ቦታ የያዝኹ እየመሰለኝ እሳቀቃለሁ።

* ጠዋት ደስ ይለኛል። ሰው ሁሉ ወደጉዳዩ ለመሄድ ሲጣደፍ በቃ። ዘው ዘው ዘው። ማኪያቶ ምናምን ልግት ልግት አድርገው ውልቅ።

*የማያውቁት ሰው ቀጥሮ መጠበቅ ደስ ይላል። ያኛው ሲያልፍ... እሱ ይሆን? ትልና በቃ ሙሉ ውይይት ታስባለህ። ደግሞ ከዚህኛውም። ደግሞ ከዚያኛውም።

* ደንበኞች ይመጡ እና የተለመደውን ይላሉ። የተለመደው ምንድን ነው ማለት ይቃጣኛል። አንዱ የተለመደው አለና አንድ ሊትር ውሃ ተሰጠው። እንዴ የውሃ የተለመደ አለ እንዴ እላለሁ።

* ቦንቦሊኖም አለ አሉ። ግን ያዘዘው ልጅ የራይድ ሹፌር ነው እና ተጠራ። በቃ ቅርብ ነው የማደርሰው መጣሁ ብሎ ሄደ። ቦንቦሊኖን እያሰቡ መንዳት ነው እንግዲህ።

* ሁሉም ይተዋወቃሉ። የሰው ጓዳ የገባሁ እየመሰለኝ ነው።

* የማላውቀው ቤት ሆኜ፣ ጉዳዬ ሳያልቅ ማኪያቶዬ ሲያልቅ ይጨንቀኛል። ምን ልሆነው ነው እንግዲህ እላለሁ። ሌላ ማኪያቶ አልል። ቦንቦሊኖ ልብላ እንዴ? ሀሀሀሀ። ምን በወጣኝ። አልወድም መሰለኝ።

* የምወደው ሰው፣ ቅብጥርጥሮሽሽ ይስፋ ይስፋፋ ምድርን ይሙላት ብሎ በመረቀኝ መሰረት በመቀባጠሬ ባህር ሰዎች እስኪወሰዱ ድረስ እቀባጥራለሁ።

@coffeeandscribblings
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትንሽ ተናግሮ ብዙ የሚያናግረኝ ጓደኛዬ፣ ካስባለኝ ነገሮች አንዱ፣
Man is a polygon but you don't know 'n' ነው።

ያስባለኝ የምለው፣ ዝም ብሎ ሲያዳምጠኝ የምላቸው ነገሮች ስለሚገርሙኝ ነው። ከእኔ ማሰብ ብቻ ሳይሆን ከእሱ ማዳመጥም የወጡ ናቸው። የሀሳቤ ፈታይ ነው። ፈትል ከጥጡ ብቻ ሳይሆን ከፈታይዋም እንዲወጣ።

ብቻ እንደዚያ ካልኹ በኋላ የሌላው ቢቀር የራሴን 'n' ልወቅ እላለሁ።

አልደርስበትም።

መዐት ነኝ። በየቀኑ የምትወልደኝ አለችን? ኋላ እንዴት በየቀኑ አዲስ ሆንሁ? ስለራሴ የማላውቀውን እያወቅኹ ነው ወይስ እንደአዲስ እየፈጠርኹ?

የዛሬ አመት ቀርቶ የዛሬ ሳምንት እንዴት ያለሁ ሰው ነበርኹ?

ከዛ ስለሌሎች አስባለሁ።

የሌላ ሰው ነፍስ ጨለማ ቦታ ነው ብሏል ዶስቶየቭስኪ።

የሌላ ሰው ነፍስ እንቆቅልሽ ነው። ጨለማ እና ጠመዝማዛ ነው። ያለበትም የሌለበትም አይታወቅም።

ሌላ ሰው፣ ነፍሳችን እስከሚወጣ ብንወደው እንኳን ሌላ ቋንቋ የሚነገርበት ሌላ አለም ነው።

እና ይደንቃል።

ሁላችን ሁሉም ነገር በውስጣችን ያለ አለሞች ነን።

ዛሬ ይሄን አሰብሁ።

ህዳር 12/16
@coffeeandscribblings
I would rather have cancer than a dishonest heart.
I heard in a poem today,

"When love leaves, tell her to leave the door open.
And say thanks for stopping by".


And it is all that I needed. For it is a blessing to be loved even for a day... even for a month...

@coffeeandscribblings
እኚህ ጋሼ ገብረክርስቶስ ደስታ ይከተሉኛል። እውነት። ጋሼ ሊነግሩኝ የፈለጉት ነገር አለ። በሬዲዮም፣ በቴሌቪዝንም፣ በማነበው መጽሀፍም ምንም ይመጣሉ። በቃ አንዴ ስዕል። አንዴ ግጥም። አንዴ ቃለመጠይቅ። አንዴ ፎቶ። ማን ያምነኛል? 😁 ግን እውነቴን ነው።
2025/06/30 19:26:59
Back to Top
HTML Embed Code: