Telegram Web Link
Forwarded from The Articulation Bureau (pap)
የዓለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን ዛሬ የካቲት 13/2014 (ፌብሯሪ 21/2022) ለሃያ ሁለተኛ ጊዜ ታሰቦ ይውላል። እ.ኤ.አ በ2000 ዓ.ም በዪኔስኮ ይሁን ባይነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረ ሲሆን፤ ይህ ቀን (ፊብሯሪ 21) የተመረጠበት ምክንያት የ1956 ዓ.ም በዳካ ከተማ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን (ማትሪብሃሳ) ለማስጠበቅ ለተሰዉት ሰዎች ማስታወሻ ይሆን ዘንድ ነው። ቀኑ በዓለም በሁሉም ጥግ የሚነገሩ ቋንቋዎችን ቅድስና ለማክበር እና ለማቆየት እንዳለብን ለማስታወስ ይውላል።

እያንዳንዱ ቋንቋ የየራሱ የሆነ የተናጋሪዎቹን ነገሮችን የመግለፅ መንገድ እና አስተሳሰብ የመቅረፅ ኃላፊነትን ይዞ የባህል ልዩነቶችን (cultural nuances)፣ የእሴት፣ የአኗኗር እና የማንነት መግለጫ ሆኖ ያገለግላል። ከማሰብ ጀምሮ የተወሳሰቡ ሃሳቦችን እንድንገልፅ የሚያስችሉንን የምንናገራቸውን ሁሉንም ቋንቋዎች (በተለይ ደግሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋችንን) ጠብቀን ብቻ ሳይሆን እያሳደግን ማቆየት ይገባናል። መልካም የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን!

The Articulation Bureau
Random dude sitting on my usual place at my usual cafe doing what I do. 😒

😒

That could be me
Coffee and Scribblings
Random dude sitting on my usual place at my usual cafe doing what I do. 😒 😒 That could be me
(በቀጣይ)

ገላመጠኝ ሰው ገላመጠኝ
ባለማወቅ አጠፋሁ መሰለኝ።
አስተናጋጇ ይጨንቃታል መሰለኝ። ቤቱን ደጋግማ ትጠርጋለች። የወንበሮቹን አንግል ታስተካክላለች። ፕላስተር መቁረጫው፣ ካላንደሩ እና ሶፍት ማቅረቢያውን ትሰድራለች።

ልጅት እኔን ተመልከቺ። እኔም ያለቦታዬ ነኝ።!!
Forwarded from HOME || ቤት 🏚
ሴቱቱ ሆይ...
በአንድ አካል ሁለት ግብር
ሁለት ታቦት በአንድ ደብር
ለባል ሚስቱ ለልጅ እናት
አንዷ ነፍስሽ ግን ስንት ናት?

የሚሞቁት አንቺን ማግደው
የሚኖሩት ከዕድሜሽ ወስደው
እናት አንቺው ሚስትም አንቺው
አንዴ ነው ግን የምትሞቺው?
ድል!
ቃሉ ራሱ ደስ ይላል!
መልካም የድል በዓል!
እንደእኔ የቡና ገበሬዎች ውለታ ያለበት የለም።
Have you got a little time? Read Frankenstein by Mary Shelly.

👹📖
Happy International Women's Day.


I want to say more. I shall say more
One word which comes to you when you hear about Women's day?
አለሁ። I hope you had a nice Saturday. 😊
የማላውቃቸውን ሰዎች እወዳለሁ። የማላውቃቸው ሰዎች ናፍቀውኝ ነበር። ፈገግታቸው ደስ ይለኛል፣ አወራራቸው ደስ ይለኛል፣ አበላላቸው ደስ ይላል፣ ሰው የሚያዩት ነገር ደስ ይላል። በአብዛኛው ጥሩ ናቸው። በአብዛኛው ያሳዝናሉ። መቼም ስማቸውን አላውቀውም። መቼም ታሪካቸው አይገባኝም። ልክ እንደእኔ ናቸው፣ ደግሞም ከእኔ የተለዩ። እወድዳቸዋለሁ።
@coffeeandscribblings

አዎን ሻይ እየጠጣሁ ነው። ቡና እንጠጣ ብሎ ተቀጣጥሮ ለብቻ እየጠጡ መጠበቅ ደስ አይልም።
ራሴን የሚያመኝ ጊዜ ከራስ ምታት በላይ የምፈራው የለም። መጣ? ሄደ። ይመጣ ይሆን? ለምን ራስ ምታት አሉት? ራስህ ከተመታ ምን ተረፈ? ሁሉ ነገር መመታት አይሉትም?


በራስ ምታት ይሞታል እንዴ? እላቸዋለሁ ዙሪያዬ ያሉትን። ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ኑዛዜዬን አስባለሁ። ያኛው መጽሐፌ ለቆንጆ... ያኛው ለሔለን...


ፊቴ አብጧል አይደል? አፍንጫዬ ተጣሟል? በደንብ እይኝ። በደንብ እይኝ። እውነቱን ንገሪኝ።

በእጄ ጥርቅም አድርጌ ካልያዝሁት ጭንቅላቴ ተነድሎ መውደቁ ነው እላለሁ።

በእንቅልፌ ራሴን ያመኛል። ጥቋቁር የለበሱ ጥቋቁር ሰዎች አያለሁ። ጠንካራ ሽቷቸው የሚሰነፍጥ። በእንቅልፌ ራሴን ያመኛል።

በምድር ከራስ ምታት በላይ ጠላት የለኝም።
@coffeeandscribblings
These things might help someone... it might change lives. Please pass it around.
Thank you
Chaya saman kitna piyara!!
Sawan ka samjho isharra
Aisee mausam mein tum bhi kuch kaho... tum bhi kuch karo!
Karo ho kyun gumsum?



What a lovely weather is this!
Try and understand the meaning of this rainfall.
In such weather, you should also say something, do something.
Why are you silent?
One Hindi song
በህልሜ የማየው:-
የአስቴር አወቀን ሙዚቃ ሳሞቅ። ማለት? በማንቆርቆርያ አድርጌ በምድጃ ጥጄ። ልጠጣው።
ስነቃ መጀመሪያ ምን አስባለሁ?
በጦሙ ሙዚቃ ልጠጣ ነበርን?
ሁለተኛ ምን አስባለሁ?
እንዴ! ሙዚቃ ይፈላልን?

መልካም ቅዳሜ! ደግሞ ያላየነው አዲስዬ ቅዳሜ መጥቷል።
@coffeeandscribblings
ከልጅነት መዝገብ

የዋሲሁን በላይ እና የሀረገወይን አሰፋ ድምጽ... ቀይ ሬዲዮ... ወተት በቡና... የእናቴ በሻርፕ የተጠቀለለ ቆንጆ ፊት... የአመድ ኮፎያ ያጠለቀ ቡናማ ሬንቦው ሰንደል...

ስለሌሎቹ ሌላ ጊዜ ግን ሰንደል ምን ያህል እንደምወድ ነግሬኃለሁ?


ከእህቴ ጋር 'ጥቁር ቆንጆ' የሚል ሰንደል ለመግዛት በመላክ ነው ለአቅመ ሱቅ የደረስነው። በእሱ ላይ ያሉትን ቆንጆ ጥቋቁር ሴቶች ቅርጽ አውጥቶ በመለጠፍ እንዝናና ነበር።

ላቭ ኦፍ ኤዥያ ሲመጣ ከህንድ ፍቅራችን ጋር ተያይዞ በሰንደል ፍቅር አበድን። ሁሉ ነገሩ ደስ ይላል እሱ ሰንደል ደግሞ። ሽፋኑ ላይ አማልክቶች ሰንደል ሲጤስላቸው ያሳይ ነበር። አጋርባቲ ይላል ደግሞ። ህንድ አንድ እርምጃ ወደ እኛ የተራመደች መሰለን።


ብለን ብለን በደብተር እና መጻህፍታችን መኃል ሰንደል እንከት ነበር። በየክፍሎቹ ሰንደል እንሰቅል ነበር።

የሙለዓለም ታደሰ ሰንደል ዋልያ ማስታወቂያን ከእኔ እና ከእህቴ ውጪ የሚያስታውሰው መኖሩን እጠራጠራለሁ። ከማዘር ኢንዲያ ዘፈኖች በአንዱ ነው የተዘፈነው።

'ያላየም አይቶ ያልሰማም ይስማ
ሰንደል ዋልያን ሁሉም ይሻማ
ይሻማ ሁሉም ይሻማ
ኦኦኦኦኦኦ'

ህም። ሰንደል ልጅነቴን ነው የሚያስታውሰኝ። በነጭ ሳሙና ላይ አመዱን እያርገፈገፈ ሲጤስ። የመልካም ነገሮች ምሳሌዬ ነው።

አሁን ራሱ ይሸተኛል።

ሰንደል እንዴት ነው የሚሰራ?

@coffeeandscribblings
Ramadan Kareem!!
2025/07/07 08:07:59
Back to Top
HTML Embed Code: