Telegram Web Link
SATURDAY.
ጭንቀቴ በክፍሉ ውስጥ እንዳለ አንድ ሌላ ሰው ያህል እውነት ነው። እጆቼን ብዘረጋ እንደምነካው ያህል... እስትንፋሱ በጆሮዬ እንደሚሰማኝ ያህል... ሙቀቱ በጉንጮቼ ይታወቀኛል።

መኃል መኃል ላይ እየቦጨቀ ይጎርሰኛል። እሱ እየገዘፈ እኔ እኮስሳለሁ። የሰናፍጭ ቅንጣት ሆኖ ጀምሮ ተራራ ያህላል።

መጨነቅ ሀጢያት ነው፣ አይደል?
@coffeeandscribblings

(ደህና ነኝ። በአንድ ወቅት የተሰማኝ ስሜት ገርሞኝ መጻፌ ነው እንጂ አሁን በጣም ደህና ነኝ። አመሰግናለሁ። 🤗)
ጸጉር ሰሪው:- ይሄን ጸጉር ስንት አመት አወቅሁት? ሁለት አመት?
እኔ:-አዎ ይሆናል። ጸጉሬ እንግዳ አይወድም። የለመደውን እጅ ይፈልጋል።
እሱ:- ታዲያስ እውነቱን ነው እኮ። እኔ እንኳን ይህቺን ቁንጮዬን ከአንድ ሰው ውጪ ሲነካት አልወድም።
(እውነትም ቁንጮ ነው።)
ሳቅሁ።
እሱ:- ቁንጮ እኮ ጥቅሟ ምን መሰለሽ? ቁመት ትጨምርልኛለች።








ጸጉር ፖለቲካ ነው። የብዙኃን መተዳደሪያ ነው። ውሳኔዎችህ ላይ ተጽዕኖ አለው። ጸጉር ቤቶች የፖለቲካ መድረኮች ናቸው። ሌላ ጊዜ እነግርኃለሁ እንዴት እንደሆነ። አሁን ጊዜ የለኝም።
@coffeeandscribblings
You will win this in the end. It is all about heart and character.
BE YOUR BEST SELF.


Standard advice from Darryl
🙏🏾
ሌላ ቅዳሜ።

አዳዲስ መንገዶች እንደፏፏቴ ሿ ብለው የተከፈቱ ይመስለኛል። በጨለማ እንኳ ቀስተደመናዎች ያሉ ይመስለኛል።

ከጊዜ ማለፍ በላይ መልካም ነገር የለም። ሌላው ቢቀር ቅዳሜን ሲወስድ ቅዳሜ ይተካል።

መልካም ቅዳሜ!
@coffeeandscribblings
A new Amharic books app called Tuba. You can buy audiobooks and ebooks for a fair price from the comfort of your home.


You gotta check it out. We gotta support such initiatives. 😊

P.S. They didn't ask to me to advertise yemir. 😁
They don't have many books now but if we help out... they can.
Coffee and Scribblings pinned «https://lozadmasu.wordpress.com/2022/04/18/%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%88%e1%8a%aa/»
መልካም የትንሣኤ በዓል!
Audio
የዋዜማ ድምጾች።
@coffeeandscribblings
ካፌዎች ሲዘጉ ይጨንቀኛል። ሌባ ትዝታዬን ይዞ የበረረ ይመስለኛል። 'ሌባ ሌባ' ብዬ ብጮህ እመኛለሁ።

ካፌዎች እንደፎቶግራፎች ናቸው። አሁን እንኳን አይኔን ጨፍኜ በዚያ ካፌ እኔ እና እናንተ የሆንነውን ሁሉ ማስታወስ እችላለለሁ። አቀማመጣችን፣ ሳቃችን፣ አወራራችን ምናምን ሁሉ ይታየኛል። ስትናፍቁኝ የነበርንበት ካፌ ሄጄ ከነበርንበት ቦታ ራቅ ብዬ የነበርንበትን አያለሁ። አታምኑኝም። ግን እውነት ነው።
በየግድግዳው ስለተሰቀሉ ስዕሎች... ስለአስተናጋጆች... ስለሙዚቃው... ስለመጻሕፍት... ስለሰዎቻችን... ስለነገሮቻችን... ያወራነው ሁሉ እንደቱባ ክር ከፊቴ ይተረተራል።

ካፌዎች የመንገድ ላይ ቤቶች ናቸው። እናንተ ትከፍቷቸዋላችሁ፤ እኛ እንኖርባቸዋለን። ሸጎጥ ብለን ራሳችንን ከዚህም ከዛም ሰብሰብ አድርገን የምንወጣበት። ምን ነካኝ? የምንልበት። በማኪያቶ ጥቁርነት በኩል የደፈረሰ እኛነታችንን የምናይበት።

ካፌዎች ቢሮዎች ናቸው። በመነሻ እና መድረሻችን መኃል ያሉ ሀሳቦቻችንን የምንሰድርበት። የምንከትበት። የበሰለ ሀሳባችንን በገበታ የምናቀርብበት።

አቦ ካፌ አትዝጉ! አትዝጉ በቃ!

ወይ እርማችንን እንድናወጣ ቀድማችሁ ንገሩን። ከዚህ ቀን ጀምሮ አገልግሎት አንሰጥም በሉ!! ቢያንስ ፎቶ እናነሳለን!!


የሚያቁነጠንጥ ሀሳባችንን ልናሳርፍ ያቺ ካፌ ድረስ ያቺ ካፌ ድረስ እያልን (ከባድ ሸክም ይዞ እንደሚንደረደር ጎረምሳ) ስንደርስ ዝግ! አይን ፍጥጥ! ሸክም ዝርግፍ!

የሰው እጅ እየጎተትን ቆይ ሀሳብህን ያዝ ቆይ ጨዋታህን ያዝ መታጠፊያው ላይ ካፌ አለች። ያዝ ትንሽ። እያልን ስንደርስ ባዶ! መቃቃር ያመጣል!! በወንድማማች መኃል ቂም የሚዘራ ነው ነገሩ!!

ካፌ አትዝጉ! አትዝጉ በቃ!!

መታሰቢያነቱ:-
ላ ፓሪዝየን (አለም ሲኒማ ጋር)
ብሉዝ ካፌ (ሜክሲኮ)

@coffeeandscribblings
Labour day is important! Don't take it for granted!

All work is significant! Don't take any for granted!!



መልካም የላብአደሮች ቀን!
Coffee and Scribblings pinned «ካፌዎች ሲዘጉ ይጨንቀኛል። ሌባ ትዝታዬን ይዞ የበረረ ይመስለኛል። 'ሌባ ሌባ' ብዬ ብጮህ እመኛለሁ። ካፌዎች እንደፎቶግራፎች ናቸው። አሁን እንኳን አይኔን ጨፍኜ በዚያ ካፌ እኔ እና እናንተ የሆንነውን ሁሉ ማስታወስ እችላለለሁ። አቀማመጣችን፣ ሳቃችን፣ አወራራችን ምናምን ሁሉ ይታየኛል። ስትናፍቁኝ የነበርንበት ካፌ ሄጄ ከነበርንበት ቦታ ራቅ ብዬ የነበርንበትን አያለሁ። አታምኑኝም። ግን እውነት ነው።…»
Eid Mubarak! 🥳
2025/07/06 23:48:12
Back to Top
HTML Embed Code: