ዝናቡ እየባሰበት ሲመጣ የጠባቡን ጸጉር ቤት በር ገጠመችው። ደብዝዞ የነበረው ሙዚቃ ደመቅ ብሎ መሰማት ጀመረ።
ኣይትጨነቂ ብኣይ ኣይትሰከፊ
እያለ ከሚያንዘረዝር ክራር ጋር።
ሶስቱም ጸጉር ሰሪዎች ሞቅ ያለ የትግርኛ ጨዋታቸውን አቁመው ከሙዚቃው ጋር ተዳበሉ።
ዝወረደ ይውረድ ብዘየግድስ
ዝወረደ ይውረድ ብዘየግድስ
'አህ የማነ ባርያ' አለች ጮህ ብላ እየሾረበችኝ ያለችው። ሁሉም አብረውት ያንጎራጉራሉ። መኃል መኃል ከንፈራቸውን ይመጣሉ።
የምትሾርበኝ ልጅ በእጅጉ ቀርባኛለች። ትንፋሿ አንገቴ ላይ ይሰማኛል። የምታንበለብለው ዘፈን በጆሮዬ። የጣደችው ወጥ ጭስ እየተትጎለጎለ ከብቦኛል። ሙዚቃዋ ሳላስበው እግሬን እና ጣቶቼን ይወዘውዘዋል። ከውጪ ዝናቡ ይደነፋል። ልቤ በጉሮሮዬ የተወተፈች መሰለኝ። ክፍሉ ውስጡ ከምናውቀው ነገር ሁሉ የሚተልቅ አንድ ነገር የገባ መሰለኝ።
የማነ ባርያ ይቀጥላል።
ዝመጻ ይምጻ ዘጓነፈኒ
ዝመጻ ይምጻ ዘጓነፈኒ
ከውጭ አንዱ በሩን ቢከፍት የሚያገኘን አይመስለኝም። ከየማነ፣ ከወጧ፣ ከሹሩባዬ፣ ከትንፋሿ እና ከዝናቡ ጋር አንዳች ቦታ ሄደን ነበር።
መልካም ቅዳሜ!
@coffeeandscribblings

የነገርኹኽ ትዝ ይልኃል?
ብርድ በወረሰው ምሽት በአስፋልቱ ጥግ እየሄድን... ወደቀዘቀዘው አፍንጫዬ ማስኬን እየጎተትሁ... አይኖቼ የማይጠገብ ፊትህን ሳይጠግቡ እያፈጠጡብህ...
"ከመጀመሪያ አመት ጀምሮ ነው የማያቸው የነበረው። በዶርም መስኮት በኩል ይታያል ቤቱ። እና ወላ ሲከፋኝ እና እግሮቼ በአየር ላይ የተንጠለጠሉ ሲመስለኝ የምወዳቸውን ነገሮች ያስታውሱኛል። ደግሞ ከአመት እስከአመት ከቦታዋ የማትወርድ ሮዝ የህጻን ልጅ ገላ ማጠቢያ አላቸው። ህጻኑን ሲያጥቡት ሁሉ አያቸዋለሁ። እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ። ልብስ ሲያጥቡ ውኃ እየደፋፋ ያስቸግራቸዋል።
አንድ ቀን ደግሞ ተለቅ ያሉት ሴትዮ ጀበና እየለቀለቁ አይቼ ሆድ ባሰኝ። የማውቃቸው ነው የመሰሉኝ። በቀሚስ ላይ ባለቁልፍ ሹራብ ደግሞ በላዩ ነጠላ አድርገው። የምር የዛን እለት ቤታቸው እንዴት መድረስ እንደምችል ባውቅ እገሰግሰው።
አሁን ብታይ በፊት ለፊቱ ቤት እየሰሩ ነው። የሚታየው ነገር ከለት እለት እያነሰ እንደሆነ በእውነት!!! እኔ ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ ቀን የምሆነውን አላውቅም።"
ብዙ በማውራቴ እንዳላፍር አድርገህ ታዳምጠኝ ነበር።
ምን መሰለህ?
አለቀ ቤቱ! ድራሻቸውም አይታይም የነዛ ሰዎች አሁን። ወላ ቡና። ወላ ህጻን። ወላ ምን የለም!
ግን አምናለሁ። ከግንቡ ጀርባ እንዳሉ። ትንሽዬ ግን ያልተከወነ ህይወታቸውን እንደሚኖሩ። ደህና እንደሆኑ።
አምናለሁ።

Didn't I tell you I make podcasts elsewhere too? I think you should give us a listen. 😊
Forwarded from HOME || ቤት 🏚
Imagine ስንት ሰዓታት ፈጀቶብህ የጻፍከው ግጥም sense አልሰጥ ሲልህ! Anyways ለምን እኔ ብቻ ልወዛገብ - Here it is...
፨፨፨
መቼስ ትደንቃለህ!
ታውቀህ መች ታልቃለህ?
ሰው ሆነህ ታውቃለህ!
ካምላክነት ሳትጎ'ል
ብትተኛም በጎል
የኔን ስጋ ለብሰህ
እንጀራዬን ጎርሰህ
እምባዬን አብሰህ
ለቅሶዬን አልቅሰህ
ስለ'ኔ ተወቅሰህ
ሆነኸው መሆኔን
አክለኸኝ እኔን
አድረሀል ባልጋዬ
ተምኖህ ዋጋዬ
በጠበበ ደረት በአጠረ ቁመት
ቀርበህ ተጠግተህ ለከንፈሬ ስመት
ተስሎ እንዳየኹት መልኬን በመልክህ ላይ
ቁልቁል እንደወረድክ ከሰማየ ሰማይ
ማየትን እሻለሁ መልክህን በመልኬ
ማምለክ ከከበደኝ ልየው ተመልኬ
ይኸው ልለምንህ አንዲት ትንሽ ነገር
ያላዋቂ ሳሚ ወይ ያዋቂ ነካሽ ሆኜ ከምቸገር
አንተ ሰው እንደሆንክ ሰጋና ደም ነስተህ
ከሰማይ ስቀለኝ ከምድር አንስተህ
አምላክነትህን ሁሌ ከምወቅሰው
ሆነህ እንዳየኸው አንተም እንደኔ ሰው
እሬቴን ጎርሰሀል ማርህን ልቅመሰው
እስኪ በተራዬ እኔን አምላክ አ'ርገኝ
ሳበኝ ወደሰማይ ሽቅብ አሳርገኝ
አምላክኛ እናውራ ከፀባዖት ልገኝ!
ያምላክ ወግ እንጠርቅ ወይ እንከራከር
በቅጥ እንለየው በጋውን ከመከር
ፍጡርን እናርቅቅ ከዝሆን እስከ ዝንብ
ፀሐይን እናውጣ ዝናብን እናዝንብ
አበባን እናስውብ ወፎችን እንመግብ
እናብጅ እንመትር የሁላለሙን ግብ
ዔሳውን እንጥላ እንውደድ ያዕቆብን
በአናታችን እንጫን የብርሃን ቆብን
እንርቀቅ እንምጠቅ ለሰው ግራ እንግባው
ኢምንትን ማከሉ ሆድ ሆዱን ያባባው
ሰዶም ገሞራ ላይ እናውርድ የእሳት ዲን
ንፍር ውሃው ይጥረግ ልበ ወለፈንዲን
ክፉን እየገፋን ከቅን እንራከብ
ኖሆችን እናድን እያሰራን መርከብ
ሙሴን እንቀድሰው ዛፍ እያነደድን
የፈርኦንን ልብ አውቀን እናደንድን
በአስር ታምር ፈተን የእስራኤልን ነገድ
አርባ ዓመት እናርገው የአርባ ቀኑን መንገድ
መና እናዝንብ ከላይ፣ ካለት ውሃ እናፍልቅ
ሰው የማይገባውን ያምላክ ወግ እንሰልቅ
አባይ ሚዛን ሰፍሮት ንፁሁ ሲበደል
ፍርድ ሲገመደል ፍትሕ ስትጓደል
ፃድቁ ሲጨቆን እስረኛ ሲደረግ
ዝም ብለን እንየው በአማልክቱ ወግ
የፀሐይ ፊት ፍሞ ምድርን ሲያደርቃት
ዓለም ውሃ ጠምቷት ሲወርሳት ንቃቃት
ደመና ማይ ነፍጎ ሰማይ ሰስቶ ጠል
ወላጅም ውላጅም በጥማት ሲቃጠል
መሬት ቧጦ በጁ ፍጥረት ቢልም "ወየው"
በአምላክነት ድባብ ዝም ብለን እንየው!
የገነትን መንገድ ፍጡር ተፀይፎ
መዐት ሲጠባበቅ ለሞት ተሰልፎ
ባይኑ ሞገስ ሲያገኝ የሲዖል አዳራሽ
ጠምቀን እንጋተው የገሞራውን ጉሽ
የእርኩሰትን ዘፈን ፍጡር ሲቀባበል
በአምላካዊ አርምሞ አብረን ዝም እንበል!
አሻፈረኝ ብሎ መዳኑን ሲገፋ
መንታ እምባ እያዠን ባምላካዊ ተስፋ
መንገድና ትልሙን ደርሶ እንዳልቀየስን
በመጥፋቱ እንዘን ደግሞ እያለቀስን!
ድርጓችን ይሁነን መከዳት፣ መረሳት
አምልኮ መጓደል፣ ምስጋና መነሳት
ሕሊና ተረግጦ፣ ምግባር አዘንብሎ
ይካደን ፍጡራችን "የላችሁም" ብሎ
በክቡር ስማችን ይነገድ ይተረፍ
መባና አስራታችን ይመዝበር ይዘረፍ
ከገዛ ቤታችን ከመቅደስ ያግልሉን
በታይታ አምልኮ በቃል ይሸንግሉን
መቅደሱ ሲከፈል በቋንቋ በነገድ
በስመ-ሃይማኖት በእምነት ሲነገድ
ካህን ሌባ ሲሆን መናኙም ወንበዴ
ሳንል "ግርዶ ግርዶ"* ሳንል "በዴ በዴ"**
ዝም ብለን እንየው በአምላካዊ ዘዴ
መሻት ይሉት ወጥመድ ዕውቀት ይሉት ድካም
እርቃን ስቀላወጥ እኔም ልክ እንደ ካም
መርምሬ ላላውቅህ ስታ'ገል አልገኝ
ፈቅደህ ሰው እንደሆንክ ፈቅደህ አምላክ አርገኝ
እንዲገባኝ ፍርድር ስራህ እንዲዘልቀኝ
ዙፋን እንጋራ ልቀመጥ ካንተ ቀኝ
ከቶ ላልጨርስህ በምናቤ ስዬህ
አንሰህ እንዳወቅከኝ ልወቅህ አክዬህ
ከዮናሳዊነት ምናልባት ብሰክን
አምላክ ሆኜ ልየው ሕማመ-አምላክን
ብዙ ለምንታ አለኝ
ከልቤ 'ማይጠፋ ቢነ'ባ ቢለቀስ
አምላክ አርገኝና
ከመንበርህ ልምጣ ጥቂት እንዋቀስ
ምናልባት ምናልባት
ልጅ ቢረ'ዳ አባቱን ሆኖ ሲያየው አባት
ይቺን ድኩም ነፍሴን
አምላክን አርጋትና አምላክነት ይግባት!
ከመንበርህ ልምጣ ከዓለም መንኜ
ሰው ሆነህ አይተሀል ልየው አምላክ ሆኜ!
[
ለመንኩ ይችን ብቻ!
አሜን
]
፨ ፧ ፨
* ግርዶ(ጉራጊኛ) = ወይኔ ፤
** በዴ (ኦሮምኛ) (ዴ አይጠብቅም!! 😂) = ጠፋሁ
፨፨፨
መቼስ ትደንቃለህ!
ታውቀህ መች ታልቃለህ?
ሰው ሆነህ ታውቃለህ!
ካምላክነት ሳትጎ'ል
ብትተኛም በጎል
የኔን ስጋ ለብሰህ
እንጀራዬን ጎርሰህ
እምባዬን አብሰህ
ለቅሶዬን አልቅሰህ
ስለ'ኔ ተወቅሰህ
ሆነኸው መሆኔን
አክለኸኝ እኔን
አድረሀል ባልጋዬ
ተምኖህ ዋጋዬ
በጠበበ ደረት በአጠረ ቁመት
ቀርበህ ተጠግተህ ለከንፈሬ ስመት
ተስሎ እንዳየኹት መልኬን በመልክህ ላይ
ቁልቁል እንደወረድክ ከሰማየ ሰማይ
ማየትን እሻለሁ መልክህን በመልኬ
ማምለክ ከከበደኝ ልየው ተመልኬ
ይኸው ልለምንህ አንዲት ትንሽ ነገር
ያላዋቂ ሳሚ ወይ ያዋቂ ነካሽ ሆኜ ከምቸገር
አንተ ሰው እንደሆንክ ሰጋና ደም ነስተህ
ከሰማይ ስቀለኝ ከምድር አንስተህ
አምላክነትህን ሁሌ ከምወቅሰው
ሆነህ እንዳየኸው አንተም እንደኔ ሰው
እሬቴን ጎርሰሀል ማርህን ልቅመሰው
እስኪ በተራዬ እኔን አምላክ አ'ርገኝ
ሳበኝ ወደሰማይ ሽቅብ አሳርገኝ
አምላክኛ እናውራ ከፀባዖት ልገኝ!
ያምላክ ወግ እንጠርቅ ወይ እንከራከር
በቅጥ እንለየው በጋውን ከመከር
ፍጡርን እናርቅቅ ከዝሆን እስከ ዝንብ
ፀሐይን እናውጣ ዝናብን እናዝንብ
አበባን እናስውብ ወፎችን እንመግብ
እናብጅ እንመትር የሁላለሙን ግብ
ዔሳውን እንጥላ እንውደድ ያዕቆብን
በአናታችን እንጫን የብርሃን ቆብን
እንርቀቅ እንምጠቅ ለሰው ግራ እንግባው
ኢምንትን ማከሉ ሆድ ሆዱን ያባባው
ሰዶም ገሞራ ላይ እናውርድ የእሳት ዲን
ንፍር ውሃው ይጥረግ ልበ ወለፈንዲን
ክፉን እየገፋን ከቅን እንራከብ
ኖሆችን እናድን እያሰራን መርከብ
ሙሴን እንቀድሰው ዛፍ እያነደድን
የፈርኦንን ልብ አውቀን እናደንድን
በአስር ታምር ፈተን የእስራኤልን ነገድ
አርባ ዓመት እናርገው የአርባ ቀኑን መንገድ
መና እናዝንብ ከላይ፣ ካለት ውሃ እናፍልቅ
ሰው የማይገባውን ያምላክ ወግ እንሰልቅ
አባይ ሚዛን ሰፍሮት ንፁሁ ሲበደል
ፍርድ ሲገመደል ፍትሕ ስትጓደል
ፃድቁ ሲጨቆን እስረኛ ሲደረግ
ዝም ብለን እንየው በአማልክቱ ወግ
የፀሐይ ፊት ፍሞ ምድርን ሲያደርቃት
ዓለም ውሃ ጠምቷት ሲወርሳት ንቃቃት
ደመና ማይ ነፍጎ ሰማይ ሰስቶ ጠል
ወላጅም ውላጅም በጥማት ሲቃጠል
መሬት ቧጦ በጁ ፍጥረት ቢልም "ወየው"
በአምላክነት ድባብ ዝም ብለን እንየው!
የገነትን መንገድ ፍጡር ተፀይፎ
መዐት ሲጠባበቅ ለሞት ተሰልፎ
ባይኑ ሞገስ ሲያገኝ የሲዖል አዳራሽ
ጠምቀን እንጋተው የገሞራውን ጉሽ
የእርኩሰትን ዘፈን ፍጡር ሲቀባበል
በአምላካዊ አርምሞ አብረን ዝም እንበል!
አሻፈረኝ ብሎ መዳኑን ሲገፋ
መንታ እምባ እያዠን ባምላካዊ ተስፋ
መንገድና ትልሙን ደርሶ እንዳልቀየስን
በመጥፋቱ እንዘን ደግሞ እያለቀስን!
ድርጓችን ይሁነን መከዳት፣ መረሳት
አምልኮ መጓደል፣ ምስጋና መነሳት
ሕሊና ተረግጦ፣ ምግባር አዘንብሎ
ይካደን ፍጡራችን "የላችሁም" ብሎ
በክቡር ስማችን ይነገድ ይተረፍ
መባና አስራታችን ይመዝበር ይዘረፍ
ከገዛ ቤታችን ከመቅደስ ያግልሉን
በታይታ አምልኮ በቃል ይሸንግሉን
መቅደሱ ሲከፈል በቋንቋ በነገድ
በስመ-ሃይማኖት በእምነት ሲነገድ
ካህን ሌባ ሲሆን መናኙም ወንበዴ
ሳንል "ግርዶ ግርዶ"* ሳንል "በዴ በዴ"**
ዝም ብለን እንየው በአምላካዊ ዘዴ
መሻት ይሉት ወጥመድ ዕውቀት ይሉት ድካም
እርቃን ስቀላወጥ እኔም ልክ እንደ ካም
መርምሬ ላላውቅህ ስታ'ገል አልገኝ
ፈቅደህ ሰው እንደሆንክ ፈቅደህ አምላክ አርገኝ
እንዲገባኝ ፍርድር ስራህ እንዲዘልቀኝ
ዙፋን እንጋራ ልቀመጥ ካንተ ቀኝ
ከቶ ላልጨርስህ በምናቤ ስዬህ
አንሰህ እንዳወቅከኝ ልወቅህ አክዬህ
ከዮናሳዊነት ምናልባት ብሰክን
አምላክ ሆኜ ልየው ሕማመ-አምላክን
ብዙ ለምንታ አለኝ
ከልቤ 'ማይጠፋ ቢነ'ባ ቢለቀስ
አምላክ አርገኝና
ከመንበርህ ልምጣ ጥቂት እንዋቀስ
ምናልባት ምናልባት
ልጅ ቢረ'ዳ አባቱን ሆኖ ሲያየው አባት
ይቺን ድኩም ነፍሴን
አምላክን አርጋትና አምላክነት ይግባት!
ከመንበርህ ልምጣ ከዓለም መንኜ
ሰው ሆነህ አይተሀል ልየው አምላክ ሆኜ!
[
ለመንኩ ይችን ብቻ!
አሜን
]
፨ ፧ ፨
* ግርዶ(ጉራጊኛ) = ወይኔ ፤
** በዴ (ኦሮምኛ) (ዴ አይጠብቅም!! 😂) = ጠፋሁ
What is life like? It is like how my phone's storage is always full but I don't really know what is occupying it because I don't have half of the things I want to have on my phone because of a storage problem.
What is relief like? It is like making one very long sentence with many of your frustrations in it.
@coffeeandscribblings
What is relief like? It is like making one very long sentence with many of your frustrations in it.
@coffeeandscribblings
Happy Left Handers Day!!!
The second picture shows me writing on the first ever left handed single chair I found in 24 years.
And no, I am not growing out of this left handers day thingy. I refuse to.
The second picture shows me writing on the first ever left handed single chair I found in 24 years.
And no, I am not growing out of this left handers day thingy. I refuse to.
የአንዲት ሀገር ዜጎች አንድ አይነት ስነልቦና ያላቸው ናቸው ይላል። ምን ማለቱ ነው? አበበ በሶ በላ እያሉ አረፍተ ነገር የሚሰሩ ናቸው ማለቱ ነው? ወይስ በአንድ ሰሞን ሁሉም የሚያወሩት እና የሚያስቡት የሚተነፍሱት ሁሉ ስለአንድ ነገር ነው ማለቱ ነው? ከማላውቃቸው 100 ሚሊዮን ሰዎች ጋር አንድ አይነት ስነልቦና አለሽ መባሉ ይከነክነኛል። በአንድ አይነት ሙዚቃ አንድ አይነት የምንወዛወዝ ምስኪኖች ነንን?
*******
አረፍተ ነገር የሚገርም ሀረግ ነውና። ነገርህ ሲያርፍ ነው እኮ። የማን ነገሩ ያረፈለት አለ?
@coffeeandscribblings
*******
አረፍተ ነገር የሚገርም ሀረግ ነውና። ነገርህ ሲያርፍ ነው እኮ። የማን ነገሩ ያረፈለት አለ?
@coffeeandscribblings
Coffee and Scribblings
https://lozadmasu.wordpress.com/2021/11/28/%e1%8b%9c%e1%8a%93-%e1%88%98%e1%8b%8b%e1%8b%95%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%8a%94-%e1%89%a2%e1%8c%a4%e1%8b%ad%e1%89%b5/
ድጋሚ በሜክሲኮ ስሄድ ይህችን ሴት አጣኋት። ደግሞም ድጋሚ ስሄድ አጣኋት። ብዙ ብዙ አመት ያላጣኋትን አጣኋት።
እንግዲህ ባለችበት ሰላም እንድትሆን ታስቧት ዘንድ እለምናለሁ።
@coffeeandscribblings
እንግዲህ ባለችበት ሰላም እንድትሆን ታስቧት ዘንድ እለምናለሁ።
@coffeeandscribblings
Forwarded from Sost Kilo
ᵀʰᵉʳᵉ ʷᵉʳᵉ ᵃˡˡ ᵏⁱⁿᵈˢ ᵒᶠ ˢᵗᵒʳⁱᵉˢ ᵗᵒˡᵈ ᵃᵇᵒᵘᵗ ᵗʰᵉ ʷᵃʳ ᵗʰᵃᵗ ᵐᵃᵈᵉ ⁱᵗ ˢᵒᵘⁿᵈ ᵃˢ ⁱᶠ ⁱᵗ ʷᵃˢ ʰᵃᵖᵖᵉⁿⁱⁿᵍ ⁱⁿ ᵃ ᶠᵃʳᵃʷᵃʸ ᵃⁿᵈ ᵈⁱᶠᶠᵉʳᵉⁿᵗ ˡᵃⁿᵈ° ᴵᵗ ʷᵃˢⁿ'ᵗ ᵘⁿᵗⁱˡ ʳᵉᶠᵘᵍᵉᵉˢ ˢᵗᵃʳᵗᵉᵈ ᵖᵃˢˢⁱⁿᵍ ᵗʰʳᵒᵘᵍʰ ᵒᵘʳ ᵗᵒʷⁿ ••• | 𝙸𝚜𝚑𝚖𝚊𝚎𝚕 𝙱𝚎𝚊𝚑 | 𝙰 𝙻𝚘𝚗𝚐 𝚆𝚊𝚢 𝙶𝚘𝚗𝚎: 𝙼𝚎𝚖𝚘𝚒𝚛.
Read.
They say there are no good books anymore. There really is no time to read. But I say unto you... read.
Meet people.
They say there aren't good people anymore. That they are not worth the while... yet meet people ... you will be surprised.
Love yourself.
They don't say anything about it. But I say nothing goes if you are not in sync with yourself...hence love thee.

ሃገራችን በቡና ኤክስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ 1.4 ቢሊየን ዶላር በማግኘቷ እንኳን ደስ አለን!
መልካም አዲስ ዓመት!
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር
This makes me really happy
መልካም አዲስ ዓመት!
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር
This makes me really happy