Yours is graduating from medical school tomorrow. This channel and all the people in it had been one of my support systems. Thank you for all the love through the years.
@coffeeandscribblings
@coffeeandscribblings
ደግሞ አንድ የመጸዳጃ ቤት በር ላይ እንዲህ ተብሎ ተፅፏል።
'I am here crying- እያለቀስሁ ነው።'
'Me too- እኔም።'
'ኦ! አይዞን ፈጣሪ አለ።'
የሚገርም ነው። ሰዎች ሽንት ቤት ውስጥ እስክርቢቶ ይዘው እየሄዱ ያለቅሳሉ። ማለት... አይገርምም?
@coffeeandscribblings
'I am here crying- እያለቀስሁ ነው።'
'Me too- እኔም።'
'ኦ! አይዞን ፈጣሪ አለ።'
የሚገርም ነው። ሰዎች ሽንት ቤት ውስጥ እስክርቢቶ ይዘው እየሄዱ ያለቅሳሉ። ማለት... አይገርምም?
@coffeeandscribblings
ጓዜን በቦርሳ ለመክተት እሞክራለሁ። ጓዜ ህይወቴ ነው። እንደበቆሎ ነቅዬ ሌላ ቦታ ልተክለው አልችልም። ስነቅለው አለቀ። ስተክለው ደሞ ሌላ ህይወት ነው። ሌላ በቆሎ። ይህችን የማስክ ካርቶን አንስቼ ወደቤቴ ብወስዳት ራሷን ትሆናለች? በካምፓስ ቁምሳጥን ውስጥ የወከለችውን ሁሉ ትሆናለች?
ልቤ ራደ።
ይህችን ቁራጭ ወረቀት ለምን በቁምሳጥኔ ከተትኋት? ይሄንንስ? ያንንስ? የቱ ትዝታ ነው ጠቃሚ? የቱ ነው በትዝታ መኃል የገባ ቅራቅንቦ? ሁሉንም ላስታውሳቸው እፈልጋለሁ። ሁሉንም ላስታውስ አልችልም።
እንዲህ ብዙ ኖርሁን? ፍቅርና ትዝታ ቤትም ጭምር በልብ እንጂ በምድር አለመሆኑን አውቅ የለምን? ለምን እንደዚህ እፈራለሁ? ሆዴን ለምን ባር ባር ይለዋል?
ግድግዳዎቹን ልሳማቸው? ቁምሳጥኔን ልጠምጠምበት? ደህና ሁን አንጀት የሚያርሰው ምን ሲደረግ ነው?
ድካሜን ሁሉ የጠጣው አልጋዬን ለማን ትቼው ልሂድ?
ስንብት መጭነቁ።
ነሀሴ 8/15

አማርኛ መጽሐፍ ላይ የነበረ ግጥም ነው። የደበበ ሰይፉ።
ልጅቱ የዘመነችቱ።
መዘመን እንዲህ ነው እንዴ እል ነበር።
ዱሩላ ምንድነው እላለሁ? አይነግሩኝም። ፕሮቫ ግን ከምንባቡ ታች ያሉ የቃላት ፍቺ ላይ ነበር።
ልጅ መሆን ጥሩ ነው። ጸሀፊ ሁሉ አዋቂ ይመስልኃል። የተጻፈ ሁሉ እውነት ያለው ይመስልኃል።
አባቴ፣ አንብቦ አንብቦ ዝም ብሎ ነው ይል ነበር ሳይዋጥለት ሲቀር። እንዴት ዝም ብሎ ይሆናል? ጽፎት? መጽሐፍ ሆኖ? እል ነበር።
እንደጥንት ህዝብ ባየሁትና በወደድሁት አማልክት ብሰራ የመጽሐፍ አምላክ ይኖረኝ ነበር። ትልቅ ገጽ ምናምን።

I read Julius Cesar as ጁሊየስ ቄሳር in 2nd grade. I still have a difficult time saying Cesar and prefer ቄሳር 😁
I thought it was a violent and sad murder of a leader for political reasons followed by a series of deaths.
But rereading it this week, made me think a lot about right and wrong.
Although the play is titled Julius Caesar, the real protagonist is Marcus Junius Brutus. Caesar has very few lines and it must suck a little bit to play him. I kind of like him from Cleopatra's story though. Not for the relationship with her. So he was fighting this guy, Pompey. And Pompey fled to Egypt when things got dire to his ally, Ptoleme, who killed him to please Cesar. Then he presented his head to Cesar when he arrived to Egypt. Contrary to what he thought, Cesar wept and was quite mad at Ptolemy. Although a bit violent himself, he thought betrayal as a greater crime.
And we see Cesar being stabbed violently by people he trusts. 23 times. (Unnecessary. Isn't once or thrice enough?) Finally by his beloved Brutus, and says the famous line et tu Brute? Some accounts say he didn't... some say he said smoething else... but all agree he was surprised by Brutus' betrayal. For Brutus was like a child to him and he saved his life though he had sided with Pompey.
Now look at Brutus. A good man. He has good intentions to Rome and his people. He just believed Caesar was being too ambitious Which might make Rome regress to monarchy. He loved Cesar but he loved Rome more. He was asked to choose between killing his friend and letting Rome fall to tyranny. (In my humble opinion, unnecessary. They can just talk to him or even if he does become a 'king' which he probably wouldn't have, maybe he won't be a tyrant).
But he chose what he thought was right. It was not an easy choice too. He vexed and vexed to decide. Then he chose. And pays the price.
What do you think about Brutus?
Favorite line:
"The fault, dear Brutus, is not in our stars,
But in ourselves,that we are underlings."

የትልቅ ሰው ፍቅር ይከብዳል። የማውቀውን ሁሉ እያወቅሁ፣ ብዙውን መዝኜው ብዙው ቀሎብኝ፣የራስን ጥዑምነት እና መራራነት ተምሬ፣ ከዚህ ሁሉ በኋላ እወድኃለሁ ካልኹ... አይከብድም? @coffeeandscribblings
At 25, I have loved many things and got over them again. But books remain a constant in the ups and downs.
Did these books find me or did I find them?
@coffeeandscribblings
Did these books find me or did I find them?
@coffeeandscribblings
ጳጉሜ የ360 ቀናቶቼ እንጥፍጣፊ ይመስለኛል። የዛኛውም ደግሞ የዛኛውም ደግሞ የዚኛውም።
እዚህ በሆዴ ተንበልብዬ ለ6ቱ ቀናት 360ዎቹን ብገርብ እላለሁ። ብዙ ሳቅ ደግሞ ብዙ ማልቀስ ደግሞ ብዙ ቡና ደግሞ ብዙ ሻይ አለበት። ደስ ካላቸው ጋር መደሰት አለበት። ካዘኑ ጋር ማዘን አለበት። የሌሊት ስራዎች አሉበት። በ10 ሰዐት ምናምን መንገድ ላይ መሆን። መዐት የእግር ህመሞች አሉበት። ደግሞ መዐትትትት ምርቃቶች። ''የልብሽ ይሙላ።'' የልቤን መች አወቅኹት አለበት። ጓደኝነት አለበት። ቤተሰብ አለበት። ትንሽ የምወዳት ስትወለድ ያየኋት ህጻን አለች። የልቤ ክፋይ። የሆነ የልቤ ግድግዳ የወጣ የምትመስለኝ። ምን ላድርግሽ? ልዋጥሽ የምላት።
ዝም ብሎ ጎረምሳ ውድድ ማድረግ አለበት። መወደድ አለበት። እየተያዩ መሳሳቅ አለበት። አስቴር አወቀ ውድድ ውድድድድድድድ እያለች እንደምትቀውጠው ያለ ነገር ማሰብ ነው። ስልክ ማንሳት መጣል። መወስወስ አለበት።
አስቴር አወቀ አለችበት። መጻሕፍት አሉበት። የጀመሩትን መጨረስ አለበት። መሰናበት አለበት። (የማያልቅ ቻው ቻው ግን እንገናኛለን ግን ቻው። ደግሞ እቅፍ።) መጠራጠር፣ መጨነቅ፣ ተስፋ መቁረጥ አለበት። እኔ ማን ነኝ አለበት።
ከሁሉ በላይ የሆነው አለበት።
በ13ተኛ ወር ስለ12 ወሮች ከማሰብ ውጪ ሌላ ያለ አይመስለኝም።
ጳጉሜ 1 አሮጌ ልደታ የምትባለውም በምክንያት ነው።

My sister once said, ''You can't hold me accountable for something I said in the morning because I grow by the hour''. She said it jokingly but My God it is very true. I think we do all grow by the hour.

Up again upon request for a comment section.

ሆይ ሆይ እያሉ በህይወት አቀበት የሚያወጡኝ ሰዎች ናቸው። የሚወዱኝ። የምወዳቸው። እንዲህ ቢሆን እንዲያ፣ እንዲያ ቢሆን እንዲህ የሚሉኝ። ብጽፍ ስለሰዎች ነው። ባነብ ስለሰዎች ነው።
ህዝባዊ አብዮት ነኝ።
@coffeeandscribblings
ህዝባዊ አብዮት ነኝ።
@coffeeandscribblings
ከአውቶቡሱ ወንበር ላይ ጭንቅላቷን ወደኋላ ጥላ ተኝታለች። አፏ በትንሹ ከፈት ብሏል። የፊተኛው ጥርሷ ነጭ ነጥብ መስላ በክፍተቱ ትታያለች። የተከደነው አይኗ በኩል ደምቋል። ጠይም ረዘም ያለ ፊት አላት። አፍንጫዋ ወደታች እንደሚወርድ ዘንግ። ካርታ የመሰሉ ቡኒ ማድያቶች ግራ እና ቀኝ ጉንጯ ተለጥፈዋል።
ማነሽ? ፌቨኝ ነሽ ወይስ ማክዳ? ማህሌት? ቤቲ? ህሊና? ሂሩት? ሩት? የፋሲካ እለት የተወለድሽ ትንሳኤ ነሽ? ወይስ ለእንቁጣጣሽ የተወለድሽ መስከረም? የተባልሽውን ለምን ሆንሽ? ስትወለጂ ዜና ስታነብ በነበረችው ልጅ ነው? ባምላክ? ሔርሜላ? አጎትሽ ያወጣልሽ? ምን አስቦ? ማነሽ?
አንገቷ ረዥም ነው። እንቅርት ቢጤ ጉች ብሎባታል። ጭንቅላቷን ወደኋላ ባታደርግ ይታይ ይሆን? አንቺ ልጅ እንቅርትሽን አይተሽዋል? ትደባብሺዋለሽ ወይ? ትወጂዋለሽ ወይ? ወይስ ትጠይዋለሽ? ወይስ የምትጠይው እየመሰልሽ ትወጂዋለሽ ወይ? ጆሮ ደግፍ ቢይዘኝ ጉዴ ትይ ይሆናል። በእትዬ ባንቺይርጉና በአንቺ መኃል ያለው ልዩነት በአንድ እርምጃ ጠበበ ማለት አይደለም? እትዬ ባንቺይርጉን ታውቂያቸው ይሆን?
የአንገቷ ተዳፋት ላይ የደም ስሯ ትር ትር ይላል። አሳ ትመስላለች። የምትቃትት ጠይም አሳ። አንቺ ሴት የምትቃትቺበት ነገር አለ ወይ? ስራ እንዴት ነው? ትማርያለሽ ወይ? የምትከፍይው አጥተሽ ሀሳብ ይበላሽ ይሆን? የምትወጃቸው ሁሉ ሰላም ወጥተው እየገቡ ነው? የወደድሽው አለ? የወለድሽው? የሚያቃትትሽ ነገር አለ?
ቦርሳዋን በእጇ አጣምራ ከደረቷ አቅፋዋለች። አራት ማዕዘን የሆነ ጥቁር ተለቅ ያለ ቦርሳ ነው። ማንገቻው ፊት እና ኋላ ወድቋል። ከደረቷ ጥብቅ ብሏል። ከትንፋሿ ጋር ከፍ ዝቅ ይላል። ውስጡ ምን አለ? ምናልባት ዣንጥላ። ሻርፕ። ስልኳ። (ይጠራ ይሆናል። ሳትሰማው እንቅልፏን ስትለጥጥ ስልክ አታነሳም ብሎ የሚበሳጭ ይኖራል። ቴክስት ልኮ የሚንቆራጠጥላት ጎረምሳ ይኖራል። ተኝታለች ባክህ።) ምናልባት ኢርፎን። ሙዚቃ ባይሆን መዝሙር እሱም ባይሆን ሬዲዮ ትሰማ ይሆናል። ወይ ተበላሽቶባት ወይ ጠፍቶባት ስትገባ ልትገዛ ይሆናል። ብሮቿ። ወይ ብዙ። ወይ ትንሽ። መጽሐፍ ይኖራት ይሆናል ወይ ሊፕስቲክ። ፌስታል። ሰዎች ፌስታል ለክፉም ለደጉም ስለሚከቱ። ምሳ ዕቃ ይኖራት ይሆናል። ፍርፍር በልታ ይሆናል ወይ ሩዝ ወይ ምስር ወይ እንቁላል። ወይ አልበላች ርቧት ይሆናል። ሌላም ሌላም ነገር።
ሰማያዊ ሹራብና ጥቁር ሱሪ አድርጋለች። ጥቁር ረዥም ጸጉሯ ፊቷን ከብቦ ግራና ቀኝ ተኝቷል። የእንቅልፋም መአት። ጥቅልል ብሏል። ከመኃል ከፍላዋለች። ጸጉርሽን ስትሰሪ እንዴት ያለሽው ደንበኛ ነሽ? ድምጽሽን አጥፍተሽ ማንንም ሳታወሪ የምትወጪው ልጅ ነሽ? ወይስ ተጫዋቿ? ቲፕ በደንብ ትሰጫለሽ? ሰማያዊው ሹራብ ከየት አገኘሽው?
.
.
.
.
.
.
.
ሌላው ሌላው ሁሉ የማላውቀው። መቼም የማላውቀው።