Telegram Web Link
📢 ታላቅ የምስራች በስራ እና በትምህርት ምክንያት በመደበኛ ቀን የምንሰጠውን የዲን ትምህርት ለመማር ላልተመቻችሁ እህቶች 

⭐️ ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት በሁለት ፈረቃ ጠዋት ከ3:00-6:30 ወይም ከሰአት ከ7:30-10:00

⓵ አንደኛ ደረጃ የሚቀሩ ኪታቦች፦
☞ ዐቂዳ📚ኡሱሉ ሰላሳ

☞ ሀዲስ📚አርበዑነ- ነወዊያ

☞ ተርቢያ 📚 ተውጂሃት

⓶ ሁለተኛ ደረጃ የሚቀሩ ኪታቦች
☞ ዐቂዳ  📚ኪታቡ ተውሂድ
(ሸይኽ ሙሀመድ አ/ወሃብ)

ፊቅህ 📚መንሃጁ-ሳሊኪን

ተርቢያ 📚ተንቢሃት

🕌 የመማሪያ ቦታ፦ ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ የሚገኘው አባጅፋር መስጂድ አካባቢ (የቀድሞው መርየም መድረሳ)

🌻ትምህርቱ የሚጀመረው በአላህ ፈቃድ ቀጣይ ቅዳሜ ጥቅምት 5፣2014 ይሆናል።

☎️ ለበለጠ መረጃ፦ 👇
  
▪️+251904366666
▪️+251967671891

⚠️መልእክቱን ሼር በማድረግ ከአጅሩ እንቋደስ!

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
ዳሩል ሀዲስ
@darulhadis18
የተከበራቹ የነሲሓ ቤተሰቦች:-

አሰላሙ አላይኩም ወራህመቱላህ

ነሲሓ ቲቪ በቅርቡ ከኢትዮ ሳት [NSS-12] መውጣቱን ተከትሎ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወዳጆቻችን ነሲሓን ወደ ኢትዮሳት የማስመለስ ቅስቀሳ መጀመራቸውን አስተውለናል...
አላህ ኸይር ጀዛ ይክፈላቸው።

የነሲሓ ቲቪ አስተዳደር ይህንን ውሳኔ ሲወስን፤ ከዶላር መናር ጋር በተያያዘ የሳተላይት ክፍያ አቅምን በከፍተኛ ደረጃ የፈተነ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሲሆን በሁለቱም ሳተላይቶች ላይ መቀጠሉ አዳጋች ሆኗል። ስለሆነም አማራጮችን በመገምገም በናይል ሳት ላይ ብቻ መቀጠሉ የተሻለ ሆኖ አግኝተነዋል።

የተሻለ የሳተላይት ክፍያ መገኘቱ በናይልሳት ብቻ እንድንቀጥል ካደረጉን ምክንያቶች አንዱ ሲሆን፤ ከሀገር  ውጭ ያሉ ተመልካቾች እንዲያገኙን ማስቻሉም ሌላኛው ምክንያት ነው። የሐረመይን ቻነሎችን ጨምሮ በርካታ ጠቃሚ ዲናዊ ቻነሎች በናይልሳት መገኘታቸውም ለውሳኔው ተጠቃሽ ምክንያት ነው። ስለሆነም የነሲሓ ቤተሰቦች ዲሻቸውን ወደ ናይል ሳት በማዞር ኢስላማዊ እውቀት እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

በናይል ሳት የሚተላለፈውን ስርጭት ቀጣይነት ለማረጋገጥና የፕሮግራሙን ጥራት ለማስጠበቅ በነሲሓ ወዳጆች የተጀመረው የድጋፍ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠሉ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

ወሰላሙ አለይኩም

ኢሊያስ አወል
ሥ/አስኪያጅ

@nesihatv
ዲን እየተማሩ ነውን?

ኢስላም ከማንኛውም ነገር በፊት ዕውቀትን በመገብየት ላይ አደራ ይላል፡፡ ምክንቱም የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዕውቀትን መሰረት ያላደረጉ ከሆነ አላዋቂ ሳሚ ... እንደሚባለው ብሂል ከልማቱ የምንዘፈቅበት አዘቅቱ ያመዝናል፡፡  አንዳንዴም በኛ ሳይገደብ የኛው የጥፋት ረመጥ ይቀጥልና ሌሎችን እኛ የሰመጥንበት አዘቅጥ ውስጥ እንዲዋኙ የጥፋት ጀልባ እና መቅዘፊያ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ 
       
ቁርአን ስለ እውቀት ፋይዳዎችና ስለ አዋቂዎች ደረጃ ብዙ ይላል። ዓዋቂው አምላካችን ስለ እውቀት ባለቤቶች ከፍ ያለ ደረጃ ዓዋቂዎች በሚገነዘቡት መልኩ እንዲህ ይላል፡-

يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ [٥٨:١١]
«አላህ ከናንተ እነዚያ ያመኑትንና እነዚያ ዕውቀት የተሰጡትን በደረጃ ከፍ ያደርጋል» ሙጃደላህ፡11
                           
ታላቁ ሶሃብይና የቁርአን ተፍሲር ዓዋቂ ዓብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንዲህ ሲል የአንቀፁን መልዕክት የሚያጠናክር ንግግር አላቸው «የተማሩ ሰዎች ደረጃ ከተራው ሙዕሚን ሰባት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡ ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ ያለው ርቀት የአምስት መቶ ዓመት ርቀት ይሆናል»

በሌላ የቁርአን አንቀፅ አላህ እንዲህ ይላል፡-

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ [٣٥:٢٨]
«አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው»  ፋጢር፡28

መልዕክተኛው (ﷺ)  እንዲህ አሉ፤ «ዕውቀትን ቅሰሙ አላህን የምትፈሩት ባወቃችሁት ልክ ነውና»

አዎን! የማያውቁትን አካል እንዴት ተገቢውን ፍራቻ ይፈሩታል?!

አላህ መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲጨምርላቸው እንዲጠይቁት ያዘዘው ብቸኛ ነገር ዕውቀት ነው! ከየት አመጣኸው ትይኝ ይሆናልና ማስረጃውን :-

وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا
«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ በል» 20፡114

የትኛውም የዕውቀት ደረጃ ላይ ብንገኝ በአላህ ከታገዝንና ጥረት ካደረግን ብዙ መሻሻል ይቻላልና አሁኑኑ ጥረት ማድረጉን እንጀምር።
አላህ  በኢስላማዊ ዕውቀት ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንል አንድ ያግዘን፤ እውቀትን ያግራልን። ልባችንን በቁርአን ያብራልን።

አሚን !
_
@abujunaidposts
💐ሴቶች ለሴቶች ወርሃዊ የሙሃደራ ፕሮግራም

በእለቱ በአላህ ፈቃድ 

▪️ስለተፈጠርንበት አላማ

▪️ቀጣይነት ስላለው ሰደቃ

የምንማማርበትን  ድንቅ ፕሮግራም አዘጋጅተን የእናንተን ውድ እህቶቻችንን መምጣት በናፍቆት እየጠበቅን ነው!

🗓 ቅዳሜ ጥቅምት 19 ፣2015

ከጠዋቱ 3:00-6:30

🕌 አድራሻ
ኢማሙ አህመድ መስጂድ
(አለም ባንክ)

መልእክቱን ሼር እናድርገው።

@darulhadis18
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር በዳሩል ሀዲስ የሸሪዓ ትምህርት እና የአረበኛ ቋንቋ ኢንስቲትዩት ሲያስተምራቸው የቆዩ 231ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።

እሁድ ከቀኑ 08፡30 ጀምሮ

በድጋሚ እሁድ ምሽት 2፡30 ላይ በነሲሓ ቲቪ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን ::

ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

@nesihatv
https://www.tg-me.com/Maahad_DarulHdith
👆ይህ በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር የዳሩል ሀዲስ የሴቶች ክፍል ኦፊሺያል ግሩፕ ሊንክ ነው።

ጆይን በማድረግ ይቀላቀሉን ስለ ዳሩል ሀዲስ ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።

@darulhadis18
"በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ"(አል-ማኢዳ 2)

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
የዳረ'ል ሐዲሥ ኢስላማዊ ኮሌጅ

አስ'ሰላም ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ

  ላለፉት 14 አመታት ኢስላማዊ ዕውቀትን በተለያዩ ደረጃዎች ላሉ ተማሪዎች በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ሲሰጥ የቆየው የዳረል ሐዲሥ ኢኒስቲትዩት ሲያስተምረበት የቆየውን ህንፃ ግንባታውን በማስፋፋት ወደ ተሻለ እርከን ከፍ ለማድረግ ስራዎችን በትጋት  እየሰራ ይገኛል።

በጥንስሱ ላይም ይህንን መርከዝ እውን ለማድረግ የሴቶች የጎላ ተሳትፎና ሚና ከፍተኛ እንደነበር አይዘነጋም።

እነሆ!  በማስፋፋቱ ሂደቱ የመጨረሻ እርከን ላይም የተለመደውን አሻራችሁን ታሳርፉ ዘንድ በተዘጋጀው የሴቶች ዳእዋና የጉብኝት ፕሮግራም እርስዎም እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

እሁድ ህዳር 4፣2015 ከጠዋቱ 3:00
   
አድራሻ :-18 አደባባይ አካባቢ የቀድሞ አል-አፊያ ት/ቤት በሚገኘው የኢብኑ መስኡድ መርከዝ

https://www.tg-me.com/Maahad_DarulHdith
"በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ"
አል-ማኢዳ 2

ነሲሓ ቲቪን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ የዳእዋ ስራዎችን በመስራት ህብረተሰቡን እየኻደመ ያለው
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር የግንባታ ማስፋፊያ የመጨረሻ እርከን ላይ አሻራዎትን ያሳርፉ።

1000506109683
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
ዳሩል ሀዲስ
ንግድ ባንክ

📌 ወዳጅ ዘመድዎን ወደዚህ ኸይር በማመላከት የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የመልካም ስራ ጥሪ ቀርቧል

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር 18 አደባባይ አካባቢ ተገንብቶ ለረጅም ግዜ አገልግሎት የሰጠውን መርከዝ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ የግንባታ ማስፋፊያና ማሻሻያ በማድረግ ላይ እንገኛለን። በአላህ ፈቃድ ሲጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ይሰጣል። መስጂድ፣ ላይብረሪ፣ የወንዶች ኮሌጅ ከነማደሪያው፣ የሴቶች ኮሌጅ፣ የሒፍዝ ማእከል፣ የነሲሓ ቲቪ ስቱድዮና ቢሮዎችን ያካትታል። ተባብረን እናሳካው!

በንግድ ባንክ ለመርዳት 444 አጭር ቁጥር አካውንታችን ነው።

መርከዙ የለበትን ሁኔታ ለመጎብኘትና
ለበለጠ መረጃ +251972757575

Ibnu Masoud islamic center

@merkezuna
📢ተጋብዛችኋል!

◾️በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር የተዘጋጀ ልዩ የሴቶች ለሴቶች ዲን መማማሪያ መድረክ።

☑️በእለቱ የሚዳሰሱ ርእሶች:-

❶ ተቅዋ(አላህን መፍራት)

❷ ትርፋማው ንግድ

🗓ታህሳስ 1፣2015

🕘ቅዳሜ ከጠዋቱ 3:00 -6:30

አድራሻ :ቤተል ጥቁር አባይ አልአፊያ ት/ቤት

📮 እናቶችና እህቶች ይህን ምርጥ ፕሮግራም ይታደሙ ዘንድ መልእክቱን ሼር ያድርጉት።

📱0904366666
Teleg. https://www.tg-me.com/Maahad_DarulHdith

@darulhadis18
የተከበራችሁ የነሲሓ ቲቪ ቤተሰቦች

የነሲሓ ቲቪ ስርጭት ይመለስ ዘንድ መላው የነሲሓ ቤተሰቦች ጠንካራ ርብርቦሽ በማድረግ ላይ ናቸው። ኢን ሻ አላህ በናንተ ትብብር በቅርቡ ይመለሳል።

ነሲሓ ቲቪ ለኢስላማዊ እውቀትና ዳዕዋ ወሳኝ መድረክ ነውና በዚህ ጣቢያውን በዘላቂነት  በምናስቀጥልበት ዘመቻ ኃላፊነትዎን ይወጡ። ሁላችሁም የተቻላችሁን ድጋፍ እንደምታደርጉ ተስፋ እናደርጋለን።

ጣቢያውን በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚደረገውን ዘመቻ በማገዝ ከጎናችን ለቆማችሁ ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

የሚከተሉትን አካውንቶች በመጠቀም የበኩልዎን ድጋፍ ያድርጉ።
ባረከላሁ ፊኩም!

– ንግድ ባንክ 444 ወይም 1000145615929

– ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል 1445091300001

– አቢሲኒያ ባንክ
73169062

– ንብ ኢንተርናሽናል 7000025634638

– ዘምዘም ባንክ 7122

– አዋሽ ባንክ 01410844116300

https://www.tg-me.com/nesihatv
📢ተጋብዛችኋል!

◾️በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ቤተል ቅርንጫፍ የተዘጋጀ ልዩ የሴቶች ለሴቶች ዲን መማማሪያ መድረክ።

☑️በእለቱ የሚዳሰሱ ርእሶች:-

❶ እምነታችን

❷ ኢስላማዊ ቤተሰብ

🗓ጥር 20፣2015

🕘ቅዳሜ ከጠዋቱ 3:00 -6:30

አድራሻ :ቤተል አደባባይ ከተቅዋ መስጂድ ፊት ለፊት ንግድ ባንክ ያለበት ህንጻ

📮 ይህን ምርጥ ፕሮግራም እህቶች ይታደሙ ዘንድ መልእክቱን ሼር ያድርጉት።

Teleg. https://www.tg-me.com/Maahad_DarulHdith

@darulhadis18
📢መልካም ዜና ለወላጆች

▫️ለልጅዎ ንፁህ ኢስላማዊ ተርቢያ ተርበዋል?

▫️የዚህ ዘመን ከባባድ የስብዕና ጥፋት ዘመቻዎች ማዕበል በልጆዎ ላይ ሰግተዋል?

▫️ልጆች የእረፍት ቀናቶችን በምን እንደሚያሳልፉ አሳስቦታል?

ነሲሓ ቲቪ ከመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ጋር በመተባበር በአይነቱ ልዩ የሆነ ታዳጊዎችን በመልካም ኢስላማዊ ተርቢያ የሚቀርፁ የአራት ቀን የታዳጊዎች ኮርስ አሰናድቶ ይጠብቆታል!

▪️ኮርሱ የሚሰጠው በሁለት ደረጃዎች ተከፍሎ ሲሆን፦

ደረጃ 1፡ ዕድሜያቸው ከ10-13

የሚሰጠው ትምህርት

1.የእምነት መሰረቶች (አቂዳ)
2.መልካም ስነምግባር(አኽላቅ)
3. ሶላት

ደረጃ 2፡ ዕድሜያቸው ከ14-18

የሚሰጠው ትምህርት

1.አቂዳ
2.የአላህ ትእዛዞች የምንፈጽምበት ስርአት
3.ማህበራዊ ሚዲያና ታዳጊዎች ጥፋትና ጉዳት እንዲሁም እርምትና ልማት

ጁሙኣ:- ሴቶችን ብቻ የተመለከተ ልዩ ሙሀደራ

🗓ቀን ከሰኞ ጥር 22 - 25፣2015

🕘ጠዋት ከ2:30-6:30

🕌 አድራሻ
ለወንዶችና ሴቶች፦ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስኡድ ዋና ቢሮ

ለሴቶች ብቻ፦ቤተል አደባባይ ንግድ ባንክ ያለበት ፎቅ ላይ

ለተጨማሪ መረጃ

18 ማዞሪያ
ለሴቶች 0904366666
ለወንዶች 0972757575

ቤተል(ለሴቶች)
093 048 4284  ይደውሉ

⚠️ወላጆች ልጆቻችሁን በመላክ ኃላፊነታችሁን ተወጡ!

መልእክቱን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን❗️

https://www.tg-me.com/darulhadis18
📢ነገ ተጋብዛችኋል(ለሴቶች)

የኮርስ መዝጊያ ልዩ ፕሮግራም


🌱አዳቡ'ል መርኣቱ ሷሊሓ🌱

☞"የመልካም ሴት ስነምግባር" የተሰኘ በአይነቱ ልዩ የሆነ ሴቶችን ብቻ የተመለከተ የነድዋ ፕሮግራም!

📮በእለቱ የሚዳሰሱ ነጥቦች ፦

የሓያእ አሳሳቢነት

የሒጃብ አንገብጋቢነት

የኢኽቲላጥ አስከፊነት

⇉እንዲሁም ሌሎችም እጅግ አሳሳቢ የሆኑ ርዕሶች ተመርጠው በሰፊው ይዳሰሳሉ።

💧እውነተኛ የሙስሊም ሴት ስነ-ባህሪን ለመላበስ መሰል ፕሮግራሞችን በመገኘት እውቀትዎን ያዳብሩ!

 💦 ከዘመኑ የሴት ልጅ የማንነት አዘቅትና ፈተና ራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ!

የማይቀርበት ልዩ ፕሮግራም መሆኑን በሚገባ አስተዉለው ፕሮገራምዎትን ከወዲሁ ያመቻቹ

🗓ቀን ጁሙኣ ጥር 26 ፣2015

🕘ጠዋት ከ3:00-6:30

🕌 አድራሻ

☞ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስኡድ ዋና ቢሮ

☞ቤተል አደባባይ ንግድ ባንክ ያለበት ፎቅ ላይ

☞ለተጨማሪ መረጃ
18 መርከዝ ኢብኑ መስዑድ

0904366666

☞ቤተል

093 048 4284  ይደውሉ

መልእክቱን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን❗️

https://www.tg-me.com/darulhadis18
ኩኑዝ የማንነት እነፃ

የካቲት 12 /2015

❶ ጥያቄ እና መልስ
ሸይኽ ኢልያስ አህመድ

❷ ራስን መመርመር
በኡስታዝ መሀመድ ሀስን ማሜ

ቦታ: ከመርካቶ ወደ ጥቁር አንበሳ መሄጃ - ስልጤ መስጅድ


@merkezuna
✍🏻 ስለ ሻዕባን ወር አጫጭር ጥቆማዎች
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄


☞ በሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን

«ሙስሊሞች ሆይ ያለነው በሻዕባን ወር ላይ ነውና በዚህ ወር ዙርያ አንድ ስድስት ነጥቦችን በማውሳት ልንከተለው ስለሚገባን ግዴታችን እናብራራለን።

💥የመጀመርያው ነጥብ
የሻዕባን ወር ከሌሎች ወራት በተለየ ሁኔታ በፆም ይለያልን? አዎን ይለያል ። ምክንያቱም ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] «በዚህ ወር ፆም ያበዛሉ። ከወሩ ጥቂት ቀናት እስኪቀራቸው ወሩን ይፆሙት ነበርና።»
በዚህም ሱና መሰረት የአላህ መልእክተኛን [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] በመከተል በዚህ በሻዕባን ወር ፆም ማብዛት አለብን።

💥ሁለተኛው ነጥብ
የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ፆምን የተመለከተው ነው። ይህንን ቀን ለይቶ መፆምን የሚመለከቱ ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኙና ትክክለኛ ያልሆኑ ደካማ ሀዲሶች ተነግረዋል። በነዚህ ተመርኩዞ ይህንን ዒባዳ መፈፀም ደግሞ አይቻልም። ከነቢዩ ለመተላለፉ ባልተረጋገጠ ማንኛውም ነገር አላህን ማምለክ አይፈቀድም። በመሆኑም የሻዕባን አስራ አምስተኛው ቀንን ለይቶ መፆም የሌለ ነገር ነው። ከመልእክተኛው ለመገኘቱ መረጃ ከሌለ ደግሞ ቢደዐ ነው።

💥ሶስተኛው ነጥብ፤ የሻዕባን ወር አስራ አምስተኛው ቀን ሌሊት ትሩፋትን ይመለከታል።
ልክ ቀኑን መፆም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለው ሁሉ ለሌሊቱም ከሌሎች ሌሊቶች በላጭ ነው ተብለው የተነገሩት ሀዲሶች ከነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለመነገራቸው ትክክለኛ መረጃ የሌላቸው ደካማዎች ናቸው።
ስለሆነም የሻእባን አጋማሽ ሌሊት ልክ እንደ ረቢዕ ወር ሌሊት፣ እንደ ረጀብ ወር ሌሊት እንጂ የተለየ ነገር የለውም። ተነገረ የተባለውም መረጃ ቀድሜ እንደገለፅኩት ደካማዎች ናቸው።

💥አራተኛው ነጥብ
ይህችን የአስራ አምስተኛዋን ሌሊት ለየት አድርጎ ዝግጅት ፈጥሮ ማሳለፍ ቢደዐ ነው። ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለየት አድርገው ያሳዩን፣ ሌሊቱን የሚሰገድ አምልኮትም ዝግጅትም የለምና። ስለዚህ ምሽቷ ልክ እንደ ሌሎች ምሽት ናት። አንድ ሰው ከዚያች ሌሊት በፊትም የለይል ሰላት መስገድ ልምዱ ከነበረ በዚያች ሌሊትም ተነስቶ መስገዱ ልክ እንደበፊቱ ነውና ችግር የለውም። ካልሆነና በፊት የማይሰግድ ከነበረ ዛሬ በሻዕባን "ለይለቱ ኒስፍን" ለየት አድርጎ መስገድ የለበትም። ምክንያቱም ከአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኘ ተግባር ነውና። ከዚህም የከፋው ደግሞ አንዳንዱ ሰው የሆነ ያህል ረከዓ በዚህ ምሽት ይሰገዳል በሚል ለየት ያደርገዋል። ይሁንና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህንን ምሽት ነጥሎ ለየት ማድረግ ስላልተገኘ ይህችን ምሽት በሰላት ልዩ አናደርግም።

💥አምስተኛው ነጥብ
የአላህ ሱብሃነሁ ለነገሮች የሚያደርገው ውሳኔ በሻዕባን አስራ አምስተኛዋ (አጋማሽ) ምሽት ነውን

ምላሹም አይደለም ሲሆን፤ ምሽቷም የመወሰኛይቱ ሌሊት [ለይለቱል ቀድር] አይደለችምና ነው። ምክንያቱም "ለይለቱል ቀድር" በረመዳን ውስጥ የምትገኝ ምሽት ናት። ሃያሉ አላህ እንዳለው፤
”إنا انزلناه“
"እኛ አወረድነው" ማለትም ቁርኣንን ለመጀመርያ ግዜ ያወረድነው ማለቱ ነው። ይህም ሙሉ ምዕራፉ ሲነበብ እንዲህ ይላል፤
إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ ﴿١﴾ وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ ﴿٢﴾ لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ ﴿٣﴾ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ ﴿٤﴾ سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ ﴿٥﴾
Al-Qadr☞ القدر:- [1-5]

[እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡ (1)መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? (2)መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡ (3) በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡ (4) እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡(5)]
ይህ ክስተትና ምሽቱም መቼ እንደሆነ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፤
(شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖوَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّـهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّـهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ) البقرة:- 185
[(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡ (185)]

በዚህም መረጃ መሰረት ለይለቱል ቀድር ማለትም ፈጣሪያችን አላህ ለማንኛውም ነገር ሁሉ አመታዊ ውሳኔ የሚሰጥበት ምሽት በረመዳን ወር ውስጥ የምትገኝ አንዲት ሌሊት መሆኗን እንረዳለን። ምክንያቱም ሌሊቷ ቁርኣን የወረደባት ሌሊት ነች ። ቁርኣን ደግሞ የወረደው በረመዳን ወር ነውና የመወሰኛይቱ ምሽትም የምትገኘው በረመዳን እንጂ በሌላ ወር አይደለም። ስለሆነም የሻዕባን አጋማሽ ሌሊት "ለይለቱል ቀድር" የመወሰኛይቱ ምሽት አይደለችም። በዚያች ሌሊትም ለአመቱ የሚሆን ምንም የሚወሰን ነገር የለም።

💥ስድስተኛው ነጥብ፦ የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ላይ አንዳንዶች ምግብ አዘጋጅተው ለድሆች በሚል የሚያከፋፍሉትና የእናት እራት፣ የአባት እራት ወይም የወላጆች እራት የሚሉት [እንዲሁም ባገራችን የእህል ዘሮችን ባንድ ላይ ሰብስቦ በመቀቀልና ከዚያም መጀመርያ ግቢ ውስጥና ውጪም በመበተን አመቱ የጥጋብ የርጋታ ይሁንልን የሚሉት] ሁሉ ከነቢዩ ያልተላለፈልን ከሰሃቦችም ሪድዋኑላሂ አለይሂም ያልተገኘ መጤ የሆነ ቢድዐ ነው።

👆 እነዚህን ስድስት ነጥቦች ጠቅሼ ብቆጥራቸውም ሌሎች ላብራራቸው የሚገቡ ሆነው ያለፍኳቸው እንዳሉ ግልፅ ነው። አላህ እኛንም እናንተንም ሱናን የሚያሰራጩ፣ ቢድዐን የሚያስጠነቅቁና ተመርተው የሚመሩ (ቅን ሆነው የሚያቀኑ) ያድርገን። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በጁምዓ ኩጥባቸው ወቅት እንደገለፁት ከምሪቶች ሁሉ በላጩ የሳቸው ምሪት ነውና ቅኑን መንገድ የሚከተሉ፣ በሳቸው አመራርም የሚመሩ ያድርገን። «በማስከተል፤ ከንግግሮች ሁሉ በላጩ የአላህ ኪታብ ነው። ከአመራሮች ሁሉ በላጩም የሙሀመድ ምሪት ነው። መጥፎ ጉዳይ ማለት መጤዎቹ ናቸው። ሁሉም ፈጠራዎች ጥመት ናቸውና።»ብለዋል።
🍀🍀
በታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን [ረሂመሁላህ]
__
3 ሻዕባን 1437/ 11 ሜይ 2016
ትርጉም፦ አቡፈውዛን
•┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈•

www.facebook.com/tenbihat
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱ፡

📢ልዩ ፕሮግራም ለልዩዎች

በቅድሚያ እንኳን ደስስ አላችሁ!

እንኳን አብሮ ደስ አለ … ግን ማንን ነው?

በ2014 የት/ርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ በምርጥ ውጤት ወደ ከፍተኛ ት/ርት ተቋማት የተመደባችሁ እና ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለምትሄዱ ሙስሊም ተማሪዎች እናንተን ነው!

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!

እነሆ የምስራች!

ለዚህ ታላቅ ውጤታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዛችሁት የምትሄዱት ጣፋጭ ስንቅ አዘጋጅተናልና መጥታችሁ የድርሻችሁን ውሰዱ!

ምን?

አዎ! እመኑን! ተማሪዎች በዚህ ወሳኝና ልዩ ፕሮግራም ለሁለቱም ዓለም ስኬታማ ህይወት የሚረዳችሁን ስንቅ ሰንቃችሁ ትመለሳላችሁ!


ማን ነው ያዘጋጀው? መቼ?  … ስንት ሰዓት? … የት ነው?

አዘጋጅ: ኢብን መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

ቀን: የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 18-2015

ሰዓት: ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ

አድራሻ: 18 ማዞርያ በሚገኘው መርከዝ ኢብን መስዑድ

ማስታወሻ!

ወላጆችም ልጆችዎን ወደዚህ ድንቅ ዝግጅት በመላክ የህይወት ስንቅን ያውርሱ።

https://www.tg-me.com/darulhadis18
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
🌤አሰደሳች ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ 
አል-ኑር የቁርአን ሂፍዝ እና የተርቢያ ማእከል ሸሪአዊ ትምህርት ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በጥራትና አመቺ በሆነ አቀራረብ ባሉበት ሆነው የሸሪአ ትምህርቶችን ይከታተሉ ዘንድ  ዝግጅቱን አጠናቆ ወደናንተ ብቅ ብሏል።

📚የሚሰጡት የትምህርት ዘርፎች

❶ አቂዳ
❷ ሀዲስ
❸ ፊቂህ
❹ ሲራ
❺ ሉጋ(አረብኛ ቋንቋ)

➪ትምህርቱ በኡስታዝ ሰኢድ ግዛው የሚሰጥ ሲሆን ተማሪው የመድረሳውን ህግ ማክበር፣ በሚላኩት ፒዲኤፍ በመታገዝ ኦዲዮዎችን ማዳመጥና ፈተናዎችን በጊዜው መስራት ይጠበቅባቸዋል።

➪ኮርሱን በብቃት ላጠናቀቁ ተማሪዎች ሰርተፊኬት የምንሰጥ ሲሆን በመጀመርያ ዙር የምንቀበለው ተማሪ ውስን በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ።

➪ምዝገባው የሚካሄደው ማስታወቂያው ከተለቀቀበት እስከ መጋቢት5 ነው

ለበለጠ መረጃ ዋናው ቻናል https://www.tg-me.com/nurmerkeznew

ቴሌግራም @IknowLifeisshort

0975258540
0960297488

ለመመዝገብ 👇👇👇

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSc3mf5DqSNs5ghWWBv9sHEXnLHe1HmfSEAzgofkJkzy7gXjBQ/viewform?usp=sf_link

🌸🍃🌸🍃..........🌸🍃🌸🍃
ሙስሊሟና የረመዳን ፆም ቀዳ
አቡ ጁነይድ ሳላህ አሕመድ
🗓 ሙስሊሟና የረመዳን ፆም ቀዷ

🎙አቡ ጁነይድ ሳላሕ አሕመድ

👌 አጭር ወቅታዊ ጥቆማ!

🔗 Share Link
https://www.tg-me.com/abujunaidposts/328
----------------
📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts
2025/10/25 07:21:26
Back to Top
HTML Embed Code: