Telegram Web Link
ዲን እየተማሩ ነውን?

ኢስላም ከማንኛውም ነገር በፊት ዕውቀትን በመገብየት ላይ አደራ ይላል፡፡ ምክንቱም የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዕውቀትን መሰረት ያላደረጉ ከሆነ አላዋቂ ሳሚ ... እንደሚባለው ብሂል ከልማቱ የምንዘፈቅበት አዘቅቱ ያመዝናል፡፡  አንዳንዴም በኛ ሳይገደብ የኛው የጥፋት ረመጥ ይቀጥልና ሌሎችን እኛ የሰመጥንበት አዘቅጥ ውስጥ እንዲዋኙ የጥፋት ጀልባ እና መቅዘፊያ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ 
       
ቁርአን ስለ እውቀት ፋይዳዎችና ስለ አዋቂዎች ደረጃ ብዙ ይላል። ዓዋቂው አምላካችን ስለ እውቀት ባለቤቶች ከፍ ያለ ደረጃ ዓዋቂዎች በሚገነዘቡት መልኩ እንዲህ ይላል፡-

"يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ" [٥٨:١١]
«አላህ ከናንተ እነዚያ ያመኑትንና እነዚያ ዕውቀት የተሰጡትን በደረጃ ከፍ ያደርጋል» ሙጃደላህ፡11
                           
ታላቁ ሶሃብይና የቁርአን ተፍሲር ዓዋቂ ዓብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንዲህ ሲል የአንቀፁን መልዕክት የሚያጠናክር ንግግር አላቸው «የተማሩ ሰዎች ደረጃ ከተራው ሙዕሚን ሰባት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡ ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ ያለው ርቀት የአምስት መቶ ዓመት ርቀት ይሆናል»

በሌላ የቁርአን አንቀፅ አላህ እንዲህ ይላል፡-

"إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ" [٣٥:٢٨]
«አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው»  ፋጢር፡28

መልዕክተኛው (ﷺ)  እንዲህ አሉ፤ «ዕውቀትን ቅሰሙ አላህን የምትፈሩት ባወቃችሁት ልክ ነውና»

አዎን! የማያውቁትን አካል እንዴት ተገቢውን ፍራቻ ይፈሩታል?!

አላህ መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲጨምርላቸው እንዲጠይቁት ያዘዘው ብቸኛ ነገር ዕውቀት ነው! ከየት አመጣኸው ትይኝ ይሆናልና ማስረጃውን :-

"وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا "
«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ በል» 20፡114

የትኛውም የዕውቀት ደረጃ ላይ ብንገኝ በአላህ ከታገዝንና ጥረት ካደረግን ብዙ መሻሻል ይቻላልና አሁኑኑ ጥረት ማድረጉን እንጀምር።
አላህ  በኢስላማዊ ዕውቀት ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንል አንድ ያግዘን፤ እውቀትን ያግራልን። ልባችንን በቁርአን ያብራልን።

አሚን !
_
@abujunaidposts
አላህ መልካም ለሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል

📌 ታላቅ የምስራች ለኢስላማዊ እውቀት ፈላጊ ሴቶች በሙሉ

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ የሸሪዓ ትምህርቶችና የዐረብኛ ቋንቋ መማሪያ ኢንስቲትዩት  እድሜያቸው  ከ15 አመት በላይ ለሆኑ ሴቶች የዲን ትምህርት ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ መጀመሩን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው


1⃣ቁርአን (ከሰኞ -ጁሙኣ)

▪️የቁርአን ሂፍዝ(ሙሉ ቀን)*

▪️ቁርአንን በተጅዊድ (ከ3:00-6:30)*

▪️ለጀማሪዎች የቁርአን ንባብ *
ጠዋት ከ3:00-6:30
ከሰአት ከ8:00-10:00
አስር    ከ10:00-12:00

*ከመሰረታዊ የዲን ትምህርት ጋር

2⃣የኪታብ ቂረኣ እና አረብኛ ት/ት
(3:00-6:30)

▪️ የሁለት አመት የሰርተፊኬት ፕሮግራም(ከሰኞ-ጁሙኣ)

▪️በሳምንት ቅዳሜ ብቻ

🗓 የምዝገባ ጊዜ፦ ከሰኞ እስከ ጁሙዓ
ከነሐሴ15- 30/2015

የምዝገባ ሰአት ከ3:00_7:00


🕌 የምዝገባ ቦታ፦ 18 አካባቢ በሚገኘው መርከዝ

☎️ ለበለጠ መረጃ፦
በስልክ ቁጥር  0904 36 66 66
ወይም 0967 67 18 91 ይደውሉ
  
⚠️መልእክቱን ሼር በማድረግ ከአጅሩ እንቋደስ!

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
@darulhadis18
📣በምዝገባ ላይ(ለሴቶች)

"አላህ መልካም ለሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል”

ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር አዲስ አበባ 18 በሚገኘው መርከዝና በቤተል ቅርንጫፍ ለ2016 የትምህርት ዘመን የዲን ትምህርቶችን ለመስጠት ምዝገባ ጀምሯል።

የሚሰጡ ትምህርቶች
📖 ቁርአን
🔅 በነዘር (ለጀማሪዎች)
🔅በተጅዊድ
🔅በሂፍዝ

📚እንዲሁም የተለያዩ ኪታቦች ቂራአት

🕥የሰአት አማራጭ

▪️ጠዋት፣ከሰአት፣ከአስር
በኋላ

▪️ለተማሪና ለሰራተኛ ቅዳሜ ጠዋት ወይም ከሰአት

ለበለጠ መረጃ፦
ለ18☎️ 0904 36 66 66
ወይም 0967 67 18 91

ለቤተል☎️0911062499/
0913840323 ወይም 0911692377 ይደውሉ።

⚠️መልእክቱን ሼር በማድረግ የበኩላችንን አስተዋጽዖ እናድርግ።

https://www.tg-me.com/darulhadis18
🌸ቅዳሜ ተጋብዛችኋል🌸

የክረምት ትምህርት መዝጊያ የሙሀደራ ግብዣ ለሴቶች

ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር በክረምቱ በዋናው መርከዙና በቅርንጫፎቹ ሲሰጥ የቆየውን ትምህርት መጠናቀቁን ምክኒያት በማድረግ የተዘ ጋጀ ልዩ መድረክ።

▪️የሚዳሰሱ ርእሶች

⭐️የተውሂድ አሳሳቢነትና ፍሬዎቹ

⭐️የኢስላም ውበት

🗓 የፊታችን ቅዳሜ ጿግሜ
4፣2015

ከ3:00-6:30

🕌18 አካባቢ በሚገኘው መርከዝ

⚠️መልእክቱን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን!

https://www.tg-me.com/darulhadis18
«አል‐ዐቂደቱ አል‐ዋሲጢያህ» የኪታብ ቂራአት ማሟያ በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

📌 ከእሮብ መስከረም 2/2016 ጀምሮ  4:00 ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ ትምህርት

🔖 ባሳለፍነው ክረምት በነሲሓ የዒልም ቅፍለት ኮርስ ቁ.10 መካሄዱ ይታወሳል። 
ይህ ደርስ በወቅቱ ያልተጠናቀቀውን የ አል‐ዐቂደቱ አል‐ዋሲጢያህ ማብራሪያ ለማጠናቀቅ ያለመ ነው። አላህ ይጠብቀው፤ ለኛም የዲን ዕውቀትና ግንዛቤን ይለግሰን።

ቦታ:– 18 አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (መርከዝ)

____
www.tg-me.com/merkezuna
የመርከዝ ፕሮጀክት... የትብብር ፍሬ!

ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር፤
ከ2001 አብነት አካባቢ ከሁለት በጎ ፈቃደኛ ወንድማማቾች ባገኘው ትንሽ ቤት ውስጥ ኢስላማዊ ቤተ መፃህፍት፣ ነሲሓ ኢስላማዊ ስቱዲዮ፣ ዳሩል ሐዲስ የሰርተፊኬትና የዲፕሎማ ፕሮግራሞች፣ መስማት የተሳናቸው ወገኖችን ጨምሮ በርካታ የትምህርት ፕሮግራሞችን እውን በማድረግ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ሆኖም በጠባብ ቦታ ላይ የተጀመሩትን እንቅስቃሴዎች ማሳለጥ ይችል ዘንድ፤ በተለምዶ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቦታ ለመግዛትና ቋሚ የመርከዝ ህንፃ ለመገንባት ፕሮጀክት ነድፎ ህዝበ ሙስሊሙን በማስተባበር ቦታ ገዝቶ ግንባታ ማከናወን ጀመረ።

ከዚያ በፊት በአብዛኛው መሰል ፕሮጀክቶች የሚፈፀሙት በውጭ ድጋፍ ስለነበር የመርከዙ እቅድ ለአንዳንዶች የማይሳካ ህልም መስሏቸውም ነበር። ሆኖም በአላህ ፈቃድ በአጭር ግዜ ውስጥ ውጥኑ የብዙዎችን ቀልብ በመሳብ የአስተሳሰብ ለውጥ ከማምጣቱ ባሻገር በራስ አቅም ዳዕዋን መደገፍ እንደሚቻል ህያው ማሳያ ሆኖ ነበር። እጅግ አስደናቂ በሆነ ተነሳሽነትና የአላማ አንድነት ከሴት ተማሪዎች እሰከ ባለሀብቶች ባደረጉት ድጋፍ ሁለት ወለል ማጠናቀቅ ተችሏል።

በወቅቱ የዳዕዋ ተቋማት ላይ የተጋረጡ አደጋዎች፣ ጫናዎችና እጅግ ፈታኝ ሂደቶች ስለነበሩ በትዕግስትና በጥበብ ማለፍን ይጠይቅ ነበር። ስለሆነም በከፊል ከተጠናቀቀው ግንባታ ከፊሉን በማከራየት በአብነት ለሚገኘው መርከዝ ቋሚ የዳዕዋ ድጋፍ ማግኘት ተችሏል። የተወሰኑ ወለሎች ቢቀሩትም ግንባታውን ከፍ ወዳለ ደረጃ በማሸጋገርና የተገነቡ ወለሎችን በዘመናዊ ሁኔታ በማጠናቀቅ መስጅድ፣ የሙሐደራትና ኮርሶች አዳራሽ፣ ቤተ መፃህፍት በማሟላት የታህፊዝና የሴቶች ማዕሐድ ከጥር 1/2008 ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ሲሰጥ ቆይቷል። በሁለቱም መርከዞች በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተምረዋል። ይህ መርከዝ ከምስረታው ጀምሮ ለሴቶች ከፍተኛ ትኩረት የሰጡ የትምህርት የተርቢያና የስልጠና መርሐ ግብሮችን ተፈፃሚ አድርጓል።

አሁንም በአላህ ፀጋና በረከት ቀሪውን ግንባታ በማድረግ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ በቀጣይ ኢስላማዊ ኮሌጅን ጨምሮ በርካታ ፕሮግራሞችን ማካሄድ የሚያስችል ሆኗል።

እሁድ መስከረም 13 /2016 ረፋዱ ላይ ለፕሮጀክቱ እውን መሆን አሻራቸውን ያኖሩ ሁሉ በመርከዙ በመገኘት የልፋታቸውን መልካም ፍሬ የሚያዩበት፣ ለዋለላቸው ፀጋ አላህን የሚያመሰግኑበት ቀን ነው።

وَمَا بِكُم مِّن نِّعۡمَةࣲ فَمِنَ ٱللَّهِ
(ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ነው) አል-ነሕል: 53

የብዙ ጀግኖች አሻራ አርፎበት ለስኬት የበቃው ይህ ፕሮጀክት፤ ለቀጣይ የዳዕዋ ጉዟችንና ወኔ ለሚጠይቁ ፕሮጀክቶቻችን ተግባራዊ ምሳሌ ስለሆነ ለቀጣይ ስኬቶች እንዘጋጅ።

አልሐምዱሊላህ!

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
መስከረም 7/2016
____
🕌 ibnu Masoud islamic Center
@merkezuna
ማስታወቂያ

ለኢብኑ መስዑድ የ18 እና የቤተል ተማሪዎች በሙሉ

ጁሙኣ እና ቅዳሜ መንገድ ዝግ ስለሚሆን በእለቱ ሁለቱም መድረሳ ዝግ ይሆናል።
🪸ወርሀዊ የሙሀደራ ግብዣ ለሴቶች🪸

እንዳያመልጥሽ❗️

☀️የአካላችን ንጉስ ስለሆነው የምንማማርበት ልዩ መድረክ

🍃እሁድ ጥቅምት 4፣2016

🍃ከጠዋቱ 3:00 - 6:30

🍃18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

⚠️መልእክቱን ሼር በማድረግ ዳእዋን ተደራሽ ያድርጉ

https://www.tg-me.com/darulhadis18
🪷መልካም እድል🪷

🍃ከጠዋቱ 1:00-2:30 ቁርአን ለመቅራት ለምትፈልጉ ሴቶች

▪️ትምህርቱ  ሰኞ ጥቅምት 12፣2016  የሚጀመር ይሆናል።

▪️ለበለጠ መረጃ 0904346666/
0967671891 ይደውሉ

▪️አድራሻ: 18 አካባቢ በሚገኘው መርከዝ
ኢብኑ መስዑድ

📬 እህቶች ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ መልእክቱን ሼር እናድርገው!
                                  🪷🍃🪷🍃🪷🍃

https://www.tg-me.com/darulhadis18
📢የማይቀርበት ልዩ ፕሮግራም ለሴቶች

➪በቤተሰብዎ፣ በግዜዎ፣በገንዘብዎ፣ በልጅዎ፣ በስራዎ በአጠቃላይ በህይወትዎ በረካን (ረድዔትን) አጥተዋል?

ዘመኑ "በረካ የመነመነበት ዘመን ነው!" የሚለው ስሞታ ዘውትር በጆሮዎ ያቃጭላል?

➪እነሆ! ለዚህ የዘመኑ ጠንቅ ለሆነው የበረካ መነፈግ መፍትሄ የሚሆን አስተማሪ ፕሮግራም ይዘን ቀርበናል።

በእለቱ
➤የበረካ ምንነት፣ በረካ ከየት ይገኛል ከማንስ ይፈለጋል? በረካን ያለ ቦታው መፈለግ ወደ ሺርክ የሚያዳርስ አደገኛ ወንጀል ነውን? የሚሉ ከበረካ ጋር የተቆራኙ ትክክለኛ ቁርኣናዊና ነብያዊ አስተምሮዎች ይዳሰሳሉ።

➤የበረካ አስፈላጊነት በህይወትዎ ምን ያህል ድርሻ እንዳለውም ይረዳሉ።

▪️ታዲያ ከፕሮግራሙ ይቀራሉ?  በፍፁም!

➤እሁድ ህዳር 9፣2016

➤ከጠዋቱ 3:00-:6:00

➤18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

▪️የፕሮግራሙ ታዳሚ በመሆን፣ እህቶችንም በመጋበዝ የእውቀትና የምንዳ ተካፋይ ይሁኑ!

https://www.tg-me.com/darulhadis18
📣አስደሳች ዜና ለእውቀት ፈላጊ እህቶች

☑️ዘወትር ከሰኞ እስከ ሀሙስ ከጠዋቱ 4:00-6:00

🌴የሚሰጡ ትምህርቶች

▫️አቂዳ(ሃኢያ ኢብን አቢ ዳውድ)
▫️ኡምደቱል አህካም
▫️ተፍሲር
▫️ተርቢያ

🌴ተማሪዋ ማሟላት ያለባት መስፈርት
1.ቁርአንን በነዘር የቀራች
2.መሰረታዊ የዲን ኪታቦችን የተማረች
3.አረብኛ ማንበብና መረዳት የምትችል
4.የመርከዙን ህግና ደንብ የምታከብር

ምዝገባ ከነገ ሰኞ ህዳር 17 ጀምሮ

ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ 18 በሚገኘው መርከዝ

ለበለጠ መረጃ 0904366666 ይደውሉ።

"አላህ መልካም ለሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል”

ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር

https://www.tg-me.com/darulhadis18
📢አጭር ኮርስ ሴቶች ለሴቶች

➤ሰኞና ሀሙስ ከ5:00-6:00

➪የሚሰጠው ትምህርት

➤ሴቶች በኢስላም ያላቸው ደረጃና ያለባቸው ሀላፊነት

"የልእልናሽ ጋሻ"
በሸይኽ በክር አቡ ዘይድ የ ተጻፈውና በአጭሩ የተዘጋጀው
"ተልኺስ ኪታብ ሒራሰቱል ፈዲላ"

➪ነገ ሀሙስ ህዳር 27 ይጀምራል!

የኪታቡ ኮፒ እዛው ይገኛል

➪ቦታ:18 በሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስዑድ

⭐️መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የዳእዋ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

https://www.tg-me.com/darulhadis18
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📢إعلان

محاضرة لفضيلة الدكتور الشيخ إبراهيم بن رافع الغامدي - للنساء،

بعنوان
▫️"عشرون عائقا في طلب العلم "
▫️في مركز ابن مسعود الإسلامي
▫️الوقت: ٥ صباحا بتوقيت إثيوبيا

https://www.tg-me.com/darulhadis18
📢ልዩ ግብዣ ለዕውቀት ፈላጊ ሴቶች

በአላህ ፈቃድ ነገ እሁድ ታህሳስ 14/2016

"عشرون عائقا في طلب العلم "

▪️እውቀት ፍለጋ ላይ የሚያጋጥሙ 20 እንቅፋቶችን የሚያብራራ ትምህርት

🫧ትምህርቱ በአረብኛ በሸይኽ ኢብራሂም አልጋሚዲይ ይሰጣል

🫧ትርጉም በአማርኛ በኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ

ሰአት :ጠዋት 5:00-6:15

ቦታ :18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

⚠️ለእህቶች መልእክቱን በማድረስ ጠቅመን እንጠቀም!

https://www.tg-me.com/darulhadis18
📢ልዩ ስንቅ ለታዳጊዎች የመጪው ጊዜ የኢስላም ተረካቢዎች!

⭐️ውድ ለሆኑት ትውልዶች! ለታዳጊ ተማሪዎች የተዘጋጀ  ለ 4 ቀናት የሚቆይ ድንቅ ኮርስ!

ኮርሱ በአላህ ፈቃድ፦

▪️መልካም ስነ ምግባርን የሚቀስሙበት
▪️ ተግባራዊ ኢባዳዎችን የሚማሩበት
▪️እምነታቸውን የሚያድሱበት ይሆናል።
 
▫️እድሜ ከ10 አመት በላይ

🗓 ከጥር 27- 30፣2016

🕘ጠዋት ከ2:30-6:30

ቦታ:-
1⃣ 18 ማዞሪያ በሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስዑድ
ለመመዝገብ፦
ለሴቶች- 0904 36 66 66
ለወንዶች- 0912 02 31 90

2⃣ ቤተል (የሴቶች ብቻ)
30 ሜትር ላይ በሚገኘው አልአፊያ ት/ቤት
ለመመዝገብ:-
+251911375952
+251911062499

⚠️ወላጆች ልጆችዎን ወደዚህ ድንቅ ዝግጅት በመላክ የህይወት ስንቅን ያውርሱ።

✔️እኛም መልዕክቱን በማስተላለፍ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

https://www.tg-me.com/darulhadis18
🌼ለሴቶች ነገ ቅዳሜ ተጋብዛችኋል🌼

⭐️ልዩ የኮርስ መዝጊያ ፕሮግራም
ለታዳጊዎች ለወጣቶችና ለወላጆች

"وصاحبهما في الدنيا معروفا"

በእለቱ የሚዳሰሱ ነጥቦች

ከኢስላማዊ አደብ
(ስነስር አት) የሚመደበውና
ሁላችንንም ስለሚመለከተው
የወላጆች ሃቅ

እና ሌሎችም ቁም ነገሮች

⚠️እውነተኛ የሙስሊም ሴት ስነ-ባህሪን ለመላበስ መሰል ፕሮግራሞችን ሴት ልጅዎንና
ራስዎን በማስገኘት እውቀትዎን ያዳብሩ !

🗓ቀን ቅዳሜ የካቲት 2 ፣2016

🕘ጠዋት ከ3:00-6:30

🕌 አድራሻ

☞ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስኡድ

መልእክቱን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን❗️

https://www.tg-me.com/darulhadis18
2025/10/22 14:47:58
Back to Top
HTML Embed Code: