Telegram Web Link
✍🏻 ስለ ሻዕባን ወር አጫጭር ጥቆማዎች
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄


☞ በሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን

«ሙስሊሞች ሆይ ያለነው በሻዕባን ወር ላይ ነውና በዚህ ወር ዙርያ አንድ ስድስት ነጥቦችን በማውሳት ልንከተለው ስለሚገባን ግዴታችን እናብራራለን።

💥የመጀመርያው ነጥብ
የሻዕባን ወር ከሌሎች ወራት በተለየ ሁኔታ በፆም ይለያልን? አዎን ይለያል ። ምክንያቱም ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] «በዚህ ወር ፆም ያበዛሉ። ከወሩ ጥቂት ቀናት እስኪቀራቸው ወሩን ይፆሙት ነበርና።»
በዚህም ሱና መሰረት የአላህ መልእክተኛን [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] በመከተል በዚህ በሻዕባን ወር ፆም ማብዛት አለብን።

💥ሁለተኛው ነጥብ
የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ፆምን የተመለከተው ነው። ይህንን ቀን ለይቶ መፆምን የሚመለከቱ ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኙና ትክክለኛ ያልሆኑ ደካማ ሀዲሶች ተነግረዋል። በነዚህ ተመርኩዞ ይህንን ዒባዳ መፈፀም ደግሞ አይቻልም። ከነቢዩ ለመተላለፉ ባልተረጋገጠ ማንኛውም ነገር አላህን ማምለክ አይፈቀድም። በመሆኑም የሻዕባን አስራ አምስተኛው ቀንን ለይቶ መፆም የሌለ ነገር ነው። ከመልእክተኛው ለመገኘቱ መረጃ ከሌለ ደግሞ ቢደዐ ነው።

💥ሶስተኛው ነጥብ፤ የሻዕባን ወር አስራ አምስተኛው ቀን ሌሊት ትሩፋትን ይመለከታል።
ልክ ቀኑን መፆም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለው ሁሉ ለሌሊቱም ከሌሎች ሌሊቶች በላጭ ነው ተብለው የተነገሩት ሀዲሶች ከነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለመነገራቸው ትክክለኛ መረጃ የሌላቸው ደካማዎች ናቸው።
ስለሆነም የሻእባን አጋማሽ ሌሊት ልክ እንደ ረቢዕ ወር ሌሊት፣ እንደ ረጀብ ወር ሌሊት እንጂ የተለየ ነገር የለውም። ተነገረ የተባለውም መረጃ ቀድሜ እንደገለፅኩት ደካማዎች ናቸው።

💥አራተኛው ነጥብ
ይህችን የአስራ አምስተኛዋን ሌሊት ለየት አድርጎ ዝግጅት ፈጥሮ ማሳለፍ ቢደዐ ነው። ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለየት አድርገው ያሳዩን፣ ሌሊቱን የሚሰገድ አምልኮትም ዝግጅትም የለምና። ስለዚህ ምሽቷ ልክ እንደ ሌሎች ምሽት ናት። አንድ ሰው ከዚያች ሌሊት በፊትም የለይል ሰላት መስገድ ልምዱ ከነበረ በዚያች ሌሊትም ተነስቶ መስገዱ ልክ እንደበፊቱ ነውና ችግር የለውም። ካልሆነና በፊት የማይሰግድ ከነበረ ዛሬ በሻዕባን "ለይለቱ ኒስፍን" ለየት አድርጎ መስገድ የለበትም። ምክንያቱም ከአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኘ ተግባር ነውና። ከዚህም የከፋው ደግሞ አንዳንዱ ሰው የሆነ ያህል ረከዓ በዚህ ምሽት ይሰገዳል በሚል ለየት ያደርገዋል። ይሁንና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህንን ምሽት ነጥሎ ለየት ማድረግ ስላልተገኘ ይህችን ምሽት በሰላት ልዩ አናደርግም።

💥አምስተኛው ነጥብ
የአላህ ሱብሃነሁ ለነገሮች የሚያደርገው ውሳኔ በሻዕባን አስራ አምስተኛዋ (አጋማሽ) ምሽት ነውን

ምላሹም አይደለም ሲሆን፤ ምሽቷም የመወሰኛይቱ ሌሊት [ለይለቱል ቀድር] አይደለችምና ነው። ምክንያቱም "ለይለቱል ቀድር" በረመዳን ውስጥ የምትገኝ ምሽት ናት። ሃያሉ አላህ እንዳለው፤
”إنا انزلناه“
"እኛ አወረድነው" ማለትም ቁርኣንን ለመጀመርያ ግዜ ያወረድነው ማለቱ ነው። ይህም ሙሉ ምዕራፉ ሲነበብ እንዲህ ይላል፤
إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ ﴿١﴾ وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ ﴿٢﴾ لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ ﴿٣﴾ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ ﴿٤﴾ سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ ﴿٥﴾
Al-Qadr☞ القدر:- [1-5]

[እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡ (1)መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? (2)መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡ (3) በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡ (4) እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡(5)]
ይህ ክስተትና ምሽቱም መቼ እንደሆነ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፤
(شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖوَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّـهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّـهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ) البقرة:- 185
[(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡ (185)]

በዚህም መረጃ መሰረት ለይለቱል ቀድር ማለትም ፈጣሪያችን አላህ ለማንኛውም ነገር ሁሉ አመታዊ ውሳኔ የሚሰጥበት ምሽት በረመዳን ወር ውስጥ የምትገኝ አንዲት ሌሊት መሆኗን እንረዳለን። ምክንያቱም ሌሊቷ ቁርኣን የወረደባት ሌሊት ነች ። ቁርኣን ደግሞ የወረደው በረመዳን ወር ነውና የመወሰኛይቱ ምሽትም የምትገኘው በረመዳን እንጂ በሌላ ወር አይደለም። ስለሆነም የሻዕባን አጋማሽ ሌሊት "ለይለቱል ቀድር" የመወሰኛይቱ ምሽት አይደለችም። በዚያች ሌሊትም ለአመቱ የሚሆን ምንም የሚወሰን ነገር የለም።

💥ስድስተኛው ነጥብ፦ የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ላይ አንዳንዶች ምግብ አዘጋጅተው ለድሆች በሚል የሚያከፋፍሉትና የእናት እራት፣ የአባት እራት ወይም የወላጆች እራት የሚሉት [እንዲሁም ባገራችን የእህል ዘሮችን ባንድ ላይ ሰብስቦ በመቀቀልና ከዚያም መጀመርያ ግቢ ውስጥና ውጪም በመበተን አመቱ የጥጋብ የርጋታ ይሁንልን የሚሉት] ሁሉ ከነቢዩ ያልተላለፈልን ከሰሃቦችም ሪድዋኑላሂ አለይሂም ያልተገኘ መጤ የሆነ ቢድዐ ነው።

👆 እነዚህን ስድስት ነጥቦች ጠቅሼ ብቆጥራቸውም ሌሎች ላብራራቸው የሚገቡ ሆነው ያለፍኳቸው እንዳሉ ግልፅ ነው። አላህ እኛንም እናንተንም ሱናን የሚያሰራጩ፣ ቢድዐን የሚያስጠነቅቁና ተመርተው የሚመሩ (ቅን ሆነው የሚያቀኑ) ያድርገን። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በጁምዓ ኩጥባቸው ወቅት እንደገለፁት ከምሪቶች ሁሉ በላጩ የሳቸው ምሪት ነውና ቅኑን መንገድ የሚከተሉ፣ በሳቸው አመራርም የሚመሩ ያድርገን። «በማስከተል፤ ከንግግሮች ሁሉ በላጩ የአላህ ኪታብ ነው። ከአመራሮች ሁሉ በላጩም የሙሀመድ ምሪት ነው። መጥፎ ጉዳይ ማለት መጤዎቹ ናቸው። ሁሉም ፈጠራዎች ጥመት ናቸውና።»ብለዋል።
🍀🍀
በታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን [ረሂመሁላህ]
__
3 ሻዕባን 1437/ 11 ሜይ 2016
ትርጉም፦ አቡፈውዛን
•┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈•

www.facebook.com/tenbihat
📃የረመዳንን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር

ሸይኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ:-

“የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”

ሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:-

"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው።

ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ:-

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"

በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል"

ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው።

ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።

ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።

ረመዳን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"

አላህ የረመዳን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን ያ ረ ብ ያ ረ ብ!

#ዝክረ_ረመዳን
_
📚
ቅህን ለመገንዘብ📚
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ታላቅ የ"ነሲሓ ኮንፈረንስ"
በሚሊኒየም አዳራሽ

============================
መጋቢት 1/ ሻዕባን 29 እሁድ ከጧቱ 03፡00 ጀምሮ በአላህ ፈቃድ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
እርስዎም በዚህ ልዩ ኮንፈረንስ ላይ እዲሳተፉ በታላቅ አክብሮት ጋብዘንዎታል።

@nesihatv
ነሲሓ ኮንፈረንስ የሚታደሙበትን የመግቢያ ትኬት online በመመዝገብ በነፃ ይውሰዱ

ታላላቅ ኡለማዎች የሚሳተፉበት ልዩ የነሲሓ ኮንፈረንስ በአላህ ፈቃድ በሚሊኒየም አዳራሽ መጋቢት 1/2016 ይካሄዳል። በተከታዩ ሊንክ ከዌብሳይታቸን በስምዎ ነፃ የመግቢያ ቲኬት ማግኘት ይችላሉ።

https://conference.nesiha.tv

ለፕሮግራሙ ድጎማ በማድረግ አጋራችን ለመሆን Cbe 444 የሂሳብ ቁጥራችንን ይጠቀሙ።

እናመሰግናለን


____
🕌 ibnu Masoud islamic Center
@merkezuna
📣ወቅታዊ ሙሃደራ ለሴቶች

"لعلكم تتقون "
ረመዳንን በእውቀት እንጹም!

በእለቱ የሚዳሰሱ ነጥቦች

🔆 የረመዳን ህግጋቶች

🔆የረመዳንና የጾም ቱሩፋት

እና ሌሎችም ቁም ነገሮች

🗓ቀን እሁድ የካቲት 24  ፣2016

🕘ጠዋት ከ3:00-6:30

🕌 አድራሻ

☞ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስኡድ

⚠️ሴቶች የረመዳንን ደረጃ አውቀው ከገፀ በረከቱ ይታደሉ ዘንድ መልአክቱን ያስተላልፉ።

https://www.tg-me.com/darulhadis18
ትኬት መቁረጥ የሚቻለው እስከ መቼ ነው?

የመግቢያ ትኬት መመዝገቢያ ቅፁ ክፍት የሚሆነው እስከ ነገ ጁምዓ ከቀኑ 7:00 ወይም ከዛ በፊት የተፈለገው ቁጥር እስኪሞላ ብቻ እንደሆነ ለመግለፅ እንወዳለን።

የትኬት መቁረጫ ቅፅ
https://conference.nesiha.tv

ለፕሮግራሙ የገንዘብ ድጎማ በማድረግ የአጅር ተቋዳሽ ለመሆን 444 የንግድ ባንክ አካውንታችን ትራንስፈር ያደርጉ። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን!

____
@nesihatv
ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
Photo
🌙የማይቀርበት ልዩ የረመዳን ሙሃደራ
 
"هَٰذَا بَيَانٌ لِّلنَّاسِ وَهُدًى
 وَمَوْعِظَةٌ لِّلْمُتَّقِينَ"
 እሁድ መጋቢት 15፣2016 ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር ባዘጋጀው የእውቀት ማእድ ላይ ከነቤተሰቦ  እንዲገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
 
❶ የጀነት አቋራጭ መንገድ
 
በኡስታዝ ሻሚል ሙዘሚል
 
❷ ስራችንን የሚያበላሹ ነገሮች
 
በኡስታዝ አብዱሰላም አህመድ
 
 
ከጠዋቱ 4:30 ጀምሮ
ለሴቶች በቂ ቦታ አለ

🕌18 ማዞሪያ በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዋና ቢሮ ቅጥር ግቢ
🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙
===============
🖌 በኢልያስ አሕመድ

በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።
              ››››› ‹‹‹‹‹

በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦

1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው።
ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው።

2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል።

በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦

👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!)

👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣

👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣

👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣

እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው።

📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦
«“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው።
በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦
እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ።
በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ....
“ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።»
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)]

📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦
«ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም  መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]

📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦
«ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)]

ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል።

አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ።
📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦
«የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)]

👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነውበተለይ እንደ ዒድ ሰላት በጎዳና/በአደባባይ ላይ የሚተገበር ከሆነ!
ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦

ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም።
📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?»
እርሳቸውም፦
«مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا»
= «ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም – ካልበዙ በስተቀር

📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል።

«ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል!
[“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣
አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)]

👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው።
ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል።

አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤  ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ።

አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው።

ረመዳን 15/1445
____
@ustazilyas
🌙የረመዷን ሙሃደራ ለሴቶች

"لعلكم تتقون "

በእለቱ የሚዳሰሱ ነጥቦች

💎የኢእቲካፍ ፣የለይልቱል ቀድር፣ የዘካተል ፊጥር፣ የኢድ እና የሸዋል ፆም ሽሪአዊ ድንጋጌዎችና ቱሩፋቶች

💎በመልካም ስራ ላይ መፅናት

እና ሌሎችም ቁም ነገሮች

🗓ቀን እሁድ መጋቢት 22  ፣2016

🕘ጠዋት ከ3:00-6:30

🕌 አድራሻ

☞ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስኡድ

⚠️ መልአክቱን ለእህቶች በማድረስ መልካም ስራን ያስመዝግቡ።

https://www.tg-me.com/darulhadis18
📢ቅዳሜ ተጋብዛችኋል(ለሴቶች)

🌙ልዩ የረመዳን ትምህርት🌙

📮በእለቱ የሚዳሰሱ ርእሶች ፦

❶  አላህን መፍራት (ተቅዋ)

❷ በዲን ላይ መፅናት (ኢስቲቃማ)

🗓ቀን ቅዳሜ መጋቢት 21 ፣2016

🕘ጠዋት ከ3:30-6:30

🕌 አድራሻ

☞ቤተል አደባባይ ከተቅዋ መስጂድ ፊት ለፊት ባለው መንገድ (ብሩክ ብረታ ብረት) ገባ ብሎ


መልእክቱን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን❗️

✔️ዳሩል ሀዲስ ቤተል ቅርንጫፍ
https://www.tg-me.com/darulhadis18
🌟 ልዩ የዳዕዋ ዝግጅት በነሲሓ መስጂድ

👌እሁድ ዙልቂዕዳ 26/1445 ዓ.
ግንቦት 25/2026 ከ 3፡30 ጀምሮ 18 ማዞሪያ በሚገኘው ነሲሓ መስጂድ


ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

__
🕌 ibnu Masoud islamic Center
www.tg-me.com/merkezuna
10ቱ የዙልሒጃ ቀናት.pdf
333.4 KB
🗞 ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት

ዝግጅት፦ አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ ህዳር 2004

🔗 የፅሁፉ ሊንክ
https://d1.islamhouse.com/data/am/ih_articles/single/am_Virtues_of_the_Ten_Days_of_Dhul_Hijjah.pdf

🔗 telegram Share Link
https://www.tg-me.com/abujunaidposts/374


----------------
📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts
💎ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀናት💎

➢ ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሐጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያለቸው እነኝህ ቀናት ናቸው።

➢ ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል ፦

«ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው »

(ሰሂሁል ጃሚዕ 1133)

📌 በነዚህ ቀናቶች በአላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑና ወደሱ የሚያቃርቡንን መልካም ስራዎች በመተግበር ላይ ልንበረታና ቤተሰቦቻችንንም የዚህ ኸይር ተቋዳሽ እንዲሆኑ በማድረግ ልናሳልፈው ይገባል።

📩 http://www.tg-me.com/nesiha_ouserya
📣 አስደሳች ዜና ለወላጆች

ክረምት እየደረሰ ነው ……

አያምልጦት እድሉን ይጠቀሙ !


ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳረል ሀዲስ ከ 10 አመት በላይ ላሉ ለሴት ታዳጊዎችና ወጣቶች ልዩ የ 2 ወር የዲን ኮርስ በ4 ደረጃዎች አዘጋጅቶ መምጣታችሁን እየጠበቀ ነው።

ይህ ኮርስ በአላህ ፈቃድ

✔️እምነታችውን ከምንጩ የሚያውቁበት !

✔️ተቀባይነት ያለው ሶላት እንዲሰግዱ የሚያግዛቸውን ት/ት የሚያገኙበት!


✔️ኢስላማዊ ስነ ምግባርና አደቦችን የሚቀስሙበት!

✔️አርአያዎቻቸውን የሚተዋወቁበት!

✔️ለሴት ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ክህሎት የሚማሩበት!

🔸በየደረጃው የሚሰጡ ኮርሶች ፦
☑️ቃኢዳ
☑️ቁርአን
☑️ዐቂዳ 
☑️ ፊቅህ
☑️ ተርቢያ 
☑️ ሲራ
☑️ ተጅዊድ…

ትምህርቱ የሚሰጠው
📆ከሐምሌ 1-ነሐሴ 30
🕘ጠዋት ከ2:30-6:30

የምዝገባ ቀን፦ ከሰኔ 3-23(የኢድ ቀናቶች ዝግ ነው)
ሰአት :-ከጠዋት 3:00-9:00

▫️ለበለጠ መረጃ:-

1.ለ18 ማዞሪያ (መርከዝ ዋና ቢሮ)
0904366666

2.ለቤተል ቅርንጫፍ
0911105653/0911375952

3 ለፉሪ ቅርንጫፍ
0911479151/0912058590

⚠️ወላጆች ልጆቻችሁን በማስመዝገብ ለልጆቻችሁ መስተካከል ሰበብ በማድረስ ኀላፊነታችሁን ተወጡ!

👆መልዕክቱን ሼር እናድርገው።

@darulhadis18
በዓረፋ ቀን ልንተገብራቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት የትኞቹ ናቸው?

ኢብኑ ረጀብ ለጣኢፉ አል-መዓሪፍ በተባለው ኪታባቸው ላይ የጠቀሱትን እና ሌሎችም ዑለማዎች ከጠቆሟቸው ነጥቦች ከዋና ዋናዎቹ የተወሰኑትን በአጭሩ እንመልከት:‐
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ:- “በዓረፋ እለት ከእሳት ነፃ መውጣቱን እና ለወንጀሎቹ ምህረትን የሚፈልግ ሰው ለዚያ ሰበብ የሚሆኑ ነገሮችን መፈፀም ይኖርበታል:: ከነዚያ ሰበቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:-
1️⃣ የዓረፋን ቀን መፆም:-
አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)

2️⃣ መላ አካላትን አላህ ከከለከላቸው ነገሮች ማራቅ በተለይ ፈፅሞ አላህ ምህረት ከማያድርግለት ወንጀል በእሱ ላይ ማጋራት (ሺርክ) እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል::

3️⃣ የተውሂድ መገለጫ የሆነውን እና የአላህን አጋር የሌለው ብቸኛ አምላክነት እንዲሁም በሁሉ ነገር ላይ ቻይነት የሚያረጋግጠውን “ላ ኢላሃ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢ ቀዲር ” የሚለውን ዚክር ማብዛት:: ይህ ዚክር በእለቱ አላህን ከምናወድስባቸው ቃላት የተሻለውና ምርጡ እንደሆነ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ በተናገሩበት ወቅት እንዲህ ሲሉ አሳውቀዋል:– "እኔና ከኔ በፊት የመጡት ነብያት ከተናገርነው ንግግር ሁሉ በላጩ ይህ ነው።"

4️⃣ አላህን ምህረት እንዲያደርግለት እና ከእሳት ነፃ ከሚወጡት ባሮቹ እንዲያደርገው አብዝቶ መለመን:: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- “ከዓረፋ ቀን የበለጠ አላህ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም::” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በተጨማሪም ዱዓእ ተቀባይነት ሊያገኝበት ከሚችልባቸው ቀናት መካከል አንዱ እና ልዩ ቀን ነው:: መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት የዓረፋ ቀን ዱዓእ ገልፀዋል:- “ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓእ ነው::” ስለሆነም በዚህ ቀን ለራሳችን፣ ለወላጆቻችን፣ ለልጆቻችን፣ ለባለቤቶቻችን፣ ለቅርብ ዘመዶቻችን፣ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ በርትተን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።

5⃣ በአጠቃላይ በተሰማራንበት ቦታ ሁሉ በቻልነው አቅም መልካም ነገሮችን ከማድረግ እንዲሁም አላህን ከማውሳት ልንሳነፍ አይገባም:: በተለይ ከሰላት በኋላ ተክቢራ ማድረግ ከዛሬው እለት ፈጅር ሰላት የሚጀምር መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም:: ይህም ማለት ተክቢራ ማድረጉ ዛሬ የተጀመረው ከአምስቱ ግዴታ ሰላቶች በኋላ የተገደበ (ሙቀየድ) በመባል የሚታወቀው ነው እንጂ ከዚያ ውጪ ያልተገደበ (ሙጥለቅ) በመባል የሚታወቀው የተክቢራ አይነት እስከ አያመ-አተሽሪቅ ማብቂያ ማለትም የአስራ ሶስተኛው ቀን ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ይቀጥላል::

አላህ በመልካም ስራ ላይ ያበረታን እንዲሁም ይቀበለን!

✍️ ጣሀ አህመድ

🌐
https://www.tg-me.com/tahaahmed9
2025/10/22 04:28:32
Back to Top
HTML Embed Code: