†                             


[        ኃይሌና አምባዬ መጠጊያዬ       ]


• ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም
- [ ለአንተ ኃይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለዘለዓለሙ ገንዘብህ ነው ]

• አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም
- [ ፈጣሬዬ አማኑኤል ሆይ ኃይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለዘለዓለሙ የአንተ ነው ]

• ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም
- [ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኃይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለአንተ ይገባል ]

• ኃይልየ ወፀወንየ ዉእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት አቡነ ዘበሰማያት እስከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለም ዓለም።
- [ ኃይሌና አምባዬ መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው ረዳቴ ሆነህልኛልና በምስጋና እንዲህ እላላው አባታችን ሆይ እስከ ኃይል ክብር ምሥጋና ለዘለዓለሙ አሜን። ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
                         †                         

" እነሆም ፥ በጎና ጻድቅ ሰው የሸንጎ አማካሪም የሆነ ዮሴፍ የሚባል ሰው ነበረ ፤

ይህም በምክራቸውና በሥራቸው አልተባበረም ነበር ፤ አርማትያስም ከምትባል ከአይሁድ ከተማ ሆኖ እርሱ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር።

ይኸውም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው ፤ አውርዶም በተልባ እግር ልብስ ከፈነው ፥ ማንም ገና ባልተቀበረበት ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው።" [ ሉቃ . ፳፫ ፥ ፶ - ፶፫ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
ክርስቲያኖች ሁላችሁ ኑ እናፅናናት

#ክርስቲያን_ሁላችሁ ኑ ድንግል ማርያምን #እናፅናናት፤ በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና፥ እንባን ከመጠጧ ጋር አመድንም ከምግቧ ጋር ቀላቅላለችና። #የተወደደ_ልጇ_በመስቀል ተሰቅሎ ስታየው አንድ ጊዜ ከእሾህ አንድ ጊዜ ከድንጋይ ላይ እየወደቀች አለቀሰች። ወንድም የሌለው አንድ ልጇ እንዲህ ሲሰቃይ የወለደ አንጀቷ እንደምን ይቻል? ምንስ ብላ ትፅናና? ያፅናኗት ዘንድ ሊቃነ መልአክት በዙሪያዋ መጡ ግን አልተፅናናችም፤ ልጄ እያለ የሚጠራት አባቷ ዳዊትም መጣ ድንግል ግን እርቃኑን የተሰቀለው ልጇን እያየች መሪር #እንባን_አፈሰሰች። ስለ ልጇ ብዙ መከራ አሳልፋለች፥ ያሁኑ የልጇ መከራ ግን ከሀዘኖች ሁሉ የከፋ ሆነባት። አንድ ልጇ እየሞተ ምን ብላ ትፅናና ? የእናቱን አለመፅናናት ያየ ጌታ ኢየሱስ ከሃዘን ብዛት እንዳትሞት ያፅናናት ዘንድ ቁጽረ ገፅ ለተባለው ለዮሐንስ እነኋት እናትህ አለው። በእውነት እነኋት እናታችን በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ እናፅናናት።"😭😭😭😥😓

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
                         †                         

🕊    †          ስቅለት        †    🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

[     ላሐ ማርያም [  የማርያም ለቅሶ  ]      ]
------------------------------------------------


የእመቤታችን ለቅሶ ሰማይን ስቅጥጥ ፣ ስቅጥጥ  አደረገው፡፡ ምድርን አንቀጠቀጠ፡፡ ባሕሩን አነቃነቀ ፡፡ ሐዋርያትን ሦስት ቀን አስለቀሰ፡፡ የለቅሶውም ድምጽ ሰውነታቸውን እንደ ሰም አቀለጠ፡፡

--------------------------------------------------

"ልጄ ፡ ሆይ ከዚህ ፡ ካገኘህ ፡ የሞት ፡ ፃዕር ፡ የተነሣ ፡ ግፌን የሚመለከትልኝ ፡ ሹም ፡ ወይም ፡ በሐዘን ፡ የተሰበረውን ፡ ልቤን ፡ አይቶ ፡ በማስተዋል ፡ የሚፈርድልኝ ፡ ዳኛ ፡ አላገኘሁም።

መኰንን ፡ ሆይ ፡ እንደ ፡ ሕጉ ፡ የምትፈርድስ ፡ ቢሆን ፡ ኖሮ ፡ ንጉሥ ፡ ልጄን ፡ እንደራበው ፡ እንደጠማው ፡ የአይሁድ ፡ ወገኖች ፡ ባልሰቀሉትም ፡ ነበር።

አንተም ፡ ሊቀ ፡ ካህናት ፡ በዕውነት ፡ ፈራጅ ፡ ብትሆን ፡ ባርያ ፡ በጌታው ፡ ፈንታ ፡ መሞት ፡ በተገባው ፡ ነበር። በበርባን ፡ ፈንታ ፤

ሹም ፡ ሆይ ፡ በቅን ፡ የምትፈርድ ፡ ብትሆን ፡ ልጄን ፡ ባልሰቀልከውም ፡ ነበር። አንተም ፡ ሊቀ ፡ ካህናት ፡ በዕውነት ፡ የምትፈርድ ፡ ብትሆን ፡ ከልጄ ፡ ይልቅ ፡ ይሁዳ ፡ ለሞት ፡ የተገባው ፡ በሆነ ፡ ነበር። ሹም ፡ ሆይ ፡ ፍርድን ፡ የምታውቅ ፡ ቢሆን ፡ ልጄን ፡ ሥጋውን ፡ አራቁተህ ፡ መስቀል ፡ ባልተገባህም ፡ ነበር።

ሊቀ ፡ ካህናት ፡ ሆይ በቅን ፡ የምትፈርድ ብትሆን ፡ ወንበዴውን ፡ አድነህ ፡ ጻድቁን ባልገደልከውም ፡ ነበር።

ዳኛ ፡ ሆይ ፡ መልካም ፡ ፍርድን ፡ የምታውቅ ብትሆን ፡ ኑሮ ፡ ጦሮች ፡ በላይህ ላይ ሲያንዣብቡ ፡ ጽኑዕ ፡ የሆነውን ፡ ባልገደልከውም ነበር።

አንተም ፡ ሊቀ ፡ ካህናት ፡ በቅን ፡ የምትፈርድ ብትሆን ፡ የጌታህን ፡ ፊት ፡ ባፈርክ ነበር። እኔ ፡ ስለጦርነት ፡ ሰልፍ ፡ ስሰማ ፡ የንጉሥ ፡ ልጅ ፡ በጦርነቱ ፡ ውስጥ ፡ የተያዘ ፡ እንደሆን ፡ እንዳይሞት ፡ ስለእርሱ ፡ እጅግ ፡ በርትተው ፡ እየተዋጉ ፡ ወደ ፡ አባቱ፡ በፍጹም ፡ ጌትነትና ፡ ክብር ፡ እስከ ፡ አደረሱት ፡ ድረስ ፡ ይጠብቁታል።

ሊቀ ፡ ካህናት ፡ ሆይ ፡ ለምን ፡ እንዲህ ፡ ሆነ ፡ በጠየቅኸው ፡ ጊዜ ፡ ዕውነቱን ፡ አስረዳህ ፡ ግን ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የተጠላ ፡ ሆነ ፡ ሐሰትን ፡ ወደድክ ፤ እምነትህንም ፡ በሐሰቱ ፡ ላይ ፡ አጸናህ ፤ እንግዲህ ፡ ከእውነተኛው ፡ ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ማንን ፡ ትጠይቃለህ። በፊትህ ፡ የቆመው ፡ እርሱ ፡ እውነተኛ ፡ እንደሆነ ፡ አታውቅምን ፡ እርሱም ፡ በዕውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው።

ንጽሕት ፡ ድንግል ፡ ሆይ ፡ በኢየሩሳሌም ፡ ከተማ ፡ በዚች ፡ ትውልድ ፡ መካከል የሆነውን ፡ ታላቅ ፡ ግፍ ፡ እዪ ፣ እነሆ ፡ ከእነርሱ በሚበልጠው ፡ ላይ ፡ ተሰብስበው ፡ ስም ለሞት ፍርድ ፡ ሰጥተውታልና።

ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ በኋላ ፡ ክርስቶስ ፡ በመስቀል ላይ ፡ እንደሆነ ፡ ነበር ፣ የመቶ ፡ አለቃውን በዕውነት ፡ ይህ ፡ ሰው ፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ፡ ብሎ ፡ አመነ ፤ እሊህ ፡ ተአምራቶቹ በሁሉ ፡ ዘንድ ፡ ታመኑ። በዕንጨት ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ሳለ ምዕመናን ሁሉ ፡ በአንድነት ፡ አለቀሱለት።

ላሐ ማርያም [  የማርያም ለቅሶ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
🕊

[     ፫. በማርያም እሙ    ]  ፦

†                     †                       †

. . . ሶበ ሰማዕኪ ማርያም ዘነገሩኪ በቃል ፤
ዘውኅዘ እምአዕይንትኪ ፥ ከመ ማየ ክረምት ዘይፈለፍል ፤
ድንግል ድንግል ፥ ወላዲተ አምላክ ቃል ፤
ቤዛ ይኲነነ ፥ ማየ አንብዕኪ እምኃጉል !

- የልጅሽን መከራ በነገሩሽ ጊዜ ፤
እንደ ክረምት ዝናም ከዐይኖችሽ የፈሰሰው እንባ ፤
የአካላዊ ቃል እናቱ ድንግል ሆይ ፤
ከጥፋት እንድንድን ቤዛ ይሁነን !

እንኳን አደረሰን !

በዕጸ መስቀሉ ቤዛነት ያዳነን ቸሩ መድኃኔዓለም ፥ በምድር በመቅሠፍት ፥ በሰማይ በገሃነመ እሳት አያጥፋን !

አሜን  !

[  ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ    ]


               †       †       †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
#እውነት__ተሰቀለ


እውነት ተገኝታ አታውቅም ነበር። ሰዎች ለእውነት ያላቸውን ጥላቻ በእውነተኞች ላይ ይፈጽሙት ነበር። በመጋዝ በመሰንጠቅ ፣ በፍላት በመቀቀል፣ በእሳት በመቃጠል፣ ለተራቡ አንበሶች በመሰጠት፣ ደጋግ አበው፣ ቡሩካን ነቢያት፣ ጣዕመ ዓለምን የናቁ ፈላስፎች እውነት ብትገኝ የሚገጥማትን ጉዳት ተቀብለዋል። ዛሬ ግን እውነተኛ ሳይሆን ራሱ እውነት ተገኝቷል። ላይማሩበት ስለ እውነት ሰዎች ይጠይቃሉ። አንገታቸውን ይነቀንቃሉ፣ ሕይወታቸው ግን ከወላዋይነት ንቅንቅ አይልም። ከተቃዋሚዎች በላይ መሐል ሰፋሪዎች እውነትን ተፋልመዋል። ተቃዋሚዎች ላመኑበት ይሞታሉ፣ ወላዋዮች ግን የሚኖሩለት ነገር የላቸውምና የሚሞቱለት ነገር አይኖራቸውም። ወላዋዮች በጆሮ እየሰሙ በኑሮ ግን ይቃወማሉ። ተቃዋሚዎች ግን አንሰማም የሚሉት ከሰሙት እንደሚኖሩለት ስለሚያውቁ ነው። ብዙ ሰው ቀድሞ ለሰማው እንጂ ለእውነት አልታመነምና ያሳዝናል።

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

[ ሚያዝያ ፳፮  [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

🕊  ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ   🕊

ቅዱስ ዮሐንስ በ፬ [ 4 ] ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ቅዱስ ሰው ነው:: ወላጅ አባቱ ጣኦት ጠራቢና አምላኪ: የጣኦቱ አጣኝም ነበረ:: እናቱ ግን በድብቅ ክርስቶስን ታመልክ ነበር::

ልጇን ክርስትና ብታስተምረው አባቱ ጨካኝ በመሆኑ ይገድለዋልና ዘወትር ጧት ማታ ወደ ፈጣሪዋ በዕንባ ትለምን ነበር:: ጧት ጧት አባቱ ጣኦት መጥረብና ማምለክን ያስተምረው ነበር:: አንድ ቀን እግዚአብሔር ለሕጻኑ ዮሐንስ በራዕዩ ተገለጠለት:: ምስሥጢራትንም አስተማረው::

ለተወሰነ ጊዜ በሚደነቅ የክርስትና ሕይወት ከኖረ በኋላ ምንም ገና እድሜው ፲፪ [12] ዓመት ቢሆንም አባቱን ጣኦትህን ተው ሲል መከረው:: አባት ግን ጨካኝ ነውና ትልቅ መጥረቢያ አንስቶ አንገቱን መታው:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ መሬት ላይ ስትወድቅ አካሉ ግን ለ፩ [1] ሰዓት ቆሞ በደሙ ተጠመቀ:: ይሕ ሁሉ ሲሆን የተባረከች እናቱ ቆማ ታይ ነበር::

መንፈሳዊት እናት ናትና አላዘነችም:: ይልቁኑ ከልጇ ደም ለበረከት ተቀባች:: አለችም:- "ጌታ ሆይ! የምሰጥህ ምንም የለኝም:: ይህንን ንጹሕ መስዋዕት ግን ተቀበለኝ::"

ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ካለፈ በኋላ አባቱን ርኩሳን መናፍስት አሳበዱት:: እናት ግን አረማዊ ባለቤቷን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መቃብር ወስዳ ጸለየች :- "ልጄ ሆይ! አባትህን ይቅር ብለህ ከፈጣሪ ዘንድ አማልድ::"

ይሕንን ብላ ባሏን ከመቃብሩ አፈር ወስዳ ቀባችው:: አባትም በቅጽበት ድኖ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ስለ ሰራው ሁሉ ተጸጽቶ አለቀሰ:: በእውነተኛ አምላክ በክርስቶስ አምኖ: ተጠምቆ: በመልካም ክርስትና ኑሮ ኑሮ: ከተባረከች ባለቤቱ ጋር ለገነት በቅቷል::

🕊   ቅዱስ ሱስንዮስ   🕊

ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሱስንዮስ ተሰይፏል:: ቅዱሱ በዘመነ ሰማዕታት ቤተ ክርስቲያንን በገድላቸው ካስጌጧት ታላላቅ ሰማዕታት አንዱ ነው::

እግዚአብሔር አምላክ ከሰማዕታቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን
ይክፈለን::

🕊

[ † ሚያዝያ ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት [ወልደ ፀራቢ]
፪. ቅዱስ ሱስንዮስ ሰማዕት [ሶርያዊ]
፫. ሰማዕታት [የቅዱስ ሱስንዮስ ማሕበር]
፬. አባ ሠርጋ
፭. ቅዱስ ይድራስ

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩፡ አቡነ ሐብተ ማርያም
፪፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ
፫፡ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
፬፡ ቅዱስ ቶማስ
፭፡ ሰማዕታተ ናግራን

" ሰውን ከአባቱ : ሴት ልጅንም ከእናቷ : ምራትንም ከአማቷ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና:: ለሰውም ቤተሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል:: ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: መስቀሉን የማይዝ በኋላየም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም::" [ማቴ.፲፥፴፭-፴፱] (10:35-39)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
እንኳን አደረሳችሁ
ቀዳም ስዑር
26/8/2016
2024/05/05 08:32:16
Back to Top
HTML Embed Code: