Telegram Web Link
የዝምታ ጩኸት...ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው
ዮሐንስ ባለ ራዕይ - Yohanis baleray
(የዝምታ ጩኸት )

ጸሐፊ መ/ር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

አንባቢ ቢኒያም ብርሃኑ
_
ጌታ ሆይ ጩኸታችን አልሆነልንም:: ዝምታችንን ሰምተህ ሀገራችንን ከከበባት ጥፋት ታደግልን::
የእኛ መጨቃጨቅና ጠብ ባሕር አይከፍልም::
የእኛ ጩኸት ከመነካከስ በቀር አያሻግርም::
በአርምሞ የሚለምኑህን በእኛ ፊት ዝም አሉ የምንላቸው በአንተ ፊት ግን የሚጮኹትን ሰምተህ ታደገን::
Watch "🛑ዐቢይ ጾም || ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ" on YouTube
https://youtu.be/E3W76kkwNGI
ቅዱሳን መላእክት ለሰዉ ልጆች ድኅነት እጅግ የሚጓጉ
ከእግዚአብሔር የተሰጡ ጠባቂዎቻችን ናቸዉ። እርግጥ ነዉ፤ በመጀመሪያ እኛም እንደ መላእክት
ክብሩን ለመዉረስ ስሙን ለመቀደስ የተፈጠርን ነበርን
ግንኙነታችንም እነርሱ ከእኛ ቀድመዉ በመፈጠራቸዉ
ታላላቅ ወንድሞቻችን ናቸዉ። ከሰዉ ልጅ ዉድቀት
በኋላ ግን ነገሮች ተለወጡ። በእኛ የባህርይ መጎስቆል
ምክንያት ታላቅ ወንድም የታመመ ታናሹን እንደሚጠብቅ ጠባቂዎቻችን ሆኑ።

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳለዉ፦ የሰዉ ልጅ
ከመላእክት ጋር ክቡር ሆኖ ሲፈጠር፤ ጠባቂን
አይሻም ነበር፤ ሰዉ በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ግን
እግዚአብሔር መላእክትን ጠባቂ አደረገለት።
ምክንያቱም ዲያብሎስ ሰዉን ለማጥፋት ሁል ጊዜ
ምክንያቶችን ስለሚፈልግ ነዉ።

እነዚህ መላእክት ከጠባቂነታቸዉ ባሻገር ለሰዉ ልጅ
መዳን እጅግ የሚጓጉ ሰዉን ወዳጆች ናቸዉ። አምላክ
ሰዉ ሆኖ በተወለደበት በዚያች ምሽት ሲዘምሩ
ያደሩት በአምላክ ሰዉ መሆን የሚያገኙት ጥቅም ኖሮ
ሳይሆን ለሰዉ ልጅ መዳን ካላቸዉ ፍላጎትና ፍቅር
የተነሳ ነዉ። በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን
በምድርም ሰላም የሚለዉ ዝማሬያቸዉ የእኛ ሰላም
ለእነርሱ ምስጋና ምክንያት መሆን የሚያሳይ ምስጋና
ነበር። ሉቃ 2:14

የማያገቡትና የማይጋቡት እነዚህ መላእክት በሰማይ
የሰርግ ያህል ደስ የሚሰኙት በምድር አንድ ኃጢአተኛ
ንሰሓ ሲገባ መሆኑ ምን ያህል የእኛ ወዳጆች
መሆናቸዉን ያሳያል ሉቃስ15;10።

ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ የተላኩ ስላላቸዉ ለማገዝ
የሚላኩ መናፍስት አይደሉምን?

ምንጭ ኢትዮጵያዊዉ ጃንደረባ በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ'
+ ያደረግሽው ምንድር ነው? +

አዳም ዕፀ በለስን በበላና ክብሩን ባጣ ጊዜ እግዚአብሔር ሲጠይቀው እንዲህ አለ :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ::

ከዚያ በኁዋላ ግን እግዚአብሔር ለሔዋን :- ለምን ዛፉን ብላ ብለሽ ሠጠሽው? አላላትም:: "ያደረግሽው ምንድነው" ብቻ አላት::

እርሱ በሰዎች አስተያየት አይፈርድም:: ሌላው ስለ አንተ የሚለውን ትቶ አንተን ለብቻህ ይጠይቅሃል:: የሰዎችን ግምገማ አይሰማም:: እንደ ሃናንያ "ኸረ ጌታ ሆይ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ነበረኮ" ቢሉትም ቸል ብሎ ምርጥ ዕቃው ያደርግሃል:: በድንጋይ ልትወገር ይገባታል ሲሉት ክሱን ትቶ ከሳሾቹን ሊከስስ መሬት ላይ ይጽፋል::
ዐሥርቱ ትእዛዛትን በጻፉ ጣቶቹ ዘማዊትዋን ሴት ነጻ ሊያወጣ አፈር ይጭራል::

ሰው ጨካኝ ፈራጅ እንደሆነ ያውቃልና በአዳም አስተያየት ሔዋን ላይ አይፈርድም:: "ያደረግሽው ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቃት::

እግዚአብሔር ዛሬም ነፍሳችንን ይጠይቃታል::

ያደረግሽው ምንድር ነው? የአዳምን ክስ ሰምቻለሁ! ሰዎች ስለ አንቺ የሚሉትን አዳምጫለሁ:: አንቺ ግን ንገሪኝ:: ግራውን ሰምቼ አልፈርድም:: ምናልባት ቀኙን ብሰማ ይሻላል የሚል ርኅሩኅ አምላክ ነው::
እኛ የምንፈርድባቸው ሰዎች ሁሉ ቢጠየቁ የሚናገሩት የየራሳቸው የታሪክ ማዕዘን (side of the story) አላቸው::
ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ሰምቶ አልፈረደም ሔዋንን ጠርቶ ጠየቃት
"ያደረግሽው ምንድር ነው?"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 2 / 2012 ዓ ም
  አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
Deacon Henok Haile
ጸሐፊ መምህርና የሥነ ልቡና ባለሙያው ቀሲስ ታምራት ውቤ በበሳል የትርጉምና ወጥ ሥራዎቻቸው እንዲሁም በአማካሪነታቸው እጅግ ብዙ ሥራ የሠሩ የቤተ ክርስቲያን አባት ናቸው:: መገለጥ ግድ ነውና ኤጲፋንያ (መገለጥ) በሚል ስያሜ በዩቲዩብ ቻናል መጥተዋል:: ይህንን ቻናል ሰብስክራይብ አድርጉና በዐቢይ ጾም መንፈሳዊ ስንቅ ሰንቁ::
https://youtu.be/wxmsJPQR27I
+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::
ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?
ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

የዐቢይ ጾም የወንጌል ምንባብ ስለ ዲያቢሎስ ፈተና ሦስቱ ወንጌላት የተናገሩትን ስናስተውል ሦስት ዓይነት ጥቅሶች እናገኛለን::

አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። (ሉቃ 4:2)

በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ (ማር 1:13)
የሚሉት ቃላት ጌታችን ዐርባውንም ቀን መፈተኑን ያሳያሉ::

አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ እንዲህ አለው (ማቴ 4:2)

የሚለው ደግሞ ከጾሙ በኁዋላ የቀረቡለትን ሦስት ፈተናዎች የሚያሳይ ነው::
ሦስተኛው ጥቅስ ደግሞ ከተፈተነ በኁዋላ ያለው ሲሆን

ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ። (ሉቃ 4:13) ይላል:: ዲያቢሎስ ፈተናውን ቢጨርስም የሚተወው ለጊዜው እንጂ መፈተኑን አያቆምም:: የዲያቢሎስ ፈተና ስልቱ ይቀያየራል እንጂ ይቀጥላል::

ዐቢይ ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በዐቢይ ጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: ከነስሙ ሁዳዴ (ሰፊ እርሻዬ) የምንለው ይህ ጾም ለነፍሳችን ብዙ ዘር የምንዘራበት አጋንንት መድረሻ የሚያጡበት ጾም ነው:: በዐቢይ ጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በዐቢይ ጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::

ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::

ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 15 2012 ዓ ም
ዝዋይ ኢትዮጵያ

Deacon Henok Haile

ይህ ዓይነቱ ጽሑፍ ለእርስዎም ለሌሎችም እንዲደርስ
ፔጁን Like Share Comment ያድርጉ::
#henokhaile #deaconhenokhaile #eotc #christian #orthodoxchurch #ethiopian #bible #gospel
_እኛ_ልናወጣው_ያልቻልነው_ለምንድነው_ማቴ_17_21_በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ_Ethiopian_Orthodo…
<unknown>
፨እኛ ልናወጣው ያልቻልነው ለምድን ነው? ማቴ 17፥19፨
🌻 በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ 🌻
ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ ( ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው )
ዮሐንስ ባለ ራዕይ - Yohanis baleray
+ከሁሉ በኃላ ጭጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ +
ጸሐፊ መ/ር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://www.tg-me.com/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
2025/07/13 12:41:32
Back to Top
HTML Embed Code: