2016ን
የኪዳነ ምሕረት ዓመት ያድርግልን!
እርስ በእርስ የምንበላላ በላዔ ሰብኦች ነንና እስካሁን ድረስ በግፍ የበላናቸው ነፍሳት በቅተውን በምሕረት ኪዳን ልባችን የሚመለስበት ፤ የሰው ሞት ዜናን ስንሰማ እንደ ቀድሞው ዘመን የምደነግጥበትዓመት ይሁን።
የአባይን ውኃ መግደብ ችላ የደም ጎርፍን ግን መገደብ ያቃጣትን ኢትዮጵያ የሚያሻግር የምሕረት መርከብ ይታዘዝላት:: በኖኅ ዘመን የታየው የኪዳነ ምሕረት ቀስተ ደመና የጥፋት ውኃዋ አላባራ ባለው ሀገራችን ላይ ይታይ
የአባቶቻቸውን ጸሎት አስታውሶ የገባውን ኪዳነ ምሕረት አስቦ እስራኤልን ይቅር ያለ ጌታ ኢትዮጵያውያንም ዛሬ ያወረድነውን እጃችንን ሳይሆን ትናንት ኢትዮጵያ ትዘረጋለች የተባለችውን እጅዋን አስቦ የኪዳነ ምሕረት ዓመት ያድርግልን።
"ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ? አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ ሰ. ኤርምያስ 5:21
▫️@diyakonhenokhaile
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጳጉሜን 3 2015 ዓ.ም
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile

❤118🙏29👍28🥰14
+ ከአንተ ባላውቅም .+
በገነተ አበው (The Paradise of fathers) መጽሐፍ ላይ ይህ ታሪክ ተጽፎአል::
አንድ መነኩሴ በበአቱ ቁጭ ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብ አንድ ቃል ሊገባው አልቻለም:: ለመረዳት በጣም ሲያስቸግረው "ይኼን ቃልስ እንዲገልጽልኝ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ አለብኝ' ብሎ ወሰነ:: ነቢያቱ ያደርጉት እንደነበረውም እግዚአብሔር የቃሉን ፍቺ እስኪገልጽለት ድረስ መጾምና መጸለይ ጀመረ:: ነገር ግን ለሰባ ሳምንታት ያህል እየጾመ ቢጠባበቅም ምንም ነገር ሊገለጽለት አልቻለም:: በየሳምንቱ መጨረሻ ቃሉን ደግሞ ሲያነበውም የበለጠ እየተወሳሰበበት ሔደ እንጂ ጨርሶ ሊገባው አልቻለም::
@diyakonhenokhaile
በመጨረሻም ተስፋ ቆረጠ:: ስለዚህ ሌላ መነኩሴ ጋር ሔዶ ስለዚህ ቃል ትርጉም ሊጠይቀው ወሰነ:: በአቱን ዘግቶ መንገድ ሊጀምር ሲዞር ግን የእግዚአብሔር መልአክ በፊቱ ቆሞ ታየው::
"አይዞህ አትፍራ የፈለግኸውን የቃሉን ትርጉም ልገልጽልህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬያለሁ' አለው::
መነኩሴው ግራ ገባው "የጌታ መልአክ ሆይ ሰባ ሳምንት ሙሉ እየጾምሁ እንዲገልጥልኝ ስለምን ቆይቼ ምንም መልስ አላገኘሁም:: አሁን ተስፋ ስቆርጥ እግዚአብሔር ስለምን መለሰልኝ" አለ በፍርሃት ውስጥ ሆኖ
"እግዚአብሔር ሰባ ሳምንታት ከጾምኸው ጾም ይልቅ ወንድምህን ለመጠየቅ በመሔድ ያሳየኸውን ትሕትና ተቀብሎታል' አለው::
አላዋቂ መስሎ መታየትን ያህል የምንፈራው ነገር የለም:: "አላውቀውም አንተ ንገረኝ” ከማለት ይልቅ ብዙ ሰው ሞት ይመርጣል:: ትንሽ ተምሬያለሁ የሚል ሰውማ ጥያቄ መጠየቅ ዲግሪውን ማቃጠል ይሆንበታል:: የብዙዎቻችን ትሕትና የማፈቅድልን ሰዓት ለመጠየቅ ብቻ ነው:: "ከአንተ አላውቅም ...' ብለው የሚጀምሩ ዐረፍተ ነገሮች ራሱ ልብ ብለን ከሰማናቸው ይዘታቸው “ከእኔ አታውቅም ነው::
የእውቀታችንን ውስንነት ለማመን የሚከብደን በሥጋችን ውስጥ ያለችው ለባዊት ነፍሳችን በሥጋዊ እውቀት ራስዋን መገደብ ስለምትቸገርም ነው::እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ''አሁን ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ ብሎ የእውቀትን ውስንነት ማመን ግን ዕረፍት ይሠጣል:: 1ቆሮ. 13:12
@diyakonhenokhaile
በመንፈሳዊው ዓለም እንዲህ ሲሆን ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ እውነታ ነው:: "የቀለም ቀንድ 1 "የእውቀት ምንጭ'' 1 ''መልስ በጉንጩ'፣ 'ተጠያቂው የሚለውን የክብር ሥፍራ ስንፈልግ በማናውቀው ጉዳይ ሌሎችን ከመጠየቅ ይከለክለናል:: አላውቀውም አላነበብኩትም አልሰማሁትም ከማለት ይልቅ ሁሉን አዋቂ ሆኖ ለመገኘት ስንል የምንበላቸው ዕፀ በለሶች ብዙ ናቸው::
'ብዙ የማውቀው ነበረ ሰዓት ገደበኝ እንጂ " ብሎ ውስን እውቀቱን ባሕር ለማድረግ የሚደክምና ሰዎች ከተናገረው ከጻፈው በላይ አድርገው እንዲያሰቡት የሚገፋፋ ሰው የሚወለደው ካላዋቂነት ፍርሃት ውስጥ ነው:: በጥቂት ንባብ ውስጥ ራስን በጥልቅ ምሁር ዓይን ማየትና “እኔ የማውቀው ማወቁን ነው" ማለት የአላዋቂነት ፍርሃት የሚወልዳቸው ኢሶቅራጥሶች መርሕ ነው::
ከሌላው በታች አላዋቂ መስሎ መታየትን እንፈራለን:: ስለዚህ ሌላውን ከመጠየቅና እንደ ጃንደረባው ''የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?” "ነቢዩ ይኼን ስለማን ተናግሮታል?' ብሎ ከመማር ይልቅ በራሳችን ለመረዳት ብንሟሟት እንመርጣለን:: ብዙ የእምነት' denominations የተፈጠሩትም ሌላውን ከመጠየቅ ሞት በሚመርጡ ትዕቢተኞችና እንደገባኝና እንደተረዳሁት” በሚል አስተሳሰባቸው እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል::
"ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር” ፊልጵ. 2:3
▫️@diyakonhenokhaile
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 2016 ዓ.ም.

Telegram
ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile
Henok Haile
Author
https://instagram.com/henok.haile?igshid=MzRlODBiNWFlZA==

❤112👍56🙏17🥰12🎉1
"እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር" ሐዋ. 16:24
"የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች፤ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል" ምሳ. 27:7
ለመመዝገብ ይህንን ይጫኑ
https://forms.gle/XGBUJspsT9KydX2a8

❤39👍17
Forwarded from Janderebaw Media
+ የአእላፋት ዝማሬ ሊካሔድ ነው +
ጃንደረባው ሚዲያ |መስከረም 2 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ - ጃን ያሬድ የኅብረ ዝማሬ አገልግሎት ክፍል በ2016 ዓ.ም. የመድኃኔዓለም ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ምእመናን የሚሳተፉበት "የአእላፋት ዝማሬ" የተሰኘ የአደባባይ ዝማሬ ዝግጅት ሊያከናውን መሆኑን የኢጃት ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ለጃንደረባው ሚዲያ ገልጸዋል::
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሄኖክ ቡራኬና ጸሎት ፈቃድ አግኝቶ የተጀመረው ይህ የዝማሬ ድግስ ከፊታችን መስከረም 5 ጀምሮ በይፋ ምዝገባ የሚካሔድበት ሲሆን የዘንድሮን የገና በዓል ወጣቶች ጌታ ባልተወለደበት ሥፍራ ልደቱን በኃጢአት እንዳያከብሩ ለማድረግ የታለመ ሲሆን የተራበችን ነፍስ በማጥገብ ኃጢአትን እንድትጸየፍ ማድረግ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል::
የጃን ያሬድ ሰብሳቢ አቶ ወንድሙ ካሣ በበኩላቸው "የዝግጅቱ ዋነኛ ዓላማ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዝማሬ አገልግሎት የሚያገለግሉ ወጣቶችን ሰብስቦ መዘመር ሳይሆን ከቤተ ክርስቲያን በርቀት ያሉትን መዝሙር የማያውቁትን ወጣቶች ሰውና መላእክት አብረው ከዘመሩበት ከልደቱ በዓል በረከት እንዲካፈሉ ማድረግ ነው" ብለዋል:: አያይዘውም "ምዝገባው እንደተጠናቀቀ የዝማሬው ተሳታፊዎች በጃን ያሬድ የቴሌግራም ቻናልና የፌስቡክ ገጽ ላይ በየዕለቱ የመዝሙር ጥናት ፣ መዝሙር ነክ አጫጭር ሥልጠናዎች እንደሚካሔዱም አያይዘው ገልጸዋል::

👍72❤18🥰2
Forwarded from Janderebaw Media
Janderebaw Media
+ የአእላፋት ዝማሬ ሊካሔድ ነው + ጃንደረባው ሚዲያ |መስከረም 2 2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ - ጃን ያሬድ የኅብረ ዝማሬ አገልግሎት ክፍል በ2016 ዓ.ም. የመድኃኔዓለም ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ምእመናን የሚሳተፉበት "የአእላፋት ዝማሬ" የተሰኘ የአደባባይ ዝማሬ ዝግጅት ሊያከናውን መሆኑን የኢጃት ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ዲ/ን ሄኖክ…
ይህ ታላቅ የዝማሬ ማዕድ በመሐረነ አብ ጸሎትና በምሕላ እንደሚጀምር የተገለጸ ሲሆን "የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የመሐረነ አብ ጸሎትን የትውልዱ ጸሎት ለማድረግ ታጥቆ ተነሥቶአል:: ስለዚህም መሐረነ አብን ለሁሉም ሰው ለማስተማር የምንችለውን እናደርጋለን" ሲሉ የጃን እስጢፋኖስ ሰብሳቢ ዲያቆን ኤፍሬም ገልጸዋል::
እስከአሁን አራት ዙር የቅዳሴ ተሰጥኦ ተማሪዎችን ያስመረቀው የጃን ቅዳሴ ሰብሳቢ ዲ/ን ኃይለ ኢየሱስ
"የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ መሐረነ አብን ላለፉት ሁለት ዓመታት መደበኛ ጸሎት አድርጎ ሲያደርስ መቆየቱን አስታውሰው ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር በምነጋገርም ከፊልጶስ አንገርጋሪ የተወሰደ "ጥምቀተ አምጽአ ሕጽወ ንግሥት ለእሊአሁ" የሚል አንቀጽ በጸሎቱ ላይ በማካተት የኢትዮጵያዊው ጃንደረባን የቅዱስ ፊልጶስንና የአባ ሰላማን ውለታ እየዘከርንበት ቆይተናል:: በ2016 ግን መሐረነ አብ የማያውቅ ኦርቶዶክሳዊ እንዳይኖር የሚቻለንን እናደርጋለን ከአእላፋት ዝማሬው በፊት ባሉት ወራትም በየሳምንቱ ልዩ የመሐረነ አብ ጸሎተ ምሕላ በየአድባራቱ በመዞር እናደርጋለን" ብለዋል::
"የአእላፋት ዝማሬ" አስመልክቶ ዝርዝር ሁኔታውን ለመረዳት የሚከተለውን ቪድዮ ይመልከቱ::
https://youtu.be/anPbnTryT68?si=mz9kFaaaWQWF2KBw

YouTube
የአእላፋት ዝማሬ | ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
"እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር" ሐዋ. 16:24
"የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች፤ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል" ምሳ. 27:7
ለመመዝገብ ይህንን ይጫኑ
https://form…

❤143👍68🙏10👏8
ሰይጣን የኢዮብን ሀብት ሲያወድምበት ፣ ዐሥር ልጆቹን ሲገድልበት ፣ ጤናውን ሲወስድበት አንድ ነገር ግን አልነካበትም::
ሚስቱን:
ለምን?
ሚስቱን ያልነካው ምናልባት ነገረኛ ቢጤ ስለሆነች ከኢዮብ መከራ ውስጥ ተቆጥራ ይሆን? ሰይጣን ሚስቱን ያልነጠቀው " ታንገብግበው" ብሎ ይሆን?
ጠቢቡ በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው' ይላል:: ምሳ.27:15 ምናልባት በሰይጣን እይታ ኢዮብን ለማማረር ሚስቱ መቆየት ነበረባት ይሆን?
በእርግጥ የኢዮብ ሚስት "ፈጣሪን ሰድበህ ሙት" የምትል መሆንዋን ስናይ ለኢዮብ ፈተና እንድትሆን ይሆናል ሳንል አንቀርም:: ሰይጣንም እንዲህ ብናስብ አይጠላም።
ነገሩ ግን ወዲህ ነው:: ሰይጣን የኢዮብን ሚስት እንዳይነካት ያደረገው የራሱ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር::
"ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ እርሱ በእጅህ ነው" ብሎ እግዚአብሔር ለሰይጣን አስጠንቅቆት ነበር:: ሕይወቱን አትንካ የተባለው ሰይጣን ሌላውን ሁሉ ሲያጠፋ ሚስቱን ግን ያልነካው ሚስት ሕይወት ስለሆነች ነው:: ሚስቱን መንካትም ራሱን ኢዮብን መንካት ነበር::
አዳምም አለ :-
ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት'
"አዳምም ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር”
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 2016 ዓ.ም. ሕንድ ውቅያኖስ
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
ሚስቱን:
ለምን?
ሚስቱን ያልነካው ምናልባት ነገረኛ ቢጤ ስለሆነች ከኢዮብ መከራ ውስጥ ተቆጥራ ይሆን? ሰይጣን ሚስቱን ያልነጠቀው " ታንገብግበው" ብሎ ይሆን?
ጠቢቡ በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው' ይላል:: ምሳ.27:15 ምናልባት በሰይጣን እይታ ኢዮብን ለማማረር ሚስቱ መቆየት ነበረባት ይሆን?
በእርግጥ የኢዮብ ሚስት "ፈጣሪን ሰድበህ ሙት" የምትል መሆንዋን ስናይ ለኢዮብ ፈተና እንድትሆን ይሆናል ሳንል አንቀርም:: ሰይጣንም እንዲህ ብናስብ አይጠላም።
ነገሩ ግን ወዲህ ነው:: ሰይጣን የኢዮብን ሚስት እንዳይነካት ያደረገው የራሱ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር::
"ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ እርሱ በእጅህ ነው" ብሎ እግዚአብሔር ለሰይጣን አስጠንቅቆት ነበር:: ሕይወቱን አትንካ የተባለው ሰይጣን ሌላውን ሁሉ ሲያጠፋ ሚስቱን ግን ያልነካው ሚስት ሕይወት ስለሆነች ነው:: ሚስቱን መንካትም ራሱን ኢዮብን መንካት ነበር::
አዳምም አለ :-
ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት'
"አዳምም ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር”
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 2016 ዓ.ም. ሕንድ ውቅያኖስ
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
Telegram
ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile
Henok Haile
Author
https://instagram.com/henok.haile?igshid=MzRlODBiNWFlZA==
Author
https://instagram.com/henok.haile?igshid=MzRlODBiNWFlZA==
❤136👍44💯12🎉1
+ የመስቀሉ ደም +
መስቀል ደም አለው ወይ? ከእንጨት የተሠራ ነገር ቢወጉት ይፋፋቅ ይሆናል እንጂ አይደማም::
ስለ ክርስቶስ መስቀል ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ግን "በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ አለ:: (ቆላ 1:20) "ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ”
የመስቀሉ ደም የሚለው ቃል መስቀሉ ደምቶአል ለማለት አይደለም:: ጌታ የተሰቀለበት መስቀል ጠዋት ሦስት ሰዓት ሊቶስጥራ ላይ ጌታን ሲያሸክሙት የመስቀሉ ቀለም የእንጨት ብቻ ነበረ:: ክርስቶስ መስቀሉን ተሸክሞ ለሦስት ሰዓታት ከወጣና ለሦስት ሰዓት ተሰቅሎ ነፍሱን ከሠጠ በኋላ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን ከመስቀሉ ሲያወርዱት የመስቀሉ መልክ የእንጨት አልነበረም:: በጥሩ ባለሙያ ቀይ ቀለም የተቀባ እስኪመስል ድረስ መስቀሉ በክርስቶስ ደም ታጥቦ ነበር:: እሾህ ከደፋው ራሱ ፣ ከተቸነከሩት እጆቹ ፣ ከተገረፈው ጀርባው ፣ ሚስማር ከያዛቸው እግሮቹ እንደ ውኃ የፈሰሰው ደም በመስቀሉ ላይ ፈስሶ ነበር::
መፍሰስን ለመግለፅ በግእዝ ሁለት ቃላት አሉ 'ክዒው' እና ''ሙኒዝ የሚሉ:: ወደ አማርኛ ሲመለሱ ሁለቱም መፍሰስ ቢሆኑም ግን ልዩነት አላቸው:: አንድ ሰው በብርጭቆ ውኃ ቢያፈስስ ውኃው ፈሰሰ ይባላል:: የወንዝ ውኃ ሲፈስስም ፈሰሰ ይባላል:: ግእዙ ግን ከአንድ ብርጭቆ ለሚፈስሰው ውኃ "ተክዕወ' ሲል እንደ ወንዝ ላለው ብዙ ፈሳሽ ደግሞ "ውኅዘ ብሎ ይለየዋል::
ቅዱስ ኤፍሬም ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ብለው አንገታቸው ተሰይፎ እንደሞቱ ሲናገር "ወከዓዉ ደሞሙ በእንተ መንግሥተ ሰማያት” ስለ መንግሥተ ሰማያት ደማቸውን አፈሰሱ” ይላል::
@diyakonhenokhaile
ይኸው አባት ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ክርስቶስ ደም መፍሰስ ሲናገር ግን “በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሖሙ ለመሃይምናን "በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ያመኑትን አነጻቸው ብሎአል:: የጌታችንን ደም መፍሰስ ለወንዝ ፈሳሽበሚነገርበት ቃል ውኂዝ የተባለው ከጌታችን የፈሰሰው ደም ከመላው ሰውነቱ ስለነበረ ነው::
፣ መስቀሉን ለዓመታት መፈለግ ፣ ማክበር ግድ የሆነውም መስቀሉ ዓለም በተገዛበት በከበረ ደም ስለተቀደሰ ነው:: (እስመ ተቀደሰ በደመ ክርስቶስ መድኀን)
ወዳጄ ሆይ በደም የታጠበ መስቀል ስታይ ምን ይሰማሃል? በደም የተቀደሰው የመስቀሉ ክብር አይታይህም? አዎ መስቀል ክቡር ነው::
የመስቀሉ ደም ሌላ የሚያሳየው ክብርም አለ:: እርሱም የእኔና የአንተን ክብር ነው:: ምክንያቱም ያ ሁሉ ደም የፈሰሰው ለእኔና ለአንተ ነው:: በሰዎች የመጠሪያ ስምህ ማን ነው? ማን ብለው ሲጠሩህ አቤት ትላለህ?

👍62❤26❤🔥4🎉1
ቅዱስ ጳውሎስ ግን ለእኔም ለአንተም ስም አውጥቶልናል:: ጳውሎስ አንተን ለሰዎች ሲያስተውቅህ እንዲህ ብሎ ነው :
"ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው" 1ቆሮ.8:11 ወዳጄ የአንተ ክብር እዚህ ድረስ ነው:: አንተ ክርስቶስ የሞተልህ ወንድም ነህ:: አንቺ ክርስቶስ የሞተልሽ እኅት ነሽ::
ቅዱስ ጴጥሮስ ጨምሮበታል :-
" በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ" 1ኛ ጴጥ. 1:18-19 ቅዱስ ያሬድም "አኮ በወርቅ ኃላፊ ዘተሳየጠነ አላ በደሙ ክቡር ቤዘወነ" ብሎ ዘምሮታል::
የእኔና አንተ ዋጋ በወርቅ በብር የሚመዘን አይደለም:: ዋጋችን በመስቀል ላይ የፈሰሰው ክቡር ደም ነው:: ጌታ "መላእክቶቻቸው የአባቴን ፊት ያያሉና ማንንም እንዳትንቁ” ብሎ ነበር:: (ማቴ 18:10) ሰውን ስለ መልአኩ ብለን እንዳንንቅ ከተነገረን ስለፈሰሰለት ደምማ ምንኛ ልናከብረው ይገባን ይሆን?
ውድ ክፍያ ተከፍሎ ልብስ የተገዛለት ልጅ ልብሱን ስለተከፈለበት ዋጋ ሲል ተጠንቅቆ ይለብሰዋል:: በውድ የተገዛ ዕቃ የተሠጠው ሰው በጥንቃቄ ይጠቀምበታል:: የእኛ ሰውነት ግን የተገዛው በአምላካዊ ደም ነው:: እንደተከፈለልን እየኖርን ይሆን?
@diyakonhenokhaile
ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ብሔራዊ ቴአትር ጋር ያለውን ሐውልት እጅግ በውድ ዋጋ አሠርተው ነበር ይባላል:: ንጉሡ የአንበሳ ሐውልት ሊመርቁ ሲከፍቱ ግን ሐውልቱ አንበሳ አይመስልም:: የአንበሳና ቀጭኔ ዲቃላ መስሎ ጉብ ብሎአል:: ንጉሡ አንጀታቸው እያረረ ከመረቁ በኋላ ንግግር ሲያደርጉ ይህ አንበሳ አንበሳ ባይመስልም የወጣበት ገንዘብ ግን አንበሳ ያደርገዋል' አሉ ይባላል::
የእኛም ሕይወት እንደዚያ ነው:: ስንታይ ምናችንም ክርስቶስን አይመስልም:: አንዳንዴም በክፋት ከሰውነት ተራ እንወርዳለን:: ሆኖም እንዲህ ብንበድልም ክርስቶስ የሞተልን ነን ምንም እንኳን ክርስቲያን ባንመስል የተከፈለልን ደም የክርስቶስ ያደርገናል:: ምንም እንኳን የከበረ ሕይወት ባይኖረንም የፈሰሰልን ክቡር ደም ክቡራን ያደርገናል::
@diyakonhenokhaile
“በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ 1ኛ ቆሮ 6:19
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 17 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
"ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው" 1ቆሮ.8:11 ወዳጄ የአንተ ክብር እዚህ ድረስ ነው:: አንተ ክርስቶስ የሞተልህ ወንድም ነህ:: አንቺ ክርስቶስ የሞተልሽ እኅት ነሽ::
ቅዱስ ጴጥሮስ ጨምሮበታል :-
" በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ" 1ኛ ጴጥ. 1:18-19 ቅዱስ ያሬድም "አኮ በወርቅ ኃላፊ ዘተሳየጠነ አላ በደሙ ክቡር ቤዘወነ" ብሎ ዘምሮታል::
የእኔና አንተ ዋጋ በወርቅ በብር የሚመዘን አይደለም:: ዋጋችን በመስቀል ላይ የፈሰሰው ክቡር ደም ነው:: ጌታ "መላእክቶቻቸው የአባቴን ፊት ያያሉና ማንንም እንዳትንቁ” ብሎ ነበር:: (ማቴ 18:10) ሰውን ስለ መልአኩ ብለን እንዳንንቅ ከተነገረን ስለፈሰሰለት ደምማ ምንኛ ልናከብረው ይገባን ይሆን?
ውድ ክፍያ ተከፍሎ ልብስ የተገዛለት ልጅ ልብሱን ስለተከፈለበት ዋጋ ሲል ተጠንቅቆ ይለብሰዋል:: በውድ የተገዛ ዕቃ የተሠጠው ሰው በጥንቃቄ ይጠቀምበታል:: የእኛ ሰውነት ግን የተገዛው በአምላካዊ ደም ነው:: እንደተከፈለልን እየኖርን ይሆን?
@diyakonhenokhaile
ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ብሔራዊ ቴአትር ጋር ያለውን ሐውልት እጅግ በውድ ዋጋ አሠርተው ነበር ይባላል:: ንጉሡ የአንበሳ ሐውልት ሊመርቁ ሲከፍቱ ግን ሐውልቱ አንበሳ አይመስልም:: የአንበሳና ቀጭኔ ዲቃላ መስሎ ጉብ ብሎአል:: ንጉሡ አንጀታቸው እያረረ ከመረቁ በኋላ ንግግር ሲያደርጉ ይህ አንበሳ አንበሳ ባይመስልም የወጣበት ገንዘብ ግን አንበሳ ያደርገዋል' አሉ ይባላል::
የእኛም ሕይወት እንደዚያ ነው:: ስንታይ ምናችንም ክርስቶስን አይመስልም:: አንዳንዴም በክፋት ከሰውነት ተራ እንወርዳለን:: ሆኖም እንዲህ ብንበድልም ክርስቶስ የሞተልን ነን ምንም እንኳን ክርስቲያን ባንመስል የተከፈለልን ደም የክርስቶስ ያደርገናል:: ምንም እንኳን የከበረ ሕይወት ባይኖረንም የፈሰሰልን ክቡር ደም ክቡራን ያደርገናል::
@diyakonhenokhaile
“በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ 1ኛ ቆሮ 6:19
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 17 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
Telegram
ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile
Henok Haile
Author
https://instagram.com/henok.haile?igshid=MzRlODBiNWFlZA==
Author
https://instagram.com/henok.haile?igshid=MzRlODBiNWFlZA==
👍72❤63🙏23🥰8😍6
+ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? +
ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ 'የእግዚአብሔር በግ እነሆ የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት::
"ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው፡፡ እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው፡፡ መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ” ዮሐ. 1:37-39
@diyakonhenokhaile
ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ::
"ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው፡፡ መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ::
ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20)
እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?' ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም?
ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው::

❤45👍13🎉3😢2
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ''ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ መዝ, 43:3
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ'' ብቻ ነው፡
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ መጥታችሁ እዩ'' ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር::
የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: ''የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን“ እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23)
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁመዝ 139:8 ለአድራሻ የሚያስተግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ መጥታችሁ እዩ'' ብቻ ነው::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር።
@diyakonhenokhaile
የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን” እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23)
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ” እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን?

❤39👍22🤩1
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ::
"ወዴት ትኖራለህ?” ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ “መጥተህ እይ“ በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም::
ዮሐንስ ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: “እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13)
@diyakonhenokhaile
ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ::
ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ::
አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ “እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ” ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር::
የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው።
ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን::
ረቢ ወዴት ትኖራለህ?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 21 2016 ዓ.ም. ለእመብዙኃን ዝክር የተጻፈ

❤67👍40😭4👏1
"እግዚአብሔር ብፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን”
ባሕርያት (Elements) ለዚህ ዘመን ክርስቲያን ወጣቶች የተበረከተ እጅግ ውብ የሥነ ጽሑፍ ሥራ ነው:: ይህ ውድ መጽሐፍ አምስት ቅጽ ያላቸው እጅግ የተዋቡ መጻሕፍት ውሕድ ሲሆን በዘመናዊው ዓለም እግዚአብሔርን በመምሰል ሕይወትን እንዴት መለማመድ እንደሚቻል የሚያሳይ በዳያስፖራነት የተወለዱ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ሕይወት የለወጠ እና በብዙ ሺህዎች ኮፒ የተሸጠ መጽሐፍ ነው::
የዚህን መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጽ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ አማርኛ የተረጎምሁት ሲሆን እስከ ኅዳር ማርያም የአርታኢያንን ዱላ ቀምሶ በኅትመት ቤት አልፎ ከእጃችሁ ይገባል:: የቀሩትም መጻሕፍት በወራት ልዩነት ውስጥ ይከተላሉ::
.. የዛሬ ዓመት ገደማ ሊወጣ መንገድ ጀምሮ የነበረው ሉተርና ሚካኤል” የተሰኘ መጽሐፍ በታላላቅ አባቶቼና ወንድሞቼ በሳል ምክር ምክንያት ከይዘቱ የተነሣ የሚወጣበትን ምቹ ጊዜ እየጠበቀና ተከድኖ እየበሰለ ያለ መሆኑን እገልጻለሁ::
"ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን" 2ኛ ቆሮ. 2:14

❤213👍99🥰19💯12😍9🎉7👏6
+ በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ +
ይድረስ ለተከፋኸው ወንድሜ መኖር ለደከመህ ፣ ሕይወት ለታከተህ ፣ የሚሰማህ ላጣኸው ፣ የሚረዳህ ሰው ላላገኘኸው መከረኛው ወዳጄ!
ከሞት ውጪ ሌላ መፍትሔ አልታይ ካለህ የአንተ ቢጤ መከረኞቹ ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ ሆነው እንዲህ ይሉሃል::
“በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" ሐዋ. 16:28
አውቃለሁ ዙሪያው ገደል ሆኖብሃል:: ምነው ባልተፈጠርሁ እስክትል ድረስ ተጨንቀሃል። ግን ይህ ስሜት በአንተ አልተጀመረም:: ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ኑሮ ያልመረረው ማን አለ? መሞት ያልተመኘስ ማን አለ?
ሞት ያማረህ አንተን ብቻ መሰለህ?
" ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ያለውን ጻድቅ ኢዮብ አልሰማህም? (ኢዮ. 10:18)
"ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ” ብሎ እንዲሞት የለመነውን ኤልያስን አላየኸውም? 1ነገሥ.19:4
ዮናስንስ "አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ፡ አለው' ሲል አልሰማኸውም? (ዮናስ 4:3)
@diyakonhenokhaile
ወንድሜ እመነኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መኖር ያላስጠላው ሰው በታሪክ ፈልገህ አታገኝም::
ሞት ሞት የሸተተው ልቡ የተሰበረ ብዙ ነው:: አንተ ላይ ብቻ የደረሰ ልዩ ፈተና የለም:: "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" ይላል መጽሐፍ:: 1ኛ ቆሮ. 10:13

❤131👍51😢5🎉3😍1