World Books Day!
Dedicated to my lovely Mom who Instilled in me the joy of reading.
Pic: my mother reading my book before it was published.
@diyakonhenokhaile

ንጉሥ_በአህያ_ላይ
(ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ)🌿
"አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት። የዚህች በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው። በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣ ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት።
ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት።
🌿
ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ።
🌿
ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።
🌿
"የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት?
ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም።
እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል። መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን።
#share
#share
🌿ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ🌿
▫️@diyakonhenokhaile 🌿
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile

ንጉሰ ሰላም🌿
ጨርሰህ የምትጀምር ፣ ቃለ ሕይወትን የምትሰጥ የቃል መፍለቂያ ፣ ንጉሰ ሰላም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አመሰግንሃለሁ ። ደብረዘይትና ቤተ ፋጌ እንደሚቀራረቡ ልቤን ወደ ቃላህ አቅርብልኝ ። ከመንደር ውስጥ የምትገለገልባቸውን አህያና ውርጫይቱን እንዳገኘ የልቤን መንደር ፈትሸውና አረሙን አቃጥልልኝ። አህያና ውርጫይቱ ላይ መቀመጥህ ተአምር ነው ደንቆኛል ! እኩል የሆኑ አህዮች ላይ መቀመጥ በራሱ ከባድ ነው ፤ አንተ ግን ውርጫይቱ ላይ ተቀመጥከ ። አንዷ ትንሽ ናት አንዷ ከፍ ያለች ናት ። አንዷ ልምጥ ነች አንዷ ደልዳላ ነች አንተ ግን በተአምራት ሁለቱም ላይ ተቀመጥክባቸው። ምግባሬ ትንሽ ትዕቢቴ ብዙ ፣ ለትዕዛዝህ ልምጥ ለኃጢአት ብርቱ የሆንኩ ነኝ ። ሚገድብህ ድንበር የሌለ ንጉሰ ሰላም ክርስቶስ ሆይ የማልመቸውን ልጅህን ስራኝ ። በእስራኤላውያን ልማድ ሀገር ላይ ጦርነት ሲኖር ንጉሱ በፈረስ ላይ ጦር ይዞ በመንደር ውስጥ ይመላለሳል። ሀገሪቱ ሰላም ከሆነች በአህያ ላይ ተቀምጦ መንደሩን በሙሉ እንደሚመላለሳል አንተ ንጉሰ ሰላም ነህና ውርጫይቱ ላይ ተቀምጠህ ወደ ከተማው ገባህ፤ ጌታዬ ሆይ ሀገሬ ኢትዮጵያ አትገባም ወይ ? ወደ ታወከው ልቤስ አትገባም ወይ? የኔ ጌታ ቀርበህ ለከተማይቱ አዘንክ አይደል! ኢትዮጵያን ስትቀርባት ስንቴ አዝነህ ይሆን? የሰላም ንጉሷን አንተን ገፍታ መሳሪያን ስትደገፍ ለኢትዮጵያ አታዝንም ወይ ? አንተን አምላክ ብሎ ሌላ ለሚሚመኘው ልቤስ ስንቴ አዝነህ ይሆን ? ንጉሰ ሰላመቸውን ትተው የዓለማዊያንን ዕቅድ ለሚያራምዱ አገልጋዮች እንዴት አዝነህ ይሆን? ብቻ ሆሳዕና በአርያም ለአንተ ይሁን።ስባዝን በሚሰበስበኝ ፍቅርህ ፣ ስደክም በሚያበረታኝ ድምፅህ ፣ ስታሰር በሚፈታኝ ቃልህ ለዘለዓለሙ አሜን !
#share
#share
ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ🌿
ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም.

በኢያሪኮ መንገድ ቆመው ይለምኑ የነበሩ ሁለት ዓይነ ስውሮች ክርስቶስ በዚያ እያለፈ መሆኑን ሲሰሙ "የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን" እያሉ ፈውስ ይማጸኑት ጀመር። ነገር ግን ከጌታችን ፊት ቀድመው ይሄዱ የነበሩ ሰዎች እኒህን ነዳያን "ዝም በሉ!" ብለው ገሰጿቸው።(ሉቃ 18፥39) ልብ በሉ፤ የገሰጿቸው ሰዎች ጌታን ከኋላ የሚከተሉ ወይም ከአጠገቡ አብረው የሚሄዱት አልነበሩም። ከፊት ከፊት የሚቀድሙት እንጂ። በእርግጥም ከጌታው ፊት ቀደም ቀደም የሚል ሰው ጠባይ ይህ ነው። ራሱን ከባለቤቱ በላይ ዐዋቂ ያደርጋል። ምስኪኖችን "ዝም በሉ" እያለ የሚያሳቅ፣ የጌታውን ቸርነት የሚሸፍን አጉል ጠበቃ ይሆናል። እስኪ አሁን "ማረን" ማለት ምን ነውር አለው? ቃሉስ የስድብ ያህል የሚያስቆጣና "ዝም በሉ" የሚያሰኝ ነው? እነዚህ ሁለቱ ዕውሮች የገጠሟቸው እንዲህ ያሉ "በባለቤቱ ያልተወከሉ ጠበቆች" ነበሩ። ግን አልተበገሩም "ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ ማረን" እያሉ ከቀድሞው ይልቅ አብዝተው ጮኹ። እርሱም ልመናቸውን ሰምቶ ወደዚህ አምጧቸው አለ፣ ፈወሳቸውም።
እነ እገሌ ፊት ነሱኝ፣ ተቆጡኝ፣ አመናጨቁኝ ብለህ ከቤተ ክርስቲያን አትቅር ጸሎትህንም አታቋርጥ። ጉዳይህን ከባለቤቱ ጋር ብቻ አድርግ። ያኔ የልመናህን ድምፅ ይሰማል። ሊፈውስህም ወደ እርሱ የሚያቀርቡ ወዳጆቹን ይልክልሃል።
#share
#share
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
እነ እገሌ ፊት ነሱኝ፣ ተቆጡኝ፣ አመናጨቁኝ ብለህ ከቤተ ክርስቲያን አትቅር ጸሎትህንም አታቋርጥ። ጉዳይህን ከባለቤቱ ጋር ብቻ አድርግ። ያኔ የልመናህን ድምፅ ይሰማል። ሊፈውስህም ወደ እርሱ የሚያቀርቡ ወዳጆቹን ይልክልሃል።
#share
#share
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"እጅግም አዝነው እያንዳንዱ፦ “ጌታ ሆይ፥ እኔ እሆንን?” ይሉት ጀመር" ማቴ. 26:22
ስንት የአጥቢያ ኮከቦች ለአንተ
ዘምረውልህ ወደቁ
በሰማይ መቅደስህ አጥነው
በትዕቢት ረግፈው አለቁ
እፈራለሁ እኔም ለራሴ
መንገዴን ንገረኝ ጌታ
ጠዋት በዘመርሁበት አፍ
እንዳልሳደብ በማታ
#share
#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
ስንት የአጥቢያ ኮከቦች ለአንተ
ዘምረውልህ ወደቁ
በሰማይ መቅደስህ አጥነው
በትዕቢት ረግፈው አለቁ
እፈራለሁ እኔም ለራሴ
መንገዴን ንገረኝ ጌታ
ጠዋት በዘመርሁበት አፍ
እንዳልሳደብ በማታ
#share
#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
የምንወዳቸውን ሰዎች እስከ መጨረሻው መውደድ የማንችለው ለምንድን ነው?
እንወዳቸው የነበሩትን አሁን ስማቸውን መስማት አንፈልግም:: አሁን የምንወዳቸውን ደግሞ ነገ እንጠላቸዋለን:: የእኛ ፍቅር የሚያልቅ ነው:: ክርስቶስ ግን
"የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው" ዮሐ. 13:1
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
እንወዳቸው የነበሩትን አሁን ስማቸውን መስማት አንፈልግም:: አሁን የምንወዳቸውን ደግሞ ነገ እንጠላቸዋለን:: የእኛ ፍቅር የሚያልቅ ነው:: ክርስቶስ ግን
"የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው" ዮሐ. 13:1
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
+ የሚያምር እግር +
በጸሎተ ሐሙስ ልብን የሚሰውር አንድ ነገር ተፈጽሞ አለፈ፡፡ ይህም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር የማጠቡ ነገር ነው፡፡ የሰውን የቆሸሸ እግር እያሸ የሚያጥብ አምላክ ፣ የተማሪዎቹን እግር የሚያጥብ መምህር ፣ የባሪያዎቹን እግር የሚያጸዳ ጌታ ማየት እንዴት ያስጨንቃል?
እስቲ ለአንድ አፍታ ወደዚያ ቤት በሕሊናችን ተጉዘን እንግባና ጌታን እግር ሲያጥብ አብረን እንመልከተው፡፡
የአምስተኛው ክፍለ ዘመን ባለቅኔ የቅዱስ ኤፍሬም ተማሪ ሶርያዊው ቄርሎና በመንፈስ ሆኖ ያንን ቤት በዓይነ ሕሊናው እንዲህ ቃኝቶት ነበር ፦
'ጌታ ውኃ ቀዳና መታጠቢያውን ተሸከመ። የማበሻ ጨርቅ ያዘና ታጠቀ፡፡ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ፡፡ ሕሊናዬን አንዳች ነገር ሲወጋው ተሰማኝ ዕንባዬም ፈሰሰ። በፍርሃት ፊቴን ሸፈንኩ ዓይኖቼንም በመሳቀቅ ዞር አደረግሁ፡፡ ሲያጥባቸው ለማየት አቅም የለኝምና ብወጣ ተመኘሁ' ይላል፡፡ (Hymns of Cyrillona, On The Washing of the feet, Gorgias Press pg 72)እውነትም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር አጎንብሶ ማጠብ ለማሰብ ይከብዳል፡፡
@diyakonhenokhaile
ጌታችን ሐሙስ ዕለት ያደረገውን ነገር መጥምቁ ዮሐንስ ቢያይ ኖሮ ምን ይል ይሆን? ጌታ ሊጠመቅ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ ዮሐንስ 'አንተ እንዴት ልትጠመቅ ወደ እኔ ትመጣለህ?' ብሎ አልነበር? መጥምቁ ዮሐንስ ሆይ ና ተመልከት! በአንተ በባሪያው እጅ ሊጠመቅ ሲመጣ ስለ ትሕትናው የተደነቅህበት ጌታ ዛሬ ደግሞ አጥምቁኝ ከማለት አልፎ የባሪያዎቹን እግር ሲያጥብ አጎንብሶ ታየ፡፡ አንተ 'የጫማውን ጠፍር ተጎንብሼ ልፈታ አይገባኝም' ያልክለት ጌታ አጎንብሶ የሐዋርያቱን ጫማ ሲፈታና እግራቸውን ሲያጥብ ብታይ ምን ትል ይሆን? በዮርዳኖስ ዳር 'አንተ እንዴት ልትጠመቅ ወደ እኔ ትመጣለህ?' ያልከውን ጌታ ቅዱስ ጴጥሮስ 'አንተ እንዴት የእኔን እግር ታጥባለህ?' ሲለው ተመልከት! በእርግጥ በዮርዳኖስ ወንዝ ከታየው ትሕትና የበለጠ ትሕትና በዚያች የመታጠቢያ ወኃ ውስጥ ታየ፡፡ ውኃ በተሞላ በአንድ ማስታጠቢያ ውስጥ የፍጡር እግርና የፈጣሪ እጅ አንድ ላይ ሆነው የታዩበትን ያን ቅጽበት እጅግ ታላቅ ትሕትና ተማርንበት፡፡ ፍጡር ፈጣሪውን ሲያጠምቀው ከማየት በላይ ፈጣሪ የፍጡርን እግር ሲያጥብ ማየት ድንጋይ ልባችንን የሚሰብር ቅጽበት ነው፡፡
ከመጥምቁ ዮሐንስ በፊት የነበሩት ነቢያትስ ይህንን ቢያዩ እንዴት ይደነቁ ይሆን? ኢሳይያስ ሆይ 'ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ሆኖ አየሁት' ያልክለት ጌታ ዝቅ ባለ መቀመጫ ላይ ቁጭ ብሎ የአሳ አጥማጆችን እግር ሲያጥብ ተመልከተው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ሆይ 'እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን' ብለህ የዘመርክለት ጌታ እግር እያጠበ ነው፡፡ የሚገርመው እግር ከማጠቡ በፊትም ውኃ አስቀረበ አይልም ምክንያቱም ውኃውን የቀዳውም እርሱ ራሱ ነበረ፡። አብርሃም ለእንግዶቹ እንዳለው 'ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ' ብሎ ውኃ አላስቀዳም፡፡ (ዘፍ. 18፡4) ራሱ ወኃወን ቀድቶ በመታጠቢያው ሞልቶ የባሪያዎቹን እግር አጠበ። ለነገሩ በትሕትና የተጠመቀበትን የዮርዳኖስን ወንዝስ ቢሆን በወኃ የሞላው እርሱ አልነበረምን? ...
ጴጥሮስ ተጨነቀ ፤ 'ጌታ ሆይ አንተ እንዴት የእኔን እግር ታጥባለህ?' አለና ተከላከለ፡፡ የጴጥሮስ ጭንቀት ብዙ ነገር ከማሰብ የመነጨ ነው፡፡ 'ኪሩቤል በፊትህ ግርማ እንዳይቃጠል ፈርተው በፊትህ ሲቆሙ በክንፎቻቸው እግራቸውን ይሸፍናሉ፡፡ ታዲያ እኔ እጠብልኝ ብዬ እንዴት ደፍሬ እግሬን እሠጥሃለሁ? ሱራፌል የልብስህን ጫፍ የማይነኩህ ጌታ የእኔን እግር እንዴት ታጥባለህ? በባሕር ላይ በአንተ ትእዛዝ የተራመድሁት አይበቃኝም? እንዴት እግርህን ልጠብህ ትለኛለህ? ይህንን ዕዳ እንዴ እሸከመዋለሁ?' የሚል ጽኑ ጭንቀት ያዘለ ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታ ግን ዕውር ባበራባቸው እጆቹ እግር አጠበባቸው፡፡ ሸክላ ሠሪው አጎንብሶ የሸክላውን እግር አጠበ፡፡ ሰውን ከምድር አፈር የፈጠረው አምላክ ትቢያውን በክብር አስቀምጦ እግሩን አጠበው፡፡
ጌታችን ያጠበው ከሰዓታት በኋላ እግሬ አውጪኝ ብለው ጥለውት የሚሸሹትን የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ነበረ፡፡ ለአንድ ሰዓት እንኳን አብረውት ሊተጉ የማይችሉትን ተማሪዎቹን እግር አጠበ፡፡ ጥለውት እንደሚሔዱ እያወቀ 'ንጹሐን ናችሁ' ብሎ አወደሳቸው፡፡ 'ወደ አብ እንደሚሔድ አውቆ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው' እንደሚል ምድር ላይ በቀረችው ጊዜ ያልከፈለው የፍቅር ዕዳ እንዲኖርበት አልፈለገምና ጊዜውን ለመውደድ ተጠቀመበት፡፡ የሚወዳቸውን ደቀ መዛሙርት እግራቸውን አጥቦ በፍቅር ተሰናበታቸው፡፡
ጌታ ሆይ የእኔንስ እግር የምታጥበው መቼ ነው? በእውነት በምድር ላይ ከእኔ እግር በላይ የቆሸሸ አለ? ያልረገጥሁት የኃጢአት ጭቃ ፣ ያልነካሁት የበደል ቆሻሻ እንደሌለ አታውቅምን? 'በክፉዎች ምክር የሔደ' እግሬን የማታጸዳው ለምንድን ነው? (መዝ. 1፡2) 'የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም' ብለህ የለምን? እውነት ነው ፤ እግሬን ከኃጢአት ከከለከልክልኝ ሌላውን አካሌን ማዳንህም አይደል? አጥብቀህ ከምትጠላቸው ነገሮች መካከል አንዱ የሆነውን 'ወደ ክፉ የሚሮጥ እግሬን' የማታጥብልኝ ለምንድን ነው? (ምሳ. 6፡18)እባክህን እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ፡፡ በእርግጥ የሐዋርያትን የቆሸሸ እግር በውኃ እንዳጠብከው አስበን አደነቅን እንጂ በማግሥቱ ደግሞ የዓለምን ኃጢአት በደምህ አጥበሃል፡፡ ከዳንሁ በኋላ የቆሰልሁትን ፣ ከታጠብኩ በኋላ ያደፍሁትን እኔን በከበረ ሥጋና ደምህ ከኃጢአቴ እድፍ ታጥበኝ ዘንድ ነው ልመናዬ፡፡
በጌታ እጅ የታጠበው የሐዋርያት እግር እንዴት የታደለ ነው? በእሱ ስለታጠበ ዓለምን ዞሮ ወንጌል ለማዳረስ የቻለ እግር ሆነ፡፡ ጌታ ያላጠበው እግር ወንጌል ለዓለም አያደርስም፡፡ ባልታጠበ እግራችን ብንዞር እኛ እንጂ ወንጌል ዓለምን አይዞርም፡፡ ስለዚህ ሐዋርያ ሊሆን የሚሻ ሁሉ ጌታ ሆይ እግሬን እጠብልኝ ብሎ መለመን አለበት፡፡ ወንጌሉም 'የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ' ይላልና ክርስቶስ ደቀ መዝሙሩ ሊሆኑ ለሚወዱ ሁሉ እግራቸውን ማጠቡን አሁንም አያቋርጥም፡፡
ጌታ ያጠበው እግር ምን ይሆናል ካልከኝ 'የሚያምር እግር ይሆናል' እልሃለሁ፡፡ ሐዋርያት እግራቸው እጅግ ያምር ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ በእግሩ እብጠት የማይንቀሳቀሰው ቅዱስ ያዕቆብ ሳይቀር እግሩ ያማረ ነበር፡፡ ምክንያቱም 'መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው?' ተብሎ ተጽፎአል፡፡ ሮሜ 10፡15
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 24 2016 ዓ.ም.
ኢየሩሳሌም ፤ ፳ኤል

"ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ”
ማር.16:6
በጌታችን መቃብር በጎልጎታ ከቅዱሱ እሳት ጋር::
የትንሣኤውን ማብሰሪያ ሻማ ራሱ መድኃኒታችን በተአምራት በቅዱስ እሳት (The Holy Fire) እንደሚለኩሰው ታውቁ ይሆን? ዛሬም ሌሊት በተአምራት ቅዱሱ እሳት ወርዶ በእጃችን ከብበን ይዘነዋል:: የዛሬን አያድርገውና በአንድ ወቅት እሳቱ ለኢትዮጵያዊ ሰው ስለወረደ በየዓመቱ ከግሪኮችም ከአርመኖችም በፊት ኢትዮጵያውያን እንዲለኩሱ ይደረግ ነበር:: ዛሬ ደግሞ እኛ ከእሳቱ ተቀባዮች ነን:: ይሁንና የጌታችንን የትንሣኤ ብርሃን ዛሬም አብርተናል:: ብርሃኑን ለኩሰን ስንወጣ አንድ የባሕር ማዶ ጋዜጠኛ gabriel_crisan ፎቶዎች ላንሣህ ብሎ እነዚህን አነሣና ላከልኝ:: ከጀርባዬ ያለው ቀራንዮ ነው:: እንኳን አደረሳችሁ!

ጴጥሮሳዊ ቅጽበት
አርብ ዕለት ጌታ ከሰማቸው ስድቦች ሁሉ በፊት ጌታን የሚያቆስል አንድ ቃል ነበረ::
የሚወደው ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስ "አላውቀውም" እያለ ሲምል ሲገዘት ጌታ ሲሰማው ምንኛ ይሰማው ይሆን? እየሰማህ ስትታማ እንኩዋን ይከብዳል:: እየሰማህ አላውቀውም መባል ደግሞ የባሰ ነው::
ጴጥሮስ ያደረገው ታውቆት መራራ ለቅሶ አለቀሰ:: የእኔና የአንተ የአንቺ ጴጥሮሳዊ ቅጽበት መቼ ይሆን?

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው" ዘፍ.2:4
"የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ" ገላ. 4:4
" እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ" ዕብ. 4:16
" አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም" ራእይ 21:1
እንኳን ለሕይወታችን ተስፋ ለወላዲተ ክብር ለእመብርሃን ልደት አደረሳችሁ::
ግንቦት 1 2016 ዓ.ም.
በኤማሁስ