Telegram Web Link
“እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16

#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
"ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ" ፊልጵ. 3:13

ሰማዕቱ ቅዱስ ጳውሎስ ትቶልን ከሔዳቸው ትምህርቶች አንዱ ያለፈውን መርሳትና የወደፊቱን ለመያዝ መዘርጋት ነው:: ብዙዎቻችን በትናንት ቁስል ስናነክስ ወደ ነገ ለመሻገር እንቸገራለን:: ስላለፈው ስናወራ የሚመጣውን መቀበያ አቅማችንን እንጨርሳለን:: የትናንት ስኬት አስደስቶት ዕድገቱን የሚያቆም ብዙ ሰው አለ:: የትናንት ውድቀቱን ተዝካር እያወጣም ዛሬውን የሚያበላሽም ብዙ አለ:: መፍትሔው ግን እንደ ጳውሎስ "በኋላ ያለውን መርሳትና ወደ ፊት መዘርጋት" ነው::
የዛሬው ቀን ቅዱስ ጳውሎስ የትናንቱን አሳዳጅነቱን ረስቶ የፊቱን ሰማዕትነት ሊቀበል የተዘረጋበት ቀን ነው:: የድል አክሊልንም የያዘው ዛሬ ነው::

ፎቶ:- ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነት በተቀበለበት ሥፍራ የተወሰደ ማስታወሻ
#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ለመዝገበ ቃላታቸው እንደ ዋነኛ ማጣቀሻ የጠቀሱትና የተቀኙለት ጀርመናዊው ኦርየንታሊስት እና የግእዝ ሊቅ ኦገስት ዲልማን (August Dillmann) እንዲህ አለ:-

"የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ለማወቅ ሦስት ነገሮች ያስፈልጋሉ:: አንደኛው ግእዝን ማወቅ ፤ ሁለተኛው ግእዝን ማወቅ ሲሆን ሦስተኛውም ግእዝን ማወቅ ነው"

ግዕዝ መፅሐፍ ቅዱስ ከምንጭ ቋንቋዎቹ (Source languages) ከዕብራይስጥና ግሪክ በቀጥታ መጀመሪያ ከተተረጎመባቸው የዓለማችን ሰባት ቋንቋዎች አንዱ የሆነ የመግለፅ አቅሙ ከፍተኛ የሆነ ቋንቋ ነው::

#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
የሕይወት ልቃቂት

አንዲት ሴት ልብስ ልታሠራ ፈትል እየፈተለች ነው፡፡ የጥጡ ልቃቂት የማይበቃ መስሏት ከዚያ ከዚያ እያለች ለልብስዋ እንዲበቃ ለማድረግ ቁጥሩን አትርፋ መፍተልዋን ቀጠለች፡፡

ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ በዚያ እያለፈ ነበርና ከሩቅ አያት፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋው የፈተለችው ለምታሠራው ልብስ የሚበቃ መሆኑን አውቆ ሴቲቱን እንዲህ አላት፦

'ሞልቷልና አትድከሚ'

በዚህ ምክንያት የዚያ አካባቢም ሥፍራ 'ኅድጊ ወትጻምዊ' 'ተይ አትድከሚ' ተብሎ ይጠራል፡፡

ይህንን ታሪክ ሳነብ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ስለ አንዲት ሴት ጥጥ መባከን ብቻ የተናገረው ሆኖ አልተሰማኝም፡፡

ከሚያስፈልገን በላይ እየፈተልን የምንደክምባቸው የሕይወት ልቃቂቶች ስንት ናቸው? ለምንኖረው ዕድሜ የሚበቃንን ሳናውቅ የምንኳትንባቸው ስንት ጉዳዮች አሉ? ለአጭር ቀሪ ዕድሜ በረዥሙ መዘጋጀት ፣ ለማናጭደው አዝመራ አዲስ ጎተራ መገንባት ፣ በንባብ ላይ ንባብ በምርቃት ላይ ምርቃት ፣ ለማንገነባው ሕንፃ መሠረቱን ማስፋፋት ፣ ከፈትሉ በላይ ልቃቂት ስናከማች ሕይወትን ሳናጣጥም መቅረት የሁላችን ችግር ነው:: ከሚያስፈልገን በላይ ስንሰፍር ብዙ ዋጋ ላላቸው ነገሮች ጊዜ አጣን::

እንደዚህች ሴት ለነፍሳችን "ሞልቶአልና አትድከሚ" የሚላት ማን ይሆን?

ቅዱስ አባታችን ሆይ እኛንም 'ሞልቶአልና አትድከሙ' በለን፡፡
#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
ሐምሌ 15 የትሕትና ባሕር ፣ የቅኔ ዋናተኛ ፣ የኤፍራጥስ ወንዝ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ያረፈበት ዕለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ጸጋን በሚሸከም ትሕትና የተሞላ አባት ነበር::

ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያን ለማግኘት ባደረገው ጉዞ ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ ባስልዮስ እየሰበከ ነበር፡፡ ስብከቱን ሲፈጽም በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት አንድ ቋንቋ ከመናገራቸው በፊት በአስተርጓሚ እርዳታ

'ኤፍሬም ነህ ወይ?' አስብሎ ቅዱስ ባስልዮስ አስጠየቀው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም በባስልዮስ አንደበት ስሙ ሲጠራ ሲሰማ “ከመንግሥተ ሰማያት መንገድ СФ የተጣልሁ ኤፍሬም እኔ ነኝ" ካለ በኋላ በዕንባ እየታጠበ 'አባቴ ሆይ ኃጢአተኛው ክፉ ሰው ራርተህ በጠባቡ መንገድ ምራኝ” አለ፡፡

አንድ ሶርያዊ መነኩሴ አግኝቼ የቅዱስ ኤፍሬምን መቃብር መሳለም እንደምፈልግ ጠይቄያቸው ነበር:: ፈገግ አሉና እንዲህ አሉ :‐ "ቅዱስ ኤፍሬም እኮ መቃብሩ እንዳይታወቅ ታናዝዞ ስለሞተ የት እንደተቀበረ የሶርያ ቤተ ክርስቲያንም አታውቅም"

ቅዱስ አባታችን ሆይ በመንፈሳዊው ብዕርህ ትዕቢተኛ ልባችንን ፈውስልን::
#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
...ሁለቱ ጸሐፍያን በደብረ ታቦር ...
ክፍል አንድ

በሕይወት ታሪካችን ብዙ የቅርብ ፣ የሩቅም ወዳጆች አሉን ፡፡ እጅግ ቅርብ በሆኑን ወዳጆቻችን በኩል ለእነርሱ ቅርብ ፥ ለእኛ ደግም በጣም ሩቅ ስለሆኑ ሰዎች ሰምተናል ። ስለ ማንነታቸው ፣ አስተሳሰባቸው ፣ ፍልስፍናቸው ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው ፣ ዝናቸው ባጠቃላይ ስለ ነገረ ሥራቸው ሁሉ የተደነቅን ከመስማታችን የተነሳ በአካል ሳናውቃቸው የልብ ወዳጆቻችን የሆኑ ብዙዎች አሉ ። ታዲያ! እነዚህን ሰዎች በአጋጣሚ በአካል ብናገኛቸው ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል ? ስለምን እናወራቸው? ምንስ እንጠይቃቸው ይሆን? ይህን ጥያቄ እንድንጠይቅ ከሚያጓጉን ታሪኮች አንዱ በደብረ ታቦር የተፈጸመው ነው ፡፡

እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው ሦስቱ ወንጌላውያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን ምስጢር አዘል ታሪክ በተመሳሳይ ሁኔታ መዝግበዋል ፡፡ ምንም እንኳን ሶስቱ ወንጌላውያን በደብረ ታቦር ተራራ የተከናወነውን ድንቅ ክስተት ቢመዘግቡም የተለያየ የታሪክ አጻጻፍ ተክትለዋል ፡፡ አንዱ ያጎደለውን አንዱ አንዱ እየጨመረ ፣ አንዱ የረሳውን አንዱ እያስታወሰ ጽፈዋል። ማቴ 17÷ 1-9 , ማር 9÷ 2-10 ,ሉቃ 9÷ 28-36

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እስከገለጠበት እስከዚያች ቀን ድረስ ለሐዋርያት ፥ እስራኤላውያን አብልጠው ስለሚወዱት ሙሴ እንዲሁም “ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል " ተብሎ ስለ ተነገረለት ኤልያስ ፥ ብዙ ጊዜ ስማቸውን እያነሳ ብዙ አስተምሯቸዋል ፡፡ ታዲያ! በክርስቶስ አንደበት ስለ እነዚህ ታላላቅ አባቶች ታሪክና ድንቅ ሥራ የተገረሙ ሲሰሙ የነበሩ ሐዋርያት እነዚህን አባቶች ምን ያህል ማየትና መነጋገር ሽተው ይሆን? የሐዋርያትና የእነዚህ አባቶች መገናኘት አስደናቂ ገጠመኝ ነው ፡፡

ይህን የደብረ ታቦር ታሪክ በተመለከተ የሶርያውያን ፀሐይ ፣ የኤዴሳው ዲያቆን ቅዱስ ኤፍሬም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮት የተገለጠበት ተራራ ላይ የተፈጸመውን

"There the authors of the old covenant saw the authors of the new. Holy Moses saw Simon Peter the sanctified; the steward of the Father saw the administrator of the Son... The virgin of the old covenant (Elijah) saw the Virgin of the new (John); the one who mounted on the chariot of fire and the one who leaned on the breast of the Flame. And the mountain became a type of the Church, and on it Jesus united the two covenants :...

'የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ ፤ ቅዱሱ ሙሴ ቅዱስ ጴጥሮስን አየው የአብ እንደራሴ የወልድን አገልጋይ ተመለከተው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ድንግል ኤልያስ የሐዲስ ኪዳኑን ድንግል ዮሐንስን አየው፡፡ በእሳት ሰረገላ ላይ የተሳፈረው ኤልያስ ወደ እሳታዊው ክርስቶስ ደረት የተጠጋውን ዮሐንስን አየው፡፡ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆነ ፤ ክርስቶስም ሁለቱን ኪዳናት አዋሐዳቸው!' " በማለት በንጽጽር ድንቅ ምስጢር ይነግረናል ።
#share


▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
2025/07/01 08:25:18
Back to Top
HTML Embed Code: