Telegram Web Link
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ቅምሻ - ፩

አሐቲ ድንግል - አንዲት ድንግል
 

ድንግል ማርያም ለምን አንዲት ድንግል ትባላለች?

እመቤታችን ድንግል ማርያም በምድርም በሰማይም አቻ የማይገኝላት አንዲት ድንግል ናት። ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌልም የምትልቅ በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች በወንጌል የተፃፈች አንዲት ድንግል አለች። ይላል ቅዱስ ያሬድ።

ከዚህም ተነስቶ አንድ ሰው ተነስቶ በወንጌል ሌሎች ደናግል የሉምን? ስለምን በወንጌል የተጻፈች አንዲት ድንግል ትላለህ? ብሎ ቢጠይቀው ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌል የምትበልጥበት የድንግልና ዘውድ ያላት አንዲት ድንግል አልኩህ እንጂ ደናግላንማ ብዙ ደናግል አሉ ብሎ ይመልስለታል።

ቀጥሎም በመላዕክት ክንፍ የምትጋረድ በክብሩ መንበር በፊት ምህረት የምትለምን በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊል የተቀዳጀች አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል አለች።

አሁንም ቅዱስ ያሬድን ስለምን አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል ትላለህ አርሱ የመረጣቸው ብዙ ደናግላን የሉምን? ብሎ የሚጠይቀው ቢኖር፥ አማኑኤል ሥጋን ይለብስ ዘንድ የመረጣት፤ ከእርስዋም ሥጋን ለብሶ አማኑኤል የተባለባት፥ በመላእክት ክንፍ የምትጋረድ፥ እግዚአብሔር በክብሩ ዙፋን በፊቱ ለመቆም የመረጣት፥ በእናትነት የሰለጠነ የባለሟልነት ዘውድን የተቀዳጀች አንዲት ድንግል አልኩ እንጂ እርሱ የመረጣቸው ደናግላንማ ስንቱ! ብሎ ይመልስለታል።

ደግሞም ፀጉሯ እንደ ሐር ፈትል ያማረ፥ የአንደበቷ መዓዛ እንደ እንኮይ የጣፈጠ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች የልዑል ንጽሕት አዳራሽ የሆነች አንዲት ድንግል አለች።

የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆኑ ሌሎች ደናግላን የሉምን ስለምን ለይቶ እርሷን አንዲት ድንግል አለ ቢሉ? ከእርሷ ስጋ ይነሳ ዘንድ እግዚአብሔርን በማህፀኗ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የወሰነች እውነተኛ የእርሱ ማደሪያ ሌላ ድንግል ከማርያም በቀር ወዴት አለ ይለዋል! ብቻዋን የእግዚአብሔር መቅደስ ለመሆን የበቃች እንደሆነች ሁሉ ከቅዱሳን ሁሉ ተለይታ በእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው እንደ እንኮይ የጣፈጠ አማላጅነት ያላት አንዲት ድንግል እርሷ ብቻ ናት! ስለዚህ እንደ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችን ብቻዋን አንዲት ድንግል የተሰኘችበት  ወላዲተ አምላክነቷ፤ ንፅሕናዋ ፤ማኅደረ መለኮትነቷ አማላጅነቷ እና ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ ናቸው ማለት ነው።

፩.በድንጋሌ ሥጋ ዘለዓለማዊ
በተፈትሆ የማይመረመር ድንግልናዋ ነው።
ይህም ሥስት የማይመረመሩ ግብራት አሉት። ድንግል እንደሆነች መፀነስ፥ ድንግል ሆና ሳለ መውለዷ፥ ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና መኖሯ ናቸው። እነዚህ በህገ ተፈጥሮ የማይታሰቡ ረቂቅ ግብራት ናቸው። ሰው ድንግል ሆኖ ያለ ወንድ ዘር መፀነስ አይቻለውም፥ በድንግልና እያለ የፀነሰ መሆን አይችልም፥ ሰው በድንግልና መውለድ አይቻለውም፥ ከወለደ በኋላ ደግሞ ድንግል መሆን እንዴት ይችላል? ድንግል የሆነች ሌላ ሰው እናት አይደለችም፥ እናትም ከሆነች ድንግል አይደለችም። ይህ ለአንዲቱ ለድንግል ማርያም ብቻ የተቻለ ነው።

፪. ድንግል በቃሏ - በቃሏም ድንግል
የቃል ድንግልና በሦስት ወገን ነው። እኒህም ክፉ አለመናገር፥ ምስጋና አለመብላትና በጎውን መናገር ናቸው። ሰው በንግግሩ ብዙ ኃጢአቶች ይሰራል። ሐሜት፣ ማጉረምረም፥ ቁጣ፥ ብስጭት፥ መዋሸት፥ መርገም፥ መሳደብ፥ ዋዛ ፈዛዛ፥ ያለጊዜው መሳቅ መሳለቅ፥ ዘፈን፥ ተውኔት፥ ድንፋታ፥ መንፈግ ነገር ማመላለስ፥ ቃል መለዋወጥ፥ አደራ መብላት፥ በሀሰት መማል፥ ሰጥቶ መንሳት፥ ክህደት፥ ማታለል፥ ማስነወር፥ አድልዎ፥ መጠራጠር፥ ማሽሟጠጥ፥ አሽሙር፥ ኃጢአትን ማመስገንና ማስፈራራት እነዚህን የመሳሰሉ ሁሉ ናቸው።

እመቤታችን በማንም ክፋትን ተናግራ አታውቅም አንደበቷ የለዘበ የለመለመ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና የማይታሰብ ዕፁብ ድንቅ የመውለዷን ዜና ሲነግራትም እኔ ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል ብላ ነገሩን ወደ መረዳት ተሻገረች እንጂ ይህ የማይሆን ነገር ነው ብላ ወደ መጠራጠር ወይም መልአኩን ወደ መንቀፍ አልቃጣችም። የአንደበት ድንግልና ማለት የማይቻል ጭንቅ ፍጹም ከተፈጥሮ ህግ በላይ የሆነን ነገር በመስማት ጊዜም ቢሆን ያለመጠራጠር በሃይማኖት መጠየቅና ፍፃሜውን በትዕግሥት መጠበቅ ነው።

መከራ በደረሰ ጊዜ ብዙ የቃል ድንግልና ያላቸው ቅዱሳን ችግሩን የፈጠሩትን ከመንቀፍ ይልቅ በእኔ ችግር የተከሰተ ነው ብለው ራሳቸውን ይወቅሳሉ። ነገር ግን እነርሱ ቀድሞ መበደላቸውን እያስታወሱ ነው። የድንግል ማርያም ግን የሚደንቀው ምንም ነውር የሌለባት ስትሆን በቃሏ ድንግል ስለሆነች እኔ ኃጢተኛ ነኝ ትል ነበር። በብስራተ መልአክ አምላክን የፀነስኩ እናት ነኝ ስትል ገናንነቷን አትናገርም። መልካም በመናገር ንግግሯ ሁሉ ሃይማኖት ተስፋና ፍቅር ናቸው።

፫. ድንግል በኅሊናሃ - በኅሊና ድንግልና የፀናች አንዲት ድንግል፦
ሰው በተግባር ቢነጻ በንግግር አይነጻም፥ በንግግር ቢነጻ በኅሊናው መንፃት አይቻለውም። ጻድቃንም ቢሆኑ ወድቀው ተነስተው በተጋድሎ ለክብር ይበቃሉ እንጂ ከጅማሬ እስከ ፍፃሜው አለመበደል ከቶ የተቻለው የለም። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በኅሊናዋ እንኳን ያልበደለች ፍጽምት  አንዲት ድንግል ነች። ጽድቅን ሁሉ የተሞላች ድንግል ማርያም ንጽሕት በመሆኗ በኅሊናዋን ድንግልና፤ የቃሏን ድንግልና፤ የስጋዋን  ድንግልና በአንድ ላይ "እንዘ ኢይአምር ብእሴ" "ወንድ ስለማላውቅ" በሚል የንፅህና ሸማ ጠቅልላ ተናገረች (ሉቃ.፩፥፴፬) በዚህ ድንግልናዋም አምላክን ለመፀነስ በቃች።.....(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል መጽሐፍ ገፅ 241-251 የተቀነጨበ)

▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
+ ለእንቅልፋሞች መልካም ዜና +

እንቅልፍ ሲበዛ የስንፍና ምልክት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው:: "ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፤ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ” ፤ “የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳል" የሚሉት ጥቅሶች ለዚህ ምስክር ናቸው:: (ምሳሌ 20:13 ፣ 23:21)

ሆኖም በእንቅልፋቸው የተጠቀሙ ብዙ ሰዎችም አሉ:: አንቀላፍቶ ሚስቱን ያገኘው አዳም እንዴት ይረሳል? ከኤሳው ጋር ሲታገል የኖረው ያዕቆብ ሲባረክ ያደረውስ በእንቅልፉ አልነበር? ያዕቆብማ ምነው ባልነቃ ያሰኛል:: ሰማይ ድረስ መሰላል ወጥቶ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ያየው በእንቅልፉ ምክንያት ነበር:: በባቢሎን ምርኮ ዘመን የነበረው አቤሜሌክ ደግሞ የእንቅልፋሞች ንጉሥ ቢባል አያንስበትም:: የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየኝ ብሎ ሲጸልይ የነበረው ይህ ሰው በፈጣሪ ፈቃድ ለስድሳ ስድስት ዓመታት ያህል ተኝቶ ነበር:: ከእንቅልፉ ሲነሣም እንቅልፍ ሳይጠግብ እየተበሳጨ ነበር:: ማንቀላፋቱ ግን ብዙ ጉድ ከማየት አዳነው:: (ተረፈ ኤርምያስን ይመልከቱ)

ዛሬ ግን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የአቤሜሌክን የእንቅልፍ ክብረ ወሰን የሰበሩ ሰባቱ እንቅልፋሞች (The Seven Sleepers) የተሰኙ ቅዱሳንን እንተዋወቅ:: ወቅቱ የሮም ነገሥታት አላውያን የነበሩበት ክርስቲያኖች በግፍ እየተገደሉ የነበረበት ዘመነ ሰማዕታት ነው:: ክርስቲያን መሆን ወንጀል በነበረበት በዚያ ወቅት ክርስቲያኖች ከአንበሳ ጋር እየታገሉ በመስቀል እየተሰቀሉ በሰይፍ እየተቀሉ እየሞቱ የነበረበት ዘመን ነው::

በንጉሥ ዳክዮስ ዘመነ መንግሥት (249-251) ታዲያ በንጉሣዊ ምክር ቤቱ ውስጥ አባል የነበሩ ሰባት ወጣት ልዑላን ድንገት ክርስትናን ተቀብለው "ለጣዖት መሥዋዕት አንሠዋም" ብለው አሻፈረኝ አሉ፡፡ ወጣቶቹ ይህን በማድረጋቸው የሚከተለውን ጽኑ ቅጣት ያውቁ ነበረና ፈርተውም በቅርብ ወዳለ አንድ ተራራ ሸሽተው በዋሻ ውስጥ ተደበቁ።
@diyakonhenokhaile

በዚያ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው እያሉ ታዲያ ሰባቱንም እንቅልፍ ይጥላቸዋል፡፡ ንጉሥ ዳክዮስ አሳድዶአቸው ሲመጣ ተኝተው እንዳሉ ያያል:: አውሬው ንጉሥ ሁኔታውን ሲያውቅ እዚያው ዋሻ ውስጥ ይሙቱ ብሎ የዋሻውን መግቢያ በር በግንብ አስደፍኖት ሔደ፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ወጣቶቹ እንቅልፍ ላይ ናቸው::

ከመቶ ሃምሳ እስከ ሁለት መቶ ዓመታት ገደማ ከሆነ በኋላ እነዚህ ወጣቶች ከእንቅልፋቸው ይነቁና የረሃብ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ከእነርሱ አንዱን ወደ ከተማ ሔዶ ምግብ እንዲገዛላቸው ይልኩታል፡፡

ዋሻው የተዘጋበት በር ከዘመን ብዛት ፈርሶ ነበርና የተላከው ወጣት ከዋሻው በቀላሉ ወጥቶ ወደ ከተማ አቀና፡፡ ወደ ከተማ ገብቶ ለሰባቱም የሚበቃቸውን ምግብ አገኘና ሂሳብ ሊከፍል ከኮሮጆው ሳንቲም አወጣ፡፡ ያወጣው ገንዘብ ግን ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት መገበያያ የነበረውን 'የጣዖት አምላኪዎቹን' ነገሥታት የወርቅ ሳንቲም ነበር። ሰባቱ ያንቀላፉ ቅዱሳን ከእንቅልፍ የነቁበት ያ ዘመን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ የኤፌሶን ከተማ ሙሉ በሙሉ ክርስቲያናዊት ከተማ በሆነችበት ደግ ዘመን ነበር፡፡
@diyakonhenokhaile

የሰባቱ ወጣቶች ዝና ወዲያው በወቅቱ የነበሩት ክርስቲያን ነገሥታትና ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ደረሰ፡፡ ወጣቱ ወደ ዋሻው ከተመለሰ በኋላ ግን ሰባቱም ቅዱሳን ድጋሚ እንቅልፍ ጣላቸው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሲተኙ ግን እስከወዲያኛው በክብር አሸለቡ፡፡ ለእነዚህ ሰባት ሰማዕታት በሥፍራው ትልቅ ቤተ መቅደስ ተሠርቶላቸዋል፡፡

"እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ" መዝ.3:5

“የኤፌሶን ወንዝ” ገፅ 64 የግርጌ ማስታወሻ ላይ የተወሰደ

ሙሉ ገቢው ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እድሳት የሚውለው የኤፌሶን ወንዝ መጽሐፍ የመጀመሪያ እትም እያለቀ ነው:: እርስዎ እጅ ገብቶ ይሆን?

አርጋኖን መጻሕፍት መደብር Areganon Book Store

#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
አህያና ግርዛት

አሁን ሐዲስ ኪዳን ነው:: መገረዝ ግዴታ አይደለም:: ዋናው ጥምቀት ነው:: ባንገረዝ ምንም አይጎድልብንም:: በዚህ ጉዳይ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ተነሣ:: አሕዛብ ሳይገረዙ ኖረዋልና ጸረ ግዝረት ሆኑ:: አይሁድ ደግሞ እንዴት ግዝረት እንተዋለን አሉ::

ወደ ክርስትና የተጠሩት እነዚህ ሁለት ወገኖች ሁለቱም ከራሳቸው አመጣጥ አንጻር እውነት አላቸው:: አሕዛብ የማያውቁትን ነገር መቀበል ሊገደዱ አይችሉም:: ክርስትናም አላስገደዳቸውም:: አይሁድ ደግሞ የኖሩበትን መተው አይችሉም:: ክርስትናም ግዝረትን ባይጠይቅም አልከለከለም::

በመጨረሻ በብዙ ምክር የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አሕዛብንም ያላገለለ እስራኤልንም ያላቃለለ ውሳኔ ወሰነች:: ውሳኔውን በጥሩ ቃል በመልእክቱ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል::

“ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ፡፡ ... እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር" 1 ቆሮንቶስ 7:18፣ 20

በዚህ መሠረት ኦሪትን ተቀብለው ተገርዘው ወደ ክርስትና የተጠሩት እስራኤል በመገረዛቸው ይቀጥሉ እንጂ ወደ አለመገረዝ አይመለሱ ተባለላቸው:: ሳይገረዙ የተጠሩት አሕዛብ ግን መገረዝ የእነርሱ ልማድ አልነበረምና አይገረዙ ተባለ:: ይህ ለእስራኤል የተወሰነ ውሳኔም እንደ ኢትዮጵያ ኦሪትን ተቀብላ ለኖረችና ተገርዛ ሳለ የተጠራች (ሐውልቶችዋ ሳይቀር የተገረዘ ወንድን የሚያሳዩባት) ሀገርም ላይ ይጸናል::

ይህ ውሳኔ ለሁሉም እንደ ግዝረት ያሉ ሕግጋት ይሠራል::

“ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ”

"ማንም አህያ እየበላ ተጠርቶ እንደ ሆነ አህያ ወዳለመብላት አይመለስ ፤ ማንም አህያ ሳይበላ ተጠርቶ እንደሆነም አህያ አይብላ"

እስራኤል በግዝረት ቀጥሉ ሲባሉ ደስ አላቸው አሕዛብም አትገረዙ ሲባል ደስ አላቸው:: ለእስራኤል ሔደህ የአሕዛብን ዜና ብትነግራቸው ምንም እንኩዋን ግዝረት ግድ ባይሆንም ቅር ይላቸዋል:: የአህያ መበላት ዜናም የሚያስደስተው አህያን እንዴት ልንተው እንችላለን ብለው ለተጨነቁ አሕዛብ ብቻ እንጂ ለእኛ ሆድ የሚበጠብጥ ዜና ነው::

ከዚያ ውጪ እንደ ክርስቲያን ብሉ ብለን ልንሰብከው የሚገባን የሕይወት እንጀራ ሥጋ ወደሙ ብቻ ነው::

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት ይኑር!

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ቄራ(የበሬ)

#share

▫️ @diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
Forwarded from Janderebaw Media
በጃን ማዕተብ የተሰናዳውን "ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ" የተሰኘውን ዘጋቢ ፊልም በጃንደረባው ሚድያ አሁን መመልከት ይችላሉ:: ኦርቶዶክስ ማለት ርትዕት የቀናች ማለት እንደመሆኑ ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ ማለት "ወደ ርትዕት ሃይማኖት መመለስ" ማለት ነው::

በዚህ ዘለግ ያለ ፊልም ላይ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን የተመለሱ ልጆች "ለምን ሔዱ? ለምን መጡ? እንዴት እንመናቸው?" የሚሉ አንገብጋቢ ጥያቄዎችና በአጠቃላይ ተቅዋማዊ ዕቅበተ እምነት ላይ ዝርዝር መረጃዎች ቀርበዋል:: ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የምትጨነቁ የሚመለሱ ሰዎችም አመላለሳቸው ምን መምሰል እንዳለበት የሚገዳችሁ ሁሉ ይህንን ዘለግ ያለ ዘጋቢ ፊልም በትዕግሥት ተመልከቱ::

https://youtu.be/HqyhPq_Jf-g
በአንቺ ዘንድ ያለው ደስታ ከኤልሳቤጥ ደስታ የሚበልጥ ሲሆን የምሥራቹን ሳትንቂ ደስታዋን ልትካፈይ ወደ እርስዋ የገሰገስሽው እመቤታችን ሆይ አንቺ የደረሰብሽ ኀዘን ከኀዘናችን እጅግ ቢበልጥም ፣

አንቺ ያሳለፍሽው ስደት ከስደታችን እጅግ ቢልቅም ፣ ዐርብ ዕለት ያለቀስሽው ልቅሶሽ ከልቅሶአችን ብዙ እጥፍ ቢሆንም የምናዝነውና መከራን የምንታገሠው በአቅማችን ነውና ኀዘናችንን ለመካፈል ወደ እኛም ከመምጣት እንዳትቀሪ፡፡

እርግጥ ነው እኛ እንደ ኤልሳቤጥ ለአንቺ የሚሰግድ ፅንስ በሆዳችን የለም፡፡ በእኛ ዘንድ የተፀነሰው 'ለፀነሱ ወዮላቸው' 'ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች' ተብሎ የተነገረለት የኃጢአት ፅንስ ነው፡፡ እንደ ኤልሳቤጥ በደስታ የሚያስጮኸን ሳይሆን በኀዘን የሚውጠን የበደል ፅንስ ይዘናልና ድንግል ሆይ እኛን ለመርዳት ፍጠኚ፡፡ በሆዳችን የያዝነውን የኃጢአት ፅንስ ነቢዩ ዳዊት እንደተመኘው በሆድሽ ውስጥ በያዝሽው ዓለት ላይ እስክንፈጠፍጠውና ዕረፍት እስክናገኝ ድረስ ጓጉተናልና ወደ ኤልሳቤጥ እንደመጣሽ ወደ እኛም ነዪ፡፡

በተራራማው ሀገር በአስቸጋሪ መንገድ ወደ ኤልሳቤጥ የገሰገስሽው እመቤታችን ሆይ ወደ እኛ ነይ ስንልሽም መንገዱ እንደማይመችሽ እናውቃለን፡፡ 'ተራራው ዝቅ ይበል' ተብሎ የተነገረለት ተራራማው ልባችን በትዕቢት ተራሮች ስለተሞላ ከይሁዳ ተራሮች በላይ ወደ እኛ መምጣት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሉቃ. ፫፥፫ ድንጋይ ብቻ የሆነው ጭንጫው ልባችን ለመንገደኛ የማይመች እንደሆነ እናውቃለን፡፡

የኃጢአት ወኃ ገብ የሆነው ሕሊናችንም አቋርጠሽ ለመምጣት የሚያስቸግር የበደል ጭቃ የሚበዛው መሆኑን እናውቃለን፡፡ ሆኖም ወደ ተራራ ልባችን ፣ ወደ ጭቃው ሕይወታችን እንድትመጪ እንሻለንና ከአባቶቻችን ጋር 'ንዒ ኀቤየ' 'ንዒ ርግብየ' ከእናቶቻችን ጋር 'ነይ ነይ እምዬ ማርያም' ማለትን አናቆምም፡፡

ልባችን ምንስ ዓይነት ተራራ ቢሆን ላንቺ ምንሽ ነው? 'ይህን ተራራ ወደዚያ ሒድ' የምትይበት የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት 'ካመንሽው ብፅዕት' ዘንድ ይጠፋልን?

እንደ ዘሩባቤል 'ታላቁ ተራራ ሆይ አንተ ምንድርን ነህ? በማርያም ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ' የምትዪበት የልዑል ኃይል በሆድሽ አይደለምን? ሕይወታችን ምንም

እንኳን ቢጨቀይም አንቺ እንደሆንሽ ከነ ልጅሽ በሚሸት በረት ውስጥ እንኳን ለመምጣት አልተጸየፍሽም:: ሕይወታችን እንደ እንስሳ ቢሆንብሽ እንኳን ልጅሽን ከእንስሳት መካከል ለማስተኛት ፈቃድሽ አልነበረምን? ወደ እኛ መምጣትሸን ተስፋ እያደረግን ቅዱሳኑ ሁሉ 'ወደ እኔ ነይ' 'ወደ እኛ ነይ' ብለው የደረሱልሽን ዜማ እያደረስን መምጣትሽን እንጠባበቃለን፡፡
🙏🙏

▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
2025/06/29 14:31:27
Back to Top
HTML Embed Code: