በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!'
መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም 'ለሰው ፊት የማያዳላ' እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም። (ሐዋ 10፥34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡
'የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ' ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው።
(Deacon Abel Kassahun Mekuria)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09

👍24
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
መልካም በዓል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
መልካም በዓል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
❤12👍7
#ቤተ_ክርስቲያን_ሆይ፦
የምለው ባጣ እንዲህ አልኩኝ ቤተክርስቲያን ሆይ ዕንባችን አልቆ ዕዥ ያነባንብሽ፣ የእኛ የማልቀሻ ስፍራችን፣ የኃጢአት ሸክም ማውረጃችን ሰላም እልሻለው እንዳንቺ ያለ ከቶ አላየንም፣ መሠረትሽ ደም፣ ግድግዳሽ ውኃ፣ ሕንጻሽ የነፍሶች ግጥግጥ፣ ጉልላትሽ ተስፋ ነው፡፡
ጠላት በውጭ ሲያቅተው በውስጥ የሚታገልሽ ላይነቅል የሚነቀንቅሽ፣ ለገንዘብ እንጂ ለነፍስ ግድ በማይላቸው ጽንፈኞች የተጨነቅሽ አንቺ ስንዱ እመቤት ሆይ ሙሽራሽ ሊመጣ ነው መሰለኝ ጉልበትሽን አጠንክሪ፡፡
ሰው ሁሉ በዘረኝነት ሰክሮ ቋንቋ ሲጠፋው አንቺ ግን በመንፈስ ቅዱስ ሰክረሽ በዓለም ቋንቋ ያወረሽ ከቶ ምን አግኝቶሽ ነው ዛሬ፡፡ ፓለቲከኞች እና ዘረኞች ለዛሬ እንጂ ለነገ የማይፈልጉሽ አንቺን ባያከብሩ እንኳን የሀገር ውለታ መሆንሽን ግን ለምን ረሱ?
አንቺ የሰማይ ደጃፍ፣ የአርያም አምሳል፣ የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ደጅ መጥኛ፣ የድሆች መጠጊያ፣ የተገፉት መጽናኛ፣ የማልቀሻ ስፍራ፣ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት መቀበያ ቤተክርስቲያን ሆይ አጥፊዎሽ ይጥፉ እንጂ አንቺ ግን መቼም ቢሆን ክፉ አይንካሽ፡፡
በእለተ አርብ የደም ቀለበት ከአምላክሽ ጋር ያሰርሽ በሃምሳኛው ቀን ሠርግሽን ያከበርሽ በጌታ ደም የተመሰረትሽ ቤተክርስቲያኔ ሆይ ክፉ አይንካሽ፡፡ ጠላቶችሽ ይጠፋሉ እንጂ አንቺ ግን ዘላለም ትኖሪያለሽና መሰረትሽ ክርስቶስ ነውና ዘለዓለም ትኖሪ አለሽ፡፡
(Via Bizuneh Admassu)

👍12❤10
Forwarded from ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ (◦•●Yaredo●•◦)
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሃሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን የምናሳውቅ ይሆናል።
የብፁዕነታቸው ቡረከት ይደርብን
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS

😢32👍12
+ የመስቀሉ ደም +
መስቀል ደም አለው ወይ? ከእንጨት የተሠራ ነገር ቢወጉት ይፋፋቅ ይሆናል እንጂ አይደማም::
ስለ ክርስቶስ መስቀል ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ግን "በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ" አለ:: (ቆላ. 1:20)
"ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ"
የመስቀሉ ደም የሚለው ቃል መስቀሉ ደምቶአል ለማለት አይደለም:: ጌታ የተሰቀለበት መስቀል ጠዋት ሦስት ሰዓት ሊቶስጥራ ላይ ጌታን ሲያሸክሙት የመስቀሉ ቀለም የእንጨት ብቻ ነበረ:: ክርስቶስ መስቀሉን ተሸክሞ ለሦስት ሰዓታት ከወጣና ለሦስት ሰዓት ተሰቅሎ ነፍሱን ከሠጠ በኋላ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሥጋውን ከመስቀሉ ሲያወርዱት የመስቀሉ መልክ የእንጨት አልነበረም:: በጥሩ ባለሙያ ቀይ ቀለም የተቀባ እስኪመስል ድረስ መስቀሉ በክርስቶስ ደም ታጥቦ ነበር:: እሾህ ከደፋው ራሱ ፣ ከተቸነከሩት እጆቹ ፣ ከተገረፈው ጀርባው ፣ ሚስማር ከያዛቸው እግሮቹ እንደ ውኃ የፈሰሰው ደም በመስቀሉ ላይ ፈስሶ ነበር::
መፍሰስን ለመግለፅ በግእዝ ሁለት ቃላት አሉ "ክዒው" እና "ውኂዝ" የሚሉ:: ወደ አማርኛ ሲመለሱ ሁለቱም መፍሰስ ቢሆኑም ግን ልዩነት አላቸው:: አንድ ሰው በብርጭቆ ውኃ ቢያፈስስ ውኃው ፈሰሰ ይባላል:: የወንዝ ውኃ ሲፈስስም ፈሰሰ ይባላል:: ግእዙ ግን ከአንድ ብርጭቆ ለሚፈስሰው ውኃ "ተክዕወ" ሲል እንደ ወንዝ ላለው ብዙ ፈሳሽ ደግሞ "ውኅዘ" ብሎ ይለየዋል::
ቅዱስ ኤፍሬም ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ብለው አንገታቸው ተሰይፎ እንደሞቱ ሲናገር "ወከዓዉ ደሞሙ በእንተ መንግሥተ ሰማያት" "ስለ መንግሥተ ሰማያት ደማቸውን አፈሰሱ" ይላል::
ይኸው አባት ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ክርስቶስ ደም መፍሰስ ሲናገር ግን "በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሖሙ ለመሃይምናን" "በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ያመኑትን አነጻቸው" ብሎአል:: የጌታችንን ደም መፍሰስ ለወንዝ ፈሳሽ በሚነገርበት ቃል ውኂዝ የተባለው ከጌታችን የፈሰሰው ደም ከመላው ሰውነቱ ስለነበረ ነው::
መስቀሉን ለዓመታት መፈለግ ፣ ማክበር ግድ የሆነውም መስቀሉ ዓለም በተገዛበት በከበረ ደም ስለተቀደሰ ነው:: (እስመ ተቀደሰ በደመ ክርስቶስ መድኅን)
ወዳጄ ሆይ በደም የታጠበ መስቀል ስታይ ምን ይሰማሃል? በደም የተቀደሰው የመስቀሉ ክብር አይታይህም? አዎ መስቀል ክቡር ነው::
የመስቀሉ ደም ሌላ የሚያሳየው ክብርም አለ:: እርሱም የእኔና የአንተን ክብር ነው:: ምክንያቱም ያ ሁሉ ደም የፈሰሰው ለእኔና ለአንተ ነው:: በሰዎች የመጠሪያ ስምህ ማን ነው? ማን ብለው ሲጠሩህ አቤት ትላለህ?
ቅዱስ ጳውሎስ ግን ለእኔም ለአንተም ስም አውጥቶልናል:: ጳውሎስ አንተን ለሰዎች ሲያስተውቅህ እንዲህ ብሎ ነው :-
"ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው" 1ቆሮ.8:11
ወዳጄ የአንተ ክብር እዚህ ድረስ ነው:: አንተ ክርስቶስ የሞተልህ ወንድም ነህ:: አንቺ ክርስቶስ የሞተልሽ እኅት ነሽ::
ቅዱስ ጴጥሮስ ጨምሮበታል :-
"በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ" 1ኛ ጴጥ. 1:18-19 ቅዱስ ያሬድም "አኮ በወርቅ ኃላፊ ዘተሳየጠነ አላ በደሙ ክቡር ቤዘወነ" ብሎ ዘምሮታል::
የእኔና አንተ ዋጋ በወርቅ በብር የሚመዘን አይደለም:: ዋጋችን በመስቀል ላይ የፈሰሰው ክቡር ደም ነው::
ጌታ "መላእክቶቻቸው የአባቴን ፊት ያያሉና ማንንም እንዳትንቁ" ብሎ ነበር:: (ማቴ.18:10) ሰውን ስለ መልአኩ ብለን እንዳንንቅ ከተነገረን ስለፈሰሰለት ደምማ ምንኛ ልናከብረው ይገባን ይሆን?
ውድ ክፍያ ተከፍሎ ልብስ የተገዛለት ልጅ ልብሱን ስለተከፈለበት ዋጋ ሲል ተጠንቅቆ ይለብሰዋል:: በውድ የተገዛ ዕቃ የተሠጠው ሰው በጥንቃቄ ይጠቀምበታል:: የእኛ ሰውነት ግን የተገዛው በአምላካዊ ደም ነው:: እንደተከፈለልን እየኖርን ይሆን?
ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ብሔራዊ ቴአትር ጋር ያለውን ሐውልት እጅግ በውድ ዋጋ አሠርተው ነበር ይባላል:: ንጉሡ የአንበሳ ሐውልት ሊመርቁ ሲከፍቱ ግን ሐውልቱ አንበሳ አይመስልም:: የአንበሳና ቀጭኔ ዲቃላ መስሎ ጉብ ብሎአል:: ንጉሡ አንጀታቸው እያረረ ከመረቁ በኋላ ንግግር ሲያደርጉ "ይህ አንበሳ አንበሳ ባይመስልም የወጣበት ገንዘብ ግን አንበሳ ያደርገዋል" አሉ ይባላል::
የእኛም ሕይወት እንደዚያ ነው:: ስንታይ ምናችንም ክርስቶስን አይመስልም:: አንዳንዴም በክፋት ከሰውነት ተራ እንወርዳለን:: ሆኖም እንዲህ ብንበድልም "ክርስቶስ የሞተልን ነን"
ምንም እንኳን ክርስቲያን ባንመስል የተከፈለልን ደም የክርስቶስ ያደርገናል:: ምንም እንኳን የከበረ ሕይወት ባይኖረንም የፈሰሰልን ክቡር ደም ክቡራን ያደርገናል::
"በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ"
1ኛ ቆሮ.6:19
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 17 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

👍31❤6😢2
Forwarded from ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ (◦•●Yaredo●•◦)
በአርሲ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙ ተገለጸ!!!
መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በመስቀል ደመራ ዋዜማ መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም በአርሲ ሀገረ ስብከት በምሥራቅ አርሲ ዞን በኦንቆሎ ዋቤ ወረዳ ብሎ ቀበሌ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።
ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ምእመናን ላይ ጭካኔ የተላበሱ ጭፍጨፋዎች በመስፋፋት ላይ የሚገኙ ሲሆን በዕለቱ ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በተፈጸመው በዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ 6 ንጹሃን ዜጎች የተገደሉ ሲሆን አንድ ሰው የት እንደደረሰ ለማወቅ አለመቻሉ ነው የተገለጸው።
ከሟቾቹ በተጨማሪ 5 ንጹሃን ዜጎች በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኙም ተገልጿል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
🔸 @Z_TEWODROS
✍️Comment @Channel_admin09
መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በመስቀል ደመራ ዋዜማ መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም በአርሲ ሀገረ ስብከት በምሥራቅ አርሲ ዞን በኦንቆሎ ዋቤ ወረዳ ብሎ ቀበሌ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።
ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ምእመናን ላይ ጭካኔ የተላበሱ ጭፍጨፋዎች በመስፋፋት ላይ የሚገኙ ሲሆን በዕለቱ ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በተፈጸመው በዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ 6 ንጹሃን ዜጎች የተገደሉ ሲሆን አንድ ሰው የት እንደደረሰ ለማወቅ አለመቻሉ ነው የተገለጸው።
ከሟቾቹ በተጨማሪ 5 ንጹሃን ዜጎች በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኙም ተገልጿል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
🔸 @Z_TEWODROS
✍️Comment @Channel_admin09
😢22👍12🕊3❤1
ብዙኃን ማርያም
በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው
ክፍል አንድ
[ ክፍል ሁለትን በሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ቻናል ላይ ከታች ባለው ሊንክ ታገኙታላችሁ ]
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤
በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን ‹‹ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ›› ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ መካከል ፫፻፲፰ (ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው ‹‹ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው›› ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም ‹‹ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን›› ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡
፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት ‹‹ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን›› የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት ‹‹ብዙኃን ማርያም›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው ‹‹የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል›› አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር ‹‹የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ›› የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ ‹‹ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት›› ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡
ቀጣዩን ክፍል በሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ቻናል ላይ በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ
| https://www.tg-me.com/z_tewodros/10859 |

Telegram
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ብዙኃን ማርያም
ክፍል ሁለት
[ ክፍል አንድን በመምህር ዘበነ ለማ ቻናል ላይ ከታች ባለው ሊንክ ታገኙታላችሁ ]
ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው…

👍17🕊1
ማስታወቂያ
🛸ሰላም የዚህ ቻናል ተከታታዮች
🧱ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ ብቻ 🧱
☎️ ምርትና አገልግሎታችሁን እንዲሁም አዲስ የከፈታችሁትን ቻናል ወይም ግሩፕ ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ የማስታወቂያውን ይዘት ተመልክተን ካረጋገጥን በኋላ በተመጣጣኝ ዋጋ የምንሰራ መሆኑን ስንገልፅ በደስታ ነው።
🚀ማስተዋወቅ የምትፈልጉትን በዚህ አድራሻ @channel_admin09 ላይ መላክ ትችላላችሁ።
🛑በተመጣጣኝ ዋጋ ነው😁

👍4❤1😢1
#ምጽዋት_ሥርየተ_ኃጢአትን_ትሰጣለች፡፡ ሞትንም ቢኾን ታርቃለች፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም ቀጥዬ ግልጽ አደርግልሃለሁ፡፡
“መጽውቶ ከሞት የተረፈ ማን አለ?” ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ ወዳጄ ሆይ! ምጽዋት ሞትን እንድታርቅ ኃይል ጉልበት እንዳላት በእውን ከተደረገ ታሪክ ተነሥቼ እነግርሃለሁና የምነግርህን ነገር አትጠራጠር፡፡
ጣቢታ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፡፡ መልካም ሥራን የሞላባትና ምጽዋትን የምትወድ በዚህም ለራሷ መዝገብ የምታከማች ነበረች፡፡ ለመበለቶች ልብስንና የሚያስፈልጋቸውን ኹሉ ትሰጣቸው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ሞተች፡፡
አሁን ደግሞ እነዚያ እርሷ ስትረዳቸው የነበሩ መበለቶች በየትኛው ሰዓት ብድራታቸውን እንደሚከፍሉ ተመልከት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን መበለቶቹ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ኼዱ፡፡ ጣቢታ የሰጠቻቸውን ልብስንና ሌላውን ኹሉ አሳዩት፡፡ ከእነርሱ ጋር በሕይወተ ሥጋ ሳለች ምን ምን ታደርግላቸው እንደ ነበረች ነገሩት፡፡ እንደ እናት የምትኾንላቸውን እንደ አጡ አልቅሰው ነገሩት፡፡ ስለ እነርሱ እጅግ እንዲያዝንም አደረጉት፡፡
የተወደደ ጴጥሮስስ ምን አደረገ? “ኹሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮ ጸለየ፡፡ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ ‘ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ’ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች፡፡ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች፡፡ እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፡፡ ምእመናንንና መበለቶችንም ጠራ፡፡ ሕያውም ኾና በፊታቸው አቆማት” (ሐዋ.9፡40-41)፡፡
የሐዋርያውን ኃይል ወይም በሐዋርያው አድሮ እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ አስተዋልህን? በወዲያኛው ዓለምስ ተወውና በዚህ ዓለምም ሳይቀር ጣቢታ ስለ መልካም ሥራዋ ምን እንደ ተቀበለች ተገነዘብን? እርሷ ለመበለቶች የሰጠችውንና መበለቶቹም ለእርሷ የሰጡትን አየህን? እርሷ ምግብና ልብስ ሰጠቻቸው፤ እነርሱ ግን ከሞት ወደ ሕይወት እንድትመጣ አደረጓት፡፡ ለመበለቶቹ ባሳየችው ቸርነት ቸሩ እግዚአብሔር ብድራቷን ከፈላት፡፡
እንግዲህ የምጽዋት የመድኃኒነቷን ኃይል ተመለከትህን? እንግዲያውስ እኛም ይህን መድኃኒት ለራሳችን እናዘጋጅ፡፡ መድኃኒቱ ይህን ያህል ጽኑ መድኃኒት ቢኾንም ቅሉ እጅግ ርካሽ እንጂ ውድ አይደለምና ለራሳችን እንግዛ፡፡ ይህን መድኃኒት ለመግዛት ብዙ ወጪ አይጠይቅምና እንግዛ፡፡ መልካም ሥራ መልካም የሚባለው በሚሰጡት ገንዘብ መጠን ሳይኾን በሚሰጡት የእደ ልብ ስፋት መጠን ነውና እንግዛ፡፡ አንድ ሰው አንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ሰጥቶ እጅግ እንደ ሰጠ የሚቈጠርለትም እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን የሚሻው ወደንና ፈቅደን የምንሰጠው በጎ ፈቃዳችንን መኾኑን የሚያሳይ ነውና ይህን እንግዛ፡፡ መበለቶች፥ እንደ ጣቢታ ከሞተ ነፍስ ይታደጉን ዘንድ ይህን መድኃኒት ከእነርሱ እንግዛ፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

👍25❤4❤🔥4
ሚስትህን አትናቃት
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
“በቤት ውስጥ በሚስትህ ምክንያት አንድ ደስ የማያሰኝ ስሕተት ቢፈጠር ‘አይዞሽ’ ልትላት ይገባል እንጂ ኀዘኗን ልታባብሰው አይገባህም፡፡ ኹሉንም ነገር ብታጣም እንኳን ከጎኗ ኹን፡፡
እርግጥ ነው ለባልዋ ደንታ ከሌላት ሚስት በላይ ምንም አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ በእናንተ መካከል ጸብ ክርክር ከሚፈጥር የሚስትህ ጥፋት በላይ አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ ስለዚሁ ዋና ምክንያት ግን ለእርስዋ ያለህ ፍቅር እጅግ ጽኑዕ ሊኾን ይገባዋል፡፡ እኛ ክርስቲያኖች አንዳችን የሌላችንን ሸክም እንድንሸከም የታዘዝን ከኾነ፥ ከዚህ በላይ ደግሞ አንተ የሚስትህን ሸክም ልትሸከም ይገባሃል፡፡
በመኾኑም ድኻ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት በፍጹም አትናቃት፡፡ ሰነፍ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት አስተካክላት እንጂ አታዋርዳት፡፡ እርስዋ አካልህ ነችና፤ አንተም አካልዋ ነህና፤ አንድ አካል ናችሁና፡፡
‘ክፉ ነች፤ ቁጡ ነች፤ ራስዋን መቈጣጠር የማትችል ግልፍተኛ ነች’ ልትለኝ ትችላለህ፡፡ ስለዚሁ ጠባይዋ እጅግ ልታዝን ይገባሃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ጠባይ ያርቅላት ዘንድ ጸልይላት እንጂ አንተም መልሰህ አትቈጣት፡፡ ልታሳምናት ሞክር እንጂ ወደ ሙግት አትግባ፡፡ እነዚህን ክፍተቶችዋን ከእርስዋ ለማራቅ ኹሉንም ዓይነት በጎ ዘዴዎችን ተጠቀም፡፡”
“ይህን እንደማድረግ ሚስትህን የምትመታትና የምታሠቃያት ከኾነ ግን እነዚህ ሕመሞችዋ እንዲድኑ አታደርጋቸውም፡፡
ኃይለኝነት የሚወገደው በጭካኔ ሥራ ሳይኾን በየውሃት ነውና፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም ሚስትህ በየውሃት ስትይዛት ከእግዚአብሔር ዘንድ ሹመት ሽልማት እንደምታገኝ አስታውስ፡፡
ከአሕዛብ ፈላስፎች አንዱ ክፉ፣ መራራና ሥርዓት የለሽ ሚስት ነበረችው ይባላል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ለምን ከእርስዋ ጋር እንደሚኖር (ለምን እንደማይፈታት) በተጠየቀ ጊዜ ጠቢቡ ሰው በገዛ ቤቱ ውስጥ የፍልስፍና ትምህርት ቤት እንዳለው ነበር የመለሰው፡፡ ‘ዕለት ዕለት በዚህ ትምህርት ቤት የምማር ከኾነ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ታጋሽ እኾናለሁ’ ነበር ያለው፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እኔ ግን መላእክት እንዲያውም ከእነርሱም በላይ የዋሃን ኾነን እግዚአብሔርን እንድንመስለው ከታዘዝነው ከእኛ ይልቅ አረማውያን ሰዎች ጠቢባን ኾነው ስመለከታቸው ፈጽሜ አለቅሳለሁ፡፡ ያ ፈላስፋ ሚስቱን እንዳይፈታት ምክንያት የኾነው የእርስዋ ክፉ ጠባይ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ‘ይህ ፈላስፋ ይህቺን ሴት ሚስት ትኾነው ዘንድ ያገባት ይህን ለማግኘት ብሎ ነው’ ይላሉ፡፡
አንተም ዕጮኛ ስትመርጥ በምርጫህ ተሳስተህ ክፉ ሚስት አግብተህ ከኾነ (ብታገባ) ቢያንስ ቢያንስ ይህን አረማዊ ፈላስፋ አብነት አድርገው፡፡ ሚስትህን ለማስተካከል የተቻለህን አድርግ፡፡ ክፋትዋን በሌላ ክፋት አትመልስላት፡፡
ከእርስዋ ጋር ኾነህ የትዳርን ቀንበር የምትሸከም ከኾነ ሌሎች ብዙ ረብ ጥቅሞችንም ታገኛለህና፤ መንፈሳዊ ተግባራትን ለመተግበር ቀላል ይኾንልሃልና፡፡”

👍35❤14❤🔥2
“ማግባት ለሚሹ” የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር
ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡
ስለዚህ ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡
አባቶች ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡
እናቶች ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡
እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡
እናንተ ልጃገረዶች ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡
የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡

👍44❤24❤🔥1
ወርኃ ጽጌ -
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡
በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡
የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡

👍27❤9
እግዚአብሔር ለምን ይቆጣናል?
እግዚአብሔር የሚቆጣን ስለ ራሱ ክብር ብሎ አይደለም፡፡ ብንሰድበውም ብንክደውም እንኳን የሚቆጣን ስለ ሰደብነው ወይም ስለ ካድነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም እኛ ስለ ካድነው እግዚአብሔር ምንም አይጎድልበትም፡፡ እኛ ስለ ሰደብነው እግዚአብሔር ምንም አይጎድልበትም፡፡ ይልቁንም እንዲህ በማድረጋችን የምንጎዳው እኛው ነን፡፡ በመኾኑም የሚቀጣን ለእኛ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ ነው፡፡ የሚቆነጥጠን ለእኛ ካለው ወደርየለሽ ጠብቆቱ የተነሣ ነው፡፡ እርሱን እየናቅነውና እየራቅነው ስንሔድ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን ስንሔድ እንዳንጎዳ ሽቶ ነው፡፡
ብርሃንን የሚጠላ ሰው ብርሃኑን ሊጎዳው አይችልም፤ በጨለማ ውስጥ በመቀመጡ ራሱን ይጎዳል እንጂ፤ በራሱ ላይ የጉዳት ዓይነትን ይከምራል እንጂ፡፡ እኛም እግዚአብሔርን ብንጠላው በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ ምንም ነገር አናጎድልም፤ ምረረ ገሃነምን በራሳችን ላይ እንፈርዳለን እንጂ፡፡
እግዚአብሔር በእኛ እይታ እጅግ ክፉ የሚመስሉ ነገሮች በእኛ ላይ ሲያመጣ እኛን ከመበቀል አንጻር አይደለም፤ ይበልጥ ወደ እርሱ እንድንቀርብ እንጂ፡፡ ሐኪሞች አእምሮአቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡዋቸው አይከፋቸውም፡፡ በዚህ አኩርፈውም መድኃኒት ማድረጋቸውን አያቆሙም፡፡ ሕሙማኑ ለዚህ በሽታ የዳረጋቸውን በሽታ ይፈውሱላቸው ዘንድ ይተጋሉ እንጂ፡፡ የሕሙማኑን ችግር እንጂ የእነርሱ መሰደብ አያሳስባቸውም፡፡ እግዚአብሔር አምላካችንም የሚቆነጥጠን ስለ ሠራነው ኃጢአት አይደለም፤ ኃጢአት ሕመም ነውና ከሕመማችን እንድንፈወስ ሽቶ እንጂ፡፡
ቸር አባት ሆይ! ይህ ከአእምሮ የሚያልፍና የዚህ ዓለም ቋንቋ ሊገልፀው የማይችለው ፍቅርህና ጠብቆትህ ዘወትር እናስበው ዘንድ፣ አስበንም በተግባር እንኖረው ዘንድ አእምሮን ለብዎን ስጠን፡፡ ለዚህ ግሩም ፍቅርህ ያልተገባንና የዕውቀት ግምጃ ቤት ብቻ ኾነን እንዳንገኝ ብርታቱን አድለን፡፡ አሜን!
(Mekrez z tewahido)

❤18👍12😢1🕊1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሰማዕት ቅድስት አርሴማ እረፍት - መስከረም 29
የቅድስት አርሴማ እናት አትናስያ ትባላለች ልጅ በማጣት ለረጅም ዘመን ታዝን ታለቅስ ነበር በኃላም እግዚያብሔር ልመናዋን ሰማት ይህችን ክብርት ቅድስት ልጅንም ሰጣት፤ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ነው የተወለደችው፤15 ዓመት ሲሆናት ሊያጋቡአት አሰቡ እርሷ ግን ይህን አልወደደችም፤ በደናግል ገዳም ገብታ በተጋድሎ መኖር ጀመረች። ከዚህ በኃላ እንዲህ ሆነ ከሃዲው ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ሊያገባት ወደደ ቅድስት አርሴማ ግን ከደናግሉ ጋር ሸሽታ ወደ አርማንያ ሄደች በዚያም በበርሃ ለጥቂት ቀናት ተቀመጠች በኃላ ላይ ድርጣድስ የሚባል አገር ገዢ በበርሃ እንደሚኖሩ ሰማ ወታደሮችንም ልኮ አስመጣቸው፤ የቅድስት አርሴማን መልክ በተመለከተ ጊዜ ፈዞ ደንዝዞ ቀረ የፊቷ ውበት እጹብ ድንቅ፤ ግርማዋ የሚያስደነግጥ ልብ የሚያርድ ነበርና፤ስለዚህም ሊያሰቃያት አልደፈረም በእንክብካቤ በሰገነት ላይ አኖራት፤ ሌሎቹን ግን ለጣአት እንዲሰግዱ ገረፋቸው፤ ቅድስት አርሴማ እኔንም አሰቃዩኝ እያለች አምርራ ታለቀስ ነበር። ድርጣድስ ብዙ ጊዜ ሊሸነግላት ሞከረ እርሷ ግን ትዘልፈው ጣኦታቱንም ትረግም ነበር፤ እርሷ ጸንታ ደናግሉን ታጸና ነበር ትመክራቸው ታረጋጋቸው ነበር፤ ድርጣድስ ሽንገላው እንደማያዋጠው በአወቀ ጊዜ ማሰቃየት ጀመረ፤ በመጨረሻም ከብዙ ስቃይ በኃላ መስከረም 29 ቀን አንገቷን ቆረጣት ከእረሷ ጋር 27 ሰማዕታት አብረው ተሰይፈዋል። የሰማዕቷ በረከት ከእኛ ጋር ይሁን፡፡

👍27❤13🕊2❤🔥1
ሥራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲገባ በቅድሚያ የሚያየው ነገር ከቤቱ ግድግዳ ላይ ያለውን የክርስቶስን ቅዱስ ሥዕል ነው። ሥራው አድካሚ ነው። "ይበቃኛል" የሚለውን ዓይነት ገንዘብ አያገኝበትም። ስለዚህ ሁል ጊዜ እንደ ተነጫነጨና እንዳማረረ ነው።
ከሥራ ደክሞት ቤት ሲገባ በመጀመሪያ የሚያገኘው ደግሞ ሥዕለ ክርስቶስን በመሆኑ፣ የመጀመሪያውን ምሬቱን በጸሎት የሚገልጸው በርሱ ፊት ነው።
"ተው ግን ተው ጌታዬ ሎተሪ እንዲደርሰኝ አድርግ" ይላል ዘወትር ወደ ሥዕሉ ዞሮ።
ከሥራ ወደ ቤቱ ሲገባ ሥዕሉ ፊት የሚያቀርበው የሁልጊዜ ልመናው/ንጭንጩ/ምሬቱ ይህ ነው:-
ከዕለታት በአንዱ ታዲያ ሥራ ውሎ ደክሞት ወደ ቤቱ ሲገባ እንደለመደው "ጌታ ሆይ ምናለ ግን ሎተሪ ቢደርሰኝ?" ሲል
የጌታ ሥዕልም በሰው አንደበት "ልጄ እባክህ እስኪ መጀመሪያ ትኬት ቁረጥ" አለው። ለካንስ "ሎተሪ ካልደረሰኝ" ሲል የነበረው ትኬት እንኳን ሳይቆርጥ ነበር።
እንደዚህ ሰውዬ የድርሻችንን ሳንወጣ ዱብ የሚል ስኬትን የምንጠብቅ ብዙዎች እንኖራለን፤ እንዲሁ ቁጭ ብለን ፈጣሪን "ካልሰጠኸኝ" ብለን የምናማርር።
በቅድሚያ እስኪ ትኬቱን እንቁረጥ፤ የድርሻችንን እንወጣ።
(Hilina Belete ZeHohitebirhan)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
ከሥራ ደክሞት ቤት ሲገባ በመጀመሪያ የሚያገኘው ደግሞ ሥዕለ ክርስቶስን በመሆኑ፣ የመጀመሪያውን ምሬቱን በጸሎት የሚገልጸው በርሱ ፊት ነው።
"ተው ግን ተው ጌታዬ ሎተሪ እንዲደርሰኝ አድርግ" ይላል ዘወትር ወደ ሥዕሉ ዞሮ።
ከሥራ ወደ ቤቱ ሲገባ ሥዕሉ ፊት የሚያቀርበው የሁልጊዜ ልመናው/ንጭንጩ/ምሬቱ ይህ ነው:-
ከዕለታት በአንዱ ታዲያ ሥራ ውሎ ደክሞት ወደ ቤቱ ሲገባ እንደለመደው "ጌታ ሆይ ምናለ ግን ሎተሪ ቢደርሰኝ?" ሲል
የጌታ ሥዕልም በሰው አንደበት "ልጄ እባክህ እስኪ መጀመሪያ ትኬት ቁረጥ" አለው። ለካንስ "ሎተሪ ካልደረሰኝ" ሲል የነበረው ትኬት እንኳን ሳይቆርጥ ነበር።
እንደዚህ ሰውዬ የድርሻችንን ሳንወጣ ዱብ የሚል ስኬትን የምንጠብቅ ብዙዎች እንኖራለን፤ እንዲሁ ቁጭ ብለን ፈጣሪን "ካልሰጠኸኝ" ብለን የምናማርር።
በቅድሚያ እስኪ ትኬቱን እንቁረጥ፤ የድርሻችንን እንወጣ።
(Hilina Belete ZeHohitebirhan)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
👍40❤18🕊1
#የክርስቲያን_መከራ
ለአንድ ክርስቲያን መከራ ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ ፡- ስንፍናንና ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብር መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራ ክብርን ያስገኛል፡፡ ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያስገኝ ነውና የክርስቲያን መከራ የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡
የቅዱሳኑ ክብራቸው እንዲህ ደምቆ ልናየው የቻልነው ከምን የተነሣ እንደ ኾነ እንመልከተው፡፡ ስላገኛቸው መከራ አይደለምን? ፈቃድህ ከኾነ ገና ከመነሻው አንሥተን እንቍጠራቸው፡፡ አዎ! ከአቤልና ከኖኅ ጀምረን እስኪ እንቍጠራቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በዚያ ለመቍጠር እንኳን በሚታክቱ ክፉዎች ሰዎች መካከል እየኖሩ ያለ መከራ ክብርን ማግኘት አልተቻላቸውም፤ እንዲህ እንደ ተባለ፡- “ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኘው” (ዘፍ.6፥9)፡፡ ተመልከት! ለእኛ አብነት የሚኾኑን እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች አሉን፡፡ ብዙ አበውን፣ ብዙ ሕፃናትን፣ ብዙ መምህራንን አብነት አድርገን መከራ እንቀበላለን፡፡ በሰብአ ትካት መካከል ኾኖ መከራ ስለ ተቀበለው ስለ ኖኅ ምን እንላለን? በዙሪያው ስለ ነበረው እንግዳና አስደናቂ ዝናብስ ምን እንናገራለን? ወይስ አብርሃም ከአገር አገር ሲሰደድ መኖሩን፣ ሚስቱን እንደ ቀሙት፣ ጦርነትና ረሃብ እንዳገኘው እናገር ዘንድ ይገባኛልን? ወይስ እጅግ አስጨናቂ ነገሮች ስላገኙት፣ ከቦታ ቦታ ስላሳደዱት፣ ድካሙ ከንቱ ይኾንበት ስለ ነበረው፣ በድካሙ ላይ ሌሎች ሰዎች ይጠቀሙበት ስለ ነበረው ስለ ይስሐቅ ልናገርን? ወይስ ስለ ያዕቆብ ልናገርን? ያዕቆብ ያገኘውን መከራ እዘረዝር ዘንድ አይገባኝም፤ እርሱ ራሱ ለፈርዖን የተናገረውን ምስክር አድርጌ ላቅርብ እንጂ፤ እንዲህ ያለውን፡- “የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ኾኑብኝ፡፡ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም” (ዘፍ.47፥9)፡፡ ወይስ ስለ ዮሴፍ ልናገር ይገባኛልን? ወይስ ስለ ሙሴ፣ ወይስ ስለ ኢያሱ፣ ወይስ ስለ ዳዊት፣ ወይስ ስለ ኤልያስ፣ ወይስ ስለ ሳሙኤል፣ ወይስ ስለ ነቢያት ኹሉ ልናገር ይገባኛልን? እነዚህ ኹሉ በመከራ እንደ ከበሩ አታውቅምን? ሰው ሆይ! ከዕረፍትና ከቅምጥል ሕይወት ክብርን ልታገኘ ትሻለህን? እኔ እነግርሃለሁ፤ በፍጹም አታገኘውም፡፡
ወይስ ስለ ሐዋሪያት ልናገርን? እነዚህስ ከኹሉም በላይ መከራ ተቀበሉ፡፡ ጌታችን ክርስቶስም እንዲህ ብሏልና፡- “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፥33)፤ “እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፡፡ ዓለም ግን ደስ ይሏል” (ዮሐ.16፥20)፤ “ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ መንገዷም ቀጭን ናትና የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው” (ማቴ.7፥14)፡፡ ታዲያ እስኪ ንገረኝ! ጌታችን መንገዷ ጠባብ ናት እያለ አንተ ሰፊውን መንገድ ትፈልጋለህን? ይህስ እንደ ምን ሊኾን ይችላል? በሌላ መንገድ የምትኼድ ከኾነም ወደ ሕይወት አትደርስም፤ እንደ ምርጫህ ምረረ ገሃነም ያገኝሃል እንጂ፡፡
የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው በገብረ እግዚአብሔር ኪደ

👍18❤11
ተወዳጆች ሆይ አንድ የልብ ምክር አለኝና አድምጡኝ፦
ወዳጄ የቤተሰብ ሓላፊ ከሆንህ፡- እኔ ለቤተሰቤ እንደ ኢዮብ ካህን ነኝ ስለዚህ በመንፈስ ሁል ጊዜ፤ በአካል ደግሞ እንደ ችሎታዬ መጠን ስለራሴ ምክንያቱም በመልካም ማስተዋል ቤተሰቤን እመራ ዘንድ ስለቤተሰቤ ምክንያቱም ቤተሰቤ በኃጢአት ምክንያት አእምሮው እንዳይቆሽሽ በራስ መተማመን እንዳያጣ በማስተዋልና እግዚአብሔርን በመፍራት እንዲመላለሱ ስለሀገሬ ሰዎች ደግሞ በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ማስተዋልንና እርስ በእርስ መግባባትን እንዲሰጣቸው ፍቅር እንድትነግሥ ስለዓለሙ ሁሉ ደግሞ “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” እንድንል ጌታ እንዳስተማረን የምንኖርባት ዓለም ፈቃዱን ለማድረግ እንደሚተጉ መላእክት ለመልካም ሥራ እንዲበረቱ በጸሎት መትጋት አለብኝ ብለህ ለልብህ ንገረው፡፡
ለቤተሰባቸው እማወራ ለሆኑ እናቶችና ሚስቶች ደግሞ ለልባቸው እንዲህ ብለው ይንገሩ፡- እኔ ለቤተሰቤ አካሉ ነኝ፡፡
በእርግጥም ባለቤቴ ራሴ ነው እኔም አካሉ ነኝ ልጆቼም ከእኔ የወጡ የአካሌ ክፋዮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ሳራን “ካንቺ ሕዝብና አሕዛብ ይወጣሉ” እንደተባለች ከእኔ ማኅበረሱ ተገኝቶአል ይገኛልም፡፡ እኔ ለማኅበረሰቡ ፣ እንደ ሀገር ለሚቆጠረው ሕዝብና ለዓለሙ ሁሉ እንደ መሠረት ነኝ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ቡሆው ቅዱስ ከሆነ ሊጡም ቅዱስ ይሆናል” እንዲል የእኔ ቅድስና ለእነርሱ ቅድስና መሠረት ነው፡፡ ይህን ሁሌም ላስበው ይገባል ትበል፡፡ ሁሌም ይህን አስቤ እንደ ተምሳሌቴ እንደ ቤተ ክርስቲያን ማስተዋልን ያድለኝ ዘንድ ስለሀገሬ ስለ ዓለሙ ሁሉ ሰላም በመንፈስ ሁልጊዜ ፤ በአካል እንደ ችሎታዬ መጠን በጸሎትና ራሴን በማስተዋል ለማነጽ ልተጋ ይገባኛል ትበል፡፡
ልጅም እንደ ክርስቶስ በመንፈስም በአካልም በጥበብም በእግዚአብሔርም በሰው ፊት ሊያድግ እንዲገባው ዘወትር ያስብ የእርሱ ወጣትነት ዘመን ክርስቶስ ዓለምን ለማስተማር
በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት የተመላለሰበት ዘመን እንደሆነ ያስብ፡፡ ስለዚህም ሰውነቱን በኃጢአት ሳይተደደፍ ወጣትነቱን በንጽሕና ይጠብቃት ዘንድ ክርስቶስን ማወቅ ከቅዱሳን ጋር ማኅበርተኛ መሆንን ሊለማመድ እንደሚገባው ቆጥሮ በጸሎትም በምንባብም በተመስጦም ሊተጋ እንዲገባው ለልቡ ይንገረው፡፡ ሁሉ ነገር ከራስ ሲጀመር እጅግ መልካም ነው፡፡
የቅድስና መንገዱም ይህ ነው፡፡ ጌታስ ቢሆን ያስተማረው ይሄንኑ አይደለምን? አንተ ግብዝ አስቀድመህ በዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ በኋላ የወንድምህን ጉድፍ ማየት ይቻልሃል” ብሎ አላስተማረንምን? ወገኖቼ በጸሎት አንዳችንለአንዳችን እንትጋ፡፡
(ከዲ/ን ሽመልስ መርጊያ)

👍21❤9❤🔥2
#ጥቅምት_5
#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)
ጥቅምት አምስት በዚህች ቀን የታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ። ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ። አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።
ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።
ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው፤ ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።
ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።
ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ። "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ።" እንዲል።
ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ)

👍31❤10
ተወዳጆች ሆይ! ሌላ ሰው አደረሰብኝ የምትሉት ጉዳት ምንድነው? ተቆጥቶ ሰደበኝ፤ ያለ ስሜም የሆነ ስም ሰጠኝ የሚል ነውን? ታዲያ ይኼ ምን ጉዳት አለው? በፍጹም ጉዳት የለውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ጉዳቶች ሳይሆኑ ትዕግሥተኞች ከሆናችሁ ጥቅማቸው የበዛ ነውና፡፡ ሲጀምር በእናንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚፈልገው ሰው የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ የሚያደርገው ሁሉ ወዶና ፈቅዶ አይደለም፡፡ምንም እንኳን እናንተን የጐዳ ቢመስለውም ራሱን እየጐዳ ነው፡፡ የብዙዎቻችን ችግር ጐጂውና ተጐጂው ማን መሆኑን ለይተን አለማወቃችን ነው፡፡ ምክንያቱም ይኼንን ለይተን ብናውቅ ኖሮ ራሳችንን ለመጉዳት ባልተነሣሳን ነበር፤ ሌሎች ክፉ ይደርስባቸው ዘንድ ባልጸለይን ነበር፤ ማንንም መጕዳት እንደማንችል በገባን ነበር፡፡ ትልቁ በደል ደግሞ ክፉን መቀበል ሳይሆን በሌሎች ላይ ክፉትን መፈጸም ነው፡፡
ስለዚህ ከዛሬ ጀምራችሁ ሌላ ሰውን በድላችሁ ከሆነ ራሳችሁን ውቀሱ፤ ሌላው ክፉ አድርጐባችሁ እንደሆነ ግን ለእናንተ ያደረገው ነገር መልካም ነውና ጸልዩለት፡፡ ምንም እንኳን ሰውዬው እናንተን ለመጥቀም ብሎ ያደረገው ባይሆንም በመታገሣችሁ ግን ትልቅ ጥቅምን ታገኛላችሁ፡፡ ክፉ አደረገብኝ የምትሉት ሰውዬ ድርጊቱ ክፉ እንደሆነ ሰዎችም የእግዚአብሔር ቃልም ይፈርዱበታል፤ እናንተ ግን እንዲህ ስትታገሡ ለጊዜው ምንም የተጐዳችሁ ቢመስላችሁም ጌታ እንደተናገረ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
ስለዚህ ከዛሬ ጀምራችሁ ሌላ ሰውን በድላችሁ ከሆነ ራሳችሁን ውቀሱ፤ ሌላው ክፉ አድርጐባችሁ እንደሆነ ግን ለእናንተ ያደረገው ነገር መልካም ነውና ጸልዩለት፡፡ ምንም እንኳን ሰውዬው እናንተን ለመጥቀም ብሎ ያደረገው ባይሆንም በመታገሣችሁ ግን ትልቅ ጥቅምን ታገኛላችሁ፡፡ ክፉ አደረገብኝ የምትሉት ሰውዬ ድርጊቱ ክፉ እንደሆነ ሰዎችም የእግዚአብሔር ቃልም ይፈርዱበታል፤ እናንተ ግን እንዲህ ስትታገሡ ለጊዜው ምንም የተጐዳችሁ ቢመስላችሁም ጌታ እንደተናገረ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
👍11❤3
"ክርስትና የሚጀምረው ከተግባር እንጂ ከወሬ አይደለም፡፡ ሕይወታችን በጥቅስ ተገንዞ በጥቅስ የተቀበረ ከሕይወትና ከሥራ የተለየ እንዲሆን አንፍቀድለት፡፡"
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
"ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሰላማዊ ስትሆን ሰላማዊ ትሆናለች፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች፡፡"
አንጋረ ፈላስፋ
"ራስህን ለማየት ወደ መስታወት ብትመለከት ውበትህን ወይም ጉድለትህን ያሳይሃል፡፡ ምንም ነገር እንዳታይ ታደርግ ዘንድ ከመስታወቱ መሰወር አትችልም፡፡ ማንም ሊያመልጥበት በማይችለው በፍርድ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡"
አንጋረ ፈላስፋ
"የአንጥረኛ ዕቃ በየቀኑ በተመታ ቁጥር የበለጠ ጽሩይ እየሆነ እንደሚሄደዉ ሁሉ ሰውነቱን ለማድከም ራሱን የሚያስገዛ ሰዉም እንዲሁ ነዉ፡፡ በየቀኑ እየተማረ፣ እየጠራ እየነጻ ከጠላት ስውር ወጥመድ እየተጠበቀ ይሄዳል፡፡"
አንጋረ ፈላስፋ
"ሀብትን ብታከማች ያንተ አይደለም፡፡ ብትመፀውተው ግን ታከማቸዋለህ፡፡"
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
"ስለ ወንድሙ መዳን የማይደክም ድኗል ብዬ አላምንም፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"እግዚአብሔር አንድን የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ሊሰጥህ ቢወድ ፀጋውን ልትጠብቀው ከምትችለው ከትህትና ጋር ይሰጥህ ዘንድ ለምነው አለበለዚያ ግን ከአንተ እንዲያርቀው ጠይቅ፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እዉነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለሁ፡፡ እውነተኛ ትህትና ትሩፋትን መሥራት ነዉ፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ስለ ሌሎች ሰዎች ያለማቋረጥ ፀልዩ፡፡ወደ እግዚአብሔር ይደርሱ ዘንድ የንስሐ እድል አላቸውና፡፡ ለእነርሱ ነቀፋ እናንተ ምላሻችሁ ፀሎት ይሁን፡፡"
ቅዱስ አግናጥዮስ

👍18❤2