Telegram Web Link
Forwarded from RAMA PRINTING
ለበአሉ ደመቅ ሸብረቅረቅ የምትሉበት የመስቀል ቲሸርት

ዋጋ 450 ብር
የምትፈልጉትን ብዛት በቴሌግራም @RAMA_PRINT
ወይም በስልክ ቁጥር 0926863365 በመደወል ማዘዝ ትችላላችሁ በጥራት እና በፍጥነት ሰርተን እናስረክባለን።
ሌላ አይነት ዲዛይን መምረጥ ከፈለጉ @rama_printing ላይ ያገኛሉ።

መልካም በአል
👍9
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሷል፤ ያበሰብሷልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍265
አምላክ ሆይ፥ ለአንተ እሰግዳለሁ! ቸሩ ሆይ፥ አንተን አመሰግናለሁ! ቅዱስ ሆይ፥ አንተን እማልዳለሁ! መፍቀሬ ሰብእ ሆይ፥ በፊትህ እንበረከካለሁ!

አንተ የፈጣሬ ኵሉ የእግዚአብሔር አብ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለህ የባሕርይ ልጁ ነህና ክርስቶስ ሆይ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ!

ንጹሃ ባሕርይ ሆይ፥ ለእኔ ለማይገባኝ ለኃጥኡ ስትል፥ አዎ ነፍሴን ከኃጢአት ቀንበር ነጻ ታደርጋት ዘንድ ራስህን በመልዕልተ መስቀል ላይ ሞተሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ!

አምላክ ሆይ፥ ለዚህ ኹሉ ፍቅርህ ምን እከፍልሃለሁ? መፍቀሬ ሰብእ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! መሐሪ ወመስተሳሕል ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! ተዓጋሢ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! በኃጢአት በበደል የወደቀውን ሰው (ንስሐ ገብቶ ሲመለስ) ይቅር የምትለው ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን!

ነፍሳችንን ታድን ዘንድ ከሰማየ ሰማያት ወርደህ ከድንግል ተወልደህ የመጣህ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! ከሥጋዋ ሥጋ (ከነፍስዋም ነፍስ) ነስተህ በማኅፀነ ድንግል ያደርክ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! ልዑለ ባሕርይ ስትኾን አርአያ ገብርን ይዘህ ወደ እኛ የመጣህ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! ከገዛ ባሮችህ ግርፋትን የተቀበልክ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! ባለጠጋ ስትኾን ለእኛ ስትል ድኻ የኾንክ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይገባል! (እከብርበታለሁ ብለህ ያይደለ እኛን ታከብርበት ዘንድ) የተሰቀልክ ሆይ ክብር፥ ለአንተ ይገባል! ርደተ መቃብርን ርደተ ገሃነምንም ታጠፋ ዘንድ የተቀበርክ ሆይ ክብር ለአንተ ይገባል፡፡

(ሞታችንን ገድለህ የትንሣኤያችንም በኵር ኾነህ) ከሙታን ተለይተህ የተነሣህ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይገባል! ነቢያት ትንቢት የተናገሩልህ ሱባኤም የቈጠሩልህ ሆይ፥ ዕበይ ለአንተ ይገባል! ያመንንብህ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይገባል! ወደ ሰማያት ያረግህ ሆይ፥ አኰቴት ለአንተ ይገባል! በአብ ቀኝ በአብ ክብር የተቀመጥህ፥ ቅድስት ሕማምህን በተሳለቁት ላይም ዳግም ለመፍረድ የምትመጣ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን!

በዚያች በምታስፈራና በምታስደነግጥ፣ ሰማያውያን ኃይላት በሚነሡባት፣ መላእክትና ሊቃነ መላእክት፥ ሱራፌልና ኪሩቤል በክብርህ ፊት በፍርሐትና በረዓድ ኾነው በሚቆሙባት፣ የምድር መሠረቶች በሚነዋወጥባት፣ እስትንፋስ ያለው ኹሉ ከክብርህ ታላቅነትና አይመረመሬነት የተነሣ በሚንቀጠቀጥባት፥ አዎን በዚያች ሰዓት “እንደ ምሕረቱ ብዛት ኃጥኡን ማዳን ለወደደ ለእርሱ ለእግዚአብሔር አኰቴት፣ ዕበይ ወእዘዝ ይኹን” ብዬ አመሰግንህ ዘንድ፥ በክንፍህ ጥላ ሥር ውሰደኝ፡፡ ነፍሴን ከዚያ አስፈሪ እሳት፣ ከጥርስ ማፋጨት፣ በውጭ ካለው ጨለማ፣ የዘለዓለም ከኾነም ዋይታ አድናት፡፡

#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶሪያዊ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2011
Forwarded from RAMA PRINTING
ለበአሉ ደመቅ ሸብረቅረቅ የምትሉበት የመስቀል ቲሸርት

ዋጋ 450 ብር
የምትፈልጉትን ብዛት በቴሌግራም @RAMA_PRINT
ወይም በስልክ ቁጥር 0926863365 በመደወል ማዘዝ ትችላላችሁ በጥራት እና በፍጥነት ሰርተን እናስረክባለን።
ሌላ አይነት ዲዛይን መምረጥ ከፈለጉ @rama_printing ላይ ያገኛሉ።

መልካም በአል
👍54
#ቤተ_ክርስቲያን_እና_ሆስፒታል

(በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ልጆቼ! ተጠራርታችሁ ወደ አባታችሁ ቤት ለመምጣት ያደረጋችሁትን ቅንአት ተመልክቼ ደስ ተሰኝቼባችኋለሁ፡፡ እኔም ይህን ቅንአታችሁን አይቼ ስለ ነፍሳችሁ ጤና ይበልጥ እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቀዶ ጥገና የሚደረግባት ሐኪም ቤት ናት፡፡ የሥጋ ቀዶ ጥገና ግን አይደለም፤ የነፍስ ቀዶ ጥገና ነው እንጂ፡፡ የምናክመው የሥጋን ቁስል አይደለም፤ መንፈሳዊ ቁስልን እንጂ፡፡ መድኃኒቱም ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ መድኃኒት በምድር ላይ ከሚበቅሉት ዕፅዋት የተቀመመ አይደለም፤ ከሰማያት ከሚመጣው ቃል እንጂ፡፡ ይህን መድኃኒት በቁስል ላይ ለመጨመር ሐኪሞች አያስፈልጉም፤ የሰባክያነ ወንጌል አንደበት እንጂ፡፡ ቀዶ ጥገናውን ለማከናወን ብዙ ሰዓታትን አይፈጅም፡፡ ቀዶ ጥገናው ላይሳካ ይችላል ተብሎ የሚጠረጠር አይደለም፡፡ ከጊዜ በኋላ ወይም በሌላ ሕመም ምክንያት የተደረገው ቀዶ ጥገና ሊከሽፍ ይችላል ተብሎም አይገመትም፡፡ ሐኪሞች የሚሰጡን መድኃኒት እንዲህ ዓይነት ችግር ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ሐኪሞች የሚሰጡን መድኃኒተ ሥጋ ለጊዜው ብርቱ ነው፤ ሰውነታችን እያረጀ እንደሚሔደው ኹሉ መድኃኒቱም በጊዜ ሒደት ብርታቱን እያጣ ይሔዳል፡፡ ሌላ ደዌ ዘሥጋ ሲገጥመንም መቋቋም የሚችል አይደለም፡፡ ምክንያቱም መድኃኒቱን የቀመሙት ሰዎች ስለኾኑ፡፡ ከእግዚአብሔር የሚሰጠን መድኃኒት ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ ምንም ያህል ጊዜ ቢቆይም አይበላሽም፤ ጊዜው አያልፍበትም፤ ኃይሉም ብርታቱም ያው ነው አይቀንስም፡፡

ሙሴ የተቀበለው ቃለ እግዚአብሔር በጊዜው የነበሩትን ሰዎች ፈውሷቸዋል፤ አሁንም ያ ቃል ይፈውሳል፡፡ የመፈወስ ኃይሉ ብርታቱ እስከ አሁን ድረስ አላጣም፤ ሌላ ምንም ዓይነት በሽታም አላሸነፈውም፡፡ ይህን መድኃኒት ለመግዛት ብር አይበቃውም፤ ቅን ልቡና ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ በዚህ መድኃኒት ባለጸጋውም ድኻውም እኩል ይታከማሉ፡፡ ወደ ምድራዊው ሆስፒታል ሲኬድ ባለጸጋው ብር ስላለው ያሻውን ሕክምና አግኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ድኻው ግን ብር ስለሌለው መድኃኒቱንም መግዛት ስለማይችል ሳይታከም ከነሕመሙ ወደ ቤቱ ይመለሳል፡፡ ይህ ከቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው መድኃኒት ግን በብር የሚገዛ አይደለም፡፡ ይህን መድኃኒት ለማግኘት የሚያስፈልገውም ብር ሳይኾን እምነትና ምግባር ነው፡፡ እምነትና ምግባር የከፈለ ሰው ይህን መድኃኒት ማግኘት ይቻሏል፡፡ እነዚህን የከፈለ ጤናውን አግኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል፡፡ በመኾኑም ድኻውም ባለጸጋውም እኩል ታክመውበት ይሔዳሉ፡፡ እንደዉም ከባለጸጋው ይልቅ ድኻው በመድኃኒቱ ይበልጥ ተጠቅሞ ይሔዳል፡፡ ለዚህስ ምክንያቱ ምንድነው? ምክንያቱም ባለጸጋው ብር ስላለው በብዙ ሐሳብ የተያዘ ነው፡፡ ሀብታም ነኝ ብሎ ስለሚያስብ ትዕቢተኛ ነው፡፡ ሕይወቱን የሚመራው በቸልተኝነት ነው፡፡ በስንፍና ስለሚያዝ መድኃኒት የኾነውን ቃሉን ለማድመጥ ስልቹ ነው፡፡ ድኻው ግን በቅንጦትና በስንፍና ኑሮ ስለማይኖር፣ ጊዜውን በእንተ ፈንቶ ነገሮች ስለማያሳልፍ መድኃኒተ ነፍሱን ለማግኘት ንቁ ነው፡፡ ቃሉን ለማድመጥ ፈጣን ነው፡፡ ቸልተኝነት አይጠጋውም፡፡ የተባለውን ለማድመጥ ልቡናው ዘወትር ዝግጁ ነው፡፡ የሚከፍለው ክፍያ ብዙ ነው ማለት ነው፤ የሚያገኘውም መድኃኒት እንደዚያ ብዙ ነው፡፡

ይህን ኹሉ ዘርዝሬ መናገሬ ግን ባለጸጋውን ኹሉ በደፈናው መኰነኔ አይደለም፡፡ ድኻውንም ኹሉ እንደሁ ማመስገኔ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሀብት በራሱ መጥፎ አይደለም፤ መጥፎ የሚያደርገው የእኛ አጠቃቀም ነው፡፡ ድኽነቱም በራሱ በጎ አይደለም፤ በጎ የሚያደርገው የኛ አጠቃቀም ነው፡፡ ባለጸጋው ነዌ ወደ ሲዖል የተወረወረው ሀብታም ስለነበረ አይደለም፤ ጨካኝና ሰብአዊነት የማይሰማው ክፉ ስለነበረ ነው እንጂ፡፡ አልዓዛርም በአብርሃም ዕቅፍ የተቀመተው እንዲሁ ድኻ ስለነበረ አይደለም፤ ድኻም ቢኾን አመስጋኝ ስለነበረ እንጂ፡፡

ይህን በማስተዋል ታደምጡ ዘንድ እማልዳችኋለኁ፡፡ አንዳንድ መልካም የኾነ ነገር አለ፡፡ አንዳንድ መጥፎ የኾነ ነገርም አለ፡፡ አንዳንዱ ደግሞ መጥፎም በጎም ጎን ያለው አለ፡፡ ሀብትና ድኽነት ግን በጎም ክፉም አይደሉም፡፡ ኹለቱም በጎ ወይም ክፉ የሚኾኑት እንደተጠቃሚው ሰው ነው፡፡ ሀብታችሁ ለበጎ አድራጎት የምትጠቀሙበት ከኾነ በጎ ነው፡፡ ከዚሁ በተቃራኒ ለክፉ ግብር የምታውሉት ከኾነ ግን ክፉ ነው፡፡ ክፉ ነው ማለቴ ግን ሀብቱ በራሱ ክፉ ኾኖ አይደለም፤ ክፉ ያደረገው የእናንተው አጠቃቀም ነው፡፡ ድኽነቱም ቢኾን እግዚአብሔርን ለማመስገን የምትጠቀሙበት ከኾነ ሹመት ሽልማታችሁ ብዙ ነው፡፡ በድኽነታችሁ አመካኝታችሁ እግዚአብሔርን የምታማርሩ ከኾነ ግን ድኽነታችሁ ክፉ ነው፡፡ ነገር ግን ሀብታችሁ በራሱ በጎ ወይም ክፉ እንዳልኾነ ኹሉ ድኽነታችሁም በራሱ ክፉ ወይም በጎ ኾኖ አይደለም፡፡ በጎ ወይም ክፉ የሚያደርገው የእናንተው አያያዝ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ማመስገን ወይም ማማረር የሚመነጨው ከድኽነቱ ሳይኾን ከእኛ ነው፡፡ ሀብት መልካም ነው፤ መልካም የሚኾነው ግን ኃጢአት ላልሠራበት ሰው ብቻ ነው፡፡ ድኽነትም መጥፎ ነው፤ መጥፎ የሚኾነው ግን እምነት ለሌለው ሰው ነው፡፡ እምነት የሌለው ሰው አይጠግብም፤ ዘወትር እግዚአብሔርን ያማርራል፤ ዘወትር ብስጩ ነው፤ “እግዚአብሔር ስለምን ፈጠረኝ?” እያለ ይበሳጫልና ድኽነት እምነት ለሌለው ሰው መጥፎ ነው፡፡

ስለዚህ ባለጸጎችን እንዲሁ በደፈናው አንውቀሳቸው፤ ድኽነትንም እንዲሁ አንጥላው፡፡ መውቀስ ካለብን እነዚህን ኹለቱንም በአግባቡ የማይጠቀሙባቸው ሰዎችን ነው፡፡ አስቀድሜ እንደተናገርኩት ድኽነት ወይም ሀብት በራሳቸው መጥፎ ወይም በጎ አይደሉምና፡፡ ስለዚህ በቤተክርስቲያን የሚሰጠው መድኃኒት ድኻውም ባለጸጋውም እኩል ታክመውበት ይሔዳሉ፡፡ ከባለጸጋው ይበልጥ ደግሞ ድኻው፡፡ የቃለ እግዚአብሔር ጥቅሙ መድኃኒተ ነፍስ መኾኑ ብቻ አይደለም፤ ጥራቱ በጊዜ ብዛትም አይበላሽም፡፡ በሌላ በሽታ ተጨማሪ ጉዳትን አያመጣም፡፡ በነጻ የሚታደል ነው፡፡ የድኻውም የባለ ጸጋውም ዓቅም ያገናዘበ ነው፡፡ ከዚህ ባልተናነሰ መልኩ ሌላም ጥቅምም አለው፡፡ እርሱስ ምንድነው? አንድ ታካሚ ለቀዶ ጥገና ወደዚህ በመጣ ጊዜ ቁስሉ ሌላ ሰው እንዲያየው አይደረግም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ወደኾነው ሆስፒታል ብትሔዱ ግን አንድ የቀዶ ጥገና ልዩ ባለ ሙያ (Specialist) አስቀድሞ የታካሚውን ቁስል ሳያይ የቁስል ፋሻን ማድረግ አይችልም፡፡

በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ አንደኛ በአንድ ጊዜ ብዙ ሕሙማን ይታያሉ፡፡ ኹለተኛ ሕክምናው የሚሰጠው በምሥጢር ነው፡፡ የእያንዳንዱን ኃጢአተኛ ኃጢአትን በአደባባይ አንናገርም፡፡ ከዚያ ይልቅ መጀመሪያ ኹሉንም አንድ ላይ እናስተምራለን፡፡ ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ሕሊናውን እንዲያደምጥ እናደርጋለን፡፡ ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ካስተማርነው ትምህርት እንደ በሽታው ዓይነት የሚስማማውን መድኃኒት እያነሣ ይወስዳል፡፡ ሰባኬ ወንጌሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማንና ቀኖናን ያስተምራል፡፡ በዚያም አብሮ ክፉ ምግባርን ይገሥፃል፤ በጎ ምግባርን ያወድሳል፡፡ ዋልጌነትን ይነቅፋል፤ ንጽህናን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡ ትዕቢትን ይገሥጻል፤ ትሕትናን ያመሰግናል፡፡ መድኃኒተ ሥጋ በውስጡ ሕመሙን ማከም የሚችሉ ብዙ ንጥረ ነገርን እንደያዘ ኹሉ ከሰባኪው የሚወጣው ቃለ እግዚአብሔርም እንደዚሁ ለእያንዳንዱ ሰው የሚኾን ፈውስን ይዟል፡፡ ቃሉ ኹሉም እየሰማ ይነገራል፤ ወደ እያንዳንዱ ሕሊና እንዲገባ
👍1311
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2
መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ "እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና።" /2ቆሮ 9፥7/ እንዲል። እግዚአብሔር የምትሰጠውን ገንዘብ ሳይሆን የመጀመሪያውን ፍሬ እና ቃል ኪዳን የሆነውን ከማዕረጎች ሁሉ የሚልቀውንና ያለ ነቀፋ በነፃነት የሚሰጠውን ፍቅር ከአንተ ይጠብቃል።

ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ የመጀመርያ ፍሬ ነው። ስለዚህ ጌታ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን በነቀፋ ንሥሓም እንዲገባ በጠራው ጊዜ ነቀፋውን የተወሰነ ኃጢአትን በመግለጽ ሳይሆን በአንድ ሐረግ አጠቃልሎ "ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።" /ራዕ 2፥4/ በማለት ነው።

እግዚአብሔር ይህንን ፍቅር ይፈልጋል ስለዚህ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።" /ምሳ 23፥26/ አለ። ትእዛዙን መፈጸም የፍቅር ተፈጥሮአዊ ፍሬ ነው።

ውጪያዊ የንሥሓ ሕይወት ብቻ የሚኖሩ ነገር ግን ውስጣዊ ፍቅር የሌላቸው ይወድቃሉ። ምክንያቱም ሥራዎቻቸውና ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ፍቅር የጎደለው ነውና።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ "ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፣ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርሷም ባልጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትል ናት። ኦሪትና ነቢያት በነዚህ በሁለቱም ትእዛዛት ጸኑ።" /ማቴ 22፥36-40/ የሚል ነበር።

በዚያን ቀን ብዙዎቹ "ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም በስምህ አጋንንት አላወጣንም?" /ማቴ 7፥22/ ይሉታል። ነገር ግን እርሱ ይህን ሁሉ ትቶ በውስጣቸው ስላለው ፍቅር ይጠይቃቸዋል።

ይህ የተአምራት እና የስጦታዎች ችግር አይደለም፣ ባሏቸው በተሰጡአቸው ስጦታዎች የተነሳ የሚጠፉ ብዙዎች ናቸውና። ለዚያ ነው ሐዋርያት ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ባወሩ ጊዜ ሁሉ ይህንን ከሁሉ ይልቅ በተሻለ መንገድ አብራርተውታል።

#አብነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍124🕊3
ከምን ዓይነት ነገር መላቀቅ እንዳለብህ ታዉቃለህ ??

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምድራዊ ምኞት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና እንዴት ከዚህ ነገር ነፃ መውጣት እንዳለብን እንዲህ በማለት ይመክሩናል፦

"ወዳጄ ከምድራዊ ምኞትህ ተላቀቅ ከምን አይነት ነገር መራቅ እንዳለብህ ታውቃለህ? ከምድራዊ ፍላጎት ከመሳሰሉት ራቅ ፍፁም የመንፈስ ነፃነት እንዲኖርህ ከፈለክ ከምድራዊ ምኞቶችህ ተላቀቅ።

በእርጋታና በግልጽነት ላውጋህ እጅግ አብዝተህ የምትጨነቅባቸው ልብህን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ምድራዊ ተስፋዎች አሉህ።

እነኚህም ሃሳብህን ሁሉ ይቆጣጠሩታል ብቻህን በምቶንበት ጊዜ በምናብ ይመጡብሃል በምትተኛ ጊዜ ህልምህ ሁሉ ይህ ይሆናል ልትክዳቸው የማትችለው ነገር ግን የምታውቃቸው ምድራዊ አላማዎች አሉህ። ተፈላጊነት እንዲኖርህ ትመኛለህ፣ ስልጣን እንዲኖርህና፣ ኃያል እንድትሆን፣ ዕውቅና እንዲኖርህና ስምህ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እንዲናኝ ትፈልጋለህ።

በሀብት፣ በምድራዊ ስልጣን፣ በዕውቀት በማዕረግና በመልክ ዝነኛ የመሆን ተስፋ አለህ ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በምግብ፣ በልብስና በሰውነት ደስታን በሚሰጡ ነገሮችም ተስፋ አለህ።

ዓለም በአንተ እንጂ አንተ በዓለም እየኖርክ አይደለም። ስለዚህ አንተነትህ በዚህ ምድራዊ ተስፋ የታጠረ ነው። መንፈስህም ከስጋ ፍላጎቶች መራቅን ትመኛለች ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በሥጋ ላይ ይመኛልና። (ገላ.5፥17) እነዚህ ሥጋዊ ተስፋዎችና ፍላጎቶች ስኬታማ ስለማይሆኑ ግራ ትጋባለህ።

ይህን በእርግጥ ቅሬታን ያመጣብሃል።
እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትናፍቃለህ ነገር ግን ናፍቆትህ አያስደስትህም። ስለዚህ ለምኞትህ ሁሉ ማስተካከያ ታበጅለት ይሆናል ምናልባትም ይጠቅሙኛል የምትላቸውን ሰዎች ማግኘት፣ በምኞትህ ዙሪያ የተጻፈ መዛግብት ማገላበጥ ትፈልግ ይሆናል በዚህም ላይ ታች ስትል ምኞትህን ለማሳካት ትታገላለህ እንዲሆን ሌላ ዘዴ ልትፈጥር ትችላለህ ይሁን እንጂ ሳይሳካልህ ቀርቶ በሃሳብና በጥረት ትታክታለህ ከዚያም ትበሳጫለህ። ከዚህ የከፋው ነገር በእነዚህ ምኞቶችና ተስፋዎች ስኬታማ አለመሆን ምክንያት ለከፋ ሕይወት መዳረግህ ነው።

እንደምትሰለች አውቃለሁ አዘንኩልህ እስከመቼ ድርስ በምኞት ማዕበል ውስጥ ትኖራለህ? የምትመኘውን ባገኘህ ጊዜ ደስተኛ ትሆናለህ ይህ ደስታ ስለማያረካህ ሌላ አዲስ ደስታን እንድትመኝ ያደርግሃል። ልክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል" (ዮሐ.4፥13 ) እንዳለው እርካታ አይኖርህም።

ስለዚህ ውድ ወንድሜ ነገሩን በእርጋታ ከአንተ ጋር ለመነጋገር እፈልጋለሁ። "አለሙም ምኞቱም ያልፋል" (1ኛ ዮሐ.2፥17) ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ? አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ። ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ. 1፥21)

ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ። ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም። በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ። መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም።

ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን!!! ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ።

ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና (ማቴ.6፥21) የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው። (ማቴ.4፥8-9)

አሁን አስተውል እነዚህን ነገሮችን ብትይዝ በጥሩ ምኞት ያላሰርካት ነፍስህን ብታጣ ጥቅሙ ምንድን ነው? ነፍስህ ነጻነትን ትሻለች።

ከስጋ ምኞት ተላቀን የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።"(ገላ.5፥22) እንዳለው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ገንዘብ አድርገን እንድንኖር እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን!!

(የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "የመንፈስ ነጻነት "ከሚለውና በዲ/ን ደስታ ፍፁም ከተተረጎመው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2215🕊8
ይሁዳ ያንን ሁሉ ኃጢአት ከሠራ በኋላ ንስሐ ገብቶ ነበር፤ "ንጹህ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ" በማለት /ማቴ.27፥4/፡፡ ዲያብሎስም እነዚህን ቃላት ሰማ፡፡ ይሁዳ የድኅነት መንገድ መጀመሩን አየ፤ አስተዋለም፡፡ የይሁዳ መለወጥ በጣም አስደነገጠው፡፡ ምክንያቱም የይሁዳ ጌታ የኃጢአተኞች ወዳጅ እንደኾነ አሳምሮ ያውቃልና፡፡ ጌታውን አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት ይለወጥና መንገዱን ያስተካክል ዘንድ በብዙ መንገድ ይነግረው ከነበረ፥ አሁን ራሱ ይሁዳ ወዶና ፈቅዶ ሲመጣ ደግሞ ይበልጥ እንደሚቀበለው በደንብ ያውቃል፡፡ ሰው ሆኖ የመጣውም ለዚሁ ዓላማ ማለትም ኃጢአተኞችን ይጠራ ዘንድ ነውና፡፡ በመሆኑም ዲያብሎስ አንድ ነገር ያደርግ ዘንድ ተጣደፈ፡፡ እርሱስ ምንድነው? ይሁዳ አሁን የጀመረውን የድኅነት መንገድ (ንስሓዉን) ትቶ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ፡፡ በአሁኑ አያያዙ በሕይወት ከቆየ ወደ ፊት ንስሐ ሊገባ ስለሚችል ይህንን ዕድል እንዳይጠቀም ፈጥኖ ራሱን እንዲሰቅል ማድረግ፡፡

ተወዳጆች ሆይ! ንስሐ ዲያብሎስን እንዴት እንደሚያስደነግጠው ታያላችሁን? ዲያብሎስ እንደምን ያለ ወዳጅ እንዳለን ምን ያህል እንደሚያውቅና ይህንንም እንዳንጠቀምበት እንዴት እንደሚታትር ታስተውላላችሁን? የይሁዳ ታሪክ እንዲህ መጻፉ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው፡፡ ምክንያቱም እኛም በእርሱ (በይሁዳ) መንገድ ሔደን እንዳንጠፋ፥ ይልቁንም በንስሐ ተመልሰን ብንመጣ አምላካችን የምሕረት እጁን ዘርግቶ እንደሚቀበለን ሲያስተምረን ነው፡፡ ታዲያ መቼ ነው የምንመለሰው? መቼ ይሆን ወደ እርሱ በቃል ሳይሆን በተግባር የምንቀርበው?

ተወዳጆች ሆይ! ይህንን ስታነቡ በአፍአ ብቻ አትጸጸቱ፤ በተግባር እንጂ፡፡ ጸጸታችሁ ፍሬ ያፍራ፡፡ ንስሐ አባቶቻችንን እናግኛቸው፡፡ ወደ ምሥጢር እንቅረብ፡፡ ያኔ ነው ከይሁዳ ተማርን የሚባለው፡፡

(Mekrez ZeTewahdo)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍186
"ክርስትና የሚጀምረው ከተግባር እንጂ ከወሬ አይደለም፡፡ ሕይወታችን በጥቅስ ተገንዞ በጥቅስ የተቀበረ ከሕይወትና ከሥራ የተለየ እንዲሆን አንፍቀድለት፡፡"
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

"ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሰላማዊ ስትሆን ሰላማዊ ትሆናለች፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች፡፡"
አንጋረ ፈላስፋ

"ራስህን ለማየት ወደ መስታወት ብትመለከት ውበትህን ወይም ጉድለትህን ያሳይሃል፡፡ ምንም ነገር እንዳታይ ታደርግ ዘንድ ከመስታወቱ መሰወር አትችልም፡፡ ማንም ሊያመልጥበት በማይችለው በፍርድ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡"
አንጋረ ፈላስፋ

"የአንጥረኛ ዕቃ በየቀኑ በተመታ ቁጥር የበለጠ ጽሩይ እየሆነ እንደሚሄደዉ ሁሉ ሰውነቱን ለማድከም ራሱን የሚያስገዛ ሰዉም እንዲሁ ነዉ፡፡ በየቀኑ እየተማረ፣ እየጠራ እየነጻ ከጠላት ስውር ወጥመድ እየተጠበቀ ይሄዳል፡፡"
አንጋረ ፈላስፋ

"ሀብትን ብታከማች ያንተ አይደለም፡፡ ብትመፀውተው ግን ታከማቸዋለህ፡፡"
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ

"ስለ ወንድሙ መዳን የማይደክም ድኗል ብዬ አላምንም፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"እግዚአብሔር አንድን የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ሊሰጥህ ቢወድ ፀጋውን ልትጠብቀው ከምትችለው ከትህትና ጋር ይሰጥህ ዘንድ ለምነው አለበለዚያ ግን ከአንተ እንዲያርቀው ጠይቅ፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እዉነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለሁ፡፡ እውነተኛ ትህትና ትሩፋትን መሥራት ነዉ፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"ስለ ሌሎች ሰዎች ያለማቋረጥ ፀልዩ፡፡ወደ እግዚአብሔር ይደርሱ ዘንድ የንስሐ እድል አላቸውና፡፡ ለእነርሱ ነቀፋ እናንተ ምላሻችሁ ፀሎት ይሁን፡፡"
ቅዱስ አግናጥዮስ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
20👍13❤‍🔥4🕊1
ሰይጣን የኢዮብን ሀብት ሲያወድምበት ፣ ዐሥር ልጆቹን ሲገድልበት ፣ ጤናውን ሲወስድበት አንድ ነገር ግን አልነካበትም::

ሚስቱን::

ለምን?

ሚስቱን ያልነካው ምናልባት ነገረኛ ቢጤ ስለሆነች ከኢዮብ መከራ ውስጥ ተቆጥራ ይሆን? ሰይጣን ሚስቱን ያልነጠቀው " ታንገብግበው" ብሎ ይሆን?

ጠቢቡ "በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው" ይላል:: ምሳ.27:15 ምናልባት በሰይጣን እይታ ኢዮብን ለማማረር ሚስቱ መቆየት ነበረባት ይሆን?

በእርግጥ የኢዮብ ሚስት "ፈጣሪን ሰድበህ ሙት" የምትል መሆንዋን ስናይ ለኢዮብ ፈተና እንድትሆን ይሆናል ሳንል አንቀርም:: ሰይጣንም እንዲህ ብናስብ አይጠላም::

ነገሩ ግን ወዲህ ነው:: ሰይጣን የኢዮብን ሚስት እንዳይነካት ያደረገው የራሱ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር::

"ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ እርሱ በእጅህ ነው" ብሎ እግዚአብሔር ለሰይጣን አስጠንቅቆት ነበር:: ሕይወቱን አትንካ የተባለው ሰይጣን ሌላውን ሁሉ ሲያጠፋ ሚስቱን ግን ያልነካው ሚስት ሕይወት ስለሆነች ነው:: ሚስቱን መንካትም ራሱን ኢዮብን መንካት ነበር:: አዎ ሚስት ሕይወት ናት:: እንደ ኢዮብ ሚስት ብትከፋም እንደ ምሳ. 31ዋ ሚስት መልካም ብትሆንም ሕይወት ናት:: ሕይወት ደስታም ኀዘንም አለበት:: "ሕይወት እንዲህ ናት" c'est la vie እንዲል ፈረንሳይ:: ራሱ ኢዮብም "በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?" ብሎአል:: ኢዮ. 7:1

አዳምም አለ :-

"ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት"

"አዳምም ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 2016 ዓ.ም.
ሕንድ ውቅያኖስ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍225❤‍🔥2
“ባትመለሱ እግዚአብሔር ሰይፉን ይስላል” (መዝ.7፡12)፡፡

እግዚአብሔር እንደዚህ ዓይነት አነጋገርን የሚናገረው ለምን ይኾን? ሰማዕያኑ ከቁሳዊነት ጋር ካላቸው ቁርኝት የተነሣና በእነዚህ ጥንቱንም በሚያውቋቸው መንገዶች ሊያስፈራቸው ሊያስደነግጣቸው ብሎ ነው፡፡ ልብ በሉ! ወታደሮች የጦር ዕቃ መሣሪያን የሚታጠቁት ጠላታቸውን ለመቅጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር የጦር ዕቃ መሣሪያ እንደ ያዘ ኾኖ መታየቱ ግን ሰዎችን ለመቅጣት ሳይኾን ፈርተን ወደ ቀልባችን እንድንመለስና ከመከራ [ሥጋ ከመከራ ነፍስ] እንድንድን ብሎ ነው፡፡ ስለዚህ “ሰይፍ” ብሎ መናገሩ የጥልቅ ፍቅሩ ምልክት ነውና የምንደነግጥ አንኹን፡፡

ቃላቱ ለመስማት እንኳን ጭንቅ የኾኑት ከፍጹም ቸርነቱ የተነሣ ነው፡፡ እንደምታውቁት፥ አባቶች ልጆቻቸውን እንዳይቀጧቸው ሲፈልጉ አምርረው ይቈጧቸዋል፡፡ እግዚአብሔርም እንደዚሁ በኃይላተ ቃላቱ ፍርሐታችንን ከፍ የሚያደርገው እንዳይቀጣን ስለሚፈልግ ነው፡፡ እሳተ ገሃነም እንዳዘጋጀ የሚነግረን በእሳተ ገሃነም እንዳይቀጣን ብሎ ነው፡፡ ስለ መንግሥተ ሰማያት ከተነገረው በላይ በወንጌላት ውስጥ ስለ ምረረ ገሃነም ተጽፎ የምናገኝበት ዋናው ምክንያትም ይህ ነው፡፡ ልል ዘሊላን የኾኑ ሰዎች ዘንድ የምረረ ገሃነም ፍርሐት ያህል ወደ ምግባር ስለማይመራቸውና ከክፋት እንዲርቁ ስለማያደርጋቸው፥ ስለዚሁ ምክንያት እግዚአብሔርም ከጣዕመ መንግሥተ ሰማያት ይልቅ አብዝቶ ስለ ምረረ ገሃነም ይናገራል፡፡ ስለዚህ የሚያስፈሩ የሚያስነግጡ ቃላትን ባደመጥን ጊዜ የሚሰጡን በቁዔት ብዙ የብዙ ብዙ ነውና የምንታወክ አንኹን፡፡

ይልቅ የእግዚአብሔር በአንድ መልኩ ታጋሽ፥ በሌላ መልኩ ደግሞ ፈታሒ በጽድቅ ኰናኒ በርትዕ መኾኑን እናስብ፡፡ አስታውሱ! እግዚአብሔር ታጋሽ ነው፡፡ ስለዚህም ተስፋ ድኅነት የለንም አንበል፡፡ ግን ደግሞ እግዚአብሔር እውነተኛ ፈራጅም ነው፡፡ ስለዚህም ልል ዘሊላን አንኹን፡፡ በዚህ ዓለም ብዙ የብዙ ብዙ ይታገሣል፤ በወዲያኛው ዓለም ግን እዚህ ካሳያቸው ትዕግሥቱ ረብ ጥቅም ያላገኙት ሰዎች ለምረረ ገሃነም አሳልፎ ይሰጣቸዋል፡፡ እንግዲያውስ ዕጣ ፈንታችን ፅዋ ተርታችን ይህ እንዳይኾን በዚህ ዓለም ሳለን ከትዕግሥቱ የምንጠቀም እንኹን ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
13👍9
በእንተ ቅዱስ መስቀል (#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)

የጌታችን የክርስቶስ መስቀል ለእንደ ምን ያለ ታላቅ በረከት ምክንያት እንደ ኾነልን እናስበው፡፡ ምንም እንኳን ከአፍአ ሲታይ የጌታችን መስቀል አሳዛኝና አሰቃቂ ቢመስልም፥ እንደ እውነቱ ግን ደስታንና ሐሴትን የተሞላ ነው፡፡ መስቀል የቤተ ክርስቲያን መድኃኒት ነውና፤ መስቀል ተስፋ ለሚያደርጉት መመኪያቸው ነውና፤ መስቀል ጠላቶች [ደቂቀ አዳም] ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቁበት [የታረቁበት]፥ ኃጥአንም ወደ ክርስቶስ የተመለሱበት [አሁንም የሚመለሱበት] ነውና፡፡

በመስቀል ከጠላትነት ድነናል፤ በመስቀል ወደ እግዚአብሔር አንድነት ተመልሰናል፡፡ በመስቀል ከግብርናተ ዲያብሎስ አርነት ወጥተናል፤ በመስቀል ከሞትና ከጥፋት ድነናል፡፡ ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን በሞት ጥላ ሥር ተይዘን ነበር፤ አሁን ብሥራተ መስቀል በተገለጠበት ጊዜ ግን ህልውና እንኳን እንደሌለው አድርገን ቈጥረን የዘለዓለም ሕይወትን እየናፈቅን ሞትን ንቀነዋል፡፡ ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን ለገነት እንግዶች ነበርን፤ መስቀል በተገለጠ ጊዜ ግን ወንበዴስ እንኳን ለገነት የተገባ ኾኖ ተገኘ፡፡ የሰው ልጅ እንደዚህ ካለ ጨለማ መጠን ወደ ሌለው ብርሃን፣ ከሞት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት፣ ከመዋቲነት ወደ ኢመዋቲነት ታድሶ ተሸጋገረ፡፡ ዓይነ ልቡና ባለማወቅ ጽልመት ከመታወር ድኖ በመስቀል የዕውቀት ብርሃን ተጥለቀለቀ፡፡ እዝነ ልቡና ካለማመን ድንቁርና ወጥቶ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ መስማት ተመለሰ፤ ዕውራንም [መንፈሳዊ] ብርሃናቸው ተመልሶላቸው የእግዚአብሔርን ክብር ማየት ተችሎአቸዋል፡፡ በቅዱስ መስቀሉ የተሰጡን ሀብታት እነዚህ ናቸው፡፡ በቅዱስ መስቀሉ ያልተሰጡን በረከቶችስ ምን አሉ?

እነሆ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ በእግዚአብሔር ማመንም ተመልሷል፤ እውነትም [ወንጌልም] ወደ ዓለም ኹሉ ደርሷል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ ሰማዕታትም [ከመስቀል በኋላ ሞት ሞት መኾኑ እንደ ቀረና የሹመት የሽልማት ማሳ መኾኑን ዐውቀው አብረው] ተገልጠዋል፤ በክርስቶስ ማመንም በኹሉም ዘንድ ተሰራጭቷል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል፤ [በእርሱም ሞት ራሱ ሞቷልና] ትንሣኤ ሙታንም ተገልጧል፤ ሕይወትም ታይታለች፤ መንግሥተ እግዚአብሔርም እንደዚሁ እርግጥ ኾናለች፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ለእነዚህ ኹሉ ነገሮች ምክንያት ኾኗል፡፡ በመስቀሉ እግዚአብሔርን ማመስገን ተማርን፡፡ እንግዲህ ከቅዱስ መስቀሉ ይልቅ ሌላ የተወደደ ምን አለ? እኮ ከቅዱስ መስቀሉ በላይ ለነፍሳችን የሚረባት [የረባት፣ የጠቀማት] ሌላ ምን አለ? ስለዚህ በሙሉ ልባችን ይህን እንመስክር እንጂ ስለ ቅዱስ መስቀሉ ለመናገር ቅንጣት ታህልስ እንኳን አንፈር፡፡

ክርስቶስ በቅዱስ መስቀል ላይ ተሰቀለ፤ ዲያብሎስም በድን ኾነ፡፡ ክርስቶስ በቅዱስ መስቀል ላይ እጆቹን ዘረጋ፤ ለዓለምም የመዳን መንገድ ተሰጠ፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተቸነከረ፤ ነፍሳትም ኹሉ ከእስራታቸው ተፈቱ፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ዋለ፤ ፍጥረታትም ኹሉ ከጥፋት ባርነት ነፃ ወጡ፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እንግዳ ነገርም ለዓለም ኹሉ ታየ ፀሐይ ብርሃኗን ከለከለች ንዑድ ክቡር የሚኾን ነቢዩ አሰምቶ እንደ ተናገረው - እንዲህ ሲል፡- “በዚያን ቀን ፀሐይ በቀትር ይገባል፤ ብርሃንም በምድር ላይ በቀን ይጨልማል” (አሞ.8፡9)፡፡ ተወዳጆች ሆይ! የነቢዩ ቃል እንደ ምን ያለ ግሩም ምሥጢር በውስጡ ቋጥሮ እንደ ያዘ ታያላችሁን? እዚህ ላይ የኹላቸውም -የእስራኤላውያንም የአሕዛብም - ግብር ተገልጧል፤ ኹላቸውም በአንድነት በድለዋልና፡፡

እንደ ኦሪቱ ሕግ በዓላትን የሚያከብሩት ያዝናሉ፤ በመዝሙር ፈንታም በኢየሩሳሌም ላይ.ያለቅሳሉ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ኢየሩሳሌም የተቀደሱትን ሥርዓተ አምልኮዎችን ይዛ አትቀጥልምና፤ ከእንግዲህ ወዲህም በእርሷ ዘንድ በዓላት አይከበሩምና፡፡ የአሕዛብ አገራትም እንደዚሁ ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ያዝናሉ፤ መጽሐፍ “የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው” እንዳለ ኀዘን የበረከት ምንጭ ነውና ይተክዛሉ (ማቴ.5፡4)፡፡ አዎ! ትርጉም ለሌላቸው በዓላቶቻቸውና ሥርዓት ለሌላቸው ዘፈኖቻቸው ለርኵሳት መናፍስት ይቀርብ እንደ ነበረ ዐውቀው ያዝናሉ፤ ይተክዛሉም፡፡ ዛሬ አሕዛብ ያከናውኑአቸው ለነበሩት ክፉ ክፉ ነገሮች እንዴት እንደሚጸጸቱባቸው አስተውሉ፤ ከነቢዩ ጋር በአንድነት እንዲህ ይላሉና፡- “በድለናል፤ በሐፍረታችንም ጠፍተናል፤ በዓመፃ ተሞልተናልና ኃጢአታችን ሸፍናናለች፡፡ እንደ አባቶቻችን በድለናል፡፡”

እንግዲያውስ እኛም ስለ ሠራናቸው ኃጣውእ እናልቅስ፤ እንዘንም፡፡ ተስፋችንን በእርሱ ላይ.አኑረን ወደ ቅዱስ መስቀሉ እንጠጋ፡፡ እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብሩና ጌትነቱ አንድ በሚኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነትና ሰውን መውደድ የመንግሥቱ ወራሾች እንኾን ዘንድ በመስቀሉ [ቃል] ተምረን አሳባችንን በሰማያት እናኑር፤ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ለዓለም ወለዓለም፥ አሜን!!!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍18❤‍🔥1😢1🕊1
2025/07/14 17:40:30
Back to Top
HTML Embed Code: