Telegram Web Link
አበው ስለ እመቤታችን እንዲህ አሉ

"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው "
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት"
ቅዱስ አውግስጢኖስ

"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"
ቅዱስ ኤፍሬም

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2623🕊4
እግዚአብሔር ሕግን ወይም ትዕዛዝን ከመስጠቱ በፊት ሰንበትን የባረከውና የቀደሰው መሆኑ ነው። በሥነ ፍጥረት እግዚአብሔር ብዙ ድንቆችን አድርጓል እርሱ ብርሃናትን፣ ሰማያትን፣ ቀላያትን፣ ምድርን፣ ዕጽዋትን፣ እንስሳትን፣ የሰውን ልጅ ሁሉ ፈጥሯል። እነዚህን ሁሉ ፍጥረታት ከፈጠረባቸው ዕለታት መካከል እግዚአብሔር ባርኮታል ቀድሶታልም የተባለለት ከሰንበት በቀር ሌላ ቀን የለም። ስለ ሁሉም ዕለታት የተነገረ ቢኖር "ያ መልካም እንደሆነ አየ "የተባለው ብቻ ነው (ዘፍ 1፥12)።

ከሳምንቱ ሰባት ቀናት መካከል ለዕረፍት የተቀደሰው የተባረከውም ዕለት ሰንበት ብቻ ነው ። ሌሎቹ ቀናት የተባረኩት ለሥራ ነው እርሱ ሠርቶባቸው እኛም ልንሰራባቸው ሰጥቶናል። ይህም ሰው በየፊናው የግል ሥራውን የሚያከናውንባቸው ሌሎች ዕለታት ከእግዚአብሔር ጋር ከሚነጋገርበት በስብሐት እግዚአብሔር ከሚጠመድበት መንፈሳዊና ሰማያዊውን ነገር ብቻ በማሰብ ከሚውልበት ዕለት ሰንበት ጋር የሚስተካከል ቅድስናና በረከት እንዲሁም ክብር የሌላቸው መሆኑን የሚያስረዳ ነው።

በዚህ መሠረት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብትም ሁሉ ከተፈጠሩበት ዕለት ይልቅ አንድ ሰንበት የዕረፍት ቀን የበለጠ መሆኑን እናስተውላለን ። ማርታ ደስ እያላት ያለ አንዳች እረፍት የሠራችው ሥራ ማርያም ከጌታ እግር ስር ተቀምጣ በጸጥታ ቃለ እግዚአብሔርን ከመስማቷ የበለጠ ክብር አልነበረውም። (ሉቃ 10፥40)

በመሆኑም ዕለተ ሰንበት ዐርፈው ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰሙበት በተዘክሮተ እግዚአብሔር የሚያሳልፉት መንፈሳዊውን ተግባራትን የሚሠሩበት በመሆኑ ከሌሎቹ ዕለታት የከበረ ነው ።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍267❤‍🔥1
ጸሎት ለማድረግ አታቅማማ፤ ሥጋ ከምግብ በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች፡፡ (አቡነ ማቴዎስ ግብፃዊ)

ስለሁሉም ነገር ሳታቋርጥ ጸልይ፤ እንዲህ ካላደረግክ ምንም ነገር ያለ ልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ የማታከናውን ትሆናለህ፡፡ ያለጸሎት ራሱን በማንኛውም ዓለማዊ ጉዳዮች የሚያደክም ሰው በመጨረሻ ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው ራሱን ኃጢአተኛ እንደሆነ እያሰበ ወደ እግዚአብሔር ካለየ ጸሎቱ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡ (አባ አጋቶን)

እግዚአብሔር ለሰው ምሕረትን ሲያድል አንድ ሰው እንዲጸልይለት ያነሣሣዋል፡፡ በዚህ ጸሎት አማካኝነትም ይረዳዋል፡፡ በመከራ ጊዜ ያለማቋረጥ መሓሪውን አምላክ በጸሎት ጥራው፡፡ ባለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ለነፍስ ቁስል መድኃኒት ነው፡፡ ሰው በታመመ ጊዜ ዶክተሩ ፍቱን መድኃኒትን ፈልጎ ለበሽተኛው እንደሚሰጠው መድኃኒቱም ወደ ሰውነቱ ገብቶ ሥራ ሲሠራ እንጂ እንዴት እንደሚሰራ እንደማናውቀው በተመሳሳይ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ስም አዘውትረን ስንጠራ እንዴት ጸሎታችን እንደሰራ ሳናውቅ የእግዚአብሔርን ፍቅር ምህረትና ርኅራኄ በእኛ ላይ ሲደረግ እንመለከታለን፡፡

(አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
26👍21
ልጆቼ! በድህነቴ ላይ ቸርነትን አድርጉልኝ፡፡ በዚህስ አልችልም ካላችሁ እሺ በቁስሌ ላይ ዘይትን አፍሱልኝ፡፡ አሁንም ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወደ እኔ ጠጋ በሉና አናግሩኝ፡፡ እናንተን ማየት፣ ከእናንተ ጋር መጨዋወት ይናፍቀኛልና፡፡ በገዛ ደሜ የገዛኋችሁ ልጆቼ! ከባድ ነገር እኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እኔ የምፈልገው ትንሽ ዳቦ፣ ጊዜአዊ ማደርያ፣ እንዲሁም የሚያጽናኑ ቃላትን ብቻ ነው፡፡ “ይህ ሁሉ ማድረጌ ምን ይጠቅመኛል?” ካላችሁ ስለ ምሰጣችሁን ርስት መንግሥተ ሰማያት ብላችሁ አድርጉት፡፡ አሁንም ልባችሁ አልተነካምን? ስለ መንግሥተ ሰማያት አታድርጉት፤ ግን ደግሞ ስለ ሰብአዊ ርኅራኄ ይህን አድርጉልኝ፡፡ የእኔን መራቆት የሚያሳዝናችሁ በቀራንዮ አደባባይ ስለ እናንተ ብዬ የተራቆትኩት ብቻ ነውን? ታድያ አሁንም ‘ኮ በደጃችሁ ላይ ተጥዬ ዕራቆቴን ነኝ፡፡ ለምን አላዘናችሁልኝም? የታሰርኩት በቀራንዮ ብቻ ነውን? አይደለም፡፡ ታድያ እንደምን አታዝኑልኝም?

የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ሳለሁ “ተጠማሁ” እንዳለኩ ዛሬስ ስለ እናንተ ብዬ ደጋግሜ ይህን ቃል አልተናገርኩምን? ጕሮሮዬ ደርቆ ስለምን ትንሽ እንኳ
አላሳዝናችሁም? ስለምንስ ይህ ሁሉ ፍቅር ስለ እናንተ መሆኑን ትዘነጉብኛላችሁ? የምለምናችሁ እናንተን ባለጸጋ ለማድረግ አይደለምን? ይህችን ትንሽ ቸርነት ስላደረጋችሁልኝ በዐይን ያልታየች፣ በጀሮ ያልተሰማች፣ በሰውም አእምሮ ያልታሰበች ርስት መንግሥተ ሰማያት እንድታገኙ ብዬ አይደለምን? ስለ እናንተ ብዬ ደሀ
የሆንኩት ያኔ በመዋዕለ ሥጋዌዬ ብቻ እንደሆነ አታስቡ ልጆቼ! ዛሬም ቢሆን በደጃችሁ የተጣልኩት ስለ እናንተ ጥቅም እንደሆነ ተረዱልኝ፡፡

ከባድ ነገር ‘ኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እስር ቤት መጥታችሁ
ጠይቁኝ እንጂ አስፈቱኝ አላልኳችሁም፡፡ ታምሜ ጠይቁኝ እንጂ ፈውሱኝ አላልኳችሁም፡፡ ከጠየቃችሁኝ ብቻ በቂዬ ነው፡፡ እስኪ ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! በዚያ በአስፈሪው ቀን ስመጣ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” የሚለውን ቃለ ሕይወት መስማት አትፈልጉምን? ዛሬ የሰጣችሁኝ ሁሉ የምረሳ ይመስላችኋልን? ያኔ በክብር ስመጣ ከእልፍ ወለዱ ጋር እንድሰጣችሁ አትሹምን? የማፈቅራችሁ ልጆቼ! ከደጃችሁ ተጥዬ የምለምናችሁ፣ ከበራችሁ ላይ ቆሜ ማደርያን የምጠይቃችሁ፣ እጄን ዘርግቼ እናንተን እናንተን የማየው ያኔ ትሉ ወደማይጠፋው እሳቱ ወደማያንቀላፋው እሳት እንዳትሄዱብኝ ብዬ ነው፡፡ ታድያ ይህን ለምን አትረዱልኝ ልጆቼ? ስለምን እንዳስቸገርኳችሁ ታስባላችሁ? ለእናንተ ጥቅም እንደሆነ እንዳትረዱ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? ከእናንተ ጋር ቁጭ ብዬ ልብላ ስላችሁ ስለምን ትገፈትሩኛለችሁ? ይህን ያህል ቸርነት አድርጌላችሁ ሳለሁስ ስለምን በግልምጫ አያችሁኝ? ይህን ያህል መውደድ ወድጃችሁ ሳለሁ ስለምን በቅጡ ልታነጋገግሩኝ አልወደዳችሁም? ከአዳም ጀምሮ ዓለም እስኪያልፍ ድረስ ያለው ሕዝብ ሁሉ በአንድ አደባባይ ላይ ቆሞ፣ እልፍ አእላፍ መላእክት በዙርያዬ ረበው “ይህ/ ይህቺ ልጅ ወዳጄ ነው/ ናት፤ በመሆኑም በታላቅ ክብርና ዕልልታ አጅባችሁ ወደ ዘለዓለም ደስታዋ አግቡት/ አግቧት” የሚለውን ፍርዴ አትናፍቁምን?

ልጆቼ! እኔን ላለማየት ስለምን ፊታችሁን ትሸፍናላችሁ? ስለምን፡ታፍራላችሁ? እኔ ሳላፍርባችሁ ስለምን እናንተ አፈራችሁ?

ልጆቼ! ልባችሁ እንደተነካ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ስሜት ብቻ አይሁን፡፡ ከንፈራችሁን ብቻ አትምጠጡብኝ፡፡ ከእናንተ የምፈልገው አንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ ከላይ የጠየቅኳችሁን ነገሮች ወደ ተግባር ቀይሯቸው፡፡ ለማይጠቅማችሁ ነገር አብዝታችሁ እየሮጣችሁ ለሚጠቅማችሁ ነገር አትስነፉ፡፡ “እኔኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፤ ይህን እንደምን እችላለሁ?” አትበሉኝ፡፡ አውቃለሁ! ነገር ግን ፈቃዳችሁን ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ራሴ አደርግላችኋለሁ፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብዬ.ያስተማርኳችሁን ቃል ረሳችሁትን? /ዮሐ.15፡5/፡፡ እንግዲያውስ ከእናንተ የምፈልገው ፈቃዳችሁን ነው፡፡ አሁን ካላችሁበት ቦታ ተንቀሳቅሳችሁ ወጣ ስትሉ ታገኙኛላችሁ፡፡ አናግሩኝ! አፍቃሪያችሁ መድኃኔዓለም ነኝ፡፡

#መቅረዝ_ዘተዋሕዶ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
13👍13❤‍🔥3
ልጆቼ! በድህነቴ ላይ ቸርነትን አድርጉልኝ፡፡ በዚህስ አልችልም ካላችሁ እሺ በቁስሌ ላይ ዘይትን አፍሱልኝ፡፡ አሁንም ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወደ እኔ ጠጋ በሉና አናግሩኝ፡፡ እናንተን ማየት፣ ከእናንተ ጋር መጨዋወት ይናፍቀኛልና፡፡ በገዛ ደሜ የገዛኋችሁ ልጆቼ! ከባድ ነገር እኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እኔ የምፈልገው ትንሽ ዳቦ፣ ጊዜአዊ ማደርያ፣ እንዲሁም የሚያጽናኑ ቃላትን ብቻ ነው፡፡ “ይህ ሁሉ ማድረጌ ምን ይጠቅመኛል?” ካላችሁ ስለ ምሰጣችሁን ርስት መንግሥተ ሰማያት ብላችሁ አድርጉት፡፡ አሁንም ልባችሁ አልተነካምን? ስለ መንግሥተ ሰማያት አታድርጉት፤ ግን ደግሞ ስለ ሰብአዊ ርኅራኄ ይህን አድርጉልኝ፡፡ የእኔን መራቆት የሚያሳዝናችሁ በቀራንዮ አደባባይ ስለ እናንተ ብዬ የተራቆትኩት ብቻ ነውን? ታድያ አሁንም ‘ኮ በደጃችሁ ላይ ተጥዬ ዕራቆቴን ነኝ፡፡ ለምን አላዘናችሁልኝም? የታሰርኩት በቀራንዮ ብቻ ነውን? አይደለም፡፡ ታድያ እንደምን አታዝኑልኝም?

የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ሳለሁ “ተጠማሁ” እንዳለኩ ዛሬስ ስለ እናንተ ብዬ ደጋግሜ ይህን ቃል አልተናገርኩምን? ጕሮሮዬ ደርቆ ስለምን ትንሽ እንኳ
አላሳዝናችሁም? ስለምንስ ይህ ሁሉ ፍቅር ስለ እናንተ መሆኑን ትዘነጉብኛላችሁ? የምለምናችሁ እናንተን ባለጸጋ ለማድረግ አይደለምን? ይህችን ትንሽ ቸርነት ስላደረጋችሁልኝ በዐይን ያልታየች፣ በጀሮ ያልተሰማች፣ በሰውም አእምሮ ያልታሰበች ርስት መንግሥተ ሰማያት እንድታገኙ ብዬ አይደለምን? ስለ እናንተ ብዬ ደሀ
የሆንኩት ያኔ በመዋዕለ ሥጋዌዬ ብቻ እንደሆነ አታስቡ ልጆቼ! ዛሬም ቢሆን በደጃችሁ የተጣልኩት ስለ እናንተ ጥቅም እንደሆነ ተረዱልኝ፡፡

ከባድ ነገር ‘ኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እስር ቤት መጥታችሁ
ጠይቁኝ እንጂ አስፈቱኝ አላልኳችሁም፡፡ ታምሜ ጠይቁኝ እንጂ ፈውሱኝ አላልኳችሁም፡፡ ከጠየቃችሁኝ ብቻ በቂዬ ነው፡፡ እስኪ ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! በዚያ በአስፈሪው ቀን ስመጣ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” የሚለውን ቃለ ሕይወት መስማት አትፈልጉምን? ዛሬ የሰጣችሁኝ ሁሉ የምረሳ ይመስላችኋልን? ያኔ በክብር ስመጣ ከእልፍ ወለዱ ጋር እንድሰጣችሁ አትሹምን? የማፈቅራችሁ ልጆቼ! ከደጃችሁ ተጥዬ የምለምናችሁ፣ ከበራችሁ ላይ ቆሜ ማደርያን የምጠይቃችሁ፣ እጄን ዘርግቼ እናንተን እናንተን የማየው ያኔ ትሉ ወደማይጠፋው እሳቱ ወደማያንቀላፋው እሳት እንዳትሄዱብኝ ብዬ ነው፡፡ ታድያ ይህን ለምን አትረዱልኝ ልጆቼ? ስለምን እንዳስቸገርኳችሁ ታስባላችሁ? ለእናንተ ጥቅም እንደሆነ እንዳትረዱ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? ከእናንተ ጋር ቁጭ ብዬ ልብላ ስላችሁ ስለምን ትገፈትሩኛለችሁ? ይህን ያህል ቸርነት አድርጌላችሁ ሳለሁስ ስለምን በግልምጫ አያችሁኝ? ይህን ያህል መውደድ ወድጃችሁ ሳለሁ ስለምን በቅጡ ልታነጋገግሩኝ አልወደዳችሁም? ከአዳም ጀምሮ ዓለም እስኪያልፍ ድረስ ያለው ሕዝብ ሁሉ በአንድ አደባባይ ላይ ቆሞ፣ እልፍ አእላፍ መላእክት በዙርያዬ ረበው “ይህ/ ይህቺ ልጅ ወዳጄ ነው/ ናት፤ በመሆኑም በታላቅ ክብርና ዕልልታ አጅባችሁ ወደ ዘለዓለም ደስታዋ አግቡት/ አግቧት” የሚለውን ፍርዴ አትናፍቁምን?

ልጆቼ! እኔን ላለማየት ስለምን ፊታችሁን ትሸፍናላችሁ? ስለምን፡ታፍራላችሁ? እኔ ሳላፍርባችሁ ስለምን እናንተ አፈራችሁ?

ልጆቼ! ልባችሁ እንደተነካ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ስሜት ብቻ አይሁን፡፡ ከንፈራችሁን ብቻ አትምጠጡብኝ፡፡ ከእናንተ የምፈልገው አንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ ከላይ የጠየቅኳችሁን ነገሮች ወደ ተግባር ቀይሯቸው፡፡ ለማይጠቅማችሁ ነገር አብዝታችሁ እየሮጣችሁ ለሚጠቅማችሁ ነገር አትስነፉ፡፡ “እኔኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፤ ይህን እንደምን እችላለሁ?” አትበሉኝ፡፡ አውቃለሁ! ነገር ግን ፈቃዳችሁን ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ራሴ አደርግላችኋለሁ፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብዬ.ያስተማርኳችሁን ቃል ረሳችሁትን? /ዮሐ.15፡5/፡፡ እንግዲያውስ ከእናንተ የምፈልገው ፈቃዳችሁን ነው፡፡ አሁን ካላችሁበት ቦታ ተንቀሳቅሳችሁ ወጣ ስትሉ ታገኙኛላችሁ፡፡ አናግሩኝ! አፍቃሪያችሁ መድኃኔዓለም ነኝ፡፡

#መቅረዝ_ዘተዋሕዶ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
19👍5
ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት"

ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን

(#በዲያቆን_መላኩ_ይፍሩ መጠነኛ ለውጥ የተደረገበት)
👍4220
ሃሌሉያ

ብዙዎቻችን ሃሌሉያ ብለን ለማመስገን እንቸገራለን ምክንያቱም የሌሎች እምነት ተከታዮች በሆነው ባልሆነው ሃሌ ሉያ ስለሚሉ የእነሱ መገለጫ አድርገን እንድናስብ ስላደረጉን በዚህ ምስጋና ለማመስገን እንቸገራለን። ነገር ግን ይህ ምስጋና ከጥንት ጀምሮ አባቶቻችን በቅዳሴ፣ በማህሌትና በሰአታት የሚያመሰግኑበት ታላቅ ምስጋና ነው።
ሃሌሉያ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ከተተረጎመው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መጽሐፈ ሰዓታት ላይ ያገኘሁትን ላካፍላችሁ፦

ሃሌ ሉያ ማለት፦ ሃሌ ሉያ (Hallelujah) ሃሌ ሉያህ የሚለው ቃል የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን በዕብራይስጥ "ሃሌል" ማለት የሚመሰገን፣ ለምስጋና የተገባ፣ ምስጉን ማለት ሲሆን "jah" (ያህ) የሚለው ቀል "ያህዌ" ማለት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ጌታ መጠሪያ ነው። እኒህ ሁለቱ ቃላት አንድ ላይ "ሃሌሉያ" ሲባሉ "ምስጉን ጌታን እናመሰግነዋለን" ማለት ሲሆን ሁለቱን ቃሎችን ለያይተን ስናነባቸው ደግሞ "ምስጋና ለጌታ ይሁን" ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይም ከ32 ጊዜያት በላይ ተገልጿል። በተለይ ቅዱስ ዳዊት በተደጋጋሚ ምስጉን የሆነውን ጌታውን በዚህ ምስጋና አመስግኖበታል።

በዚህ ምስጋና የጻድቃን በኅብረት እንደሚያመሰግኑት ቅዲስ ዳዊት በመዝሙ " ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት፤ ምስጋናው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው።"(መዝ 149፥1) በማለት ጠቅሶታል። በአፀደ ሥጋ በአፀደ ነፍስ በገነት ያሉት የቅዱሳን ጉባኤ እንደሚያመሰግኑት ሁሉ ቅዱሳን መላእክትም በዚሁ ቃል ፈጣሪያቸውን እንደሚያመሰግኑ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ላይ" ደግመውም ሃሌ ሉያ አሉ፤ ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።

ሀያ አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር። አሜን፥ ሃሌ ሉያ እያሉ ሰገዱለት።ድምፅም ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ፥ አምላካችንን አመስግኑ ሲል ከዙፋኑ ወጣ። እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውኃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል። ሃሌ ሉያ፤ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።" በማለት የመላእክትን ምስጋና ገልጿል። ራእ.19፥3-6

ሰለዚህ እኛም እንደ ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን አምላካችንን ሃሌ ሉያ ብለን ልናመስገን ይገባል እንጂ የመናፍቃኑ መገለጫ አድርገን ልናስብ አይገባም።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍3212
በጥቂቱ መታመን

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ!.." ማቴ 25፥21፡፡ ይህም ማለት በምድራዊ ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ በሰማያዊ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ማለት ነው፡፡ በዚኛው ዓለም ታማኝ ሆነ ከቆየህ በዘለዓለማዊነት ውስጥ እሾምሃለው ማለት ነው፡፡ ይህ መመሪያ በብዙ መስኮች ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል... ዘመዶችህን በመውደድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ጠላቶችህንም በመውደድ ላይ ይሾምሃል፡፡ ጠላትህን የምትወድበት ጸጋ ያድልሃል ማለት ነው፡፡

በትርፍ ጊዜዎችህ እግዚአብሔርን የምታገለግል ከሆንህ በሕይወትህ ጊዜ ሙሉ በእርሱ ላይ ትኩረት የምታደርግበትን ፍቅር ያድልሃል፡፡ የፈቃድ ኃጢአቶችን ከአንተ በማስወገድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ያለ ፈቃድ ከሚመጡ ኃጢአቶች ነጻ ያወጣሃል፡፡

ንቁ ኅሊናህን ከክፉ አሳቦች የምትጠብቅ ከሆንህ እግዚአብሔር ንቁ ያልሆነው ኅሊናህን ንጽሕና ያድልሃል፤ ከዚህ በተጨማሪ የህልሞችህን ንጽሕናም ያድልሃል፡፡ ልጅ እያለህ ታማኝ ከሆንህ እግዚአብሔር ውጊያዎች በሚበዙበት በወጣትነትህ ዘመን ውስጥም ታማኝነትን ያድልሃል ሌሎች ሰዎች ላይ በቃላት ብቻ የማትፈርድባቸው ሆነህ በመገኘትህ ታማኝ ከሆንህ ይበልጥ አስቸጋሪ በሆነው በአሳብ እንዳትፈርድባቸው ያስችልሃል፡፡ ልክ እንደዚሁ ራስህን ከውጫዊ ንዴት በመጠበቅ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አውስጣዊ ቁጣ፣ንዴትና ቅናት ነጻ ያወጣሃል፡፡

በተለመዱ መንፈሳዊነቶች (በመንፈስ ፍሬዎች) ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የመንፈስ ስጦታዎችን ያድልሃል፤ በመጀመሪያው ላይ ታማኝ ሆነህ ካልተገኘህ ሁለተኛውን ፈጽመህ ልታገኘው አትችልምና፡፡

እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሚፈትሽህ በጥቂት ነገር ነው፡፡ በዚህች በጥቂቷ ነገር ላይ ታማኝ መሆንህ ካረጋገጥህ እርሱ በሚበልጠው ነገር ላይ ይሾምሃል፡፡ ውድቀትህንና አለመታመንህን በጥቂቷ ነገር ላይ ከገለጽህ ግን እግዚአብሔር በሚበልጠው ነገር ላይ አይሾምህም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና፦ "ከእረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱህ ቢደክሙህ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ?" ኤር 12፥5 ብዙ ሰዎች ዝቅተኛውን ኃላፊነት መወጣት ሳይችሉ ከፍተኛውን ኃላፊነት ለመቀበል ማሰባቸው እጅግ አስደናቂ ነገር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ ሳይጠቀሙ ተጨማሪ ጸጋ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ይህን ሲያደርጉም "በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ" የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመዘንጋት ነው፡፡

"መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅማቸው" ከሚለው #አያሌው_ዘኢየሱስ ከተረጎመው #የብጹዕ_አቡነ_ሽኖዳ መጽሐፍ የተወሰደ!!!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍1914
https://www.tg-me.com/+NrZ-LDtB9Qc1NTVk
https://www.tg-me.com/+NrZ-LDtB9Qc1NTVk
🌿🌿🌿ፀሎት በእንተ አለም ለሰማይ ወምድር እፀ ፈዉስ🎪🎪🎪🎪🎪እንዲህም አለ፡-እግዚሃብሄርን በጥበብ ፈልጉት፡ ታገኙታላቹህና!!
         +251 917468918
➡️የምንሰጣቸዉ አገልግሎቶች
🌿 ለመፍትሄ ሀብት
🌿 ለመስተፋቅር
🌿 ለአይነ ጥላ
🌿 ለጥይት
🌿 ለሁሉ መስተፍቅር
🌿 ለገበያ (ለንግድ)
🌿 ለእቁብ
🌿 ለማንኛዉም የስራ እድል ለማግኘት
🌿 ለሎተሪ
🌿 ትምህርት ለማይገበዉ
🌿 ለኪንታሮት
🌿 ለድክመተ ወሲብ
🌿ለአምሮ ህመም
🌿ለሽተሌ (ልጅ መዉለድ ለከለከላቸዉ)
🌿ለግርማ ሞገስ
🌿ስልጣን ለመያዝ
🌿ጠላት ሊጎዳን ካሰበ አፍዞ የሚይዝ፡
🌿ለድምፅ
🌿ለቁማር
🌿ለክርክር
🌿ለመፍዝዝ.....
🌿ለእፀ መሰዉር.....
🌿ለመክስት
🌿ለስራ መፍትሄ
🌿ለዘኢያወርድ
የምትፈልጉትን ነገር በስልክ እየደወላቹህ አናግሩኝ፡፡📞📞+251917468918
---0917468918---+
እውጭ አገር የምትኖሩ ካላቹሁ እና መፍትሄ የፈለጋቹሁ እኛጋ መፍትሄ ታገኛላቹሁ ደውላቹሁ አናግሩኝ
🙏ልጆቼ-አደራ-በኛ-ስም-ከሚያጭበረብሩ-ሰዎች-ተጠንቀቁ-እላለሁ-መርጌታ ይትባረክ ጋሻዉ -ነኝ-አደራ-ተጠንቀቁ!!!!
ለበለጠ መረጃ
1👍1
«የጠፋው ልጅ» ሉቃ ፩፭ ፥ ፲፩- ፳፬

አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት። ከእነርሱም ታናሹ አባቱን "አባቴ ሆይ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ" አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው። ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። ከዚያም እያባከነ ገንዘቡንም በተነ። ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ እርሱም ይጨነቅ ጀመር። ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች ከአንዱ ጋር ተዳበለ እርሱም እሪያ (አሳማ) ሊያሰማራ ወደ ሜዳ ሰደደው። እሪያዎችም ከሚበሉት አሰር ሊጠግብ ይመኝ ነበር የሚሰጠውም አልነበረም። ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ "እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ። ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፤ አባቴ ሆይ በሰማይና በፊትህ በደልሁ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ " እለዋለሁ አለ። ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው። ልጁም " አባቴ ሆይ በሰማይና በፊትህ በደልሁ ወፈ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም" አለው። አባቱ ግን ባሪያዎቹን አለ "ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ የሰባውንም ፊሪዳ አምጥታችሁ እረዱት እንብላም ደስ ይበለን ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ልጁ በመመለሱ በአባቱ ጥልቅ ደስታ ሆነ።

#አባት የተባለው ስለእኛ ብሎ ፍቅር አሸንፎት ወደ ምድር የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

#የጠፋው_ልጅ የተባለው እኛ ሰዎች ነን ከሞቀው ቤታችን ፍቅር ሰላም ረድኤት በረከት ከሞላበት ከአባትችን እቅፍ ከቅድስት ቤተክርስቲያን እርቀን በዚች ከንቱ ዓለም ስንባዝን ዓለም እንደ ሸንኮራ አገዳ መጣ ስጥለን አንድ ቀን መባዘናችን፣ ሀጢያት መስራታችን እና መበደላችን ታውቆን ወደ አባታችን ቤት ስንመለስ የቀድሞ ክፋታችንን የቀድሞ ሀጢያታችን የቀድሞ በደላችንን አያይም፤ እንዲህ አድርገሀል እንዲህ ሰርተሀል አይለንም። መድኃኒዓለም ደስ የሚለው ወደ ቤቱ መመለሳችን ነው። በንስሀ ሳሙና ታጥበን ፍቅር እና ሰላም ወደ አለበት ወደ ቤታችን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ስንመለስ በመንግስተ ሰማያት በእግዚአብሔር እና በመላእክት ዘንድ ትልቅ ደስታ ነው።

በድያለው ኃጢአት ሰርቻለሁ እንዴት ትችው ወደ ወጣሁት ቤት እመለሳለሁ አንበል። ልዑል እግዚአብሔር ያለፈውን በደላችንን ያለፈውን ክፋታችንን ያለፈውን ሀጢያታችንን አይመለከትም ያለፈውን አይቆጥርብንም ገብቶን መመለሳችን ብቻ ነው የምያው አቅፎ ስሞ ይቀበለናል የቀድሞውን ማንነታችን ቀይሮ አዲስ ሰው ያደርገናል የፍቅር አምላክ ስለሆነ። ስለዚህ ዛሬ ነገ ሳንል "ንስሀ" እንገባ መቼ እንደምናልፍ አናውቀውም። የመዳን ቀን አሁን ነው እንደሚል ቅድስ መፅሐፍ ንስሀ እንገባ። ነፍስ አባት የሌለን ነፍስ አባት እንያዝ።

ለንስሀ የተዘጋጀ ልቦና ለሁላችንም እንደ ቸርነቱ ያድለን። ንስሀ ገብተን ክቡር ደሙን ቅዱስ ስጋውን ተቀብለን ተስፋ የምናደርጋትን እርስት መንግስተ ሰማያትን እንድንወረስ የአምላካችን ቅዱስ ፍቃድ እንደ ቸርነቱ ይሁንልን።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
22👍12
ማስታወቂያ

🛸ሰላም የዚህ ቻናል ተከታታዮች

🧱ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ ብቻ 🧱

☎️ ምርትና አገልግሎታችሁን እንዲሁም አዲስ የከፈታችሁትን  ቻናል ወይም ግሩፕ ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ የማስታወቂያውን ይዘት ተመልክተን ካረጋገጥን በኋላ በተመጣጣኝ ዋጋ የምንሰራ መሆኑን ስንገልፅ በደስታ ነው።

🚀ማስተዋወቅ የምትፈልጉትን በዚህ አድራሻ
@channel_admin09 ላይ መላክ ትችላላችሁ።

🛑በተመጣጣኝ ዋጋ ነው😁
👍41
“ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር”

"የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው፤ እነሆ የተወደደ (መልካም) ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ (በዕቅፍሽ) እንዲጠጋ (እንዲደገፍ፣ እንዲንተራስ) በርሱ ዐማጽኚ፡፡"

አባ ጽጌ ድንግል (ማህሌተ ጽጌ)

እንኳን አደረሳችሁ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
🕊10👍7😢1
" ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " - ብፁዕነታቸው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት  የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን ተሻግረው የጣሊያን ወረራን አልፈዋል እንዲሁም በየዘመናቱ በተፈጠሩ የእርስበርስ ጦርነቶች ጉዳት ሳያደርሱባቸው እዚህ ደርሰዋል ብላለች።

ይሁን እንጂ አሁን ባለበንበት ዘመን በአካባቢው  በተፈጠረው ከፍተኛ የሰላም እጦትና ጦርነት  ምክንያት ከፍተኛ  የአደጋ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን በይፋ አሳውቃለች።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት በከፍተኛ የአደጋ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን ገልጸው ፤ ቅዱሱን ቅርስ ከስጋት ነጻ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሁሉም አካል ወደ #ሰላም_መድረክ መምጣት እንዳለበት በቅድሚያ ጠቁመዋል።

" ይህ ካልሆነ ግን ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና   የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ  የቅዱስ ላሊበላ ቅርስና የአምልኮ ቦታ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባለድርሻ አካላት ቅዱሱ ቅርስ  ከአደጋ ስጋት ውጭ እንዲሆን ዓለም አቀፍ  ተቋማት የመንግስት አካላት እንዲሁም  የቅዱሱ ቅርስ  የጋራ ሀብትነት የሚያሳስበው ሁሉ  በጉዳዩ ላይ  በጎ ተጽእኖ በማሳደር ድምጽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

(የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ነው)
👍212😢2❤‍🔥1
++ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ++

ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ፊት በዚያች ምሽት በጭንቀት ቆመዋል፡፡ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሠጠኛል ብሎ ነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህ ተጨንቀዋል፡፡ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? እያሉ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ተራ በተራ ጠየቁት፡፡

የቀሩት ሊሸጠው ተስማምቶ የመጣው ይሁዳና ወንጌላዊው ዮሐንስ ናቸው፡፡ ይሁዳ እኔ እሆንን ማለቱ ልቡ እያወቀ ስለነበር ከዐሥሩ ጋር አብረን አንቆጥረውም፡፡ ዮሐንስ ደግሞ ለጌታ ካለው የፍቅር ጥልቀት የተነሣ እኔ እሸጠው ይሆን? የሚል ሥጋት ስላልነበረበት ‘’ጌታ ሆይ አሳልፎ የሚሠጥህ ማነው?’’ አለ እንጂ እኔ እሆንን አላለም፡፡ የሐዋርያቱ የጭንቀት ጥያቄ በማግሥቱ መልስ አግኝቷል፡፡ ሆኖም ይህንን ትሕትና የተሞላ ጥያቄያቸውን ለእኛ ሳይበጅ አይቀርም፡፡

በዙሪያችን ለተደረጉ ፣ ለሚደረጉ ክፉ ነገሮች ሁሉ ምክንያቱ ምንድር ነው? ጥፋቱ የማን ነው? መነሻው ምንድርን ነው? ብንባል ሁላችንም ጣት የምንቀስርበት ሰው አናጣም፡፡
አዳም ዕጸ በለስን ለመብላቱ ‘’ም ክን ያቴ ሔዋን ናት ‘’ አለ
ሔዋን ‘’ዕባብ አሳተኝ ‘ አለች ዕባብም ጠያቂ ቢያገኝ ሰይጣን ማለቱ አይቀርም ነበር፡፡ አንዳቸውም ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ማለት አልቻሉም፡፡ እንደ ዳዊት ‘’እኔ መተላለፌን አውቃለሁ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊትህ ነው’’ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ለሚሆኑ ነገሮች ሁሉ የምንከስሰው ሰው አናጣም:: መፍትሔው ግን ራስን ማየት ነው:: "እስመ አዕይንቲሁ ለጠቢብ ዲበ ርእሱ" (የጠቢብ ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው) እንዲል

ቅዱሳን በምንም ነገር ራሳቸውን ይወቅሱ ነበር:: በገድላቸው ብዛት በሚጸልዩበት ሥፍራ ዶፍ ዝናብ እየወረደ ሳለ እርሳቸውን እንዳይነካቸው በቆሙበት ሥፍራ እንዳይዘንም ያደረገላቸው ዳግማዊው ኤልያስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያሉትን እናስታውስ:: በቆሙበት ሥፍራ ዝናም እንዳልዘነመ ሲያዩ "ይህችን መሬት በኃጢአቴ ዝናም አስከለከልኳት" ነበር ያሉት:: ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ይህም አይደል?

የሙሴ ወንድም አሮን በእስራኤል ግፊት ጣኦት ሠራ፡፡ ከወርቅ አቅልጦ ጥጃ አምላክ አድርጎ ሠራላቸው፡፡ ከሠራ በኋላም መሥዋዕት ለጣኦቱ አቀረበ፡፡ ሙሴ መጥቶ ሲቆጣ ሲያይ ግን አሮን ፈራና በሕዝቡ አሳበበ የራሱን ድርሻ በተመለከተ ግን እንዲህ አለ ‘ወርቅ ሰጡኝ በእሳት ላይ ጣልሁት ይህ ጥጃ ወጣ’ {ዘጸ 32፡24} ራሱ ከእጃቸው ተቀብሎ በመቅረጫ ቀርጾ የሠራውን ጣኦት ‘ስጥለው ጥጃ ሆነ’ አለ፡፡ ራሱ ሕዝቡን ‘ስድ ለቅቋቸው’ የነበረ በመሆኑ ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ብሎ ራሱን ሊከስስ ይጠበቅበት ነበር፡፡

በትምህርት ቤት ሕይወታችን የማይረሱ ቀናት ግሬድ የሚለጠፉባቸው ቀናት ናቸው፡፡ ከብዙ የመታወቂያ ቁጥር መካከል ውጤቱን ያየ ተማሪ በዚያ የትምህርት ዓይነት A እንዳገኘ ሲያውቅ ለጓደኞቹ ‘’A አገኘሁ እኮ’’ ይላል፡፡ በተቃራኒው ‘F’ ያገኘ ከሆነ ‘’F ሠጠኝ’’ ይላል እንጂ ‘F አገኘሁ’ አይልም፡፡ A ከሆነ ያገኘው ተማሪው ነው ፤ F ከሆነ ግን በድክመቴ አገኘሁ ከማለት ይልቅ ጥፋቱ የመምህሩ ይሆናል፡፡ ነገሩን አልኩ እንጂ ሀገር ሰላም ብሎ የቆመ በር ጋር ስንጋጭም ‘በሩ መታኝ’ እንጂ መታሁት አንልም፡፡
እናም በሕይወታችን ለሆኑትና ለሚሆኑት ነገሮች ‘ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ትልቅ ጸሎት ነው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
25👍19🕊3
​​#ህዳር 6

+በዚች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው።

ታድያ ጌታችን በእመቤታችን ጀርባ ላይ ሆኖ በእነዛ የምህረት ጣቶቹ ወደ #ኢትዮጵያ ይጠቁም ነበር እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን ምታመለክተው ስትለው ""ያቺ የተባረከች ሀገር ናት"" እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት!!ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገሉኛል በዚች አገር ያሉ ግን ሳያዩ ያምኑኛል አስራት በኩራት ትሁንሽ ብሎ ሰቷታል በቅዱስ እግራቸውም ጣና ሀይቅን ዋልድባንና ሌሎችንም ዞረው እንደባረኩም ድርሳነ ኡራኤልና ታምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል።

እመቤታችንን ከሐና መሀፀን ፈጥሮ ከፍጥረት አለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን ! የእመቤታችን ቁስቋም ማርያም ምልጃዋና በረከቷ አይለየን !! ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን !!
ኀዳር 6 ቀን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡

ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡

ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ 11÷1
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር - እነሆ የተወደደው ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ!

«ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ ...ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ » መኃ ፯፥፩ የተዋህዶ ልጆች እንኳን እመቤታችን ከስደት ተመልሳ ቁስቋም የገባችበት በዓል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
42👍23🕊5
+ #የአንድ_ሰው_ውሎና_አመሻሽ +

አንድ ወንድም ስልኩን ድምፅ አልባ ማድረግ ረስቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ስብከት ይማራል:: በዚህ መካከል ስልኩ ይጮሀል::
ሰባኪው ስብከቱን አቁሞ በዓይኖቹ ተቆጣው:: ከስብከቱ በኋላ ምእመናን ስብከቱን በመረበሹ ወቀሱት:: አንዳንዶቹም እያዩት ራሳቸውን በትዝብት ነቀነቁ:: ከሚስቱ ጋር ወደ ቤታቸው ሲሔዱም ሚስቱ ስለ ቸልተኝነቱ ምክር መሥጠትዋን ቀጠለች::
እፍረት መሸማቀቅና ውርደት ዘልቆ እንደተሰማው በፊቱ ላይ ይታይ ነበር:: ከዚያች ሰንበት በኋላ እግሩን ወደ ቤተ ክርስቲያን አንሥቶ አያውቅም::

ውስጡ የተረበሸው ይህ ሰው ያንኑ ምሽት ወደ መጠጥ ቤት አመራ:: አእምሮው እንደታወከ ነበር::
ቁጭ ባለበት ድንገት የሚጠጣበት ጠርሙስ ወድቆ ተሰበረና መጠጡም በዙሪያ ተረጨ:: ፍንጣሪው የነካቸው ሰዎች ወደ እሱ መጠጋት ጀመሩ:: ሊጮኹበትና በጥፊ ሊሉት እንደሆነ ታውቆት ቀድሞ ዓይኖቹን ጨፈነ::

ሰዎቹ ግን በተሰበረው ጠርሙስ ስብርባሪ ተጎድቶ እንደሆነ ተጨንቀው ጠየቁት::

አስተናጋጁ መጥቶ የፈሰሰበትን እንዲያደርቅ ማበሻ ሰጠው:: የጽዳት ሠራተኛዋ መሬቱን ወለወለች::

የቤቱ ባለቤት "አይዞህ ያጋጥማል? ዕቃ የማይሰብር ማን አለና?" አለችውና ሌላ መጠጥ አስመጣችለት::
ከዚያች ቀን ጀምሮ ከዚያ መጠጥ ቤት ቀርቶ አያውቅም::

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስልክን ክፍት ማድረግና ሥርዓተ አምልኮ መረበሽ መቅደስ ውስጥ ጫማ አድርጎ የመግባት ያህል ስኅተት ነው:: እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ኤምባሲ እንኩዋን ስልክህን ውጪ አስቀምጠህ ትገባለህ:: ሰውዬው ላጠፋው ጥፋት ግን በፍቅር የሚያናግረው ሰው በማጣቱ ከነ ስልኩ ሊጠፋ ወሰነ::

ቤተ ክርስቲያን የድኅነት ሥፍራ ናት:: መጠጥ ቤት ደግሞ የጥፋት ጎዳና ነው:: በዚህ ሰው ታሪክ ውስጥ ግን በድኅነት ሥፍራ ካሉ ሰዎች ይልቅ በጥፋት ሥፍራ ያሉ ሰዎች ለሰውዬው ስኅተት የተሻለ ፍቅር አሳዩ:: አንዳንዴ የአንዳንድ ምእመናን ጠባይ ነፍሳትን ወደ ሲኦል ይሰድዳል::

አንዳችን የአንዳችን ጠባቂ መሆን እንችላለን ዓለምን ለመፈወስ የሚቻለንን እናድርግ:: ነፍሳትን ከማዳን ነፍሳትን ማጥፋት በጣም ቀላል ነው::

መድኃኔዓለም ክርስቶስ የኃጢአተኞች ወዳጅ ነበረ:: እሱ የማንንም ቅስም በክፉ ቃል አልሰበረም:: እኛ ግን ሰው ላይ ስንጨክን መጠን የለንም:: በዚህ ምክንያት እንደ ኒቼ ያሉ ሰዎች "ብቸኛው ክርስቲያን መስቀል ላይ የሞተው ነው" ብለው እስኪዘብቱብን ደርሰዋል::

መጽሐፍ ግን ሰው ሲሳሳት ስናይ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲህ ሲል ይናገራል :-

"ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት" ገላ. 6:1

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍344🕊1
[ኅዳር 8 የእግዚአብሔርን ዙፋን የሚሸከሙ የኪሩቤል እና የሱራፌል በዓል]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
👉 ኪሩቤልና ሱራፌል የተባሉት የልዑል እግዚአብሔርን ዙፋን በፍርሀት በረዐድ ኹነው የሚሸከሙ መላእክት ሲኾኑ ነቢዩ ኢሳይያስም ዙፋኑን እንደሚሸከሙ በምዕ ፴፯፥፲፮ ላይ
✍️ “አቤቱ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ ሆይ አንተ ብቻኽን የምድር መንግሥታት ኹሉ አምላክ ነኽ ሰማይንና ምድርን ፈጥረኻል” በማለት ሲናገር፤ ነቢዩ ሕዝቅኤልም በፍርሀት ኹነው ሱራፌል ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳት) ዙፋኑን እንደተሸከሙ ኾኖ አይቷል (ሕዝ ፲፥፩-፳፪፤ ፲፩፥፳፪)፡፡

👉 “የሚሸከሙት” ሲባል ግን በጸጋ የሚያድርባቸው፣ የሚቀድሱት፣ ዙፋኑን ተሸክመው ይታያሉና እንዲኽ ተባለ እንጂ “ይጸውር ድደ ወይነብር ጠፈረ ኲሉ እኁዝ ውስተ እራኁ ወአጽናፈ ዓለም በእዴሁ” ማለት (በጠፈር ተቀምጦ መሠረትን ይሸከማል፤ ኹሉ በመኻል እጁ የተያዘ የዓለም ዳርቾችም በእጁ ያሉ) እንዲለው የሚሸከማቸውስ ርሱ ነው ይላሉ መተርጉማን ሊቃውንት፡፡

💥 ጌታችን እሳታውያን በኾኑ በኪሩቤል ዠርባ ላይ ተቀምጦ በአንድነት በሦስትነት እንደሚቀደስ ቅዱሳት መጻሕፍት በስፋት ያስተምራሉ ዳዊትም
✍️ “በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ በነፋስም ክንፍ በረረ” (መዝ ፲፰፥፲) በማለት ሲገልጽ፤ ዳግመኛም በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ተቀምጦ የሚመሰገነው የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤል ዘነፍስ ጠባቂ ሊቀ ኖሎት ተገልጾ እንዲያድናቸው፦
✍️ “ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ” በማለት የናፍቆት ልመናን ይለምን ነበር (መዝ ፸፱፥፩)፡፡

💥 ዮሐንስም በራእዩ ላይ በፍርሀት ኹነው ዙፋኑን ስለሚሸከሙት ስለ አርባእቱ እንስሳ ሲገልጽ
✍️ “በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ፤ በዙፋኑም መኻከል በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በኋላ ዐይኖች የመሏቸው አራት እንስሶች ነበሩ፤ ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ኹለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበርረውን ንስር ይመስላል፤ አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች አሏቸው በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች መልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ኹሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም” በማለት የኪሩቤልን የማያቋርጥ ምስጋናቸውን ተናግሯል (ራእ ፬፥፮‐፯)፡፡

💥 ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ የሥነ ፍጥረት ነገር ተገልጾለት በጻፈው መጽሐፍ ላይ
✍️ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ ኪሩቤል ካህናተ ቅዳሴ ወውዳሴ እምታሕተ ሐቌሆሙ አሐዱ ወእምላዕለ ሐቌሆሙ አርባዕቱ እለ ግሉፋን በአዕይንት” ብሎ እንደገለጸው ኹለተኛውን አመስጋኞች የኾኑት ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ኪሩቤል ሲላቸው ከወገባቸው በታች አንድ ከወገባቸው በላይ አራት አድርጎ ሲፈጥራቸው ዐይናቸው ብዙ ነው። ይኽም ኀላፍያትን መጻእያትን በማወቃቸው ይተረጐማል፤ አለቃቸው ኪሩብ ሲኾን የሰው መልክና የአንበሳ መልክ ያለው ነው፡፡ ሦስተኛውን ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ሱራፌል ሲላቸው የእነዚኽ አለቃቸው የንስር መልክና የእንስሳ መልክ ያለው ሲኾን ሱራፊ ሲባል ሲፈጥራቸውም ስድስት ስድስት ክንፍ አድርጎ ፈጥሯቸዋል (ሕዝ ፩፥፬‐፲፩)

💥 ሊቁ ኤጲፋንዮስም የሥነ ፍጥረትን ነገር በሚናገረው መጽሐፉ ላይ አኗኗራቸውን በጥልቀት ሲተነትነው
✍️ “ወነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ኪሩቤል ክልኤተ አርእስተ ዘውእቶሙ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ ወዓዲ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሱራፌል ክልኤተ ክልኤተ አርእስተ ዘውእቶሙ ገጸ ንስር ወገጸ እንስሳ ወለክኦሙ መልዕልተ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት በማእዘንተ መርሕባ ለአርያም ወሰፍሐ ዲበ ዘባናቲሆሙ ሰማየ ዘሕብሩ በረድ” ይላል ከነገደ ኪሩቤል ኹለት ገጸ ሰብእ እና ገጸ አንበሳን ከሱራፌል ኹለት ገጸ ንስርና ገጸ እንስሳን አንሥቶ ከኢየሩሳሌም ሰማያዊት በላይ ከሰማይ ውዱድ በታች አቁሞ በነርሱ ላይ ሰማይ ውዱድን እንደ መረሻት ጫነባቸው፤ በላይም ሕብሩ በረድ የመሰለውን ዙፋን እንደ ሠረገላ ጭኖባቸዋል።

👉 እነዚኽንም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን፣ በደቡብ በአራቱ መኣዝን ዠርባቸውን ወደ ውስጥ ፊታቸውን ወደ ውጪ እያደረገ አቁሟቸዋል፤ ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለዚኽ ነገር በምዕ ፩፥፲፪ ላይ “እያንዳንዱም ወደ ፊት ቀጥ ብሎ ይኼድ ነበር መንፈስም ወደሚኼድበት ኹሉ ይኼዱ ነበር፥ ሲኼዱም አይገላመጡም ነበር” በማለት እንደተናገረ ገጽ ለገጽ ሳይተያዩ ሥላሴ በፈቀዱት ፍኖት አንዱ በኼደበት ሦስቱ እየተከታተሉ ይኼዳሉ፡፡

💥 እነዚኽንም እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል ገለጻ ፲፮ ሲኾኑ የቀሩት ከውስጥ ስለኾኑ ስለማይታዩ አራቱ ግን ብቅ ብቅ ብለው ስለሚታዩ ዮሐንስ አራት ብሏቸዋል እንጂ እንደ ሕዝቅኤል ገጻቸው ፲፮ ነው፡፡

💥 ሊቁ “እምርእሶሙ እስከ ሐቌሆሙ አርባዕቱ ወእምሐቌሆሙ እስከ እግሮሙ አሐዱ ከመ ርእየተ እለ ቄጥሩ ዘውእቱ ዖፍ ዘይነብር በሀገረ ፋርስ” እንዲላቸው፤ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በመጽሐፈ ድጓው ላይ “ከመ ርእየተ እለቄጥሩ ገጸ በገጽ ኢይትናጸሩ” ብሎ እንደገለጻቸው በፋርስ ሀገር የሚኖረው እለቄጥሩ የተባለውን ዎፍ ከወገቡ በታች አንድ ከወገቡ በላይ አራት እንደኾነ እነዚኽንም ከወገባቸው በታች አንድ ከወገባቸው በላይ አራት አድርጎ ፈጥሯቸዋል።
👉 የገጸ ሰብእ አቋቋሙ በምሥራቅ አተያዩ ወደ ምዕራብ ነው።

👉 የገጸ አንበሳ አቋቋሙ በምዕራብ አተያዩ ወደ ምሥራቅ፤

👉 የገጸ ላሕም አቋቋሙ በሰሜን አተያዩ ወደ ደቡብ፤

👉 የገጸ ንስር አቋቋሙ በደቡብ አተያዩ ወደ ሰሜን ሲኾን ገጽ ለገጽ አይተያዩም፡፡

💥 የሰው መልክ ያለው ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል፤ የአንበሳ መልክ ያለው ስለ አራዊት ይለምናል፤ የንስር መልክ ያለው ስለ አዕዋፍ ይለምናል፤ የላም መልክ ያለው ስለ እንስሳ የሚለምን ሲኾን ከመላእክት ኹሉ ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት የቀረቡ ናቸው፡፡

💥 በኢሳ ፮፥፩-፫ ላይ፡- “ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየኹት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን መልቶት ነበር፤ ሱራፌልም ከርሱ በላይ ቆመው ነበር ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው በኹለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር በኹለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር በኹለቱም ክንፍ ይበር ነበር፤ አንዱም ለአንዱ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ኹሉ ከክብሩ ተመልታለች እያለ ይጮኽ ነበር” ይላል።

💥 ይኽ መሸፈናቸው ያድናቸዋል ቢሉ? መተርጉማን ትእምርተ ፍርሀት ነው ይላሉ፤ ዛሬ በዚኽ ዓለም ሴቶችን ሕፃናትን እንመታችኋለን ባሏቸው ጊዜ እጃቸውን መጋረዳቸው የሚያድናቸው ኾኖ ሳይኾን ትእምርተ ፍርሀት እንደኾነ ኹሉ፡፡

👉 አንድም በኹለት ክንፋቸው ፊታቸውን መሸፈናቸው ፊትኽን ማየት አይቻለንም ሲሉ በኹለት ክንፋቸው እግራቸውን መሸፈናቸው ከፊትኽ መቆም አይቻለንም ሲሉ፤ ኹለት ክንፋቸውን ወዲያና ወዲኽ ያደርጋሉ አለ ትእምርተ ተልእኮ ነው፡፡

👉 አንድም በኹለት ክንፋቸው ፊታቸውን መሸፈናቸው ባሕርይኽን መመርመር አይቻለንም ሲሉ፤ በኹለት ክንፋቸው እግራቸውን መሸፈናቸው ባሕርይኽን መረማመድ መተላለፍ አይቻለንም ሲሉ፤ ኹለት ክንፋቸውን ወዲያ ወዲኽ ያደርጋሉ ከእእምሮ ወደ አእምሮ ለመፋለሳቸው፡፡
👍133🕊1
👉 አንድም ኹለት ክንፋቸውን ወደ ላይ አድርገው ይታያሉ አለ ወደላይ ቢወጡ ቢወጡ አትገኝም ሲሉ፤ ኹለት ክንፋቸውን ወደታች አድርገው ይታያሉ ወደታች ቢወርዱ ቢወርዱ አትገኝም ሲሉ፤ ክንፋቸውን ወዲያና ወዲኽ ያደርጋሉ ወዲያና ወዲኽ ቢሉ አትገኝም ሲሉ፤

👉 አንድም ወደላይ መዘርጋት በሰማይ ምሉእ ነኽ ሲሉ ወደታች መዘርጋቸው በምድርም ምሉእ ነኽ ሲሉ፤ ወዲያና ወዲኽ መዘርጋታቸው በኹሉ ምሉእ ነኽ ማለታቸው ነው፤

👉 አንድም ወደላይ መዘርጋት ትእምርተ ተመስጦ ወደታች መዘርጋት ትእምርተ ትሕትና፤ ወዲያና ወዲኽ ረብቦ መታየት ትእምርተ ተልእኮ ነው።

💥 በአጠቃላይ ኹለት ክንፋቸውን ወደላይ ኹለት ክንፋቸውን ወደታች ኹለት ክንፋቸውን ወዲያና ወዲኽ አድርገው ትእምርተ መስቀል መሥራታቸው በብሉይ ኪዳን ከኾነ እንዲኽ ባለ መስቀል ተሰቅለኽ ዓለምን ታድነዋለኽ ሲሉ በዘመነ ሐዲስ የኾነ እንደኾነ እንዲኽ ባለ ትእምርተ መስቀል ተሰቅለኽ ዓለምን አድነኸዋል ሲሉ ነው፡፡

💥 የእነዚኽ አርባዕቱ እንስሳ ፊታቸው በርካታ ምስጢራትን ሲያመለክቱ ገጸ ሰብእ በማቴዎስ፤ ገጸ አንበሳ በማርቆስ፤ ገጸ ላሕም በሉቃስ፤ ገጸ ንስር በዮሐንስ ተመስሏል፤ በሌላ ምስጢር የሰው ገጽ ያለው የጌታን ሰው የመኾንን ነገር፤ የላም መልክ ያለው በቀራንዮ ላይ ደሙን ማፍሰሱ፤ የአንበሳው መልክ ያለው የጌታችንን ትንሣኤ፤ የንስር መልክ ያለው የጌታን ዕርገት እንደሚያመለክቱ መተርጒማን ይተነትኑታል፤

💥 ዐምደ ሃይማኖት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም እጅግ ምጡቅ በኾነው ዕውቀቱ ዕጓለ አንበሳ የተባለው የወልድ የባሕርይ አባቱን አብን በአንበሳ ይመስለዋል፤ ሥጋን ተውሕዶ ፍጹም ሰው የኾነው ወልድን የሰው መልክ ባለው መስሎ ገልጾታል፡፡ በአምሳለ ርግብ ወርዶ በወልድ ራስ ላይ ተቀምጦ የታየው መንፈስ ቅዱስን የንስር መልክ ባለው መስሎ አብራርቶ ጽፎታል፤ በቀንዱ የማይበራታ ላሕም ተብሎ የተመሰገነው የወልደ እግዚአብሔር ቅዱስ ሥጋው የሚፈትትባት፤ ክቡር ደሙ የሚቀዳባት በአራቱ ኪሩቤል አምሳል አራት መአዝን ያላት ቤተ ክርስቲያንን በገጸ ላሕም አምሳል ገልጦ አመስጥሮታል፡፡

✍️ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ፡-
“አርባእቱ እንስሳ በእንቲኣነ ጸልዩ
ኢይልክፈነ ለእሳት ዋዕዩ
እንስሳ አርባዕቱ መናብርቲሁ ለዋሕድ
መተንብላን ለኲሉ ትውልድ”

(አራቱ እንስሳ የሲኦል እሳት ግለቱ እንዳይነካን ስለ እኛ ጸልዩ፤ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለውን አምላክ ዙፋኖቹ የኾኑ አራቱ እንስሳ ለትውልድ ኹሉ አማላጅ ናቸው) በማለት አንደተማፀነ እኛም የአምላካችንን ዙፋን የሚሸከሙ እነዚኽን ግሩማን መንፈሳውያን መላእክትን ከጌታችን ከአምላካችን ከክርስቶስ እንዲያማልዱን እንለምናለን፡፡
[ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ፤ መጽሐፈ ሰዓታት ንባቡና ትርጓሜው ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ]

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
9👍7😢2
የ“at least” ክርስትና -

|ጃንደረባው ሚዲያ - መስከረም 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ቀሲስ ታምራት ውቤ እንደጻፉት
(በእውነታ ላይ የተመሠረተ ምናባዊ ጽሑፍ)

በቅርብ በቅዱስ ጋብቻ አንድ ከሆኑ ጥንዶች ጋር ስለ ክርስትና ሕይወታቸው አባታችንን ለማወያየት ፈልገው በቤታቸው ተገናኘን፡፡ በውይይታችን ከተነሡት በርካታ ጉዳዮች የዘመኑን የክርስትና ሕይወት አጉልቶ የሚያሳዩ ሁለት ነጥቦችን እነሆ፡-

የመጀመሪያው ከእንግዶቹ የተነሣው ሐሳብ “ከአንዳንድ ወንድምና እኅቶች ጋር ስለ መንፈሳዊ ሕይወት ስንመካከር በክርስትና ሕይወት ስንኖር ‘at least’ እነዚህ የመሰሉ ነገሮችን ልንፈጽም እንደሚገባ ነግረውናል፡፡ እርስዎስ ምን ይመክሩናል?” በማለት አባታችንን በጠየቋቸው ጥያቄ ውይይታችንን ጀመርን፡፡

አባታችን በተቀመጡበት ትንሽ በዝምታ ከቆዩ በኋላ እንዲህ ሲሉ ጀመሩ፡፡

“የጌታ እግዚአብሔር ፈቃዱ የተገለጠባቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት በኅሊናዬ ለመዳሰስ ሞከርኩ፡፡ እናም ላገኘው ያልቻልኩት ነገር ቢኖር ‘ቢያንስ (at least)’ በሚል ቀዳሚ ቅጽል የተቀመጠን ትእዛዝ ነው፡፡ መንግሥተ እግዚአብሔርን ለመውረስ የተቀመጠ ‘አነስተኛ መሥፈርት (minimum requirement)’ ምን እንደሆነ ማወቅ ብችል ብዬ አሁንም ለማሰብ ሞከርኩ፤ ግን አሁንም መልስ ማግኘት አልቻልኩም፡፡” አሉን ትክዝ ባለ ድምፅ፡፡

“ምክንያቱም…” ሲሉ ቀጠሉ “ምክንያቱም ያ መሥፈርት መንግሥቱን ለመውረስ ካበቃ ‘ዝቅተኛ መሥፈርት’ ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን በተለምዶ አንዳንድ መምህራነ ወንጌል ‘ክርስቲያኖች ከሆንን ቢያንስ (at least) ይህን ልንፈጽም ይገባናል’ እያልን ስለምናስተምር፣ የነፍስ አባቶችም ልጆቻችንን ስንመክር ‘ልጆቼ ቢያንስ ይህንና ይህን ለማድረግ ሞክሩ’ ስለምንል ምእመኑን የ‘ቢያንስ (at least)’ ክርስትና ውስጥ አመቻቸነው፡፡ ምእመኑም ለሚበልጠው ጸጋ ከሚተጋ ይልቅ ‘at least’ ይህን ይህን እየፈጸምኩ ነው በማለት ለራሱ የጽድቅ መሥፈርት አስቀምጦ ተዘናጋ፡፡ ከእነቅዱስ ጳውሎስ የተማርነው ግን “ … እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቆጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፡፡ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፡፡” የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 3÷13)

በመጽሐፍ ቅዱስ ‘አድርግ አታድርግ፤ ሁን አትሁን’ እንጂ፤ ‘at least’ ይህን አድርግ ይህን አታድርግ፤ ‘at least’ ይህን ሁን ይህን አትሁን’ የሚል የለም፡፡ወጥመድ የማይመስሉ የክፉውን ማዘናጊያና የምኞታችንን ማባበያ ትተን “ንቁ! በሃይማኖት ቁሙ፣ ጠንክሩ” (1ኛቆሮ. 16÷13) የሚሉትን የአባቶቻችን የሐዋርያትን ምክር መስማት ካልቻልን ሊውጠን ፈልጎ በዙሪያችን ለሚያገሳው አንበሳ ጥሩ ታዳኝ እንሆናለን፡፡

ለአባታችን ያነሣነው ሁለተኛው ነጥብ ዓለም ዛሬ የሚቀበለው ማስረጃ የሚቀርብበትን ጉዳይ ስለሆነ ይህን አካሄድ ከእምነት ጋር ማስማማት የሚቻልበት ምን መንገድ ሊኖር እንደሚችል ነበር፡፡ ከልምዴ እንደማውቀው አዲስ ነገር ሊነግሩን ሲሉ እንደሚያደርጉት ፈገግታ የተቀላቀለው ረዥም ትንፋሽ አወጡና “በየጊዜው የእግዚአብሔርን ቃል ለማሰማት በቆምኩባቸው ጉባኤዎች ሁሉ እየታዘብኩ የመጣሁት ምእመናኑ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ‘ማስረጃ’ እንዲቀርብ ያለው ፍላጎትና መምህራንም ምእመኑን በማስረጃ እያበለጸግን በእምነት ግን እያደኸየን መምጣታችንን ነው፡፡ ይህ በሊቃውንት (በኢትዮጵያ ሊቃውንት ዘንድ ብቻ ማለቴ አይደለም) ዘንድ ‘ቶማሳዊነት’ ይባላል፡፡ ‘ጌታ ተነሥቷል ሲባል ጣቴን በችንካሩ ካላገባሁ፤ በእጆቼም የተወጋ ጎኑን ካልዳሰስኩ አላምንም’ ማለት ነው፤ ለሁሉ ማስረጃ ፍለጋ! ጌታችን ለዚህ መልስ ሲሰጥ “ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው” ነው ያለው፡፡ (ዮሐ. 20)

እምነትና ማስረጃ ፍጹም የተለያዩ መንገዶች ናቸው፡፡ እምነት የማስረጃ ጥገኛ አይደለም፡፡ በራሱ ጸንቶ የቆመና ጸንቶ ለማቆምም መሠረት መሆን የሚችል ነው፡፡ በክርስትና ለሁሉ ነገር ማስረጃ ከፈለግን ከማመን ይልቅ ለመካድ ቅርብ እንሆናለን፡፡ መምህራንም ያሳመንን እየመሰለን በማስረጃ ጋጋታ ከእምነት ምእመኑን እያራቆትነው ነው፡፡(ይህ ሲባል እንደው ጠቅሎ ማስረጃ አያስፈልግም ለማለት አይደለም፤ የማስረጃ ጥገኝነታችን ልኩን እያለፈ መምጣቱ ለእምነት የሚፈጥረውን እንቅፋት ለማመልከት እንጂ፡፡ ለሚያምን “ጸሎተ ሃይማኖት በቂው ነው” እንዲሉ አበው፡፡) ማስረጃ አንድን ነገር እውነት ወይም ሐሰት መሆኑን ያሳውቀናል፡፡ ማስረጃ ከዕውቀት ጋር እንጂ ከእምነት ጋር ባሕርያዊ መስመር አያገናኛቸውም፡፡ በክርስትና በእምነት እንጂ በማስረጃ ምንም ያህል ርቀት እንደማንሄድ ብዙ ማስረጃ ማምጣት ይቻላል፡፡ ግን ከዘረዘርኩ አሁንም ማስረጃ ላቀርብ ነውና በሐሳቤ ተቃርኖ ላይ ልቆም ነው፡፡ ስለዚህ እመን!!!

ይህ በሽታ ሲጀምር አንድ ቃለ እግዚአብሔር በተነገረ ቁጥር ‘ምን ላይ ተጽፏል?’ በማለት ይጀምራል፡፡ ይህ ማለት በሚያስተምረን መምህር ላይ እምነት የለንም ማለት ነው፡፡ ግን እኮ መምህሩ ለጠቀሰው ጥቅስ እንጂ ለሰጠው ማብራሪያና ትንታኔ፣ ላመጣው ትርጓሜና ላመሠጠረው ምሥጢር ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ወይስ ጥቅሱን ማሳየቱ ብቻውን ያቀረበውን ትንታኔና የተረጎመውን ትርጓሜ ትክክል ያደርገዋል? ያለው አማራጭ አንድ ነው፡፡ መምህሩን ካመንከው አዳምጠው ካላመንከው አታዳምጠው፡፡ (የኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ ዋና መለያ “understanding scriptures through the eyes of the fathers” - መጻሕፍትን በአበው የትርጓሜ ቅኝት መረዳት የሚል ነው፡፡ አበው ብለን የምንቀበላቸውም ከሐዋርያት ለጥቀው የተነሱ በይበልጥ “በሃይማኖተ አበው” ደገኛ እምነታቸው የተመሰከረላቸውን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና እነርሱን የመሰሉትን ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን መምህር ለመለየት የአበውን መንገድና ትምህርተ ሃይማኖትን የሚገልጡበትን የአነጋገር ዘይቤ የሚጠቀሟቸውንም ቃላት ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለአምልኮ መሥዋዕት የሚቀርቡ ከአትክልትም፣ ከአዝርዕትም፣ ከዕፅዋትም እንዳለ ሁሉ ለነገረ መለኮት ማመሥጠሪያ የተመረጡ ቃላትና የአነጋገር ዘይቤም አለ፡፡ እውነተኛ መምህር በኑሮው ብቻ ሳይሆን በንግግር ፍሬውም ይታወቃል፡፡)

በሽታው እያደገ ሲሄድ ምሥጢራትንና በምሥጢራት የምናገኘውን ጸጋ መጠራጠር እንጀምራለን፡፡ ይህም ‘እምነት አልቦ ክርስቲያኖች’ የምንሆንበት ደረጃ ነው፡፡ የሚታይብንም በልማድ የምንፈጽመው ሥርዓት እንጂ በመንፈስ በእውነትና በእምነት የሆነ አምልኮ አይደለም፡፡ የሥርዓት ክርስቲያኖች(Canonical Christians) እንጂ መንፈሳዊ ክርስቲያኖች (Spiritual Christians) ለመሆን እንቸገራለን፡፡ ፍጻሜውም የጸጋው ባለቤት የሆነውን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስን መጠራጠርን ያመጣል፡፡

ዛሬ በቤተክርስቲያን ለምናየው ፍሬ ሃይማኖትና መዓዛ ምግባር መታጣት አንዱ ምክንያት ይሄ ነው፡፡ አገልጋዩና ምእመኑ አይተማመኑም፡፡ (አገልጋዩ ከምእመኑ በትምህርተ ሃይማኖት የተሻለ ሆኖ ካልተገኘ፤ ለምእመናን ጥያቄ መልስ ለመስጠት ለሕይወታቸውም አቅጣጫ ለማሳየት የማይበቃ ከሆነ በሹመቱ እንጂ በትምህርቱ ቁጥሩ ከምዕመናን ይሆናል፡፡ “እልል በሉ” ንማ ሁሉም ያውቀዋል፡፡ ሁለተኛው በእምነት፣ በምግባርና በትሩፋት ከእነርሱ ተሽሎ ካልተገኘ ተግሣጹን ይንቁታል ምክሩን ያቃልሉታል፡፡ በመሆኑም ደግ የሃይማኖት መምህር በትምህርቱም በሕይወቱም ላቅ ብሎ መታየት ይኖርበታል፡፡) ስለዚህ የምንማረውም ሆነ
👍189😢1
የምናስተምረው ወደ ክህደት ለመድረስ ነው፡፡ ሳናውቀው!!!”

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍9
2025/07/13 15:14:27
Back to Top
HTML Embed Code: