Telegram Web Link
“እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እህቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ  ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡

የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንሆናለን፡፡”
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                      •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
“እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እህቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ  ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡

የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንሆናለን፡፡”
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                      •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
#አዲሱ_ዓመት
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

#ወዳጄ_ሆይ! ገንዘብ የለህምን? ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርግ፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ የምታደርግ ከኾነ ገንዘብ ካላቸው በላይ ባለጠጋ ነህ፡፡ “እንዴት?” ትለኝ ይኾናል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- የእነዚያ (የባለጠጐቹ) ገንዘብ ያልቃል፡፡ ያንተ ግን ብል አይበላውም፡፡ ጊዜ አይለውጠዉም፡፡ አያልቅም፡፡ ወደ ሰማያት፣ ወደ ሰማየ ሰማያት፣ ወደ ምድር፣ ወደ አየራት፣ ወደ እንስሳቱ ዓይነት፣ ብዙ የብዙ ብዙ ወደሚኾኑት ዕፅዋት፣ ወደ ደቂቀ አዳም በጠቅላላው፣ ወደ መላዕክት፣ ወደ መላዕክት አለቆች፣ ወደ ኀይላት ተመልከት፡፡ እነዚህ ኹሉ የአምላክህ ፍጥረቶች ናቸው፡፡ የእነዚህን አምላክና መጋቢ ባሪያ መኾን ድኻ መኾን አይደለምና ድኻ አይደለህም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

#ተወዳጆች_ሆይ! ቀናትን ቆጥሮ በዓል ማድረግ የክርስቲያን ግብር አይደለም፤ የአሕዛብ ግብር እንጂ፡፡ እንዴት? የክርስቲያኖች ተፈጥሮ በቀንና በወር የተገደበ አይደለምና፡፡ አገራችን ሰማይ ነው፡፡ ግብራችን ሰማያዊ ነው፡፡ ኅብረታችንም ከሰማያውያን መላዕክት ጋር ነው፡፡ በዚያ መዓልት ለሌሊት ስፍራውን አይለቅም፡፡ ሌሊትም በተራው ለመዓልት አይለቅም፡፡ እዚያ ኹሌ መዓልት ነው፡፡ እዚያ ኹል ጊዜ ብርሃን ነው፡፡ ስለዚህ “ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ” እንደተባልን ኹል ጊዜ ማሰብ ያለብን ይህንን ነው (ቈላስ.3፡1)፡፡ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮአችን ከዚህ ምድራዊ አቈጣጠር በላይ ነው፡፡ በንጽህና በቅድስና እየኖርን ዘወትር በዓልን የምናከብር ከኾነም የዚሁ ዓለም ሌሊት ለእኛ ሌሊት አይደለም፤ መዓልት ነው እንጂ፡፡ ዘመናችንን በሙሉ በገቢረ ኀጢአት፣ በስካር፣ በዘፈን የምናሳልፈው ከኾነ ግን መዓልቱ ለእኛ መዓልት አይደለም፤ ሌሊት ነው እንጂ፡፡ ፀሐይዋ ብትወጣም ልቡናችን ገና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይኖራልና ቀን እንደወጣ አይቈጠርም፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​​​🌼 ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ

ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።

ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት  እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ

ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።

በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን

🌻 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
#ዕለታዊ_መልዕክት

መጾም ያቃተውን ሰው ጹም፣ መመጽወት የተሳነውን መጽውት፣ መራመድ የማይችለውን ሩጥ የሚሉ መካሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ መራመድ የማይችል እንዴት መሮጥ እንዳለበት ከማሳየት ይልቅ ቀንበር ማክበድ ጠባያችን ሆኗል፡፡ ይህ የሚያሳየው ቃሉ እንጂ ተግባሩ የተለየን መሆኑን ነው፡፡ በተግባር መግለጥ ብንችል ኖሮ፣ ማገዝ ቢያቅተን እናሯሩጠውና ሰውነቱ ሞቆ ተጋድሎ ሲጀምር እናፈገፍግ ነበር፡፡ እኛ ግን ልምድ የሌለውን ሁሉ ተሸከም ማለት ይቀለናል፡፡ ከባለ ግመሉ ከአባ ቆሪር ምክር ለመመጽወት የሄደ ክርስቲያን ግመሉ ከሚችለው በላይ ስለጫነው አንተ አቅም አጥተህ ምክር ለመቀበል መጥተህ ሳለ ግመሉን ካለ አቅሙ ለምን ጫንከው ተብሏል፡፡

ከአቅማቸው በላይ ተሸክመው የከበዳቸውን ሰዎች በማገዝ ሸክሙ ሳይከብዳቸው፣ ከክርስቲያናዊ ተጋድሎ ሳያፈገፍጉ በእምነት እንዲኖሩ ማገዝ ከዘመናችን የሃይማኖት ሰዎች የሚጠበቅ መሆኑን ለማስታወስ የአባ ዳንኤልን ፈሊጥ በአብነት እጠቅሰዋለሁ፡፡ አንድ አባ ዳንኤል የሚባል መነኩሴ ነበር፡፡ የደከመ ባገኝ አግዛለሁ እያለ በጨረቃ ከበዓቱ ወጥቶ ገዳማውያን በሚገኙበት በረሓ ይዞር ነበር፡፡

#በአንድ_ወቅት የማትሠራው ኃጢአት ያልነበር፣ ከጽድቅ ተግባር የማትተዋወቅ ሴት አገኘ፡፡ አባ ዳንኤልም ሴቲቱን ወደ ሴቶች ገዳም ወስዶ ልብላ ካለች ትብላ፣ ልተኛ ካለች ትተኛ፣ የፈቀደችውን ሁሉ ታድርግ፣ የገዳሙ ሕግ አይፈቅድም በማለት ቀንበር አንዳታከብዱባት ብሎ ለእመምኔቷ አስረክቧት ሔደ፡፡ እመምኔቷም እንደታዘዘችው አደረገች፡፡ ሴቲቱ በፈለገች ጊዜ ትበላለች፣ ስትፈልግ ትተኛለች፡፡ ያሰኛትን ታደርጋለች፡፡ ግን ደስታ የላትም፤ አብረዋት የሚኖሩት መነኮሳት ቤተ ክርስቲያን አድረው፣ በሥራ ተጠምደው ሲኖሩ ተመለከተች፡፡ እሷ በልታ ይርባታል፡፡ እነሱ ሳይበሉ አይራቡም፣ እሷ ተኝታ ይደክማታል፣ እነሱ ቆመው ውለው፣ ቆመው አድረው ድካም አያውቁም፡፡ ቀስ በቀስ መገረም፣ ከዚያም በሕይወታቸው መቅናት ጀመረች፡፡

#ምግብ ሲያቀርቡላት እስከ ሦስት ሰዓት ልቆይ ማለት ጸሎት አድርጋ መብላት ተለማመደች፡፡ ቆየችና እስከ ስድስት ልቆይ አለቻቸው ከዚያም እስከ ዘጠኝ፣ ከዚያም በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ መመገብ ጀመረች፡፡ ከዚያም ከሳምንት አንድ ቀን ብቻ መቅመስ በመጨረሻም በዓቷን ዘግታ በሦስት ሳምንትም፣ በወርም በሕይወት ለመቆየት ያህል መቅመስ ደረሰች ማለት ነው። አስቡት እስኪ እንዲህ ድክመታችንን ታግሰው ለክብር የሚያበቁን ባለ ፈሊጥ መምህራን ማግኘት ለዚህ ዘመን ደካማ ተሸካሚ ከዕንቊ የበለጠ ስጦታ ነው እላለው እናንተስ?
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ወንድሞቼ_ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል?

#ተወዳጆች_ሆይ!
አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡

#ልብ_በሉ!
ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡

#ክርስቶስን_ማክበር_ትወዳላችሁን?
እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ብሏልና።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
በታመምህ ጊዜ ድካም ይሰማሃል፤ ብርታት ያንስሃል፤ ፊትህም ይገረጣል፡፡ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህን በአግባቡ ማከናወን ይሳንሃል፡፡ በዚህ ጊዜም ሕመምህ ምን ያህል እንደበረታ ሰዎች ያስተውላሉ፤ መታከም እንደሚገባህም ይነግሩሃል፡፡ ስለዚህ ወደ ሐኪም ትኼዳለህ፡፡ ወደ ሐኪም የምትኼደው ግን ሐኪሙ ምን እንዲያደርግልህ ነው? አሁን ለሚሰሙህ ስሜቶች የሚሽሩ መድኃኒቶችን እንዲሰጥህ ነው፡፡ ኾኖም ይሰሙህ የነበሩ ስሜቶች ቢሻሉህም ሰውነትህ አሁንም እንደ ደከመ፣ ፊትህ እንደ ገረጣ ከቀረ፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህንም በአግባቡ ማከናወን ከተሳነህ፥ በተሰጠህ ሕክምና ደስተኛ ትኾናለህን? አትኾንም!

“እውነታው ምንድን ነው?” ስንል ወደ ሐኪሙ የኼድከው የበሽታህን ምንጭ ለመታከም ሳይኾን የበሽታህን ምልክቶች ለማስታገሥ ስለ ኾነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የበሽታህ መንሥኤ እስካልታከመ ድረስ የበሽታህ ምልክቶች ለጊዜው ቢታገሡም ቅሉ፥ ፈጽመው ሊወገዱ እንደማይችሉ ሐኪሙ በደንብ ያውቃል፡፡

በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ፣ በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳውያን የተባልን እኛም እግዚአብሔር መንፈሳዊ በሽታችንን እንዲያስወግድልን እንሻለን፡፡ እንደ እውነታው ግን ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንዲያስወግድልን የምንሻው ምልክቶቹን ነው፡፡ ለምሳሌ ችግርን፣ ኀዘንን፣ ቀቢጸ ተስፋንና የመሳሰሉትን እንዲያርቅልን እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የእነዚህ ምክንያት የኾነውንና ሥር የሰደደውን፣ ዋና ምክንያትም የኾነውን መንፈሳዊ በሽታችንን ሳይሽር እነዚህን ምልክቶች ሊያርቅልን አይፈልግም፡፡ ችግር የሚኾነውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ ምልክቶቹን እንዲያርቅልን ስንደክም፥ ወደ ውሳጤያችን ገብቶ የችግሩን ምንጭ ሊያርቅልን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ (ኃይልን) አጥብቀን እንቃወማለንና፡፡ በውሳጤያችን የተሸሸገውን በሽታ ማስወገድ አንፈልግም፡፡ አመለካከታችን እንዲለወጥ አንፈቅድም፡፡ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣውና አማን በአማን የምንታከመው ግን የልባችንን ውሳጤ ለእግዚአብሔር ስንከፍትለትና እርሱም በዚያ በመረቀዘው ቁስላችን ላይ ጽኑ መድኃኒት ሲያስርልን ነው፡፡ እንዲለወጡ የምንፈልጋቸው ምልክቶች በእርግጥም የሚለወጡት ይህ በልባችን ውስጥ የተደበቀው መንፈሳዊ በሽታችን ሲጠፋ ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
“እምነት አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡

ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡

ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡

እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
“እምነት አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡

ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡

ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡

እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
#ሰው_ሆይ!

በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ " በማለት ተናገር።
አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስኪ ከፍ ካለው ተራራ፣ ከታላቁ ባህር፣ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ 4፥4)

ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን?

ከአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ -
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
"ክርስትና የሚጀምረዉ ከተግባር እንጂ ከወሬ አይደለም፡፡ ሕይወታችን በጥቅስ ተገንዞ በጥቅስ የተቀበረ ከሕይወትና ከሥራ የተለየ እንዲሆን አንፍቀድለት፡፡"
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

‹‹ ዘመን ማለት አንተ ነህ ፡፡ አንተ ሰላማዊ ስትሆን ሰላማዊ ትሆናለች፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች፡፡››
አንጋረ ፈላስፋ

‹‹ራስህን ለማየት ወደ መስታወት ብትመለከት ዉበትህን ወይም ጉድለትህን ያሳይሀል፡፡ ምንም ነገር እንዳታይ ታደርግ ዘንድ ከመስታወቱ መሰወር አትችልም፡፡ ማንም ሊያመልጥበት በማይችለዉ በፍርድ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡››
አንጋረ ፈላስፋ

‹‹ የአንጥረኛ ዕቃ በየቀኑ በተመታ ቁጥር የበለጠ ጽሩይ እየሆነ እንደሚሄደዉ ሁሉ ሰዉነቱን ለማድከም ራሱን የሚያስገዛ ሰዉም እንዲሁ ነዉ፡፡ በየቀኑ እየተማረ፣ እየጠራ እየነጻ ከጠላት ስዉር ወጥመድ እየተጠበቀ ይሄዳል፡፡››
አንጋረ ፈላስፋ

‹‹ ሀብትን ብታከማች ያንተ አይደለም፡፡ ብትመፀዉተዉ ግን ታከማቸዋለህ፡፡››
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ

‹‹ ስለ ወንድሙ መዳን የማይደክም ድኗል ብዬ አላምንም፡፡››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

‹‹ እግዚአብሔር አንድን የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ሊሰጥህ ቢወድ ፀጋዉን ልትጠብቀዉ ከምትችለዉ ከትህትና ጋር ይሰጥህ ዘንድ ለምነዉ አለበለዚያ ግን ከአንተ እንዲያርቀዉ ጠይቅ፡፡››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

‹‹ ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እዉነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእዉነት እናገራለሁ፡፡ እዉነተኛ ትህትና ትሩፋትን መሥራት ነዉ፡፡››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

‹‹ ስለ ሌሎች ሰዎች ያለማቋረጥ ፀልዩ፡፡ወደ እግዚአብሔር ይደርሱ ዘንድ የንስሐ እድል አላቸዉና፡፡ ለእነርሱ ነቀፋ እናንተ ምላሻችሁ ፀሎት ይሁን፡፡››
ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥዉ ለአንበሳ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ማስታወቂያ

🌿  መርጌታ የባህል ህክምና ፈውስ እና ጥበብ ይደዉሉ # 0917468918
   0917468918 በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1🌿🌴 ለመፍትሄ ሀብት
2🌿🌴 ለህማም
3🌿🌴 ለመስተፋቅር
4🌿🌴 ቡዳ ለበላው
5🌿🌴 ለገበያ
6🌿🌴 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7🌿🌴 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8🌿🌴 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9🌿🌴 ለዓቃቤ ርዕስ
10🌿🌴 ለመክስት
11🌿🌴 ለቀለም(ለትምህርት)
12🌿🌴 ሰላቢ የማያስጠጋ
13🌿🌴 ለመፍትሔ ስራይ
14🌿🌴 ጋኔን ለያዘው ሰው
15🌿🌴 ለሁሉ ሠናይ
16🌿🌴 ለቁራኛ
17🌿🌴 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18🌿🌴 ለመድፍነ ፀር
19🌿🌴 ሌባ የማያስነካ
20🌿🌴 ለበረከት
21🌿🌴 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22🌿🌴 አፍዝዝ አደንግዝ
23🌿🌴 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24🌿🌴 ለግርማ ሞገስ
25🌿🌴 መርበቡተ ሰለሞን
26🌿🌴 ለዓይነ ጥላ
27🌿🌴 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28🌿🌴 ለሁሉ መስተፋቅር
29🌿🌴 ጸሎተ ዕለታት
30🌿🌴 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31🌿🌴 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32🌿🌴 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33🌿🌴 ለድምፅ
34🌿🌴 ለብልት
35🌿🌴 በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስረ
2.🌿🌴 ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
3.🌿🌴 ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
4.🌿🌴 ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
5.🌿🌴 ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምንሰራው ሰራ ደፋርና በራስ የመተማመን ችሎታ እንዲኖሮት እናደርጋለን
6.🌿🌴 ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
7.🌿🌴 ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
8.🌿🌴 ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
9.🌿🌴 ትምህርት አልገባ ላለው ቶሎ የመርሳት ችግር ላለበት በሚደገም እና በሚነበብ ፅሁፍ ብቻ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ስራ እንሰራለን
10.🌿🌴 መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
11.🌿🌴 ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ ያማክሩን ያስተውሉ እኛ ምንሰራው በጥንታዊው ከአባቶቻችን በተማርነው ጥበብ ብራናውን አንብበን እፅዋትን ቀጥፈን አዘጋጅተን ነውና ሀገራችን ካሏት ጥበብ ጥቂቱ ነው እንኳን ለነዚህ እና አባቶቻችን በደመና ይሄዱ አልነበር እፀመሰውር ሰርተው እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር ይሄ ጥበብ ንቀን ፈረንጅ አምላኪ ሆነን ነው እንጂ ጥበቡ አሁንም አለ ይምጡ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር  በስልክ ቁጥራችን
0917468918  ይደውሉልን
#እንደ_ሞተ_ሰው_ሁን

ከወንድሞች አንዱ ወደ አባ መቃርዬስ መጥቶ " አባክህ ለህይወቴ የሚሆን መመርያ ስጠኝ" አለው ፡፡ አባ መቃርዬስም ያንን ወንድም ወደ መቃብር ሂድና በሙታን ላይ ክፋ ነገር አድርግባቸው፡፡ ብሎ ላከው ሰውየውም በሙታኑ ላይ ድንጋይ በመወርወርና በመሳደብ የተላከውን ፈፅሞ መጣ ፡፡ " አባ መቃርዮስም ምን አሉህ ? ሲል ጠየቀው " ያም ወንድም "ምንም አላሉኝም " ብሎ መለሰ ፡፡ በነጋታውም ተመልሰህ ናና አመስግናቸው  አለው፡፡ በነጋታውም ያ ወንድም ወደ መቃብሩ ስፋራ ተጉዞ ሙታኑን " ሐዋርያ ፣ ቅዱሳን ፣ጻድቃን ፣ እያለ አመሠገናቸውና ተመለሰ ፡፡ መቃርዮስም  " ምን መለሱልህ አለው" ምንም አለ ፡፡" መቃርዮስም " ስትሰድባቸው ፣በድንጋይ ስትመታቸው ፣ ስታመሰግናቸውም ፣ ስታወድሳቸው ፣ ምንም አልመለሱልህም ፡፡ አንተም ለነፋስህ ድህነት ከፈለግክ  እንደ "ሞተ ሰው ሆነህ ኑር"  ፡፡ ሰዎች ክፋ ቢያደርጉብህም ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ አለው ፡፡፡

ወዳጄ ሆይ የታላቁን አባት ምክር ልብ አልክን ? የሚሰድብህንና ድንጋይ የሚወረውርብህን እንዴት ማለፋ እንዳለብህ ተማርክ ? የሚያመሰግኑህንና የሚያወድሱህን እንዴት መቀበል እንዳለብህ አስተዋልክ ?

ቀልብህን የሚቀሙህ ብዙ ሰዳቢዎች አሉብህ፡፡ የሚያስጎነብሱህ ብዙ ድንጋይ ወርዋርዎች አሉብህ ፡፡ አንዱ ድህነትህን እያነሳ ያሸማቅቅሀል ፤ሀብት የሌለህና ገንዘብ መቁጠር ያልቻልከው የማትረባ ስለሆንክ ብቻ እንሆነ በማሰብ ያሳንስሀል።

በምግባርህ የሞትህ እንደሆንክ እየጮኸ ይነግርሀል ሃይማኖትህና ኢትዮጲያዊነትህ ለድህነት አስተዋፅኦ እንዳደረገና ማንነትህ ራሱ የተዋረደ እንደሆነ በመንገር ተፈጥሮህን " ንቀህ "አርቴፋሻል እንድትሆን ኦርጅናልነትህን አርክሰህ ፌክ እንድትሆን ይሰብክሃል፡፡ በዘር ገመድ ተብትበው ከወንድምህ ጋር የሚያናቁሩህ ሃይማኖትህንና ሰብአዊነትህ ሳይቀር በዘረኝነት ሰፌድ የሚያበጥሩ ድንጋይ ወርዋርዎችን እንዴት ይሆን ያለፋካቸው፡፡

ጾምህን የሚያንቋሽሹ ፣ ሱባኤህን የሚረብሹ ፣ ጸበል መጠጣትህን ፤እምነት መቀባትህን የሚያንሻፋፉ ፤እግዚአብሔር በሞተ ነገር ላይ ታሪክ እንደሚሰራ ስትነግራቸው የሚስቁ ፤ በሰማይ ህይወት አለ ስትላቸው በሙት አምራቸው የሚሳለቁ ፤ይልቅ ዓለምህን ቅጭ ጊዜህን ተጠቀምበት  የሚሉ አለማውያንና ማንነትህን ለማርከስ ማንነታቸውን ለማንገስ የሚወረውሩት ጥቁር ድንጋይ አቁስሎህ ይሆን ?

ወዳጄ ሆይ ታላቁ አባት እንዲህ ይልሃል ለስጋውያን ለስሌታውያን እንደ ሞተ ሰው ሁን ! ደግሞስ ገና ልትሰራ የምትችለውን ገና በልዑልነትህ ንጉስ ብለውህ ገና በወጣትነትህ ጻዲቅ አድርገውህ ገና በተማሪነትህ ረብኒ ብለውህ ዳዴህን ሳትጨርስ የአትሌትነት ማዕረግን ሰጥተውህ በዲያብሎስ መዝሙር ከፋ ከፋ በጣሙን ከፋ ከፋ ሗላ ስትወድቅ አጥንትህ እንዳይተርፋ ሰቅለው በአፋጢምህ የሚደፋህን አድር ባዮችና ህሊና ቢሶች እንዴት አልፈሀቸው ይሆን ? ለእነርሱም ወሬ መንኩሰህ እንደ ሞተ ሰው ሆንክን ??

- እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ትዳር አለህ ፡፡
- እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ህይወት አለህ።
- እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታጠነክረው ወዳጅነት አለህ።
- እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምትሰራው እልፋ ስራ አለህ ፡፡

ደግሜ ደግሜ እልሃለሁ የታላቁን አባት ቃል ተውሼ ለእነዚህ እንደሞተ ሰው ሁን! እንደ ሞተ ሰው ሁን እንጂ ሙት ሁን አልተባልክም ፤ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ በግብርህ ሕያው ሁን እንጂ ሙት አትሁን፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ልጄ ሆይ፤ ዋዘኛና ቀልደኛ አትሁን፡፡ በመከራ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታዝንና የምትራራ ሁን፤ በድኃ ላይ አትጨክን፤ ርስቱንና ቤቱንም በምክንያት አትውሰድበት፤ ለመጨረስም የማትችለውን ነገር አትጀምር፡፡

ልጄ ሆይ፤ በልተህ ስትጠግብ ረኃብን፤ ስትበለጥግ ድኅነትን፤i ስትሾም ሽረትን፤ ሌላውንም ይህን የመሰለውን ሁሉ አትርሳ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ለሞተው ወዳጅህ ከማልቀስ ይልቅ በሕይወቱ ሳለ የክፋት ሥራ ለሚሠራ ወዳጅህ አልቅስለት፡፡

ልጄ ሆይ፤ ባለ ጠጋ ሰው ሁሉ ይደግፈዋል፤ ድኃ ሲወድቅ ግን ሰው ሁሉ ወዲያው ይገፋዋል፡፡ ባለ ጠጋ ሲከሰስ በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይሟገትለታል፤ ድሀ ሲከሰስ ግን በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይፈርድበታል፡፡ መልካም ዳኛ በመካከላቸው የተቀመጠ እንደ ሆነ ግን ፍርዱ እንደ ፀሐይ ያበራለታል፡፡ ስለዚህ በምትኖርበት ሀገር መልካም ዳኛ አያጥፋብህ፡፡

ልጄ ሆይ፤ በማናቸውም ነገር ቢሆን ሞት አይቀርም፡፡ ነገር ግን በሰው እጅ ከመውደቅ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻላል፡፡

ለአፍህ መሐላ አታልምደው፤ እግዚአብሔር ስሙን ከንቱ ያደረገውን ሳይቀስፈው አይቀርምና ስሙን በከንቱ አትጥራ፡፡

ልጄ ሆይ፤ የምትሠራውን ሥራ ሁሉ ሰው ቢያየው ቢሰማውም አይጎዳኝም ብለህ እንደ ሆነ ነው እንጂ አይታይብኝም፤ አይሰማብኝም ብለህ አትሥራው፡፡ አንተ ምንም ተሰውረህ ብትሠራው ከተሠራ በኋላ መታየቱና መሰማቱ አይቀርም፡፡

ልጄ ሆይ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ
ሆነ ግን፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም፡

ልጄ ሆይ፤ በጌታህም ቤት ቢሆን በሌላም ስፍራ ቢሆን ገንዘብ ወይም ሌላ እቃ ወድቆ ብታገኝ አታንሣ፡፡ ብታነሣውም መልሰህ ለጌታህ ወይም ለዳኛ ስጥ እንጂ ሰውረህ አታስቀር፡፡

ልጄ ሆይ፤ በፍፁም ልብህ ለማትወደው ሰው ቤትህንና የቤትህን ዕቃ አታሳይ፡፡

ልጄ ሆይ፤ ንፁሕ አለመሆንህን እግዚአብሔር ያውቃልና በእርሱ ፊት ንፁሕ ነኝ አትበል፡፡ በንጉሥ ፊትም ብልህ ነኝ አትበል፤ የብልሃት ሥራ ሠርተህ አሳየኝ ያለህ እንደ ሆነ ታፍራለህና፡፡

ልጄ ሆይ፤ ጠላት በዛብኝ፤ ምቀኛ አሴረብኝ ብለህ እጅግ አትጨነቅ፡፡ በዓለም የሚኖር ፍጥረት ሁሉ ጠላትና ምቀኛ አለበት እንጂ ባንተ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚሁም በጥቂቱ እጽፍልሃለሁ፡፡ በፍየል ነብር፤ በበግ ተኩላ፤ በአህያ ጅብ፤ በላም አንበሳ፤ በአይጥ ድመት፤ በዶሮ ጭልፊት አለባቸው፡፡ ይህንንም የመሰለ ብዙ አለ፡፡ ሰውም እርስ በርሱ እንዲሁ ነው፡፡ ስለዚህ የሚመጣብህን ነገር ሁሉ በትእግሥት ሆነህ ተቀበለው፡፡ በመጨረሻው ግን ሁሉ አላፊ ነውና ጠላቶችህ ሁሉ ያልፋሉ፡፡ ወይም አንተ አስቀድመህ ታልፍና ከዚህ ዓለም መከራና ጭንቀት ታርፋለህ፡፡

ልጄ ሆይ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁiሉም መሬት ሆነዋል፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ፣ ሲያዝኑ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ፣ ሲራቡ፣ ሲጠሙ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል፡፡ ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል? የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን፡፡ ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት &  የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን በጣም እወቅው፡፡

ልጄ ሆይ፤ ቀን በሥራህ ላይ፤ ሌሊት በአልጋህ ላይ፤ የሚጠብቅህ እግዚአብሔር ነውና ማታ ስትተኛ፤ ጧት ስትነሣ እግዚአብሔርን አምላክህን መለመንና ማመስገን አትተው፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
   †    መስቀል    †          🕊

🌼        🌼

❝  መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው ፤ የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው ፤ መስቀል ርኩሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው ፤ የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው፡፡

መስቀል ማኅተመ ሥላሴ የሌለው ሰው ወደ እርሱ ሊቀርበው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው። መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው፡፡ መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው ፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበሳው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው፡፡

መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው፡፡ መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራራውን ውኃ በሱር በረሐ ያጣፈጠ ነው፡፡ መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው፡፡ ❞
[  ውዳሴ መስቀል  ]
🕊 እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን
🌼
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
#ቅዱስ_መስቀል

‹‹…ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠኀቸው …›› መዝ 59፣ 4
ቅዱስ መስቀል ቀስት ከተባለ ጠላታችን ዲያቢሎስ እናመልጥ ዘንድ ድል እናደርገው ዘንድ የተሰጠን ነው ፤ ቅዱስ መስቀል መድኅን ዓለም ክርስቶስ ተሰቅሎ በክቡር ደሙ ቀድሶ የሰጠን  ሰላማችን የታወጀበት ኃይላችን ፣የሰላም አርማችን ነው፤፡፡‹‹..እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው፡፡ ›› ኤፌ 2፣14-16

ቅዱስ መስቀል በዘባነ ኪሩብ ላይ የሚቆም የጌታችን እግሮች ተቸንክረው የዋሉበት የመድኅን ዓለም ክርስቶስ ዙፋን ነው፤ቅዱስ መስቀል ዲያቢሎስ ያፈረበት ሞተ ነፍስ ድል የተደረገበት ፣የሕይወት መንገዳችን እንቅፋት የነበረው ጠላታችን ዲያቢሎስ ከመንገዳችን ተጠርቆ የተወገደበት ፣በእኛ ላይ የነበረው ኃይል የተነጠቀበት ነው ‹‹… በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዝት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወገደው….›› ቆላ 2፣14 ፤

ቅዱስ መስቀል የመድኃኒታችንን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የተፈተተበት  ፣የእናቱ እመቤታችንን እናትነት የምናስታውስበት ነው፤‹‹ በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ የእናቱም እኅት የቀለዮጵያም ሚስት ማርያም መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀመዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ አላት፤ ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን እናትህ እነኋት አለው›› ( ዮሐ 19፣27)

ቅዱስ መስቀል በበደላችን ከገነት በወጣን ጊዜ በእሳት ሰይፍ ታጥራ የነረችው ገነት በክርስቶስ ሞት እንደተከፈተችልን ዳግመኛ እንኖርባት ዘንድ እንደተሰጠችን ያስታውሰናል‹‹…ኢየሱስም እውነት እልሃለው ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው…›› ( ፤ሉቃ 23፣43)

ቅዱስ መስቀል ሥራችንን ሁሉ የምንባርክበት ትምክህታችን ነው ፤ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ምዕመናንን በላከው መልእክቱ ‹‹..  ዓለም ለእኔ ተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልኩበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ ›› ገላ 6፣14 
‹‹…እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን ..›› መዝ 131፣7

የመድኅን ዓለም ክርስቶስ እግሮቹ በቅዱስ መስቀል ላይ በዕለተ ዐርብ ተቸንክረውበታል በክቡር ደሙ ተቀድሷልና የጸጋን ስግደት እንሰግድለታለን ለዚህም ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን በጸሎቷ ምስጋናን ስታቀርብ ‹‹..እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር…›› ‹‹ ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት በክቡር ደሙ ለቀደሰው  መስቀል እሰግዳለው በማለት ምዕመናንን ለቅዱስ መስቀሉ የአክብሮት የጸጋ ስግደት እንዲሰግዱ ሥርዓትን አበጀች፡፡

መልካም በዓል !


#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
መስቀል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/347-404/ እንደ ተሰበከው

እንኳን ለ2017 ዓ.ም የመስቀል በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ !

የጌታ መስቀል ለጆሮ ደስ የማይልና የሚያሳዝን ነው ። ነገር ግን ደስታንና ሐሤትን ይዟል ። መስቀል ለአይሁዳውያን ፈተና ፣ ለአሕዛብ እብደት ነው ። ለእኛ ለአማኞች ግን ድኅነታችንን ያስታውሰናል ። አንድ ሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ መስቀል ሲያነብ ሌላኛው የመስቀሉን መከራ ይታወሰዋል ። አማኞች መስቀሉ ላይ ሳይሆን ሰቃዮቹ ላይ ይበሳጫሉ፣ የሚያሳዝን ኀዘንና ልቅሶን ያወጣሉ ። መስቀሉ የቤተ ክርስቲያን ድኅነት ፣ መስቀሉ በእርሱ ተስፋ ለሚያደርጉ ሽልማት ነው ። መስቀል ከተያዝንበት ከሰይጣን ቊራኝነት ነጻ አውጥቶናል ። የተቀበልነው የመጀመሪያው በረከትም መስቀል ነው ። መስቀል የእግዚአብሔር ጠላቶች ከእግዚአብሔር ጋር የታረቁበት ፣ ኃጥአን ለክርስቶስ ቃል የገቡበት ነው ። በመስቀሉ ከጠላትነት ነጻ ወጣን ፣ በመስቀሉም የእግዚአብሔር ወዳጆች ሆንን ። መስቀሉ ከዲያብሎስ ሥልጣን ነጻ አወጣን ፣ ከሞትና ከጥፋትም አዳነን ። መስቀሉ ከሚጠፋው ነገር አላቅቆ ለሕያውነት የተገባ ሕይወትን ሰጥቶ የሰውን ባሕርይ ወደ መልአካዊነት ቀየረ ።

የመስቀሉ ኃይል ምንኛ ታላቅ ነው ! በእርሱስ ለሰው ልጆች የሆነው ለውጥ ምን ያህል ታላቅ ነው ! ከጥልቅ ጨለማ ማለቂያ ወደሌለው ብርሃን ፣ ከሞት ወደ ዘላለማዊ ሕይወት መለሰን ፣ ከመጥፋት ወደ ሕያውነት መራን ። በመስቀሉ ያልተደረገልን ምን መልካም ነገር አለ ? በመስቀሉ በኩል ጽድቅን ቅድስናን ተረዳን የመለኮትንም ባሕርይ ተማርን ። በመስቀሉ በኩል ስለ እግዚአብሔር እውነቱን ተረዳን ። በመስቀሉ በኩል ከእርሱ ርቀን የነበርነው ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆንን ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ጸጋም የተገባን ሆንን ። በመስቀሉ በኩል የፍቅርን ኃይል ተማርን ፣ ለሌሎችም ነፍሳችንን አሳልፈን ለመስጠት ቆረጥን ። በመስቀሉ በኩል ተነቃቅተናል ። የምናደርገው ሁሉም ጊዜአዊ አይደለም ፣ የሚመጣውን በረከት እንሻለን ። የማይታየውንም እንደሚታይ አድርግን እንቀበላለን ። መስቀሉ ይሰበካል ፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለ እምነት ይገለጣል ። የእርሱም እውነት በዓለም ሙሉ ይስፋፋል ።  መስቀሉ ይሰበካል ፣ በትንሣኤ ላይ ያለው እምነት ፣ የሰማዩ መንግሥትና ሕይወትም ያለ አንዳች ጥርጣሬ ይነገራል ። ከመስቀል በላይ እጅግ የተወደደ ፣ ነፍስን አብልጦ የሚያድን ምን አለ ? መስቀሉ ርኩሳን መናፍስት ላይ የሆነ ድል ፣ ጠላትን የምንቃወምበት መሣሪያ ጌታም የእባቡን (ራስ የቀጠቀጠበት) ሰይፍ ነው ። መስቀል የአብ ፈቃድ ፣ የአንድያ ልጁ ክብር ፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ ፣ የመላእክት ጌጥ ፣ የቤተ ክርስቲያን መጠበቂያ ፣ የቅዱስ ጳውሎስ ምስጋና ፣ የቅዱሳን ከለላ ፣ የዓለምም ብርሃን ነው ።

ዛሬ መስቀሉ ምንም ያህል የሚፈለግና በተገቢ ሁኔታ የሚወደድ ቢሆንም ፣ በጥንት ዘመን እጅግ አስፈሪና አሳፋሪ ምልክት ነበር ። አሁን ግን መስቀል ለንጉሥ ዘውድ የተመረጥ ማጌጫ ዓለም ላይ እጅግ ውዱ ምልክት ነው ። የመስቀሉ ምልክት አሁን ጌታና ባርያ ፣ ሚስትና ባል ፣ ኮረዳና ባለ ትዳር ፣ ባርያና ነጻ በሆናችሁት በእናንተ ዘንድ ይገኛል ። (ክርስቲያኖች) በሁሉም ቦታ ይህን የመስቀል ምልክት በተከበረው የሰውነት ክፍልና በግንባራቸው ልክ እንደ ተሳለ ዓምድ ተሸክመው ይዞራሉ ። በተቀደሰው ማዕድ ላይ ፣ በካህኑ ልብስ ላይና በምሥጢራዊውም እራት ከጌታ ሥጋ ጋር አብሮ ይደምቃል ። በሁሉም ቦታ ከፍ ብሎ ወደ ላይ ተሰቅሎ ታዩታላችሁ ፡- በቤት ፣ በገበያ ቦታ ፣ በበረሃ ፣ በመንገድ ፣ በተራራና በኮረብታ ፣ በባሕር ፣ በመርከብ ፣ በደሴት ፣ በሣጥን ፣ በልብስ ፣ በጦር መሣሪያ ፣ በአዳራሽ ፣ በብርና በወርቅ ዕቃ ፣ በሥዕላት ፣ በታመሙ እንስሳት አካል ላይ ፣ ርኩስ መንፈስ ባደረባቸው ሰዎች አካል ላይ ፣ በጦርነት ፣ በዓለም ፣ በከሰዓት ፣ በምሽት ፣ በበዓላት ፣ በመናንያን በአት ከፍ ብሎ ተሰቅሎ ታዩታላችሁ ። ማንም ሰው አያፍርም ፣ መስቀልም የሚያሳፍር ሞት ምልክት ነው በሚለው አሳብም አይናደድም ። በተቃራኒው ሁላችንም አክሊል ፣ ወርቅና ውድ ከሆነ ድንጋይ በላይ ለራሳችን እንደ ማጌጫ አድርገን እናከብረዋለን ። አንሽሽ ፣ አንፍራ ፤ ነገር ግን አቻ እንደሌለው ሀብት እንሳመው ፣ እናክብረውም ።

መልካም በዓል !
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
«ግሸን ደብረ ከርቤ»

ግሸን ደብረከርቤ ዳግማዊት ጎልጎታ ከደሴ ከተማ 82 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ ውስጥ በሃይቅ እና በመቅደላ በደላንታና በየጁ መካከል በበሽሎ ወንዝ አዋሳኝ ከፍተኛ በሆነ ተራራ ላይ የምትገኝ ገዳም ናት፡፡ የበሸሎን ወንዝ ተሻግረን ሰማይ ጥግ የደረሱ የሚመስሉትን ተራሮች ወጥተን በስተመጨረሻ መግቢያ አንድ በር የሆነ እና ከተራራው አናት ላይ በሚገኝ ስፋራ ላይ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸ እና ግማደ መስቀሉ የሚገኝበት የእግዚአብሔር አብ አብያተ ክርስቲያናት እና ፈዋሽ ጸበል ይገኛሉ፡፡ በ1942 ዓ.ም አቡነ ሚካኤል ጳጳስ ዘጎንደር ከዚህም ጋር ''መንፈሳዊ መናኝ'' በመባል የሚታወቁት ደገኛ አባት ያሰሩት ቤተ ክርስቲያንም ይገኛል፡፡

ግሸን ይህን የአሁኑን መጠሪያ ስም ከማግኘትዋ በፊት በተለያየ መጠሪያ ስሞች ትታወቅ ነበር:: በመጀመሪያ በአጼ ድልነአድ ዘመነ መንግስት በ896 ዓ.ም ሃይቅ ደብረ እስጢፋኖስ ሲመሰረት ''ሐይቅ ደብረ ነጎድጓድ'' ተብሎ ሲሰየም ግሸንም በሃይቅ ግዛት ውስጥ ስለሆነች ስምዋ ''ደበረ - ነጎድጓድ'' ተባለች፡፡ ይህን መጠሪያ ስም እንደያዘች እስከ 11ኛው ክ/ዘመን ድረስ ቆየች፡፡ በ11ኛው ክ/ዘ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው ጻድቁ ንጉስ ላሊበላ ከቋጥኝ ድንጋይ ፈልፍሎ የሰራው ቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር አብ ስም ይጠራ ስለነበር ግሸንም ''ደብረ እግዚአብሔር'' ተብላ መጠራት ጀመረች፡፡ ነገር ግን በዚህ ስም በመጠራት ብዙም ሳይቆይ ስሟ ተለውጦ ''ደብረ ነገሥት'' ተባለች፡፡ ደብረ ነገስት የተባለችውም ነገስታቱ ይማጸኑባት የክብርና የማእረግ እቃዎች የሚያሰቀምጡባትና የነገስታቱ የመሳፍንቱ ልጆችም የቤተ መንግስት አስተዳደር የሚማሩባት ስፍራ ስለነበረች ነው፡፡ እንደገና ደግሞ በ1446 ዓ.ም ኢትዪጵያዊው ፈላስፋ እየተባሉ በሚጠሩት በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት ግማደ መስቀሉ መጥቶ በዚህ ቅዱስ ስፍራ ሲያርፍ ደብረ- ነገሥት መባልዋ ቀርቶ ''ደብረ- ከርቤ'' ተባለች፡፡

የግሸኗ እመቤት ወላዲተ አምላክ ከደጇ በረከት ታሳትፈን።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
✤እንኳን ለመስከረም 21፤ብዙኃን_ማርያም
#ብዙኃን_ሊቃውንት_ለተሰበሰቡበት_ብዙኃን_ማርያም_
#ክቡር_መስቀሉና_ሌሎችም_ንዋያተ_ቅድሳት-በግሸን_ደብረ_ከርቤ_አምባ_ላይ_በክብር_ላረፉበት_ዕለት፤
#ለቅዱስ_ቆጵርያኖስ_(ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው )ና ፡ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ ሆነው የጠፉት ታላቋ ቅድስት ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት ላረፉበት ዕለት፤
#ሃይማኖታቸው_ለቀና_ለ318ቱ_አበው_ሊቃውንት  (#በ325 ዓ.ም #አርዮስን_አስተምረው_ለመመለስ_#በኒቅያ_የተሰበሰቡባት_ዕለት )፣ /የጉባኤውም ፍጻሜ ኅዳር ዘጠኝ ነው/ እንዲሁም
#ከ72ቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነው_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢባርዮስ_ዕረፍት በሰላምና በጤና አምላከ አበው መድኀኔዓለም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
✤✤✤✤
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓሏ መስከረም ፳፩ ቀን መከበሩ ስለ  ሁለት ነገር ነው፡፡ ፠1ኛ)
መስከረም ፳፩ የምናከብርበት አንደኛው ምክንያት  መስቀልን አስመልክቶ ነው፡፡ መስቀሉ በመስቀልኛ ቦታ በግሸን ደብረ ከርቤ በክብር ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
   #ግሸን_ደብረ_ከርቤ
ደብረ #ንገሥት  ፣ ደብረ #ነጐድጓድ ፣ ደብረ #እግዚአብሔር በሚባሉ ስም ትጠራ ነበር ፡፡
በመጀመርያም የተመሠረትቸው በአፄ ካሌብ  ዘመን ነበር ፡፡ሁለት ጽላቶች ከናግርን (አጼ ካሌብ ድል አድርጎ ከተመለሰ በኃላ ) በአባ ፈቃደ ክርስቶስ አማካኝንት (መነኰስ) አምጥተዋል ፤ ከዛም ሲመጡ  ወደ ጊሸን ተራራ ሊወጡ ሲሉ በዚያ ንብ ሰፎ ማር ሲንጠባጠብ በማየታቸወው በግእዝና አረብኛ ቋንቋ   #አምባ አሰል ብለው ጠሩት ትሩጉሙም የማር አማባ ማት ነው እስካሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል፡፡ የመጡትንም ጽላቶች በማስገባት የመጀመሪያውን ቤ.ክ ሠረተው ደብሩን መስርተዋል፡፡
  በሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ሰማዕታት ሃይማኖታቸው የቀና የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከአፄ ይኩኖ አምላክ ከተረፈው የመንግሥት ቅብዓት ተቀብተው ነገሡ፡ ስመ መንግሥታቸውም #ቆስጠንቲኖስ ተባለ፡ በተወለዱም በሃምሣ ዓመት ‹‹ መስቀሌን በመስቀል ላይ አስቀምጥ የሚል ራዕይ አይተው ›› ጠይቀው ሲረዱ አባታቸው የተረከበው መስቀል በመካ መዲናው አሕዛብ ሹም እንዳለ ተረዱ ክተት ሰራዊት ብለው አደሊዋ ድረስ ዘመቱ በዚህ ጊዜ የምስሩ ንጉሥ የአባትህ ገንዘብ እኔጋ  ስላለ እባክህ ከእኔ ጋር አተዋጋ መስቀሉን ፣ ሥዕላቱን እና ንዋያተ ቅዱሳቱን እስጥካለሁ አላቸው ( ማብራርያ መስከረም 17 የለጠፋነውን ጽሑፍ ተመልከቱ ) ይህንን ተቀብለው ተመልሰው ለ3 ዓመታት መስቀለኛ ቦታ ፈለጋ በኢትዮጵያ ተራሮች ዞሩ  ቅዱስ ዑራኤልም ይራዳቸው ነበር ፡፡ ከሥስት ዓመት ቦኃላም አምባሰል ደርሰው ቦታዋ  በመስቀል አምሳል የተቀረጸች መሆኗን አዩ፡፡ መግቢያው ቦታ እጅግ አስቸጋሪ ስለነበር አረፈው በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ዑራኤል ተገልፆ ይህች ደብረ ከዛሬ ጀምሮ ደብረ ከርቤ ትባላለች ፡፡ደብረ ነጐድጓድ ትባለ የነበረውም የካህናትና የነገሥታት መኖርያ ስለሆነች ነው ፡፡ሥላሴን የሚክዱ ሊኖሩባት አይችሉም ፡፡ ወደ ውስጥ ስትገባ ሁለት አብያተ ቤ.ክ ታገኛለህ አንዲቱ #በእግዚአብሔር አብ ስም  የተሠራች ናት፡፡ አንዲቱ ደግሞ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸች ናት፡፡
    እመቤታቸንም ተገልጻለት #በኢትዮጵያ በተሰደድኩበት ጊዜ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ርስት ትሁንሽ ብሎ ስምሽ እስከ ዕለተ ምጽአት ሲመሰገን ይኑርባት ብሎ ሰጥቶኛል እና ሄድ  ብላ ቦታዋን #ጠቆመችው፡፡
    በ1446 ዓ.ም መስከረም 21 ወደ ተራረው ገብተው አይተው ተደሰቱ በታዘዙትም መሠረት ቅዱስ መስቀሉን በእግዚአብሔር ስም በተሰራው መቅድስ #አስቀመጠው፡፡
  መስከረም 21 ቀንም መስቀሉ የተቀመጠበት የእግዚአብሔር አብ ቤ.ክ ቅዳሴ ቤቱ ሆነ ፡፡ ጌታችን በዘባነ ኪሩቤል ላይ ሆኖ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር መጣ ፡፡ እጅግም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ለቦታዋም ታላቅ ክብርን ሰጣት ደብረ ታቦርም ትሁንልህ አለው ፡፡
፠፠፠ #ብዙኃን_ማርያም
፠2ኛ) ደግሞ ጉባኤ ኒቅያን ይመለከታል፤ ለ፲፰ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ካሉት ደቀ መዛሙርት መካከል አርዮስ፣ አኪላስና እለእስክንድሮስ የሚባሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ አርዮስ እውቀቱ  በመምህሩ የተመሠከረለት ሊቅ ነበር፡፡
ነገር ግን “እጅግ ጥበብ ያደርሳል ከሞት” እንዳለ ሰሎሞን የተጻፈውን ትቶ ባልተጻፈው ላይ ፍልስፍና ጀመረ፡፡ በምሳ. ፰÷፳፪ ላይ ያለውን ቃል በተሳሳተ መንገድ ፈታው፤ ነገር ግን ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ጠርቶ ቢመክረው ቢገስጸው እንቢ በማለት የክህደት ትምህርቱን ቢቀጥልበት ከሹመቱ አውርዶ አወገዘው፡፡ ተፈጻሜተ ሰማዕት ከደቀመዛሙርቱ መካከል አኪላስን ተክቶ ኅዳር ፲፱ ቀን በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አኪላስም የጓደኝነት ፍቅር አድልቶበት አርዮስን ከውግዘት ቢፈታው በመቅሠፍት ሞት ሞተ፡፡ በመንበሩም እለእስክንድሮስ ተተካ፡፡ በዚህ ጊዜ የአርዮስ የክህደት ትምህርት በሀገሪቱ ሞላ፡፡ ይህ ነገርም እየተባባሰ በመሔዱ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ ንጉስ ቈስጠንጢኖስም ይህን ሲሰማ ለአርዮስ ጥያቄ መልስ ይሠጥበት ዘንድ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ እንዲደረግ ሰኔ ፳፩ ቀን አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህንን አዋጅ የሰሙት ሊቃውንት ሁሉ መስከረም ፳፩ ቀን የእመቤታችን እለት ተሰባሰቡ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ “ለምን ቈስጠንጢኖስ መልዕክት ከላከበት ጊዜ በኋላ ወዲያውኑ ለምን አልመጡም? ለምን ዘገዩ?” የሚለው ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምክንያቱም፤
#አንደኛ መጓጓዣ ችግር ስለነበር፤
#ሁለተኛ ሁሉም ሊቃውንት አስተማሪዎች በመሆናቸው ለምዕመናኑ (ለተማሪዎቻው) ሌላ መምህር ማዘጋጀት ስለነበረባቸው፤
#ሦስተኛ ደግሞ በእድሜ የገፉ ስለነበሩ አንድም ሊቃውንቱ ሲያስተምሩ በአላውያን ነገሥታት ባላመኑ ሰዎች ግፍ ይድርስባቸው ስለነበር ነው፡፡ ለምሳሌ ቶማስ ዘመርዓስ በእነዚህ ሰዎች በግፍ እግሩና እጁ ተቆርጦ ስለነበር ለማስተማር በቅርጫት ይዘውት ነበር የሚጓዘው፡፡ ወደ ጕባኤውም ሲመጣ ደቀ መዛውርቱ ያመጡት #በቅርጫት ይዘውት ነበር ( ማብራርያ የጥቅምት 14 የለጠፍነውን እይ ) ፡፡
ከዚህ በኋላ 2,340 ሊቃውንት መስከረም ፳፩  ቀን ተሠባሰቡ፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን 318ቱ ሊቃውንት ‹‹ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ›› በማለት  በሃይማኖታቸው የጸኑ ነበሩ፡፡  ጉባኤውን ከመጀመራቸው በፊት አርባ (፵) ቀን ሱባኤ እስከ ኅዳር ዘጠኝ (፱) ቀን ይዘውና ጕባኤውን አድርገው በአንዲት ቀን ያንን ታላቅ መናፍቅ አርዮስን ድል ነሥተውታል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም የኃይማኖታችን መሠረት የሆነውን ጸሎተ ሃይማኖትን  አዘጋጅተዋል፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
2025/07/06 05:38:41
Back to Top
HTML Embed Code: