Telegram Web Link
"የአንድ ፈረስ ፈረስነቱ ምኑ ላይ ነው? በወርቅ ልጓም ማሸብረቁ፣ እጅግ ቅንጡ በኾነ ኮርቻው፣ ከሐር በተሠሩና በባለ ብዙ ኅብረ ቀለማት ባጌጠ ልብሱ፣ እጅግ በጣም በተጋጌጠ ቆቡ እንዲሁም በወርቅ ገመድ በተገመዱ ፀጉሮቹ ላይ ነውን? ወይስ እጅግ ፈጣንና ብርቱ በኾኑት እግሮቹ፣ ለመሮጥ በሚያመቸው በሰኮናው፣ ረጅም ጉዞና ውጊያም ለማድረግ ባለው ተነሣሽነቱ፣ በጦር ሜዳ ላይ በማይደነብር ባሕርይው፣ ሸሽቶ ማምለጥ ካለበትም ጋላቢውን ለማሸሽና ለማዳን ባለው ጉብዝናው ላይ ነው? አንድን ፈረስ መልካም ፈረስ የሚያስብሉት መጀመሪያ ላይ የጠቀስናቸው ነገሮች ሳይኾኑ በኹለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጥናቸው ነገሮች አይደሉምን? አህያና በቅሎስ አህያና በቅሎ የሚያስብላቸው ምናቸው ነው? ደስ እያላቸው ሽክምን የመሸከም ኃይላቸው፣ ይህን ተሸክመው በቀላሉ ጉዞዎችን ማድረጋቸው፣ ለዚህም እንደ ዓለት የጠነከረ ሰኮና ስላላቸው አይደለምን? እነዚህ እንስሳት ይህን ተግባር ለማከናወን ከአፍአ የሚያደርጉት ጌጣጌጥ አስተዋጽኦ ያደርጋልን? በጭራሽ!

የምናደንቀው ወይንስ የትኛዉን ወይን ነው? ብዙ ቅጠልና ቅርንጫፍ ያለውን ወይስ ፍሬ አፍርቶ ጎንበስ ያለውን? ከአንድ የወይራ ዛፍ የምንጠብቀውስ ምንድን ነው? ትልልቅ ቅርንጫፎችና ለማየት ደስ የሚያስኝ ቅጠል እንዲኖረው ነው ወይስ በቅርንጫፉ ኹሉ ላይ ፍሬ እንዲያፈራ?

መልካም! በሰው ልጆች ዘንድም እንዲህ እያደረግን እንመልከተው፡- አንድን ሰው ሰው የሚያስበለው ምን እንደ ኾነና ይህንንም ምን እንደሚጎዳውና እንደሚያጠፋው እንየው፡፡ እናስ ሰውን ሰው የሚያስብለው ምኑ ነው? ድኽነት የሚያስፈራው ሀብቱ አይደለም፤ በሽታ የሚጎዳው ጤንነቱ አይደለም፤ ተቃውሞ ሊነሣበት የሚችለው የሕዝብ ውዳሴ አይደለም፤ ከፊት ለፊቱ ሞት በሚጠብቀው ሕይወተ ሥጋው አይደለም፤ ባርነትን ሊያስቀሩበት በማይቻለው ነጻነቱም አይደለም፤ እውነተኛ ዶክትሪንና የቅድስና ሕይወትን በጥንቃቄ ይዞ መገኘቱ ነው እንጂ።

ተመልከቱ! አንድ ሰው ራሱ እውነተኛ ዶክትሪንና የቅድስና ሕይወትን አስፈላጊ በኾነ ጥንቃቄ እስከያዘው ድረስ (ሌላ ሰውስ ይቅርና) ዲያብሎስም ቢኾን ሊወስድበት አይችልም። እጅግ ተንኰሎኛውና ጨካኝ የኾነው ጋኔንም ይህን ጠንቅቆ ያውቃል። የኢዮብን ሀብትና ንብረቱን ያጠፋበት ስለዚሁ ዋና ዓላማ ነበር።

ዲያብሎስ ይህን ያደረገው ኢዮብን ድኻ ለማድረግ አስቦ አልነበረም፤ ኢዮብ በእዚአብሔር ላይ ነቀፋን እንዲናገር እንጂ። ሰውነቱን በቁስል የመታው ሥጋው እንዲደክም ፈልጎ አልነበረም፤ የነፍሱን በጎነት ሊያሳጣው ወድዶ እንጂ፡፡ ኾኖም በአንድ ቅጽበት ያለውን ኹሉ ቢያሳጣውም፣ በእኛ እይታ እጅግ ክፉ መስሎ የሚታየን ከባለጸግነቱ አውርዶ እጅግ ድኻ ቢያደርገውም፣ በብዙ ልጆች ተከብቦ ይኖር የነበረውን ልጅ አልባ ቢያደርገውም፣ በአደባባይ ላይ ሰውን ከሚገርፉ ጨካኞች በላይ ከፍቶ መላ ሰውነቱን ቢገርፈውም (ምክንያቱም የቆስለ ሰውነትን በትላትል መበላት የሚገርፉትን ሰው በጥፍር ከመቧጠጥ በላይ ይፀናልና)፣ እጅግ ክፉ ተግሣጽን በገዛ ጓደኞቹ ቢያመጣበትም (ምክንያቱም ኢዮብን ለመጠየቅ መጥተው ከነበሩ ጓደኞቹ አንዱ፡- “እንደ ኃጢአቶችህ መጠን አልተቀጣህም" የሚሉና ሌሎች የነቀፋ ቃላትን ተናግሮታልና)፣ ከከተማውና ከገዛ ቤቱ አውጥቶ ወደ ሌላ ከተማ እንዲወጣ ብቻ ሳይኾን እዚያ ከሔደ በኋላም እጅግ በቆሸሽ ስፍራ እንዲኖር ቢያደርገውም ግን ከዚህ ኹሉ በኋላ እርሱ (ዲያብሎስ) ራሱ ባዘጋጀው መንገድ የበዛ ክብርን አመጣለት እንጂ ምንም ጉዳትን አላደረሰበትም። እጅግ ብዙ ነገሮችን ቢወስድበትም የምግባር ሀብቱን ይበልጥ ጨመረለት እንጂ ካለው ነገር አንዳችስ እንኳን አልወሰደበትም፡ ምክንያቱም ከእነዚህ ነገሮች በኋላ አስቀድሞ ከነበረው ነገር በላይ አግኝቷል፡፡

እንግዲህ ኢዮብ እነዚህን የሚያኽሉ መከራዎችን ከሰው ሳይኾን ከሰዎች ኹሉ እጅግ ከሚከፋው ከዲያብሎስ እንኳን ምንም ጉዳት ካልደረሰበት፣ እነ እገሌ ይህንና ያንን የመሰለ ጉዳት አደረሱብኝ የሚሉት ሰዎች ምን ዓይነት ምክንያትን ነው የሚያቀርቡት? እጅግ ታላላቅ ተንኰሎችን የተሞላ ዲያብሎስ አለ የሚለውን መንገድ በመጠቀም ከተንቀሳቀሰና ጦሩን ኹሉ ካራገፈ፣ ለዚህ አንድ ሰው ብቻ ይህን ኹሉ ክፉ ነገር በላዩ ላይ ከጨመረበት፣ hዚህ በላይ እጅግ ከፍቶም የዚህን ጻድቅ ሰው ቤተሰብ ኹሉ ቢገድልበትም አንዲት ጉዳትስ እንኳን ማድረስ ካልተቻለው፣ ይልቁንም አስቀድሜ እንደተናገርኩት ከጠቀመው፣ ሰዎች'ማ እነርሱ ራሳቸው ራሳቸውን ካልጎዱ በስተቀር እነ እገሌ እንዲህና እንዲህ አድርገው ጎዱን ብለው እንዴት ወቀሳን ማቅረብ ይቻላቸዋል?"
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ክርስቲያን ሆይ ይህን ልብ በል!!

ወገኔ ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የእግዚአብሔር ወዳጆች ለተባሉት ወንድም/እኅት/፣ ከሐዋርያትና ከሰማዕታት ጋር ከበዛው ጸጋቸው ተካፋይ፣ ከእርሱም ምስክሮች ጋር አንድ ማዕድ የምትካፈል፣ የቅዱሳን ርስት ወራሽና ቅን በሆነው ፍርዱ ደስ ይልህ ዘንድ ከነቢያት የፍርድ ወንበር ላይ የተቀመጥክ፣ ከቅዱሳን መላእክት ጋር በምስጋና የምትሳተፍ፣ ከሱራፌልም ጋር የምትነጋገር፣ ከኪሩቤል ጋር በሰማያዊ ዙፋን ላይ የተቀመጥክ፣ ከክርስቶስ የጸጋ ስጦታ ተካፋይ የሆንክ፣ የብቸኛ ልጁ ሰርግ ታዳሚ ትሆን ዘንድ የተጠራህ የሰማያውያን ሠራዊተ መላእክት ወዳጅ፣ የሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም ዜግነት ያለህ ነህ፡፡ አእምሮህ ውስጥ እነዚህ በክርስቶስ ለአንተ የተሰጡት የእግዚአብሔር ቸርነቶች ከተቀመጡ የጨለማው ዓለም ገዢ አገልጋዮች የሆኑ አንተን ሊያሰነካክሉህ አይችሉም፡፡ በንስሐ ጽና፡፡ ሕሊናን ከሚያቆሽሹ ከንቱ አስተሳሰቦች ራስህን ንጹሕ አድርግ፡፡ ከእነዚህ ፈጽመህ ራቅ ከንቱ በሆኑ አስተሳሰቦችም አትሸበር፡፡”
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!'

መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም 'ለሰው ፊት የማያዳላ' እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም። (ሐዋ 10፥34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡

'የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ' ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው።
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
እየጾምኩ ነው የሚል ሰው …

ተወዳጆች ሆይ! የምታደምጡ ብቻ አትኹኑ፤ ያስተማርኳችሁን ትምህርት ለሌሎችም በማስተላለፍ መምህራን ትኾኑ ዘንድ - ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አንዱ ሌላውን ያንጸው” (1ኛ ተሰ.5፥11)፤ ዳግመኛም “በፍርሐትና በመንቀጥቀጥም የራሳችኁን መዳን ፈጽሙ” ብሎ እንደ ተናገረው በስሕተት ጐዳና ያሉትን ታድኑ ዘንድ መረባችሁን ጣሉ ብዬ እማፀናችኋለሁ (ፊልጵ.2፥12)፡፡ ይህን ስታደርጉ ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትሰፋለች፤ እኛም ይህን ዐይተን እጅግ ደስ እንሰኝባችኋለን፡፡ እናንተም ለወንድሞቻችሁ፣ ለእኅቶቻችሁ ባሳያችሁት ፍቅር በሰማያት ዘንድ ታላቅ ማዕረግና ክብር ታገኛላችሁ፡፡ እንደምታውቁት የእግዚአብሔር ፈቃድ እያንዳንዱ ክርስቲያን ስለ ራሱ መዳን ብቻ እንዲያስብ አይደለም፤ ወንድሙንም እንዲያንጽ ነው እንጂ፡፡ ሲያንጸውም በቃል ብቻ አይደለም፤ በተግባርም ጭምር እንጂ፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃዱ እያንዳንዳችን በአኗኗራችን ክርስቶስን መስለን ታምነን እንድንኖርና ፍጥረት ኹሉ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ ይኸውም ሰዎች ከምንናገረው በላይ የምንኖረውን ስለሚያምኑና ስለሚማርካቸው ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ በተዋቡ ቃላት ስለ ይቅርታ ብንናገር ነገር ግን በሕይወታችን እጅግ ቂመኞችና ይቅርታን የሚቀበል ልብ የሌለን ከኾነ ቃላችንና ሕይወታችን ስላልተስማማላቸው ሰዎች የምንለውን ነገር አያምኑንም፡፡ የምንናገረውንና የምናስተምረውን የምንኖረው ከኾነ ግን ያምኑናል፡፡ እውነቱን ለመቀበልም አይቸገሩም፡፡ በቃል መነገሩ፣ በልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ ያለውን ክርስቲያን እንዲህ ሲል አመስግኖታል፡- “የሚያደርግም የሚያስተምርም እርሱ ንዑድ ክቡር ነው” (ማቴ.5፥19)፡፡ እንግዲህ ጌታችን ሲያስተምር በተግባር የሚሰጠውን ትምህርት በቃል ከሚሰጠው ትምህርት ይልቅ እንዳስቀደመው ታስተውላላችሁን? አያችሁ! ከተግባራችን በኋላ ቃላችን ባይከተል እንኳን ሰዎችን ወደ እውነት (ክርስቶስ) ለማምጣት በቂ ነው፡፡

ስለዚህ በቃላችን ከመናገር በላይ በተግባር ክርስቲያኖች መኾናችንን እናሳያቸው፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ግን ብፁዕ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ይወቅሰናል፡- “አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን?” (ሮሜ.2፥21)፡፡ አንድ ሰው መንፈሳዊ ሕይወቱ የተስተካከለ መኾን እንደሚገባው ለመምከር የምናስብ ከኾነ እኛው ቀድመን የራሳችንን ሕይወት በተግባር ልንስተካከል ይገባናል፡፡ ይህን የምናደርግ ከኾነ የምንሰጠው ምክር ተአማኒነት አለው፡፡ የሌሎች ሰዎች ነፍስ መዳን የሚያስጨንቀን ከኾነ ከምንም በፊት እኛው ራሳችን ስለ ራሳችን መዳን እንጨነቅ፡፡ ሌሎች ሰዎች ራሳቸውን መግዛት እንዲችሉ የምንሻ ከኾነ ከማንም በፊት እኛው ራሳችን ያንን አድርገን እናሳያቸው፡፡

ትክክለኛ ጾም ማለትም ይኸው ነው፡፡ ለተወሰነ ሰዓት ከምግበ ሥጋ የመከልከላችን ዓላማም ራሳችንን መግዛት እንድንችል ነው፡፡

ስለዚህ እየጾምኩ ነው የሚል ሰው ካለ ከምንም በፊት፡- ትዕግሥተኛ፣ ልበ ትሑትና የዋህ፣ እግዚአብሔርን የሚፈራ ልቡና ያለው፣ የፍትወታትን ጅረት ከኹለንተናው የሚያስወግድ፣ ዘወትር በልቡናው ዕለተ ምጽአትን የሚያስብ፣ በእግዚአብሔር የፍርድ ዙፋን ፊት እንደሚቆም የማይረሳ፣ በፍቅረ ንዋይ ወጥመድ ተይዞ ምጽዋትን የማይጠላ፣ ወንድሙን ከልቡ የሚወድ ይኹን፡፡ እውነተኛ ጾም ማለት ይኼ ነውና፡፡

"ሰው ራሱን ቢያሳዝን፣ አንገቱንም እንደ ቀለበት ቢያቀጥን፣ ማቅ ለብሶ በአመድ ላይ ቢተኛም ይህ ጾም እግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠ አይደለም፡፡” “ታዲያ እግዚአብሔር የመረጠው ጾም እንዴት ያለ ነው?” ትሉኝ እንደኾነም ነቢዩ ኢሳይያስ የእግዚአብሔር አፈ ንጉሥ ኾኖ እንዲህ ሲል ይመልስልናል “የበደልን እስራት ፍታ፤ ለተራበው እንጀራህን አጥግበው፤ ድኾችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፡፡” እንዲህ ስታደርግ፡- “ያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፡፡ ፈውስህም ፈጥኖ ይወጣል”  (ኢሳ.58፥5-8)፡፡

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
#የመከራ_ዓለም

እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ውስጥ ይህ ዓለም ተጠቃሽ ነው። አንዳንዶች ይህን ዓለም እንደ ምድራዊ ገነት ሲቆጥሩት ሌላዎቹ ደግሞ ከመከራቸው ብዛት የተነሳ እንደ ሲኦል ይቆጥሩታል።

ብዙዎቻችን በዚህች አስጨናቂ ዓለም ውስጥ ስንኖር በሐዘን ፣ በመከራ ፣ በረሀብ ፣ በችግር ፣ በጦርነት ውስጥ እናልፍ ይሆናል ነገር ግን ዘለዓለም አብረናት አንቆይምና ልንጨነቅ አይገባም ሐዋርያውም  “እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን” /ፊል3፥20/ በማለት ይህች ዓለም የዘለዓለም መኖርያችን እንዳልሆነች አስረድቶናል።

ይህ ዓለም ለእኛ ለክርስቲያኖች ጥሩ ጎንም መጥፎ ጎንም አለው

#ጥሩ_ጎኑ ፦ በዚህ ዓላም ውስጥ ስንመላለስ ለክርስቶስ ያለን ፍቅር ምን ያክል እንደሆነ የምናሳይበትና እርሱን መውደዳችንን በተግባር የምናሳይበት ቦታ ነው ምክንያቱም ስለዚህ የዘመናችን ፍጻሜ ሳይደርስ በጊዜ ወደ እርሱ ልንመለስ ያስፈልጋል ዳዊት በመዝሙሩ “በሞት የሚያስብህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?” /መዝ 6፥5/ በማለት ተናግሯል።

ስለዚህ በዚህ ዓለም ሳለን ሞት ሳይገጥመን ያለንን ንጹ ፍቅር ለአምላካችን ለልዑል እግዚአብሔር ልናሳይ ይገባል። መውደዳችንንም የምናሳየው ትዕዛዙን በመጠበቅ ነው ምክንያቱም ጌታችን በራሱ አንደበት
“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ" /ዮሐ 14፥15/ ብሏልና ትዕዛዙን ጠብቀን መውደዳችንን መታዘዛችንን ልናሳይ ይገባል።

“ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤” /ኢሳ 48፥18/

#መጥፎ_ጎኑ ፦ በትዕዛዙ ተመርተን ወደ በጎ ህሊና እንድንኋዝና አምላካችን እግዚአብሔርን እንድናሳዝና ምክንያት እና እንቅፋት የሚሆኑብን ብዙ መከራዎችና ፈተናዎች ያሉበት ቦታ በመሆኑ እንደ መጥፎነቱ ይጠቀሳል።

ነገር ግን እኛ ክርስቲያኖች ነንና መከራ መኖሩ ሊያስፈራን ፣ ሊያስጨንቀንና ሊያስደነግጠን  አይገባም ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዓለም ስንኖር መከራ ፈተና ቢኖርም  እርሱ እንዳሸነፈው ነግሮናል “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።” / ዮሐ 16፥33/ እኛም ህይንን አውቀን “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።” /ፊል 4፥13/ ብለን ፈተናውን በድል ልንወጣ ይገባል።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ወዳጄ ሆይ ከመብል ሽሽ፤ ከመጠጥም ራቅ፡፡ ጥጋብ ስንፍናን ትወልዳለችና፡፡ ጾምን ጠብቅ። በጾም ኃጢአት ይሠረያልና፡፡ እንዳይጠግብ፣ የሚጋልበውንም እንዳይጥለው ፈረስን እንደሚለጕሙት አንተም እንዲሁም ሥጋህ በፍትወት ነፍስህም በኃጢአት እንዳይወድቅ አፍህን ከመብልና ከመጠጥ ለጕም፡፡ ጌታችን እንበላና እንጠጣ ዘንድ አላዘዘንምና፡፡ ነገር ግን ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጹሙ ጸልዩ አለን እንጂ፡፡

የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፡፡ ስለ መብል በወጥመድ ውስጥ ይወድቃሉና፡፡ አጥማጆችም በሚያጠምዱበት ጊዜ ወጥመዱን በመብል ይሠውሩታልና፡፡ እንዲሁም ሰይጣን ጣፋጩን ተስፋ አስደርጎ መራራውን ይሰጣል፡፡ ዳግመኛም ብዙውን ተስፋ አስደርጎ ትንሽን ይሰጣል፡፡ አዳምን አምላክ እንደሚሆን ተስፋ እንዲያደርግ አደረገው፡፡ ነገር ግን ከገነት ዕራቍቱን አስወጣው፡፡

በጌታውም ዘንድ የተናቀ አደረገው፡፡ በዚህም መርገምን ወረሰ፡፡ በእርሱ ምክንያትም ምድር ተረገመች፡፡ ሞትም በሰው ላይ ሁሉ ሠለጠነ። የሚበር ወፍ ወደ ምድር ካልተመለከተ ወደ ወጥመድ አይወርድም፡፡ እንዲሁም ለሚጾም ሰው ልቡ በሰማይ ያለውን ያስብ ዘንድ ሥጋው በኃጢአት እንዳይወድቅ ለሰውነቱ ምኞቷን ይከለክላት ዘንድ ይገባል፡፡

ጾም የጸናች ናት፡፡ ትሕትናም የንስሓ ራስ ናት፡፡ በጾም ኤልያስ ከመላእክት ጋር ተቆጥሯልና፡፡ ኤልሳዕም የመምህሩን የኤልያስን መንገድ ተከተለ፡፡ ዕጥፍ ድርብ በረከቱንም አገኘ፡፡

ወንድሞቼ ሆይ በአጋንንት ላይ በሥጋ ድል ማድረግን እናገኝ ዘንድ በጾምና በበጎ ሥራ ሁሉ የመምህሮቻችንን መንገድ እንከተል፡፡ ንጹሕና የተመረጠ ጾምን እግዚአብሔር ይወዳል፡፡ አመፃ ስንፍና ናት፡፡ እግዚአብሔር አማፅያንን ፈጽሞ ይጠላቸዋል፡፡ በአፉ እየጾመ ወንድሙን ለሚገድል ለእርሱ ወዮለት፡፡ በአፉ ጾምን ለሚያውጅ በአንደበቱ ደግሞ አመፃን ለሚናገር ለእርሱ ወዮለት፡፡

ወንድሜ ሆይ አፍህ ከጾመ ልብህም እንዲሁ ይጾም ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ እነሆ ዐይንኖችህ ክፉን ከመመልከት ይጹሙ፡፡ እጆችህና እግሮችህም ከክፉ ሁሉ ይጹሙ፡፡ የጠላት ወጥመዱ ብዙ ነውና፡፡ በንጉሥ ፊት ተጋዳይ ወታደርን ልትሆን ብትወድ የጦር ዕቃን ትይዝ ዘንድ ተገቢ ነው፡፡ እንዲሁም ከሰይጣን ወጥመድ መዳን የሚወድ ሰው የክርስቶስን ትዕዛዙን ይጠብቅ፡፡ ከገሃነም እሳት ትድን ዘንድ ከትዕቢት ራቅ፡፡ መንግሥተ ሰማያትንም ትወርስ ዘንድ ትሕትናን ፈልግ፡፡

ወዳጄ ሆይ እኔስ ከመብልና ከመጠጥ ትሸሽ ዘንድ ጾምንም በፍጹም ልብህ ትከተላት ዘንድ እፈልጋለሁ፡፡ ትሑታንን ውደዳቸው ከትዕቢተኞችም ራቅ፤ ከጥላቻ ፈቀቅ በል፤ ሰላምንም ፈልጋት፡፡ የክርስቶስን ትዕዛዝ ትፈጽምም ዘንድ በፍቅር ሩጥ፡፡ በአንተ ላይ የኃጢአት ፍሬ እንዳይታይም ከልብህ ቂምንና በቀልን አስወግድ፡፡ ክፉ ሕሊና በመጣብህ ጊዜ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በምታስፈራ የፍርድ ዐደባባይ የምትቆምባትን የፍርድ ቀን አስባት፡፡
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
#አባታችን_ሆይ_እንደፈቃድህ_ይሁን

ብዙ ሰው "ያሰብኩት ሁሉ ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም" እያለ ያጉረመርማል፤ ያም ብቻ አይደለም "እግዚአብሔርማ እኔን ሳይተወኝ አልቀረም!" እያለ ፈጣሪውን የሚያማርርም አለ። "እርሱ ይሰጠኛል" ሳይሆን "እኔ አገኘዋለሁ" ብሎ ይጀምርና ሳይሆን ሲቀር በእጁ ላይ የነበረውን ነገር እንደነጠቀው ያህል አምላኩ ላይ ያለቅሳል።

ወዳጄ መጀመሪያ ስታቅድ ያላስታወስከውን አምላክ ያቀድከው ሲፈርስ ስሙን እየጠራህ ስለምን ትወቅሰዋለህ? በሕይወትህ መቼ ቦታ ሰጠኸውና? እንደ ፈቃዴ ካልሆነ አልህ እንጂ መቼ "እንደ ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ጸለይክና? ባላማከርከው ነገር ለምን ተከሳሽ ታደርገዋለህ?

ምናልባት በተለያዩ ጉዳዬች በሥራ ፣ በትምህርት ፣ በህመም ምክንያት በተቻኮልክበትና ጊዜ ባጣህበት ቀን እንዲሁ በግዴለሽነት ስሙን ጠርተህ እንደ ሆነም ራስህን መርምር? በትክክል ጸልየህና በመንገድህ ሁሉ ይመራህ ዘንድ ፈቅደህ ከጀመርህ ግን ግድ የለም እረኛህን እመነው። አንተ እንደ ሎጥ ከመረጥኸው እና ለጊዜው የገነት አምሳል ሆኖ ከሚታይህ ነገር ግን እግዚአብሔር ከማይከብርበት ከለምለሙ ሰዶምና ገሞራ ይልቅ፣ አሁን ብዙም ለአይን የማይስበው በኋላ ግን ወተትና ማር የሚያፈሰው ለልጅ ልጆችህም ርስት የሚሆነው እግዚአብሔር የሚሰጥህ ከነአን ይሻልሃል። ስለዚህ እንደ ፈቃድህ ይሁን በለው።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ለተቸገሩ ሰዎች መስጠት ማለት ስጦታችንን በሌላ በማንም ሳይኾን በራሱ በእግዚአብሔር እጅ ማስቀመጥ ነው፡፡ እንዲህም ስለ ኾነ የሰጠነው እንደሚመለስልን ብቻ ሳይኾን መቶ ዕጥፍ ኾኖ እንደሚሰጠን የታወቀ የተረዳ ነው፡፡ ላሳየነው ጥቂት ቸርነት የሚደረግልን ቸርነትም ታላቅ ነው፡፡

እግዚአብሔር የሰጠነውን አብዝቶ የሚመልስልንስ ለምንድን ነው? የምንሰጠው ስጦታ ጥንቱንም የሰጠን እርሱ እንደ ኾነ እየመሰከርን ስለ ኾነ ነው፡፡ በመኾኑም ወደንና ፈቅደን ይህን በተግባር ስንመሰክር፥ በተቀበለን እጁ የሰጠነውን ብቻ ሳይኾን ከሰጠነውም ጋር አብሮ መንግሥተ ሰማያትን ይሰጠናል፤ አክሊል ሽልማትን ያቀዳጀናል፤ ስፍር ቊጥር የሌለው በጎ በጎ በረከትም ያድለናል፡፡

እስኪ ንገሩኝ! እግዚአብሔር እየጠየቀን ያለው ከባድ ነገር ነውን? በፍጹም! እየጠየቀን ያለው በቤታችን ውስጥ ያስቀመጥነውንና የማንጠቀምበትን ነገር ለሌሎች እንድንሰጠው ነው፡፡ ይህን እንድናደርግ የሚሻውም የክብር አክሊል እንዲያቀዳጀን ምክንያት ሲፈልግብን እንጂ ለእነዚህ ችግረኞች የሚያስፈልጋቸውን ነገር መስጠት ተስኖት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ይህን እንድናደርግ የሚፈልገው ቃል የገባልንን ርስቱንና መንግሥቱን እንዲያወርሰን እጅግ ስለሚቸኩል ነው፡፡

ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ! እማልዳችኋለሁ እማፀናችሁማለሁ! እግዚአብሔር ጥቂት ምክንያት አግኝቶብን ሊሰጠን የሚወደውን እንዳናጣ በቤታችን ያስቀመጥነውንና የማንጠቀምበትን ነገር [ልብስ፣ ጫማ፣ ወዘተ] አውጥተን ለተቸገሩት ሰዎች እንስጣቸው፡፡ እግዚአብሔርም ያደረግናትን ጥቂቷን ምጽዋት በወዲያኛው ዓለም ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አምላክ አይደለም፡፡ በዚህም ዓለም በመስጠታችን ምክንያት የሚያገኘንን ነገር መፍራት አይገባንም፡፡ ቃለ እግዚአብሔር፡- “ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ - በተነ፤ ለችግረኞችም ሰጠ” ካለ በኋላ፥ ጨምሮም፡- “ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም ዓለም - ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ይላልና (መዝ.111፥9)፡፡

ኦ ምጽዋት! እንደ ምን ትደንቅ? እንደ ምንስ ትረቅ? ሰው ባልንጀራውን አፍቅሮ ለጥቂት ጊዜ ጥቂት ነገርን ይሰጣል፡፡ ይህን በማድረጉ ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኘው ፍቅር ግን ለዘለዓም ዓለም ጸንቶ የሚኖር ነው፡፡

ተወዳጆች ሆይ! ዘወትር ምጽዋትን እንድታፈቅሯት የምለምናችሁ ለዚህ ነው፡፡ ኹልጊዜ ምጽዋትን እንድትወዷት የምማፀናችሁ ለተቸገሩ ሰዎች ጥቂት ቸርነትን አድርገን ከእግዚአብሔር ዘንድ መጠን ወሰን የሌለውን ቸርነት እንድንቀበል ነው፡፡ ደጋግሜ ለተቸገሩ ሰዎች ፍቅርን እናሳይ የምላችሁ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደር የሌለውን ፍቅር እንድንቀበል ነው፡፡

ስለዚህ ያለንን ለድኾች እናካፍል፡፡ ያን ጊዜም “በተኑ፤ ለችግረኞችም ሰጡ፡፡ ጽድቃቸውም ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ይባልልናል፡፡ እግዚአብሔር በክቡር ዳዊት አድሮ “ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ - በተነ፤ ለችግረኞችም ሰጠ” ብሎ ሲናገር መበተን ማለት ማጣት ማለት እንዳልኾነ እንድናውቅ እንድንረዳም ሽቶ ወድያውኑ፡- “ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም ዓለም - ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ብሎ የሚነግረን ለዚህ ነውና፡፡ “ያላቸውን ለተቸገሩ ሰዎች የሚያካፍሉ ሰዎች ጽድቃቸው የዘለዓለም ዓለም ነው፤ አይጠፋባቸውም፡፡ እነርሱ አላፊና ጠፊ ነገር ይሰጣሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚቀበሉት ግን መቼም ቢኾን መች የማያልፍ፣ መቼም ቢኾን መች የማይጠፋ፣ መቼም ቢኾን መች የማያረጅ ኾኖ ነው” ብሎ ሲነግረን ነውና!!
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ምጽዋት ሥርየተ ኃጢአትን ትሰጣለች፡፡ ሞትንም ቢኾን ታርቃለች፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም ቀጥዬ ግልጽ አደርግልሃለሁ፡፡

“መጽውቶ ከሞት የተረፈ ማን አለ?” ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ ወዳጄ ሆይ! ምጽዋት ሞትን እንድታርቅ ኃይል ጉልበት እንዳላት በእውን ከተደረገ ታሪክ ተነሥቼ እነግርሃለሁና የምነግርህን ነገር አትጠራጠር፡፡

ጣቢታ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፡፡ መልካም ሥራን የሞላባትና ምጽዋትን የምትወድ በዚህም ለራሷ መዝገብ የምታከማች ነበረች፡፡ ለመበለቶች ልብስንና የሚያስፈልጋቸውን ኹሉ ትሰጣቸው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ሞተች፡፡

አሁን ደግሞ እነዚያ እርሷ ስትረዳቸው የነበሩ መበለቶች በየትኛው ሰዓት ብድራታቸውን እንደሚከፍሉ ተመልከት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን መበለቶቹ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ኼዱ፡፡ ጣቢታ የሰጠቻቸውን ልብስንና ሌላውን ኹሉ አሳዩት፡፡ ከእነርሱ ጋር በሕይወተ ሥጋ ሳለች ምን ምን ታደርግላቸው እንደ ነበረች ነገሩት፡፡ እንደ እናት የምትኾንላቸውን እንደ አጡ አልቅሰው ነገሩት፡፡ ስለ እነርሱ እጅግ እንዲያዝንም አደረጉት፡፡ 

የተወደደ ጴጥሮስስ ምን አደረገ? “ኹሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮ ጸለየ፡፡ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ ‘ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ’ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች፡፡ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች፡፡ እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፡፡ ምእመናንንና መበለቶችንም ጠራ፡፡ ሕያውም ኾና በፊታቸው አቆማት”  (ሐዋ.9፥40-41)፡፡

የሐዋርያውን ኃይል ወይም በሐዋርያው አድሮ እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ አስተዋልህን? በወዲያኛው ዓለምስ ተወውና በዚህ ዓለምም ሳይቀር ጣቢታ ስለ መልካም ሥራዋ ምን እንደ ተቀበለች ተገነዘብን? እርሷ ለመበለቶች የሰጠችውንና መበለቶቹም ለእርሷ የሰጡትን አየህን? እርሷ ምግብና ልብስ ሰጠቻቸው፤ እነርሱ ግን ከሞት ወደ ሕይወት እንድትመጣ አደረጓት፡፡ ለመበለቶቹ ባሳየችው ቸርነት ቸሩ እግዚአብሔር ብድራቷን ከፈላት፡፡ 

እንግዲህ የምጽዋት የመድኃኒትነቷን ኃይል ተመለከትህን? እንግዲያውስ እኛም ይህን መድኃኒት ለራሳችን እናዘጋጅ፡፡ መድኃኒቱ ይህን ያህል ጽኑ መድኃኒት ቢኾንም ቅሉ እጅግ ርካሽ እንጂ ውድ አይደለምና ለራሳችን እንግዛ፡፡ ይህን መድኃኒት ለመግዛት ብዙ ወጪ አይጠይቅምና እንግዛ፡፡ መልካም ሥራ መልካም የሚባለው በሚሰጡት ገንዘብ መጠን ሳይኾን በሚሰጡት የእደ ልብ ስፋት መጠን ነውና እንግዛ፡፡ አንድ ሰው አንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ሰጥቶ እጅግ እንደ ሰጠ የሚቈጠርለትም እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን የሚሻው ወደንና ፈቅደን የምንሰጠው በጎ ፈቃዳችንን መኾኑን የሚያሳይ ነውና ይህን እንግዛ፡፡ መበለቶች፥ እንደ ጣቢታ ከሞተ ነፍስ ይታደጉን ዘንድ ይህን መድኃኒት ከእነርሱ እንግዛ፡፡

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
መንግስትህ ትምጣ!

  ክርስቶስ በመጀመሪያ ምጽአቱ ለኃጢአት ድርቀትን በረሃማነትን ከፈለው። የክርስቶስ ምጽአት የሌሊቱ ማለፍ ነው። እርሱ የሚመጣው የንጋት ኮከብ ሆኖ ነው። የንጋት ኮከብ ምንድን ነው? የንጋት ኮከብ ሌሊቱ  አልፎ ጨለማና ብርሃን ሲለያዩ የሚታይ ነው። መከራው ራሱ አልቆ አይቆምም የመከራው ድንበሩ የክርስቶስ መምጣት ነው። የመጀመሪያ የአዳም መከራ የቆመው በክርስቶስ መምጣት ነው። ክርስቶስ በመጀመሪያ ምጽአቱና ሞቱ ለሞት ሞትን ከፈለው። ሞት ለዘመናት ቆንጆ እየነጠቀ ንጉሥን ከዙፋኑ እያንከባለለ ወሰደ ለዘመናት ያለበርና መስኮት ሲንጎማለል ኖረ። ከትልልቅ አባቶች ፈላስፎች አንድስ እንኳ ሞትን ያሸነፈ የለም። የዚህ ዓለም ክቡራን በሁለት ፊደል ሕይወታቸው ተጠናቋል ሞተ በሚል። በሽታ መድኃኒትን ሞቴ ጥፋቴ መከራዬ ማለቂያዬ ብሎ ይጠራዋል። የክርስቶስ መምጣት ለዚህ ዓለም እንዲሁ ነው። እኛ ደግሞ የክርስቶስን መምጣት መድኃኒቴ ሕይወቴ እንለዋለው። ክርስቶስ በመጀመሪያ ምጽአቱ ሞትን ገደበ። በሁለተኛው ምጽአቱ መከራን ይገድበዋል። ክርስቶስ ካልመጣ አንዱ መከራ አልቆ መሬት ሳያስነካ ለቀጣዩ መከራ ያስረክበናል። እቺ ዓለም ቢሻላት እንጂ አትድንም። የክርስቶስ መምጣት የዓለም የእርጅናዋ ዘመን ነው። እርጅና አልጋ ላይ ይጥላል። ዓለም አርጅታ አልጋ ላይ ወድቃለች። ሰው ሲያረጅ በሽታ አልጋ ላይ ይጥለዋል።  ዓለም ታማለች በበሽታ ወድቃ አልጋ ላይ ነች። ዓለም አትታመንም የራሷን ሰው እንኳ ማስደሰት አትችልም።

ኧረ አንቺ ዓለም ኧረ አንቺ ዓለም
የጀመረሽ እንጂ የጨረሰሽ የለም

ተብሏል!

ዓለም  ያለ ክርስቶስ መንገዷ እሾክ ነው። ብትከተሏትም ሞት ነው ባልከተሏትም ክርስቶስን ባለመከተላችን የሞት ገበታ ያላት ብቸኛ አስቆ ገዳይ አስብተሸ አራጅ ነች። የክርስቶስ መምጣት የጥያቄው መልስ ነው። ክርስቶስ ሲመጣ ላለብን ጥያቄ መልስ ሊሰጥ አይደለም። ራሱ መልስ ነው። የዓለም መልሷ ጥያቄ ነው። ስልጣኑ ጭስ የማይታይበት ቃጠሎ ነው። አዎ ጌታ ይመጣል። ራሱ ባለቤቱ ነግሯናል ክርስቶስ ብናምነውም ባናምነው ይመጣል። የሚመጣው እመጣለሁ ስላለለ ነው። ይህ ቃል የንጉሥ እውነተኛ ቃል ነው። ያልነገረንን የሚነግሩን ነቢያት አይመጡም። የነገረንን  ግን ይመጣል። በመጨረሻም በልጁ ተናግሮናልና። እኛ በክርስቶስ ታውቀናል። የዘመን መልክ በክርስቶስ ተነግሮናል። የሚጠነቁል አያስፈልግም። በዚህ ዘመን የሚያስፈልገን እረኛ ነው። ስታስቀድስ ስትቆርብ አላይህም የሚል አባት የሚገስጽ አባት በፍቅር የሚፈልገን አባት ያስፈልገናል። ዛሬ ሃይማኖታዊ  ተውኔት አያስፈልገንም። ከዓለም ክርስቲያን ተለይቶ የኢትዮጵያ ክርስቲያን ብቻ ጋኔን አለብኝ ብሎ ያምናል። የሚጮህበት መድረክ ስላገኘ ይጮሃል። የክርስቶስ ማደሪያ የሆነ ምዕመንና ካህን እንዳይተማመን ራሱ ካህኑ ጋኔን አለብኝ ብሎ እንዲያምን እየተደረገ ነው ያለው። ገንዘባችንን ለእነዚህ እየሰጠን ለወንጌል ግን ዱሽ ነን።  ለወንጌል ፈዘናል ለዘራፊ ተመቻችተናል። እኛ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ ነን። ስለመጨረሻ ቀን ሚተረጉም እንጂ እኔ አውቅልሃለሁ የሚል ትምህርት አያስፈልግም። ከወረቀቱ ልንገርህ ወይስ በቀጥታ ከሰማይ ልንገርህ የሚል ቀልድ በጌታ ቃል እየተቀለደ ነው። በእውነት አርዮስም እንዲህ አላዋረደውም። በእውነት ዲያቢሎስም እንዲህ አላዋረደው። ዛሬ የእግዚአብሔርን ልጅ ላይ በስሙ እያፌዙ ነው። እግዚአብሔር የሚያናግረው በቃሉ ነው። ዛሬ ቃሉ ያነሰባችሁ ይቅር ይበላችሁ። ቃሉ ዘላለም የሚያኖር ቃል ነው። አይ አይበቃኝም ብለን ሌላ ቦታ ምንሄድ አለን ይቅር ይበለን።

ጸሎት
ጌታ ሆይ! በሰፈር ልጆች የተጠቃ ሕጻን አባትህ ይመጣል። ያጠቁህን የመቱህን ልክ ያስገባቸዋል ሲባል ምፈራ ከሆነ ምኑን ልጅ ሆንኩት?
የክርስቶስ መምጣት ክርሰቲያንን ሊይስደነግጥ አያስፈልግም። አቤቱ በቃልህ አበርታኝ ማራናታ ጌታ ሆይ ተሎ ና። መንግስትህ ትምጣ ብዬ ሊመጣ ነው ስንባል ምንፈራ ከሆነ ክርስቲያን አይደለሁምና ጽድቄን ይቅር በለው!

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
.....በየዕለቱ ምን ያህል ተስፋ አስቆራጭ ነገሮች ወደ እኛ ይመጣሉ? ትዕግሥትን ገንዘብ በማድረግ በአስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉን እየቻልን መከራዎች እንዳያጠቁን ለሚጠብቀን አምላካችን ምስጋናና ክብርን ለማቅረብ እንዴት ያለ ብርቱ ነፍስ ያስፈልገን ይሆን? ምን ያህልስ ያልተጠበቁ መከራዎች ሊነሱብን ይችሉ ይሆን? ጻድቁ ኢዮብ ብዛት ያላቸውና ከባድ ፈተናዎችን በተጋፈጠ ጊዜ ከአንደበቱ ምንም ዓይነት የስንፍና ንግግር ሳይወጣው ለአምላኩ ምስጋና ማቅረቡን እንዳላቋረጠ ሁሉ እኛም የሚመጣብንን ክፉ አሳብ በሙሉ መልሰን መዋጋት አለብን።

አንዳንድ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ሲሰናከሉ ወይም በሌሎች ስማቸው ሲጠፋ ወይም ከባድ በሆኑ በሽታዎች ሲያዙ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መንቀፍ ይጀምራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ለበሽታው ሕመም አሳልፈው ይስጡ እንጂ ከሚገኘው ጥቅም ወይም በረከት ራሳቸውን ያራቁ ናቸው፡፡

ሰው ሆይ! የመድኃኒትህን፣ የረዳትህንና የጠባቂህን ስም በከንቱ ስታጠፋ ምን እያደረግህ ነው? ወይስ ከታላቅ የገደል ጫፍ ላይ የመጨረሻ መውደቂያ ወደ ሆነው ጉድጓድ ራስህን እየወረወርክ መሆንህ አይታወቅህ ይሆንን? የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ብታጠፋ መከራህን ልትቀንስ አትችልም። ትችላለህን? ይልቁንም መከራህን በማባባስ ጭንቀትህን የበለጠ ከባድ ታደርጋለህ፡፡ ዲያብሎስም ለዚሁ ጉዳይ ብሎ የሚያዘጋጃቸው ብዛት ያላቸው መከራዎች አንተን ወደ ጉድጓዱ ይመሩሀል፡፡ እርሱ እግዚአብሔርን ማማረርህን እንደ ቀጠልህ ሲመለከት መከራዎቹን በመጨመር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያደርሳቸዋል። እንዲህ በማድረግም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንድትገለው ያደርግሃል፡፡ ነገር ግን በጽናት ተቋቁመህ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብህን ካላቋረጥክ የመከራው ብዛት እየከፋ ይሂድ እንጂ ከአንተ ጋር መዋጋቱ ጥቅም የሌለው መሆኑን ስለሚያውቅ አንተን መፈታተኑን ያቆማል፡፡ አንድ ውሻ በማዕዱ ፊት ለፊት ተቀምጦ በመመገብ ላይ ያለው ሰው ፍርፋሪ የሚሰጠው ከሆነ በጽናት ቁጭ ብሎ ይጠብቃል። ነገር ግን ምንም የሚበላ ነገር የማይወረውርለት መሆኑን ካወቀ መጠበቁ ዋጋ የሌለው መሆኑን ስለሚረዳ ከዚያ ቦታ ፈቀቅ ብሎ ይሄዳል፡፡ ልክ ውሻው የሚበላ ነገር ይወረወርልኛል ብሎ እንደሚጠብቀው ዲያብሎስም የእግዚአብሔርን ስም የሚያጠፋ ቃል ይወረወርልኛል ብሎ ይጠብቃል፡፡ ከወረወርክለት በድጋሚ ያጠቃሀል፡፡ ነገር ግን ምስጋና በማቅረብህ ከቀጠልህ በረሀብ አለንጋ ስለምትገርፈው ከጫንቃህ ላይ ትወረውረዋለህ፡፡

አንተ ግን በጭንቀት ስዋጥ ዝም ማለት አልችልም ብለሃል፡፡ እኔ ምንም ዓይነት ቃል እንዳይወጣህ አልከለክልህም። የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ከምታነሣ ይልቅ ምስጋናን አቅርብለት፡፡ ተስፋ ከመቁረጥም በእግዚአብሔር ታመን፡፡ ንስሓ በመግባት ድምፅህን ጮኽ አድርገህ በጸሎት ዕንባህን አንባ፡፡ አምላክህንም ከፍ ባለ ድምፅ አመስግን፡፡ እንዲህ ባለው መንገድ መከራዎችህን ታቀልላለህ፡፡ ምክንያቱም አንተ ለጌታህ ለእግዚአብሔር ምስጋና ስታቀርብ ተራዳኢነቱ በአጠገብህ ስለሚገኝ ዲያብሎስ ከአንተ ይሸሻል፡፡ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ብታነሣ ወይም ብታማርር ግን የእግዚአብሔርን እርዳታ ከአንተ ስለምታርቅ ዲያብሎስ በአንተ ላይ የበለጠ እንዲነሳሳ በማድረግ ራስህን የከፋ መከራ ውስጥ ትከታለህ፡፡ ምስጋና የምታቀርብ ከሆነም የዲያብሎስን ደባ ከአጠገብህ ስለምታጠፋ የጠባቂህ የእግዚአብሔርን እንክብካቤ ወደ አንተ ታቀርባለህ፡፡

እንዲያው ልማድ ሆኖበት ብዙ ጊዜ አንደበት ክፉ ቃላትን ማውጣት ይጀምራል፡፡ እንደዚህ ማድረግ በሚጀምርበት ሰዓት ያንን ክፉ ቃል ከመናገሩ በፊት መላስህን በጥርስህ ንከሰው፡፡ መላስህ አንዲት ጠብታ ውኃ አጥቶ ጥማቱን ማርካት ከሚሳነው ይልቅ አሁን በደም ቢታጠብ ይሻለዋል:: ልክ ባለጸጋው ሰው በነበልባሉ ሲቃጠል ምንም ማስታገሻ እንዳላገኘ ሁሉ ምላሳችን ማብቂያ የሌለውን ቅጣት ከምትቀበል ዛሬ ጊዜያዊ ሕመም ብትታመም ይሻላታል፡፡ እግዚአብሔር ጠላቶቻችሁን እንድትወዱ አዝዟችኋል፡፡ እናንተስ ከሚወዳችሁ ከእግዚአብሔር ትርቃላችሁን? «ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፣ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፣ ስለሚበድሏችሁም ጸልዩ፡፡» (ሉቃ 6፥27-28)። እናንተ ግን ክፉ ሲገጥማችሁ በረዳታችሁና በጠባቂያችሁ ላይ መጥፎ ልትናገሩ ትችላላችሁን? ከገጠማችሁ ፈተና ሊያወጣችሁ እንደማይችል አልተናገራችሁምን? እርሱ ግን ይህንን ጠባያችሁን እንድታሻሽሉ ፈቅዶላችኋል። በአንጻሩ እናንተ ወድቄያለሁ ጠፍቻለሁም ትሉታላችሁ፡፡ የጠፋችሁት ግን ከፈተናችሁ ክብደት ሳይሆን በራሳችሁ ስንፍና ነው፡፡

እስቲ ንገሩኝ! የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ማንሣት ይሻላል ወይስ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ? በእርግጥ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ማንሳት አድማጮችህ እንዲጠሉህና ወደ ተስፋ መቁረጥ እንዲገቡ ካደረጋቸው በኋላ በመጨረሻ ታላቅ ሥቃይን ያመጣባቸዋል፡፡ ምስጋናን ማቅረብ ግን ብዛት ያላቸው የጥበብ አክሊሎችን አግኝተህ በእያንዳንዱ ሰው እንድትደነቅ ያደርግሃል፡፡ ይህም በመጨረሻ ታላቅ ዋጋን ከእግዚአብሔር ዘንድ ያስገኝልሀል፡፡ ታዲያ እንዴት ቀላል፣ የሚረዳህንና ጣፋጭ የሆነውን ትተህ የሚጎዳህን የሚያሳምምህንና የማይረባህን ትከተላለህ?

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ለተቸገሩ ሰዎች መስጠት ማለት ስጦታችንን በሌላ በማንም ሳይኾን በራሱ በእግዚአብሔር እጅ ማስቀመጥ ነው፡፡ እንዲህም ስለ ኾነ የሰጠነው እንደሚመለስልን ብቻ ሳይኾን መቶ ዕጥፍ ኾኖ እንደሚሰጠን የታወቀ የተረዳ ነው፡፡ ላሳየነው ጥቂት ቸርነት የሚደረግልን ቸርነትም ታላቅ ነው፡፡

እግዚአብሔር የሰጠነውን አብዝቶ የሚመልስልንስ ለምንድን ነው? የምንሰጠው ስጦታ ጥንቱንም የሰጠን እርሱ እንደ ኾነ እየመሰከርን ስለ ኾነ ነው፡፡ በመኾኑም ወደንና ፈቅደን ይህን በተግባር ስንመሰክር፥ በተቀበለን እጁ የሰጠነውን ብቻ ሳይኾን ከሰጠነውም ጋር አብሮ መንግሥተ ሰማያትን ይሰጠናል፤ አክሊል ሽልማትን ያቀዳጀናል፤ ስፍር ቊጥር የሌለው በጎ በጎ በረከትም ያድለናል፡፡

እስኪ ንገሩኝ! እግዚአብሔር እየጠየቀን ያለው ከባድ ነገር ነውን? በፍጹም! እየጠየቀን ያለው በቤታችን ውስጥ ያስቀመጥነውንና የማንጠቀምበትን ነገር ለሌሎች እንድንሰጠው ነው፡፡ ይህን እንድናደርግ የሚሻውም የክብር አክሊል እንዲያቀዳጀን ምክንያት ሲፈልግብን እንጂ ለእነዚህ ችግረኞች የሚያስፈልጋቸውን ነገር መስጠት ተስኖት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ይህን እንድናደርግ የሚፈልገው ቃል የገባልንን ርስቱንና መንግሥቱን እንዲያወርሰን እጅግ ስለሚቸኩል ነው፡፡

ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ! እማልዳችኋለሁ እማፀናችሁማለሁ! እግዚአብሔር ጥቂት ምክንያት አግኝቶብን ሊሰጠን የሚወደውን እንዳናጣ በቤታችን ያስቀመጥነውንና የማንጠቀምበትን ነገር [ልብስ፣ ጫማ፣ ወዘተ] አውጥተን ለተቸገሩት ሰዎች እንስጣቸው፡፡ እግዚአብሔርም ያደረግናትን ጥቂቷን ምጽዋት በወዲያኛው ዓለም ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አምላክ አይደለም፡፡ በዚህም ዓለም በመስጠታችን ምክንያት የሚያገኘንን ነገር መፍራት አይገባንም፡፡ ቃለ እግዚአብሔር፡- “ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ - በተነ፤ ለችግረኞችም ሰጠ” ካለ በኋላ፥ ጨምሮም፡- “ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም ዓለም - ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ይላልና (መዝ.111፥9)፡፡

ኦ ምጽዋት! እንደ ምን ትደንቅ? እንደ ምንስ ትረቅ? ሰው ባልንጀራውን አፍቅሮ ለጥቂት ጊዜ ጥቂት ነገርን ይሰጣል፡፡ ይህን በማድረጉ ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኘው ፍቅር ግን ለዘለዓም ዓለም ጸንቶ የሚኖር ነው፡፡

ተወዳጆች ሆይ! ዘወትር ምጽዋትን እንድታፈቅሯት የምለምናችሁ ለዚህ ነው፡፡ ኹልጊዜ ምጽዋትን እንድትወዷት የምማፀናችሁ ለተቸገሩ ሰዎች ጥቂት ቸርነትን አድርገን ከእግዚአብሔር ዘንድ መጠን ወሰን የሌለውን ቸርነት እንድንቀበል ነው፡፡ ደጋግሜ ለተቸገሩ ሰዎች ፍቅርን እናሳይ የምላችሁ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደር የሌለውን ፍቅር እንድንቀበል ነው፡፡

ስለዚህ ያለንን ለድኾች እናካፍል፡፡ ያን ጊዜም “በተኑ፤ ለችግረኞችም ሰጡ፡፡ ጽድቃቸውም ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ይባልልናል፡፡ እግዚአብሔር በክቡር ዳዊት አድሮ “ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ - በተነ፤ ለችግረኞችም ሰጠ” ብሎ ሲናገር መበተን ማለት ማጣት ማለት እንዳልኾነ እንድናውቅ እንድንረዳም ሽቶ ወድያውኑ፡- “ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም ዓለም - ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ብሎ የሚነግረን ለዚህ ነውና፡፡ “ያላቸውን ለተቸገሩ ሰዎች የሚያካፍሉ ሰዎች ጽድቃቸው የዘለዓለም ዓለም ነው፤ አይጠፋባቸውም፡፡ እነርሱ አላፊና ጠፊ ነገር ይሰጣሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚቀበሉት ግን መቼም ቢኾን መች የማያልፍ፣ መቼም ቢኾን መች የማይጠፋ፣ መቼም ቢኾን መች የማያረጅ ኾኖ ነው” ብሎ ሲነግረን ነውና!!

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
''እውነተኛ ጿሚ ራሱን ከክፉ ምግባራት የከለከለ፤ ከንቱ የሆኑ ንግግሮችን ከመናገር የተቆጠበ፣ ሐሰትን የማይናገር፣ ሐሜተኛ ያልሆነ፣ በማንም ላይ የማይፈርድ፣ ሽንገላን የማይወድና እኒህንም ከመሰሉ ነገሮች ራሱን የተጠበቀ ፣የማይቆጣ፣ የማይበሳጭ ፣ተንኮለኛ ያልሆነ፣ ቂመኛ ያልሆነና፣ እነዚህን ከመሳሰሉ ክፋቶች ሁሉ የራቀ ሰው ነው፡፡

ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ ከስድብ፣ ከውሸት ፣ከማታለል፣ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡''
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
“አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል" / ኤፌ 5÷14/

ወዳጆቼ ብዙዎቻችን ስልክ ስናወራ ሳንቲሜ ቆጠረ እንጂ ዕድሜዬ ቆጠረ አንልም ከዕድሜው ይልቅ ለሳንቲም ዋጋ እንሰጣለን። በስልክ ከወዳጆቻችን ጋር የምናወራውን ያክል እንኳ ከፈጣሪያችን ጋር ማውራት ሸክም ሆኖብናል።

በመንፈሳዊ ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት በፕሮግራም ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው መኋዝ ያለብን።  ነገ እጀምራለው ነገ ይህን አደርጋለው እያልን ቆጠሮ ብንሰጥ ትርፉ መሰላቸት ነው ማድረግ ያለብንን ዛሬ አሁኑን እንጀምረው። የእግዚአብሔር ፈቃዱም አሁኑኑ እንድንድን ነው።

ነቢያት ስላልመጣው ዘመን ያውቁ ነበር ፤ እኛ ግን የምንኖርበት ዘመን ምንነት እንኳ ተሰውሮብናል። ሐዋርያት ሄደው ዓለምን ዞረው ይሰብኩ ነበር ፣ እኛ ግን በተመቻቸ ቦታ መጥታችሁ ተሰበኩ እንላለን። ሰማዕታት ለክርስቶስ ፍቅር ሞቱ ፣ እኛ ግን ለጥቅማችን ፣ ለምኞታችን ፣ ለኃጢያታችን እንሞታለን። ጻድቃን የዚህን ዓለምን ጣዕም ንቀው መነኑ ፣ እኛ ግን ዓለም መራራ ሆናብንም እንኳ ደግመን ደጋግመን እንፈልጋታለን።

ቅዱሳን አባቶቻችን ከሕግ አልፈው በትሩፋት ኖሩ ፣ እኛ ልጆቻቸው ግን የታዘዝነውን እንኳ መፈጸም ተስኖናል። ደናግል መነኮሳት የክርስቶስ ሙሽሮች ሆኑ ፣ እኛ ግን በአንድ ሃይማኖታችን ጸንተን ክርስቶስን መከተል (ማምለክ) አቅቶናል። ሊቃውንት አባቶቻችን አህያ እንኳ የማትሸከመውን መጽሐፍ በቃላቸው አጠኑ ፣ እኛ ግን አንድ ጥቅስ ለማጥናት ያዙኝ ልቀቁኝ እንላለን።

ጌታ ሆይ እባክህን እኛን እንቅልፋሞቹን ከእንቅፋችን አንቃን !


ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ከጠላት ፈተናዎች ተጠንቀቅ!

ዲያቢሎስ ቀስቱን ሲወረውርብንና በውጊያው ሲያውከን ይህ በእኛ ላይ ብቻ የተደረገ ቁጣና ጠላትነት አይደለም፤ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔርም ጠላት ነውና በእኛ ላይ ሚደርሰው መከራ በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ተቃውሞ ነው። ዲያቢሎስ እግዚአብሔርን ማጥቃት ባለመቻሉ ፍጥረታቱን በማታለልና ከእርሱ ከእርሱ ጋር ወደ ዘላለማዊ ቅጣት እንዲገቡ በማድረግ ሊበቀለው ይጥራል፡፡

የተወደድኸው ሆይ! ይህንን ነገር አስተውል! ዲያቢሎስን ስትቃወመውና ስትዋጋው ክፉን ነገር ከእናንተ እያራቅህ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየተዋጋህ ነው፡፡ ስለዚህም የክፉውን ዲያቢሎስ ዲያቢሎስ ማማለያና መደለያ በመቀበል እግዚአብሔርን ከማሳዘን ይልቅ ፈተናውን በጽናት ስትታገል በውጊያው ላይ ብትሞት ይሻልሃል፡፡

ለአፍታም ቢሆን ብቻህ እየተዋጋ እንዳለህ አድርገህ አታስብ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላትህ ላይ ድል መንሣትን ይሰጥሃል፡፡ "አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል ድሆችን አትርሳ፡፡ ኃጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቆጣው? በልቡ:: አይመራመረኝም ይላልና፡፡" (መዝ ፲ ፥ ፲፪ -፲፫) ጥሩርና ጋሻ ያዝ፤ እኔንም ለመርዳት ተነሥ፡፡ ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት።›› (መዝ. ፴፭፥፪-፫)

"አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ፡፡ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ  አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።" (ኢሳ. ፫፥፩-፪)

በነፍሳችን ላይ ደካማነትን እስካላየ ድረስ ሰይጣን አያጠቃንም፡፡ ጎበዝ አዳኝ ወፎችን ለማደን እንደሚያደርገው ዲያቢሎስም ወጥመዱን ለማስገባት ሁልጊዜ ከእኛ ላይ ቀዳዳን ይፈልጋል፡፡ ብዙ ጊዜም ይዋጋናል፣ ይሸነግለናል በምኞቶቻችንም እየገባ ያገኘናል፡፡

አዳምን በሔዋን፣ ሶምሶንን በምወድደው ደሊላ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በእንግዶች ሴቶች ፍቅር፣ የአስቆሮቱ ይሁዳንም በገንዘብ ፍቅር እንደጣላቸው አላየህም፡፡ ስለዚህ እንደ ጎበዝ ሐኪም ሁን፣ ጉድለትህንና ሕመምህንም አክም፤ ኩራትህን በትሕትናና በየዋህነት ድል አድርገው፣ የትዕቢት በሽታህንም አንተነትህን በመናቅ ፈውሰው፡፡ በተአምራትና በታላቅ ነገሮችም ከመመካት ተጠበቅ ምክንያቱም ዲያቢሎስ ራሱ በብርሃን መልአክ መመስል ይችላል፡፡ በስብ ውስጥ መርዙን ሊከት፣ በማጥመጃው ዘንግ ውስጥም የመደለያ ጣፋጭ ምግብን ሊያደርግና መልካምና ጠቃሚ ነገር ይከተላል ብለህ እንድታምን ሊያታልልህ ይችላል፡፡ አንተ ግን ፈጽሞ አትታለል፣ በከንቱም አትነዳ፡፡ ይልቅስ ከዲያቢሎስ ጥቃት ትጠበቅ ዘንድ ሁሉን ነገር አስተውልና መርምር፡፡

ይሁዳ ጌታውን አልከዳምን? ኢዮአብስ ወዳጅና የሚታመን ሰው መስሎ አሜሳይን አልገደለውምን? (፪ነገ. ፳ ፥ ፱)

በእግዚአብሔር ታመን! ከመሪ በላይ አጥብቀህ ያዘው፤ ሁሉን ነገር ወደ እርሱ አምጣው፡፡ ድጋፍህና መጠጊያህ አድርገው፤ እርሱ ሁለንተናህ አድርገው።
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሩፋኤል (#ታኅሣሥ_13)

ታኅሣሥ ዐስራ ሦስት በዚህች ቀን በዚህች ዕለት ፈታሄ ማህጸን ሊቀ መልአክት ቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱና ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው፡፡ ሰማያውያን ከሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው፡፡ "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል፡፡ ጦቢት 12፡15፡፡ ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል መልአከ የሰላምና የጤና መልአክ ይባላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል ይፈወስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” መጽሐፈ ሄኖክ 6፡3፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል፡፡ ሄኖክ 10፡13፡፡ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ በማኅፀን ላለ ችግርና ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት በማሕፀን እያለ ማለትም በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነት ያለን ረቂቅ ርኩስ መንፈስ ያውቃል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሠቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል ጦቢት 3፡8-17፡፡

ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ሄኖክ 3፡5-7፡፡ በዚህ መሠረት ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሄኖክ 2፡18፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠብቃቸው እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ የሚከፍታቸዉ የሚዘረጋቸዉ ይህ ታላቅ መልአክ ነዉ፡፡

የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሥራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል፡፡ "ፈታሄ ማህጸን" ይባላል-እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡ እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡ ዳግመኛም "ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ" ይባላል-ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ ስለሆነ ነው፡፡ ዳግመኛም "መራሔ ፍኖት" ይባላል-ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና ነው፡፡ እንዲሁም "መላከ ክብካብ" ይባላል-ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ ነው፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል እስኪፈፀም ድረስ በከበረ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎፍሎስ ዘመን በምድረ ግብጽ ውስጥ ከእስክንድርያ ውጭ በታናፀች አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ከአሳ አንበሪ ላይ የታነፀች ነበር፡፡ ነገር ግን በወደቡ አጠገብ ከነበረ ግዙፍ አንበሪ ጀርባ ላይ መታነጿን ቀድሞ ያነጿት ሰዎች ቢሆኑ ከካህናትም ቢኾን ያወቀ አልነበረም፡፡

ያ አንበሪም የቤተክርስቲያኑ ህንጻ በከበደው ጊዜ ፈጽሞ ተንቀሳቀሰ፡፡ ከአሸዋማው መሬት ላይ በባህሩ ዳርቻ የታነፀች ይህች ቤተ ክርስቲያንም ከመሰረቷ አናወጻት፡፡ ያን ጊዜ ትልቁም ትንሹም ወንዱም፣ ሴቶችም፣ የተሾሙ ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ሕዝቡም ሁሉ ደነገጡ ታወኩ፡፡ አሣ አንበሪው ግን መንቀሳቀሱን አልተወም፡፡ በመንቀሳቀሱም የቤተ ክርስያኗ ሕንፃ እኩሌታ ይሰነጠቅ ዘንድ ጀመረ፣ ምድርን ተናወፀች፣ ንጉስና፣ ሊቀ ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም፣ ዲያቆናቱም፣ ህዝቡም፣ ሁሉም ካሉበት በባህሩ ወደብ ከተሰራች ከዚህች ቤተ ክርስቲያን መናወጥ የተነሳ ፍርሃት መንቀጥቀጥ በላያቸው ወረደ፡፡ ያ አንበሪ ግን በባህሩ ውስጥ ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗም በጀርባው ላይ ነበረች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የሉትም ሁሉ ያ አሳ አንበሪ ወደ ባሕሩ ውስጥ ሊያሰጥመን ነው ሲሉ አሠቡ፡፡ ያን ጊዜም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ስዕል ፊት በጽኑ አለቀሱ፡፡ በአንድ ቃልም "ገናናው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ ርዳታህ ፈጥኖ ይደርስልን ዘንድ በቅድስት ቤተክርስቲያን ወደተሰበሰብን ወዳጆችህ ተመልከት" እያሉ ይጸልዩ ጀመር፡፡ ያንጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ ያችን ቤተክርስቲያን በብሩሃት ክንፎቹ እንደደመና ጋረዳት፡፡ በእጁ በተያዘ የብርሃን በትረ መስቀሉ ያን ኣሣ አንበሪ ወገቶ "በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይል ከቦታህ ሳትንቀሳቀስ እስከትውልድ ፍፃሜ ዘመን ለዘለአለም ትኖር ዘንድ አዝዝሃለሁ" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያኗን ከነመዓዘኗ ከግርግዳዎቿ ከመሠዊያዋ በውስጧ ተተክለው ካሉት ሁሉ ጋር ከጀርባው ላይ እያለች ያንን አሳ አንበሪ ወግቶ በያዘበት ብርሃናዊ በትረ መስቀሉ ወደቀድሞው የባሕሩ ወደብ ጎተተው፡፡ ያንጊዜም ግንቡ ቦታውን ሳይለቅ እርስ በእርሱ ተጣበቀ፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አሣ አንበሪውን በቀድሞ ሥፍራው ያቺን ቤተክርስቲያን በቀደመ መሠረቷ ላይ አጽንቷቸዋልና፡፡ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም አዳኝ የሆነ የጌታው የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ጠርቶ ከሞት እንዳዳናቸው ሁሉም አስተዋሉ፡፡ በድንቅ ተዓምራቱ የዳኑ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ በሊቀመላእክቱ ቅዱስ ሩፋኤል ላይ አድሮ ድንቅ ተዓምራቱን ስለገለጸላቸው የቅዱስ ሩፋኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክም በዓለም ሁሉ በየአውራጃዎቹም ተሰማ፡፡ የቅርብም የሩቅም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ታላቁ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የለመኑትን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ የነገሩትን ያማልዳቸው ዘንድ በውስጧ ይጸልያሉ፡፡ በዚችም ቤተክርስትያን ብዙ ውስጥ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀንም ተአምራቶቹ ከተፈጸመባቸው ዕለታት አንዷ ናት፡፡ ቅዳሴ ቤቱም በዚሁ ዕለት ተከናውኗል፡፡

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ጥበቃው አይለየን።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
...እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን አዕምሮ ውስጥ የተረጋጋና ንቁ ዳኛ የሆነውን ሕሊናችንን ለምን ፈጠረ? በሰዎች መካከል እንደ ሕሊናችን ያለ የማያንቀላፋ ፈራጅ የትም አይገኝም። በዚህ ዓለም ያሉ ዳኞች በሙስና ውስጥ የተዘፈቁ፣ በሽንገላ የሚደለሉና በሰዎች ማስፈራራት ትክክለኛ ፍርድ የማይፈርዱ ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ትክክለኛ የሆኑትን ውሳኔዎች ያጣምማሉ። የሕሊናችን ፍርድ ቤት ግን እነዚህን በመሰሉ ተጽዕኖዎች የሚበገር አይደለም። ጉቦ ብትሰጡት፣ ብትደልሉት፣ ብታስፈራሩት ወይም ደግሞ ከዚህ በተለየ መንገድ ብትጠቀሙ ይህ ፍርድ ቤት በኃጢአት የተሞሉ አሳቦቻችሁ ላይ ትክክለኛ ፍርድ ከመፍረድ ወደ ኋላ አይልም፡፡

ኃጢአት የሚሠራ ሰው ማንም ሳይከሰው ራሱን ይከሳል፡፡ ይህ ደግሞ ለአንዴ ወይም ለሁለቴ ሳይሆን በሕይወቱ ሙሉ በተደጋጋሚ የሚቀጥል ክስ ነው፡፡ ረዘም ያለ ጊዜ ቢያልፍም እንኳ ሕሊና ምን እንደተደረገ በፍጹም አይዘነጋም፡፡ ሌላው ቀርቶ ኃጢአት ከመፈጸሙ በፊት፣ በሚፈጽምበት ጊዜና ከተፈጸመ በኋላ ሕሊና እኛን በመቃወም ኃይለኛ ከሳሽ ሆኖ ይቆማል፡፡ ኃጢአትን በምንፈጽምበት ጊዜ በደስታ ስለምንስክር የምንሠራውን ሥራ በትክክል አንገነዘበውም፡፡ ነገር ግን ደስታችን የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሶ ከተሟጠጠ በኋላ ልክ በምጥ እንደ ተያዙ ሴቶች የሚያስጨንቅ የፀፀት በትር በእኛ ላይ ይመጣብናል፡፡ በምጥ የተያዙ ሴቶች ልጅ ለመውለድ በሚያደርጉት እጅግ ከባድ ጥረት ውስጥ ከጭንቀታቸው በላይ የሚሰማቸው ኃይለኛ ሕመም አለ፡፡ ነገር ግን ከወለዱ በኋላ ልጁ በከባድ ጭንቀት ውስጥ አልፎ ስለ መጣ ታላቅ እፎይታና ደስታ ይሰማቸዋል፡፡ ኃጢአትን በተመለከተ ግን እንዲህ ያለው ጉዳይ የተለየ ነው፡፡ እኛ ክፉ ሥራችን ባመጣብን ከባድ ምጥ ውስጥ ሆነን ራሳችንን በደስታ እናዝናናለን፡፡ ነገር ግን የክፋትን ልጅ እርሱም ኃጢአትን በወለድን ጊዜ አሳፋሪውን ልጃችንን በማየት እንመረራለን፡፡ በዚህም በምጥ ላይ ያሉ ሴቶች ከሚጨነቁት የበለጠ አንሠቃያለን። ስለዚህ ምንም ዓይነት ፍላጎትን ገና ከጅምሩ እንዳትቀበሉ እለምናችኋለሁ፡፡ ከተቀበልነው ደግሞ ተግባር ላይ ሳናውለው በዚያው እናስቀረው፡፡ ነገር ግን እዚህ ደረጃ ላይ ደርስን የኃጢአት ፍላጎት ገፍቶ ከመጣብን ራሳችንን በመውቀስ በንስሓና በዕንባ እንግደለው፡፡

ስለ ኃጢአት በንስሓና በዕንባ ራስን እንደ መውቀስና እንደ መክሰስ ያለ ጠቃሚ ነገር የለም፡፡ ኃጢአትህን አውግዘህ ታውቃለህን? ሸክሙን ከላይህ ላይ አራግፍ፡፡ ይህን ያለው በእኛ ላይ የሚፈርደው እግዚአብሔር ነው፡፡ "አሳስበኝ:- በአንድነትም ሆነን እንፋረድ፤ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር።" (ኢሳ 43፥26)።

እስቲ ንገረኝ! ኃጢአትህን ለመናዘዝ ስለ ምን ታፍራለህ? ስለ ምንስ ትሳቀቃለህ? ኃጢአትህን የምትናገረው እኮ ለሚያጋልጥህ ለባልንጀራህ አይደለም። የምትናገረው ቁስልህን ለምታሳየው፣ ለሚያክምህና ለሚንከባከብህ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ የተደረገውን ነገር ሁሉ ከመሆኑ በፊት ስለሚያውቅ አንተ ኃጢአትህን ባትናዘዝ እንኳ የማያውቅ እንዳይመስልህ፡፡

ታዲያ ለምንድር ነው ኃጢአትህን የማትናዘዘው? ራስህን የምትወቅስ ከሆነ ኃጢአትህ ይቀልልሃል እንጂ የበለጠ አይከብድብህም፡፡ ይከብድብሃልን? ይልቁንም ሸክምህ ልዝብና ቀሊል ይሆንልሀል። በዚህም ምክንያት ኃጢአትህን እንድትናዘዝ የሚፈልገው ሊቀጣህ ሳይሆን ይቅር ሊልህ ነው፡፡ ወይም ይህን የሚያደርገው ኃጢአትህን ለማወቅ አይደለም፤ ይልቁንም በይቅርታው ብዛት ምን ያህል የኃጢአትህን ዕዳ እንደ ተወልህ እንድታውቅ ነው። የዕዳህን ታላቅነት የማትናዘዝ ከሆነ የጸጋውን መጠን ልታውቅ አትችልም፡፡
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
“ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ አላት።” /ማር 5÷34/

"እምነት" በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ እግዚአብሔር ከፅንሰቱ እስከ እርገቱ ድረስ በምድር ላይ ሰው ሆኖ በፈቃዱቨ ያደረገውን ሁሉ ማመን መቀበል ሳያጎድሉ በምልዐት መቀበል ነው (ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ መድልተ ጽድቅ ቅጽ 1) የሰው ልጅ ውድቀቱ መነሳቱ በእምነት ማጣት እና ማግኘት ነው።

አስቀድሞ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ሲፈጥረው እንደራሱ አድሮጎ በተፈጠረለት ማንነቱ በንፅሕናው ተፈጥሮ መልካምና ክፍውን ይለይ ዘንድ ነፃ ፍቃድ ሰጥቶ ፈጠው ከእርሱ በፈት የተፈጠሩት ፍጥረታት ሁሉ አዳም የእግዚአብሔር ስራ አይቶ በመድነቅ ከእግዚአብሔር ጋር በእምነት በታማኝነት አንድላይ ይኖሩ ዘንድ ፍጥረታት ተፈጠሩለት እግዚአብሔር ከዚህ ከተፈጠረለት ማንነት እንዳይወጣ አሰቀድሞ " ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካም እና ክፍውን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ በማለት አዞት " ግን ከእግዚአብሔር ይልቅ የሴጣንን ምክር ሰምቶ አምኖ ሞትን በራሱ ላይ አመጣ የቀደመችው ሔዋን ሴጣንን አምና ሞትን  በእራሷና ከአብራኩ ካስገኛት አዳም ሞትን አመጣች።

ዳግማዊቷ ሔዋን ድንግል ማርያም ግን መጀመርያ ሞት በመጣበት መንገድ የእምነት ማጣት ትሞላ ዘንድ ቀድማ የሴጣንን ምክር በተቀበለችው ሔዋን  ፍንታ የመላኩን ቃል በእምነት በመቀበል ለፈጣሪ ያለንን እምነት መለሰችልን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእምነት በመኖራቸው የእምነታቸውን ፍሬ ያፈሩ እና በሕይወታቸው ሁሉን የእግዚአብሔር  ቻይነት የመሰከሩ እሩስም ታማኝነታቸውን በበረከት የመሰከረላቸው አሉ ከእንዚህም ውስጥ የመጥምቁ እናት ቅድስት ኤልሳቤጥ ናት እስከ  እርጅናዋ ዘመን ድረስ እግዚአብሔር ስታገለግል የኖረች የካህኑ ዘካርያስ ሚስት ኤልሳቤት ታሪኳ በሉቃ 1÷5 ተፅፎ እናገኛለች ኤልሳቤጥ በዘመኗ ሁሉ እግዚአብሔር ባይሰጣትም ልጅ እንደሚሰጣት አንድ ቀን አምና የእግዚአብሔር ሁሉ ቻይነት እመሰከረች ኖረች።

እግዚአብሔር የኤልሳቤጥን እሱን አምና ለዘመናት ሳታማርር መኖሯን አይቶ ጌታን የሚያጠምቀውን መጥምቁ ዮሐንስን ሰጥቷት እምነቷን መሰከረላት ይህ ሁሉ የሆነው በኤልሳቤጥ በእምነት መኖር ነው። ሰማዕታት የእግዚአብሔርን ክብር እየመሰከሩ በርሃብ እርሱን ምግብ አርገው ሁሉን  እንደማያሳጣቸው እየመሰከሩ ኖሩ እግዚአብሔር በገባላቸው ቃልኪዳን ዘወትር ፍጥረታትን በስማቸው እየመገበ እምነታቸውን መሰከረላቸው።

(ማቴ 20÷22) ተፅፎ የምናገኘው አንድ ታሪክ አለ ከአስራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም ይፈሳት የነበረች ሴት ብዙ ባለመዳኒቶች ጋር ገንዘቧን የጨረሰች ግን የገንዘቧ ማለቅ ደሟ መፍሰሱን ያላስለቀቀላት" ያልቆመላት ሴት። ይች ሴት ክርስቶስን ልብሱን የነካው እንደሆነ እፈወሳለሁ ብላ በእምነት አምና ቀረበች ዳሰሰችውም ዳነች። ክርስቶስ ልጄ ሆይ አይዞሽ እምነትሽ አድኖሻል ብሎ መሰከረላት። ይህች ሴት የክርስቶስን በስጋ ውስጥ ሳይታይ ያለውን ሁሉን ቻይነት አምና ሊፈውሳት እንደሚችል አምላክነቱን በእምነት መሰከረች። ክርስቶስ በማይታየው እምነቷ የሚታየውን በሽታዋን በመፈወስ እምነቷን መሰከረላት።

ወዳጆቼ ብዙ የሚታይ በሽታ ይዞን ይሆናል እንደ ዘመኑ ሰው የመግደል በሽታ አልቅሶ እስካለየነው ደስታ የማይሰማን የመሆን በሽታ ፍቅርን በመግፍት አንጂ በተጠላን ልክ የማይገኝ ሲመሰለን በትውልድ ውስጥ ጥላቻ እየጫሩ የመኖር ይህ ሁሉ የሚታይ የግፍ ውጤት ሊቆም ያልቻለው የማይታየው እምነት ስለሌለን ፈጣሪ ሳይሆን ሴጣን እየመሰከረልን እየኖርን እንገኛል። ስለዚህ ፈጣሪ እንዲመሰክርልን ወደ እርሱ እንመለስ።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ምጽዋት

የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ፡፡ የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ፡፡

አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው፡፡ የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፡፡ ታድያ ወንድምህስ? የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነው? መሆን የለበትም፡፡ ማስቀመጫ እንዳጣ መጣያ አታርገው ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው፡፡ ከምትለብሳቸው ሁለት ልብሶች አንዱን ስጠው፡፡ የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው፡፡ ለአንተ የምትመኘውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ፡፡

“ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው” ያለውን የእግዚአብሔር ቃል መለስ ብለህ አስብና፣ የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ፡፡ ከዚሁ ጋር አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋዕት እንዴት እንደነበረ አስብ፡፡ “አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፡፡” (ዘፍ 4፥4) ለምን መረጠለት? ብትል ፣ ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ስላቀረበ ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ 4፥34-35 ላይ ሠፍሮ የሚገኘውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ፡፡ ክብርን ለመፈለግ አትስጥ በአንደበትህም ይሁን በልብህ፣ በስሜትህም ይሁን በሃሳብህ የራስህ ነገር ኖሮህ እንደሰጠህ አስበህ አትኩራራ፡፡ ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን እንደ ትልቅ ማስረጃ ተጠቀም፡፡ “አንተ እድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልክ ከሆነ ግን እንዳልተቀበልክ የምትመካ ስለምንድር ነው?” (1 ቆሮ 4፥7) ስለዚህ ስጦታ ሁሉ ከእግዚአብሔር ተቀብለን የምንሠጠው እንጂ የራሳችን እንደሆነ በከንቱ የምንመካበት አይደለም፡፡
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም። ኃጢአትን ከፈጸሙና ከሠሩ በኋላ ለኃጢአት ያበቃ ሌላ ምክንያት ማቅረብና በዚያም አንፃር ለመጽናናት መሞከር በራሱ ኃጢአት ነው። በዚህ አይነት ለኃጢአቱ ምክንያት እየደረደረ የሚጽናና ሰው ኃጢአትን እየለመደ ወደ ባሰ አዘቅት ከመውረድ በቀር ንስሐ ለመግባት አይችልም። ምንም ምክንያት ቢደረድር ኃጢአት ምን ጊዜም ኃጢአት ነውና። ለሠራነወ ኃጢአት የተለያዩ ምክንያቶችን በማበጀት ራሳችንን እያጽናናን ነፃ ለመሆን መጣር የለብንም ።

ስለ ሰሩት ኃጢአት ምክንያትን የደረደሩ አዳምና ሔዋንም ባቀረቡት ምክንያት ከመቀጣት አልዳኑም ። እግዚአብሔርም አዳም ስለ አቀረበው ምክንያት "የሚስትህን ቃል ሰምተኻልና ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዘዝኩህ ዛፍም በልተኻልና " በማለት ለኃጢአቱ የሚገባውን ቅጣት ሰጠው እንጂ አልተወውም። [ዘፍ3፥17] ይባስ ብሎ በእነርሱ ምክንያት በመጣው መርገም ቅጣቱ በትውልዳችን ሁሉ ሆነ እንደ እነርሱ ሁሉ እኛም ዘወትር ምክንያት በመደርደር ከኃጢአታችን የተነሣ ከሚመጣው ቅጣት ለማምለጥ የምንሞክር ሆንን ስለዚህ ንስሐ ለመግባት በጣም ስንቸገር እንታያለን ።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
2025/07/04 18:02:15
Back to Top
HTML Embed Code: