Telegram Web Link
ምን ጥቂት ነገር አለህ?

       ጌታችን እርሱን ተከትለው የወጡትን የአምስት ገበያ ህዝብ(አምስት ሺ አባውራ) አመሻሹ ላይ ሐዋርያት የሚበላ ስለሌላቸው እንዲያሰናብታቸው ጠየቁት።  እርሱ ግን የሚበሉት እንዲሰጧቸው ነገራቸው አሁን ጌታችን ያላቸው ምግብ ለህዝቡ እንደማይበቃ ጠፍቶት አይደለም ነገር ግን ችግራችንን ጉድለታችንን ሊሞላልን ሲፈልግ አስቀድመን ችግራችንን ልንነግረው ይፈልጋልና ሐዋርያቱ ያላቸው ምግብ ትንሽ መሆኑን እንዲነግሩት ነበር ። ወዳጄ አንተስ ችግርህ ምንድን ነው? ልታደርገው አቅደህ አልበቃ ያለህ ምንድን ነው? በአገልግሎት በመንፈሳዊ ህይወት ልትተጋ አስበህ ምን ጎሎህ ነው የነበሩህን እቅዶች ለመሸኘት የተገደድከው? ከቃሉ ከአገልግሎቱ  የራከው ምን አንሶህ ነው? ጊዜ አጥሮህ ነውንን? ትጋት አጥሮህ ነውን? ትዕግስት አጥተህ ነውን? ምንድን ነው ያነሰህ? ብቻ ችግርህን ንገረው እርሱ ያነሰህን ነገር አበርክቶ  ተትረፍርፎህ ታየዋለህ።

           ለጌታችን ሐዋርያት ያለን ሁለት ዓሳና አምስት እንጀራ ብቻ ነው አሉት። አሁን ይህ ምግብ  እንኳንስ ለህዝቡ ይቅርና ጌታችንንና ደቀመዛሙርቱን እንኳን በቅጡ የሚያጠግብ  አልነበረም ነገር ግን ሐዋርያቱ እጅ ላይ የነበረውን  ጥቂቷን ነገር ሠጡት እርሱም ባርኮ አበርክቶ አምስትሺውን ህዝብ አብልቶ 12መሶብ ከተረፈው ተሰበሰበ።

         ወዳጄ እጅህ ላይ ምን አለ? በእጅህስ የያዝከው ምን አለ? ጥቂት ነው ለምንም አይበቃም ያልከው ምናልባት መኖሩንም የረሳኸው ሊሆን ይችላል እርሱን ይዘህ ቅረብ ለእርሱም ስጠው እርሱ ባርኮ መልሶ ይሰጥኻል። ከብዙ የዓለም መባዘን የተረፈህ ትንሽ ጊዜ አለህ እርሱን እስኪ ለእግዚአብሔር ስጠው ያን ይባርክልኻል። ጉልበት አለህ እርሱንም ለእግዚአብሔር ስጠው አገልግልበት እውቀት አለህ እርሱንም ቢሆን ለእግዚአብሔር ስጠው። ያለህን ጥቂት ነገርም ቢሆን ስጠው እርሱ ባርኮ ሲመልስል ትልቅና ካሰብከውም በላይ ነው።እመ ሣሙኤል ሃናን ተመልከት ህፃኑን ሣሙኤል ለእግዚአብሔር ሰጠችው እርሱም በሞገስና በጥበብ አሳድጎ ታላቅ ነቢይ የእስራኤልም አባት ንጉስን ቀብቶ የሚሾም አደረገው ። ኢያቄምና ሃናንም ተመልከት የ3 ዓመት ህፃን እመቤታችንን ሰጡት እርሱም የዓለም እናት አድርጎ ሠጣቸው የወለዷት እናት ሆነቻቸው መርታም ወደ ገነት አስገባቻቸው። አንተም ያለህን ጥቂት ነው የምትለውንም ቢሆን ስጠው ካሰብከው በላይ አድርጎ ይሰጥኻልና። ወዳጄ ሆይ አንተስ ምን አለህ? መቼም ምንም የለኝም አትለኝም ሰጪው እግዚአብሔርን በሐሰት መክሰስ ይሆንብሃልና ቢያንስ ሕይወት አለህ፤ ይህን ጹሑፍ ማንበብህ በራሱ ማንበብ የምትችል በመሆንህ ነው። ልክ እንደዚሁ ሁሉ አንተ መኖሩን እንኳን የረሳኸው ያም ባይሆን ጥቂት ነው ይህማ ለምንም አይበቃም ያልከው ነገር አይጠፋምና እርሱን ይዘህ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ ያ ጥቂት ነው ያልከው ተትረፍርፎ ትመለከታለህ።

ወዳጄ ሆይ ጥቂትም ብትሆን ምን አለህ?

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ግንቦት ፲፱ /19/

በዚች ቀን ከአባ መቃርስ ገዳም ቅዱስ አባት ቀሲስ ይስሐቅ አረፈ። ይህም አባት ከምሥር ከታናናሽ ቦታዎች ከአንዲት ቦታ ነው ወላጆቹም ድኆች ሲሆኑ ግን በበጎ ስራ ባለጸጎች ናቸው።

አረጋውያን መነኰሳትም የእጅ ስራቸውን ሊሸጡ ወደ ምሥር በሄዱ ጊዜ ተከትሏቸው ወደ አስቄጥስ ገዳም መጥቶ ሲአገለግላቸው ኖረ። በቀንበራቸውም ተጠምዶ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ በዘመኑም ሁሉ ከቶ ምንም ጥሪት አላደረገም።

በዕድሜውም በሸመገለ ጊዜ ትሩፋቱና ጽድቁም በበዛ ጊዜ ቅስና ይሾሙት ዘንድ አረጋውያን ተሰብስበው ተማከሩ።

እርሱም ከእርሳቸው ሸሽቶ ከተዘራ ማሳ ውስጥ ገብቶ ተሠወረ። እርሱንም እየፈለጉ ዞሩት አላገኙትም ያቺንም ማሳ አልፈው ከዳርዋ ተቀመጡ ጥቂት ሊያርፉ። ከእርሳቸውም ጋር አህያ ነበረ ወደ ማሳውም ሩጦ ገብቶ ይህ አባት በተሸሸገበት ቦታ ቆመ። አህያውን ሊያስወጡትም በገቡ ጊዜ ያንን አባት አገኙት። ደግሞ እንዳይሸሽ ሊአሥሩት ፈለጉ አሁንስ ዐውቄዋለሁ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አላቸው ከዚያም አብሮአቸው ሒዶ ቅስና ሾሙት።

ከዚህ በፈቃድኋላም ተጋድሎውንና ለአረጋውያን መታዘዙን ጨመረ እግዚአብሔርን አገልግሎ በፍቅር በሰላም አረፈ የሕይወት አክሊልንም አገኘ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከቱም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ባለህ ተደሰት

በዚህ ዓለም ላይ ትልቁ ፍልስፍና ፣ ትልቁ ጥበብ፣ ትልቁ እምነት “እንደ ፈቃድህ” ማለት ነው። በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደዚህ ዓለም መጥተናል፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከዚህ ዓለም እንሄዳለን። የእግዚአብሔር ፈቃድ ገዥ ነው። ፈቃድህ ይሁን ባንልም ፈቃዱ ይሆናል። ፈቃዱ ይሁን በማለት ግን ሕይወት ጥያቄ ሳይሆን መልስ እንድትሆን ያደርጋል። ትልቅ ፍልስፍና ራስን መጣል አይደለም፣ ራስን መጣል ስንፍና ነው። ፈላስፎች ከምድር ጀምረው በምድር ይጨርሳሉ። ያለ ክርስቶስም ለዚህ ዓለም ስለሚሞቱ ትንሣኤ የላቸውም። ዓለም ከንቱ ናት ቢሉም ብርቱ በሆነው በክርስቶስ ግን አልቀየሩአትም። ትልቅ ፍልስፍና የሕይወቴን መግቢያና መውጫ ለያዘው እግዚአብሔር መንገድ መልቀቅ ነው። ያለ ፈቃዴ መጥቼ ያለ ፈቃዴ በምሞትበት ዓለም ላይ ፈቃድህ ይሁን ማለት ምቹ ትራስ እንጂ የድንጋይ መደገፊያ አይደለም። ትልቅ ጥበብም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅና ማክበር ነው። ጥበብ እውቀትን የምንኖርበት ተግባራዊነት፣ እሾሁን ሳይሆን ጽጌረዳውን የምናይበት መነጽር ነው። “የማይጋፉትን ግንብ ዞረው ያልፉታል” እንዲሉ የማንጋፋውን ፈቃድ መቀበል ከመጋጨት ያድናል። ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሲጣላ ቀጥሎ ከሰው ጋር ሳይሆን ከራሱ ጋር ይጋጫል። ከራሱ ጋር የተጋጨም ከሰው ጋር ሰላም የለውም። ትልቁ እምነትም ተአምራት ማድረግ ሳይሆን “ፈቃድህ ይሁን” ብሎ ማረፍ ነው። ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የተሰጠን ነገር እንደሌለ ያለ ፈቃዱም የሚወሰድብን ነገር የለም።

ይህች ዓለም ጉድለትዋ የጀመረው ዛሬ ሳይሆን አዳም በስደት ከመጣባት ጊዜ አንሥቶ ነው። ለምለም እንድታበቅል የተፈጠረችው እሾህ አሜኬላ ሲበቅልባት፣ እየደሙና እያደሙ መኖር ሲበዛባት፣ አንዱ ላንዱ ዕረፍት መሆን ትቶ ሐፍረት ሲሆንባት ዓለም ከንቱ ነው እንላለን። ዛሬ የጀመረ የመሰለን ክስተትም ኃጢአትም የለም። የሚሆነው ሲሆን የነበረ ነው። “ደንቆሮ የሰማ ቀን ያብዳል” እንዲሉ አላዋቂ ዛሬ ሲሰማ ያ ነገር ዛሬ የጀመረ ይመስለዋል። ልቅሶ ላልሰማው ሰው ሁልጊዜ አዲስ ነው። ሰውዬው ሚስቱ በሞተች ባመቱ የሰማ ሰው መጥቶ ሲያለቅስ “እኔ ረስቻታለሁ አንተ እስካሁን ታስባታለህ” አለ ይባላል። ፍላጎታችንን በውል መረዳት በማንችልበት ዓለም ላይ ነን። ትላንት የምንፈልገውና ዛሬ የምንፈልገው እርስ በርሱ የሚቃረን ነው። በምኞት ስንሰጥ ኖረን ስናገኝ ስስታም ነን። ሁሉም ነገር ቢሟላ ዓለም ዓለም መሆንዋ ይቀር ነበር። “ብልህ ልጅ የሰጡትን ይዞ ያለቅሳል” እንዲሉ የመጣውን መቀበል ያልመጣውን ለመጠበቅ ኃይል ነው።

ብዙ ሰው ከፍላጎቱ ውጭ የተማረ፣ የሚሠራ ፣ የሚኖር ሊሆን ይችላል። የሚወደውን ነገር ያገኘ ጥቂት ነው። ዕለት ዕለት የምንሸከመው መስቀል የማንወደውን ነገር መታገሥ ነው። ደስታን ማሳደድ በበዛበት በዛሬው ዘመን፣ ደስታ ላግኝ እንጂ በየትም በኩል ይምጣ በሚባልበት በእኛ ዓለም፣ በቆሻሻ ውኃም ቢሆን እሳትን ማጥፋት ይቻላል ተብሎ ከእውነት ስሜት በሚከበርበት ምድር የሚወዱትን ማጣት ብርቱ ነገር ነው። በዚህ ምድር ላይ የምንኖረው ግን የምንወደውን ስላገኘን ብቻ ሳይሆን በማንወደው ነገር ውስጥም ትዕግሥትን ለመለማመድ ነው። እንደ እኛ አሳብ በዚህ አገር፣ በዚህ ኑሮ ውስጥ አልነበርንም። ከመረጥነው የተመረጠልን ይሻላልና ደስ ሊለን ይገባል። የትም ቢሄዱ ሰማይና አፈር አንድ ነው። የትም ቢሄዱ ምግብ የሚባል ነገር አናገኘም፣ የምግብ ልዋጭ እንጂ እግዚአብሔር ብቻ እንግዳ ደስታ ነው።

የምንወደው ወዳጃችን፣ የመከራችን ጓድ ዛሬ በቅርበትም በሕይወትም ላይኖር ይችላል። ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት ይሻላልና ያገኘነውን መውደድ ያስፈልጋል። ሰው የሚኖረው ወዳጁ ያለበት ሳይሆን እንጀራው ያለበት ነው። እየተዋደድን ከብዙ ወዳጆቻችን ጋር በእንጀራና በሞት ምክንያት ተለያይተናል። ዛሬ ያሉት ወዳጆቻችን እንደ ቀድሞዎቹ ላይሆኑልን ይችላሉ። ፍቅር እየቀነሰ ባለበት ዘመን ባለመጥፋቱ ማመስገን ይገባናል። ከመልካምና ከክፉ ማነጻጸር በድሎት ዘመን ነው። በክፉ ዘመን ከክፉ የተሻለው ክፉ ይመረጣል። የምንወደውን ትምህርት እየተማርን ላይሆን ይችላል። ሰው ግን የሚኖረው በትምህርቱ ሳይሆን እግዚአብሔር በሚሰጠው ዕድል ነውና መከፋትና ማዘን አይገባም። የትምህርት አንካሳ የለውምና ሁሉን መማር መልካም ነው። በምንወደው ሥራ ላይ ላንሆን እንችላለን፣ የምንወደው ጋ ለመድረስ ያገኘነውን መውደድ መሰላል ነው።

የምንወደውን ማግኘት አለመቻላችን የሚያናድድ ሳይሆን ሰው መሆናችንን የሚያስረግጥ ነው። ሰው ማለት አቅሙ የተወሰነ ፍጡር ነውና። እኛ የምንወደው ባይገኝም እግዚአብሔር ይሁን ያለው ግን አልቀረም። በገጠመን ዕድል ሳይሆን በመረጥነው ክፉ እንጠየቃለን። እነዚያ ነገሮች ባይሆኑ መልካም ነበር። ፈቃዳችን ሳይሆን በሆኑት ነገሮች ግን ጸጸት ሊሰማን አይገባም። ከንቱ ጸጸት ተመጻቂነት  ነውና።  የዛሬ አለመቻል የነገ መቻል ነው። አለመቻልን እንደ መቻል ስንቀበለው የምንችልበት ቀን ይመጣል። ትንሣኤ ያለው ትንሣኤ ውስጥ ሳይሆን ውድቀት ውስጥ ነው።

በጠለቀችው ፀሐይ ሳይሆን በወጡት ጨረቃና በፈኩት ከዋክብት አመስግን። ጨለማ ባይመጣ ከዋክብት አይታዩም ነበር ፣ ክፉ ቀኖችም ሰዎችን ያሳውቁሃል።

በእጃችን ያለው ትንሽ ነገር፣ የማንወደው ቢሆንም ደስ ይበለን። የምንወደው እየቀረበ ይመጣል። ምስጋና ጨለማን ብርሃን፣ መንፈሳዊ ደስታም ጉብኝትን ያመጣል። ባንወደውም ወደ ሞት የምንጓዝ ነንና የምወደው ቀረብኝ ብለን መከፋት አይገባንም። የምንወደውን ብናገኝም ሞት አይቀርም። በሥላሴ ማመን ግን ከሲኦል ሞት ያድናል።

የምትወዱትን ስላላገኛችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ተመልከተኝ

          ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያች እለተ ምስጢር (በእለተ ሐሙስ) ስለሚገጥመው መከራ እያነሳ ሲነግራቸው ከሐዋርያቱ መካከል ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ “ ጌታ ሆይ፥ ወደ ወኅኒም ወደ ሞትም ከአንተ ጋር ለመሄድ የተዘጋጀሁ ነኝ ”ሉቃስ 22፥33 እያለ ቢናገርም ጌታ ግን መልሶ እንዲህ ብሎታል፦“ጴጥሮስ ሆይ፥ እልሃለሁ፥ እንዳታውቀኝ ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ድረስ ዛሬ ዶሮ አይጮኽም አለው።” ይህ ሆነ በኋላ በዚች ምሽት ጌታችን ከተያዘ በኋላ በጲላጦስ ግቢ ከደቀመዛሙርቱ መካከል የተገኙት ሁሉቱ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ ብቻ ነበሩ።

           ቅዱስ ጴጥሮስ እሳት ለመሞቅ ወደ እሳቱ ቢጠጋ አንዲት ታናሽ አገልጋይ(ገረድ) ቀርባ ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበረ አለች። እርሱ ግን አንቺ ሴት አላውቀውም ሲል  መረቡን በአሳ የሞላለትን አማቱን ከንዳድ የፈወሰለትን አምላክ ካደ። ከጥቂት ቆይታ በኋላም ደግሞ አንዱ አይቶት አንተ ደግሞ ከእርሱ ወገን ነህ አለው። አንተ ሰው እኔ አይደለሁም ብሎ ከአንተ ወደ ማን እንሔዳለን አንተ የዘለዓለም የህይወት ቃል አለህ ብሎ የመሰከረለትን አምላክ በደብረ ታቦር ለጥቂት ደቂቃ  ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ ቢያሳየው ከእርሱ ጋር ለዘለዓለምን መኖር ሽቱ 'በዚህ መኖር መልካም ነው።' እንዳላለ  ከእርሱ ጋር የነበርኩ እኔ አይደለሁም ሲል በድጋሚ ካደ። ከአንድ ሰዓት በኋላ ሌላኛውም መጥቶ፦እርሱ የገሊላ ሰው ነውና በእውነት ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበረ አለ። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ከቀድሞ አብልጦ እየማለና እየተገዘተ ከአሳ ማጥመድ አውጥቶ ሰው አጥማጅ ያደረገውን የመንግስተ ሰማይ ቁልፍ የሰጠውን አምላክ ሙት ያስነሳ ህሙማንን ይፈውስ አጋንንትን ያስወጣ ዘንድ ሥልጣን የሰጠውን ከአንተ ጋር ለመሞትም ዝግጁ ነኝ ያለውን አምላክ አላውቀም  አለ።

         ጴጥሮስ ለሶስተኛ ጊዜ አላውቀውም ብሎ ገና ሲናገር ዶሮ ጮኸ።በዚህ ጊዜ  ጌታ ጴጥሮስን ዘወር ብሎ ተመለከተው። ጴጥሮስም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ። ጴጥሮስ ሆይ ያስለቀሰህ ምን ይሆን ዐይንህን በእንባ የሞላው ልቦናህን ለጸጸት ያተጋው እግርህንስ ለንስሐ ያሮጠው ምንድን ነው?  የሂፖ ሊቀ ጳጳስ አውግስጢኖስ ስለዚህ ነገር እንዲህ ይላል "ክርስቶስ ባይመለከተው ኖሮ ባላለቀሰ ነበር።" ጴጥሮስን ለጸጸት ለእንባ ለንስሐ ያሮጠው የክርስቶስ መመልከት ነበር። ጌታዬ ሆይ አለቅስ ዘንድ የምትመለከተኝ መቼ ነው? ለበደሌ የምትተወኝ እስከመቼ ነው?  ስንቴ ስበድልህስ ይሆን ዞረህ የምትመለከተኝ? ቁጥር አልባ ጊዜ በግብሬ ህልውናህን ክጃለው ታዲያ እኔን አትመለከተኝምን? ያ ጴጥሮስ ሊቋቋመው ያልቻለውን ዐይንህን የምታሳየኝ አንተስ የምትመለከተኝ መቼ ነው?

         ጌታዬ ሆይ እባክህን ተመልከተኝ ያለ አንተ ከዚህ ጎስቋላ ህይወት ከኃጢአትም ኑሮ ሊታደገኝ የሚችል የለምና።  የቅዱሱን አባት ጸሎትም ጸሎቴ አድርጌ እማጸንሀለው፦ "አቤቱ በደሌንና ነውሬን የሚያጥብ ዕንባን ሥጠኝ፤ አቤቱ አንተን የሚያገለግል ዕንባን ሥጠኝ፤ አቤቱ የሚያቃጥል ዕንባን ስጠኝ፤ አቤቱ ከዐይኔ ፈስሶ የአካሌን እድፍ የሚያጥብልኝን ዕንባን ስጠኝ፤ የተጸጸቱ ሰዎችን ዕንባ የምትቀበል  ጌታ ሆይ አንተ የተቀበልከውን ጽኑ ልቅሶ እንዳለቀሰ እንደ ጴጥሮስ ያለ ዕንባን ሥጠኝ፤ አቤቲ እንደ ባህር የምትፈስስ እንባን እጠበኝ የማያቋርጥ የዕንባን ጎርፍ አፍስስልኝ" (ውዳሴ አምላክ ዘእሁድ) ጌታዬ ሆይ ኃጢአቴን አስቤ በእንባ እታጠብ ዘንድ እባክህን ጴጥሮስን በተመለከትክበት ዐይንህ ተመልከተኝ።

"ጌታችን ሆይ ወደ እኛም ተመልከት ስለ ኃጢአታችንም እንድናለቅስ አድርገን" ሊቁ አምብሮስ
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​የተሠጠህን ቁጠር

ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው:: የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም:: ዕባብ ደግሞ የሰይጣን አንደበት ነበረ::

ሰይጣን እንዲህ አላት :- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።
ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም። የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው። ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ:: ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ።

ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም። ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር። ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቶአት ሔደ። ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች። የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች።

ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል።

በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን:: ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ:: ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ:: አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ።

ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ  አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
እንደ በሽተኛ ሁን

መልካም ክርስቲያን የሚባለው እንደ በሽተኛ ሰው ሆኖ የሚኖር ነው። ምክንያቱም በሽተኛ ያገኘውን ፣ ያቀረቡለትን ሁሉ አይመገብም። ክርስቲያንም ያየው ነገር ሁሉ ሊያምረውና ሊያጓጓው አይገባም። ምግብም ቢሆን ተገኘ ብሎም ማግበስበስ የለበትም። ምግብ ፈተና ያመጣበታል ሕዋሳቱን ያንቀሳቅስበታል ፣ ሥጋዊ ምኞቱን ያነሳሳበታልና በመጠኑ ሊኖር ይገባል። በመንገድ ሲጓዝም ቢሆን አስተውሎ ፣ ረጋ ብሎ ነው እንጅ አይዋከብም።

በሽተኛ ብዙ አያወራም። ክርስቲያንም ብዙ ማውራት መለፍለፍ የለበትም። በሽተኛ ድምፁ ከፍ ያለ ነገር ሁሉ ስለሚረብሸው ይጸየፋል። በሽተኛ አይበሳጭም ትእግስተኛ ነው ጉልበትም ቢሆን አይጠቀምም ይልቁን ጉልበቴ እግዚአብሔር ነው ይላል። ማንም ቢናገረው ዝም ብሎ ያሳልፋል። ክርስቲያንም እንደዚህ በሽተኛ ሊሆን ይገባዋል።

ምናልባት በሽተኛው ስላልቻለ ሊሆን ይችላል ዝም የሚለው ክርስቲያን ግን ጉልበት እያለው እየቻለ እንኳ እንደ ደካማ ሊሆን ይገባዋል። ክፉ ሲናገሩት መመለስ እንደማይችል ሰው መሆን አለበት። ስለዚህ መልካም ክርስቲያን ለመሆን ከፈለግን እንደ በሽተኛ ሰው እንኑር።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​ቃል ኪዳን

እግዚአብሔር ለቅዱሳን ፍጹም የሆነ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” መዝ 88፤3 በማለት እንደተናገረ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ያደረጋቸው ቃልኪዳኖች ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህንም ቃል ኪዳናት እስከመጨረሻው ይጠብቅላቸዋል፡፡

“አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ ለሚወዱህና ትዕዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንህንና ምህረትህን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ” ነህ 1፤5 እንዲሁም በዘዳግም ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደሆነ አምላክ እንደሆነ ለሚወዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃልኪዳኑንና ምህረቱን እስከ ሺ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክእንደሆነ እወቅ” ዘዳ 7፤9 በተጨማሪም በመጽሐፈ ነገስት ላይ ያለውን ተመልከት 1ነገ 8፤23 እነዚህ ጥቅሶች የሚያስረዱት ይህንን ነው፡፡

ለምሳሌ ከጥፋት ውሃ በኋላ እግዚአብሔር ኖህን “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት” ዘፍ9፤1 አለው፡፡ ኖህ ግን “ብንበዛ ምን ዋጋ አለው ሰው ከማጥፋት ላያርፍ አንተም ከመቅጣት ላታርፍ ” ሲል መለሰ፡፡ በዚህ ጊዜ ነው እግዚአብሔር “እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተ በኋላ ከሚመጣው ዘራችሁ ጋር አቆማለሁ ከእናንት ጋርም ላሉትም ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፡፡

ከእናንተ ከመርከብ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች ለእንስሳትም ለምድር አራዊትም ሁሉ ይሆናል” ያለው በዚህ ለኖህ አምላክ በሰጠው የሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን እንስሳትም አራዊትም አዕዋፍም ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከዚህም የምንረዳው እግዚአብሔር በቅዱሳን ቃል ኪዳን እንደሚጠብቀን ነው፡፡

ኢየሩሳሌም በአሶር ንጉስ በሰናክሬም ሠራዊት በተከበበች ጊዜ እግዚአብሔር ለቅዱስ ዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን አስቦ “እግዚአብሔር ስለ እኔም ስለባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ” ያለው በዚህም “የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ ከአሶርም ሰፈር መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ገደለ ማለዳም በተነሱ ጊዜ እነሆ ሁሉ በድኖች ነበሩ” ኢሳ 37፤33-36 ንጉስ ዳዊትም በዘመኑ ስለተሰጠው ቃል ኪዳን ሲገልጽ “የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ… ከእኔም ጋር በሁሉ ነገር ቅንና ጽኑ የሆነውን የዘለአለም ቃል ኪዳን አድርጎአል፡፡” ብሏል፡፡

2 ሳሙ 23፤1-5 የዘላለም በማለትም በቅዱሳን ቃል ኪዳን እረፍተ ዘመን (የዘመን ግድግዳ) የማይገታው ዘለዓለማዊ መሆኑን የተናገረው ስለዚህም ነው “መታሰቢያችሁን የሚያደርገውን ቤተክርስቲያን የሚያንጸውን በስማችሁ እንዲሁ ለተራቆተ የሚያለብሰውን የታመመ የሚጎበኘውን የተራበ የሚያበላውን የተጠማ የሚያጠጣውን ያዘነ የሚያረጋጋውን መመስገኛችሁን የፃፈውን ያፃፈውን ያነበበውን የስማውን ልጆቹን በስማችሁ የሰየመውን በበዓለ ንግሳችሁ ዝማሬ ያቀረበውን እምርላችኋለሁ፡፡ ”እንዳለ በየጊዜው የተነሱትን ቅዱሳን ቃል የሚገባላቸው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
አካላዊ ቃል መምጣቱን የሚናገር አዋጅ ነጋሪውን ቃል ላከ። ከእርሱ በኋላ ለሚመጣው መንገዱን ይጠርግ ዘንድ ጎባጣውንም ያቀና ዘንድ፥ እርሱ ሙሽራው እስከሚመጣ ድረስም እጮኛውን ያዘጋጅለት ዘንድ፡፡ እርሱ በመጣ ጊዜም ዝግጁ ሆና ከውኃው ይወስዳት ዘንድ ለማሰናዳት፡፡

የትንቢት ድምፅ የመካኒቷን ልጅ አስደነቀ! ስለዚኽም ከበረሃው አስደናቂ መልእክት እየተናገረ መጣ፡፡ ‛እነሆ የንጉሥ ልጅ መጥቷል፣ ስለዚህ ቤታችሁ ገብቶ ያድር ዘንድ መንገዳችሁን አቅኑ!’ እያለ ይናገር ጀመር፡፡

ዮሐንስ፡- “ከኋላዬ የሚመጣው ከእኔ በፊት የነበረ ነው። እኔ ድምፅ እንጂ ቃል አይደለሁም፤ ብልጭታ እንጂ ብርሃን አይደለሁም። ከቅዱሳን ብርሃን በፊት የነበረ ኮከብ፥ ከፀሐይ በፊትም የነበረ ብርሃን እርሱ ነው!” እያለ ተናገረ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በበረሃ ውስጥ እያለ «እናንተ ኃጥአን ሆይ እንግዲህ ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱና ንስሐ ግቡ፤ የንስሐ ፍሬም አፍሩ! ስንዴውን ከእንክርዳድ የሚለይ መጥቷልና›› እያለ አሰምቶ ተናገረ፡፡

ድርሳን ዘቅዱስ ኤፍሬም በእንተ ጥምቀት ወዮሐንስ

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​​​🔻 አንድ ምዕመን ንስሐ ከገባ በኋላ የሚከተሉትን በቅደም ተከተል ማድረግ አለበት።

1, የተቀበለውን ቀኖና በትክክል መፈጸም

ቀኖና የግሪክ ቃል ሲሆን መለኪያ ማለት ነው። ካህኑ ለበደለው ምዕመን እንደ ሃይማኖቱ ጽናት ፣ እንደ አእምሮው ስፋት ፤ የሠራውን በደል መጥኖ ቀኖና ከሰጠው በኋላ እንደታዘዘው መፈጸም አለበት። የነነዌ ሰዎች ፣ ት. ዮና 3 ፥1 ። ንጉሡ ህዝቅያስ ፣ ኢሳ 38 ፥ 1 ። ቅዱስ ጴጥሮስ ሉቃ 22 ፥ 54 ። እና ሌሎችም ይቅርታን ያገኙት ፤ በበደላቸው ተጸጽተው በማልቀሳቸውና ንስሃ በመግባታቸው ነው።

በንስሐ ወቅት ፡መሬት ላይ መተኛት ምግብ መቀነስ ፣ ከዓለማዊ ነገሮችና ለመንፈሳዊ ሕይወት ከማይመቹ ጓደኞች መራቅ ያስፈልጋል። በንስሐ ጊዜ እንዳናደርግ ከታዘዝነው ነገር ራሳችንን በመግዛት መቆጠብ አለብን ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ ወደ ድኅነት ከጠራን በኋላ እንደገና ተመልሰን ወደተውነው ድካማችን መመለስ የለብንም። የጊዜውን ሳይሆን የመጨረሻውን ማሰብ አለብን። 2 ጢሞ 4 ፥10 ። መዝ 6፥6 ።

2, በደላችን በንስሐ እንደሚሰረይልን ማመን

ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው በደላችንን ለመደምሰስ ስለሆነ ከበደላችን ሊያነጻን የታመነ አምላክ ነው። ከሠራነው ብዙ ኃጢአት አንጻር የሚሰጠን ቀኖና ትንሽ መስሎ ቢታየንም። ማሰብ ያለብን የራሳችንን በደል ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቸርነት ነው።

ከእኛ በደል የእግዚአብሔር የቸርነት ሥራው እጅግ ይበልጣልና የታዘዝነውን ፈጽመን የቀረውን እንደቸርነትህ ማለት ይገባል። “የታዘዛችሁትን ባደረጋችሁ ጊዜ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን በሉ” ተብለናልና ። ሉቃ 17 ፥ 10።

3, በሥጋውና በደሙ መታተም (መቁረብ)

አንድ የተራበ ሰው እጁን ስለታጠበ ብቻ አይጠግብም። የግድ ምግብ መብላት አለበት። ንስሐ ማለት መታጠብ ፣ ከእድፍ (ከኃጢአት) መንጻት ማለት ሲሆን ፤ ድኅነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት የሚሰጠውን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል ነው። ዮሐ 6፥33።

ብዙዎቹ መቁረብን እንደ ትርፍ ነገርና በዕድሜ የተገደበ (ለሽማግሌ ብቻ) አድርገው ስለሚቆጥሩት ለመቀበል ሲዘጋጁ አይታዩም። ነገር ግን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ቅዱስ ቁርባን የግድ ያስፈልገዋል ። ቀኖና የተቀበልንበት በደላችን የሚሰረየው ሥጋውን ስንበላ ፣ ደሙንም ስንጠጣ ነውና ።

4, ሁሌም ለንስሐ መዘጋጀት

ንስሐ ከገባንና ከቆርብን በኋላ እንደገና በኃጢአት ልንወድቅ እንችላለን። አምለካችን “ለምን ንስሐ አልገባህም እንጅ ለምን ኃጢአት ሠራህ? አይልምና” ሁለተኛ ስንበድል ሀፍረት ሳይሰማንና ከኃጢአት መላቀቅ ካልቻልሁ በየጊዜው የንስሐ አባቴን ከማስቸግር አርፌ ብቀመጥ ይሻለኛል በማለት ፡ ሁሉንም እርግፍ አድርገን እንድተወው ፡ ክፉ ሀሳብ በአምሯችን ሊፈታተነን ይችላል።

ነገር ግን ከንስሐ በኋላ እንደ መላእክት በቅድስና ብቻ እንኖራለን ማለት ሳይሆን “ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል ፤ ሰባት ጊዜ ይነሳል” ምሳ 24፥ 16 ። እንደተባለ ፡ አምላካችን ብንወድቅ ሊያነሳን ፤ ብንጠፋ ሊፈልገን ፤ ብንርቅ ሊያቀርበን ፤ በኃጢአት ብንረክስ ሊቀድሰን (እንደ ባዘቶ ሊያጠራን) የታመነ አምላክ ስለሆነ ተስፋ ሳንቆርጥ ፤ በኃጢአታችን ሳንደበቅ ፤ ዘወትር ለንስሓ መዘጋጀት አለብን። ኢሳ 1 ፥ 18 ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
#ሰኔ_፲፪   በዓለ ተዝካሩ #ለቅዱስ_ሚካኤል ሊቀ መላእክት #ወቅዱስ_ላሊበላ 
#ቅዱስ_ሚካኤል_አፎምያንና_ባሕራንን_ያዳነበት_እለእስክንድሮስ_ቅዳሴ_ቤቱን_ያከበረበትና_የቅዱስ_ላሊበላ_ዕረፍቱ_ነው፡፡

   #ሰኔ_፲፪ #መከበሩ_ስለምንድን_ነው_ቢሉ_
ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር፤ ንሥረ አርያም የሚባል፥ ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፥ ንዑድ ክቡር የሆነ ፥ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው  እንዲሁም  የሌሎችም ቅዱሳን መታሰቢያ ቀናቸው  (ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት) ፡፡ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው  እነርሱም፤
   #share
፠፩. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል፤
፠፪. ባሕራንን ያዳነበት፤
፠፫. የአስተራኒቆስ ሚስት ቅድስት አፎምያን ያዳነበት፤ በዓለ እረፍቷም በዚሁ እለት ነው፤
፠፬. በግብፅ ሃገር ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረበት፤
፠፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት፤
፠ ሐናፄ መቅደስና በሰማያት ያለ ምሥጢርን የተመለከተ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዓለ ዕረፍቱ ነው፤
፠67ኛ ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት ዘእስክንድርያ እረፍቱ ነው፤
፠የእስክንድርያ 6ኛ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ (ወንጌላዊና ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የክርስትና ጥምቀትን ያጠመቀው፥ ዲቁናና ቅስናን የሾመው) እረፍቱ ነው፡፡

ማብራሪያ፤
#፩. ቅዱስ ሚካኤል በፈቃደ እግዚአብሔር ከዲያብሎስ ጋር ተዋግቶ ያሸነፈበት፤ አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት እለት በመሆኑ ነው፡፡ ቀድሞ ከ100 ነገደ መላእክት ኃይላት የሚባሉ የ10 ነገደ መላእክት አለቃ ነበር፤ በዚህች ቀን ግን የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ አጋእዝት የተባሉትንና ሳጥናኤል(ሰማልያል) ይመራቸው ለነበሩት 10 ነገዶች በተጨማሪ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በአጠቃላይ ለሌሎችም 100 (99ኝ) ነገደ መላአክት አለቃ ሁኗል፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡

#፪. ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት፤ ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312 - 326/ በግብፅ ሃገር ንግሥት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ያሠራችውንና ጣዖት ይመለክበት የነበረውን ቤተ ጣዖትን አፍርሶ በቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በታላቅ ክብር ያከበረበት እለት ነው፡፡

#፫. ባሕራንን ያዳነበት
ሊቀ ጳጳሳት እለ እስክንድሮስ የተሠራውን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ከሚያከብሩ ምእመናንን አንዱ የባሕራን አባት ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር፤ በዚህ ሰው ላይ ላይ ጥላቻ ያደረበትና ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጸጋ ጐረቤት ነበረው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር፡፡

    ይህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውም በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ። ሚስቱንም ጠርቶ ‹‹በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመመጽወት ቸል አትበይ! የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ፤ ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት  ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው›› አላት፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር። ይህም ደገኛ ሰው በሰላም ዐረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ። ሚስቱም የመውለጃዋ ሰዓት በደረሰ ጊዜ ታላቅ ጭንቅ ላይ ኾነች እርሷም መልአኩን ቅዱስ ሚካኤል እንዲደርስላት ተማጸነችው በሰላምም ተገላገለች፡፡ መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና ‹‹ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል›› አለ። ያን ጊዜ ያ ባለጸጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ሐዘን ተነካ፤ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።

ብላቴናውም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት፡፡ ባለጸጋው እኔ ጋር ተንከባክቤ ላሳድገው ብሎ ከእናቱ ከተቀበለ በኋላ፤ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው፤ እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።

በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያንን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣውና ወደ ቤቱ ወስዶ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው።  ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን "ባሕራን" ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ፡፡

ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዐሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ጸጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ፡፡ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ። በግ ጠባቂውንም ‹‹ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው፣ ኪራዩንም እከፍልሃለው›› ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው። ባለጸጋውም ገብቶ ጥቂት ካረፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ ‹‹ልጅህ ነውን?›› ብሎ ጠየቀው። በግ ጠባቂውም ‹‹አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው›› አለው። ባለጸጋውም በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም ስላወቀ ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ፤ ይገድለውም ዘንድ ፈለገ፡፡ በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሐሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን ‹‹ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ›› አለው።

ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ ‹‹ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ›› ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ‹‹እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ›› አለው። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ‹‹ይህችን የመልእክት ደብዳቤ ይዞ ወደ አንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው፤ ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ›› የሚል ጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ፤ በአገልጋዩ (በሹሙ)ና በእርሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው፡፡ ለመንገዱም የሚሆነው ስንቅ ሰጥቶ ላከው።
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ 12 ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

#፬. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን፤ ወደፊት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽ ጌታችን የነገረውና የሕንጻዎቹን አሠራር ዝርዝር የነገረው በዚሁ እለት ነው፡፡


ባሕራንም መልእክቱን ለማድረስ ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው፡፡ ባሕራንም ‹‹ከአንድ ባለጸጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እርሱን ለማድረስ ዕገሊት ወደምትባል አገር እሄዳለሁ›› አለው። ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም "እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ?" አለው፡፡ ባሕራንም ‹‹ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹እሺ ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ›› አለው፡፡ ባሕራንም አሳየው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በሞቱ ደብዳቤ ላይ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትዕዛዝ ጽፎበታል፡፡ በደብዳቤው ላይ የተጻፈውን የሞት መልእክት ደምስሶ ‹‹ከእኔ ከባለጸጋ ዕገሌ የተጻፈ›› ይልና ‹‹ይህን መልእክት ይዞ ለመጣሰው ዕገሊት የምትባለዋን ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን ፥ በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና፤ በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በእኔና በአንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ›› የሚል ጽሑፍ ጻፈበት "እንግዲህ ወደ ባለጸጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ አለው፤ ባሕራንም ‹‹እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ›› ብሎ ጉዞውን ቀጠለና የዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።
ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለጸጋውን ልጅ አጋባው፣ የሠርጉንም በዓል እስከ ፵ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ። ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለጸጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ "ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው?" ሲል ጠየቀ፡፡
ሰዎቹም ‹‹ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታ፤ እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ፵ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል›› አሉት። ያም ባለጸጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት። ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር። በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ። ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቈጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን፡፡

#፭. አፎምያን ያዳነበት
ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡
ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጕል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፤ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም ፥ በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኵሴ መስሎ አጋንንትን መነኰሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡

እርሷም ‹‹ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ›› አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም ‹‹እኛማ በነግህ ጸልየናል?›› አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን ‹‹...እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ፥ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ፥ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ›› አላት፡፡ ቅድስት አፎምያም ‹‹አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ፥ አትጸልዩ ያልከኝ፤ ጌታ ምጽዋትን መጽውቱ ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? ርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም፤ ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?›› ብላ ሞገተችው፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡

ከላይ እንዳየነው በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡  ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሰኔ 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?›› በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ
የእውነተኛ ወዳጅ ምክር !

“ጠቢብ እነዚህን ከመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።” [መጽሐፈ ምሳሌ 1÷5]
"እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መሆኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡" በእርግጥ ሁላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሰራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ሆነን ንስሐ ሳንገባም ለማለፍ እንጥራለን ፣ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ደግሞ ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን ታዲያ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

እስኪ ራስህን መርምር ! ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ፣ ጓደኛህ ኃጢአት ሰርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ትክክል እንዳልሆነ እንዲያውቅ ታደርግ ይሆን? ምናልባት እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ጓደኛህ አለ አግባብ ሊቈጣህ ፣ ምን አገባህም ሊልህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትሆነው?

አየህ ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊሆን የሚገባውን መምረጥ አለበት። ስንቆጣው ቁጣችንን ታግሶ የሚጸና ብቻ ሳይሆን እኛም ስናጠፋ የሚያርመን ሊሆን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልሆነ ጓደኝነታችን ጥቅም አይኖረውም ፤ ጓደኞዬ ነው ማለትም ከንቱ ነው። ነገር ግን ልናውቀው የሚገባን አንድ ነገር አለ ! ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው ፣ በሰው ፊት ልናዋርደው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ሁልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መሆን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ሁልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሳ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልሆነ እንዲያውቅ ማድረግም አለብን ምክንያቱም እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡


ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ምን ጥቂት ነገር አለህ?

       ጌታችን እርሱን ተከትለው የወጡትን የአምስት ገበያ ህዝብ(አምስት ሺ አባውራ) አመሻሹ ላይ ሐዋርያት የሚበላ ስለሌላቸው እንዲያሰናብታቸው ጠየቁት።  እርሱ ግን የሚበሉት እንዲሰጧቸው ነገራቸው አሁን ጌታችን ያላቸው ምግብ ለህዝቡ እንደማይበቃ ጠፍቶት አይደለም ነገር ግን ችግራችንን ጉድለታችንን ሊሞላልን ሲፈልግ አስቀድመን ችግራችንን ልንነግረው ይፈልጋልና ሐዋርያቱ ያላቸው ምግብ ትንሽ መሆኑን እንዲነግሩት ነበር ። ወዳጄ አንተስ ችግርህ ምንድን ነው? ልታደርገው አቅደህ አልበቃ ያለህ ምንድን ነው? በአገልግሎት በመንፈሳዊ ህይወት ልትተጋ አስበህ ምን ጎሎህ ነው የነበሩህን እቅዶች ለመሸኘት የተገደድከው? ከቃሉ ከአገልግሎቱ  የራከው ምን አንሶህ ነው? ጊዜ አጥሮህ ነውንን? ትጋት አጥሮህ ነውን? ትዕግስት አጥተህ ነውን? ምንድን ነው ያነሰህ? ብቻ ችግርህን ንገረው እርሱ ያነሰህን ነገር አበርክቶ  ተትረፍርፎህ ታየዋለህ።

           ለጌታችን ሐዋርያት ያለን ሁለት ዓሳና አምስት እንጀራ ብቻ ነው አሉት። አሁን ይህ ምግብ  እንኳንስ ለህዝቡ ይቅርና ጌታችንንና ደቀመዛሙርቱን እንኳን በቅጡ የሚያጠግብ  አልነበረም ነገር ግን ሐዋርያቱ እጅ ላይ የነበረውን  ጥቂቷን ነገር ሠጡት እርሱም ባርኮ አበርክቶ አምስትሺውን ህዝብ አብልቶ 12መሶብ ከተረፈው ተሰበሰበ።

         ወዳጄ እጅህ ላይ ምን አለ? በእጅህስ የያዝከው ምን አለ? ጥቂት ነው ለምንም አይበቃም ያልከው ምናልባት መኖሩንም የረሳኸው ሊሆን ይችላል እርሱን ይዘህ ቅረብ ለእርሱም ስጠው እርሱ ባርኮ መልሶ ይሰጥኻል። ከብዙ የዓለም መባዘን የተረፈህ ትንሽ ጊዜ አለህ እርሱን እስኪ ለእግዚአብሔር ስጠው ያን ይባርክልኻል። ጉልበት አለህ እርሱንም ለእግዚአብሔር ስጠው አገልግልበት እውቀት አለህ እርሱንም ቢሆን ለእግዚአብሔር ስጠው። ያለህን ጥቂት ነገርም ቢሆን ስጠው እርሱ ባርኮ ሲመልስል ትልቅና ካሰብከውም በላይ ነው።እመ ሣሙኤል ሃናን ተመልከት ህፃኑን ሣሙኤል ለእግዚአብሔር ሰጠችው እርሱም በሞገስና በጥበብ አሳድጎ ታላቅ ነቢይ የእስራኤልም አባት ንጉስን ቀብቶ የሚሾም አደረገው ። ኢያቄምና ሃናንም ተመልከት የ3 ዓመት ህፃን እመቤታችንን ሰጡት እርሱም የዓለም እናት አድርጎ ሠጣቸው የወለዷት እናት ሆነቻቸው መርታም ወደ ገነት አስገባቻቸው። አንተም ያለህን ጥቂት ነው የምትለውንም ቢሆን ስጠው ካሰብከው በላይ አድርጎ ይሰጥኻልና። ወዳጄ ሆይ አንተስ ምን አለህ? መቼም ምንም የለኝም አትለኝም ሰጪው እግዚአብሔርን በሐሰት መክሰስ ይሆንብሃልና ቢያንስ ሕይወት አለህ፤ ይህን ጹሑፍ ማንበብህ በራሱ ማንበብ የምትችል በመሆንህ ነው። ልክ እንደዚሁ ሁሉ አንተ መኖሩን እንኳን የረሳኸው ያም ባይሆን ጥቂት ነው ይህማ ለምንም አይበቃም ያልከው ነገር አይጠፋምና እርሱን ይዘህ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ ያ ጥቂት ነው ያልከው ተትረፍርፎ ትመለከታለህ።

ወዳጄ ሆይ ጥቂትም ብትሆን ምን አለህ?

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
+++ ልሸፈንላችሁ? +++

ሙሴ ከሲና ተራራ ወርዶ ከሕዝቡ ጋር ሲገናኝ የፊቱን ማንጸባረቅ አይተው "ተሸፈንልን" ያሉት ሕዝቡ ናቸው። እርሱ "ከእግዚአብሔር ጋር ስነጋገር ቆይቼ እኮ አሁን መውረዴ ነው? ምነው የፊቴ ብርሃን አስቸገራችሁ? ልሸፈንላችሁ እንዴ?" አላለም። እንዲያውም ቅዱስ መጽሐፍ "ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ የፊቱ ቁርበት እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር" ነው የሚለው።(ዘጸ 34፥29) ለቅዱሳን እግዚአብሔር በፊታቸው የሚሥለው የክብር ብርሃን እነርሱን ለሚመለከታቸው እንጂ ለራሳቸው አይታወቃቸውም። እውነተኞቹ ቅዱሳን  "ተሸፈኑልን" የሚባሉ እንጂ "ልሸፈንላችሁ" የሚሉ አይደሉም።

ጥቂት በጎ ሥራ ሠርተህ ጻድቅነትህን በግድ ለማሳየት አትሞክር። ሌሎች ተሸፈንልን ይበሉህ እንጂ፣ አንተ ራስህ "ልሸፈንላችሁ" እያልህ የዋሐንን አታስጨንቅ።

በአገራችን የሚታወቅ ተረት አለ። አንድ ጊዜ ትንኝ በሬ ቀንድ ላይ ቆመችና "ከብጄህ እንደ ሆነ ንገረኝና ልነሣልህ" አለችው። በሬውም "እንኳን ልትከብጅኝ መኖርሽንም አላወቅሁም" አላት።

"ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው"   ሉቃስ 18፥9
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
          
#ሰው_ሆይ!

በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ " በማለት ተናገር።
አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስኪ ከፍ ካለው ተራራ፣ ከታላቁ ባህር፣ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ 4፥4)

ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን?

ከአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ -
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
+ ምልጃ ለምን ያስፈልጋል +

#የእግዚአብሔርን_ብዙኅ_ምሕረት_ብዛት_ እንድናውቅ ፦

እግዚአብሔር ከበደል በኋላ የሚጸጸት ሰው አለ የማይጸጸትም አለ እንደ በደለ አያውቅምና ። እንደ በደለም እያወቀ ልቡናውን የሚያገዝፍ አለ ። ሰው እንደበደለ በተሰማው በደሉም በቆረቆረው ጊዜ እግዚአብሔርን ይለመናልና ። ሲለምን ግን እግዚአብሔር እንዲሞረው የሚያሳስቡ ከእርሱ የተሻሉትን የሚበልጡትን እግዚአብሔር ደስ የሚያሰኛቸውን ሰዎች በማሳሰብ ነው ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ምሕረት ተሰፍራ የምትለካ ስላልሆነች ደጋጎቹን ባሰበ ጊዜ ብዙኅ ምሕረቱ ስለሚፈስስ ኃጥአንም ይቅር ይባላሉና ።

#እነ ሙሴ እነዳዊት ስለ እስራኤል ሲለምኑ በደጋጎቹ በኩል አድርገው ነበር ፤ ቅዱሳኑ በአካለ ስጋ ባይኖሩም እንኳን ስለ እነርሱ የሚያደርገው ምሕረቱ በዘመን የማይገታ በመኾኑ ።

"....ዘራቹሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ ይኽችንም የተናገርኳትን ምድር ኹሉ ለዘራቹሁ እሰጣለሁ ለዘለዓለም ይወርሷታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪዎችሆን አብርሃምንና ይሰሐቅን እስራኤልንም አስብ። እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ላያደርግ ስላሰበው ክፍት ራራ። " ዘጸ.32፥13-14  ተብሎ እንደ ተጻፈው በዘመን የማይገታ የእግዚአብሔር ምሕረት በእስራኤል በደል ሳይገደብ በዝቶ የተደረገው ሙሴ አብርሃምን እና ይስሐቅን እስራኤል የተባለ ያዕቆብን አንስቶ ስለ ማለደው ነው ።

ሙሴ የእግዚአብሔር ብዝኅ ምሕረትን በቅዱሳን ስም የሚማለድ መኾኑን ስለ አወቀ አደረገው እንጂ እኔ በቃለሁ አላለም ስለዚህ እግዚአብሔር ምልጃን የፈቀደው በዘመን የማይገታ ምሕረት ያለው መኾኑን አውቀን እንድንጠቀም ነው ። "ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ ለአብርሃም ለዘሩ የዘላለም ምሕረቱን አስቦ እስራኤልን ብላቴናውን ረድቷል ።" ሉቃ 1፥55 እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር በቅዱሳኑ በኩል ዘለዓለማዊ ምሕረትን አድርጓል ። ክብሩ ፣ ገናንነቱ ፣ ጌትነቱ የሚታወቀው በእነርሱ ስም በማለድነው ጊዜ ነው ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ማስታወቂያ

መምህር ይትባረክ ጋሻው ከፍተኛ የባህል ፈውስ መድህኒት አዋቂ እና ቀማሚ  ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦ በውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
0917468918
0917468918
1 👉ለመፍትሄ ሀብት
2 👉ለህማም
3 👉ለመስተፋቅር
4 👉ቡዳ ለበላው
5 👉ለገበያ
6 👉የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 👉ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 👉ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 👉ለዓቃቤ ርዕስ
10👉ለመክስት
11 👉ለቀለም(ለትምህርት)
12 👉ሰላቢ የማያስጠጋ
13 👉ለመፍትሔ ስራይ
14 👉ጋኔን ለያዘው ሰው
15 👉ለሁሉ ሠናይ
16 👉ለቁራኛ
17 👉ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 👉ለመድፍነ ፀር
19 👉ሌባ የማያስነካ
20 👉ለበረከት
21 👉ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 👉አፍዝዝ አደንግዝ
23 👉ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 👉ለግርማ ሞገስ
25 👉መርበቡተ ሰለሞን
26 👉ለዓይነ ጥላ
27 👉ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 👉ለሁሉ መስተፋቅር
29 👉ጸሎተ ዕለታት
30 👉ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 👉ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 👉ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 👉ለድምፅ
34 👉ለብልት
35 👉በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ
0917468918
0917468918

      💚💛❤️ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 💚💛❤️
🌼🌻🌼🌻
👉የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ ሙሉ ስማቸውን ብቻ በመላክ በምንሰራው ስራ በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንሰጣለን ለዚህም ብዙ ምቅክሮች አሉ
👉ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
👉ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
👉ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
👉ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምንሰራው ሰራ ደፋርና በራስ የመተማመን ችሎታ እንዲኖሮት እናደርጋለን
👉ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
👉ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
👉ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
👉ትምህርት አልገባ ላለው ቶሎ የመርሳት ችግር ላለበት በሚደገም እና በሚነበብ ፅሁፍ ብቻ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ስራ እንሰራለን
👉መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
👉ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን  💚💛❤️      
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ ያማክሩን ያስተውሉ እኛ ምንሰራው በጥንታዊው ከአባቶቻችን በተማርነው ጥበብ ብራናውን አንብበን እፅዋትን ቀጥፈን አዘጋጅተን ነውና ሀገራችን ካሏት ጥበብ ጥቂቱ ነው እንኳን ለነዚህ እና አባቶቻችን በደመና ይሄዱ አልነበር እፀመሰውር ሰርተው እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር እኛ ጥበብ ንቀን ፈረንጅ አምላኪ ሆነን ነው እንጂ ጥበቡ አሁንም አለ ይምጡ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር በሜሴጅ በውስጥ መስመር ይፃፉልኝ ወይም በቴሌግራም መሪጌታ ይትባረክ ጋሻው ብላችሁ ታገኙናላችሁ
ወይም በስልክ ቁጥር ይደውሉልን
0917468918
0917468918
#ሰኔ_21

#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም (ህንጸተ ቤተክርስቲያን)

ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው።

ከሁሉ አስቀድሞ ያቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች።

ይኸውም ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ከሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያንም አልነበራቸውም ነበር። ስለዚህም ወደ ጴጥሮስና ወደ ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልእክትን ላኩ።

ሐዋርያትም እንዲህ ብለው መለሱላቸው ክብር ይግባውና ያለ ጌታችን ፈቃድ እኛ ምንም ምን አንሠራም። ነገር ግን የምንሠራውን እስኪያስረዳን ድረስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩና እየማለዱ አንድ ሱባኤ ይጾሙ ዘንድ ወደ ሃይማኖት የተመለሱ አሕዛብን እዘዙአቸው እንዲህም አዘዙአቸው።

በሱባዔውም ፍጻሜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጸላቸው ሐዋርያትንም ሁሉ ከየአገሮች ሁሉ እስከ ፊልጵስዮስ በደመና ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ጋር ጳውሎስና በርናባስ ነበሩ ጌታችንም ባረካቸው እንዲህም ብሎ ነገራቸው "ይቺ ዕለት በእናቴ በማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት እንድታንፁ የፈቀድኩባት ናት።"

ይህንንም ብሎ ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ በኲል አወጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱንም ቦታና መሠረቷን ወሰነላቸው ከእርሳቸውም ጋራ የእግዚአብሔር ኃይል ነበረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ እስከ ተፈፀመ ድረስ ደንጊያዎች በሐዋርያት እጆች ውስጥ ይለመልሙ ነበረ ጌታችንም ነዋየ ቅድሳቷን አልባሳትዋንና መሠዊያዋን አዘጋጀ።

ከዚህ በኋላ ጌታችን እጁን በጴጥሮስ ራስ ላይ ጭኖ በአራቱ ማእዘነ ዓለም ውስጥ "አርሳይሮስ" ብሎ ሾመው ይህም "ሊቀ ጳጳሳት" ማለት ነው። ለሐዋርያት አለቃ ጴጥሮስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የጳጳሳት አለቃ ይሆን ዘንድ ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል እያሉ ሰማያውያን መላእክትና ምድራውያን ሰዎች ሦስት ጊዜ አሰምተው ተናገሩ።

ከዚህም በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን የቊርባኑን ቅዳሴ ሥርዓት ያከናውኑ ዘንድ ለሕዝቡም ሥጋውን ደሙን ያቀብሏቸው ዘንድ አዘዛቸው እንዲህም የሚል አለ ራሱ መድኃኒታችን ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት አቀበላቸው። እንዲህም አላቸው በዚች ቀን የእጃቸውን ሥራ እንዳይሠሩ ሕዝቡን ሁሉ እዘዙአቸው ይኸውም በሰኔ ወር ሃያ አንድ ቀን ነው።

ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ከእርሳቸው ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚያችም ቀን ጀመሮ አባቶቻችን ሐዋርያት በዓለሙ ሁሉ ውስጥ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን የሚያሳንፁ ሆኑ።

በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውስጡ የእመቤታችን የማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት።

ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ ባለጸጋውም ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም። ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ ልጆቹም ፈሩ ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና እንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት።

ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የእመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዓሊ ሰጠው። እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ ላይ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛ ሰው እጅ ወስዶታልና። እጅግም ያማረ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ ያንንም ሠሌዳ አገኘው ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው።

ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳቸው እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው በላያቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ አፈለቀ በውስጥዋም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ።

እንዲሁም ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ ይህ ሁሉ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ወር በሃያ አንድ ቀን ነው።

በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ አላት በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት እርሷ የረከሰች ስትሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።

እኛ ሁላችን የክርስቲያን ወገኖች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም ለመታሰቢያዋ መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል ሰለ እርሷ ለአዳምና ለሁላችን ለልጆቹ ድኅነት ሆኖአልና ይህንንም በዓል ለማድረግ የሚተጋ የተመሰገነ ነው።

እርሷን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እንድትወልደው ላደረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእርሷ በእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ ➛ ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ፔጅ የተወሰደ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
2025/06/29 02:35:03
Back to Top
HTML Embed Code: