Forwarded from Dr Million B
Forwarded from Dr Million B
ጥብቅ ማሳሰቢያ

በደንብ ፁሁፉን ሳያነቡ ወይም የመልእክቱ ሀሳብ ሳይረዱ ጥያቄ አልያም ምንም አይነት ኮመንት ባይሰጡን ይመረጣል ነገር ግን ሀሳቡን ሳይረዱን ለእናተ አስተማሪ ነው ብለን ነጨንቀን የምናካፍላችሁ የጤና መረጃ በደንብ አለማንበብ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ስለተደጋገሙብኝ ነው እና ይህንን ስላችሁ ከታላቅ ይቅር ጋር ነው በደንብ ካነበቡ በኋላ የጠየቃችሁንን ጥያቄ በአግባቡ እናስተናግድችሁለን

ሰላም ሰላም እደምን አመሻችሁ የተከበራችሁ የገፃችን ተከታዮች በእናተ ጥቆማ በተነሳ ስለ ማይግሬን ሰፋያለ ማብራሪያ ይዤ ቀርቤላችሁለው በጥሞና ያንብቡት ፁሁፉ ትንሽ እረዘም ስለሚል እዳትሰላችሁ መልካም ንባብ

📍 በዚህ ህመም ለሚሰቃዩ ሁሉ መልካም መረጃ ነውና ሼር ያድርጉት!

• ማይግሬን ምንድን ነው? (ከፍተኛ ራስ ምታት)
📍ማይግሬን ከፍተኛ እና በተደጋጋሚ የሚከሰት ራስ ምታት ነው። የተለያዩ ምክንያቶችን ተከትሎ የሚነሳ እና እነዚህ ምክንያቶች ሲወገዱ ደግሞ የሚቀንስ በሽታ ነው፡፡
📍 የነዚህ የደም ስሮች እብጠት በዙሪያቸው ከሚገኙ ነርቮች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንዲለቁቀ ያደርጋል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ እነዚህ የተመረቱ ንጥረ ነገሮች አእምሮአችን ለህመም ያለውን ስሜት ከፍ ያደርጉታል፡፡ በመሆኑም ለትንሽ የህመም መንስኤ ከፍተኛ የህመም ስሜት እንዲሰማ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ የሚመጣ ህመምም ወጋ ወጋ የሚያደርግ አይነት ነው፡፡

• በየትኛው እድሜ ይከሰታል ?
📍 ይህ በሽታ ከ40 አመት በፊት ይጀምር እና ከ60 በላይ ሲሆኑ በተለይ በሴቶች ዘንድ ይቀንሳሉ እስከመጥፋትም ይደርሳል፡፡ በዚህ በሽታ ህፃናት ተጠቂ ሊሆኑ ቢችሉም በብዛት ግን አይታይባቸውም፡፡ ምንም እንኳን ፈውስ የሌለው በሽታ ቢሆንም በተለያዩ መድሃኒቶች እና የአኗኗር ዘይቤዎች ልትቆጣጠረው ትችላለህ፡፡

•የማይግሬን ምልክቶች ምንድናቸው ?

📍 ከፍተኛ የሆነ በተደጋጋሚ የሚነሳ እና በመሃል እረፍት የሚሰጥ አይነት የራስ ምታት የመጀመሪያው ምልክት ነው፡፡ህመሙ ቀስ በቀስ የሚጨምር ሲሆን ከእቅልፍህ ስትነሳ እያመመህ ከሆነ ግን ከፍተኛው የህመም ደረጃ ላይ ልታገኘው ትችላለህ፡፡
📍📍📍 በጭንቅላትህ ግማሽ ክፍል ብቻ የሚኖር ህመም የተለመደ መገለጫው ሲሆን ከግራ ወደቀኝ (ወይም በተቃራኒው) እያለ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ክፍልን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ህመሙ ከአራት ሰአት እስከ ሁለት እና ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከጭንቅላት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ይባባሳል፡፡ ሰውነትህን ሁሉ ከመክበድ ባለፈ ሊያስመልስህም ይችላል፡፡ በተጨማሪም ለሽታዎች፣ ለድምፅ እና ለብርሃን ያለህን ስሜት ይጨምራል፡፡
📍ህፃናት ላይም ተመሳሳይ ምልክቶች ሲኖረው የሚቆይበት ጊዜ ግን አጠር ይላል ይህም ከግማሽ ሰአት እስከ አንድ ቀን ቢሆን ነው፡፡
📍 ራስ ምታቱ ከመምጣቱ አስቀድሞ የሚታዩ ምልክቶች አሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ሁሉም ህመምተኞች ላይ የሚከሰቱ ባይሆኑም ለሚታዩባቸው ሰዎች ግን ማይግሬን ሊነሳባቸው እንደሆነ ጥሩ ማመላከቻዎች ናቸው፡፡ በአማካይ ከአንድ ቀን በፊት በጣም ንቁ የመሆን በአንዳንዶች ላይ ደግሞ ቶሎ የመድከም ፣ የመናደድ፣ ጣፋጭ ምግቦችን የመፈለግ እና የመሳሰሉ ባህሪዎችን ያሳያሉ፡፡ የአይን ብዥታ፣ የእጅ ጣት መጠዝጠዝና መደንዘን፣ የንግግር መጓተት የመሳሰሉት ምልክቶች ማይግሬን ከመምጣቱ ከጥቂት ደቂቃወች በፊት ይታያሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ከታዪ በኋላ ማይግሬን ሊከተል ወይም ደግሞ ምንም እንኳን ያልተለመደ ቢሆንም ማይግሬኑ ላይከሰትም ይችላል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ራስ ምታቱ ሊነሳ እንደሆነ አስቀድመው ያውቃሉ፡፡ ማይግሬኑ ከሄደ በኋላም ድካም፣ ቶሎ መናደድ፣ መደበት ብሎም የተለያዩ የቆዳ ክፍሎችህን መበለዝ ልታስተውል ትችላለህ፡፡
•የማይግሬን መንስኤዎች ምንድን ናቸው ?
ከ 50% በላይ የሚሆኑ በማይግሬን የተያዙ ህመምተኞች ከቤተሰባቸው ይወርሱታል፡፡ ስለዚህ በቤተሰብሽ ውስጥ የማይግሬን በሽተኛ ካለ በተለይ ደግሞ እናት፣አባት፣እህት፣ወንድም በዚህ በሽታ ተጠቂ ከሆኑ አንቺም በበሽታው ተጠቂ የመሆን እድልሽ ይጨምራል፡፡ በሽታው ከተለያዩ ሆርሞኖች ጋር ተያያዥነት ስላለው ሴት መሆን በራሱም በበሽታው የመጠቃት እድልን በትንሹ ይጨምራል፡፡
•ማይግሬንን የሚቀሰቅሱ ምክንያቶች ምንድናቸው?
📍📍📍 የተለያዩ በሽታዎች በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚነሱ ሁሉ ማይግሬንም የራሱ ቀስቃሽ ምክንያቶች አሉት፡፡ ከነዚህ መካከል ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰው ጭንቀት ነው፡፡ ጭንቀት በራሱ ራስ ምታትን የሚያመጣ ሲሆን ማይግሬን ላለበት ሰው ግን ዋና ቀስቃሹ ነው፡፡
ረሃብ፣ የፈሳሽ ምግብ ብቻ ተመጋቢ መሆን ወይም የተዘበራረቀ የምግብ ፕሮግራም በሽታውን ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡ አልኮል መጠጦች፣ ኮምጣጣ ምግቦች፣ ቸኮሌት እና ቺዝ የመሳሰሉ ምግቦች በሽታንውን ያሰነሳሉ፡፡ ብዙ ወይም ትንሸ እንቅልፍ፣ የአየር ሙቀት ለውጦች፣ ሀይለኛ ሽታ፣ፀሃይ፣ ከፍተኛ ድምፆች በሽታውን ከሚያስነሱ ምክንያቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
በሴቶች በኩል ደግሞ የወር አበባ ኡደትን ተከትለው የሚጨምሩ እና የሚቀንሱ የሴት ሆርሞኖች ይህንን በሽታ ያባብሱታል፡፡ በተለይ የወር አበባሽ በሚመጣበት ጊዜ በሽታው ከድሮው በበለጠ ይጨምራል፡፡ ስለዚህም አንድ ሴት ስታርጥ የማይግሬን በሽታዋ ከመቀነስ አልፎ ሊጠፋም ይችላል፡፡ እርግዝናም የራሱ የሆነ ለውጥ ያስከትላል፡፡
•ማይግሬንን እንዴት ልከላከል?
📍📍📍 ማይግሬን የማይድን በሽታ ቢሆንም የሚከሰትባቸውን ጊዜያት ለመቀነስ የተለያዩ ነገሮች ማደረግ ትችያለሽ፡፡ በሽታውን ምን እንደሚያስነሳብሽ ለይተሸ ማወቅ እና ከነዚህ ነገሮች እራስሽ መጠበቅ የመጀመሪያው እና ዋናው ተግባርሽ ሊሆን ይገባል፡፡ ራስ ምታቱ በሚጀምርሽ ጊዜ መቼ እንደጀመረሽ፣ ህመሙ ሀይለኛ ወይስ ለዘብ ያለ እንደነበር፣ መድሃኒት ወስደሽ ከሆነ የወሰድሽውን መድሃኒት፣እና ሌሎች ምክንያቶችን በመፃፍ እና በተለያዩ ጊዜያት የወሰድሻቸውን ማስታወሻዎች በማመሳከር ምክንያቶቹን በቀላሉ ማወቅ ትችያለሽ፡፡

📍📍📍 ከዚህ በተጨማሪ የአኗኗር ዘይቤሽን መቃኘት ተገቢ ነው፡፡ጭንቀትን ማስወገድ፣ ምግብ በሰአቱ መብላት፣ እንቅልፍ በልኩ መተኛት፣ አልኮል መጠጦችን ማስወገድ እና ከላይ የተጠቀሱ ምግቦችን ባለመብላት ራስ ምታቱን መቀነስ ትችያለሽ፡፡ የተለያዩ ረጋ ያሉ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን መስራት እና እራስን ከማዝናናት በተጨማሪ ደረቅ መርፌ (acupuncture) መጠቀምም ሊረዳሽ ይችላል፡፡

•ራስ ምታቱ ከጀመረኝ በኋላ ምን ላደርግ እችላለሁ?
አንዴ ራስ ምታቱ ከጀመረህ በኋላ መድሃኒት በመውሰድ ፀጥ እና ጨለም ያለ ቦታ ላይ እረፍት አድርግ፡፡ ቀዝቃዛ ነገር ለምሳሌ በፎጣ የተጠቀለለ በረዶ ግምባርህ ላይ ማድረግ እንዲሁም ቡና መጠጣት ሊረዳህ ይችላል፡፡
• የማይግሬን ህክምና ምንድን ነው?
ምንም እኳን በሽታው የማይድን ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ብዙ መድሃኒቶች እየተፈበረኩ ሲሆን ከብቃታቸው አንፃር ስናይም በጣም ጥሩ ናቸው፡፡ አንዳዶቹ ራስ ምታቱ ከመጀመሩ በፊት የሚከላከሉ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ህመሙ ከጀመረ በኋላ ህመሙን የመቀነስ ስራ ይሰራሉ፡፡ ነገር ግን መድሃኒት ከመጀመርሽ በፊት ሀኪምሽን ማማከር አለብሽ፡፡
Forwarded from Dr Million B
Vacancy by Hayat Hospital Medical College Plc:-

1. Position: Matron

Education: BSc Degree in Nursing with proven similar working experience, out of which 3 years as a matron in well known hospital

Minimum Experience: 3 Years


2. Position: Druggist

Education: Diploma in Pharmacy or related fields with proven working experience as a druggist

Quantity Required: 2

Minimum Experience: 2 Years


3. Position: Senior Clinical Nurse

Education: BSc Degree or Diploma in Clinical Nursing or related fields with relevant work experience

Quantity Required: 3

Minimum Experience: 5 Years

Location: Addis Ababa

Deadline: November 2, 2021

How To Apply: In person at Hayat Hospital Medical College, located in Bole area, in front of Moenco, to Human Resource Team Office. For further information contact Tel. 0900464646 / 0116614250
የግል ሐኪምዎ

በስትሮክ የመሞት አደጋን ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል!!!

👉ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል!

በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት እየተመረተ ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል።

ብዙዎቻችን ሙዝን ለምግብነት በማዋል ለሰውነታችን ሃይልና ሙቀት ለማግኘት እንደምንችል ከማወቅ የዘለለ ነገር አስበን አናውቅም፡፡ ነገር ግን ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሮአዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ፣ ስክሮስ፣ እና ፍሩክቶስ የተባሉት ንጥረነገራት ከሙዝ የፋይበር (የቃጫነት) ተፈጥሮ ጋር ተዳምረው መጠነሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ።

ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡

1. ለአእምሮ እድገት
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ የፖታሺየም ንጥረነገርን ይዟል፡፡ ይህም ንጥረ ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ንቁና ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

2. ለስትሮክ
በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡

3. ለደም ግፊት
ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ የሚይዘው ዝቅተኛ የጨው መጠን በመሆኑ የደም ግፊትን ለማረጋጋት ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ ያለው ፖታሺየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

4. ለጨጓራ ህመም
አብዛኛዎቻችን ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ በማሰብ፣ ሙዝ የጨጓራ ህመማችንን እንደሚያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ሙዝ ለጨጓራ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሙዝ በባህርይው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን በመሸፈን፣ የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ ያስችላል፡፡

5. ለድብርት
ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የባለ ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
ይህ ሆርሞን አይነተኛ ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ ማድረግ ነው፡፡

6. ለሆድ ድርቀት
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት ሥርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ የምግብ መፍጨት ሥርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ ሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው አላስፈላጊ ነገሮች (ቆሻሻዎች) እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡

7. ለስኳር ህመም
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ቫይታሚን B6 የያዘ ነው። ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ያስችለናል፡፡ ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጠዋት ህመምንም ያስቀራል፡፡

8. ሙዝና ደም ማነስ
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይህም በሔሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡

9. ሙዝ ለስካር
ሙዝ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስካር ሳቢያ የሚከሰትን ሃንግኦቨር (ያደረ ድምር) በቀላሉ ያስወግዳል፡፡ በመጠጥ ሳቢያ የተጐዳን ሰውነት እንዲነቃቃና ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ የሲጋራ እና መሰል ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ ሙዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

10. ለሞቃታማ አየር
በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀቱን እንዲቋቋም በማድረግ፣ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡

11. የሙዝ ተጨማሪ ጠቀሜታዎች
በወባ ትንኝ የተነደፈ ሰው ወይንም በማንኛውም ተናካሽ ወይም ተናዳፊ ነፍሳት የተነደፈ (የተነከሰ) ሰው በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ክፍል የተነደፈበትን (የተነከሰበትን) ቦታ በደንብ በማሸት እብጠቱን መቀነስ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ንድፍያው (ንክሻው) የፈጠረበትን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ለማስወገድ ይችላል፡፡

👉 ጫማዎን ከጠረጉና ቆሻሻውን ካስወገዱ በኋላ በሙዝ ልጣጭ ቢወለውሉት ጫማዎ እንደመስታወት ያበራልዎታል።

👉 ፍሪጅዎ መጥፎ ጠረን (ሽታ) ካመጣብዎ አንድ ሁለት ሙዞችን ያስቀምጡበት፡፡ የፍሪጅዎ ጠረን በቅጽበት ይቀየራል፡፡

👉 ሰውነትዎ በድካም ወይም በህመም ከተጐዳና የምግብ ፍላጐት ከሌለዎ አንድ ሙዝ እንደምንም ይመገቡ፡፡ ሰውነትዎ ሲበረታና የምግብ ፍላጐትዎ ሲጨምር ይታወቅዎታል፡፡

በአጠቃላይ ሁላችንም እንደቀላል የምናየውና ብዙም ትኩረት የማንሰጠው ሙዝ ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚዳርጉንን በሽታዎች ለመከላከልና ለማስወገድ ይረዳናል፡
ስለ ራስምታት ምንነት፣ መንስኤና መፍትሄው ፡-
.
ራስ ምታት በአብዛኛው በራሱ በሽታ ከመሆን ይልቅ የሌላ በሽታ መገለጫ ነው፡፡

ብዙ የራስ ምታት አይነቶች ቢኖሩም ሁሉም አንድ የሆነ መለያ አላቸው፡፡
ይኸውም ህመም ማስከተላቸው ነው፡፡
አንዳንዶቹ በራስ ህመም ብቻ ሲያቆሙ ሌሎቹ ደግሞ እንደ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ የመሳሰሉትን ያስከትላሉ፡፡

ራስ ምታት በብዛት አደጋ የሌለውና በቀላሉ ልትከላከለው የምትችለው ነገር ነው፡፡

የራስ ምታት መነሻ ምክንያቶች -
• መጠጥ ወይም አልኮል ( በተለይ ቀይ ወይን)
• የእንቅልፍ ማጣት
• ጭንቀት
• ድንገተኛ የሳይነስ ኢንፌክሽን
• በጭንቅላት ዉስጥ ደም መርጋት
• በጭንቅላት ዉስጥ የደም ቧንቧ መወጠር
• የጭንቅላት ዉስጥ ዕጢ
• በካርቦን ሞኖክሳይድ (ከሰል ጭስ) መመረዝ
• የፈሳሽ ዕጥረት
• የጥርስ ችግር
• የጆሮ ኢንፌክሽን
....ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
>> የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባን -
የራስ ምታት እንደ ስትሮክና የማጅራት ገትር ለመሳሰሉ በጣም አደገኛ/ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር ሊያመጡ ለሚችሉ ህመሞች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
ስለሆነም በህይወትዎ አይተዉት የማያዉቁት የራስ ምታት ስሜት፣
በድንገት የመጣና ከፍተኛ የራስምታት አይነት ካለዎና የሚከተሉት ምልክቶች ከራስምታቱ ጋር ተያይዞ ካለዎ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ድንገተኛ የህክምና መስጫ ተቛም ባስቸኳይ መሄድ ይገዎታል፡፡
>> አስጊ ደረጃ የሚደርሰው -
- ምንም እንኳን በተደጋጋሚ ማስታገሻ ብትወስድም ከመሻል ይልቅ እየባሰ ከሄደ፣
- ከአንድ ሳምንት በላይ ከቆየ
- ለመጀመሪያ ጊዜ ሃይለኛ ራስ ምታት ሲያምህ ከሃምሳ አመት በላይ ከሆንክ
- ከዚህ በፊት የነበረውን አይነት ቀይሮ አዲስ ፀባይ ካመጣ፣
- ህመሙ ከየእለት ኑሮህ የሚያስተጓጉልህ ከሆነ፣ ለምሳሌ ስራ ለመስራት የማያስችል አይነት ህመም ካለህ፣
- ከራስ ምታቱ በተጨማሪ የተለያዩ የበሽታ ምልክቶች ለምሳሌ....
ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ ካለ
• እራስን መሳት
• የመቀበጣጠር ወይም የሰዎችን ንግግር መረዳት ያለመቻል
• ከፍተኛ ትኩሳት
• ባንድ በኩል ያለዉ የሰዉነት ክፍልዎ የመደንዘዝ፣
የመስነፍ ወይም ሽባ ከሆነ
• የአንገት ያለመታጠፍ ችግር ካለዎ ( Stiff neck)
• የዕይታ ችግር
• የመናገር ችግር
• የመራመድ ችግር
• ማቅለሽለሽና ትዉከት
.........የመሳሰሉት ከታዩን ወደሆስፒታል ወደ ህክምና መሄድ የግድ ነው
መፍትሄው
• በቂ እንቅልፍ ማግኘት፡-
በእያንዳንዱ ሌሊት በቂ እንቅልፍ ለማግኘት መቻል ነዉ እንጂ ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ መተኛት የለብዎትም፡፡ ሁሌም ቢሆን ወደ አልጋ ለእንቅልፍ የሚሄዱበትና ሲነጋ የሚነሱበት ሰዓት ተመሳሳይ ቢሆን ይመረጣል፡፡
• እረፍት ማድረግና ዘና ማለት፡-
ያለው ራስምታት ሚግሬይን ከሆነ ከተቻለ ፀጥ ያለና ጨለማ ክፍል ቢያርፉ ይመረጣል፡፡
Forwarded from Dr Million B
#AmharaRegion

የጠቅላላ ሀኪም የቋሚ ቅጥር ፦

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ስር ባሉ ጤና ተቋማት ጠቅላላ ሀኪሞችን መድቦ ማሰራት ይፈልጋል።

👉 የስራ መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም
👉 ደመወዝ - 9,056 ብር (ዘጠኝ ሺ ሃምሳ ስድስት ብር)
👉 ብዛት - 631 (#ስድስት_መቶ_ሰላሳ_አንድ)
👉 የስራ ቦታ - በክልሉ ባሉ የጤና ተቋማት ክፍት ቦታዎች
👉 ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት - በጠቅላላ ሀኪም የመጀመሪያ ዲግሪ እና 0 (#ዜሮ) ዓመት የስራ ልምድ
👉 የሞያ ፍቃድ ያለው / ያላት

የመመዝገቢያ ቦታ በአብክመ ጤና ቢሮ እና በሁሉም ዞን ጤና መምሪያዎች ማስረጃዎቻችሁን ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

የዞን ጤና መምሪያዎች ምዝገባው ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሶፍት ኮፒ እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. በማንኛውም ጤና ተቋም ዕጣ በደረሰው ቦታ ላይ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች
2ኛ. ከዚህ በፊት በመንግስት ጤና ተቋም በቋሚ ቅጥር ያልተቀጠረ/ያልተቀጠረች
2025/06/29 04:15:40
Back to Top
HTML Embed Code: