Telegram Web Link
በአያት ሪል እስቴት ግንባታ ላይ እየደረሰ ያለው ተደጋጋሚ አደጋ እጅግ አሳሳቢ ነው። የብዙ ንጹሃን ሠራተኞች ሕይወት እየጠፋ ነው።

ዛሬ ደግሞ...

ዛሬ ረፋድ ላይ በሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ በሚገኘው አያት ሪል እስቴት ግንባታ ላይ ሁለት ሠራተኞች ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወታቸው አልፏል።

አደጋው የደረሰው በልስን ሥራ ላይ ሳሉ የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦ በመበጠሱ ነው። ከወደቁት ውስጥ አንዱ በቅጽበት ሲሞት፣

ሌላኛው በከባድ ጉዳት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ነበር። ከሕንጻው ሥር ይጎዝ የነበረ አንድ ሠራተኛም በወደቀው ዊንች ተመትቶ ወዲያው ሕይወቱ አልፏል።

ተደጋጋሚው አደጋ:-

* ትናንትና: ሁለት ሠራተኞች ሕይወታቸው አልፏል፣ ሁለት ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

* ከትናንት በስተያ (ሐሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም): ሁለት ሠራተኞች ሕይወታቸው አልፏል፣ ሦስት ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የሠራተኞች ስጋት:-

በግንባታው ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች እንደሚሉት፣ በየሳምንቱ አንድ ወይም ሁለት ሠራተኞች ተመሳሳይ አደጋ ይደርስባቸዋል።

የሪል እስቴቱ የሠራተኞችን ደህንነት እንዲያረጋግጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ አሳዛኝ ክስተት በግንባታ ቦታዎች የሠራተኞች ደህንነት ምን ያህል ችላ እንደተባለ ያሳያል።

ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ፣
ይህን የመሰለ የሕይወት መጥፋት ይቀጥላል።

ለሟቾች ነፍስ ይማር፣

ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እንመኛለን።


https://www.tg-me.com/engineer03
2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአርማታ ብረት /ፌሮ/ ኪሎ ግራም ለማወቅ!!!
https://www.tg-me.com/engineer03
4👍1
2017 4th Quarter Constraction Works Item Direct Cost (1).pdf
22.3 MB
የ2017 4ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት

Source :
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

You can compare with
https://www.tg-me.com/engineer03
3
#አስቸኳይ
2 ሰው ፎርማል ይፈለጋል!!! #location Addis Abeba

Contact
@A_B_C_D_E_F_G_H_J_K
Civil Engineering
#አስቸኳይ 2 ሰው ፎርማል ይፈለጋል!!! #location Addis Abeba Contact ➥ @A_B_C_D_E_F_G_H_J_K
#No More time sorry.
Just send your
➥CV
➥documents
➥Living area?
And
➥Expecting sales you want ?
⚡️ያለፈቃድ የግንባታ ዲዛይን ማስፋፊያ ለሚያደርጉ አካላት በየእርከኑ የ100 ሺሕ ብር ቅጣት ተጣለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረገው የቅጣት ማሻሻያ በሕንፃ ግንባታ ህግጋት መሰረት በተጣለው የህንፃ ደህንነትና ተያያዥ ቅጣት በተለያዩ ተግባራት ከ15 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን ገልጿል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው የባለስልጣኑ መረጃ እንዲሚያስረዳው፥ የማስፋፊያ ሥራ የዲዛይን ማሻሻያን ስለሚፈልግ፣ ያልተፈቀደ ግንባታ የዲዛይን ጥራት ስለሚጎድለው የመደርመስ አደጋ ስለሚያስከትል ያለፈቃድ የማስፋፋት ሥራ ማከናወን (በየእርከኑ) 100 ሺሕ ብር ያስቀጣል።

እንዲሁም፣ ጥራት ያለው ስካፎልዲንግ፣ ሾርኒንግና መሰል መሳሪያዎችን አለመጠቀም ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ በግንባታ ወቅት እነዚህን መስፈርቶች ለማያሟሉ አካላት (በእርከን) 50 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን አመልክቷል።

ቅጣቱ "በየእርከኑ" ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ባለስልጣኑ ሲያስረዳም፣ "ለምሳሌ አንድ G+10 ህንጻ 26 የክትትል እርከኖች ይኖሩታል፤ 26*50,000=1,300,000 ይሆናል" ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ያለተቆጣጣሪ ማሰራት ለአደጋ አጋላጭ በመሆኑ የግንባታ ስራዎችን ያለተቆጣጣሪ የሚያሰሩ አካላት (በየእርከኑ) 25 ሺሕ ብር እንደሚቀጡም ተጠቁሟል።

ስቶር፣ ልብስ መሸጫ፣ መመገቢያና ሌሎች የቅድመ ግንባታ መስፈርቶችን ሳያዘጋጁ ሥራ ለሚጀምሩ አካላት የ15 ሺሕ ብር፤ በሚሰጥ የማስታወቂያ ትዕዛዝ መሰረት ተረፈ ምርትን በወቅቱ ለማያነሱ 15 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን የደረሰን የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል።

ሕጋዊ ተጠያቂነትን በተመለከተ የማማከር ኃላፊነትን በአግበባቡ አለመወጣት ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ30 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ፤ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ማከናወን ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ50 እስከ 100 ሺሕ የገንዘብ ቅጣቶች መጣላቸው ተመልክቷል፡፡

እንዲሁም፣ ግባታውን በህዝብ ደህንነት አደጋ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ ከ5 እስከ 10 ዓመታት የእስራት እና ከ20 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት የተገለጸ ሲሆን፣ ጥፈተኛ ሆኖ የተገኘ አማካሪ/ሥራ ተቋራጭ ከ15 ዓመት እስከ ከፍተኛ የእስር ጊዜው ፈቃዱ ይታገዳል ተብሏል፡፡

(የቀድሞው እና የተሻሻለውን ቅጣት፤ የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዘው የባለስልጣኑ መረጃ ከላይ ተያይዟል)
3
#ሳይጉላሉ
ለ graduated engineer license
ለ professional engineer license
ለ practice License ፍቃድ ለማውጣት ምንም ሳይጉላሉ በአንድ ቀን አሰርተንልዎት በጊዜ ወደ ቤትዎ ይገባሉ!
#የስራ ልምድም እናፀፍልዎታለን!!
👇ያግኙን / ያማክሩን👇
@A_B_C_D_E_F_G_H_J_K
2👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን ቪዲዮ ለጥንቃቄ ተጠቀሙበት

ጥቅል የኤሌክትሪክ ነው ብለው የሸጡላቸውን ተመልከቱ።

https://www.tg-me.com/engineer03
🔥21
2025/10/19 01:35:21
Back to Top
HTML Embed Code: