Telegram Web Link
ቅድስት ቤተክርስቲያን
#አርብ
በዚህች እለት ጌታችን በደሙ ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንደመሠረታት ይነገርበታል።

@eotchntc
ቅዱሳት አንስት
#ቅዳሜ
በዚህች እለት ከጌታችን ጋር አብረው የነበሩ ሲማሩ ሲያገለግሉ ከሐዋርያት ጋር በኅብረት ሆነውየቆዩትን፣የጌታችንን ትንሳኤ ቀድመው ያዩትን በጽናትና በምልዐት የጌታን አንድነት የጠበቁ 36ቱን ቅዱሳት አንስትን ቅድስት ቤተክርስቲያን በጉልህ ታስባቸዋለች።

@eotchntc
ውድ የሐመረ ኖኅ አባላት የሮሜ መልእክት
በቅርቡ ከሰኞ ጀምሮ እንደተለመደው
ይቀጥላል።
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
@eotchntc
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                        †                        

[ ዳግሚያ ትንሳኤ ! ]

እንኩዋን ለዳግሚያ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ

✞ እሁድ - ዳግም ትንሣኤ ይባላል ፦

በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

---------------------------------------------

"ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ 'ሰላም ለእናንተ ይሁን' አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን 'ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን' አለው:: ቶማስም 'ጌታዬ አምላኬም' ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም 'ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው' አለው::" [ዮሐ.፳፥፳፮-፳፱]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
#እመቤታችን_ቤዛ_ነች
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጌታችን እናት መሆኗ ብቻ ያላትን ክብር እና ቅድስና ያሳያል።
ቅድስት ድንግልን ማርያም "እንደ እኛ ሰው ናት እኛ እና እርሷ አንድ ነን" የሚሉ ሰዎች አንድ ነጥብ እንኳን ለክብሯ የሚደርሱ አይደሉም።
ቅድስቲቷ
የእግዚአብሔር እናት(theotokos) ነች።
ያመነች ብጽዕት የተባለች በዚህም ብቸኛ ትውልድ የሚያመሰግናት፣በሥላሴ ፊት ስልጣን ያላት የሥላሴ ዙፋን ነች።
እመቤታችን ቤዛዊተ ኩሎ አለም ነች። ይህም ጌታችንን በመውለድ ለመዳናችን ምክንያት በመሆኗ ነው።መ

መጽሐፍ ቅዱስ ሙሴን ቤዛ ብሎ ጠቅሶታል።
ሐዋ. ሥራ 7:35: ‘ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው?’ ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።

መጽሐፍ ቅዱስ ሐብትን(ገንዘብን)ቤዛ ይለዋል።
ምሳሌ 13:8
ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤
ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።
ዘኍልቍ 3:46
በሌዋውያን ላይ ከእስራኤል ልጆች በኵር ስለ ተረፉት ስለ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ቤዛ፥ በየራሱ አምስት ሰቅል ውሰድ፤
ስለሆነም ሙሴና ገንዘብ ቤዛ ቢባሉ እንደ ክርስቶስ ቤዛነት የሆነ ቤዛነት ነው ማለት ፈጽሞ አይደለም።

ብጹዕነታቸው የቤዛነትን ትርጉም ገድበው ብቻ መንገር አልነበረባቸውም። ቤዛነት አንድ ብቻ ሀሳብ ቢኖረው መጽሐፍ ቅዱስ ተሳስቷል ማለት ነው። ቤዛነትን ለብዙ ነገሮች ሰጥቶአልና
እንደ ክርስቲያን ሁሉን ለይተን እንደወገኑ ይህንን ማመን ይገባናል።

@eotchntc
#ንጹህ_የሆነ_የክርስቶስ_ስብከት
አንዳድሰዎች ክርስቶስን እንስበክ ብለው ተነስተው በውስጡ በማር የተለወሱ መርዝ የሆነ ትምህርት ሲያስተምሩ ተገኝተው ተው ሲባሉ "ተገፋን" ሲሉ ይደመጣሉ።
ንጹህ የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል ስበኩ ከእግዚአብሔር የሆነውን ብቻ ከራሳችሁ የመነጨውን አትንገሩን ሐዋርያው እንዳለ ከቀደመው ትምህርት የተለየ ትምህርት በመልአክ እንኳ ቢሰበክ የተረገመ ይሁን እንዳለ።
ስለ ክርስቶስ መስበክ ይቻላል።ግድም ነው ግን ከምንፍቅና ፈጽሞ የጸዳውን በዙፋኑ ላይ ያለውን የአብን አንድያ ልጅ እንዲሁም የእመቤታችን ልጅ ኢየሱስን
ይሁን።ጌታን ለመስበክ ቅዱሳንንና እመቤታችን አታጥላሉብን ፈጽሞ ደስ አይለውም።
@eotchntc
ቤዛነት ፣መካከለኛነት፣ አማላጅ የእያንዳቸው ትርጉም ከ መጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ምን ይመስላል?........ ቤዛነት፣መካከለኛነት፣አማላጅነት ምንድናቸው?
ቤዛነት ማለት ቤዛ ወይንም ለውጥ፤ምትክ መሆን አንዱ በአንዱ ቦታ ተገብቶ ስለዚያ ሰው ዋጋን መክፈል ወይም መታደግ መቤዠት ማለት ነው።ቤዛነት በአጭሩ ራስን ስለሌሎች አሳልፎ መስጠት ነው።
“ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥6 ቤዛነትን ለክርስቶስ ኢየሱስ እና ለቅዱሳኑ ብለን መስጠት እንችላለን።
ለክርስቶስ ስንል ከባህርይው የመነጨ በፍጹም የታመነና ሰዎችን ያዳነ ብሎም የሚያድን ክፍያ ነው። ቅዱሳኑ ግን ቤዛ የሚባሉት በጸጋ ከአምላክ ያገኙት ከባህርያቸው ያይደለ ካለ ክርስቶስ(ካለ እግዚአብሔር )ምንም ምን ማድረግ የማይቻለው ነው። ቢሆንም ግን በክርስቶስ ቤዛነት አምኖ የሚኖረውን ከክብርት ቤተክርስቲያን ህብረት እንዳይለይ፣በጸጋ መንፈስቅዱስ እንዲከብር፣በቅድስና ህይወት እንዲመላለስ የሚያስችል ነው።ቅዱሳንን ቤዛ ማለት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ መሆን አይደለም። ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ሀብት(ገንዘብ) ራሱ ቤዛ ተብሎ ተነግሯል።
“ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።”
— ምሳሌ 13፥8
“የማስተስረያውንም ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለመገናኛው ድንኳን ማገልገያ ታደርገዋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ይሁን።”
— ዘጸአት 30፥16
ገንዘብ ለሰው ቤዛ ከተባለ የቅዱሳን ቤዛነትማ እጅግ የታመነና የተከበረ እውነታ ነው። ቅዱሳኑ ቤዛ ሲባሉ አንድም በእግዚአብሔር ፊት በከበረ ጸሎት ልመናቸው ነው።
መካከለኛ(μεσίτης):-mesítēs means it is a mediators or performe the mediation )
መካከለኛ መሆን ማለት ደግሞ በሁለት አካላት መካከል መሆን የሁለት አካላትን ባህርይ ተላብሶ(ተዋህዶ) ሁለቱን አካላት ማስታረቅ ከዚህ አለፍ ሲልም ይህ የሁለቱን አካላት ባህርይ የለበሰው ሰው ከራሱ ጋር ያስታርቃል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ሆነ በቅድስት ቤተክርስቲያን ፍጹም መካከለኛ ተብሎ የሚጠራውም የሚነገረውም እግዚአብሔር የሆነው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 2
⁵ አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
⁶ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤
መካከለኛ (ፍጹም ሰውም እግዚአብሔርም)በመሆን ብሎም ስለ ሰዎች ቤዛ(ምትክ)በመሆን አለሙን ሁሉ አድኗል እያዳነም ይኖራል።
መካከለኛ የግድ አማላጅ ማለት አይደለም።ምክንያቱም የክርስቶስ መካከለኛነት ከዚህ ሀሳብ (ከ አማላጅነት)እጅጉኑ የራቀ ነውና
የኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛነት ደግሞ ለአለሙ ሁሉ የሆነ ነገር ግን እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ አንድ ብቻ ጀሆነ ነው"።
“መካከለኛውም ለአንድ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።”
— ገላትያ 3፥20
አማላጅ ማለት በሁለት ወገኖች ማለትም በሚለመንለትና በሚለመነው አካል መካከል ቀርቦ ለሚለመንለት አካል ለነፍሱ ሥርየተ-ኀጢአት ወይንም ልዩ ልዩ ፍላጎቶች ልመናን ወይም ጸሎትን ማቅረብ ማለት ነው።
ምናልባትም በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጌታችን መድኀኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃ ማቅረቡን፣ በተመለከተ የሚነገሩ አንዳንድ ጥቅሶችና ንግግሮች አሉ። ነገር ግን የነዚህ ጥቅሶች መኖር አንደኛውም ክብር ይግባውና ክርስቶስን አማላጅ አድርጎ የሚያስቆጥር አይደለም።ኢየሱስ ልመናን ወይም ምልጃን ቢያቀርብ አማላጅ እንደሆነ ለማሳየት አይደለም።ምክንያቱም ምልጃ ማቅረብ በፍጹም የፍጡራን ባህርይ ነውና እንደሚታወቀው ደግሞ ኢየሱስ እግዚአብሔር የሆነ አንድ አምላክ ነው።ታዲያ ኢየሱስ ለምን ልመናን አቀረበ ካልን
#የመጀመሪያው እርሱ ፍጹም አምላክ ብቻ ሳይሆን ፍጹም ሰው መሆኑን ለማስረዳት ያደረገው ነው። ኢየሱስ ፍጹም ሰው በመሆኑ ከኀጢአት በቀር በሁሉም ነገር ልመናን በማቅረብም ጭምር እኛን ሊመስል ተገብቶት ከአብ ዘንድ ተልኮ የመጣ ብቸኛው የአብ ቃሉ እና ብቸኛ ልጁ ነው ከኀጢአት በር በሁሉ እኛን መስሏልና
“ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።”
— ዕብራውያን 2፥17
“ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።”
— ዕብራውያን 4፥15

ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌ ያቀረባቸው ልመናዎች ወይንም ምልጃዎች እርሱ መደበኛ አማላጅ ስለሆነ አይደለም።ትህትናውን አርያነቱን ሊያሳየን ነው እንጂ
“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”
— ማቴዎስ 11፥29 በዋነኛነት ክርስቶስ ስለተዋሀደው ወይንም ስለተካፈለው ስጋ ከኛ ጋር አንድ ሆኖ ለመቆጠር አላፈረም ብሎም ሞትን ለመቅመስ ከፈጠራቸው ከቅዱሳን መላእክት እንኳን አንሶ ተቆጠረ በመሆኑም ከእርሱ አባቱ እንደሚበልጥ ነገረን
“ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።”
— ዕብራውያን 2፥9
“እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።”
— ዮሐንስ 14፥28
ስለዚህም ስለተዋሀደው ወይም ስለተገለጠበት ስጋ ከአብ ደግሞም ከቅዱሳን መላእክት አንሶ ከተቆጠረ ልመናን ቢያቀርብ ምንም አያስደነግጥም።
ኢየሱስ ፍጹም አምላክ እንደመሆኑ ፍጹም ሰው ስለሆነ ተርቧል፣ተጠምቷል፣ ደክሟል፣ ልመናን አቅርቧል፣ተኝቷል፣ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች ምትክ እየሆነ ካሳ እየከፈለ የሰውን ልጅ ለማዳን ያደረጋቸው ሁነቶች ናቸው።
አንድ ነገር ማወቅ ያለብን ኢየሱስ ልመናን ሲያቀርብ መልስን ከአቢቱ አይጠብቅም ምክንያቱም ከአባቱ ጋር በባህርይ የተካከለ ነውና

ዲያቆን የኋላሸት
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#ወደ_ነው። _ሰዎች ክፍል 55 ሐ ዕብራውያን 9 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፤ ⁷ በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤ ⁸ ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና…
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 55 መ

የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን የማንጻት ሥራ ግን የመማለድ የማማለድ ሀሳብ የለውም።
ልማልድ ወይም ልለምን ራሱ ቢል አብ የሚባለው የባህርይ አባቱ እና ከእርሱ ጋር በዕሪና ያለ እና የሚተካከል ነው።
- ዕብራውያን 7:25
ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።

...ሊያማልድ ዘወትር በህይወት ይኖራል ማለቱ ስለ ፍጹም የማዳን ፍቅሩ ስለ ርህራሄው የተገለጸ ነው ምክንያቱም ከታች
በጌታ አምነው ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ያድናቸዋል የሚል አሳብ ተናግሯል።
በእውነት ጌታ እንደ ጥሬ ቃሉ አማላጅ ቢሆን ማዳን አይችልም ነበር።

ሌላኛው ጌታ እነዚህ የምልጃ እና የልመና ቃላት ቢነሱበት ስለ ነገረ ሥጋዌ(ስለ ሰውነቱ)የተነገሩ ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ ጌታ ሰው በመሆኑ አይደለም ከአብ ከመላእክት አንሶ መቆጠሩን ይነግረናል።

Hebrews 2 አማ - ዕብራውያን
9: ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።

በሌላ በኩል መጽሐፍ ቅዱስ በባህርይው አንዳንድ ጊዜ የተፈጸመን ነገር ወደ ፊት እንደ ሚፈጸም አድርጎ ይናገራል።
ለዚህም ጌታ በመስቀል ላይ በዕለተ አርብ
ስለ ሰው ልጆች ስለ ቀደመው አዳም
ዳግማዊው አዳም ክርስቶስ በእርሱ ቦታ ተገብቶ የሰው ልጆችን ጩኸት የጮኸበትን ያንን ሀሳብ ሐዋርያው
ገና ወደ ፊት እንደ ሚፈጸም አድርጎ ያቀርበዋል።
ሉቃስ 23 34: ኢየሱስም፦ “አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፡” አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት።
ስናጠቃልል ለጌታ ከላይ እስካሁን ያየናቸው የምልጃ ቃላት ተነግረዋል።

ሲጠቃለል:-ክብር ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አማላጅ አይደለም።

ነገር ግን የምልጃ የልመና ቃላቶች ለእርሱ ተነግረዋል ይህም ስለ ፍጹም ፍቅሩ ርኅራሄው፣ስለ ደሙ ፍጹም የማንጻት ሥራ እና ስለ ሌሎችም ነገሮች

ይቀጥላል ......

@eotchntc
#የኤማሁስ_መንገደኞች
የጌታችን ትንሳኤ የቀረ መስሎአቸው
በተሰበረ ልብና በሃዘኔታ ሲራመዱ የነበሩቱ ቀለዮጳና ሉቃስ
ኋላም ጌታ ተገልጦ የባረካቸውና ያሳረፋቸው

Luke 24 አማ - ሉቃስ
13: እነሆም፥ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር፤
14: ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።
15: ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤
16: ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።
17: እርሱም፦ “እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው?” አላቸው።
18: ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ፦ “አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን?” አለው።Luke 24 አማ - ሉቃስ
19: እርሱም፦ “ይህ ምንድር ነው?” አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤
20: እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው።
21: እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው።
22: “ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን፤
23: ሥጋውንም ባጡ ጊዜ፦ ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን፡ ሲሉ መጥተው ነበር።
24: ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም።”
Luke 24 አማ - ሉቃስ
25: እርሱም አላቸው፦ “እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤
26: ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን?”
27: ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።
28: ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው።
29: እነርሱም፦ “ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል፡” ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።
30: ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤
Luke 24 አማ - ሉቃስ
31: ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።
32: እርስ በርሳቸውም፦ “በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?” ተባባሉ።
33-34: በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ አሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም፦ “ጌታ በእውነት ተነሥቶአል ለስምዖንም ታይቶአል፡” እያሉ በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው።
35: እነርሱም በመንገድ የሆነውን እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንደ ታወቀላቸው ተረኩላቸው።
36: ይህንም ሲነጋገሩ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፡” አላቸው።
Luke 24 አማ - ሉቃስ
37: ነገር ግን ደነገጡና ፈሩ መንፈስም ያዩ መሰላቸው።
38: እርሱም አላቸው፦ “ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል?
39: እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ።”
40: ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው።
41: እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ፦ “በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን?” አላቸው።
42: እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤
Luke 24 አማ - ሉቃስ
43: ተቀብሎም በፊታቸው በላ።
44: እርሱም፦ “ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል፡ ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው፡” አላቸው።
45: በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤
46: እንዲህም አላቸው፦ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥
47: በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል፡ ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።

@eotchntc
ይቅርታ አድርጉልኝና; አንዳንድ አባቶች ነገረ ማርያም ላይ የሚጠቀሙት አገላለፅ በጣም የተለጠጠ ነው:: በመስቀል ላይ የፈሰሰው የእመቤታችን ደም ነው የሚል የቤ/ክ ትምህርት የለም:: 

1 ጢሞ 4:16 " ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።"

Gadisa
#ግንቦት_1
የጌታችን እናት የልደት በዓል
እመቤታችን የተወለደችበት ድንቅ ዕለት
እንኳን አደረሰን።
@eotchntc
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ክፍል 55 መ የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን የማንጻት ሥራ ግን የመማለድ የማማለድ ሀሳብ የለውም። ልማልድ ወይም ልለምን ራሱ ቢል አብ የሚባለው የባህርይ አባቱ እና ከእርሱ ጋር በዕሪና ያለ እና የሚተካከል ነው። - ዕብራውያን 7:25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። ...ሊያማልድ ዘወትር በህይወት…
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 56
ሮሜ 8: 35
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
ሐዋርያው የክርስቶስ ፍቅር ባመኑት ክርስቲያኖች ዘንድ ጥልቅ መሆኑን ነገረን።እነዚህ ሁሉ ዝቅታዎች ከሁሉ በላይ ከሆነው ከክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ቸርነት እና ርህራሄ በታች ናቸውና

ሮሜ 8:36: ይህም እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፦
“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።”
- መዝሙር 44:22 ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል፥
እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።ሰው ክርስቶስን ሲቀበል ሲያምን ጠላት ብዙ መከራን ያመጣልና።


ሮሜ 8:37:
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።

ምንም እንኳን መከራው ቢበዛ ኃያላን ኀይላቸውን ቢያበረቱ አሸናፊዎች የተባሉ ከጌታ ጋር ኅብረት የሌላቸው ጉልበተኞች ቢበረቱም ቅሉ ያመኑቱ ክርስቲያኖች ግን በጌታ ሁሉን ድል ያደርጋሉ።
- ሮሜ 8
38: ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
39: ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።

የትኛውም ነገር ሰማያዊ ኃይላት ሆነ ምድራዊ ኃይላት ከክርስቶስ ቸርነት ፍቅር ወይም ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር ካላቸው ኅብረት የሚለያቸው ነገር አለመኖሩን ይህ የተወደደ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ነገረን።
በረከቱ ይደርብን።

ይቀጥላል

@eotchntc
#EOTC

የግንቦት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ነገ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እንደሚጀመር ተገልጿል።

የምልዓተ ጉባኤው መክፈቻ የጸሎት መርሐግብር አሁን በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እየተካሄደ ይገኛል።

ከነገ ጀምሮ ቅዱስ ሲኖዶስ በልዩ ልዩ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ ይጠበቃል።

#EOTC

@tikvahethiopia
@zemarian
#የቅዱስ_ያሬድ_ታሪክ_ባጭሩ

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ስለ ቅዱስ ያሬድ ታሪክ ሚያዝያ 5 ነግረናችሁ ነበር ለማስታወስ ያህል በጥቂቱ ኢትየጵያዊዉ ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን 505 ዓ/ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡እናቱ ታዉክሊያ/ክርስቲና/አባቱ ደግሞ ይስሐቅ/አብድዩ/ይባላሉ፡፡

አባቱ የአክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር፡፡ ያሬድ ሰባት ዓመት ሲሆነዉ አባቱ ስለሞቱበት እናቱ ት/ቤት ለማስገባት ወደ አጎቱ መምህር ጌዲዮን ጋር ወሰደችዉ፡፡ አባ ጌድዮንም በአክሱም ቤተ ቀጢን《ቤተ ጉባኤ》መምህር ነበሩ፡፡

           ያሬድ ያኔ!ምን ነበር !?

በትምህርቱ የሚያሳየዉ ዉጤት ደካማ ስለነበር ከሌሎች ህጻናት ጋር ሊወዳደር አልቻለም፡፡መምህሩ ጌዴዎን ለተግሣጽ ቢቀጡትም መታገስ ተስኖት ተስፋ ቆርጦ ከአክሱም ከተማ ወጥቶ ወደ እናቱ መንደር መደባይ ወለል ተጓዘ፡፡

ህጻን ያሬድ ከዛፍ ስር ተቀምጦ በምን ምክንያት ገጓደኞቹ በታች እንደሆነ ሲያዝን ሲተክዝ ቆየ፡፡ ታደሰ አለማየሁ ‹‹የቤተ ክርስቲያን ብርሀን ቅዱስ ያሬድ››በሚለዉ መጽሐፉ‹‹አንድ ትል የዛፉን ፍሬ ለመመገብ ፈልጎ ወደላይ እየወጣና እየወደቀ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ ከቆየ በኋላ በሰባተኛዉ ጊዜ ወጥቶ ፍሬዋን ሲመገብ ተመለከተ፡፡
         
ያሬድም የዚህ ትል ተስፋ አለመቁረጥ ትዕግስቱን ጽናቱን ተመልክቶ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
《እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ብዙ ጥረት ካደረኩ እንደዚህ ሊሳካልኝ ይችላል›ብሎ ወደ መምህሩ ለመመለስ ወሰነ ይላል》ያሬድ የ አጎቱ ምክርና ተግሣጽ ለሕይወቱ የሚጠቅም መሆኑን በመረዳቱ ትምህርቱን በትጋት ቢማርና ቢያጠና ያሰበዉ ደረጃ ለመድረስ እንደሚችል በመገንዘብ ወደ መምህሩ ጌዲዮን ጉባኤ ቤት ተመለሰ፡፡

       መምህሩም ምን አሉት!?

እሳቸውም  ተቀብለዉ አስተማሩት፡፡ አጭር ጊዜ አልገባ ያለዉ ትምህርት ተገልጾለት ትምህርቱን በሚገባ አጠናቀቀ፡፡ በኋላም የብሉይና የሐዲስ መምህር ሆኖ በመምህሩ በጌዲዮን ወንበር ተተካ፡፡
              #የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_እና_ዓይነቶቹ 
         
           የቅዱስ ያሬድ ዜማ!? 
በእግዚአብሔር ፈቃድ የተገለጸለት
ለመሆኑ መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ቅዱስ ያሬድ ዜማዉን ያዘጋጀዉ በሦስት ዓይነት ድምፅ ማለትም በግእዝ፣በዕዝል፣እና በዓራራይ ዜማ ነዉ፡፡

እነዚህ የዜማ አይነቶች የአንዱ ድምፅ ከሌላኛዉ ድምፅ ያልተደበላለቀ ወጥ የሆነ ድምፅ አላቸዉ፡፡ዜማዎቹንም በስምንት ምልክቶች ቀምሮታል፡፡ የምልክቶች አገልግሎትም በትምህርት ሂደት ጊዜ የጠቋሚነት ሚና በመጫወት ለዜማዉ መጠበቅ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ናቸዉ፡፡

ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀል!?

ቅዱስ ያሬድ የተነሳዉ ዘጠኙ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ዘመን ነዉ፡፡ በዘጠኙ ቅዱሳን የተተረጎሙት ቅዱሳን መጻሕፍት በቅዱስ ያሬድ የድርሰት ስራ ዉስጥ ጉልህ ድርሻ ነበራቸዉ፡፡

ቅዱስ ያሬድ ከመጻሕፍቱ ያገኛቸዉን ምስጢራት ቃል በቃል እየጠቀሰ እንዲሁም ሐሳባቸዉን ጨምቆ በመዉሰድ በራሱ ቋንቋ እያራቀቀ ለድርሰቱ ተጠቅሞባቸዋል፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
《ሰሎሞን ወንድሙ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሕይወት፤1998 ገጽ15》፡፡
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ቅዱስ ያሬድ ሙራደ ቃልበተባለ ቦታ ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲያዜም ንጉሱ አፄ ገብረ መስቀል ከነሰራዊቶቻቸዉ ንግስቲቱ ከነደንገ ጡሮቿ ፣መሳፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ሊቃዉንቱና ካህናቱ አየመጡ ያዳምጡ ነበር ይላሉ ርእሰ ደብር  ጥዑመ ልሳን ካሣ በመጽሐፋቸዉ፡፡
  
ቅዱስ ያሬድ ድርሰት ማ ፤ ማ ናቸው!?

በግእዝ፣በዕዝል በዓራራይ ዜማ ዝማሜ እየደረሰ እያለ ንጉሱ አፄ ገብረ መስቀል ተገኝተዉ ነበር፡፡በዜማዉ ተመስጠዉ አይን አይኑን እያዩ እንደ እርሱ እዘምማለሁ ብለዉ በያዙት የብረት ዘንግ ሳያዉቁት ቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ቸከሉት፡፡ ሁለቱም በተመስጦ ስለነበሩ የሆነዉን ነገር አላስተዋሉትም ነበር፡፡ ዜማዉ አብቅቶ ሁለቱም ከተመስጧቸዉ ሲነቁ የቅዱስ ያሬድ እግር ዘንጋቸዉ ተሰክቶ ብዙ ደም ፈሶት ነበር፡፡ንጉሡም ደንግጠዉ እጅግም አዝነዉ‹‹ደምህን አፍስሻለሁና የምትፈልገዉን ማንኛዉንም ነገር ጠይቀኝ እሰጠሃለሁ››ሲሉ ቃል ገቡለት፡፡ ቅዱስ ያሬድም‹‹ይምለምነዉ አንድ ነገር አለ እርሱን ፈጽምልኝ›› አላቸዉ፡፡ ‹‹የፈለከዉን ጠይቅ ፈቅጄልሃለሁ›› አሉት፡፡ እርሱም‹‹እስካሁን እግዚአብሔር በፈቀደልኝ መሰረት በዚህ ከተማ ከእርሰዎ ጋር ቆይቻለሁ፡፡ብዙ ደቀ መዛሙርትም ተክቼያለሁ፡፡ከእንግዲህ በኋላ የቀረኝን ዘመን በጸሎትና በብሕትዉና መኖር እንድችል ከከተማዉ ራቅ ወዳለ ቦታ ሔጄ ፈጣሪየን ማገልገል እፈልጋለሁ››ብሎ የንጉሱን ፈቃድ ጠየቀ፡፡

አፄ ገብረ መስቀልም የቅዱስ ያሬድን ቃል ሰማተዉ በዚያኑም በገቡለት ቃል መሰረት ፈቀዱለት፡፡ከዚያም ጉዞዉን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ ሰሜን ተራሮች አደረገ፡፡በዚያም አሁን በስሙ የታነጸዉ ቤተ ክርስቲያን ባለበት ቦታ ላይ በምናኔ ተወስኖ ፈጣሪዉን በብሕትዉና እያገለገለ ኖረ፡፡ምናኔ ደብረ ሐዊ ከተባለዉ ተራራ ላይ ብዙ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ በጸለምት ዋሻ በአንዱ ግንቦት 11 ቀን በ571 ዓ/ም ተሰወረ፡፡

#የቅዱስ_ያሬድ_ድርሰቶች
     
ቅዱስ ያሬድን ብቸኛ የግእዝ ሥነ ጽሑፍ መስራች አድርጎ ለማየት በቂ ምክንያት አለን፡፡ እንዲያዉም የግእዝ ስነ ጽሑፍ መስራች ከማለት ይልቅ የኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ መሥራች ልንለዉ ይገባል፡፡

《ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ኃይሌ የቅዱስ ያሬድ ታሪክና የግእዝ ስነ ጽሑፍ፤1999፤ገጽ3》ፕሮፌሰሩ በዚሁ ጥናታቸዉ እንዳብራሩት የግእዝ ስነ ጽሑፍን ለሁለት ልንከፍለዉ እንችላለን ይላሉ፡፡
ምክንያቱን ሲያብራሩ፡-አንዱ ክፍል ከባህር ማዶ ተጽፈዉ ወደ ግእዝ የተተረጎሙትን መጻሕፍት ይይዛል፡፡ ሁለተኛዉ ክፍል በቀጥታ በግእዝ የተደረሱትን ድርሰቶች ያጠቃልላል፡፡

እነዚህም፡-የቅዱስ ያሬድ፣የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣የርቱዐ ሃይማኖት፣የ አፄ ዘርአ ያዕቆብ፣የ ዐርከ ሥሉስ፣የ አባ ባሕርይ ድርሰቶች የሚቀድም በ ግእዝ ቋንቋ የተደረሰ ድርሰት እስከ አሁን አለመገኝቱን ጥናቱ ያሳያል፡፡ 《1999፡3》
ቅዱስ ያሬድ ድርሰቶችን ሲያዘጋጅ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸዉን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ እየለየ በድርሰት ሥራዎቹ እንደ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ብሉያትን ከሐዲሳት፣ከሊቃዉንት እያጣቀሰ ያለምንም ችግር የድርሰት ሥራዉን ሊያከናዉን ችሏል፡፡

የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች መንፈሳዊ ይዘት ያላቸዉ ናቸዉ፡፡በድርሰቶቹ የሚታዩት የቃላት አመራረጥ፣የ ዐረፍተ ነገር አወቃቀር፣የሚስጥር፣የዘይቤ አገላለጥ ቅዱስ ያሬድ ከፍተኛ የስነ-ጽሑፍ ተሰጥኦ እንደነበረዉ ለመረዳት ይቻላል፡፡
በቅዱስ ያሬድ የተደረሱት የዜማ መጻሕፍት አምስት ናቸዉ፡፡እነርሱም ድጓ፣ጾመ ድጓ፣ዝማሬ፣ምሥዋዕትና ምዕራፍ ናቸዉ፡፡

#ድጓ፡-የቅዱስ ያሬድ ትልቁ የዜማ መጻሕፍ ነዉ፡፡

#ድጓ:- ማለት ስብስብ ማለት ነዉ፡፡በዉስጡ የዓመቱን በዓላትና የሳምንታት መዝሙራት ሰብስቦ የያዘ ነዉ፡፡ይህ መጽሐፍ በዐበይት በዓላት በዜማ የሚቀርበዉን ምስጋና ሰብስቦ የያዘ የዜማ መድብል ነዉ፡፡

#ድጓ በአራት ትልልቅ ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ይኸዉም፡-የዮሐንስ ድጓ፣አስተምህሮ ድጓ፣ጾመ ድጓ፣የፋሲካ ድጓ ተብሎ ይታወቃል፡፡

#ጾመ_ድጓ፡-ሁለተኛዉ የዜማ መጽሐፍ ሲሆን የሚጠናና ለመምህርነት የሚያበቃ ነዉ፡፡ድጓ ቁጥሩ ከአስተምህሮ ሲሆን በዐቢይ ጾም የሚደርስ ራሱን የቻለ መጽሐፍ ነዉ፡፡

#ዝማሬ፡-ሦስተኛዉ የዜማ መጽሐፍ ነዉ፡፡ ዝማሬ ምስጋና ማለት ነው
- ዘፍጥረት 16:13
እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች፤ የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።

#እግዚአብሔርን_ለማየት
1.እግዚአብሔር ማመን
2.በንጽሕና መላለስ
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ክፍል 56 ሮሜ 8: 35 ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ሐዋርያው የክርስቶስ ፍቅር ባመኑት ክርስቲያኖች ዘንድ ጥልቅ መሆኑን ነገረን።እነዚህ ሁሉ ዝቅታዎች ከሁሉ በላይ ከሆነው ከክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ቸርነት እና ርህራሄ በታች ናቸውና ሮሜ 8:36: ይህም እንዲህ ተብሎ እንደ…
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ምእራፍ 9
ክፍል 57
መግቢያ:-በዚህ ምእራፍ ውስጥ
ከ ቁጥር 1-6 ቅዱሱ ሐዋርያ ጳውሎስ ለወገኖቹ እስራኤል ስለመጸለዩ
ከ ቁጥር 7-13 ብሉይ ኪዳን ለእስራኤል ተስፋ ስለመነገሩ
ከ ቁጥር 14-24እግዚአብሔር በምህረትም ሆነ በመዓት ላይ ስልጣን ያለው መሆኑን
ከቁጥር 25-26አሕዛብ የእግዚአብሔር ልጅ ስለመባላቸው
ከ ቁጥር 25-33 ከእስራኤል ብዙዎች ኦንደማይጸድቁ ስለመነገሩ
ሮሜ 9
1-2: ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።

ሐዋርያው ከማያቋርጥ ሀዘን ወይንም ከከፋ ሀዘን የተነሳ ጭንቀት ውስጥ መጨነቁን ያሳየናል።ይህ ሀዘን የሚመነጨው በሥጋ ዘመዶቹ የሆኑ እስራኤል በክርስቶስ ካለማመናቸው የተነሳ ይኸውም ለማያቋርጥ ስቃይ እንደሚጠብቃቸው ከማሰቡ ነው።ይህንንም ሀዘን ለቅዱሱ ሐዋርያ ሁሉን የሚመረምረው መንፈስ ቅዱስ ብቻ የሚያውቀው ነው።
ሮሜ 9 :3 በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና።
ጳውሎስ ወገኖቹ እንዲያምኑ በብዙ ከመፈለጉ የተነሳ ራሱን ቤዛ እስከማድረግ ጸሎትን ይጸልይ ነበር።
ሮሜ 9:4 እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤

እነሱ እስራኤላውያን ናቸው ማለቱ ሕዝበ እግዚአብሔር መሆናቸውን ሲናገር ነው።
ልጅነት ሲል እስራኤል የእግዚአብሔር ልጅ መሆናቸውን ሲነግረን ነው ከልጅም የበኩር ።ይህም ከመጽሐፍ ቅዱስ
ዘጸአት 4:22 ፈርዖንንም፦ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤
ኪዳን ማለቱ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ኪዳን መግባቱን ሲያመለክት ነው።
ዘፍጥረት 17: 7:ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።.......... ይቀጥላል።

@eotchntc
Forwarded from 💎Super📣ፕሮሞሽን
ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ  ። የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው  ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው ቁርአን በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....read more

ትምህርቱ ተከታታይ ክፍል ተጀምሯል።
Forwarded from Quality button
አዜብ ወደ ሰሎሞን ስትሔድ ስንት ደናግላን አስከተለች???
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ pinned «#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ምእራፍ 9 ክፍል 57 መግቢያ:-በዚህ ምእራፍ ውስጥ ከ ቁጥር 1-6 ቅዱሱ ሐዋርያ ጳውሎስ ለወገኖቹ እስራኤል ስለመጸለዩ ከ ቁጥር 7-13 ብሉይ ኪዳን ለእስራኤል ተስፋ ስለመነገሩ ከ ቁጥር 14-24እግዚአብሔር በምህረትም ሆነ በመዓት ላይ ስልጣን ያለው መሆኑን ከቁጥር 25-26አሕዛብ የእግዚአብሔር ልጅ ስለመባላቸው ከ ቁጥር 25-33 ከእስራኤል ብዙዎች ኦንደማይጸድቁ ስለመነገሩ ሮሜ 9…»
ጰራቅሊጦስ

መንፈስቅዱስ(παράκλητος)

ጰራቅሊጦስ  ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የአንዱ አምላክ  እግዚአብሔር  ሦስተኛው አካል(person )ነው።
መንፈስቅዱስ በባህሪው መንጽዔ(የሚያጸና)  እና መንጽሒ(የሚያነጻ) ሲሆን ለእግዚአብሔር  ሥላሴ እስትንፋሳቸው ነው። እግዚአብሔር  መንፈስቅዱስ አንድም ከሳቴ ምስጢር  ወይንም  ምስጢር ገላጭ በመባል ይጠራል።
መንፈስቅዱስ  የእግዚአብሔር  እስትንፋስ (ህይወት )ነው። በአብና በወልድ ውስጥ ህልው ሆኖ ይኖራል።
Holly sprit is  also called  peraclitos and
he is the third person of the one the Almighty  God
መንፈስቅዱስ  ኀያል እግዚአብሔር በመሆኑ የእግዚአብሔር  ነገር መመርመር የሚችል  ብቸኛ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ብዙ መጠሪያዎች አሉት ከነዚህም መካከል
፩.መንጽሒ (የሚያነጻ)ሲሆን  ሰዎችን ከኀጢአት  ጠብቆ የሚያነጻ  ብሎም  ሰዎች በኀጢአት ከ ወደቁ በኋላ ንስሐ ሲገቡ በልባቸው ታትሞ ይቅር በማለት ያነጻቸዋል።
፪.መጽንዒ(የሚያጸና) በሁኔታዎች  በችግሮችና   በተግዳሮቶች ውስጥ  ሰዎችን አጽንቶ እግዚአብሔርን እንዳይክዱና በምልአት እንዲገልጡት  የሚረዳቸው ነው።
፫.ከሳቴ ምስጢር(ምስጢርን የሚገልጥ)
ከእግዚአብሔር  የሆነውን ምስጢር  እውቀት  እንደ ፈቃደ እግዚአብሔር   ይገልጣል። ሰዎችም በዚህ መንፈስ ተነሳስተው  ትንቢትን ይናገራሉ።
፬.ናዛዚ(የሚያረጋጋ) የሚያጽናና ነው
“እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።”
  — ዮሐንስ 16፥7
፭.መስተስርይ (ይቅር ባይ)ፍጹም አምላክ  በመሆኑ ኀጢአትን  ሁሉ ይቅር ይላል።
በዓለ  ጰራቅሊጦስ  የተለያዩ አይነት  ስያሜዎች  አሉት እነርሱም
በዓለ  ጰራቅሊጦስ
በዓለ ጰንጠቆስጤ (50ቀን)
በዓለ ሀምሳ
በዓለ ሰዊት(የአይሁድ  በዓል የነበረ)በዚያን እለት የሚከበር
መንፈስቅዱስ  በሐዋርያት  መካከል ጌታ ኢየሱስ  ካረገ ከ 10ቀን በኋላ  በመካከላቸው  በእሳትና  በነፋስ  አምሳል  ተገለጠ። የመንግስትን ወንጌል እንዲያስፋፉ 72 ቋንቋዎች ተገለጡላቸው። በዕለቱም በ ረድኤት ወ በ ኀይለ መንፈስ ቅዱስ  በመክበራቸው በስብከት 3000 ምዕመናንን ለጌታ ጨምረዋል።
መንፈስቅዱስ  አንድ የህይወት  ምንጭ ሲሆን የተለያየ  ጸጋ ለሰዎች ይሰጣል ።
ሐዋርያት  በዚህ ቅዱስ መንፈስ ከከበሩ በኋላ ወደ ጾም  ገቡ  አለምንም በወንጌል ማጥለቅለቅ ጀምረው እስከ ፍጸሜያቸው ድረስ አድርገውታል።
እግዚአብሔር  መንፈስቅዱስ  በቤተክርስቲያን  ውስጥ ያለ የነበረ የሚኖረውም እርሱ ከአብና ከ ወልድ ጋር  እርሱ  ነው።
ክብርና አምልኮ ውዳሴ ከምድር እስከ አርያም  ድረስ ለእርሱ ለመንፈስቅዱስ

ይሁን።

አሜን

ዲያቆን የኋላሸት

ባህርዳር


2015 ዓ.ም
Glory to the Hollysprit

እንኳን አደረሰን
2025/06/29 21:51:23
Back to Top
HTML Embed Code: