Telegram Web Link
#ያለኝን_እሰጥሃለሁ

አንድ ሰው ያለውን ነገር ለወዳጁ ወይንም ለሌላ ሰው ይሰጣል።
ያም የሚሰጠው ነገር ለተቀባዩ በእጅጉ የሚልቅ እና ችግርን የሚፈታ ወይንም ተግዳሮትን የሚያቃልል ነው።

እንደሚሰጠው ስጦታ ዓይነተና መጠን በሰጪውና በተሰጪው መካከል ያለውን ግንኙነትና ቅርበት ከዚያም አለፍ ሲል ፍቅርን ይገለጽበታል።

በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሶስት ላይ ያለውን ታሪክ ስንመለከት የሚሰጥ ስጦታ ፣ሰጭ ፣
ተቀባይ እንዳለ እንረዳለን።
የሚሰጠው ስጦታ ብቸኛና አንድ እንዲሁም ምትክና ወደር የሌለው ሲሆን ሰጪውም ደግሞ ከሚሰጠው ስጦታ ጋር እጅግ መልካም የሆነ ቅርበትና ግንኙነት ያለው ሲሆን ተቀባዩ ደግሞ ካለበት ችግርና መጎዳት አርነት የሚወጣበትን ሥጦታ የተጠማ ነገር ግን ያንን ለዘላለም ከችግሩ ነጻ የሚያወጣ ስጦታ ምን እንደሆነ የማያውቅ ነገር ግን ጊዜውን ጊዜያዊ በሆነ ና በሚያልፍ ነገር ላይ የሚያጠፋ ምስኪን ነው።

ታዲያ አምላክ በፈቀደው ሰዓት እና አለት አንዲትም ሽርፍራፊ ቅጽበት(second )ሳያልፍ ሶስቱም አካላት ከቤተመቅደስ ደጃፍ ተገናኙ።

ሰጪው ጴጥሮስ(ኬፋ) የተባለው የጌታ ኀሩይ እቃ ተሰጪው ደግሞ ክብር ይግባውና
ተወዳዳሪና ምትክ የሌለውመድኀኒታችን ኢየሱስ ሲሆን ተቀባዩ ደግሞ ከእናቱ ማኀጸን ጀምሮ አንካሳ የነበረ እና ምጽዋትን ለመለን ሰዎች ሁል ጊዜ እየተሸከሙ ከመቅደስ ደጃፍ የሚያስቀምጡት አንካሳ

እንግዲህ መልካም በምትባል መቅደስ ሰዎች ሲቀመጡ ኬፋን የመሰለ ወዳጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን ይቀበላሉ።

ይኼ ተቀባይ ኢየሱስን ሲቀበል ቀጥ ብሎ ቆመ። የአንካሳነቱ ዘመን አበቃ።
በጌታችን እጅ ላይ ታሪክ ተበላሽቶ አያውቅም።
አለቀ፣ ተደመደመ ፣ሞተ የተባለ ማንነት ህይወት፣ ዘመን፣ታሪክ ታድሶ ዘመንን ይገዛል።

ልክ የነብዩ ሳሙኤል እናት "“ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች፦ ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል።”
— 1ኛ ሳሙኤል 2፥1

በማዳኑ ሁሌም አዲስ ነው። እግዚአብሔር ወልድ(ኢየሱስ) ማር ከተባለ ጣፋጭ ገንዘብ ከተባለ ሁሉን አድራጊ ይልቅ የከበበረ እና የጣፈጠ ነው። ከዚህ ስጦታ ለመጠቀም በእምነትና በትህትና ሁኖ መቀበል ነው ።


“ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።”
— ሐዋርያት 3፥6






ፍቅሩ በልባችን ይደር
አሜን።

ዲያቆን የኋላሸት ይኸነው

ጥር/23/2016 ዓ.ም

ባህርዳር
#ዓይኖቼ_ማዳኑን_አይቷልና

(ὀφθαλμός εἴδω σοῦ σωτήριον)

የሰዎች ዓይን ነገሮችን ለመመልከት የተፈጠረ አንዱና ዋነኛው የስሜት ህዋስ (sense organ) ነው።

የሰው ልጅ ካለ ዓይን ሙሉ ሆኖ ነገሮችን ለመከወን ብዙ ልፋቶችና መሰናክሎች ይገጥሙታል።እነዚህን ደግሞ በትዕግስት እና በጥበብ ሊያልፍ ግድ ይለዋል።

ዓይን ማለት ብርሃን ማለት ነው።

“የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤”
— ማቴዎስ 6፥22

ዓይን ቢታመም መላው አካል የታመመ እስኪመስል የሰው ሰውነት ይታወካል።

በዚህም ምክንያት የሚመጣው ጨለማ በእጅጉ የበረታ ነው።

“ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!”
— ማቴዎስ 6፥23


ዓይን በእጅጉ ውድ የሆነ የሰውነት አካል ክፍል ነው።

ታዲያ በዚህ ውድ በሆነ የሰውነት የአካል ክፍል መልካሙንና ያማረውን

“አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ውስጥ ነን፤ ለዓይንህም መልካምና ቅን የመሰለውን ነገር አድርግብን አሉት።”
— ኢያሱ 9፥25

ብሎም ርኩሰቱን አሊያም ሌሎች ነገሮችን

“ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።”
— ዘፍጥረት 3፥6

ልናይበት እንችላለን።

በኢየሩሳሌም የነበረው መንፈስ ቅዱስ አንድ ትልቅ ተስፋን የነገረው ስምኦን ግን አንድ ና ብቸኛ የሆነውን ዓለም የሚበራበትን ከርኩሰት የምትወጣበትን ከባርነት ተላቃ በነጻነት የምትኖርበትን በቤተልሔም የተወለደውን የናዝሬቱን መልካም አየ። በእርግጥም የታደሉ አይኖች

ይኼ ሰው ይህንን ካየ በኋላ አይኖቼ ማዳኑን አይተዋል በማለት በደስታ መሰከረ። ከዚህም በኋላ ሌላ ዓለም ኑሮ ህይወት አልፈለገም።
ለነገሩ ለምን ይፈልጋል ለምንስ ይቃትታል።
ወዲያውኑ በሰላም ወደ ዘለዓለም እረፍት ወደ ህይወት መግባትን ማረፍን ተመኘ።

አረጋዊው ያየው ማዳን የተባለው ህጻኑንና ኀያሉን አምላክ የይሁዳ አንበሳ ኢየሱስን ነው።
የእረፍት ወደብ የሆነውን ከእርሱ የሚገኘው ሰላም ደግሞ አዕምሮን የሚያልፍ ልብን የሚያሳርፍ ነው።

በመሆኑም የመጨረሻ የእረፍት ጥግ የሆነውን የሰዎችን አለኝታ ቅዱሱን የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤል ጠባቂ መስፍንን መሲሁ ክርስቶስን ስላየ ከዚህም በኋላ ደግሞ ከዚህ የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ

መሰናበትን ፈለገ።

ለእኛም እንደ ዚህ ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን የጌታችንን ቤዛነት የመንፈስ ቅዱስን የጸጋ ሥጦታ ለማየትና ለመኖር መድኀኒአለም ይርዳን አሜን!!!!


ዲያቆን የኋላሸት

ጥር /26/2016 ዓ.ም
#ወደፊት_እዘረጋለሁ

በሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ብዙ ነገሮች ይከወናሉ።

እግዚአብሔርን ማወቅ፣ እርሱን ማምለክ ፣ በኀይሉ መታመን፣በፍቅሩ መጽናናት፣በቸርነቱ መታመንና እጅግ ብዙ መልካም የሆኑ ነገሮች
ከዚህ ጋር በተቃረነ መልኩ ደግሞ ብዙ ኀጢአቶች፣ በእግዚአብሔር ስም ላይ መሸቀጦች የትየለሌ ክፉ ሀሳቦች፣እልቆ መሳፍርት የከፉ ተግባራት ሲከወን ይታያል። በነዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ወይም ከፍታ ና ዝቅታ ግን ሁሌም ቢሆን የሰው ልጅ አምላኩን ጨርሶ ዘንግቶ አያውቅም።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ነገሮች በእያንዳንዶቻችን ውስጥ ያሉ ያለፉ #ትናንትናዎቻችን ናቸው። እነዚህ ትናንትናዎቻችን ለዛሬያዊ እኛነታችን መሰረቶቻችን ናቸው። ነገር ግን በመልካም ያሳለፍናቸውን ብቻ እንዲቀጥሉ መፍቀድ ይኖርብናል።
የአመጻውና የዝቅታው ትናንት ከአሁኑ የህይወት ክፍላችን ገብቶ ሊጎትተን የይለፍ ቃል ልንሰጠው አይገባም።
ምክንያቱም አሁን ሊኖረን የሚገባውን ህይወታችንን የሚቀብርብን ነውና

መልካሙንም ትናንት ቢሆን መልካም ስለ ሆነ እግዚአብሔርን እየባረክን እኛ ግን ወደ ፊት መሮጥ
ስለዚህም የኋላችንን እየረሳን ወደ ፊት በእምነት እና በቅድስና መንፈስ መዘርጋት

ልክ ቅዱሱ ሐዋርያ እንዳለ


“ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥”
— ፊልጵስዩስ 3፥13

በረከቱ ይደርብን
አሜን

ዱያቆን የኋላሸት ይኸነው

ጥር 28/2016 ዓ.ም
#ያየብንን_ያላሳየብን

እግዚአብሔር ቸር፣ይቅር ባይ፣ እና ከባቲ አበሳ/በደልን የሚሰውር/ የሚሸሽግ ሩህሩህ አምላክ ነው።

ቸሩ አምላካችን በደልን በማንም ፊት ገልጦ አያሳይም ይልቁኑ ይከድናል እንጂ
የሰው ልጅ ደካማ ሆኖ ሳለ ምንም እንኳን በበደል መውደቅ ያለበትን ለኀጢአት የሚስማማ ደካማ ስጋን ቢይዝም ከዚህ ድካም አለማምለጥ ባይችልም ግን ለወንድሙ ጥቂት ጉድፍ(ኀጢአት) ይቅርታን ማድረግ ሲሳነው እናስተውላለን።

ነገር ግን ከኀጢአት ሁሉ ነጻ የሆነው ንጹሐ ባህሪ ገንዘቡ የሆነው አምላክ ንጉሥ ክርስቶስ ግን ሊራራልን የማይችል አምላክ አይደለም።

“ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።”
— ዕብራውያን 4፥15
ሁል ጊዜም #የእንደገና እድል የሚሰጥ ቸር ጠባቂ ነው።

ብዙዎቻችን ከነጠላ ስር፣በልብስ ውስጥ፣በህሊናችን መዝገብነት ብዙ በደሎችን ሸሸግናል።

የተሸከሙን የእግዚአብሔር ትከሾች ሰፊ ባይሆኑ ኑሮ መቆም የምንችል አይደለም።
በምሕረቱ ስፋት ልክ በሌለው ደግነቱ ስራችን ተሸፍኖ እንጂ በፊቱ በድፍረት መቅረብ የሚገባን አልነበረም።

በጸጋው ስፋት እና ጥልቀት እየማረን እንጂ ከጽድቃችን መብዛት አልነበረም
ድፍረታችን አምላካችን ነው።

ይህንንም ድፍረት በመያዝ በእምነት ሁነን ምህረቱን እናገኝ ዘንድ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት ሁነን መቅረብ ያስፈልገናል።

“እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።”
— ዕብራውያን 4፥16

አምላካችን እኮ ብዙ ያየብን በደሎች አሉ ነገር ግን ሰው አይደለምና አንድ ጊዜ ይቅር ካለ በሌሎች ፊት አይገልጥብንም። ፈጽሞ ይረሳዋል።

የሰው ልጅ ምንም እንኳ ወዳጅ ቢሆንም አንድ ቀን ትከሻው ይታክታል። "አሁንስ መረረኝ" የሚል ንግግርን ማሰማቱና በደልንና ኀጢአትን በሰው ፊት መግለጡ አይቀሬ ነው።

የምንሸሸግበት ጥላችን የምንደርስበት ወደባችን ማረፊያችን እርሱ ነው።
በደላችንን ሲሸሽግ ምህረቱን ደግሞ በአደባባይ የሚሰጥ ቅዱስ ነው።

“በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ እግዚአብሔር ይመስገን።”
— መዝሙር 31፥21
በኀጢአታችን ምክንያት የፊቱን ጸዳል የማያጨልምብን ፣ የምህረት የሆኑ ቀናትን ሲጨምርልን እጃችንን በአፋችን የሚያስጭነን ክቡር ነው።

ሊምረን ሁሌም ሊቀድሰን ደግሞም በጸጋው እየሞላ ሊያድሰን ዘንድ እለት ተእለት የሚሻ ደግ ሳምራዊ ነው።

ልጆች ተብለን ከተጠራን ዘንድ ምህረቱን ተማምነን ልንጓዝ ይገባናል።

ዲያቆን የኋላሸት ይኸነው

ጥር 29/201 ዓ.ም
#ከሌለህበት_አታኑረኝ

የኔ አባት ጌታ ሆይ ሁልጊዜም አንተን ማግኘት ፣በአባትነትህ ፍቅር መጎብኘት፣ በአንተ ጥላነት መጠለል፣ በቸርነትህ ከነፍስም ሆነ ከስጋ ውጣ ውረድ መገላገል፣ ብቻ ሰላምን የሚያድለውን ያንተን ድምጽ መስማት ሁልጊዜም ይናፍቀኛል።

አባ ብቸኝነት፣ ካንተ ይልቅ የሚባል ህይወት እንዴት ይጨንቃል።
ካለመገኘትህ መኖር ፣ ካላንተ መጓዝ ለካ በድቅድቅ ጨለማ የመጓዝን አስፈሪነት ያስንቃል።

ካለስምህ ለካ ማዕረጌ ሁሉ ባዶ እውቀቴ ጎደሎ የማይጠቅም ሞኝነት ነው።
እና የኔ አባት ጌታ ኢየሱስ ሆይ በምህረትህ ብዛት በልቤ ጓዳ ተመላለስ
ቃልህን ሰምቼ የምኖር እና የማደርገው እሆን ዘንድ ቅዱስ መንፈስህን አድለኝ።
የመዳኒቴ አምላክ ሆይ አንተነትህ በማይነገርበት አደባባይ አታቁመኝ

አንተ ከሌለህበት የስም አጠራሬ ይኖር ዘንድ አትተወኝ።
ይልቁኑ አንተ ካለህ ረሀቡ ጥጋብ ድቅድቁ ብርሀን ገደሉ ሜዳ መከራው ደስታ ፈተናው የክብር ይሆንልኛል።

የኔ አባት አኪያዬ ጌታ መድኀኒአለም
አንተ ካለህ ሲኦል እንኳን ገነት ይሆናል።
ስለዚህ ባርከኝና ከእቅፍህ አግባኝ።

ዘመኔን ቀድሰው።
ባንተ ቤት በእቅፍህ ያልቅ ዘንድ ይሁን
አሜን

ዲያቆን የኋላሸት ይኸነው
የካቲት 5/2016
ባህርዳር
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ትንቢተ ዮናስ Jonah 1

ምዕራፍ፡1።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደዐማቴ፡ልጅ፡ወደ፡ዮናስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤ተነሥተኽ፡ወደዚያች፡ወደ፡ታላቂቱ፡ከተማ፡ወደ፡ነነዌ፡ኺድ፥ክፋታቸውም፡ወደ፡ፊቴ፡
ወጥቷልና፥በርሷ፡ላይ፡ስበክ።
3፤ዮናስ፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ወደ፡ተርሴስ፡ይኰበልል፡ዘንድ፡ተነሣ፤ወደ፡ኢዮጴም፡ወረደ፥ወደ፡
ተርሴስም፡የምታልፍ፡መርከብ፡አገኘ፤ከእግዚአብሔርም፡ፊት፡ኰብሎ፟፡ከነርሱ፡ጋራ፡ወደ፡ተርሴስ፡ይኼድ፡
ዘንድ፡ዋጋ፡ሰጥቶ፡ወደ፡ርሷ፡ገባ።
4፤እግዚአብሔርም፡በባሕሩ፡ላይ፡ታላቅ፡ነፋስን፡አመጣ፥በባሕርም፡ላይ፡ታላቅ፡ማዕበል፡ኾነ፥መርከቢቱም፡
ልትሰበር፡ቀረበች።
5፤መርከበኛዎቹም፡ፈሩ፥እያንዳንዱም፡ወደ፡አምላኩ፡ጮኸ፤መርከቢቱም፡እንድትቀል፟ላቸው፡በውስጧ፡
የነበረውን፡ዕቃ፡ወደ፡ባሕር፡ጣሉት፤ዮናስ፡ግን፡ወደ፡መርከቡ፡ውስጠኛው፡ክፍል፡ወርዶ፡ነበር፥በከባድ፡
እንቅልፍም፡ተኝቶ፡ነበር።
6፤የመርከቡም፡አለቃ፡ወደ፡ርሱ፡ቀርቦ፦ምነው፡ተኝተኻል፧እንዳንጠፋ፡እግዚአብሔር፡ያስበን፡እንደ፡ኾነ፡
ተነሥተኽ፡አምላክኽን፡ጥራ፡አለው።
7፤ርስ፡በርሳቸውም፦ይህ፡ክፉ፡ነገር፡በማን፡ምክንያት፡እንዳገኘን፡እናውቅ፡ዘንድ፡ኑ፥ዕጣ፡እንጣጣል፡
ተባባሉ።ዕጣም፡ተጣጣሉ፥ዕጣውም፡በዮናስ፡ላይ፡ወደቀ።
8፤የዚያን፡ጊዜም፦ይህ፡ክፉ፡ነገር፡በማን፡ምክንያት፡እንዳገኘን፡እባክኽ፡ንገረን፤ሥራኽ፡ምንድር፡
ነው፧ከወዴትስ፡መጣኽ፧አገርኽስ፡ወዴት፡ነው፧ወይስ፡ከማን፡ወገን፡ነኽ፧አሉት።
9፤ርሱም፦እኔ፡ዕብራዊ፡ነኝ፤ባሕሩንና፡የብሱን፡የፈጠረውን፡የሰማይን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡
አመልካለኹ፡አላቸው።
10፤እነዚያም፡ሰዎች፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡እንደ፡ኰበለለ፡ርሱ፡ስለ፡ነገራቸው፡ዐውቀዋልና፥እጅግ፡
ፈርተው፦ይህ፡ያደረግኸው፡ምንድር፡ነው፧አሉት።
11፤ባሕሩንም፡ሞገዱ፡አጥብቆ፡ያናውጠው፡ነበርና፦ባሕሩ፡ከእኛ፡ዘንድ፡ጸጥ፡እንዲል፡ምን፡
እናድርግብኽ፧አሉት።
12፤ርሱም፦ይህ፡ታላቅ፡ማዕበል፡በእኔ፡ምክንያት፡እንዳገኛችኹ፡ዐውቃለኹና፡አንሥታችኹ፡ወደ፡ባሕር፡
ጣሉኝ፥ባሕሩም፡ጸጥ፡ይልላችዃል፡አላቸው።
13፤ሰዎቹ፡ግን፡ወደ፡ምድሩ፡ሊመለሱ፡አጥብቀው፡ቀዘፉ፤ዳሩ፡ግን፡ባሕሩ፡እጅግ፡አብዝቶ፡ይናወጥባቸው፡
ነበርና፥አልቻሉም።
14፤ስለዚህ፥ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸው፦አቤቱ፥እንደ፡ወደድኽ፡
አድርገኻልና፥እንለምንኻለን፤አቤቱ፥ስለዚህ፡ሰው፡ነፍስ፡እንዳንጠፋ፡ንጹሕም፡ደም፡በእኛ፡ላይ፡
እንዳታደርግ፡እንለምንኻለን፡አሉ።
15፤ዮናስንም፡ወስደው፡ወደ፡ባሕሩ፡ጣሉት፤ባሕሩም፡ከመናወጡ፡ጸጥ፡አለ።
16፤ሰዎችም፡እግዚአብሔርን፡እጅግ፡ፈሩ፥ለእግዚአብሔርም፡መሥዋዕትን፡አቀረቡ፥ስእለትንም፡ተሳሉ።
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (@sarina)
ሠላም ውድ ክርስታያኖች ዛሬ የአብይ ፃም ዋዜማ ላይ ነን እና እንኳን አደረሳችሁ ። ቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያውን ሳምንትዘወረደ ሲል ሰይሞታል ።ይኽም የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ መውረድ ምንማማርበት ሳምንት ነው። ጌታ ቢፈቅድ ሰፋ አርገን ሁሉንም ለማየት እንሞክራለን ። ወአልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እም ሰማይ። ከሰማይ ከወረደው ከክርስቶስ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም። እስመ ዘእምላዕሉ መጽዐ መልዕልተ ኩሉ ውእቱ ።ከሰማይ የመጣው እርሱ ከሁሉ በላይ ነውና። ዮሐ 3:13 እስከፍፃሜ አንብቡት።ሰናይ ወርኀ ፃም ያድርግልን ።ወስበሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (የኋላሸት)
Audio
#ቀዳሜ_ጸጋ
መዝሙር
Forwarded from RAMA (Wintana)
2. ቅድስት
ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaedit2
Share 🙏
https://www.tg-me.com/joinchat-V2t-Wam1Ovdhi6op
#ቅድስት
#ዘማሪ ዲ/ን ቀዳሜፀጋ ዮሐንስ @Z_TEWODROS
#ሰንበተ_ክርስትያን

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
#አዝ
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
#አዝ
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
#አዝ
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💚
💛 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💛
💖 •✥• @Z_TEWODROS •✥• 💖
ደም ግባት አልባ 16k
በሊቀመዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
#ደም_ግባት_አልባ

ጌታዬ ሆነ ደም ግባት አልባ
ጀርባው በጅራፍ ስለኔ ደማ
የኔን መገርፍ እርሱ ተገርፎ
ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ ( ፪ )

በሀሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ
ጌታ ተያዘ ህይወቴን ፈቅዶ
ክፉዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ
ለኔ ግን ሆኗል መዉጫ መንገዴ(፪)
#ታስረኃል_ስለኔ_ኢየሱስ_መድኅኔ(፪)

(አገቱኒ ከለባተ ብዙኀ ወአኀዙኒ ማህበሮሙ ለእኩያን
አገቱኒ ከለባተ ብዙኀ)
#አዝ
ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፉ
የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፉ
በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ
እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ(፪)
#ታርደኃል_ስለኔ_ኢየሱስ_መድኅኔ(፪)
(ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ)
#አዝ
ህይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑ
ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ
እጅ እግሩን ምስማር ሲቸነክረዉ
የሞትን እሾህ ከኔ ነቀለው(፪)
#ተወጋ_ስለኔ_ኢየሱስ_መድኅኔ(፪)

(ወወደዩ ሃሞተ ውስተ መብልየ ወአሰተዩኒ ምሂአ ለፅምእየ
ወወደዩ ሃሞተ ውስተ መብልየ)
#አዝ
እርቃኑን ሆኖ ፈተለው ልብሴን
አንዲሁ ወዶኝ ጠጣ ሆምጣጤን
በምህረቱ ጠል ነብሴን አርክቶ
አለመለመኝ አርሱ ተጠምቶ (፪)
#ተጠማ_ስለኔ_ኢየሱስ_መድኅኔ(፪)

ሊቀመዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
✧┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✧
•✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥•
@Z_TEWODROS
•✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥•
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
"እግዚአብሔር መልካም ነው" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 24k
ማኅቶት ቲዩብ - Mahtot Tube
#እግዚአብሔር_መልካም_ነው

እግዚአብሔር መልካም ነው
በመከራ ቀንም መሸሽጊያ ነው (2)

ከገነት ሲሰደድ አዳም አባታችን
ሞት ነግሦብን ሳለ በእኛ በሁላችን
ቃል እንደገባለት ተወልዶ ሊያድነው
በመከራ ጊዜ መሸሸጊያ ሆነው (2)
#አዝ
አብርሃም ከካራን ከእናት ከአባቱ ቤት
ከነዓን ሲገባ ሲሰደድ በእምነት
ከተሰጠው ተስፋ አንዳች ሳይጎድልበት
እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን አበዛለት (2)
#አዝ
በሃዘን በችግር በመከራ ጊዜ
ጭንቅን የሚያርቅ ነው የነፍስን ትካዜ
የቀድመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ
እግዚአብሔር መልካም ነው ሃዘኔን አስረሳኝ
የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ
ከርስቶስ ኢየሱስ ሀዘኔን አስረሳኝ

ሊቀመዘምራን
ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
✧┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✧
•✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥•
@Z_TEWODROS
•✥• 🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥•
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
ሕማማት ክፍል 1
@kokuha_haymanot
#ህማማት
የዲያቆን ሄኖክ ኀይሌ መጽሐፍ
#አሳልፎ_የሚሰጥህ_ማነው?
የመጀመሪያው ቁስል
@eotchntc
ሕማማት ክፍል 2
@ኰኲሐ ሃይማኖት
" #ሕማማት "

ክፍል 2

"ይሁዳ የመረጠው ጌታ"

#ጸሐፊዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

#ተራኪኢዮብ ዮናስ
@eotchntc
ሕማማት ክፍል 03
የ መዝሙር ግጥሞች
ሕማማት ክፍል 03

👉 የይሁዳ እግሮች
ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ቢኒያም ብርሃኑ

#ሼር
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
Audio
" #ሕማማት "

ክፍል 4

"የጦር መሪው ይሁዳ"

#ጸሐፊዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

#ተራኪኢዮብ ዮናስ
Audio
" #ሕማማት "

ክፍል 5

"ከማቁሰል የከፋ መሳም"

#ጸሐፊዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

#ተራኪኢዮብ ዮናስ
2024/05/19 20:44:32
Back to Top
HTML Embed Code: