Telegram Web Link
Forwarded from Quality button
ወንጌላዊው ዮሐንስ ስንት መልዕክታትን ፅፏል?
#እነሆ_አዲስ_ዓመት


መዝሙር 65
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።
¹² የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።
¹³ ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም።

ውድ የሆናችሁ በክርስቶስ የተዋጃችሁ ክርስቲያኖች  በክርስቶስ ፍቅር  ሰላም እላችኋለሁ ።
እነሆ እንደ ጌታ መልካምና ቅዱስ ፈቃድ አዲስ ዓመት ላይ እንገኛለን።

የደረስነው ከኛ ሳይሆን ከፍቅሩና ከምህረቱ ብሎም ከቸርነቱ የተነሳ ነው።
እግዚአብሔር  በዘመናት ፍሰት ውስጥ የነበረ መግቦቱንና ጠብቆቱን ሳያቋርጥብን ለዚህ አበቃን።
አዲስ ዓመት የአዲስ ነገሮች ሀሳቦችና ክዋኔዎች ማቀጃ አለፍ ሲልም መፈጸሚያ ነው።
ስለሆነም  ብዙዎቻችን ብዙ እቅድ ይኖረናል።
በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊው ነገር
ነገር ግን በእቅዶቻችን ሁሉ ግን በክርስቶስ  የተወደድን ክርስቲያኖች መሆናችንን ልናስብ ያስፈልገናል።
አዲስ ዓመት ቁጥር አሳልፎ ቁጥርን የመቀበል
የቁጥር ጨዋታ  ሊሆንብን  አይገባም። እኛ እኮ ከአባታችን ከኢየሱስ  ነን ኢየሱስ  ደግሞ ፍቅር በረከት ፣ቸርነት፣ ደስታ ፣ህይወት ነው።እኛ ደግሞ  በአዲስ ዓመት እርሱን  ልንመስለው ይገባናል።

ከእቅዶቻችን መካከል ጌታችንን  ኢየሱስን  ደስ የሚያሰኘውን ነገር ብቻ እንከውን።
ስራዎቻችንን ስንሰራ በድፍረት ወደ ኢየሱስ  መመልከት ከቻልን በትክክል ያ መልካም እቅድ ነው።

በሱስ፣በዝሙት፣በሴተኛ አዳሪነት፣በዘፋኝነት እና በሌላ ያለን ካለን ጌታ የሞተለትን ቤተመቅደስ  የተባለ ሰውነታችንን እንጠብቀው በጸሎት ወደ ጸጋው ዙፋን እንቅረብ።
ጌታ ኢየሱስ  ዘወትር ሊምረን የታመነ ነው።
ጌታ አንድ ነገርን አይችልም  ይቅር አለማለትን

በመሆኑም ከልባችን ሆነን በአዲሱ ዓመት እንለምነው እንዲባርከን

መልካም አዲስ ዓመት
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
💁 " ፍልሰታ " ማለት ምን ማለት ነው
#የቃሉን_ወተት

1ኛ ጢሞቴዎስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤
¹³ አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፥
¹⁴ የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ።
¹⁵ ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤
¹⁶ ስለዚህ ግን፥ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ፥ ምህረትን አገኘሁ።
¹⁷ ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የቃሉን_ወተት

መዝሙር 81
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በረድኤታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ።
² ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር፤
³ በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤


⁵ ከግብጽ በወጣ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክር አቆመው። ያላወቅሁትን ቋንቋ ሰማሁ።
⁶ ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።
⁷ በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ አዳንሁህም፥ በተሰወረ ዐውሎም መለስሁልህ፥ በክርክር ውኃ ዘንድም ፈተንሁህ።
⁸ ሕዝቤ ሆይ፥ስማኝ እነግርሃለሁም፤ እስራኤል ሆይ፥ እመሰክርልሃለሁ።
⁹ አንተስ ብትሰማኝ ሌላ አምላክ አይሆንልህም፥ ለሌላ አምላክም አትሰግድም።
¹⁰ ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ አፍህን አስፋ እሞላዋለሁም።
Forwarded from quality botton
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስንት መልእክታትን ጽፏል??
#የቃሉን_ወተት

ያዕቆብ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
²-³ ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት
⁴ ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።


⁶ ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።
⁷-⁸ ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።
⁹-¹⁰ የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና።
¹¹ ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።
¹² በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
¹³ ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።
#ትምህርት
ዮሐንስ 3
#የቃሉን_ወተት

ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
¹⁷ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
¹⁸ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።
¹⁹ ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።
²⁰ ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤
²¹ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።
#የቃሉን_ወተት

1ኛ ቆሮንቶስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³-⁴ ለሚመረምሩኝ መልሴ ይህ ነው። ልንበላና ልንጠጣ መብት የለንምን?
⁵ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ኬፋም፥ እኅት ሚስታችንን ይዘን ልንዞር መብት የለንምን?
⁶ ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?
⁷ ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይስ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
⁸ ይህን በሰው ሥልጣን ብቻ እላለሁን?
⁹ ሕግስ ደግሞ ያን አይልምን? የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር ተብሎ በሙሴ ሕግ ተጽፎአልና። እግዚአብሔርስ ስለ በሬዎች ይገደዋልን?
¹⁰ ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ የሚያበራይም እንዲካፈል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው በእውነት ስለ እኛ ተጽፎአል።
¹¹ እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን?
¹² ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ ይልቁን እንዴታ? ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ በዚህ መብት አልተጠቀምንም።
¹³ በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን?
¹⁴ እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል።
¹⁵ እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና።
¹⁶ ወንጌልን ብሰብክ እንኳ የምመካበት የለኝም፤ ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።
Forwarded from 💎Super📣ፕሮሞሽን
ወንጌላዊው ዮሐንስ ስንት መልዕክታትን ፅፏል?
Forwarded from Quality button
ናሁ ማለት ምን ማለት ነው?
Forwarded from Quality button
🌿🌿🌿መንፈሳዊ ጥያቄዎች 🍀🍀




1, ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
2, ሰንበት በብሉይ ቅዳሜ, በሐዲስ እሁድ ለምን ሆነ?
3, አእማደ ሚሥጢራት ለምን ሚሥጢር ተባለ?
4, 10ሩን የቅድስና ማዕረጋት ዘርዝሩ?
5, ሚሥጢር ማለት ምን ማለት ነው ?
6, ሚሥጢረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው?


መልስ ለማግኘት👇👇👇
#የቃሉን_ወተት

መዝሙር 23
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
² በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
³ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
⁴ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
⁵ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
⁶ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።
#የቃሉን_ወተት

“ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?”
— ሮሜ 8፥35
Audio
#የማለዳ_ጣዕም

መዝሙር

ሊቀ መዘምራን ቴውድሮስ ዮሴፍ
2025/07/08 01:53:17
Back to Top
HTML Embed Code: