#የመናብርት አለቃ የቅዱስ ሩፋኤል የቅዳሴ ቤቱ በዓለ ክብር በቢሾፍቱ ከተማ ደብረዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን
ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም
ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም
#የቃሉን_ወተት
1ኛ ዮሐንስ 1
7: ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
8: ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
9: በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።

Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (ማስያስ (መሲህ ሆይ) በመንፈስና በእውነት እንሰግድልሀለን)
የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በደሎ ደብረሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
ታህሳስ 19/2016
ታህሳስ 19/2016
#በቅርብ ቀን
በሐዲስ ኪዳን ጥናት
ሮሜ 8:26-34
መንፈስ ቅዱስ ይማልድልናል
የሚማልደው .....
እናያለን
coming soon
Study of the New Testament
Romans 8:26-34
The Holy Spirit intercedes for us
The intercessor...
let's see
yeroo dhiyootti
Qo'annoo Kakuu Haaraa
Roomaa 8:26-34
Hafuurri Qulqulluun nuuf kadhata
Araarsummaan...
mee haa ilaallu
jedhamtu
@eotchntc
በሐዲስ ኪዳን ጥናት
ሮሜ 8:26-34
መንፈስ ቅዱስ ይማልድልናል
የሚማልደው .....
እናያለን
coming soon
Study of the New Testament
Romans 8:26-34
The Holy Spirit intercedes for us
The intercessor...
let's see
yeroo dhiyootti
Qo'annoo Kakuu Haaraa
Roomaa 8:26-34
Hafuurri Qulqulluun nuuf kadhata
Araarsummaan...
mee haa ilaallu
jedhamtu
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (Y)
#የስጦታ_በዓል
አንድያ አምላክ አብ አባታችን
የሚወደውን አንድያ ልጁን የሰጠበት
ከዕለታት ሁሉ የተዋበች የላቀች እና የተቀደሰች ዕለት
በዚህ ስጦታ መድኃኒትነት ያመነ ሁሉ የሚድንበት ዘላለማዊ መድኃኒት
ዮሐንስ 3 :16
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
ዲያቆን የኋላሸት
26/4/2017 ዓ.ም

#gift_festival
The only God is our father
He gave his beloved only son
The most beautiful and sacred day of all days
This gift is an eternal medicine that will save everyone who believes in it
John 3:16
For God so loved the world that he gave his only begotten Son, that whoever believes in him should not perish, but have eternal life.
#ayyaana_kennaa
Waaqa tokkicha abbaa keenya
Ilma tokkicha isaa isa jaallatamaa kenne
Guyyaa hunda caalaa bareedaa fi qulqulluu
Kennaan kun qoricha bara baraa nama itti amanu hunda fayyisudha
Yohaannis 3:16
Waaqayyo akkasitti tokkicha ilma isaa hamma kennuutti biyya lafaa jaallate, isatti kan amanu hundinuu jireenya bara baraa akka qabaatuuf malee akka hin badneef.

#የተወለደው_የአይሁድ_ንጉሥ‼️
በእውነቱ ንጉሥ ለተወልዶ በይሁዳ ቢነግስ አያስገርምም ።
ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራተኛው ክፍለዘመን እንዲሁም ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ መጀመሪያው ክፍለ ዘመን በዓመቱ በ አራተኛው ወር ከቀኑ በ28/29ኛው ቀን የተሰማው ዜና ግን ከዚህ በፊትም ያልተሰማ ከዚህም በኋላ ደግሞ መቼም የማይሰማ በመላእክቱ የተደነቀ በእረኞች የተወደደ የተመሰገነ ተናፋቂ የነበረ ታላቅ ዜና ነው።
ይህም ዜና ለተጣሉት ተስፋን ለተበተኑትን አንድነትን የሚሰጥ ዜና ነው።
“መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤”
— ሉቃስ 2፥10
እንግዲህ መልአኩ ለእናንተ ብቻ ያይደለ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ዜና እነግረለሁ ያለው የቱን ዜና ምን ያክል የገዘፈውን ምስራች ይሆን?
የዚህን ጥያቄ መልስ ከራሱ ከመልአኩ እናገኘዋለን ።
“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
— ሉቃስ 2፥11
ይህ ዜና ለእረኞች ብቻ የመጣ አይደለም በወቅቱ በንግስና በክብር ለነበሩትም እንጂ
እውነተኛው ንጉሥ በግልጥ ተገልጧልና በመሆኑ
እነርሱም አርፈው ሊቀመጡ አይችሉም።
ንጉሡን ማሰስ ማግኘት ከዛም መስገድና አምሃቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለዚህም ከምስራቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ ቤተልሔም መጡ።
“ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።”
— ማቴዎስ 2፥1-2
መቼ ይህ ብቻ ሆነና በዚህ ንጉሥ ልደት ሰማያውያን ኀይላት ሳይቀር ታዘዙ። ልደቱን ለሰዎች ለማብሰር ሲፋጠኑ ታዩ ኮከብ ራሱ
ከተፈጥሮ ስርዓት ውጭ በመሆን መንገድ መሪ ሆነ።
“እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።”
— ማቴዎስ 2፥9
ይህ የተወለደው ንጉሥ ለመንገድ የሚሆን GPS ወይም location service አላስፈለገውም።
⭐💫⭐💫⭐💫⭐💫⭐💫
በ ኤፍራታ በስጋ ከድንግል ማርያም የተወለደው ንጉሥ ለንግስናው የአባቱን ዳዊት ንግሥናን ለማስቀጠል ታላላቅ በሆኑ በእንቁ ፈርጥ በተሸለሙ ባማሩ መብራቶች ባጌጡ አብያተ ነገሥታት ወይም አብያተ መቃድስ መወለድ አላስፈለገውም።
ይልቁኑ በተናቀው ቦታ ስለ ፍጹም ትህትናው በከብቶች በረት(ግርግም) ተወለደ።
ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥
⁷ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።
ነገር ግን በበረት እንኳን ተወልዶ በሰማያት ያሉ ሰራዊት የሚያመሰግኑትበምድር ያሉ ነገሥታት
የሚሰግዱለት ንጉሥ ነው።
“ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦”
— ሉቃስ 2፥13
በምድር ያሉ ነገሥታት
የሚሰግዱለት ስጦታን የሚገብሩለት ንጉሥ ነው።
“ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።”
— ማቴዎስ 2፥11
ምን እነርሱ ብቻ እንስሳት ራሳቸው የሚሆኑትን ቢያጡ ምን እንደሚሰጡት ቢጠፋቸው ትንፋሻቸውን ለገሱት
ነገር ግን በዚህ ንጉሥ ልደት የተደሰቱ ብቻ ሳይሆን እንደ ሄሮድስ የተናደደ በየት ይገኛል።
የአይሁድ ንጉሥ ተብሎ ሲነገር ምድራዊ መንግሥት ያለውና እርሱን እንደሚቄማው በማሰብ ሊገድለው ፈለገ በዚህም ህጻናትን አስፈጀ
“ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።”
— ማቴዎስ 2፥16
እንዲሁም የቤተ መቅደስ ካህናት ጸሐፍት ፈሪሳውያን ደግሞ የተነገረውን ትንቢት እያወቁ እየተረጎሙ ግን አላስተዋሉም።
ማቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤
⁴ የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።
⁵-⁶ እነርሱም፦ አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።
ቅድስት ቤተክርስቲያን የተወለደውን ንጉሧን በሌሊት በማህሌት
ቤዛ ኩሎ ዓለም ዮም ተወልደ በማለት ስታዜም
ስብሐተ እግዚአብሔርን ስታደርስ ታድራለች።
ከዚህም በተጨማሪ
በጌታ ልደት ለምስጋና መላእክትና እረኞች መተባበራቸውን ልቦናን በሚመስጥ ዜማ
ርእይዎ ኖሎት/፪/ አእኮትዎ መላእክት/፪/
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል /፪/
ይህም በግርድፍ ትርጉሙ
ዛሬ ከቅድስት ድንግል የተወለደውንና በግርግም ተኝቶ ያለውን ሰማያዊ እረኞች አዩት መላእክቱ አመሰገኑት። በማለት
ትህትናውን በማድነቅ ደግሞ
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ ኀደረ ማኅጸነ ድንግል/፪/
በግርግም መተኛቱን በጨርቅ መጠቅለሉ ያወሳሉ
......እፎ ተሴሰየ ኀሊበ ከመ ህጻናት በሚል የዚቅ ክፍል እንደ ህጻናት ከእናቱ ጡቶች ወተትን መለመኑን ያደንቃሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጌታ መወለዱ
1. በዘመን መጨረሻ ከህግ በታች ሁኖ ተወልዶ የሰውን ልጅ ከኀጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት ይኸውም ከህግ በታች የሆነውን የሰውን ልጅ ሊዋጅ(ሊያድን)
ገላትያ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
⁵ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።
2.ስለ መወለዱ የተነገሩ ትንቢቶች ይፈጸሙ ዘንድ
“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።”
— ኢሳይያስ 7፥14
3.ኀያል አምላክ መሆኑ ይታወቅ ዘንድ
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
— ኢሳይያስ 9፥6
4.ተጣልተው የነበሩት ሰውና መላእክት በአንድነት ያመሰግኑ ዘንድ እንዲሁም ሰማይና ምድርንም አንድ ለማድረግ
ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦
¹⁴ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።
በአጠቃላይ የተወለደው ንጉሥ ወ አምላክ
ኀያል ህጻን ድንቅ መካር ኀያል ነው።
ቀዳማዊ ሲሆን ከዘመናት በኋላ በስጋተገልጦ ታየ።
በከብቶች ግርግም ተኝቶ ተገለጸ
ይህ ንጉሥ የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሁሉ አስገኚ በጽድቅ የሚፈርድ በአውነት የሚገዛ ፍጹም አምላክ (PERFECT GOD) ነው።
በመሆኑም አምልኮና ግዛት ለዘለዓለም ይገባዋል።
በዓለ ልደትን ስናከብር በእውነት የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ እንደ እረኞቹ እንደ መላእክቱ እንደ ጥበብ ሰዎች እንፈልግና ከክርስቶስ እና ከእናቱ ጋር በምልዓት እናክብር ይህም በቤተክርስቲያን ነው።
መልካም በዓል።
ዲያቆን የኋላሸት
@Yehualazemessiah
ታህሳስ 26/2016ዓ.ም