Telegram Web Link
#የከተራ_በዓል
በቢሾፍቱ ከተማ
10/5/2017 ዓ.ም
#የጥምቀት_በዓል
ድምቀቶች
በቢሾፍቱ (ደብረዘይት )
11/5/2017 ዓ.ም
#ቃና_ዘገሊላ

በእመቤታችን ምልጃ በክርስቶስ ተአምር ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበት
የውኃ በዓል
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (የኋላሸት)
ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤
² ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።
³ የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።
⁴ ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።
⁵ እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።
⁶ አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።
⁷ ኢየሱስም፦ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።
⁸ አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።
⁹ አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፦
¹⁰ ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።
¹¹ ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (የኋላሸት)
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (የኋላሸት)
ቃና_ዘገሊላkana_zegelila_የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_መዝሙር360p.mp4
6.3 MB
Track 8
Unknown Artist
ገ/ዮሐንስ "የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም"
#ከመ_ይኩን_ቤዛ
ለብሰ ስጋ ማርያም
ይቤዠን ዘንድ የማርያምን ስጋ ለበሰ

ኀዲጎ ተስዐ ወተስዐተ ነገደ
ቆመ ማዕከለ ባህር

ዘጠና ዘጠኙን ነገድ ትቶ ሰውን በመፈለግ በባህር መካከል (በዮርዳኖስ) ተገኘ
Forwarded from Quality button
ከሚከተሉት ውስጥ''ፍሰሐ'' ለሚለው ቃል ተቃራኒ የቱ ነዉ?
የእስጢፋኖስ መዝሙር
"ካድ ይሉኛል "ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

እያየውህ በቀኙ ቆመህ
ካድ ይሉኛል አሁን ሳንገልህ
ተቀበላት ነፍሴን በሰማይ
ወርዶብኛል የአይሁድ ድንጋይ
አዝ-
ከሰው እንዳልሆነ ሲያውቅ ልቦናቸው
ይወግሩን ጀመረ በሞት አስፈራርተው
ኢየሱስ ክርስቶስ ጉልበቴ አምባዬ ነው
ከእርሱ ጋር እያለው እንዴት ሞትን ልፍራው
የድንጋዩ ናዳ ምንም አልተሰማኝ
ጌታዬን በክብር ሳየው እርሱም ሲያየኝ
ከሰባቱ ዲያቆናት መሀል
አንዱ ሆንኩኝ አቤት መታደል
ጥበብና ሞገስን ሰቶኛል
የአባቶቼ በረከት ባርኮኛል/የአባቶቼ አምላክ ጠብቆኛል
አዝ-
እንድትሰባስበው ትምህረተ ኦሪት
እንድትጠፋ ደግሞ የወንጌል ብስራት
አንዱን ጌታ በግፍ ሲገድሉ በስቅለት
መቶ ሀያ ሆነው ተነሱ ለስብከት
የድንጋዩ ናዳ ምንም አልተሰማኝ
ጌታዬን በክብር ሳየው እርሱም ሲያየኝ
ሊቀ ዲያቆን እስጢፋኖስን ገድለው
ክርስትናን ሊያጠፉ አስበው
ስምንትሺው በአለም ተበተኑ
የኢየሱስን ስሙን አገነኑ/ክርስቶስን ስሙን አገነኑ/
አዝ
ከከተማ ውጪ በአፍ አውጥተው
ልባሳቸውን ሁሉ ለጎልማሳው ሰተው
ቋጥኝ የሆነውን ድንጋይ እያነሱ
ሰባበሩት ያኔ አጥንቴን ስለሱ
የድንጋዩ ናዳ ምንም አልተሰማኝ
ጌታዬን በክብር ሳየው እርሱም ሲያየኝ
ሕያው ብሆን ብሞትም ለጌታ
ክርስትና አትጠፋም ላፍታ
እንሰብካለን በአጥንት በደማችን
ኢየሱስ ነው ፈጣሪ አምላካችን(2)
አዝ-
እንዳትሰብኩ ቢሉን ወጥታችሁ ሰገነት
ሐሰትን አንሰማም ስንታዘዝ ለእውነት
አብዝተው ሲመቱት ይጠብቃል ሚስማር
ያፀናል መከራም ያደርሳል ለክብር
የድንጋዩ ናዳ ምንም አልተሰማኝ
ጌታዬን በክብር ሳየው እርሱም ሲያየኝ
ቢበተንም የእስጢፋኖስ ማዕበል
ሊበዛ ነው የክርስቲይን ቁጥር
አትደንቅጡ ደቀመዛሙርቱ
ቶሎ ያልፋል ወጀቡም ትምክህቱ(2)
አዝ--
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
     🔸
2025/07/02 12:34:40
Back to Top
HTML Embed Code: