ጌታ በአሁኑ እሁድ ይመጣ ይሆን..??

እለቱ : እሑድ
ቀኑ : 29
ወሩ : መጋቢት
ዘመኑ : ዮሐንስ

እንዲ ሲሆን ነው ኢየሱስ የሚመጣው.. ግን ደግሞ በየትኛው ዓመተ ምህረት ላይ እንደሆነ አይታወቅም.. እንዲህ የሚል ነገር በአንዳንድ መጽሐፍት ላይ ተጽፎ ይገኛል..

ግን ይሄ እይታ ብቻ እንጂ የጌታ ቤተ ክርስቲያን እምነት አይደለም.. እንደ ሌባ እንደሚመጣ ብቻ ነው ምናውቀው.. ዛሬም ይሁን ነገ ወይ ሌላ ቀን አናውቅም

@Apostolic_Answers
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (ኢየሱስ አግዚአብሔር የእግዚአብሔር ልጅ)
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽዕ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ
መዝ ፵፱-፫
እግዚአብሔርስ በግልጽ ይመጣል
አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል።
መዝ 49:1-3
የጌታችን ምጽአት በቅድስት ቤተክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜ በተለየ መልኩ ይታሰባል
ክረምት እና የደብረዘይት (እኩለ ጾም)
ላይ
ደብረዘይት በዓብይ ጾም
መካከል 5ተኛዋ ሳምንት ስትሆን
የጾሙም እኩሌታ የሚሆንበት ነው።
የወይራ ዘይት የሚፈልቅባት ቦታ ስትሆን
ጌታችንም እጅግ የሚወዳት ቦታ ናት።
በዚህች ተራራ ጌታችን ለቅዱሳን ሐዋያርት ስለዳግም ምጽአቱ የነገራቸው ቦታ ነው።
የኢየሱስ ዳግም ምጽአት እንደቀድሞ ለመወለድ ፣ለመስቀል፣የጠፋውን ሰው(አዳም)ለማዳን ሳይሆን
ለፍርድ ነው የሚመጣው
መልካም ለሰራ ንዑ ኀቤየ(ወደኔ ኑ)
ክፉ ኀጢአት ለሰራ ሑሩ እምኔየ(ከኔ ሂዱ ወግዱ) ሊል ነው።
ስለዚህ ከየትኛው ፍርድ እንድንቆጠር
እንፈልጋለን ?
ከጥሪው ወይስ ሂዱልኝ ከሚለው
ከመጀመሪያው ያድርገን።
በእለቱ በአንዳንድ አድባራት የጌታችንና የአምላካችን የመድሐኒታችን ጽላት ይከብራል።
ምጽአቱ ድንገት ነው
ልክ ሌባ ሊገድል ሊሰርቅ እንደሚመጣ ሁሉ
ስለዚህ ከኅጢአት ከዝሙት ከመከፋፈል
ተቆጥበን በቀኙ የምንቆም በጎች (አባግዕ )🐑🐑🐑🐑🐑
እንድንሆን አምላካችንን በጸሎት
በጾም በመልካም ትሩፋት እየጸናን እንለምነው።🤲🤲🤲🤲
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ደብረዘይት

@eotchntc
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (ኢየሱስ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ልጅ)
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (.yewi habesha)
✝️✝️✝️✝️✝️
እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ፃሕማ ወድካም
አመ ከመ ዮም
ያብጽሐነ ያብጽሐክሙ
በፍስሐ ወበሰላም

በሰሙነ ሕማማት የሚባል

@eotchntc
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (ኢየሱስ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ልጅ)
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (ኢየሱስ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ልጅ)
ሰኞ
#መርገመ_በለስ
#አንጽሖተ_ቤተመቅደስ
የሰሙነ ሕማማት የመጀመሪያ ቀን
ዛሬ ዕለተ ረቡዕ ምክረ አይሁድ የተከወነበት ቀን ነች
የአለሙን ፈራጅ ኢየሱስን እንደወንበዴ ለመያዝ የቆረጡበት እለት
አንድም ባለሽቶዋ ሽቶን በእግሩ ላይ ያርከፈከፈችበት
ካህናተ አይሁድ በክፋት ሲቃጠሉ እርሷ ግን በትህትና ከበረችበት

ማቴ 26:1-16


ማቴዎስ 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ኢየሱስም እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፈጸመ ጊዜ፥
² ለደቀ መዛሙርቱ፦ ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ፥ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል አለ።
³ በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥
⁴ ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ፤
⁵ ነገር ግን፦ በሕዝቡ ዘንድ ሁከት እንዳይነሣ በበዓል አይሁን አሉ።
⁶ ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥
⁷ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።
⁸ ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና፦ ይህ ጥፋት ለምንድር ነው?
⁹ ይህ በብዙ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና አሉ።
¹⁰ ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና ሴቲቱንስ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ?
¹¹ ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤
¹² እርስዋ ይህን ሽቱ በሰውነቴ ላይ አፍስሳ ለመቃብሬ አደረገች።
¹³ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል።
¹⁴ በዚያን ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ።
¹⁵ ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ? እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት።
¹⁶ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።




ዲያቆን የኋላ ዘማስያስ
ሰላም ሰላም
ዛሬ የተወደደችዋ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ
አረንጓዴዋ ሐሙስ
ጌታችን በትህትና የሐዋርያቱን እግር ያጠበበት የትሕትና ሐሙስ
ይልቁኑ ህያውና ዘላለማዊ የሆነው
ሰዎችን በፍጹም ችሎታው ከኀጢአታቸው የሚያነጻቸው የኢየሱስ ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም የተሰጠችበት ሐሙስ ናት
በአይሁድ ዘንድ ፋሲካ (የቂጣ በዓል)ትባል ነበር።

ዮሐ 13:4-20


ዮሐንስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።
⁶ ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።
⁷ ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።
⁸ ጴጥሮስም፦ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም፦ ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት።
⁹ ስምዖን ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው።
¹⁰ ኢየሱስም፦ የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።
¹¹ አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና፤ ስለዚህ፦ ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም አለው።
¹² እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው፦ ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?
¹³ እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።
¹⁴ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።
¹⁵ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
¹⁶ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።
¹⁷ ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።
¹⁸ ስለ ሁላችሁ አልናገርም፤ እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ፦ እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣብኝ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
¹⁹ በሆነ ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ፥ ከአሁን ጀምሬ አስቀድሞ ሳይሆን እነግራችኋለሁ።
²⁰ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ማናቸውን የምልከውን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።



ዲያቆን የኋላ ዘማስያስ
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (ማስያስ (መሲህ ሆይ) በመንፈስና በእውነት እንሰግድልሀለን)
ዕለተ_ሐሙስ
#ዕጽበተ_ሐሙስ
ይህ ቀን የጌታ ትህትና በአባቶች ካህናት የሚታይበት ውብ ዕለት
Forwarded from የጥያቄዎቻችሁ መልስ (አቡ (ወንዴ))
ስሙን ሕማማት ዕለተ ሐሙስ
:-የጸሎት፣ የምስጢር፣ የሐዲስ ኪዳን፣ የነጻነት፣ የእግር መታጠብ፣ አረንጓዴው ቀን።

በዚህ ዕለት በቤተክርስቲያናችን የሚኖረው ሥርዓት
@ApostolicSuccession
#ዛሬ እለተ አርብ

አለም ከተፈጠረ በኋላ በ አርብ እለት የሰውን ልጅ በአርያውና በአምሳሉ  ፈጠረው።
ነገር ግን የራሱን አርያና መልክ  ቅዱስ ባህሪ ከፈጠረው ሰው ባጣ ጊዜ
ይህንን መጎስቆል  አስ ወግዶ
በጸጋ ሊሞላው በእግዚአብሔር  ክብር  ይኖር የነበረው።  እግዚአብሔርነት ያለው  ፍጹም እግዚአብሔር  የሆነው የናዝሬቱ ኢየሱስ  በፍቅር ተስቦ ከ ጸባኦት ወረደ።
መምጣቱ ፣በፈጠረው  በባሪያው መልክ ሲመጣ ፣የአብርሃምን ዘር ሲካፈል፣ ወንድም ተብሎ ለመጠራት አላፈረም።
ሊራራልን ደግሞ የማይችል ሊቀ ካህናት አልሆነልንም።
በስጋ ማርያም መገለጡ  በመስቀል መሞቱ  እግዚአብሔርነቱን እንደመቀማት አልቆጠረውም።
በመሆኑም  በጽንሰቱ የጀመረውን ድህነታችንን ከዛሬ 1982ዓመት በፊት ትናት ሐሙስ ማታ 3ሰአት ተይዞ ሲዘበትበት ሲመቱት አድሮ በእለተ አርብ በ 3ት ሰአት ለፍርድ ቀረበ።
ሊቀ ካህናት ክርስቶስ በሊቀ ካህናት ቀያፋ ፊት፣ ንጉሠ ሰማይ ወ ምድር በሀገረ ገዢዎቹ በ ጲላጦስና በ ሄሮድስ ፊት። ለነገሩ በእርሱ ፍርድ መቆም በጭራሽ የማይስማሙት ሀገረ ገዢዎች ታርቀዋል።
ቀጥሎም  መንፈስ ቅዱስ ቀያፋን ባናገረው መሠረት ሁሉ ከሚሞቱ አንዱ ቢሞት ይሻላል  እንዳለ በእንጨት መስቀል
ተሰቀለ።
እናም ዕለተ ሐሙስ የጀመረውን ሐዲስ ኪዳን ግልጽ አድረጎ ፈጽሞ ሰራው
ፀሐይ ጨለመች ጨረቃ ደም ሆነች
የመቅደሱ መጋረጃ ተቀደደ
የ5500ኩነኔ እና የባህሪ መጎስቆል በክርስቶስ  ኢየሱስ ቀረልን።
ከአባቱ ከራሱም ጋር እንዲሁ ከመንፈሱ ጋር አስታረቀን።

9:00 ሰአት
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በስጋ

በስጋው የኛ ጌታ ሞተ
መለኮት ያልተለየው ስጋ ሞተ።
ክርስቶስ ኢየሱስ ነፍሱን ከስጋው ለየ
ኦ አባ አማኅጽን ነፍስየ....አባቴ ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ ሲል ነው።

11:00ሰአት በአካለ ስጋ መቃብር በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ  ለተጨነቁ ሁሉ ሰላምን ሰበከላቸው።
ነጻ አደረጋቸው አደረገን።
ሀሌሉያ ዮሴፍ ወ ኒቆዲሞስ  ገነዝዎ ለኢየሱስ  በሰንዱናንት ለዘተንሥአ እሙታን ....
ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ገነዙት ሲል።

መልካም የስቅለት በዓል
4k channel megzat yemifeleg inbox me @kingo8
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (ማስያስ (መሲህ ሆይ) በመንፈስና በእውነት እንሰግድልሀለን)
#ቀዳሚት_ስዑር
በብሉይ ኪዳን ፍጥረታትን ከመፍጠር ባረፈባት እለት በመቃብር መለኮት ባልተለየው በአካለ ሥጋ ወረደ
ጌታ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር
በአካለ ነፍስ ወደሲኦል በመውረድ ሰላምን እና መዳንን ለሚሹት ሰላምን ሰበከላቸውና ነጻ አወጣቸው

ኤፌሶን 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴-¹⁵ እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥
¹⁶ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።
¹⁷ መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤
¹⁸ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።
¹⁹ እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።
Audio
#ተነስቷል
መዝሙር
Audio
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"

"ክርስቶስ መሥዋዕቱን ስለ ሁላችንም ኾኖ አቀረበ፡፡ ከመጀመሪያው ጥፋት ተጠያቂነት ሁላችንም ነጻ ያደርገን ዘንድ መቅደስ ሰውነቱን ስለ ሁላችን ሲል ለሞት አሳልፎ ሰጠ ፡፡"
ቅዱስ አትናቴዎስ

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ

መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን !!!
Audio
አልቻለውም ፍጹም ሞት ይዞ ሊያስቀረው
ተነስቷል ጌታችን እንደተናገረዉ
ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ በስተመጨረሻ የተናገራት ቃል ምን ነበረች?
2024/05/08 04:05:51
Back to Top
HTML Embed Code: