#ስለ_ፍትሓዊ__ሹም #ክፍል_1

አላህ እንዲህ ብሏል፦
“አላህ በማስተካከል፣ በማሰመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል።” (አን_ነሕል፡ 90)

“በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም። አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና።” (አል ሑጁራት፡ 9)

#ሐዲሥ 79 / 659

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሰባት ሰዎችን አላህ ከርሱ ውጭ ሌላ ጥላ በማይኖርበት ቀን ከጥላው ሥር ያስጠልላቸዋል። እነርሱም ፍትሓዊ መሪ፣ አላህን እያመለከ ያደገ ወጣት፣ ልቦናው ከመስጊድ ላይ የተንጠለጠለ (ከመስጊድ ጋር የተሳሰረ)፣ ለአላህ ሲሉ የተዋደዱ፥ በርሱ የተገናኙና በርሱው የተለያዩ ሁለት ስዎች፣ ክብርና ውበት ያላት እንስት (ለወሲብ) ጋብዛው፦ “አላህን እፈራለሁ” ያላት (ግለሰብ) የቀኝ እጁ የምትመጸውተውን የግራ እጁ የማታይ ያክል ምጽዋትን የደበቀ (ግለሰብ) ናቸው።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

➥ ከላይ የተወሱት ሰባት የሰው ዓይነቶች ያላቸው ደረጃና ክብር።
➥ ሐዲሡ በዚህ ሪዕስ ሥር የተጠቀሰው የፍትሓዊ መሪንና ሹመኛን ክብር ለማስታወስ ነው።
➥ ኢማም አል_ቡኻሪ እንዳሉት “በአላህ ጥላ ሥር የሚጠለሉ የሰው ዓይነቶች ሰባ ያህል ቢደርሱም እዚህ ላይ ሰባቱ የተወሱት ስዩጢ እንዳሉት፦ “የፈፀሙት ተግባር ከሌሎች ይበልጥ ጎላ እና ከበድ ያለ በመሆኑ ነው።”
#ስለ_ፍትሓዊ__ሹም #ክፍል_2

#ሐዲሥ 79 / 660

ዐብደላህ ኢብኑ ዓምር ኢብነል አል ዓስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “ፍትሓዊያን ከአላህ ዘንድ ከብርሃን ሚንበሮች ላይ ይሰየማሉ። እነርሱም በሚሰጡት ፍርድ፣ በቤተሰቦቻቸው ጉዳይ እና ሹመት (ኃላፊነት) በተጣለባቸው ነገር ፍትሓዊ የሆኑ ናቸው።” (ሙስሊም ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

➥ የፍትሕ ደረጃ _በሁሉም የሕይወት መስኮች፥ ከእልፍኝ እስከ አደባባይ ተግባራዊ ሊሆን ይገባል።
➥ ፍትሓዊያን በዕለተ ቂያማ የላቀ ደረጃ አላቸው።

https://www.tg-me.com/eslamic_center
📃የረመዳንን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር

ሸይኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ:-

“የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”

ሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:-

"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው።

ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ:-

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"

በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል"

ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው።

ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።

ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።

ረመዳን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"

አላህ የረመዳን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን ያ ረ ብ ያ ረ ብ!

#ዝክረ_ረመዳን
@eslamic_center
💡ዕውቀት እና 💸ገንዘብ

📚ሸይሁል ኢስላም ኢማም ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ይላሉ፦


"ዕውቀት የነብያቶች ውርስ ነው፤ ገንዘብ የንጉሶች ውርስ ነው

ዕውቀት ባለቤቱን ይጠብቃል፤ ገንዘብ በባለቤቱ ይጠበቃል

ዕውቀት ወጪ ሲደረግበት ይጨምራል፤ ገንዘብ ወጪ ሲደረግበት ይቀንሳል

ዕውቀት ያለው ሰው ሲሞት ዕውቀቱን ይከተለዋል፤ ገንዘብ ያለው ሲሞት ገንዘቡን ይተወዋል

ዕውቀት በገንዘብ ላይ ይፈርዳል፤ ገንዘብ በዕውቀት ላይ አይፈርድም

ገንዘብ ሙስሊምም ካፊርም፣ ሙዕሚንም ፋሲቅም ያገኘዋል፤ ጠቃሚ ዕውቀት ግን ሙዕሚን እንጂ አያገኘውም

ዕውቀት ያለው ሰው ንጉሶችም ተራ ሰዎችም ወደ እሱ ፈላጊ ናቸው፤ ገንዘብ ያለው ግን ድሆችና ችግረኞች እንጂ ወደ እሱ አይፈልጉም"
مفتاح دار السعادة : (413/1)

📖አንብብ📖
ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል
https://www.tg-me.com/joinchat-@eslamic_center
«ሰሑርን» በተመለከተ ጥቂት ጥቆማዎች‼️
===============================
✍️ ሰሑር ማለት በጾም ወቅት ትክክለኛው ጎህ ከመውጣቱ በስተፊት በሌሊቱ ክፍለ ግዜ ወደ ፈጅር አቅራቢያ የሚበላ ምግብ ነው።
ሰሑር ሱንና ነው። የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግብረውታል።
1️⃣ጥቅል ነጥቦች፥
``````````

✔️ አነስ ኢብኑ ማሊክ ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፥
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«تسحروا فإن في السحور بركة!»
"ሰሑርን ተመገቡ፣ ሰሑር በመመገብ ውስጥ በረከት አለ።"

[ቡኻሪ፥ 1921
ሙስሊም፥ 1095]
✔️ በሌላ ሐዲሥም ከዐምር ኢብኒል ዓስ በተገኘ ዘገባ ላይ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፥
«فصل ما بين صيامنا وصيام أهل الكتاب أكلة السحر!»
"በኛ ጾምና በኪታብ ባለቤቶች ጾም መካከል ያለው ልዩነት፤ ሰሑርን መመገብ ነው።"

[ሙስሊም: 1096]
እኛ ስንጾም ሰሑር እንመገባለን፣ አህለል ኪታቦች (የሁዳዎችና ነሷራዎች) ግን አይመገቡም።
✔️ አነስ ረዲየልሏሁ ዐንሁ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ እንዳለ አስተላልፈዋል፥
«تَسَحَّرْنَا مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ثُمَّ قَامَ إِلَى الصَّلاةِ قُلْتُ كَمْ كَانَ بَيْنَ الأَذَانِ وَالسَّحُورِ قَالَ قَدْرُ خَمْسِينَ آيَةً!»
«ከነብዩ ﷺ ጋር ሰሑር ተመገብን። ከዚያም ወደ ሶላት ቆሙ!" አለ።
"በአዛንና በሰሑር መካከል ያለው ግዜ ስንት ይሆናል?" አልኩት! (አነስ ለዘይድ ነው የሚጠይቀው!)
(ዘይድም) ሃምሳ አንቀጽ (የሚያስቀራ ግዜ) ያክል! (ብሎ መለሰለት)»
[ቡኻሪ፥ 1821]
ይህ የሚያሳየው ሰሑርን ወደ ፈጅር ማዘግየቱ የሚወደድ መሆኑን ነው።
✔️ ዐብዱልሏህ ኢብኑል ሐሪሥ ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፥
"ከነብዩ ﷺ ባልደረቦች መካከል አንዱ እንዲህ አለ፦
መልዕክተኛው ﷺ ሰሑር እየተመገቡ ሳለ ገብቼ ፥

«إنها بركة أعطاكم الله إياها؛ فلا تدعوه»
"እርሷ (ሰሑር) በረካ ናት (አለባት)። እርሷን አላህ ሰጥቷችኋል፣ እንዳትተውት።" አሉኝ አለ።

[ነሳኢይ ዘግበውታል።]
✔️ ሰልማነል ፋሪስ ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፥
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«البركة في ثلاثة: في الجماعة، والثريد، والسَّحور»
"በሶስት ነገሮች ውስጥ በረካ አለ፥ በጀመዓ፣ በሠርድ (የምግብ አይነት [ስጋና ዳቦ ቅይጥ])፣ በሰሑር።"

[ጦበራኒይ ዘግበውታል።]
✔️ አቢ ሰዒዲኒል ኹድሪይ ረዲየልሏሁ ዐንሱ ባስተላለፉት ሐዲሥ ላይ ደግሞ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«السَّحور بركة؛ فلا تدعوه..!»
"ሰሑር በረካ ነው፣ እንዳትተውት።"
[አሕመድ ዘግበውታል።]
እንዲህም ብለዋል፥
«إن الله وملائكتة يصلون على المتسحّرين»
"አላህና መላእክቱ በሰሑር ተመጋቢዎች ላይ አክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ!" ]
[አሕመድ ዘግበውታል።]
*
2️⃣ሰሑርን ማዘግየት ይወደዳል!!
``````````````````````````

ሰሑር ያልተመገበ ሰው ጾሙ ትክክል ነው አይበላሽም፣ ግን ሱንናው አምልጦታል።
✔️ ስለዚህ ጉዳይ አቡበከር ኺሷስ "አሕካሙል ቁርኣን፥ 1/265" ላይ አስፍረዋል።
*
«فالسنة السحور، ولكن ليس بواجب، من لم يتسحر فلا إثم عليه، لكن ترك السنة، فينبغي أن يتسحر ولو بقليل، ليس من اللازم أن يكون كثيراً، يتسحر بما تيسر ولو تمرات أو ما تيسر من أنواع الطعام في آخر الليل»
"ሱንናው ሰሑር መመገብ ነው። ነገር ግን ግደታ አይደለም። ሰሑር ያልተመገበ በርሱ ላይ ወንጀል የለበትም። ነገር ግን ሱንናን ትቷል። በትንሽ ነገርም ቢሆን ሰሑር ሊመገብ ይገባል። ብዙ መሆኑ ግድ የሚል አይደለም። በሌሊቱ መጨረሻ ላይ በገራለት ነገር በተምሮችም ሆነ በገራለት የምግብ አይነት ሰሑር ሊመገብ ይገባል።..."

[ኢብኑ ባዝ፥ ኑሩን ዓለ ደርብ]"
✔️ እናታችን ዓኢሻእ ረዲየልሏሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፥
«عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّ بِلالا كَانَ يُؤَذِّنُ بِلَيْلٍ ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( كُلُوا وَاشْرَبُوا حَتَّى يُؤَذِّنَ ابْنُ أُمِّ مَكْتُومٍ ، فَإِنَّهُ لا يُؤَذِّنُ حَتَّى يَطْلُعَ الْفَجْرُ ) »
"ቢላል በሌሊት አዛን ያደርግ ነበር። ረሱልሏህ ﷺ እንዲህ አሉ፥ «ኢብኑ መክቱም (ዐብዱልሏህ) አዛን እስከሚል ድረስ ብሉ፣ ጠጡ፤ እርሱ ፈጅር ሳይወጣ አዛን አይልም።»"

[ቡኻሪ፥ 1919
ሙስሊም፥ 1092"
✔️ ኢማመ ነወዊይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፥
«اتَّفَقَ أَصْحَابُنَا وَغَيْرُهُمْ مِنْ الْعُلَمَاءِ عَلَى أَنَّ السَّحُورَ سُنَّةٌ , وَأَنَّ تَأْخِيرَهُ أَفْضَلُ ، وَدَلِيلُ ذَلِكَ كُلُّهُ الأَحَادِيثُ الصَّحِيحَةُ , وَلأَنَّ فِيهِمَا (يعني السحور وتأخيره) إعَانَةً عَلَى الصَّوْمِ , وَلأَنَّ فِيهِمَا مُخَالَفَةً لِلْكُفَّارِ...»
"ሰሑር ሱንና መሆኑንና እርሱን ማዘግየቱም በላጭ መሆኑን የኛ ባልደረቦቻችን (ሻፊዒይያዎች) እና ከዑለማዎች ሌሎችም ተስማምተዋል።
ይህንንም ሁሉም ትክክለኛ ሐዲሦች ያመላክታሉ።
በነርሱም ውስጥ (ሰሑር በመገብና በማዘግየቱ) ለጾሙ ይረዳል፣ በነርሱም ውስጥ ከሃዲያንን መቃረን አለበት።..."
[አል-መጅሙዕ፥ 6/406]
✔️ ለጂነቲ ዳኢማም ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቃ፣ በ10/284 ላይ ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልስ አስፍራለች።

ሸይኽ ኢብኑ ባዝም ተጠይቀው የመለሱት በመጅሙዐቱል ፈታዋ ኢብኑ ባዝ፥ 15/281 ላይ ይገኛል።
*
ጽሁፉ እንዳይረዝም ነው።
ዐብዱልሏህ ኢብኑ ጀብሪንም ተጠይቀው የመለሱት አለ።

|@eslamic_center
ቁርዓን የወረደው በ 23 ዓመታት ውስጥ ሲሆን 13 ዓመታት በመካ 10 ዓመታት በመዲና ነው ።
*
የጁዞች ብዛት 30 ሲሆን 114 ምዕራፎች አሉት ።
*
ታላቋ አንቀፅ 'አያተል ኩርሲ ' ስትሆን ' ሱረት አል-ኢኽላስ የቁርአንን 1/3 ትመዝናለች ።
*
ውስጡ 6,248 አንቀጾችን ይዟል፤ ከፊሉ “ሙሕከም” ከፊሉ ደግሞ “ሙተሻቢህ” ነው። “ሙሕከም” ማለትም ትርጉሙ ግልጽ የሆነ ሲሆን “ሙተሻቢሕ” ማለት ደግሞ በግልጹ የማይተሮገም የሙፈሲሮች እይታ የሚያስፈልገው ነው።
*
ረዥሙ አንቀፅ ሱረት አል በቀራህ ውሰጥ የብድር ( የደይን ) አንቀፅ ሲሆን አጭሩ አንቀፅ በአረህማን ምእራፍ ውስጥ የሚገኘው 'ሙደሀመታን' ( مدهامتان ) ነው ' ያሲን ' ( يس ) ነውም ተብሏል ።
*
29 ምዕራፎች በፊደሎች ስም ይጀምራሉ፤
*
ረዥሙ ቃል 'ፈአስቀይናኩሙሁ' ( فأسقيناكموه ) ሲሆን አጭሩ ቃል ደግሞ (طه ) ነው ።
*
የቅርቢቱ ዐለም ( الدنيا ) የሚለው ቃል እንደዚሁም የመጨረሻዋ ዐለም (اﻷخرة ) የሚሉት ቃላት 115 ጊዜያት ተጠቅሷል ።
*
5 ምዕራፎች በምስጋና (..الحمد ) ይጀምራሉ አነርሱም ፋቲሀ፣ አንዐም፣ ከህፍ፣ ሰበእ እና ፋጢር ናቸው ፤
*
7 ምዕራፎች ፈጣሪን በማጥራት ይጀምራሉ እነሱም ፦ ኢስራእ፣ አዕላ፣ተጋቡን፣ ጁምዓ ፣ ሶፍ ፣ ሀሽር እና ሀዲድ ናቸው ።
*
3 ምዕራፎች አንተ ነብይ ሆይ ! ( يا أيها النبي ) በሚል ይጀምራሉ እነሱም ፦ አህዛብ ፣ ጦላቅ እና ተህሪም ናቸው ፤
*
3 ምዕራፎች እናንተ አማኞች ሆይ ! ( يا أيها الذين آمنوا ) በሚል ይጀምራሉ እነሱም አልማኢዳ፣ ሁጁራትና ሙምተሂና ናቸው ፤
*
5 ምዕራፎች በል! (قل ) በሚል ይጀመራሉ እነሱም አልጅን፣ ካፊሩን ፣ ኢኽላስ፣ ፈለቅ እና አንናስ ናቸው ፤
*
2 ምዕራፎች እናንተ ሰዎች ሆይ ! ( يا أيها الناس ) በሚል ይጀመራሉ እነሱም አንኒሳእ እና አልሀጅ ናቸው፤
*
4 ምዕራፎች እኛ ! ( انا ) በሚል ይጀመራሉ እነሱም ፈትህ፣ ኑህ፣ አል_ቀድር እና ከውሰር ናቸው ፤
*
15 ምዕራፎች በመሀላ ይጀምራሉ እነሱም ዛርያት ፣ ጡር ፣ አንነጅም፣ ሙርሰላት፣ አንናዚዓት፣ አልቡሩጅ፣ አጧሪቅ፣ አልፈጅር፣አሽሸምስ፣ አለይል፣ አዱሀ፣ አቲን፣ አልዐድያት፣ አልዐስር፣ አሷፋት ናቸው ።
~አሏሁ አዕለም ~
@eslamic_center
የቁርኣን ግብዣ
============
ሱረቱ-ል-ከህፍ
#ጁሙዓህ
#ረመዷን18

ቃሪእ: ረዒድ ሙሐመድ አል-ኩርዲይ

@eslamic_center
የረመዳን የመጨረሻዎቹ 10 ቀኖች‼️
============================
✔️ የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት «ዐሽረል አዋኺር» ይሰኛሉ።
የረመዳን ቀናቶች ከሌሎቹ የአመቱ ቀናቶች የተለዩና የተባረኩ ናቸው።
የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ደግሞ ከሌሎቹ የረመዳን ቀናት የተለዩና ድንቅ ናቸው።
*
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከምንጊዜውም በላይ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ለየት ያሉ እንደነበሩ ከእናታችን ዐኢሻህ ረዲየልሏሁ ዐንሃ የተገኘ ሐዲሥ ይጠቁመናል።
👉ዐኢሻህ ረዲየልሏሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፥
"كان النبي - صلى الله عليه وسلم - إذا دخل العشر أحيا الليل وأيقظ أهله، وجدَّ وشدَّ المئزر"
"(የረመዳን የመሸረሻዎቹ) አስር (ቀኖች) በገቡ ጊዜ፣
ሌሊቱን ያነጉ (ሕያው ያደርጉ) ነበር፣ ቤተሰባቸውን ያነቁ ነበር፣ የሚጠነክሩና ሽርጣቸውን ያጠብቁ ነበር።"
[ቡኻሪ፥ 2014
ሙስሊም፥ 1174]

"ሽርጣቸውን ያጠብቁ ነበር!" የሚለው ገለጻ በዒባዳ ላይ ይታገሉና ይተጉ ነበር ለማለት ነው ተብሏል።
አንዳንድ ዑለሞች ደግሞ ሚስቶቻቸውን ይርቁ ነበር ለማለት የተፈለገበት የአሽሙር አገላለጽ ነው ብለዋል።
*
👉 አሁን ከርሷው በተገኘ ሌላ ሐዲሥ ላይ እንዲህ ትለናለች፥
"كان رسول الله - صلى الله عليه وسلم - يجتهد في العشر الأواخر ما لا يجتهد في غيره"

"(በረመዳን) የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ውስጥ ነብዩ ﷺ በሌሎች (ቀናት) የማይታገሉትን ይታገሉ ነበር። (በዒባዳ ይበልጥ ይበረቱ ነበር።)"
[ሙስሊም፥ 1175]
||
ከነዚህ ሁለት ሐዲሦች የምንረዳው፤
ነብያችን ﷺ በመጨረሻዎቹ የረመዳን ቀኖች ከምንግዜውም በላይ በዒባዳ ይተጉ እንደነበር ነው።
*
እነዚህን የረመዳን የመሸረሻ አስር ቀናት ይበልጥ ልዩ ከሚያደርጋቸው ነገሮች መካከል አንዱና ዋናው፣
የመወሰኛዋ ሌሊት (ለይለተል ቀድር) በነዚህ አስርት ቀናት ውስጥ የምትገኝ መሆኗ ነው።
በዚህች የተባረከች ሌሊት የሚሰራ መልካም ስራ ከሰማኒያ ሶስት አመት በላይ ከሚደረግ ስራ በላይ ይበልጣል።
||
ስለዚህ በእነዚህ የተባረኩ ቀናት ውስጥ፣
ከምንጊዜውም በላይ ራሳችንንና ቤተሰባችንን በዒባዳ ልክ እንደ ነብያችን ﷺ ልንነቃና ልናነቃ ይገባል።
||
በነዚህ ቀናት ውስጥ ነቅተን የምንሰራው ስራ ጫት በመቃም ዲቤ እየወገርን መጨፈር ሳይሆን፣
የሚከተሉትን ነው።
✔️ ለይለተል ቀድርን መጠባበቅ፣
✔️ኢዕቲካፍ መውጣት፣
✔️ቁርኣን ይበልጥ ማብዛት፣
✔️በአላህ መንገድ ላይ ሶደቃ ማውጣት፣
✔️ሌሊቱን በዒባዳ ማሳለፍ (ሐይ ማድረግ)፣
✔️ቤተሰባችንን ማንቃት፣
✔️ሽርጥን ማጥበቅ፣
✔️ተሀጁድና ሌሎች ትርፍ ሶላቶችንም ጠንቅቆ መስገድ፣

እንዲሁም ሌላም ተጨማሪ ማንኛውንም መልካም የሚባል ተግባር ከወትሮው ይልቅ ይበልጥ ማብዛት።
||
የአላህ ፈቃዱ ከሆነ፣
ኢዕቲካፍ፣ ተሀጁድ፣ ለይለተል ቀድር እና ኢዕቲካፍ የሚሉ ርዕሶችን በተናጠል የምመለስባቸው ይሆናል።


አላህ ረመዳንን የምንጠቀምበት ያድርገን።
@eslamic_center
የተሀጁድ ሶላት‼️
=============
✍️ ተሀጁድ በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ የሚሰገድ ሶላት ነው።

1) ወቅቱ፥
========
ከዒሻእ ሶላት ሱንና በኋላ እስከ ሌሊቱ መጨረሻ ድረስ ፈጅር ከመውጣቱ በፊት ባለው ጊዜ መካከል ይሰገዳል።
ነገር ግን ከእንቅልፉ መንቃት ለሚችል ሰው ወደ ሌሊቱ አንድ ሶስተኛ የመጨረሻ ክፍል ማዘግየቱ በላጭ ነው።

ይህን በተመለከተ ከእናታችን ዐኢሻህ ረዲየልሏሁ ዐንሃ የተላለፉ ሐዲሦች ይጠቁማሉ።
ከጃቢር ኢብኑ ዐብዲልላህ የተገኘ ሐዲሥም "ሶሒሕ ሙስሊም: 755" ላይ አለ።
ከአቢ ሁረይራህ በተገኘ ሐዲሥም "ሙስነድ ኢማም አሕመድ: 14/46" ላይ አሕመድ ሻኪር ዘግበውታል።
*
2) ብይኑ፥
=======
የተሀጁድ ሶላት ሱንና ነው።
ግደታ አይደለም። ግን በረመዳን ሲሆን ደግሞ ምንዳው እጥፍ ድርብ ይሆናል።
አላህ በቁርኣን ላይ እንዲህ ይላል፥
"ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት፣ በርሱ (በቁርአን) ስገድ፤ ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል። "
[አል ኢስራእ፥ 79]
*
3) ብዛቱ፥
========
የረከዓው ብዛት ገደብ የለውም።
ዝም ብሎ ሁለት ሁለት ብቻ መስገድ ነው።
ግን ረሱልሏህ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስራ አንድ ረከዓ ይሰገዱ እንደነበር ሐዲሥ የሚያመላክት ሐዲሥ አለ።
አስራ ሶስት የሚልም አለ።
*
4) የአሰጋገድ ሁኔታ፥
================
ሁለት ሁለት ረከዓ በመስገድ በመሃል ማሰላመት፣ ከዚያም ቀደ ቀጣዩ መሄድ።
*
5) ቁርኣን ሲቀራ ሶላት ላይ ድምጽ የማውጣትና ያለ ማውጣት ጉዳይ፥
===================================================
ቢያወጣም ባያወጣም ችግር የለውም።

ግን መስጅድ ላይ ከሆነ ሌላውም ሰው ሲሰማ እንዲጠቀም ድምጽ ተወጥቶ በጀህር ይሰገዳል።
*
6) ከቂያመ ለይል ጋር ልዩነቱ ምንድን ነው??
==================================
ተሀጁድ ሶላት መስገድን ብቻ ይመለከታል።
ቂያመ ለይል ግን ሶላት መስገድን ጨምሮ በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ዚክር ማድረግን፣ ቁርኣን መቅራትንና ሌሎችም ሰናይ ተግባራትን መፈጸምን ያካትታል።
*
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው የመለሱትን መልስ "መጅሙዑል ፈታዋ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፥ 11/317" በስፋት መመልከት ይቻላል።
||
በተጨማሪም፥
አል መውሱዓቱ ፊቂህይያህ፥ 34/117, 2/232
ተልኺሱል ሐቢር፥ 2/35
ተፍሲሩል ቁርጡቢይ፥ 10/307 ላይ በስፋት መመልከት ይቻላል።
@eslamic_center
▪️ዒድ ሙባረክ.

🔻የረመዷንን ወር አስጨርሶ ለደስታው የዒድ ቀን ላደረሰን አሏህ ላቅ ያለ ምስጋና ይገባው። ጾማችንን ይቀበለን ፤ ለመጪውም አመት የምንደርስ ያድርገን!! አሚን!!
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
ለመላው የቻናላችን ተከታታዮች እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።
___
📣https:/@eslamic_center
#ይህ_ወንጀል_ነው!!!

💥አስካሪ መጠጥ ፣እየጠጡ የተከለከለ ምግብ እየተመገቡ "ቢስሚል'ላህ " ማለት ክልክልና ወንጀል ነው።
ልክ እንደዚሁ በዲን የማይፈቀዱ ነገሮችን እያደረጉ፣ ለሙስሊም የማይፈቀድ መንገድ ላይ እየተጓዙ ላገኙትና ስኬት ለሚሉት እንዲሁም ለደረሱበት ደረጃ " አልሐምዱ ሊላህ " ማለት ፈጽሞ አይቻልም!።
ዘፈን፣ ካፊሮች የጀመሩት ፊልምና ድራማ እና ማንኛውም ሸሪዓ የማይፈቅደው ስራን በአላህና በቂያማ ቀን የሚያምን ሙስሊም ሊርቀው፣ ሊያፍርበትና ሊጠየፈው እንጂ ሊኮራበትና በዚህ ጌታውን ሊያመሰግን አይገባም፤ አይ ብሎ ይህን ካደረገም ይህ ተግባሩ ሌላ ተጨማሪ ወንጀልና አላህን መናቅ ወይም በዲን ማሾፍ ነው የሚሆነው።
አላህ በተከበረው ቃሉ የሚከተለውን ብሏል፥
"يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُبِينٌ(٢٠٨) " سورة البقرة.
(" እናንተ አማኞች ሆይ ሁላችሁም፣ በሁሉም ነገር ላይ ጌታችሁን መታዘዝ /ኢስላም ውስጥ ጥቅልል ብላችሁ ግቡ፤ የኢስላምን ህግ በመጣስ የሸይጣንን እርምጃ አትከተሉ፤ እርሱ ለናንተ ግልጽ ጠላት ነውና") ብሏል።
💥እውነተኛ ሙስሊም ጌታው የሚጠላውን ነገር በሙሉ ይርቃል።
ዙልሒጃ 16/1442ዓሂ
🔹 🔸🔹🔸🔹🔸
(Quran: 17: 37)

وَلَا تَمۡشِ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَحًاۖ إِنَّكَ لَن تَخۡرِقَ ٱلۡأَرۡضَ وَلَن تَبۡلُغَ ٱلۡجِبَالَ طُولٗا

በምድርም ላይ የተንበጣረረክ ሆነህ፤ አትሂድ፡፡ አንተ ፈጽሞ ምድርን አትሰረጉድምና በርዝመትም ፈጽሞ ጋራዎችን አትደርስምና፡፡
እየሱስ በምድር ቆይታው የሚያመልከው አምላክ ነበረው ወይስ አልነበረውም ?



ብዙዎቹ ክርስቲያኖች ና ፕሮቴስታንቶችን ይሄን👆👆👆 ጥያቄ (? )ስጠይቃቸው ምን ማለትህ ነው እየሱስ እራሱ አምላክ ነው እኮ ይሉኛል።እስቲ አምላክ ነበረው ወይስ አልነበረውም ሚለውን እንመልከት።


“እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤”
  — ዕብራውያን 5፥7

እየሱስ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ 😭ጋር ጸሎትንና🤲 ምልጃን አቀረበ ቆይ ቆይ አምላክ ሊሞት ይችላል እንዴ🧐? እየሱስ ሊያድነው ወደ ሚችል ቆይ ግን አምላክን ማነው ሊያድነው የሚችለው🧐? ሌላ አምላክ ካልሆነ በቀር🤷‍♂። ከብርቱ ጩኸትና 😩 ከእንባ ጋር 😭ቆይ አምላክ ወደማን ነው ሚጮኸው 😩ወደ ማንስ ነው የሚያነባው😭?ሌላ አምላክ ከሌለው በቀር🤷‍♂

እየሱስ ፀሎትንና🤲 ምልጃን አቀረበ ቆይ ወደ ማን ነው ፀሎትንና 🤲 ምልጃን አቀረበ? ለአምላኩ ካልሆነ በቀር ለማን ይሆናል? እንቀጥል 👇👇👇

እግዚአብሔርን ስለመፍራቱ ተሰማለት።አው መልሳችንን አገኘን ያን ሁሉ ጩኸትና😩 ያን ሁሉ እንባ😭 ያንሁሉ ፀሎት🤲 ያን ሁሉ ምልጃ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ነበር።

ግን እኮ እንደዚ ሲሉ ሰምቻለሁ👂።እየሱስና እግዘብሔር 1 ናቸው ሲሉ ሰምቻለሁ😫። እና እየሱስ እግዚአብሔር ከሆነ ሲጮህ😩 ፣ ሲያለቅስ 😭፣ ሲፀልይ 🤲የነበረውስ  እግዚአብሔር ነበረ ?1 ናቸው ካልን እግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ነው ሲጮህ😩 ሲያለቅስ 😭ሲፀልይ🤲 የነበረው? አያቹ 1 አይደሉም ማለት ነው።

ምክኒያቱም እግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ሊጮህ 😩፣ሊያለቅስ😭 ሊፀልይ🤲 አይችልም። ለመንቃት ባትችሉ እንኳ ለመንቃት  ሞክሩ ምን አልባት ለመንቃት ስትሞኩሩ  ትነቁ ይሆናል።

ይቀጥላል...............


እውነት ተደብቃ አትቀርም🤷🤷‍♀




ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/eslamic_center
https://www.tg-me.com/eslamic_center

https://www.tg-me.com/eslamic_center

እውነት ተደብቃ አትቀርም🤷🤷‍♀
የሽብር ጥቃት አንዋር መስጊድ አድስ አበባ
የሟቾች ቁጥር 5 ሲደርስ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው እህት ወንድሞች ደግሞ ቆስለዋል....

በእርግጥም ዛሬ መንግስታዊ ሽብር በአማኙ ላይ ተፈጽሟል... ምንም ያላደረገን ህዝብ እንዲህ በጭካኔ መግደል...?

አሁን ይሄ ጨዋ ህዝብ ... ዱላ እንኳን ያልያዘ ጥይት ይተኮስበት ነበርን....?

አላህ ይፋረዳችሁ እህት ወንድሞቻችን አላህ ይዘንላቸው ያረቢ...

#አንዋርመስጊድ
#መንግስታዊ_ሽብር
አሁንም ይታሰብበት
===============
በአንዋር መስጅድ ውስጥ የሚገኙ ወንድምና እህቶች በር ተቆልፎባቸው ውስጥ ላይ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ገዳ'ዩና ደብዳቢው ኃይል በርካታ አውቶቢሶችን አዘጋጅቷል። ትንሽ መሸት ሲል ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በጅምላ አፍሶ ወደ በርሃ በመውሰድ የእስር ሰቀቀን በማቅመስ ሞራላቸውንና አካላቸውን ለመጉዳት ተሰናድቷል።

በተጫማሪም መስጂዱ የሚገኙ አባቶች በጭሱ ምክንያት እየደከሙ ነው። ደም የፈሰሳቸውም ራሳቸውን እየሳቱ ነው። የግል አምቡላንስ እንዳይገባ ተከልክሏል። በመርካቶ ዙሪያ ያሉ መስጂዶች ከበባ ላይ ናቸው። መርካቶና አካባቢው ላይ ያሉ ወጣቶች እየተያዙ ነው። መስጂድ ውስጥ ያሉትን አፍሰው ለመጫን ከታች እንደምትመለከቱት ባዶ ባሶች ተደርድረዋል።

ሰዓቱ ሳይሄድ የሚመለከተው አካል በተለይ የመጅሊስ ሰዎች በአስቸኳይ ለታገቱት ሙስሊሞች መፍትሄ ሊያፈላልጉ ይገባል።

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
2024/04/28 03:49:59
Back to Top
HTML Embed Code: