Telegram Web Link
⚪️Enlightenment-ውይይት ⚪️

<<ደሃ ወይም ድሀነት ምንድነው? የድሀነት መገለጫዎቹስ ምንድን ናቸው?>> ብዬ አንዳንድ ጥናቶችንና ጽሑፎች ስመለከት 'ከገቢና ከበልቶ ማደር' ጋር የተያያዙ ፣ ብዙ ያልተራራቁ ትርጉምና አስተያየቶችን ተመልክቻለው።

አንደኛው ጽሑፍ ግን በተለየ ሁኔታ ድሀነት በሁለት ከፍሎ ይመለከታል ፣
<<1ኛው ምክንያታዊ የሆነ ቁሳዊ እጦት
2ኛው ከስነልቦና ድክመት
የሚመነጭ የብቃት ማነስ ነው
።>> እያለ

ምክንያታዊ ቁሳዊ ዕጦታ <<ጊዜአዊ የሆነ የኑሮ አስፈላጊ ቁሶችን ማሟላት አለመቻልን>>
ከስነ-ልቦና ድክመት ሲል ደግሞ <<ነገን
በጨለመ መነጽር መመልከት፤ ከተስፋ ይልቅ ማማረርን ባህሪ አድርጎ መውሰድ። >> ነው ብሎ ይተነትናል...

እስቲ ቤተሰቦቻችን ስለ ድሀነት እንወያይ
እውነት እንደሚባለው ኢትዮጵያውያን ድሆች ነን?
ከሆንን የመላቀቂያውን መንገድ በምን እንጀምረው?

ቻናሉን ይቀላቀሉ👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
📝መልዕክተ ENLIGHTENMENT 📝

አንድ ጫማን በመጥረግ የሚተዳደር ወጣት ደምበኛው ከሆነ የታክሲ ሹፌር ጋር
እየተወያዩ ነው።

ወጣቱ ከሊስትሮ የሚያገኘው ገቢ በቂ አለመሆኑን ስለሚያውቅ ራሱ በካርቶን ባባጃጀው ሳጥን ሸቀጥ ጨምሮ መሸጥ
ይፈልጋል። ቀስ ብሎም በመቆጠብ የራሱን 'ኪዮስክ' መክፈት ያልማል። 'ሱፐርማርኬት' ፣ 'ሆቴል'፣ 'ፋብሪካ' ወዘተ ከሕልሙ ሩቅ
አለመሆናቸውንም ያምናል።
በዚህም ተስፋ ደስተኛ ሆኖ ከአላማው
ሳይዘናጋ እየሰራ ይማራል፤ እየተማረ ይሰራል።

በጨዋታቸው መሀል ለደምበኛው የቀን ገቢውን ይጠይቀዋል፣ የታክሲ ሹፌሩም
በማማረር <<ምን ገቢ ትለዋለህ ተበልቶ፣ ተጠጥቶ፣ የቤት ኪራይ ተከፍሎ ቀሪውን ለመዝናኛ የማይበቃ ገቢ ትለዋለህ ጓደኞቼ
ሚስት አግብተው ልጆች ወልደው ይኖራሉ እኔ ግን ይኸው የዕለቴን እየኖርኩኝ የማይቀየር ህይወት እገፋለው። የተሳሳትኩት ይህንን ስራ ስራ ብዬ የያዝኩኝ ቀን ነው።>>

🔴በሁለቱ ሰራተኞች መካከል ያለው ልዩነት ግልፅ ነው፣ በገቢ ደረጃ የታክሲ ሹፌሩ
ቢበልጥም ተስፋን በመሰነቅ ሊስትሮው በልጦታል።
በሊስትሮነትና በፋብሪካ ባለቤትነት መካከል ያለው ግምብ ጊዜ ብቻ ነው።
በጥረት፣ በፅናት፣ በትዕግስት፣ በቁጠባ፣ አላማን ባለመሳት ያለጥርጥር ያሰበው ግብ ላይ ይደርሳል።

🔵ከቁሳዊ ድህነት ሙሉ በሙሉ የነጻ ማህበረሰብ፣ ግለሰብ፣ ሀገር እስካሁን የለም።
ደረጃው ይለያያል እንጂ ሁላችንም ቢያንስ አንድ ቁሳዊ ችግር አለብን።
የጤና ሊሆን ይችላል፣ የመጠለያ ሊሆን ይችላል°°°ወዘተ። ነገር ግን ቁሳዊ ችግሮቻችንን አንድ በአንድ ለማሸነፍ ስነልቦናዊ ችግሮቻችንን ማከም ግድ ይለናል።

⚫️አገር በተማረ ኃይል ብዛት፣ በማዕድን እና ነዳጅ ክምችት፣ በውጪ እርዳታና
ኢንቨስትመንት ወዘተ ልትቀየር አትችልም። አገር የምትቀየረው በነዋሪዎቿ የስነልቦና ዝግጅት እና ጥንካሬ፣ ፅናትና አንድነት ነው
የስነልቦና ድሀነትን አፈር ድሜ አስግጠው ወደ ሀብት የሚንደረደሩትን በማበርታት፣ በዚሁ መስመር የበለጽጉትን አርአያነታቸውን በመከተል ተገቢውን ዕውቅና እና ክብር በመስጠት ተስፋ የቆረጡትን ስነልቦናቸውን በማከም፣ ድህነትን ታግለው
ራሳቸውን እንዲያሸንፉት በማገዝ ወደ አሸናፊ መስመር ማስገባት ያስፈልጋል።

ተስፋ የቆረጠ ዜጋ ሌብነትን ይለምዳል።
ተስፋ የቆረጠ ማኅበረሰብ አገርን ወደኋላ ይጎትታል።....

ይቀላቀሉን👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
🎭ኪነ-Enlightenment🎭

እርቃንነት

"እርቃን ብሎ ማለት፣
ይደርበው ያጣ-የገላ ባዶነት?

ወይስ

ሰውኛነት ጠፍቶ- ከ'ንስሳ ባነሰ-
ተጋልጦ መራቆት፣
ህሊና ቢስ ሆኖ-እርቃን ነፍስን ማቀፍ-
ከፍጡር መራኮት፤
ከእልፍ ድሪቶ ውስጥ-
በሃሩር በቁሩ፣
ወይቦ መገርጣት-
እስኪጠፋ ክብሩ፤
እስኪሻር መነሻው-
የሰው መሆን ውሉ፣
ከላይ ለብሶ አጊጦ-
ውስጥ ውስጡን መቅለሉ፤

የትኛው ነው ምንዱብ-
የቱ ነው መራቆት?
ርቃን መንፈስ ገላ-
ራቁት ብሎ ማለት???
©ኡመር ተ,ሲ

ይቀላቀሉን👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
⚪️Enlightenment-ውይይት ⚪️
👉👉 @Ethio_Abrhot 👈👈
ቤተሰቦቻችን አላችሁ? ኑሩልን...ጭጋግና ጨለማውን ፣ ብርድና ውርጩን እየታገልን እንጨዋወት ዘንድ...ለዛሬአችን

የበደሉንን እንዴት ይቅር ማለት እንችላለን?

በሚል ጥያቄ መጥተናል... ተጨዋወቱ...አሳባችሁን በነፃነት ግለጡ...ጠይቁ...ሳትሰስቱ መልሱ

💡ሰናይ ጊዜ💡

ይቀላቀሉን👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
ከዋክብተ ENLIGHTENMENT

የይቅርታው ሰው

እስኪ ዓለማችን ካስተናገደቻቸው ድንቅ ሠዎች መካከል 'የነጻነት አባት' በመባል ስለሚታወቀው <ኔልሰን ማንዴላ> እናንሳ።

በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የአፓርታይድ ስርአት በመቃወም ግንባር ቀደም ሚና የነበረው ሰው፤ ጥቁሮችን እንደእንስሳ ቆጥረው በሚሰለጥኑባቸው እንደ ሸቀጥ እያጋዙ ያሻቸውን በሚፈጽሟቸው ነጮች ፊት በጀግንነት የቆመው ታላቅ ሰው፤

ስለጥቁሮች እኩልነት በመጮሁ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ለ27 ዓመታት በፍርግርግ ብረቶች ፊት አካሉ ቢታጠርም ከጠንካራ ተስፋውና መንፈሱ ጋር በአላማ ጽናት የዘለቀው ሰው ፤

°°°የስቃዩና የግፉን ዘመን በርሱና በመሰሎቹ ትግል እያከተመ ሲመጣ፣ ከእስር ወጥቶ መንቀሳቀስ ሲጀምርም የመሪነት መንበር ወድዳ ፈቅዳ ያከበረችው ሰው ፤

ብዙ ጥቁሮች የደረሰባቸውን የዘመናት ጭቆና የሚያወራርዱበት፣ ነጮቹ በግፍ ያከማቹትን ሀብትና ንብረት ወርሰው የራሳቸው የሚያደርጉበት ጊዜ እንደደረሰ አምነው ግዳዩን ሊጥል እንዳሰፈሰፈ አዳኝ በሚጠባበቁበት ወቅት ታላቅ የይቅርታ አዋጅ ለሕዝቡ ያሰማው ሰው፤

እንዴት ለበደሉትን ፍፁም ይቅርታን ማድረግ ቻለ?

ለሰው ልጅ ከጊዜ የበለጠ ምን ስጦታ ኖሮ ነው ነፃነቱን ነፍገው እድሜውን ለቀሙት ሰዎች ይቅርታን የሰጠው?

እንዴት ጥላቻና ቂም ለመፍጠር ከበቂ በላይ የሆኑ የመንፈስና የስነልቡና ጉዳቶቹን ሽሮ በፍቅር ተቀበላቸው?

ማዲባ ታላቁ የነፃነት ሰው እኚያን ኃጢአቶች በሙሉ ይቅር ለማለት የሚያስችል ልብንስ ከየት ሊያገኝ ቻለ?

እፁብ ድንቅ ነው°°°

ይቀላቀሉን👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
⚪️Enlightenment-ውይይት ⚪️
👉👉@Ethio_Abrhot👈👈
ሰአቱ ደርሶ አለማወቃችን እናውቅ ዘንድ የሚመራንን ውይይት ልናደርግ ነው።የምንወዳችሁ እንዴት አላችሁ?
.......ለዛሬያችን
ወደፊት መሆን ያለብኝን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? ወደፊት የምሆነውን ካወኩስ በኋላ ምን አይነት መንገድ ተጠቅሜ መድረስ እችላለሁ?
የሚል ከቤተሰባችን የተነሳ ጥያቄ ይዘን መተናል



ተጫወቱ....ሃሳባችሁን በነፃነት ...ግለፁ....ጠይቁ...ሳትሰስቱ መልሱ

💡ሰናይ ጊዜ💡
ይቀላቀሉን
👇👇👇👇
💡@ethio_enlightenment💡
💡@ethio_enlightenment💡
💡@ethio_enlightenment💡
⚪️Enlightenment-ውይይት ⚪️
👉👉 @Ethio_Abrhot 👈👈
እንደምን አመሻችሁ ቤተሰቦች
<<ነፃነት፦ የሌሎችን መብት በመንጠቅ ፤ የሌሎችን እምነትና አመለካከት በኃይል ለማጥፋት በመስገብገብ ፤ የወገንን ሰላም በማደፍረስና ስጋት ውስጥ በመክተት.. አይገኝም!
የአንድ ሰው(ማኅበር)ነጻነት የሚረጋገጠውም ሌሎች በሚያገኙት ነፃነትና ሰላም እንጂ በሌሎች ሞት ፤ ስቃይና መፈናቀል አይደለም ፡፡>>ይላሉ የኔታ

ታዲያ ነፃነት በምንድን ነው የሚገኘው?

💡ሰናይ ጊዜ💡

ይቀላቀሉን👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💯Enlightenment views💯
ነፃ-ነት
ሊቃውንት ስለሷ አጥንታቸውን እንደብዕር፣ ደማቸውን እንደቀለም፣ ቆዳቸውን እንደ ብራና ዘርግተው ዘወትር ሲደጉሷት ፣ እኛም ስንወለድ ጀምሮ የተሰጠችን ጸጋ ብትሆንም በልባችን ጥራዝ ለመከተብ እርሷን ፍለጋ በየዕለቱ እንቃትታለን።

የእርሷ መኖር ነው ሰውን ሰው የሚያደርገው፤ የእርሷ መኖር ነው ቀንበራችንን የሚያቀልልን፤
ግዘፍ ነስታ ባናያትም እንኖራታለን፣ድምጿንም ከልባችን በሚፈልቀው የእስትንፋስ ምንጭ እናዳምጠዋለን።


አቤት! ረቂቋን የሕይወት ቅኔ ለመኖር ስንቶች ነፍሳቸውን ለውርርድ አቀረቡ? ስንቶች በሐሴት ተሰዉላት? ስንቶች ወድደው ገበሩላት? ስንቶች በወህኒ ዘመናቸውን ገፉባት? ስንቶች የዓለምን ጣዕም ንቀው መነኑላት?
እልፍ አዕላፍ ወትዕልፊት...

ውዷ ነፃነት ሆይ°°° አንቺን ማግኛ ክፍያው ሕይወት መሆኑን እያሰብኩ ሁሌም ንዑድ እንደሆንሽ እመሰክራለሁ!

ወዳንቺ የሚደረገው ጉዞ የተጀመረው ከስነፍጥረት መነሻ ቢሆንም ማብቂያና መድረሻ መቼትሽ ግን አይታወቅም።°°°

💡ሰናይ ጊዜ💡
ይቀላቀሉን👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
📚ከገፆች መሐል📚
፩፪ ፩፪ ፳፩፪ ዓም
"...የሰው ልጅ የተፈጥሮን ህግ ሊለውጥ አይችልም። ለምሳሌ ቀንና ጨለማን ፣ ሞትና ህይወትን፣ ማደግና ማርጀትን፣ ማበብና
መክሰምን ሊለውጥ አይችልም። የማይለወጡ የተፈጥሮ ህግጋት
አሉ ማለት ነው።
እነዚህን አሜን ብሎ መቀበል አንዱ የደስታ
ምንጭ ማለት ነው። አሜን ብሎ ተቀብሎ ዝም ማለት ብቻ አይደለም።


የህይወት መጨረሻ ግቡ የሰው ልጅ በዚህች ዓለም ላይ
በሚኖርበት አጭር ጊዜ ውስጥ ተፈጥሮውን አሟልቶና ተደስቶ
ለመኖር ስለሆነ፤ እያንዳንዱ ሰው ተፈጥሮውን እንዳያሟላና እንዳይደሰት የሚያደርጉትን መጥፎ ነገሮች ሁሉ ከራሱ ልብ
ውስጥም ሆነ ከአካባቢው ለማስወገድ መጣር አለበት።
ይህን ለማድረግ... ልበ ሙሉ መሆን ያስፈልጋል።
የሰው ልጅ ክብር ዋስትና መስዋዕትነት ነው። መስዋዕትነት ደግሞ ያለ ልበ ሙሉነት መች ይሆናል።

ራሳቸው እየነደዱ አልቀው ለሌላው
ብርሀን የሚሆኑ ልበ ሙሉዎች ብቻ ናቸው። መፅሀፉም'ኮ እሹ ታገኛላችሁ፣ አንኳኩ ይከፈትላችኋል ያለው ሌላ ሳይሆን
የራሳችንን ልብ ነው። ራስን ማወቅ የመጨረሻ ጥበብ ነው።


ራስን ማወቅ ሌላውንም ማወቅ ይሆናል። ካወክ ዘንድ ለራስህ
የምትሻውን ለሌላውም ትመኛለህ። ለራስህና ለሰው ልጅ ሁሉ በጎ ፈቃድና ፍቅር ይኖርሀል። ከዚህ ዕውቀት ደረጃ ላይ ስትደርስ
ለምታደርገው ነገር ሁሉ ምስጋናም ሆነ ጥቅም ከሰው ዘንድ አትሻም። ልብህ ጥቅም ላይ ካተኮረ የተፈጥሮን በጎ ምግባር
ትስታለህ።

(ደራሲው-በበዐሉ ግርማ )

ይቀላቀሉን👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
⚪️Enlightenment-ውይይት ⚪️
👉👉@Ethio_Abrhot👈👈
የምንወዳችሁ እንዴት አላችሁ?
....ዛሬ ደግሞ ለውይይታችን
"ውሳኔ" (decision making) የሚለውን ሃሳብ ይዘንላችሁ መተናል!!

ብዙ ሰዎች 'ደስታችንም ሆነ ሐዘናችን የውሳኔያችን ውጤት ነው' ይላሉ!
በተጨማሪም 'አሁን ያለበንትም ቢሆን ወደፊት የሚሆነው የውሳኔያችን ውጤት ነው' የሚሉም አሉ!

ዓለም ላይ ያሉ ትላልቅ ሥራዎች የምርጥ ውሳኔ ውጤቶች ናቸው!!

እናንተስ ምን ትላላችሁ?
<ውሳኔ ላይ አሪፍ አደለሁም ምን ላድርግ?>
የሚል ከቤተሰባችን የተነሳ ጥያቄንም አካቱት

ተጫወቱ....ሃሳባችሁን በነፃነት ...ግለፁ....ጠይቁ...ሳትሰስቱ መልሱ

💡ሰናይ ጊዜ💡
ይቀላቀሉን
👇👇👇👇
💡@ethio_enlightenment💡
💡@ethio_enlightenment💡
💡@ethio_enlightenment💡
⭕️⭕️ጥቅሶች

ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በአሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት (ሁኔታዎች) ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡
ሪያኖር ሮዝቪልት

መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሃል፡፡
ኤሪክ ቶማስ

ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ፡፡
ዚግ ዚግላር

ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ኃይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው፡፡
ጂም ዋትኪንስ

አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡
ፍራንክ ኦሽን

በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሀል ፡፡
ቶማስ ጄፈርሰን

አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡
ኢማም አሊ

በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው ፡፡
ዋልተር ባግሆት

ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም ፡፡
አርል ኒተንጋል

ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው ፡፡
አዚም ፕሪሚጂ

ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ ፡፡
አልበርት አንስታይን

አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም ፡፡
ካርል ጉስታቭ

ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
ቲም ኖትኪ

የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዐት ምናለ ከዓመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
ካረን ላንብ

ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል ፡፡
ስቴፈን ማክሬን

ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው ፡፡
ሮቢን ሻርማ

ዓለም የምትቀየረው በአንተ አስተያየት ሳይሆን በአንተ ተግባራዊ ስራ ነው ፡፡
ፓውሎ ኮኤልሆ

እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡
ኮንፊሺየስ

ሼር በማድረግ ሌሎች አሳብ እንዲያገኙ መጋበዝ ይቻላል
Ethio Enlightenment

ይቀላቀሉን👇👇👇
💡 @ETHIO_ENLIGHTENMENT 💡
💡 @ETHIO_ENLIGHTENMENT 💡
💡 @ETHIO_ENLIGHTENMENT 💡
📝መልዕክተ ENLIGHTENMENT 📝

<<የአንድ ሺ ኪሎ ሜትር መንገድ ከአንድ ርምጃ ነው የሚጀምረው>>

እንደ ኪሎሜትሩ ሩቅ የሆነ የሚመስለን የነገ ሕልማችን ላይ ለመድረስ ዛሬ የምናደርገው አንድ ርምጃ ታላቅ መሠረት ነው።
ነገር ግን ራሳችንን በ'ቢሆንስ'ና በፍርሃት አስረን ስለምንቀመጥ ያ ርምጃ እንደ ተራራ ይከብደናል። ከራሳችንም በላይ ሌላ ምክንያት ሊሆነን የሚችል የለም ።

አብዛኞቻችን አንድ ርምጃ ለመራመድ ከመወሰናችን በፊት ቀድሞ በሕይወታችን ያሳለፍናቸውን ተሞክሮዎችን ፣ ልምዶችንና እውቀታት ከተከማቹበት ማኅደር እየመዘዝን ማገላበጥ እንጀምራለን። ምናልባት ሽንፈትና ውድቀት የፈጠረውን ፍርሃት እናገኝና ለመራመድ የመወሰን ወኔውን እናጣለን።

ነጋችን ያማረ የሚሆነው ዛሬ እንቅስቃሴ ላይ ስንሆን ከሆነ ሁሌም የወደፊት ተስፋችንን እንዳያጨናግፉት የኋላውን መጥፎ ጥለን የፊቱን ለመያዝ በመዝለል ፋንታ በትውስታችን ውስጥ ብቻ ያሉት መሰናክሎች ለምን እንዲጥሉን እንፈቅዳለን?


💊ነገ የተሳካ የንግድ ሕይወት እንዲኖርህ ዛሬ የምትቆጥባት ጥቂት ገንዘብ ዋጋ አላት፤

💊ነገ በትምህርት የተሻለ ውጤት እንዲኖርህ ዛሬ የምታነበው ነጠላ ገፅ ዋጋ አለው፤

💊ነገ የተሻለ የሰውነት አቋም ለማግኘት ዛሬ የምታነሳው ትንሽዬ ክብደት ዋጋ አለው፤

⚫️በጠቅላላው ነገ ላይ ካሰብነው ለመድረስ ዛሬ አንድ እርምጃን እንራመድ ዘንድ ግድ ይለናል።⚫️

ይቀላቀሉን👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
⚪️Enlightenment-ውይይት ⚪️
👉👉@Ethio_Abrhot👈👈
የምንወዳችሁ እንዴት አላችሁ?
....ዛሬ ደግሞ ለውይይታችን
"በራስ መተማመን" (self confidence) የሚለውን ሃሳብ ይዘንላችሁ መተናል!!

በራስ መተማመን ማለት ምን
ማለት ነው?
በራስ መተማመንን የሚሰጠን
ነው? ወይስ የምናዳብረው?

ተጫወቱ....ሃሳባችሁን በነፃነት ...ግለፁ....ጠይቁ...ሳትሰስቱ መልሱ

💡ሰናይ ጊዜ💡
ይቀላቀሉን
👇👇👇👇
💡@ethio_enlightenment💡
💡@ethio_enlightenment💡
💡@ethio_enlightenment💡
🎭ኪነ-Enlightenment🎭
አደገኛ የበታችነት ስሜት ነበረባት !
ማንም ሰው ትንሽ የበታችነት ስሜት ሊኖርበት ይችላል ! የተናኘን ለየት የሚያደርገው የበታችነቷን በተጋነነ የራስ መተማመንና ሁሉነም ነገር በማናናቅ በአውቃለሁ ባይነት ለመሸፈን መሞከሯ ነበር !

ምንም ቢያደርግላት ያልተደነቀችና ከዛ በፊት የምታውቀው ለመምሰል የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም …!
💡 @ethio_enlightenment 💡

ሙሉውን👇👇👇👇ያንብቡ
https://telegra.ph/Enlightenment-story-08-20-2
📚ከገፆች መሐል📚

የእውነት ጠቢብ ወደ ራሱ ጥበብ ቤት እንድትዘልቁ አይጠራችሁም ። ወደ ገዛ አዕምሮአችሁ ደጃፍ ይመራችኋል እንጂ።

በመቀጠልም አንድ መምህር ተናገረ <ስለማስተማር ንገረን?> አለው ፤
እሱም አለ፦
<<ማንም ሰው ቢሆን ገና ድሮ በእውቀታችሁ መክፈቻ ንጋት ላይ፥በከፊል እያንቀላፋ ተጋድሞ ካለው በስተቀር፥ ሌላ ምንምነገር ሊገልጥላችሁ አይቻለውም.....

በቤተመቅደሱ ጥላ ስር ከተከታዮቹ ጋር
የሚንሸራሸረው መምህርም ከእምነቱ፣ ጋር ከፍቅር ውጪ ጥበቡን ሊሰጣቹ አይችልም። በእውነት ጠቢብ ከሆነም፤ ወደ ራሱ ጥበብ ቤት እንድትዘልቁ አይጠራችሁም። ወደ ገዛ
አእምሯችሁ ደጃፍ ይመራችሁዋል እንጂ...

የከዋክብት ተመራማሪውም ያለውን ግንዛቤ ይነግራችሁ ይሆናል። ግን ግንዛቤውን ሊሰጣቹሁ አይችልም....

ዘማሪውም በህዋ ላይ ያሉትን ዜማዎች ሁሉ ይዘምርላችሁ ይሆናል ። ዜማውን የሚያዳምጥ ጆሮንም፤ ሆነ የተደመጠውን
የሚያስተጋባ ድምፅ ሊሰጣችሁ ግን አይቻለውም ።

በሂሳብ ሳይንስ የተካነውም ሰው ቢሆን ስለክብደትና የልኬት ወሰኖች ሊነግራችሁ፥ ይችላል እንጂ ወደ እነዚያ ወሰኖች ሊያስኬዳችሁ አይችልም።

የአንድ ሰው ዓይንስ ብርሃኖቹን ለሌላ ሰው ያውሳልን?.....

እናም በእግዚአብሔር እውቀት ውስጥ እያንዳንችሁ ለየብቻ እንደምትቆሙት ሁሉ፤ ስለ እግዚአብሔር ባላችሁ እውቀትና
ስለዓለም ባላችሁ ግንዛቤም ለየብቻቹሁ መቆም ይገባችኋል ።


የጥበብ መንገድ በካህሊል ጅብራን
ተርጓሚዎች
( ደምመላሽ ጥላሁን፣ተስፋሁን ምትኩ፣ ሃብታሙ ተስፋዬ)

⭕️⭕️PDF ይለቀቅ የምትሉ ⭕️⭕️

ይቀላቀሉን👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
ENLIGHTENMENT MOTIVATION

“ The strongest people aren't always, the people who Win, but the people who don't give up when they Lose. „

#strong
#Win
#give_up
#Lose
#inspiration
#motivation
#Never_give_up

Join us👇
@ethio_enlightenment
ነሐሴ ፩፮
ለኢትዮ_Enlightenment ቤተሰቦች
🤞የinternet ጥቅል🎁 የሚያሸልሙ የጠቅላላ እውቀትና የማስተዋል ጥያቄዎች


፩ -ከዓለም ህዝብ ውስጥ አንድ ስድስተኛ የገደለው ሰው ማን ይባላል?

፪ -Hello የሚለው ቃል ከየት መጣ?
ለምንስ ያለ ቋንቋ ልዩነት የሁሉም ስልክ ደዋይ መግቢያ ሆነ?


፫- 🔑+¼+GOD= ?

፬- ዓለምን ለመጀመሪያ ጊዜ የዞረው ማነው?

፭- እንዴት ስምንት 6 ቁጥሮች ተደምረው 750 ሊያስገኙ ይችላሉ?

....❗️❗️❗️⚠️❗️❗️❗️....
🔵መልሶቻችሁን
💡 @Ethio_Abrhot💡 ጻፉልን

🔴 ከላካችሁ በኋላ በፍፁም edit ማድረግ አይቻልም

⚫️ እስከ ምሽት ፫ሰዐት ድረስ መሳተፍ ይቻላል

መቀላቀል እንዳይረሱ👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
የጥበብ_መንገድ_ካህሊል_ጅብራን_ትርጉም.pdf
53.6 MB
🔵ለመጽሐፍት መደርደሪያችን🔵

ታላቁ የጥበብ ሰው ጂብራን ካህሊል ጂብራን ፣ በደራሲነት ሕይወቱ ፣ ከጅማሬ እስከ ፍጻሜ ዘመኑ ዓለምን በአመክንዮአዊ ዓይን
እንድንመለከት የተጋ ደራሲ፣ ፈላስፋ፣ ገጣሚና ሰዓሊ ነው፡፡ለዚህም የሰራቸው ዘመን አይሽሬ መጽሐፍት ሕያው ምስክሮቹ ናቸው።


🔵በአገራችን የዚህን ዕንቁ ደራሲ ስራዎች እንድንቋደስ ከረዱን ጸሐፍት መካከል
ኃይለ ጊዮርጊስ ማሞ (ጲላጦስ) ዋነኛው ነው፡፡

ከተለያዩ ድርሰቶቹ በመጨለፍ ከብዙ አሳቢዎች ሥራዎች ጋር በማጣመር "ጥበብ" በተባሉ ስብስቦቹ በኋላም
'Jesus -The Son of Man' የተባለውን ወጥ ሥራ ተርጉሞ በማቅረብ ከጠቢባን ሊገኝ የሚችለውን ፍሬ እንድንካፈል ረድቶናል፡፡ 🙏እናመሰግናለን ጲላጦስ

🔴"የጥበብ መንገድ " በሚል ርዕስ የካህሊል ጂብራንን 10 ወጥ ሥራዎች ተርጉመው ለንባብ ያበቁ
(ደመላሽ ጥላሁን፣ ሀብታሙ ተስፋዬ እና ተስፋሁን ምትኩ) የተባሉ ደራሲዎችም እጅግ ሊመሠገኑ ይገባል፡፡

የቋንቋ አቅማቸው (ትርጉማቸው) እንዴት እንደሚጣፍጥ ያንን ስብስብ ያነበበ ሁሉ
ይረዳዋል፡፡

⚫️ከእነሱ በኋላ ደግሞ 12 የጠቢቡን ሥራዎች አንድ ላይ በማድረግ
'The Great Works of Khalil Gibran' በሚል ርዕስ በአገራችን የካህሊሉ ፍሬዎች ታትመው ቀርበዋል፡፡ ለዚህም የህንዱ
'Little Scholarz Pvt Ltd.' ምስጋና ይገባዋል፡፡

🔵ዛሬ ለመደርደሪያችን
'የጥበብ መንገድ'ን ይዘን መጥተናል፤ አንብባችሁ ተደሰቱበት።



ለሚወዱት ያጋሩ⬇️⬇️⬇️
💡 @ethio_enlightenment 💡
📝መልዕክተ ENLIGHTENMENT 📝

🔵እውነተኛ ሠላም🔵

ንጉሱ በትክክል ሠላምን ሊወክል የሚችል ስዕል መሳል ለቻለ አርቲስት (የስዕል ሙያተኛ) ወሳኝ የሆነ ሽልማት ለመስጠት ተዘጋጅቶ አሳወጀ፡፡

ብዙ የስዕል ሙያተኞችም ሙከራ አደረጉ፡፡ ነግር ግን ንጉሱ የቀረቡትን ስዕሎች ተመለከተና ሁለት ስዕሎችን ብቻ ወደደ፡፡

ንጉሱ ቀልቡ ካረፈባቸው ሁለት ስዕሎች አንዱን መምረጥ የተዘጋጀውን ሽልማት መስጠት ነበረበት፡፡

አንደኛው ስዕል ፀጥ ያለ ባሕርን የሚወክል ነው ፡፡ አሳሳሉም ባሕሩ በዙሪያው ያሉትን የተራራ ማማዎች እንደ መስታውት አንጸባርቆ ለተመልካች ቅርብ ያደርጋል፡፡ አናቱ ላይም በነጭ ደመና ተሸፍኖ ሰማዩ አረብቦበታል፡፡

🔵ይህን ስዕል የተመለከተ ማናቸውም ሰው እውነተኛ የሠላም ምልክት አድርጎ ሊወስደው የሚችል የአሳሳል ጥበብ ያረፈበት ነው፡፡

ሌላኛው ስዕል እንዲሁ የተራራ ምስል ሲሆን በተራራው ላይ የሚታየው የተራቆተና ያገጠጠ አለት ፣ በላዩ ላይም ቁጣ የሚነበብብት ሰማይ የዝናብ እንባውን ሊያንጠባጥ በብልጭታ ጥፊ እየተመታ ይታያል፡፡ በተራራው ጎንም የሚያጓራ ፏፏቴ ይታይበታል፡፡

ስዕሉን ላየ ጨርሶ የሠላም ስሜት የማይፈጥር ስዕል ነበር፡፡ ነገር ግን ንጉሱ ተጠግተው በአንክሮ ሲመለከቱት በፏፏቴው መውረጃ ጀርባ በተሰነጠቀው አለት ላይ ትንሽየ ቁጥቋጦ በቁጥቋጦው ላይ ደግሞ ወፏ ጎጆዋን ቀልሳ ተመለከቱ፡፡ በዛ በተናወጠው የፏፏቴ ድምጽ መሃል ወፏ በፍጹም ሠላም ተቀምጣለች፡፡

የመጀመሪያው ስዕል የሚያሸንፍ ቢመስልም ንጉሱ የመረጡት ስዕል ሁለተኛው ስዕል ነበር፡፡

⚫️ ለምን እንደመረጡት ንጉሱ ሲያብራሩ “ሠላም ማለት ምንም አይነት ድምጽ በማይሰማበት፣ ሁከትና ጫጫታ በሌለበት ስፍራ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ሠላም ማለት ያለነው በግር ግር መሃል ቢሆንም ፀጥ ያለ ልብ ሲኖረን ሠላም አለን ማለት ነው፡፡ እሱ ነው እውነተኛና ፍፁም ሠላም፡፡” አሉ፡፡

🔵ውስጣችን ሠላም ሲያጣ በሆነ ባልሆነው መበሳጨት እንጀምራለን፡፡ እንዲሁም ደግሞ በተቃራኒው ሠላማችን ሲጨምር መደሰቻችን ይበዛል ፡፡

💡ሠላማችሁ ይብዛ💡

Wisdom pearls
“The Real Meaning of Peace”

መቀላቀል እንዳይረሱ👇👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
💡 @ethio_enlightenment 💡
2025/07/06 04:14:14
Back to Top
HTML Embed Code: