Telegram Web Link
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር በመሆን የአባይ ድልድይን መረቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር በመሆን ከአራት አመት ተኩል በፊት ግንባታው የተጀመረውን የአባይ ድልድይን መርቀዋል።

ይህ ዘመናዊ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት ያለው በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ ነው።

የባህርዳር ከተማ ታላቅ መለያ ምልክት እንዲሆን የተገነባው የአባይ ወንዝ ድልድይ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እድገት ብሎም የመገናኛ አውታር የሚያነቃቃ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ጠ/ሚኒስትሩ እና ርዕሰ መስተዳደሩ በመሳሪያ የተደገፈ ትግል ለሚያካሂዱ #የአማራ ክልል ታጣቂዎች "መገዳደል ይብቃን" ሲሉ ጥሪ አቀረቡ!!

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ በአማራ ክልል መሳሪያ አንግበው ትግል ላይ የሚገኙ ሃይሎች “ትጥቃቸውን ፈትተው በሳላማዊ መንገድ ኑ እና ታገሉ፣ መገዳደል ይብቃን” የሚል ጥሪ አቀረቡ።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ “ጫካ ለሚገኙ ወንድሞቻችን” ሲሉ መሳሪያ አንግበር በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ባቀረቡት ጥሪ “ዛሬ አማራ መሪ አግኝቷል አረጋ ከበደን የመሰለ ታማኝ፣ ትጉህ መሪ አግኝቷል” ሲሉ በማወደስ “ለአማራ መብት የሚታገል ግለሰብም ይሁን ቡድን ከአረጋ አመራር ስር ሁኖ ክልሉን እና ህዝቡን መጥቀም ስለሚችል መገዳደል ይብቃን” ሲሉ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምሥጋና ባቀረቡበት መልዕክታቸው “በጫካ ለምትገኙ ወንድሞቻችን” ሲሉ በመጥራት “በእውነት ከክልላችን ሕዝብ ጥቅም እና ክብር ውጭ ሌላ ስውር አጀንዳ ከሌላችሁ በስተቀር ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) ባቀረቡላችሁ ጥሪ መሠረት ችግሮቻችንን በውይይት እና በድርድር እንድንፈታና ሕዝባችንም እፎይታ እንዲያገኝ በድጋሜ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ” ብለዋል።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ከሐዋሳ ወደ አዲስ_አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ያጋጠመው ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ ከሐዋሳ ወደ አዲስ_አበባ በመጓዝ ላይ በነበረዉ በአዉሮፕላል ላይ የተከሰተው ጭስ ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ ሲል ገልጿል።ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል።

የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት፤ "በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መጋጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ፤ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ" ብለዋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን እና መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን ማስቃወቁ ይታወሳል። (ካፒታል ጋዜጣ)


     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ማይክ ሀመር ከኦሮሞ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ዳውድ ኢብሳ ጋር መምከራቸው መከሩ

የአሜሪካን መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር #ከኦሮምያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ።

ሀመር የመከሩት ከኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ከኦነጉ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ጋር መሆኑም ታውቋል። የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከማይክ ሀመር ጋር በሀገራዊ እንዲሁም በኦሮምያ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች መምከራቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል።

በሀገራዊ እና በኦሮምያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለማይክ ሀመር ሙሉ ገለጻ እንዳደረጉላቸው ፕሮፌሰር መራራ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል። ከማይክ ሀመር ጋር በነበረን ቆይታ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው ሀገራዊ ምክክሩ ነበር ሲሉ የገለጹልን ፕሮፌሰር መረራ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ "ኢትዮጵያን የትም አያደርሳትም፣ ምክንያቱም ደግሞ ሁሉን ያሳተፈ አይደለም፣ በሁሉም ዘንድ ደግሞ እምነት የሚጣልበት አይደለም" ሲሉ እንደገለጹላቸው ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።

ሌላኛው ከማይክ ሀመር ጋር በነበረን ውይይት የተነሳው ነጥብ የበቴ ኡርጌሳ ግድያ ነበር ያሉት መረራ ጉዲና የፈጠረባቸውን ድንጋጤ እና የቤተሰቦቹ እስር እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ስሜቴን ለልዩ ልዑኩ አጋርቻለሁ ብለውናል።

በተያያዘ ዜና የአሜሪካ መንግስት ልዩ ልዑኩ ማይክ ሀመር በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ከኦነጉ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ጋር መምከራቸውም ከፓርቲያቸው ቃል አቀባይ ለሚ ገመቹ የኤክስ ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ዳውድ ኢብሳ እና ማይክ ሀመር በምን ጉዳዮች ላይ እንደመከሩ ቃል አቀባዩ ያሉት ነገር የለም።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
በብልፅግና ፓርቲ እና ህወሃት ግጭት የሚፈጥሩ አዝማምያዎች በጋራ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ!!

በብልፅግና ፓርቲ እና በሕወሃት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፓለቲካዊ ውይይት ለሶስተኛ ግዜ በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ ተካሂዷል።

ሁለቱም አካላት ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል ተብሏል። “ማናቸውንም ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ ሁለቱም አካላት የበኩላቸውን ፓለቲካዊ ድርሻ ለመወጣትና በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል።

በተያያዘም የሚኖሩ የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉ እና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ደርሰዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

በተጨማሪም በቅርቡ በ ራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተም በዝርዝር ውይይት ያካሄዱት ፓርቲዎቹ “ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ” መግባባት ላይ ደርሰዋል። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፓለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት፤ በቀጣይም በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ተስማምተዋል።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
Forwarded from MneCreatives
📢🎉ለ12ኛ ማትሪክ እና ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች!
ተማሪው መተግበሪያን ከፕለይስቶር በማውረድ ለፈተናዎ በቂ ዝግጅት ያድርጉ!

🔸ለ12ኛ ማትሪክ ተፈታኞች:- በመተግበሪያችን ከ አዲሱ የ12ኛ ክፍል ካሪኩለም የተወጣጡ ከ 2000 በላይ መለማመጃ ጥያቄዎችን ያገኛሉ።

🔸ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች:-
🔹ለአካውንቲንግ
🔹ቢዝነስ ማኔጅመንት
🔹ኮምፒዩተር ሳይንስ
🔹ሆቴል ማኔጅመንት
🔹ማርኬቲንግ ማኔጅመንት
መለማመጃ ጥያቄዎችን ያገኛሉ።

በተጫማሪም መተግበሪያውን ለልጅዎ፣ ለቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎ 🎁በስጦታ ማበርከት ይችላሉ።🎁
ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ ቦታ ላይ ውሳኔ ተላለፈ!

በቢጂአይ ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መካከል ተከስቶ የነበረው አለመግባባት በስምምነት መጠናቀቁን ቢጂአይ አስታወቀ ።

ፐርፐዝ ብላክ እስካሁን ዝምታን መርጧል ።

ሜክሲኮ የሚገኘውን የቢጂአይ ኢትዮጵያን ይዞታ ጨረታ አሸንፍያለሁ በማለት ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አማላይ የሆነ የቤት ግንባታ ፕሮጀክት በስፍራው ላይ አቅርቦ ብዙዎች መግዛታቸው ይታወቃል ።

ይሁን እና ገንዘቡ በውላችን መሰረት እየተከፈለኝ አይደለም በሚል ቢጂአይ ውሉን ማቋረጡ አይረሳም ። በዚህ ምክንያት ፐርፐዝ ብላክ የህዝብ ገንዘብ ሊባክኝብኝ ይችላል በሚል የቢጂአይ አካውንት እንዲታገድለት መጠየቁ ይታወሳል ።

ቢጂአይ- ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ አለመግባባታቸውን በስምምነት መፈታቱን ቢጂአይ ለሚዲያዎች በላከው መረጃ አሳውቋል ።

'' ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት መር አስማሚ በኩል አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈትተዋል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈፀመውን ስምምነት አፅድቆ ክሱን በመዝጋት እግዱም እንዲነሳ አዟል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የተከፈለውን የቀብድ ክፍያ ለፐርፐዝ ብላክ የመለሰ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት የጀመረው ክስም ተቋርጦ እግዱ ተነስቷል። '' ብሏል ።

በዚህ መረጃ መሰረት ፐርፐዝ ብላክ ቅድምያ የከፈለው ገንዘብ ተመልሶለት ቦታውን ያስረክባል ማለት ነው።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽር የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ በማቋቋም ዙሪያ ከማይክ ሀመር ጋር ተወያዩ!

የአሜሪካ መንግስት የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽር ተመስገን ጥላሁን፤ የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መልሶ ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀል እና መልሶ ማቋቋም ሂደት ዙሪያ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ኮሚሽነር ተመስገን የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የሀብት አሰባሰብ፣ አጋርነትና ትብብር ስራዎች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለልዩ መልዕክተኛው ማይክ ሐመር ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ እስካሁን የአሜሪካ መንግስት እያደረገ ያለውን ድጋፍና ትብብር አመስግነው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ልዩ መልዕክተኛው፤ “የአሜሪካ መንግስት ፕሮግራሙ በታቀደው ጊዜ እንዲሳካ ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል” ሲሉ አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል ሲል የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

የ አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ከትናንት በስቲያ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጋር የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ወደ ህብረተሰቡ የማቀላቀል እና መልሶ የማቋቋም ሂደት እና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራ ዙሪያ ተወያይተዋል።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MalefiaTrainingInstitute

💻በጥራት ያዘጋጀናቸውን የቴክኖሎጂ ኮርሶች እስከ ግንቦት 12 (May 20) ብቻ በሚቆይ የ25% ቅናሽ አቅርበንልዎታል!

Digital Marketing - ለ2 ወራት Graphic Design - ለ2 ወራትFull Stack Web Development (MERN) - ለ4 ወራት

👉 ትምህርት በመጪው ሳምንት ይጀምራል::

በዱቤ አለ አማራጫችን የመረጡትን ኮርስ እስከ 12 ወር ድረስ ከፍለው ማጠናቀቅ ይችላሉ::



📲 ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ እና ለመመዝገብ @malefiatraining ወይም 0952168429 ይጠቀሙ

#ማለፊያ_የስልጠና_ተቋም
ቄስ በላይ መኮንንን ጨምሮ በ5 ግለሰቦች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ

ቄስ በላይ መኮንንን ጨምሮ በአምስት ግለሰቦች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ በመደበኛ ችሎት ተመሰረተባቸው።

ክሱ የተመሰረተባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን÷ ተከሳሾቹም 1ኛ ቄስ በላይ መኮንን፣ 2ኛ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማራው ኢያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣ 3ኛ በኮሚሽን ሥራ የተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር፣ 4ኛ ዓለምገና ሳሙኤል ዲንሳ እና 5ኛ የኒሞና ንግድ ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ ናቸው።

4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በቁጥጥር ሥር አለመዋላቸው እና ሌሎቹ ግን በችሎቱ መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግም በተከሳሾቹ ላይ ሁለት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በአንደኛው ክስ በሁሉም ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ ቁጥር 32 ንዑስ ቁጥር 1(ሀ) እና የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 እና ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ነው።

በዚሁ የክስ ዝርዝር ላይም ተከሳሾች በጋራ በመሆን ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ክፍያ እንዲከፈላቸው የሚያደርግ ምንም ዓይነት የሥራ ግንኙነት ሳይኖራቸው፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚገኘው የኅብረቱ የባንክ ሒሳብ ላይ ገንዘብ በዶላር ተቀንሶ ለተከሳሾች ክፍያ እንዲፈፀም የተሰጠ ምንም ዓይነት የክፍያ ትዕዛዝ በሌለበት ሁኔታ ትዕዛዝ እንዳለ አስመስለው በተጭበረበረ መንገድ ከ6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በመውሰድ ለግል ጥቅማቸው በማዋል የማይገባቸውን ብልፅግና ለራሳቸው ለማግኘትና ለሌሎች ሰዎች ለማስገኘት በማሰብ የሚል ተጠቅሷል።

2ኛ ተከሳሽ ለአፍሪካ ኅብረት ድርጅት የግንባታ ቁሳቁስ እንዳቀረበ በማስመሰል የካቲት/2016 ዓ.ም በማቅረብ ወደ ተከሳሹ ሒሳብ ቁጥር 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ከአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ ተዘዋውሮ ገቢ እንዲሆንለት ያዘዘ መሆኑን የሚያሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ በስሙ እንዲዘጋጅ ማድረጉ በክሱ ላይ ተመላክቷል፡፡

3ኛ ተከሳሽ በረከት ሙላቱ ጃፋር ለአፍሪካ ኅብረት ጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለመሥራት የተስማማ በመሆኑ ከአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ ወደ ራሱ የሂሳብ ቁጥር 2 ሚሊየን 525 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንዲደረግ ማዘዙን የሚያሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ በስሙ እንዲዘጋጅ ማድረጉ በክሱ ተገልጿል፡፡

4ኛ ተከሳሽ ዓለምገና ሳሙኤል ዲንሳ ለአፍሪካ ኅብረት የጥልቅ ጉድጓድ የውኃ ቁፋሮ ሥራ የሠሩ በመሆኑ ኅብረቱ ወደ ግለሰቡ የሒሳብ ቁጥር 1 ሚሊየን 315 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንዲደረግ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ማዘዙን የሚያሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ በስሙ እንዲዘጋጅ አድርጓል ተብሏል በክሱ ዝርዝር ላይ፡፡

5ኛ ተከሳሽ አበራ መርጋ ተስፋዬ ለአፍሪካ ኅብረት ከማኅበሩ የግንባታ ቁሳቁስ እንዳቀረበ እና ከኅብረቱ ሒሳብ በክፍያ እንዲፈጸምለት ወደ ራሱ በሆነው የድርጀቱ ሒሳብ 1 ሚሊየን 210 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ክፍያ እንዲፈፀም ማዘዙን የሚሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶች በስሙ እንዲዘጋጅ ማስደረጉና ገንዘቡን ወጪ ለማድረግ ሰነዶቹን በውል ባልታወቀ ጊዜ እና ቦታ ለ1ኛ ተከሳሽ መስጠታቸው በክሱ ተጠቅሷል።

እንዲሁም በሁለተኛው የክስ መዝገብ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ ቁጥር 382 ንዑስ ቁጥር 1 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሳሾቹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅምን ወይም መሻሻልን ለማግኘት በማሰብ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8 ሠዓት ተኩል ላይ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አፍሪካ ኅብረት ቅርንጫፍ በመቅረብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚገኘው ኅብረቱ ሒሳብ ላይ ገንዘብ በአሜሪካን ዶላር ወጪ ተደርጎ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ለተጠቀሱት ተከሳሾች እንዲከፈል የሚያዙ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን ጠቅላላ ድምሩ 6 ሚሊየን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም በወቅቱ የምንዛሪ ተመን 346 ሚሊየን 843 ሺህ 475 ብር ለማስተላለፍ ሐሰተኛ ሰነዶቹን ለባንክ እንዲቀርብ በማድረግ እና በማቅረብ በፈጸሙት የክፍያ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል ተከሰዋል የሚል ዝርዝር አቅርቦባቸዋል።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ችሎት ቀርበው ማንነታቸውንና አድራሻቸውን ካስመዘገቡ በኋላ የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

3ኛ ተከሳሽ ጠበቃ የለኝም ማለታቸውን ተከትሎ ከጠበቃ ጋር ተማክረው እንዲቀርቡና ክሱንም በንባብ ለማሰማት ለፊታችን ሰኞ ተቀጥሯል።

ፍርድ ቤቱ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ፖሊስ አፈላልጎ እንዲያቀርባቸው በቀጣይ ቀጠሮ ትዕዛዝ እንደሚሰጥበት ገልጿል።(ታሪክ-አዱኛ)

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ROLEX Brand Original Watch

📍Color ፣ Gold አብረቅራቂ Rolex 2023

Price :- 3500birr ብቻ | ከነፃ ስጦታ Box ጋር

በTelegram ለማዘዝ 📲  @AntenehG1
በPhone ለማዘዝ ☎️ 0901882392/ በስራሰአት
🎧M19 earbuds With Power Bank🎧

📌can be used as a flashlight,powerbank and earbud

📌ፍላሽ ላይት ያለው 🔦
📌ፓወር ባንክ ያለው ለስልክ(emergency charge
📌በብሉቱዝ የሚሰራ አሪፍ ድምፅ ያለው፤ ማስቀመጫው ላይ ፓወር ባንክ ያለው
ማዳመጫው ተች ስለሆነ በመንካት ብቻ ሙዚቃ መቀየር፣ ማቆም፣ማስጀመር፣ ስልክ ጥሪ መመለስ እና መዝጋት የሚያስችል

📌ማዳመጫው ላይ LED ላይት ያለው
📌works on Android, IOS , Tablets & PC

🌺Price💸 1600birr / free delivery

👉 0901882392
👉 @Antenehg1
ETHIO-MEREJA®
Photo
ጃዋር መሀመድ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ አምባሰደርን የሰላም ጥሪ ማውገዙ አሳዛኝ ነው አሉ!

የአሜሪካ በኢትዮጵያ አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ “የሰጡትን ሃቀኛ እና ድፍረት የተሞላበት መግለጫ” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማውገዙ ግራ የሚያጋባ እና አሳዛኝ ነው ሲሉ አንጋፋው ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ ገለጹ።

ጃዋር መሀመድ ዛሬ በይፋዊ ፌስቡክ ገጻቸው ላይ አምባሳደሩ የሰጡትን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ይቀበለዋል ተብሎ የሚጠበቅ ባይሆንም አምባሳደሩ “በተለመደ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ሳይሸፋፍን ይልቁንም የአገር እውነተኛ ወዳጅ ማድረግ እንዳለበት ሁሉ በግልፅ እና በፍትሃዊነት ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የፖለቲካ ግጭቶችን በትጥቅ ሃይል ለመፍታት የሚያደርጓቸውን አውዳሚ እና የተሳሳተ ሙከራ እንዲተዉ” መጠየቃቸውን አስፍረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ያቀረቡት መግለጫ በሕዝብ የተመረጠን መንግስት ለመገልበጥ የተነሱ ቡድኖችን በመዘርዘር መንግስት እንዴት አገሪቷን መምራት እንዳለበት የሚገልጽ ያልተገባ ምክርን ያዘለ ነው” ሲል ተቃውሞታል።

የአምባሳደሩ መግለጫ “ያልተረጋገጡ መረጃዎች ያሉትና የሁለቱን አገራት ግንኙነት የሚጻረር መሆኑን የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “ስህተቶች እንዲታረሙ” ከኤምባሲው ጋር በቅርበት እንደሚሰራ በመግለጫው ገልጿል።

መንግስት ተቃዋሚዎቹን በወታደራዊ መንገድ ለማጥፋት ወደመሞከር የተመለሰ ሲሆን ይህ የተሞከረ እና ያልተሳካለት ስልት ባለፉት ዓመታት አገሪቱን አውድሟል ሲሉ ፖለቲከኛው ጃዋር ገልጸዋል።

በሰላማዊ መንገድ የተገኘውን ውጤት ከማጠናከር ይልቅ ከፍተኛ ወታደራዊ እና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችን መንግስት እያደረገ፤ ከዚሁ ጎን ለጎን ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ምህዳሩን ዋስትና በማስጠበቅ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ጀምሯል በማለትም አክለዋል።

በቅርቡ በነቀምት እና በባህር ዳር በተደረጉት የድጋፍ ሰልፎች ላይ ከተናገሩት በተቃራኒ በአብዛኛው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች እየተስፋፉ እንጂ እየቀነሱ አይደሉም ያሉት ጃዋር መሀመድ፤ መከላከያ ሠራዊት በአንዳንድ አካባቢዎች ጥሩ ውጤት ያስመዘገበ ቢሆንም፣ “ስለ ታጣቂዎች የጅምላ መክዳት በተመለከተ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች በጣም የተጋነኑ እና አንዳንዶቹ ፍጹም የፈጠራ ወሬዎች ናቸው” በማለት ጽፈዋል።

አብዛኛዎቹ ዞኖች እና ወረዳዎች በመንገድ አለመገናኘታቸው ማሳያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ጉዞው በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር እንደሆነ የጠቀሱት ፖለቲከኛው ጃዋር፤ ገበሬዎች ማዳበሪያ መቀበልም ሆነ ሰብል መትከል አይችሉም፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና እና ሕግ-ወጥ ግድያ ህይወትን በገጠሩ ሕዝብ ላይ መቋቋም የማይቻል አድርጎታል ብለዋል።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
2024/05/18 01:42:27
Back to Top
HTML Embed Code: