አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አድማ እያደረጉ ካሉ የጤና ባለሙያዎች ጋር “በአስቸኳይ ድርድር እንዲጀምሩ” እና የታሰሩትን ሰዎች “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” እንዲፈቱ አሳሰበ።
የሥራ ማቆም አድማው በመላ ሀገሪቱ የታካሚዎችን የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት “በእጅጉ ገድቧል” ሲል አስጠንቅቋል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ቡድን ዛሬ ግንቦት 15 ባወጣው መግለጫ፤ ለሁለተኛ ሳምንት እያተካሄደ ያለው አድማ “እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የጤና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ከፍተኛ መስተጓጎል” ፈጥሯል ብሏል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ፤ መንግስት “ቀውሱን የበለጠ ማራዘም የለበትም” ሲሉ ገልጸው፤ መንግስትም ሆነ የጤና ባለሙያዎች ይህንን አለመግባባት ለመፍታት በጋራ እና ገንቢ በሆነ ድርድር ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።በተጨማሪም አምነስቲ፤ “በሀኪሞቹ ላይ የሚደርሰውን መንገላታትና ማስፈራራት እንዲቆም” ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ከስራ ማቆም አድማው ጋር በተያያዘ የታሰሩ የጤና ሰራተኞች በሙሉ “ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ” በድጋሚ ጠይቋል።
አክለውም፤“ባለስልጣናቱ ያልተፈቱ ጉዳዮችን ለመፍታት እና የጤና አገልግሎቶችን እንደገና ለማስጀመር በማሰብ አስቸኳይ ወደ ድርድር ጠረጴዛ መምጣት አለባቸው” ብለዋል።የአምነስቲ የስራ ማቆም አድማ ግንቦት 4 ከጀመረ ወዲህ በመላ ሀገሪቱ የታሰሩ የህክምና ሰራተኞች 212 መደርሱን የሚገልጽ ዝርዝር እንደተቀበለም ገልጿል። በድርጅቱ ቃለ መጠይቅ የተደረገባቸው “የቤተሰብ አባላት እና ጠበቆች” የህክምና ባለሙያዎቹ የታሰሩበት ምክንያት ሳይነገራቸው መያዛቸውን ተናግረዋል።
ግለሰቦቹ፤ ፖሊስ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሳያቀርብ “የጦር መሳሪያና ፈንጂ ፍለጋ” ፍተሻ ማድረጉን እና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ብቻ እንደተያዙ ተናግረዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል “በስራ ማቆም አድማው ላይ ያለተሳተፉት” ፓቶሎጂስተ ዶ/ር ማህሌት ጉሽ እንደሚገኙ ድርጅቱ ገልጿል። ዶ/ር ማህሌት በቅርቡ በቢቢሲ ፖድካስት ላይ ቀርባ ተሞክሮዋን ማካፈሏን ተከትሎ ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሏ ተገልጿል። አምነስቲ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ ታስረው ከሚገኙ ቢያንስ 20 ከሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች መካከል አንዷ መሆኗን አሚነስቲ በመግለጫው ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፤ ፖሊስ ከጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ “በማኅበራዊ ሚዲያዎች ቅስቀሳ አድርገዋል፤ በሌሎች በሥራ ላይ በተገኙ ባልደረቦቻቸው ላይ ዛቻ እና ማስፈራራት አድርሰዋል” ያላቸውን የሕክምና ባለሙያዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል። ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የጤና ባለሙያዎች እያደረጉ ካሉት የስራ ማቆም አድማ ጋር ተያይዞ፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 47 የጤና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመግለጫው፤ የጤና ባለሙያዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋለው፤ “ሰሞኑን የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን የመብት ጥያቄ ሽፋን በማድረግ በሀገራችን ትርምስ እንዲፈጠር ከሚሠሩ ኃይሎች ጋር በማበር ሕገ ወጥ የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ፣ በጤና ዘርፉ ላይ ሁከት በመፍጠር እና የታካሚዎችን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል” በመጠርጠራቸው መሆኑን ገልጿል።
የጤና ባለሙያዎቹን እስር በተመለከተ ቻጉታ፤ “ደመወዝ እና ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን በመጠየቃቸው ቢያንስ 20 የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸው አሳፋሪ እና በጣም አሳሳቢ ነው” ብለዋል።ድርጅቱ ባለሥልጣናት የህዝብ ጤና ኢንቨስትመንትን እንዲጨምሩ አሳስቧል። “መንግስት እንደ ጤና ላሉት ወሳኝ የህዝብ አገልግሎቶች ከፍተኛውን በጀት መመደብ አለበት፣ ይህም ከመንግስት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎች ጋር የሚስማማ ነው” ብሏል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ

የእራኤል የገንዘብ እና የመከላከያ ሚኒስቴር ተጋጩ
ሚኒስትሮቹ የተጋጩት በጋዛ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የመከላከያ ሰራዊት ከተመደበለት በጀት በላይ ተጠቅሟል በሚል ነው።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በጋዛ ጦርነት ምክንያት የተመደበለትን በጀት ከልክ በላይ በማውጣቱ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ከፍተኛ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን የሆነው KAN ዘግቧል።
ይህ የተፈጠረው በዝግ የፀጥታ ካቢኔ ስብሰባ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር በዓመቱ የተመደበለትን ወጪ ከታቀደው ከ4 ነጥብ 17 ቢሊየን ዶላር በላይ ብልጫ እንዳለው ለመንግስት ባሳወቀበት ወቅት ነው።
የፋይናንስ ሚኒስቴር እንደገለፀው በጋዛ ግጭቱ እስከ ቀጠለ ድረስ የበጀት ክፍተቱ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ወደ 7 ቢሊዮን ዶላር ሊጠጋ እንደሚችል ካን ዘግቧል።
በገንዘብ ሚኒስትሩ ባዛል ስሞትሪች እና በመከላከያ ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር መካከል ውጥረት ስለመንገሱም ተነግሯል ።
ክርክሩ የፋይናንስ አስተዳደርን በሚመለከት የጋራ ውንጀላ ላይ ያተኮረ ነው ሲል ቲ አር ቲ ግሎባል ዘግቧል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ትራምፕ ፑቲንን 'እብድ ነው' ሲሉ ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሞስኮ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ከባድ የአየር ላይ ጥቃትን ተከትሎ በሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ደስተኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ትራምፕ ባልተለመደ ተግሳጽ “ምን ነካው? ብዙ ሰዎችን እየገደለ ነው” ያሉ ሲሆን አክለውም ፑቲንን "ፍፁም እብድ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ቀደም ብለው ዋሽንግተን በቅርብ ጊዜ በሩሲያ ጥቃቶች ላይ የነበራት "ዝምታ" ፑቲንን የሚያበረታታ ነው ሲሉ በሞስኮ ላይ "ጠንካራ ጫና" -እንዲሁም ጥብቅ ማዕቀቦችን እንድትጥል አጥብቀው አሳስበዋል።
ሩሲያ 367 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በመተኮሷ በዩክሬን በአንድ ሌሊት ቢያንስ 12 ሰዎችን ስትገድል በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል። ፑቲን በ 2022 ሙሉ ወረራ በዩክሬን ላይ ከጀመሩ ወዲህ በአንድ ሌሊት ውስጥ ከፍተኛው ጥቃት በትላንትናው እለት ፈፅመዋል።የአየር ሳይረን ማስጠንቀቂያ የሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎች ጥቃት ሲፈፀም በበርካታ የዩክሬን ክልሎች ተሰምተዋል። በሰሜን ምስራቅ ካርኪቭ ከተማ አንድ ህፃንን ጨምሮ ቢያንስ ሶስት ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ ከንቲባ ኢጆር ቴሬኮቭ ተናግረዋል። እሁድ እለት በኒው ጀርሲ ለጋዜጠኞች ትራምፕ ስለ ፑቲን ሲናገሩ “ለረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ ፣ ሁል ጊዜም ከእርሱ ጋር ተስማምቼ ነበር ፣ ግን እሱ ሮኬቶችን ወደ ከተማዎች በመላክ ሰዎችን እየገደለ ነው ፣ እና በጭራሽ አልወደውም ። ” ብለዋል።
ትራምፕ አሜሪካ በሩሲያ ላይ የምትጥለውን ማዕቀብ ለመጨመር እያሰቡ እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ “በፍፁም” ብለዋል።

#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate

FMany people have made money by joining StoneX Fund Investments, what are you waiting for?
Join StoneX Fund Investments and make money at home anytime, anywhere. Making money is as easy as breathing.
Join StoneX Fund Investments and prepare for tomorrow. If you don't keep up with the times, you will fall behind.
Join StoneX Fund Investments and find your own code to get rich.
As long as you are eager for wealth, don't hesitate and join StoneX Fund Investments immediately.
Official registration address: https://stxfunds.com/?invitation_code=66E39
Official Telegram channel: https://www.tg-me.com/StoneX_Fundinvestment000

የአውሮፓ ህብረት ለወታደራዊ ኃይል የሚውል 150 ቢሊዮን ዶላር አፀደቀ!
የአውሮፓ ህብረት የሩስያን ጥቃት በመፍራት የአህጉሪቱን ወታደራዊ ኃይል ይበልጥ ለማጠናከር የ150 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ በጀት ማፅደቁ ተሰምቷል።
በቤልጂየም ብራሰልስ በተደረገው ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ሀገራት ሚኒስትሮች የአህጉሪቱ ደህንነትን ለማጠናከር በሚያስፈልገው ህጋዊ ሰነድና የገንዘብ ፈንድ ላይ ስምምነቱን መፈረማቸው ተገልጿል።
ስምምነቱ በአውሮፓ ውስጥ በሚገኙ 26 ሀገራት መካከል የተደረሰ ነው ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን በኤክስ ገጻቸው ላይ፤ በአውሮፓ ህብረት ደረጃ ለመጀመርያ ጊዜ ትልቅ የደህንነት ኢንቨስትመንት መደረጉን ገልጸው፤ ሊያጠቁን ከሚፈልጉ አካላት የተሻለ የመከላከል አቅም ይኖረናል ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ የህብረቱ እርምጃ የተወጠነው በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር የምትመራው አሜሪካ ከአውሮፓ ሀገራት ጋር የላት ጠንካራ ግንኙነት በመሻከሩ ነው ተብሏል።
አንደ ሮይተርስ ዘገባ የህብረቱ አባል ሀገራት የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ወደ አውሮፓ ይዛመታል በሚል ስጋት ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ የመከላከያ አመታዊ በጀታቸውን በ30 በመቶ መጨመራቸው ተገልጿል።

የኤም ፖክስ በሽታ በኢትዮጵያ ያለው የስጋት ደረጃ ዝቅተኛ ነው፡- የጤና ሚኒስቴር
የኤም ፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) በሽታ በዓለም አቀፈ ደረጃ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ተብሎ ተየቀመጠ ቢሆንም በኢትዮጵያ ያለው የስጋት መጠን ዝቅተኛ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኤም ፖክስ በሽታ ተጠቂ በኢትዮጵያ መመዝገቡን ተከትሎ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ለመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ማብራያ ሰጥተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ አስተዳደር እስካሁን የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሦስት ሰዎች ላይ በሽታው ተገኝቷል፡፡
ይህንንም ተከትሎ የቅኝት እና የምላሽ ስራዎች በጤና ሚኒስቴር እና ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመሆን እየተሰራ ነው ብለዋል።
በሽታው በንክኪና በመተንፈሻ አካላት ቅርርብ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን፣ በሽታው በተገኘበት አካባቢ ከበሽታው ተጠቂዎች ጋር ቅርበት ያላቸው ሰዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።
የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠርም በየብስ እና በአየር በሚደረጉ ጉዞዎች ላይም ቅኝት እየተደረገ ነው ብለዋል።
አሁን ላይ በሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለፉት አምስት ወራት በ78 በመቶ አድጎል ያሉት ጤና ሚኒስትሯ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቅድመ ዝግጅት እና የምላሽ ስራዎች በቅንጅት እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የበሽታው ምልክት ሽፍታ፣ ትኩሳት፣ ንፍፊት፣ እብጠት፣ የጡንቻ እና የጀርባ ሕመም በመሆኑ እነዚህን ምልክቶች ያየ ሰው በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም እንዲቀርብ ተጠይቋል። አልያም 8335 እና 952 ነፃ የጥሪ አገልሎት እንዲያሳውቅ ተጠይቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መግለጫ ሰጠ!
በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በሚለው ዘገባ ላይ ባንኩ መግለጫ ሰጥቷል!!
ሙሉ መግለጫው ከታች ቀርቧል👇
"ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሚዲያ አገልግሎት በተሰኘ የዜና ማሰራጫ እንደ ሰበር ዜና የተላለፈ መልእክት “በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በማለት ባንካችን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተዘረፈ፣ ዘራፊዎቹ እንዳልተያዙ እና ባንካችንም ጉዳዩን አድበስብሶ እንዳለፈው የሚገልጽ የሐሰት ዜና ስለተዘገበ በጉዳዩ ላይ አጭር መግለጫ ለመስጠት ተገድደናል።
ከላይ የተጠቀሰው ሚዲያ እና ሌሎችም ይህንኑ ሚዲያ ያጣቀሱ ሚዲያዎች ከባንካችን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተዘረፈ የሚገልጽ ዜና ቢዘግቡም፣ እውነታው ግን፡-
➢ በሚዲያዎቹ ከተዘገበው በተቃራኒ ከባንካችን ምንም የተዘረፈ ገንዘብ አለመኖሩን፣ ይልቁንም ከፍተኛ ገንዘብ ለመዝረፍ የተደረገ ሙከራ መሆኑን፣
➢ ባንካችን ሙከራው በተደረገ በጥቂት ደቂቃዎች ዉስጥ በጠንካራው የውስጥ ቁጥጥር ስርአታችን አጠራጣሪ ግብይት መፈፀሙን ስለደረሰበት ምንም ዓይነት ገንዘብ ወጪ ሳይደረግ ሙከራው ወዲያውኑ እንዲከሽፍ መደረጉን፣
➢ ሙከራው በጥቂት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ባሰቡ ተጠርጣሪዎች የተፈፀመ እንጂ የባንካችንን ሲስተም ተላልፎ የተፈፀመ ጥቃት አለመሆኑን፣
➢ ባንካችን ሙከራ የተደረገበትን ገንዘብ ባለው ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት አማካኝነት ከጥቃት ከተከላከለ በኋላ ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማሳወቅ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉና የምርመራ ስራውም ተጠናክሮ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑን፣
➢ በማጠቃለያም ባንካችን እንደማንኛውም የፋይናንስ ተቋም በተለይም እንደ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋምነቱ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት አስበው ለሚንቀሳቀሱ አካላት ኢላማ መሆኑ እሙን ቢሆንም እንዲህ አይነቱን ሕገ ወጥ ተግባር ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓትና የዘመነ ሲስተም ያለው ለመሆኑ ይህ የሙከራ ድርጊት መክሸፉ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅትም ጉዳዩ በሕግ አካላት ተይዞ ጥብቅ ክትትል እየተደረገበት የሚገኝ እና የምርመራ ሂደቱም ያልተጠናቀቀ መሆኑን እያሳወቅን በቀጣይ የሕግ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ዝርዝር መረጃውን የምናሳውቅ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡"

በጋዛ የሃማስ መሪ የሆነው መሀመድ ሲንዋር መገደሉን እስራኤል አስታወቀች
****
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፥ በእስራኤል በጥብቅ ከሚፈለጉት የሃማስ ሰዎች መካከል አንዱ እና በጋዛ የሃማስ መሪ የሆነው መሃመድ ሲንዋር በጦራቸውመገደሉን ገልጸዋል።
መሀመድ ሲንዋር ባሳለፍነው ግንቦት 5 ቀን በደቡባዊ ካን ዮኒስ የአውሮፓ ሆስፒታል ግቢ እና አካባቢ ላይ የተደረገው የእስራኤል ከፍተኛ ጥቃት ዒላማ መሆኑ ተገልጿል። የእስራኤል ወታደራዊ ሃይል የሃማስን የምድር ውስጥ የጉዞ መስመር እና የተለያዩ ቢሮዎች በጥቃቱ ማውደም እንደቻለ በወቅቱ ገልጾ ነበር።
በጋዛ ሃማስ የሚመራ የሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ በጥቃቱ 28 ሰዎች መሞታቸውን ቢገልጽም ከሲንዋርን ጋር በተያያዘ በህወት ይኑር ወይም ይሙት ምንም አይነት መረጃን አላወጣም።
እ.ኤ.አ ጥቅምት 7/ 2023 በእስራኤል ላይ የተፈፀመው ጥቃት ዋና አቀነባባሪ የተባለው እና የመሀመድ ሲንዋር ወንድም የሆነው ያህያ ሲንዋር ባለፈው ጥቅምት ወር በእስራኤል ወታደሮች መገደሉ ይታወሳል ሲል የዘገብው ቢቢሲ ነው።
የእስራኤል እና ሃማስ ግጭት ለ20 ወራት የዘለቀ ሲሆን፤ በተለያየ ጊዜ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ቢደረጉም እስካሁን ዘላቂ መፍትሄ ሊበጅለት አልቻለም።

ትራምፕ ካናዳ ለጎልደን ዶም 61 ቢሊየን ዶላር ትከፍላለች ካልሆነ 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት ትሆናለች ሲሉ ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለካናዳ የነደፉትን የጎልድ ዶም ሚሳይል መከላከያ ስርዓት አካል ለመሆን 61 ቢሊዮን ዶላር መክፈል እንዳለባት ይህንን መክፈል ካልሆነላት ደግሞ 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት ትሆኔለች ሲሉ ተደምጠዋክ። ትራምፕ በግል ንብረታቸው ትሩዝ ሶሻክ ላይ በለጠፉት መልዕክት ካናዳ “የእኛን አስደናቂ ወርቃማ ዶሜ ስርዓት አካል መሆን በጣም ትፈልጋለች” እናም ከአሜሪካ ጋር ከተቀላቀለች ከክፍያ ነፃ ትሆናለች ብለዋል።
በታቀደው የመከላከያ ስርዓት ውስጥ ካናዳ “51 ኛ የአሜሪካ ግዛት ከሆነች ዜሮ ዶላር በመሆኑ ምንን ወጪ አታወጣም ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።የትራምፕ ይህ ጽሁፍ ይፋ የሆነው የካናዳ ፓርላማ የዩናይትድ ኪንግደም ንጉስ ቻርለስ ሳልሳዊን ያልተለመደ ንጉሣዊ ንግግር ካደረጉ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው። ንጉሣዊው የካናዳ ሉዓላዊነት “በአደገኛ እና እርግጠኛ ባልሆነ” ጊዜያት እና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት አገሪቱን የአሜሪካ አካል እንድትሆን በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወቅት የወጣ ማሳሰቢያ ነው።ካናዳ ለትራምፕ የቅርብ ጊዜ መግለጫ አስተያየት ወዲያውኑ ከመስጠት ተቆጥባለች ፣ ነገር ግን የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ካርኒ ቀደም ሲል ሀገራቸው በመከላከያ ስርዓት ጉዳይ ላይ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር “ከፍተኛ ደረጃ” ውይይት እንዳደረገች ተናግረዋል።
በአጠቃላይ፣ ትራምፕ ወርቃማው ዶም የመከላከያ ስርዓት 175 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣና አሁን ባለው የስልጣን ዘመናቸው በ2029 እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።ምንም እንኳን ትራምፕ እንዲህ ቢሉም የመከላከያ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ይጠናቀቅበታል በተባለው ጊዜ, በጀት እና አዋጭነት ላይ ጥያቄ ያነሳሉ።
@ethio_mereja

ዩክሬን ድሮኖችን በመጠቀም ቦንብ ጣይ አደገኛ የሩሲያ አውሮፕላኖችን ላይ ጥቃት ፈፅማለች!።
በዚህ ያልተጠበቀ ጥቃት 40 የሚሆኑ የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች መውደማቸው እየተገለፀ ነው።
ዩክሬን በ40 የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች ላይ በአራት ወታደራዊ ካምፖች ላይ ከባድ ጥቃቶችን ከፈጸመች በኋላ፣ ከሩሲያ ጋር ባደረገችው ጦርነት ትልቁን የረዥም ርቀት ጥቃት እሁድ ፈጽማ ማጠናቀቋን ስትገልጽ፤ ሩሲያ በበኩሏ በአምስት ክልሎቿ ዩክሬን የፈጸመችውን ጥቃት "የሽብርተኝነት ድርጊት" በማለት ፈርጃዋለች።
ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ትልቁ ኦፕሬሽን መጠናቀቁን ሲገልጹ "በኤስቢዩ የደህንነት አገልግሎት (Security Service of Ukraine (SBU) “Spider's Web" እየተባለ በሚጠራው ኦፕሬሽን 117 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቅም ላይ አውለን፣ "34% [የሩሲያ] ስትራቴጂካዊ የክሩዝ ሚሳይል ተሸካሚዎችን” መትተናል" ብለዋል።
የዩክሬን የደህንነት ምንጮች እንዳሉት "ይህን ዛሬ በሩሲያ ላይ የተፈጸመውን ከባድ ጥቃት ለማደራጀት አንድ አመት ተኩል ፈጅቷል።"
ብዛት ያላቸው የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ በሩሲያ ድንበሮች ውስጥ አልፈው ገብተው፣ የተለያዩ ወታደራዊ አየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም፣ ከ40 በላይ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ማጋየታቸውን የኪየቭ ባለስልጣናት ቀደም ሲል መናገራቸውን ተዘግቦ ነበር።

አትሌት ድርቤ ወልተጂ የግራንድ ስላም ሻምፒዮን ሆነች
በፊላደልፊያ በተደረገው ግራንድ ስላም ትራክ አጭር ርቀት አትሌቷ አሸናፊ ሆናለች።
ድርቤ ወልተጂ በ800 ሜትር አጭር ርቀት አንደኛ ስትወጣ 1 ደቂቃ 58.94 ሰከንድ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰአት ሆኗል። ትላንት በ1500 ሜትር አጭር ርቀት በተመሳሳይ አሸናፊ የነበረችው ድርቤ ወልተጂ ከሁለቱም ውድድሮች 24 ነጥብ በማምጣት የፊላደልፊያ ሻምፒዮን ሆናለች።
አትሌቷ የ100 ሺ ዶላር አሸናፊም ሆናለች።
በዚህ አመት በተጀመረው አዲስ ውድድር በቋሚነት እየተሳተፈች የምትገኝው ድርቤ ወልተጂ በጃማይካ ኪንግስተንም ሻምፒዮን እንደነበረች ይታወሳል።

ፕላስቲክ❗️ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2000 እስከ 5000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ፀደቀ!!
ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከ2000 እስከ 5000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡፡
ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50,000 ብር በማያንስና ከ200,000 ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡
የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ባቀረቡበት ወቅት፤ የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው? የሚል ጥያቄ ከጠየቁ ብኋላ የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡
አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው #ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዴት ታየ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡
ለምሳሌ «አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው ብለዋል፡፡
ለህዝቡ ግንዛቤ ለመስጠትም ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ይካሄዳል ሲሉ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡አዋጁ የፕላስቲክ ጫማዎችን፣ የውሃ ኮዳዎችን እና ወፍራም የፕላስቲክ ውጤቶችን አይጨምርም መባሉን ሰምተናል፡፡
አዋጁ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤቱ ድንበር አንስቶ ከሃያ ሜትር በላይ አካባቢውን የማጽዳት ግዴታን ያስቀምጣል፡፡አዋጁም በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ምንጭ ፣ ሸገር ኤፍ ኤም