Telegram Web Link
አሜሪካ በፈፀመችው ጥቃት የኒውክሌር ብክለት አልተከሰተም - ኢራን
**

አሜሪካ ኢስፋሃን፣ ፎርዶ እና ናታንዝ በተባሉ የኢራን የኒውክሌር ማብላያ ጣቢያዎች ላይ የፈፀመችው ጥቃት የኒውክሌር ብክለት አለመከሰቱን ኢራን ገለጸች።

የኢራን ብሔራዊ ሚዲያ የሀገሪቱን ብሔራዊ የኒውክሌር ደኅንነት ሥርዓት ማዕከልን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የጨረራ ቁጥጥር መሣሪዎች ጥቃቱ በደረሰባቸው አካባቢዎች ምንም ዓይነት የራዲዮአክቲቭ ልቀትን አልመዘገቡም።

በጣቢያዎቹ የሚገኙ የዩራንየም ንጥረ ነገሮች ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ወደ ሌላ ቦታ በመወሰዳቸው በአካባቢው ምንም የሚፈጠር የራዲዮአክቲቭ ልቀት እንደማይኖር እየተነገረ ይገኛል።

በመሆኑም ጥቃቱ እንደተፈፀመባቸው በተጠቀሱት አካባቢዎች በሚኖሩ ሰዎች ላይ የሚደርስ አደጋ እንደማይኖር ማዕከሉ ባወጣው መግለጫ መግለጹን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ቀደም ብሎም እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ማብላያ ጣብያዎች ላይ ያደረሰችው የአየር ድብደባ በተመሳሳይ መልኩ በተቋማቱ ዙሪያ ምንም ዓይነት ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር እንዲለቀቅ አለማድረጉን ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አስታውቆ ነበር።


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
🥳 ጓደኛዎችዎን ወደ አፍሮቤት ይጋብዙ እና አስደሳች ቦነስ ያግኙ!

👇 የእርስዎ ልዩ መለያዎን ለጓደኛዎ ወይም ለቅርብ ወዳጅዎ ያጋሩ ሽልማቶችን ያግኙ።

💸💰ለእያንዳንዱ አዲስ ስኬታማ ምዝገባዎች 15% ቦነስ ያገኛሉ።

🔗 አሁኑኑ ማጋራት ይጀምሩ እና ገቢዎትን ያሳድጉ!

https://bit.ly/3XbY3o7 ጋር ያሸንፉ።
#ቴምርሪልስቴት መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት ሽያጭ
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት AU አፓርትመንት ሽያጭ

👉1መኝታ 75ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 802,500ብር
ሙሉ ክፍያ 8,025,000ብር
👉2መኝታ 94ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,005,800ብር
ሙሉ ክፍያ 10,058,000ብር
👉2መኝታ 103ካሬ
10%ቅድ ክፍያ 1,102,100ብር
ሙሉ ክፍያ 11,021,000ብር
👉3መኝታ 132ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,412,400ብር
ሙሉ ክፍያ 14,124,000ብር
👉3መኝታ 146ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,562,200ብር
ሙሉ ክፍያ 15,622,000ብር
‼️ቀሪውን 90% በ 18ዙሪ ያለምንም ጭማሪ በብር የሚከፍሉት ነው
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
የኢራን ፓርላማ ወሳኙን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥን ለመዝጋት የቀረበውን ሀሳብ አፀደቀ
**

ኢራን ፓርላማ የአለማችን 20 በመቶ የሚሆነው ድፍድፍ ነዳጅ የሚተላለፍበት የባህር ሰርጥን ለመዝጋት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል፡፡

ፓርላማው ውሳኔውን ያስተላለፈው አሜሪካ እስራኤልን በማገዝ በኢራን ሶስት የኒውክሌር ማብለያ ተቋማት ወታደራዊ እርምጃ መውሰዷን ተከትሎ ነው።

የፓርላማው ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ በሚያሳልፉት የመጨረሻ ትእዛዝ መሆኑ ተነግሯል።

40 ኪሎ ሜትር ብቻ ስፋት ያለው የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ የመዘጋት አደጋ ካጋጠመው በአለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ትልቅ ተፅእኖ ሊፈጥር እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

የኢራን ፓርላማ ያቀረበው ይህ ውሳኔ የኢራኑን መሪ የአያቶላህ አሊ ኻሚኒን የመጨረሻ ውሳኔ እየጠበቀ ነው ሲል ኒውስ ዊክ የኢራን ቴሌቪዥንን ጠቅሶ ዘግቧል።

የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ፈሳሽ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ የጫኑ መርከቦች ዋነኛ መተላለፊ ሲሆን፤ እኤአ 2024 በየቀኑ ብቻ 20.3 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅና ፔትሮሊየም ተላልፎበታል ተብሏል።

አሜሪካ ፎርዶውን ጨምሮ ኢራን ውስጥ በሚገኙ 3 የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ኢራን በቀጣይ ምን አይነት እርምጃ ትወስዳለች የሚለው የሚጠበቅ ሆኗል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ETHIO-MEREJA®
Photo
አሜሪካ “የእኩለ ሌሊት መዶሻ” ባለችው የኢራኑ ጥቃት የትኞቹን የጦር መሳሪያዎች ተጠቀመች?

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች ኢራን ውስጥ የሚገኙ ሦስት የኒውክሌር ተቋማትን በቦምብ መደብደባቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል።

አሜሪካ “የእኩለ ሌሊት መዶሻ” የሚል ስያሜ በሰጠችው ኦፕሬሽን ጂቢዩ 57 ወይም ማሲቭ ኦርዲናንስ ፔኔትሬተር (ኤምኦፒ) ቦምብ ተጠቅማለች፡፡

ይህ ‘ምሽግ ደርማሽ’ ቦምብ 13 ሺህ 600 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን ከመፈንዳቱ አስቀድሞ እስከ 60 ሜትር ድረስ ወደ መሬት ሰርጎ የመግባት አቅም ያለው ነው፡፡

ቦምቡ 'ቢቱ ስቲልዝ' በተባለው አውሮፕላን አማካኝነት ከዒላማው ከ12 ሺህ እስከ 15 ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ የተጣለ ሲሆን ያለው ክብደት እና የመሬት ስበት በሚያርፈበት ቦታ ላይ ውድመት እንዲያስከትል ያደርጉታል፡፡

የተቀመጠለትን ዒላማ እንደማይስት የሚነገርለት 'ምሽግ ደርማሹ' ቦምብ በውስጡ በተገጠመለት ጂፒኤስ በመጠቀም ነው ጥቃቱን የሚያደርሰው፡፡

በዚህም ከተጣለ በኋላ ምንም ዓይነት የዒላማ ለውጥ ወይም ቁጥጥር ማድረግ አይቻልም፡፡

የአንዱ ዋጋ ከ3.5 እስከ 4 ሚሊዩን ዶላር እንደሚደርስም ተመላክቷል፡፡

ይህንን ግዙፍ ቦምብ መሸከም የሚችለው የ'ቢቱ ስቲልዝ' አውሮፕላን ባለው ቅርፅ በተለይም በፀረ-አውሮፕላን አነፍናፊ መሳሪያ ላይ ወፍ ወይም በራሪ መስሎ መታየት መቻሉ በዒላማ ማክሸፊያ እንዳይመታ ያስችለዋል፡፡

በተጨማሪም ትክክለኛ ያልሆነ የራዳር መረጃ የሚያቀብል የኤሌክትሮኒክ ቴክኒክ ያለው ነው፡፡

ሌላው አሜሪካ የተጠቀመችው ከ1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መወንጨፍ የሚችሉት የ'ቶማሃውክ ክሩዝ' ሚሳኤሎች ናቸው፡፡

ከሰርጓጅ መርከብ ላይ የተነሱት ሚሳኤሎቹ ከምድር በታች ያልሆነ ማለትም በምድር ላይ ያለ ዒላማን ለማጥቃት የሚውሉ ናቸው፡፡

በአሜሪካ የ“ሌሊት መዶሻ ኦፕሬሽን” 30 የሚሆኑ የ'ቶማሃውክ ክሩዝ' ሚሳኤሎች ከ640 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መወንጨፋቸው ተገልጿል፡፡

በራዳር ዕይታ ውስጥ እንዳይገባ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ መንሳፈፍ የሚችለው ሚሳኤሉ ከተወነጨፈ በኋላ የዒላማ ብሎም የአቅጣጫ ቅየራ እንዲያደርግ ማዘዝ ይቻላል፡፡እያንዳንዱ 'ቶማሃውክ ክሩዝ' ከ1.5 እስከ 2 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ዋጋ ያለው ነው፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
💸💲 ይመልሱ 10,000 ብር ያሸንፉ💲💸

በእግር ኳስ ታሪክ ብዙ የፊፋ ያለም ዋንጫ ያሸነፈ ሀገር ማን ነው

ትክክለኛውን ውጤት በአፍሮ ስፖርት የቴሌግራም  ወይም ፌስቡክ ቻናላችን ላይ ገብተው በመመለስ 10 ሺ ብር ይሸለሙ!

https://www.tg-me.com/afrosportsbet/663
https://www.facebook.com/share/p/1GfvEbhS7B/
#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate
ኢራን በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ኳታር በኢራን ለተቃጣባት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች❗️

ማምሻውን በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን ማጥቃት የጀመረችው ኢራን በምዕራባዊ ኢራቅ የሚገኘውን አል-አሳድ የጦር ሰፈር በሚሳኤል መደብደቧን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።

ከሰዓታት በፊት የኢራን መንግሥት በኒውክሊየር መሰረተ ልማቶቹ ላይ በአሜሪካ ለተፈጸመበት ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ ዝቶ ነበር።

በተያያዘ ኳታር በኢራን ለተቃጣባት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

የኳታር መከላከያ ሚኒስትር፥ ኢራን ኳታር በሚገኘው አል-ኡዴይድ የጦር ሰፈር ላይ ሚሳኤል ተኩሳለች፤ በዚህም ኢራን የኳታርን ሉዓላዊነት ተዳፍራለች ብለዋል።

ኳታር ከኢራን ለተቃጣበት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ የመስጠት መብቷ በዓለም አቀፍ ሕግ የተጠበቀ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። አክለውም፥ የኳታር የአየር መከላከያ ሥርዓት የከኢራን የተተኮሱ ሚሳኤሎችን በማክሸፍ ጥቃቱን መመከቱንም ተናግረዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ሳውዲ አረቢያ ኢራን "በኳታር ላይ" የፈጸመችውን ጥቃት አወገዘች
****

የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በኩል ባወጣው መግለጫ ኢራን ማምሻውን "በኳታር ላይ" የፈጸመችውን ጥቃት በጽኑ አውግዟል።

የሳውዲ መንግሥት በመግለጫው ኢራን "በኳታር ላይ" ያደረሰችውን የሚሳኤል ጥቃት በጽኑ አውግዞ፤ ድርጊቱ የኳታርን ሉዓላዊነት፣ ዓለም አቀፍ ሕግና ቻርተርን እንዲሁም የመልካም ጉርብትና መርሆን የጣሰ ነው ብሏል።

አያይዞም፥ ድርጊቱን ከማውገዝ ባሻገር ኳታር ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የምትወስዳቸውን እርምጃዎች ሳውዲ አረቢያ ትደግፋለች፤ ከጎኗ በመሆን ለማገዝም ዝግጁ ናት ብሏል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
2025/06/28 10:17:37
Back to Top
HTML Embed Code: