በአንድ ቀን ብቻ በመዲናዋ #ወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ የበከሉ 17 ድርጅቶች እና ስምንት ግለሰቦች ከአምስት ሚሊየን ብር በላይ መቀጣታቸው ተገለጸ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ 17 ድርጅቶችን እና 8 ግለሰቦችን ትላንት መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ አምስት ሚሊየን 910 ሺ ብር መቅጣቱን አስታወቀ፤ የገንዘብ ቅጣቱን ያስከፈልኩት ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ነው ብሏል።
ባለስልጣኑ ትላንት መጋቢት 10 ቀን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 2 ሚሊየን 100 ሺ ብር፤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 910 ሺ ብር ፤ በኮልፌ ክፍለ ከተማ 690 ሺ ብር፤ በየካ ክ/ከተማ 600 ሺ ብር መቅጣቱን አስታውቋል።
በተመሳሳይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 600 ሺ ብር ፤ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 600 ሺ ብር እና በልደታ ክ/ከተማ 400 ሺ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ መደረጉን የባለስልጣን መስርያ ቤቱ መረጃ ያመላክታል።
በአጠቃላይ በእለቱ 17 ድርጅት እና 8 ግለሰቦች በድምሩ 5,910,000/ አምስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ/ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ብሏል።
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻን በመበከል ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ

👍58❤3🤯2😭2😁1
ኢትዮጵያ ከግብፅ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
**
ለ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት ከግብፅ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
**
ለ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት ከግብፅ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
👍62😁18❤5👏3👎2
ETHIO-MEREJA®
Photo
የንግድ ተቋማት እስከ ምሽት 3:30 ድረስ እንዲቆዩ የሚያስገድድ ደምብ ከመጋቢት 10 ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል!!!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደምብ 185/2017 የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ምሽት 4 ሰዓት ድረስ በመንገድ ዳር የሚገኙ የንግድ ተቋማት ደግሞ ምሽት 3:30 ድረስ እንዲቆዩ የሚያስገድድ ደምብ ከመጋቢት 10 ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል።
ደንቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ያጸደቀው የካቲት 29/2017 ዓ/ም የነበረ ሲሆን ይህ ደንብ መመሪያዎች ተዘጋጅተውለት ከመጋቢት 10/2017 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
የንግድ ቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሰማ ጀማል ደንቡ የህግ ተጠያቂነትን ጨምሮ ፣የገንዘብ እና በመጨረሻም ንግድ ፈቃድን እስከ መሰረዝ የሚደርሱ ቅጣቶች እንዳሉት ተናግረዋል።
የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ በዝርዝር ምን አሉ/?
" የገንዘብ ቅጣቱ የመጀመሪያ ደረጃ ጥፋት ፣ሁለተኛ ደረጃ ጥፋት እያለ እስከ አምስተኛ ደረጃ የሚያስቀምጣቸው የገንዘብ ቅጣት እርከኖች አሉት።
በመጀመሪያ ደረጃ በሚሰጡ ማስጠንቀቂያዎች ላይ የማይታረሙ የንግድ ተቋማት ላይ እስከ መጨረሻው የገንዘብ እርከን ከተቀጡ በኋላ የንግድ ፈቃድን እስከ መሰረዝ የሚደርስ ቅጣት እንዲቀጡ ይደረጋል።
ይህ ከመሆኑ በፊት ደንቡን የማስተዋወቅ ስራ በሁሉም ሚዲያዎች ይሰራል።
ደንቡን ተግባራዊ አድርገናል እዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር አይኖረውም የማስተዋወቁ ስራ ግን በሰፊው ይሰራበታል የቅጣት እርከኖቹን ይፋ ማድረግ ጀምረናል።
ደንቡ ዝርዝር መመሪያ በቢሮው እየተዘጋጀለት ነው በፍጥነት ጨርሰን ግልጽ እናረጋለን።
ህጉ የሚሰራው የኮሪደር ልማቱ ያለባቸውን አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን በመላው አዲስ አበባ በ 11 ንዱም ክፍለ ከተሞች ዋና ዋና መንገድ ላይ የሚገኙ ሁሉንም የንግድ ተቋማትን ላይ ነው።
የትራንስፖርት እንቅስቃሴንም በተመለከተ ሁሉንም የግል የትራንስፖርት ሰጪ አካላትን ጨምሮ የሚመለከት ነው ይህንንም መንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ጋር በመሆን በጋራ ተፈጻሚ ይሆናል " ብለዋል።
አስተዳደራዊ የመጀመሪያ ደረጃ የገንዘብ ቅጣት እርከን ምን ይመስላል ?
👉ከምሽቱ 3፡30 በፊት የንግድ ተቋሙን መዝጋት 10 ሺህ ብር ያስቀጣል።
👉ለተገልጋይ ሊያቀርብ የሚችለው አገልግሎት ወይም ምርት እያለው የለም በማለት ተገልጋይ እንዳይስተናገድ ማድረግ 10 ሺህ ብር ያስቀጣል።
👉መንገድ ዳር ያሉ ንግድ ተቋማት እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከምሽት እስከ ንጋት ድረስ የተቋሙን የውጭ እና የውስጥ መብራት አለማብራት 7 ሺህ ብር ያስቀጣል።
👉የሕንጻ የፊተኛው ገጽ መብራት ወይም የፋሳድ ላይት መብራት ያለመስቀል እና/ወይም ያለማብራት 5 ሺህ ብር ያስቀጣል።
👉የንግድ ተቋሙ መግቢያ በር ዝግ ሆኖ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ ክፍት መሆኑን የሚያመለክት በኤሌክትሪክ የሚሰራ ምልክት ያለማድረግ 5 ሺህ ብር ያስቀጣል።
👉ከምሽቱ 4፡00 በፊት የትራንስፖርት አገልግሎት ማቋረጥ ፣ መውጣት ወይም የስምሪትን መስመር ማቆራረጥ 5 ሺህ ብር ያስቀጣል።
👉የከተማ አስተዳደሩ ካወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፊ በላይ ተሳፋሪውን ማስከፈል 5 ሺህ ብር ያስቀጣል።
ከገንዘብ እና አስተዳደራዊ ቅጣቶች በፊት ከምሽት 3:30 በፊት የንግድ ተቋሙን ዘግቶ የተገኘ ነጋዴ የ24 ሰዓት የማስጠንቀቂያ ጊዜ እንደሚሰጠው አቶ ሙሰማ ጀማል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
(ደንቡ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ የሚሆነው ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ሲወጣለት ሲሆን አሁን ላይ የመመሪያው እየተዘጋጀ ይገኛል)

👍39❤5👎4
🇪🇹🇪🇬ከደቂቃዎች በኃላ ሌሊት 6:00 ሰዓት ላይ ግብፅን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ አምስተኛ ጨዋታውን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል።
ለጨዋታው በቋሚ 11 የሚሰለፉ ተጫዋቾች ቋሚ አሰላለፍ ታውቋል።
በዚህም መሰረት :-
ግብ ጠባቂ :- አቡበከር ኑራ
ተከላካዮች :- አስቻለው ታምነ ፣ አማኑኤል ተርፉ ፣ ራምኬል ጄምስ ፣ ብርሀኑ በቀለ
አማካዮች :- ብሩክ ማርቆስ ፣ ያሬድ ካሳዬ ፣ አማኑኤል ዮሐንስ
አጥቂ :- አቡበከር ናስር ፣ ቸርነት ጉግሳ ፣ አብዱልከሪም ወርቁ በመሆን ወደ ሜዳ ይገባሉ።
በተጨማሪም የግብፅ ብሄራዊ ቡድን አሰላለፍ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል። በጨዋታው ላይ ሞሀመድ ሳላህ የሚጫወት ይሆናል።
መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን 🇪🇹

👍40❤5🥰2🤔1😢1
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የትምህርት ሚኒስቴር እንዲዘጋ ትዕዛዝ ሊሰጡ ነው ተባለ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር እንዲዘጋ የሚያደርገውን ትዕዛዝ በፊርማቸው ሊያፀድቁ መሆኑን እየተነገረ ነው።
የትምህርት እና የሲቪክ መብት ተከራካሪዎች እንዲሁም ዴሞክራት ፓርቲን የወከሉ እንደራሴዎች ትዕዛዙ የሀገሪቱን የትምህርት ሥርዓት ለማፈራረስ ያለመ ነው ሲሉ ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ስለመሆኑም ተነግሯል።
የጥቁሮች መብት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ‘NAACP’ የተባለ ተቋም ፕሬዚዳንት ዴሪክ ጆንሰን፣ “የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በፌዴራል መንግሥት ድጎማ ላይ ጥገኛ ለሆኑ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የአሜሪካ ሕፃናት የዛሬ ቀን ጨለማ ቀን ነው” ብለዋል።
የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተር ፓቲ ሙሬይ በበኩላቸው፣ “ትራምፕ እና ኢሎን መስክ ትምህርት ሚኒስቴርን ለማፍረስ የማይሆን ጨዋታ እየተጫወቱ እና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ግማሽ የሰው ኃይል እያባረሩ ነው” ሲሉ ተችተዋል።
የሀገሪቱ ብሔራዊ የወላጆች ኅብረት ደግሞ “እየተደረገ ያለው የትምህርት ሥርዓቱን ማስተካከል ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት የሚገባቸውን ነገር እንዳያገኙ የማድረግ እንቅስቃሴ ነው፤ እኛ ግን ይህ እንዲሆን በፍፁም አንፈቅድም” ብሏል።
እንደ ሚዲያዎች ዘገባ ከሆነ ትራምፕ የሚፈርሙት ትዕዛዝ የትምህርት ሚኒስትሯ ሊንዳ ማክማሆን የትምህርት ሚኒስቴሩ እንዲዘጋ አስፈላጊውን ሒደት እዲያመቻቹ እና ሥልጣኑን ለግዛቶች አንዲያስተላልፉ ያዝዛል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የትምህርት ሚኒስቴሩን አባካኝ እና በሊበራል ርዕዮተ ዓለም የተበከለ ነው ብለው እንደሚያስቡ አልጀዚራ ዘግቧል።

👍98😁19❤5👎3
አፍሮ ስፖርት አሸናፊ ሊያደርጎት ሁሉን አሰናድቶ እየጠበቆት ነው።
ቨርችዋል ጌሞችን እንዲሁም አለም ላይ ሉ የሊግ ጨዋታዎች ፈታ እያሉ ያሸነፉ ይላል። በሁሉም የማህበራዊ ድህረገጾች ያገኙናል ።
ለማሸነፍ ወደ https://bit.ly/3XbY3o7 ይሂዱ ይመዝገቡ። በመጀመሪያ ዲፖዚቶ 50% ቦነስ ከእኛ ነው።
የ አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
Website

👍21❤7
ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዓለም 3ኛ በመሆን አጠናቀቀች
ኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት በቻይና ናንጂንግ ሲካሄድ በቆየው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዓለም 3ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን አጠናቀቀች፡፡
ሻምፒዮናው ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በውድድሩ 2 የወርቅና በ3 የብር ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችላለች፡፡
በሴቶች 3 ሺህ ሜትር አትሌት ፍረወይኒ ኃይሉ እንዲሁም በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝተዋል።
አትሌት በሪሁ አረጋዊ በወንዶች 3 ሺህ ሜትር፣ አትሌት ድርቤ ወልተጂ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር እንዲሁም አትሌት ንግስት ጌታቸው በሴቶች 800 ሜትር ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች ናቸው፡፡
በውድድሩ አሜሪካ በ6 የወርቅ፣ 4 የብር እና 6 የነሃስ ሜዳሊያዎች በድምሩ 16 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ÷ ኖርዌይ በ3 የወርቅ እና 1 የነሃስ ሜዳሊያ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 2ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

👍84❤7👏7😁1
ነዳጅ⤴️
የነዳጅ ጭማሬው አሳሳቢ ሆኗል!!!
ከትናንት ምሽት መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጨምሯል።
የዋጋ ማሻሻያው ከትናንት ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል።
"መነሻዉ መስከረም ወር 2017 ዓ/ም በተገለፀው መሠረት በየሶስት ወሩ የሚደረገዉ የዋጋ ማሻሻያ አካል ነዉ " ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ:-
ቤንዚን 112.67
ኬሮሲን 107.93p!
ነጭ ናፍጣ 107.93
ቀላል ጥቁር ናፍጣ 109.22
ከባድ ጥቁር ናፍጣ 106.75 ብር በሊትር የሚሸጥ ይሆናል።

👍60👎22❤8😭6🤔5😁4🤯3😱1
በዛሬ እለት በአዲስ አበባ ውስጥ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በቀነኒ አዱኛ ህልፈት የተጠረጠረው አርቲስት አንዱዓለም ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
ዛሬ ለችሎቱ እስካሁን የተገኘውን የምርመራ ውጤት ያቀረበው መርማሪ ፖሊስ የሟች አስከሬን ምርመራ ያሳየው ሟች ከከፍታ ቦታ ወድቃ ህይወቷ ማለፉን ነው ብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሟች ህይወቷ ካለፈበት ስፍራ የምርመራ ናሙና ተወስዶ ለፌዴራል ፖሊስ ፎሬንሲክ ምርመራ ቢሮ ተልኮ ውጤቱም እየተጠበቀ ነው ተብሏል፡፡
የተጠርጣሪው የእጅ ስልክ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት በኩል እየተመረመረ እንደሚገኝም የገለጸው ፖሊስ ይህም ውጤቱ ለዛሬ እንዳልደረሰለት ለችሎቱ በማስረዳት ተጨማሪ የምርመራ ቀናትን ጠይቋል፡፡
የአርቲስቱ ጠበቃ በፊናቸው ዛሬ የቀረበው የአስከሬን ምርመራ ውጤት እንዳሳየው ሟች ከከፍታ ወድቃ ህይወቷ ማለፉ እንጂ የፍቅረኛዋ እጅ እንዳለበት የሚጠቁም ባለመሆኑና ፖሊስ ቀሩኝ ያሏቸው ማስረጃዎች ሆስፒታል እና በደህንነት ተቋማት እጅ የሚገኙ በመሆኑ ተጠርጣሪው እነዚህን ማስረጃዎች ያጠፋቸዋል ተብሎ ስለማይጠበቅ በዋስ እንዲለቀቅ ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ግራ-ቀኙን ያደመጠው ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የቀሩትን ምርመራዎች እንዲያጠናቅቅ የተጨማሪ 12 ቀናት ጊዜን በመፍቀድ ለመጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት የዋስትና መብት ጥያቄውንም ውድቅ አድርጓል ሲል ዶቼቬለ ዘግቧል፡፡

👍43🙏6❤5🤯1