በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቋወመ።
ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፥ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚነንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የትግራይ ህዝብ ለቀጣይ አንድ ዓመት ስልጣኑ የሚራዘመውን የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመራ ፕሬዜዳንት እንዲጠቁም አስመልክቶ ያወጡትን መልዕክት " የተናጠል ውሳኔና ተግባር " ሲል ተቃውሟል።
"የፕሪቶሪያ ሥምምነት ከተፈረመ ሁለት ዓመት ተኩል ሆኖታል " ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " ስምምነቱ በሙሉነት ተተግብሮ ትግራይ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሊኖራት ይገባ ነበር" ብሏል።
"የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሙሉነት ያልተተገበረው የፌደራል መንግስት በስምምነቱ አፈፃፀምና አተገባበር በተከተለው የተሳሳተ አካሄድና ፓለቲካዊ ቀውስ እንዲፈጠር በመስራቱ ነው " ሲልም ክስ አሰምቷል።
"በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አንቀፅ 3 መሰረት ተዋዋይ ወገን ሌላውን በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ በፕሮፓጋንዳ ማጥቃት ይከለክላል ይሁን እንጂ ይህንኑ የስምምነቱ አካል በፌደራል መንግስት በተደጋጋሚ እየተጣሰ ነው " ብሏል።
" ህወሓት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ከስልጣን ማስነሳቱ ተከትሎ ፤ ጀነራል ታደሰ ወረደ ፕረዚደንት እንዲሆኑ ማእከላይ ኮሚቴ ወስኖ የኢትዮጵያ መንግስት ተቀብሎታል " ያለም ሲሆን " ይህንን ወደ ጎን በመተው በጠቅላይ ሚንስትሩ የተናጠል ውሳኔ በሚያስመስል መልኩ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚጥስ አካሄድ ተቀባይነት የለውም " ሲል ገልጿል።
" የፌደራል መንግስት ህዝብን ከሚጎዱ ግልፅ ተግባራት በመቆጠብ ዘላቂ ጥቅምና የጋራ ሰላም በሚያረጋግጡ ተግባራት እንዲያተኩር ጥሪ እናቀርባለን " ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " የተናጠል ውሳኔዎች እንዲቆሙ " ብሏል
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ

👍104😁9❤5😱3👎1🤯1
#RemedialExam
የ2017 ትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ተማሪዎች ከማዕከል የሚሰጥ ፈተና ከግንቦት 26 እስከ ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሜጄና (ዶ/ር) በቀን መጋቢት 15/2017 ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ሰርኩላር፤ የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል እንደሚሆን አስታውሰዋል፡፡
የሪሚዲያል ተማሪዎች ከዚህ በፊት 70% በማዕከል እና 30% በተቋማት የሚዘጋጁ ምዘናዎችን ይወስዱ የነበረ ሲሆን፤ ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ከ100% ከማዕከል እንዲሰጥ በጥቅምት 2017 ዓ.ም መወሰኑ ይታወሳል፡፡
በዚህም የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች በሚማሩበት ተቋም የሚሰጥ የተከታታይና የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ ይሆናል፡፡ ከዛም በማዕከል በሚሰጥ ፈተና የተማሪዎቹ መቀጠል እና አለመቀጠል የሚወሰን ይሆናል፡፡

👍51❤9😢1
በማይናማር የርዕደ መሬት አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ1 ሺህ አለፈ
ትናንት በማይናማር በተከሰተው ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር ከ1 ሺህ ማለፉ ተነገረ።
ትንናት ሀገሪቱን ክፉኛ የመታትና በሬክታር ስኬል 7 ነጥብ 7 በተለካው ርዕደ መሬት በፍርስራሽ ስር በህይወት የተረፉን የመፈለጉ ስራ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጿል።
በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰምቷል።
የሀገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የሆነችው ማንዳላይ በርዕደ መሬቱ ክፉኛ የተመታች ሲሆን ከሟቾቹ አብዛኛውን ቁጥር የያዙት የዚህች ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ለርዕደ መሬቱ መነሻ ነጥብ የቀረበችው ከተማዋ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደች ሲሆን፤ በርካታ ህንጻዎቿ ወደ ፍርስራሽነት መለወጣቸው ተጠቅሷል።
ርዕደ መሬቱ የማይናማር ጎረቤት በሆነችው ታይላንድም ጉዳት አድርሶ በግንባታ ላይ የነበረ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ጭምር ተደርመሶ 6 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

👍44😢21😭3❤2🥰2👏2
የጠየኩትን የብር መጠን በሰዓቱ አላስገቡልኝም በማለት ያገታቸውን ሁለት ታዳጊዎች የገደለው ግለሰብ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ!!
በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀር ሰለፎ ወረዳ ውስጥ የጠየኩትን የገንዘብ መጠን በሰዓቱ አላስገቡልኝም በማለት ያገታቸውን ሁለት ታዳጊዎች በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮምኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሙልጌታ ጭምዲ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደገለፁት ተከሳሽ ለታ ሁንዴ የተባለው ግለሰብ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀር ሰለፎ ወረዳ ኮሪሶ ቀበሌ አባያ በተባለው ስፍራ የ14 ዓመት ታዳጊ የሆኑትን ብሩክ ዘውዴ እና ቦጃ ጌታቸው በመግደል ክስ ተመስርቶበታል፡፡
ተከሳሹ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ብሩክ ዘውዴን አግቶ በመውሰድ ከቤተሰቦቹ 250ሺ ብር እንደጠየቀ ተናግረዋል፡፡ ልጅ የታገተባቸው ወላጅ እናትም በወቅቱ ተደናግጠው ያላቸውን ገንዘብ በማሰባሰብ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ማለትም በሁለተኛው ቀን 100ሺ ብር ልጃቸውን ላገተው ግለሰብ በተሰጣቸው አድራሻ እና ቦታ ያስረክባሉ፡፡ነገር ግን ግለሰቡ 100ሺ ብሩን ከተረከበ በሓላ ቀሪው 150ሺ ብር በወቅቱ አልተከፈለኝም በማለት የ14 ዓመቱን ታደጊ ብሩክ ዘውዴን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል አስክሬኑን ወላጆቹ እንዲረከቡ በማድረግ የጭካኔ ተግባር መፈጸሙ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡
በተመሳሳይም የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ቦጃ ጌታቸው የተባለን የ14 ዓመት ታዳጊን አግቶ በመውሰድ ወላጆቹን 250ሺ ብር እንዲልኩ ካልሆነ ግን የልጃቸውን ህይወት እንደሚያጠፋ በመዛት ከታዳጊው ወላጅ እናት ላይ 75ሺ ብር እንደተቀበለ ገልፀዋል፡፡ይሁን እንጂ ተከሳሹ 75 ሺ ብር ቢቀበልም ቀሪው 175ሺ ብር በወቅቱ አልተከፈለኝም በማለት የታገተውን የ14 ዓመት ልጅ በመግደል እና አስክሬኑን ሜዳ ላይ በመጣል ይሰወራል፡፡የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተከሳሽ ለታ ሁንዴ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ፡፡ፖሊስም በተከሳሹ ላይ የምርመራ መዝገቡን በበቂ ማስረጃ አጣርቶ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ የላከ ሲሆን አቃቤ ህግም በከባድ የሰው መግደል ወንጀል 539 እና በከባድ የውንብድና ተግባር 670 ንዑስ አንቀጽ 2 ክስ ይመሰርታል፡፡
የተመሰረተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ተከሳሽ በግድያ ፣የውንብድና ወንጀል በመፈፀም ፤ራስን የተደራጀ የወንበዴ ቡድን አባል በማድረግ በሁለት ታዳጊዎች ላይ የፈጸመው የግድያ ወንጀል ጨካኝ እና ነውረኝነቱን እንዲሁም አደገኝነቱን የሚያሣይ በመሆኑ በእድሜ ልክ እሰራት እንዲቀጣ የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

👍73👎20🤯6😢4
ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ በመታየቷ 1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ እሁድ ተከብሮ ይውላል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ እሁድ ከሚከበረው ከ1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ጋር ተያይዞ የዒድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።
ዝግ የሚሆኑት መንጋዶች የትኞቹ ናቸው ?
👉ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ በተመሳሳይ ከቦሌ አካባቢ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ፣
👉ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣
👉ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፣
👉ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ -ሳንጆሴፍ መብራት አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ፣
👉ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ቡልጋሪያ መብራት ላይ፣
👉ከቅድስት ልደታ ፀበል በAU ቅዱስ ሚካኤል መታጠፊያ ወደ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ AU ሚካኤል መታጠፊያ፣
👉ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ፣
👉ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት ፈረሰኛ መብራት ላይ፣
👉ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ፣
👉ከመርካቶ አካባቢ በአቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ አቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ላይ
👉ከፒያሳ በባንኮዲሮማ መብራት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ባንኮዲሮማ መብራት ላይ፣
👉ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ሴቶች አደባባይ ላይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።
አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ከበዓሉ ዋዜማ ምሽት ጀምሮ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሠዓት ማቆም የተከለከለ ነው ተብሏል።

👍47😭12❤6😁4👎1
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ምስጋና አቀረበ
**
በመላ ሀገሪቱ የተከበረው 1446 ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገልጿል።
ለዚህም በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል::
መላው የሀገራችን ሕዝብ እና መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይም ለሀይማኖት አባቶች፣ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎች እና ወጣቶች ምስጋናውን አቅርቧል:: እንዲሁም ከበዓሉ ዋዜማ ጀምረው የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡ የፀጥታ ኃይሎችም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

👍43👎16❤4👏4😁2😱2🤔1🤯1
ዐቃቢ ህጎችን ጨምሮ ለሌሎች ሰራተኞች ከፍተኛ የተባለው የደመወዝ ጭማሪ ተደረገ
የፍትህ ሚኒስቴር ከጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሰራተኞቹ የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።
ይህ ማሻሻያ የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል።
በተለይም ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ረዳት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ምክትል ረዳት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ምክትል ረዳት ጠቅላይ ዐቃቤሕግ 35% የደመወዝ ጭማሪ፣ 24,000 ብር የመኖሪያ ቤት አበል እና 11,000 ብር የትራንስፖርት አበል ተደርጓል።
በተጨማሪም ለከፍተኛ ዐቃቤ ህግ እና ዐቃቤ ህግ ደረጃ 1፣ 2 እና 3 የደመወዝ ጭማሪ እና የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ተደርገዋል።
ቅዳሜ ገበያ ከሰራተኞቹ እንደሰማችሁ ዐ/ህጎች በደመወዝ ማነስ ምክንያት በከፍተኛ መጠን እየለቀቁ ነበር። የሰራተኛ ፍልሰቱን ትንሽም ቢሆን ሊያስታግሰው ይችላል። ከነበረው ደመወዝ እና ከፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች አንፃር ግን የተሻለ ጭማሪ ነው ብለዋል።

👍55🤔16❤8👏3👎1😱1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ዕጩ መልማይ ኮሚቴን ሰየሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ዕጩ መልማይ ኮሚቴን ሰየሙ፡፡
ኮሚቴው በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 133/2011 አንቀጽ 5(1) መሠረት ነው ከመጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተሰየመው፡፡
በዚህ መሰረትም፡-
1. ቀሲስ ታጋይ ታደለ - ሰብሳቢ
2. ፕ/ር ተከተል ዮሐንስ - አባል
3. አቶ ባዬ በዛብህ - አባል
4. ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ - አባል
5. አቶ ካሳሁን ፎሎ - አባል
6. ወ/ሮ እርግበ ገ/ሐዋሪያት - አባል
7. ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቴ - አባል
8. ሰብስብ አባፍራ አባጆብር - አባል

👍43🤔14👎7❤3🥰2