Telegram Web Link
ጆዜ ሞሪኒሆ ተቀጡ

በቱርክ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ከጋላታሳራይ በነበራቸው ጨዋታ ያልተገባ ድርጊት የፈጸሙት አሰልጣኙ የ3 ጨዋታ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ፌነርባቼ 2 ለ 1 በተሸነፈበት ጨዋታ ፖርቹጋላዊው ጆዜ ሞሪኒሆ የጋላታሳራይ አሰልጣኝ የሆነውን ኦካን ቡሩክ አፍንጫ ይዘው በመጎተታቸው ነው ቅጣቱ የተጣለባቸው።

የቀድሞው የቼልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ በተጨማሪም የ5 ሺህ 955 ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ሁሌም ብጥብጥ በማያጣው የኢስታምቡል ደርቢ ፌነርባቼ 2 ለ 1 ተሸንፎ ከውድድር መሰናበቱ የሚታወስ ነው::

በዚህ ጨዋታ ላይ ሁለት የጋላታሳራይ እና አንድ የፌነርባቼ ተጫዋች ቀይ ካርድ መመልከታቸውም አይዘነጋም።
በአዲሱ የአፍሮስፖርት አቪዬተር ጨዋታ ይዝናኑ!

የትልልቅ ገንዘብ እሸናፊዎች ይሁኑ!

ለመጫወት ይህን ሊንክ 👉👉https://bit.ly/3M9qBIw ሊንክ ይጫኑ።

ማህበራዊ ገፃችንን Follow በማድረግ የተለያዩ Giveaways ያሸንፉ👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
አብን ዶ/ር በለጠ ሞላን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ ሰየመ
***

የአማ
ራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን በድምቀት በማካሄድ፤ ዶ/ር በለጠ ሞላን የፓርቲው ሊቀመንበር፣ አቶ መልካሙ ጸጋዬን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ሰይሟል።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ ዛሬ መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ 3ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን፤ ጉባኤውን በድምቀት በመጸፈም ልዩ ልዩ ውሳኔወችን አሳልፏል።

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ ድርጅቱ ከምስረታው ጀምሮ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች፣ የተደረጉ ትግሎችን እና የተገኙ ድሎችን አውስተዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
#NewsAlert‼️

ትላንት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ “ጎሃ ፅዮን” እና “ቱሉ ሚልኪ” መካከል ታጣቂዎች አንድ ሙሉ ተሽከርካሪ ተሳፋሪዎችን መገታቸው ከዛም ውስጥ በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ!።

የሹፌሮችን ውሎ የሚከታተለው ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር በበኩሉ፣ በታጣቂዎች ታገቱ ከተባሉት ተሳፋሪዎች መካከል በርካቶች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን ከስፍራው መረጃ እንደደረሰው ገልጿል።

ከተገዱሉት ተሳፋሪዎች ባሻገር ታፍነው የተወሰዱ እንዳሉም ያመለከተ ሲሆን፣ እገታው የተጸመው ትላንት (ቅዳሜ መጋቢት 27 ቀን 2027 ዓ/ም) መሆኑን ተናግሯል።

አንድ የሟች የቅርብ ቤተሰብ በሰጡት ቃል፣ አንድ የልጆች አባት እንደተገደሉ፣ ነገ የቀብር ሥርዓታቸው ይፈጸማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸው፣ “ የሟች ቤተሰብ አስከሬን ለማምጣት ሄደዋል ” ብለዋል።

ሌላኛው የሌላ ሟች ጓደኛ በበኩላቸው፣ ሹፌሩን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ተሳፋሪዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ፣ የሟቾቹን አስክሬን ወደ ትውልድ ቦታቸው ለማምጣት የሟች ቤተሰቦች ዛሬ ወደ እገታ ቦታው እንደሄዱ ተናግረዋል።

የሟቾች ወላጆች የሟቾቹን አስክሬን ገና ሊቀበሉ በመሆኑ፣ ሀዘናቸውም ስለበረታ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት የሚያስችል መረጋጋት ላይ አለመሆናቸው ተመልክቷል።


ስለእገታው ከመንግስት እስካሁን በግልጽ የተባለ ነገር ባይኖርም፣ በእገታው ቦታ የፌደራል ፓሊስ ደርሶ እንደነበር በማኀበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተስተውሏል።

የትላንቱ እገታ በተፈጸመበት አካባቢ ከ19 ቀናት በፊት ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ በርካታ ተሳፋሪዎች ይዞ ሲጓዝ የነበረ " ፈለገ ግዮን " ባስ ታጣቂዎች አስቁመውት ሙሉ ተሳፋሪዎች መታገታቸውን የአይን እማኝ ሹፌሮች አሳውቀው ነበር ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

  T.me/ethio_mereja
ይህ የኢትዮጵያውያን ህክምና ባለሙያወች ጥያቄ ነው?!

የአፍሪካ ዝቅተኛዋ ደሞዝ ከፋይ ሀገር

👉Specialist ሀኪም ወርሀዊ 120ዶላር
👉አጠቃላይ ሀኪም 84ዶላር
👉ነርስ 70ዶላር ወርሀዊ ክፍያ ምትከፍል ብቸኛ ሀገር ናት

ራሱን ለtb, hepatitis virus,hiv እና ሌሎች መሰል በሽታወች አጋልጦ ሚሰራው ሀኪም የጤና insurance የለውም ..........በትንሽ ክፍያ ሚሰራው የጤና ባለሙያ ለዚህ ሁሉ በሽታ ተጋልጦ እየሰራ ያለ insurance እየሰራ የጤና መድህን እንኳን ተጠቃሚ እንዲሆን አይፈቀድለትም?

ህይወታችንን ሲያድኑ ኖረዋል አሁን ግን
ህይወታቸውን ልናድን ይገባል!!!

ሁላችንም ድምፃችንን እናሰማ!

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
በዝነኛው የአፍሮ ስፖርት አቭያተር ይብረሩና እስከ 1,000,000 ብር ያሸንፉ! 

ምን ይጠብቃሉ አሁኑኑ https://bit.ly/3M9qBIw ይግቡና እድሎን ይሞክሩ!

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
#Amhara

በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ  ጦርነት ምክንያት የንግድ ስራዉ መቀዛቀዙ ተገለፀ።

ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ የመንገድ መዘጋት ዝርፊያና የማህበረሰቡ የመሸመት አቅም ዉስንነት ነጋዴዎችን ከንግድ ስራ እያስወጣ መሆኑም ተነግሯል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በበኩላቸዉ አሁን በአማራ ክልል ያለዉ የንግድ መቀዛቀዝ በአጠቃላይ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተፅኖ ይኖረዋል ብለዋል።

ሁለት ዓመት ሊሞላዉ የተቃረበዉ በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘዉ ጦርነት በክልሉ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅኖ እንደፈጠረ በአምራች በአከፋፋይና በችርቻሮ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች ይናገራሉ። «የሆነ ሰዉ ሲያልፍ ከኔ ገባ ከኔ ገባ እያልን ነዉ አሁን የምንሰራዉ ገብቶሀል በቀን አንድ ሰዉ ሁለት ሰዉ ከገባ በጣም ነዉ የምናመሰግነዉ ከዚያ ዉጭ እጂ ሳንፈታ የምንገባበት ጊዜ ነዉ አሁን><በቀን ሁለት መኪና ሦስት መኪና ልንሸጥ እንችላለን አሁን ግን ከጦርነቱ በኃላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም የሚታሰበዉ ወጭ እንጂ ገቢ እንኳን ያን ያክል ነዉ የሚገዛም የለም» 

በክልሉ ያለዉ ግጭት በንግዱ ዘርፍ ላይ ያሳደረዉ ተፅኖ በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንዲኖር አድርጓል የሚሉት አስተያየት ሰጭዎች በበኩላቸዉ፤ «< እኛ አሁን አዕምሯችንን  ያሳመነዉ በቃ ጦርነት አለ ብለን እራሳችንን ስላሳመነዉ ነዉ እንጂ በጣም የሞተ ሽያጭ ነዉ እየሸጥን ያለነዉ»

አሁን በአማራ ክልል ካለዉ ግጭት  ጋር ተያይዞ ምርት በሚፈለገዉ መጠንና ቦታ እየደረሰ አይደለም የሚሉት አስተያየታቸውን ለዶቼቬለ የሰጡ የንግድ ፈጣሪዎች በየቦታዉ ያለዉ ተደጋጋሚ ቀረጥ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

  T.me/ethio_mereja
 
አፍሮ ስፖርት ላይ ከተመዘገቡ እና ተጫዋች ከሆኑ በኋላ ጓደኛዋን ሲጋብዙ ከእኛ ሽልማት ያገኛሉ።

በእርሶ ሪፈራል ሊንክ ጓደኛዎ ገብቶ መጫወት ሲጀምር ለእርሶ ደግሞ ሽልማት ከአፍሮ ስፖርት ያገኛሉ እና ምን ይጠብቃሉ ይጫወቱ ይጋብዙ ይሸለሙ።

ወደ 👉https://bit.ly/3XbY3o7 ይሂዱና ይመዝገቡ ከዛም ጓደኛዎን ይጋብዙ።

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
Website
ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ተረከቡ
*****

"ባለፈው አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት፣ የፕሪቶርያን ስምምነት እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን ምክር በማከል ሰፊ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል። የአቶ ጌታቸው የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ የሚቀሩ ቁልፍ ሥራዎችን የሚያከናውን አካል፣ ግዝያዊ መንግሥቱ መቀጠል አለበት የሚል ድምዳሜ ከተያዘ በኋላ፣ ይሄንን ሽግግር ማን መርቶ ከግብ ሊያደርስ ይችላል? የሚሉ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል።

ዛሬ በይፋ እና በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩን እና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል። ጄኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሰው ናችው። ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችን እና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸው። አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደ ፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምነት በብዙ አካላት የታመነ ነው። የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላም እና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
💰አሸናፊ እንዲያረጋችሁ የተዘጋጁ ምርጥ ኦዶች። 💰

አፍሮስፖርት በፈለጉት ሰዓት እና ቦታ ስልኮንን እና ኢንተርኔት በመጠቀም። ከፈለጉ ቀጥታ እየተካሄዱ ባሉ ውድድሮች ላይ እንዲሁም ጌሞች ላይ በመጫወት አሸናፊ ይሁኑ።

ወደ 👉 https://bit.ly/3XbY3o7
ይሂዱ ይመዝገቡ፣ ይጫወቱ እናም ያሸንፉ።

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
Website
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በይፋ ሥራ ጀመሩ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በይፋ ሥራቸውን ጀምረዋል፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ስብሰባ በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን÷ ሌ/ጀነራል ታደሰ በቀጣይ ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ በቀጣይ የክልሉን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑም ተገልጿል፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትራቸው አድርገው ሾመዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ህወሓት “ተቋማዊ ነጻነቴን ጠብቄ፣ ከጊዜያዊ አሰተዳደሩ ጋር ተደጋግፌ በጋራ እሰራለሁ” ሲል ገለጸ
 
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ተልዕኮዎቹን ለማስፈጸም በሚያደርገው እንቅስቃሴ ህወሓት እንደ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል በመሆን ተቋማዊ ነጻነቱን ጠብቆ ተደጋግፎ በጋራ ይሰራል ሲሉ ሊቀመንበሩ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ገለጹ።

ከፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ጋር “ተባብረን እና ተደጋግፈን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ተልዕኮዎችን በአጭር ጊዜ ለማሳካት ያለንን ዝግጁነት መግለጽ እንወዳለን” ሲሉ ሊቀመንበሩ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት በመሆን ስራ ለጀመሩት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ትላንት ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ባዘጋጀው መድረክ ባደረጉት የመልካም ስራ ምኞት ንግግር አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በበኩላቸው” ካለፉት ድክመቶቻችን ተምረን መደጋገፍ እና መተባበር ለቀጣይ ጉዟችን ወሳኝ ነው ሲሉ ገልጸዋል፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሚቀጥለው አንድ አመት የስራ ጊዜው ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት በየሶስት ወሩ ተከፋፍሎ የሚፈጸም የስራ መርሃ ግብር በማውጣት ይሰራል ብለዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰጠ ማሳሰቢያ


4ኪሎ ቤተ መንግስት ዙሪያ ባለ ሁለት ከቅጣጫ የነበረው መንገድ ባለአንድ አቅጣጫ እንዲሆን መደረጉን ባለማወቅ አንዳንድ አሽከርካሪዎች አሁንም ለደምብ መተላለፍ ቅጣት እየተዳረጉ ስለሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ።

4ኪሎ ቤተ መንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች አንድ አቅጣጫ ብቻ ሆነው እንዲያገለግሉ መደረጋቸው ቢታወቅም፤ ነገር ግን አንዳንድ አሽከርካሪዎች አሁንም የተተከሉ የመንገድ ትራፊክ ምልክቶችን እየጣሱና ለቅጣት እየተዳረጉ መሆናቸውን ፖሊስ ገልጿል። 
               
መረጃው ቀደም ሲል ለአሽከርካሪዎች በተለያዩ ሚዲያዎች የተገለፀ ቢሆንም አሁንም አንዳንዶች ክልከላውን እየተገበሩት ባለመሆኑ መረጃውን ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ፖሊስ ጠቅሷል፡፡

በዚህም መሠረት፦

👉 ከጥይት ቤት መስቀለኛ እስከ ፓርላማ ትራፊክ መብራት ድረስ፣

👉 ከፓርላማ ትራፊክ መብራት እስከ ቅዱስ ገብርኤል (ሳይንስ ሙዚየም) ድረስ እንዲሁም

👉 ከቅዱስ ገብርኤል መስቀለኛ እስከ ጥይት ቤት ድረስ ቀድሞ የነበረው ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድ (Two way) ወደ አንድ አቅጣጫ መንገድ (One way) የተቀየሩ መሆናቸውን አሽከርካሪዎች አውቀው የትራፊክ ምልክትና ማመልከቻዎችን በጥንቃቄ እያከበሩ እንዲያሽከረክሩ፤ እንዲሁም በአካባቢው የተመደቡትን የትራፊክ ፖሊስ አባላትን መረጃ ጠይቀው በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
2025/07/06 11:45:13
Back to Top
HTML Embed Code: