Telegram Web Link
#የእርዳታ_ጥሪ

ለውድ የኢትዮ-መረጃ ቤተሰቦች

ቀና ልብ ላላችሁ ወገኖች በሙሉ  የወንድማችንን ነፍስ ከሞት እንታደግ🙏🙏

ይህ ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወጣት ኤርምያስ ፍቅሬ ይባላል።

ተወልዶ ያደገዉም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣በሀድያ ዞን፣በፎንቆ ከተማ ስሆን፤ #ከልጅነቱም ጀምሮ ትሁትበስነ-ምግባሩ የታነፀበትምህርቱም ጎበዝና ለሌሎችም እንደ አራአያ የምታይ ወጣት ነዉ።

የ2ተኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት አጠናቆ በ2009ዓ.ም ወደ #ሀዋሳ_ዩንቨርስቲ በመግባት በቴክስታይል ኢንጅነርንግ(Textile Engineering) ት/ት ክፍል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ተመርቆ በሀዋሳ እንደስትርያል ፓርክ ውስጥ እየሰራ ባለበት ወቅት ድንገት ባጋጠመዉ የኩላሊት ህመም ምክንያት ስራውን አቋርጦ ህክምናዉን እየተከታተለ እያለ ህመሙ ብሶበት ሁለቱም ኩላሊቶቹ መስራት ስላቁመ ዶክተሮቹ በአፋጣኝ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዲደረግ ወስነዋል።

እናም ወደ ውጭ ሀገር ወስደን ለማሳከም የተጠየቅነዉ ብር ከአቅማችን በላይ በመሆኑ እናንተ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭም የምትኖሩ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እጃችሁን በመዘርጋት ወይም በምትችሉት ነገር ሁሉ ከጎናችን በመሆን ይህንን ወጣት ህይወት እንድትታደጉ ስንል እንማፀናለን🙏🙏

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:-1000268155938
በአዋሽ ባንክ:- 013201523182800
ERMIAS FIKRE MESSELE

ለመደወልና ኤርምያስን ለማናገር ለምትፈልጉ
📞 0941414057
📞0920992184 ወይም
📞0939580869

የተቻላችሁን ብትረዱንና የወንድማችንን ህይወት በማትረፍ ትተባበሩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏

ለምታደርጉልን ማንኛውም ቀና ትብብር እናመሰግናለን ፈጣሪ ጨምሮ ይስጥልን።

👉 👉 @Go_Fund1
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ ንዋያተ ቅዱሳት የሆኑትን ፦
👉ከበሮ፣
👉ጸናጽል፣
👉መቋሚያና እንዲሁም ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች መመዝገባቸውን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዜማ ንዋያተ ቅዱሳቱ እና ቅዱሳት መጻሕፍቱ ተመዝግበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆናቸው ከባለሥጣኑ በወጣው ደብዳቤ መረጋገጡን ገልጻለች። መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
አርሰናል በድምር ውጤት ሪያል ማድሪድን 5 ለ 1 አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፏል።

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ በሳንቲያጎ ቤርናባኦ አርሰናልን ያስተናገደው የውድድሩ ባለ ሪከርድ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ በአርሰናል በድምር ውጤት 5 ለ1 ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል።

የአርቴታው ቡድን በብዙ ተጠብቆ የነበረውን ጨዋታ በድል በመወጣት ታላቅ ታሪክ ፅፏል። በቤርናባኦ 2 ለ 1 በተጠናቀቀው ጨዋታ ቡካዩ ሳካ እና ማርቲኔሊ ለአርሰናል፣ ቪኒሽየስ ጁንየር ለማድሪድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በሌላ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ባየር ሙኒክን በድምር ውጤት 4 ለ 3 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ታይም መጽሔት ኢትዮጵያዊውን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም የ2025 የ የአለማችን 100 ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ዝርዝር መካከል አካተተ

የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር #ቴዎድሮስ አድሓኖም የ2025 የታይም መጽሔት የአለማችን 100 ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ተገለጸ።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም ይህንን አስመልክተው በማህበራዊ የትስስር ገጾቻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “ በዝርዝሩ ውስጥ መካተቴ ጤና ለሁሉም የሚለውን አላማ ለማሳካት ቀን ከሌት በከተማ፣ በገጠር እንዲሁም ግጭቶች በሚካሄድባቸው አከባቢዎች ስራቸውን ለሚሰሩ የሞያ አጋሮቼ እውቅና የሚሰጥ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ዓለም አቀፉን የጤና ገጽታ የቀየረ፣ ባለራዕይ በሪ፣ በሳይንስ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት ያላሰለሰ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሉ በመጽሄቱ ላይ ስለ ዶ/ር ቴዎድሮስ ምስክርነታቸውን ያሰፈሩት እና ፈንጣጣ ከአለማችን እንዲጠፋ ከፍተኛ አበርክቶ ያደረጉት ኢፒዲሞሎጂስቱ ፕሮፌሰር ላሪ ብሪሊያንት ገልጸዋቸዋል።

#የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ፣ ኤሎን መስክ፣ #የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስትር ኬር ስታርመርን በመፅሔቲ የአመቱ 100 ተጽእኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት መካከል ይገኙበታል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
የጸሎተ ሐሙስ ሥነ-ሥርዓተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል‼️

ጸሎተ ሀሙስ ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ የሓዋርያቱን እግር ያጠበበት እና ትሕትናን ያስተማረበት ዕለት ነው።

በሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቀሳውስትና ምዕመናን ተገኝተዋል። የእምነቱ ተከታዮች ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ ለሓዋርያቱ ያሳየውን ትሕትና በሕይወታቸው ሊገልጡት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
የአሜሪካ የአየር ድብደባ በየመን 74 ሰዎችን ገደለ፣ 171 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል

በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ የሚገኘው የአማጽያኑ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሟቾች ቁጥር እንዳመለከተው የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ሲያቃጥልና የእሳት ኳሶችን ወደ ሌሊቱ ሰማይ ሲልክ በነበረው የሌሊት ጥቃት የደረሰውን ውድመት ያሳያል።

ይህ ጥቃት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከመጋቢት 23 ጀምሮ በጀመሩት የአሜሪካ የአየር ድብደባ ዘመቻ ውስጥ እስካሁን በከፍተኛ ደረጃ የብዙ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ጥቃት ነው።

የአሜሪካ ወታደራዊ ማዕከላዊ ትዕዛዝ ስለ ንፁሀን ሰዎች ጉዳት ሲጠየቅ ምንም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። (AP)
2025/07/05 22:00:27
Back to Top
HTML Embed Code: