Telegram Web Link
#የእርዳታ_ጥሪ

ቀና ልብ ላላችሁ ወገኖች በሙሉ  የወንድማችንን ነፍስ ከሞት እንታደግ🙏🙏

ይህ ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወጣት ኤርምያስ ፍቅሬ ይባላል።

ተወልዶ ያደገዉም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በሀድያ ዞን፣ በፎንቆ ከተማ ስሆን፤ #ከልጅነቱም ጀምሮ ትሁትበስነ-ምግባሩ የታነፀበትምህርቱም ጎበዝና ለሌሎችም እንደ አራአያ የምታይ ወጣት ነዉ።

   የ2ተኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት አጠናቆ በ2009ዓ.ም ወደ #ሀዋሳ_ዩንቨርስቲ በመግባት በቴክስታይል ኢንጅነርንግ(Textile Engineering) ት/ት ክፍል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ተመርቆ በሀዋሳ እንደስትርያል ፓርክ ውስጥ እየሰራ ባለበት ወቅት ድንገት ባጋጠመዉ የኩላሊት ህመም ምክንያት ስራውን አቋርጦ ህክምናዉን እየተከታተለ እያለ ህመሙ ብሶበት ሁለቱም ኩላሊቶቹ መስራት ስላቁመ ዶክተሮቹ በአፋጣኝ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዲደረግ ወስነዋል።

እናም ወደ ውጭ ሀገር ወስደን ለማሳከም የተጠየቅነዉ ብር ከአቅማችን በላይ በመሆኑ እናንተ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭም የምትኖሩ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እጃችሁን በመዘርጋት ወይም በምትችሉት ነገር ሁሉ ከጎናችን በመሆን ይህንን ወጣት ህይወት እንድትታደጉ ስንል እንማፀናለን🙏🙏


ወንድማችን ኤርሚያስ ፍቅሬ በምርመራ 2 ኩላሊቴ Fail እንዳደረገ የተነገረው ሲሆን አሁን እየኖረ ያለው በየወሩ 60,000 ብር በሚጠይቀው የዳያሊስስ ድጋፍ ነው። ከዚህም በላይ የኩላሊት ንቅለ ተከላ በውጭ አገር እንዲሰራ ተናግሮታል ለህክምናውም ወደ 3.5 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ለ3ሰው የአየር ቲኬት፣ ለ2 ወር መቆያ እና ተያያዥ ወጪዎች 1.5ሚሊየን አከባቢ በአጠቃላይ ወደ 5 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል። ይህ ከሱ እና ከቤተሰቡ አቅም በላይ ስለሆነ እና የሁላችንም ድጋፍ ይሻል።

ለድጋፍ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:-1000268155938
በአዋሽ ባንክ:- 013201523182800
ERMIAS FIKRE MESSELE

ለመደወልና ኤርምያስን ለማናገር ለምትፈልጉ
📞 0941414057
📞0920992184 ወይም
📞0939580869

የተቻላችሁን ብትረዱንና የወንድማችንን ህይወት በማትረፍ ትተባበሩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏 ለምታደርጉልን ማንኛውም ቀና ትብብር እናመሰግናለን ፈጣሪ ጨምሮ ይስጥልን።

እሱን ለማገዝ በተዘጋጀው ግሩፕ ይቀላቀሉ
     👉 T.me/Go_Fund1
ቻይንኛ ቋንቋ ኮርሶች ምዝገባ ጀምረናል!

Registration Now Open for Chinese Language Course!

🇨🇳 Beginner Level (HSK 1-2)
🇨🇳 Intermediate Level (HSK 3-4)
🇨🇳 Advanced Level (HSK 5-6)

Interactive, immersive learning

Small class sizes for personalized attention

Online and in-person options available

Spots are limited—register now and take the next step in your Chinese language journey!

0988747878 / 0799331774

ለበለጠ መረጃ : @merahyan
#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251966244248
     +251984000520
WhatsApp. https://wa.me/251966244248
Telegram :@TemerRealEstateConsultant
በትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ🕯

በምዕራብ አርሲ ዞን ኔጌሌ አርሲ ወረዳ ራፉ ሃርጊሳ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ህይዎት ሲያልፍ በ22 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አካል ጉዳት ደረሰ፡፡

አደጋው የደረሰው፤ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ተሳቢ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በማጋጨቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አደጋውን ተከትሎም ከሟቾች በተጫመሪ በ16 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ6 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኔጌሌ አርሲ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ቋንቋ ስልጠና በመራህያን
የምንሰጣቸው የቋንቋ ስልጠናዎች ፦
ቻይንኛ 🇨🇳
እንግሊዘኛ 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿
ጀርመንኛ🇩🇪
አረብኛ 🇸🇦
ፈረንሳይኛ🇫🇷

•Online or Inperson

ለመመዝገብ:
       ☎️
0989747878
0799331774

አድራሻ፦ 22 ከ ጎላጉል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan
ቻይና በባሕር ላይ ማረፍ እና መነሳት ለሚችለው አውሮፕላን የገበያ ፈቃድ ሰጠች

በባሕር ላይ ማረፍ እና መነሳት የሚችለውየቻይናው AG600 አምፊቢየስ አውሮፕላን በሀገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር የገበያ ፍቃድ ሰርተፊኬት በይፋ ተሰጥቶታል።

‘የውሃ ድራጎን’ የሚል ስያሜ የተሰጠው አውሮፕላኑ ግዝፈቱ እና ክብደቱ የዓለማችን ትልቁ አምፊቢየስ አውሮፕላን እንዲሆን አስችሎታል፡፡

AG600 አምፊቢየስ አውሮፕላን በውኃ እና በመሬት ላይ ማረፍ እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው።

አንድ ጊዜ በተሞላ ነዳጅ 4 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር የመሸፈን አቅም ያለው ይህ አውሮፕላን፣ ከባድ እሳት አደጋን ለማጥፋት፣ የባሕር ላይ ፍለጋ ለማካሄድ እና ለነብስ አድን ተልዕኮዎች እንደሚውል ተጠቁሟል።

አውሮፕላኑ 12 ቶን ውኃ እና 50 ሰዎችን የመጫን አቅምን እንዳለውም ተጠቅሷል። ይህ የአውሮፕላን ስሪት ቻይና በአቪዬሽን ኢንደስትሪ የበላይነት እንድትቀዳጅ ከማስቻሉ ባሻገር፣ ለሚከሰቱ አደጋዎች ፈጣን እና አመርቂ እርምጃ ለመውሰድ የሚስችላት ነው ሲል ሲጂቲኤን በዘገባው አመላክቷል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
" ሚስቱን ገድሎ ሊሰወር የሞከረዉ ግለሰብ በፖሊስና በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል " - የጋሞ ዞን ፖሊስ

በአርባ ምንጭ ከተማ ባለቤቱ ገድሎ ሊሰወር የነበረ ግለሰብ መያዙን ፖሊስ ገልጿል።

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ሬታ ተክሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ አርባ ምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ ግድብ ሠፈር ነው።

ኮማንደር ሬታ ፤ የገዛ ባለቤቱን በመሳሪያ ተኩሶ በመግደል ሊሰወር የሞከረዉ ተጠርጣሪ በሕዝቡና በፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።

ተጠርጣሪው አቶ ነብዩ ጌታቸው ኤፍሬም እንደሚባልና ከሟች ጋር በትዳር ዓለም አብረዉ እንደነበሩ በመካከላቸዉ በነበረው አለመግባባት ሟች ወላጆቿ ጋር በመሄድ ላለፉት 5 ወራት ከቤተሰቦቿ ጋር ትኖር እንደነበር ገልፀዋል።

በትናትናዉ ዕለት ተጠሪጣርዉ አስቦና አቅዶ ጧት 4 ሰዓት ገደማ " ላናግርሽ እፈልጋለሁ " በማለት ካስጠራት በኋላ ሰዉ የማያይበትን ሁኔታ በማመቻቸት በሽጉጥ አንገቷ ስር ደቅኖ ተኩሶ እንደ ገደላት አስረድተዋል።

በኃላም ለመሸሸግና ለመሰወር ሲሞክር በፖሊስ ክትትልና በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዉና ሟች በትዳር አብረዉ በነበሩበት ወቅት አንድ ልጅ አፍርተዉ እንደነበርም የፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

ተጠርጣሪዉ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመበትን ሽጉጥ ወንዝ ዉስጥ እንደጣለ ቢገልፅም ፖሊስ ባደረገዉ ማጣራት ከደበቀበት በኤግዚቢትነት ይዞታል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
2025/07/05 04:47:15
Back to Top
HTML Embed Code: