Telegram Web Link
የአትሌት ገለቴ ቡርቃ የቀድሞ ባለቤት አቶ ታደለ ገብረመድህን በቁጥጥር ስር ዋለ !

አትሌት ገለቴ ቡርቃ "ዘርፎኛል "በሚል በሚዲያ የከሰሰችው  እና ብዙዎችን  ያሳዘነው የአትሌቷ ህይወት  በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ፖሊስ  የቀድሞው ባለቤቷ ታደለ ገብረመድህን  በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
አዲሱ የትራንስፖርት ግብር አከፋፈል የዘርፉን አሰራር ያላገናዘበ በመሆኑ ወደነበረበት እንዲመለስ ተጠየቀ

የትራንስፖርት ዘርፉ የግብር አከፋፈል ቀድሞ ከነበረበት የቁርጥ ክፍያ ተቀይሮ ገቢን መሠረት ባደረገ ተመን እንዲቀየር መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፤ ይህም አከፋፈል የዘርፉን አሰራር ያላገናዘበ በመሆኑ ወደነበረበት እንዲመለስ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ጠይቋል፡፡

አዲሱ አካሔድ የትራንስፖርት ዘርፉን አሰራር ያላገዘበ ከመሆኑ በተጨማሪ፤ "ግብር ሰብሳቢው ተቋም ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዳያገኝ የሚያደርግ በመሆኑ ወደነበረበት የቁርጥ ክፍያ ሊመለስ ይገባል" ሲልም ነው ፌዴሬሽኑ የጠየቀው፡፡

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወርቅዓለማው ንጋቱ ለአሐዱ እንደገለጹት አዲሱ የትራንስፖርት ግብር አከፋፈል በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ደረሰኝ የማይቀርብባቸው በርካታ ክፍያዎች ስላሉ የአሰራር ክፍተት ይፈጥራል፡፡

"አሰራሩ ግብር ከፋዮች ተገቢውን ግብር እንዳይከፍሉ ያደርጋል" ያሉት ኃላፊው፤ "በየቦታው ከሚገኙ ኬላዎች ክፍያ ጀምሮ፣ የማደሪያ ቦታዎችና በገቢዎች ተቀባይነት የማይኖራቸው ጥቃቅን ክፍያዎች፣ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ካለው አለመረጋጋት እና ግጭት ጋር ሲደመር ደረሰኝ ለመስጠት የማይመቹ ናቸው" ብለዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ዘርፉ በሀገራዊ ሎጅስቲክስና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ ሚና ያለው እንደመሆኑ ያልተገባ የገንዘብና አስተዳደራዊ ሸክሞች ሳይኖሩበት፣ ተገቢውን የመንግሥት ግብር በአግባቡ እየከፈለ እንዲቀጥል መንግሥት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቋል፡፡
ሙሉጌታ ከበደ ህይወቱ አለፈ!

ዝነኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋች የነበረው ሙሉጌታ ከበደ ዛሬ ህይወት አለፈ።

በቤተዛታ ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል የነበረው ሙሉጌታ ባለፏት ወራቶች የጤና እክል አጋጥሞት ነበር።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ETHIO-MEREJA®
Photo
#የሙሉጌታ ከበደ  የሽኝት መርሀግብር !!

የሙሉጌታ ከበደ የሽኝት ፕሮግራም ነገ ሰኔ  5 ቀን 2017 ዓ.ም  2:30  ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን በመቀጠልም  ከቀኑ በ7:00 ሰዓት የቀብር ስነስርዓቱ  ኮልፊ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር  ይፈፀማል ።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ድንቅ አጥቂ የነበረው ሙሉጌታ ከበደ (ወሎዬው) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል
=============||===========
በ1959 ዓ.ም በደሴ ከተማ ይህችን ምድር በመቀላቀል ሃገራችን ካፈራቻቸው የአጥቂ መስመር ተጫዋቾች በቀዳሚነት ስፍራ የተፈረጀ ስለመሆኑ ብዙ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ይስማማሉ፡፡ ወላጆቹ ባወጡለት ስም ሙሉጌታ ከበደ ሲባል በኳስ ክህሎቱ ግን የበርካታ ስያሜ ባለቤት ለመሆን ችሏል፡፡

እግር ኳስ መጫወት የጀመረው በትውልድ ሰፈሩ ገና በልጅነት እድሜው ሲሆን በአካባቢው ለሚገኙ የሰፈር ቡድኖች በመጫወት የድንቅ ክህሎት ባለቤት መሆኑን አስመስክሯል፡፡ በክለብ ደረጃ ከ1974 ዓ.ም እስከ 1976 ዓ.ም ለወሎው ፔፕሲ ክለብ ከመጫወቱ በላይ በፔፕሲ ውስጥ ባደረገው ምርጥ እንቅስቃሴም የሃገራችን ታላቅ ክለብ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስን የመቀላቀል እድሉን አገኘ፡፡ በ1976 ዓ.ም ክረምት ላይ ፈረሰኞቹን ሲቀላቀል ቋሚ የስራ ዕድል ለማግኘት ከመቻሉ በተጨማሪ በጊዜው ለተጫዋቾች ይከፈል የነበረውን የደሞዝ ክብረወሰን ለመስበር ችሏል፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ከ1977 ዓ.ም እስከ 1989 ዓ.ም ተጫውቶ ማሳለፍ የቻለው ሙልጌታ ከቡድኑ ጋር በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ሰባት፣በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አንድ፣በአሸናፊዎች አሸናፊ ስድስት በጥቅሉ 14 ዋንጫዎችን ከቡድኑ ጋር በክብር አንስቷል፡፡ ከነዚህ ድሎች በተጨማሪ ሙልጌታ በግሉ የተለያዩ ስኬቶችን ለማግኘት ችሏል፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታው ክለቡን ለድል ለማብቃት የበኩሉን አስተዋፅዖ ከማድረጉበላይ በግሉ በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ በኮከብ ተጫዋችነት እና ግብ አግቢነት ለመሸለም የበቃባቸው ዓመታት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በግሉ ስኬትን ያስመዘገብኩባቸው ዓመታት በ1977 ዓ.ም፤ በ1978 ዓ.ም እና በ1986 ዓ.ም ኮከብ ግብ አስቆጣሪ በ1978 ዓ.ም፣ በ1980 ዓ.ም እና በ1982 ዓ.ም ኮከብ ተጫዋች በመሆን በኢትዮጵያ ሻምፒዮናዎች ላይ ለመሸለም በቅቷል። የአዲስ አበባ ኮከብ ተጫዋችና ጎል አስቆጣሪ የሆነባቸው ዓመታቶች ነበሩ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ለቀደሞ የክለባችንና የብሔራዊ ቡድን ምርጡ ተጨዋች ለነበረው ሙሉጌታ ከበደ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን መሪር ሀዘን እየገለፀ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ለእግር ኳሱ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
Call for papers on AI to AI Journey* conference journal has started!
Prize for the best scientific paper - 1 million rubles!

Selected papers will be published in the scientific journal Doklady Mathematics.

📖 The journal:
- Indexed in the largest bibliographic databases of scientific citations
- Accessible to an international audience and published in the world’s digital libraries.

Submit your article by August 20 and get the opportunity not only to publish your research the scientific journal, but also to present it at the AI Journey conference.

More detailed information can be found in the Selection Rules -> AI Journey
ትራምፕ በ5 ሚሊዮን ዶላር ቋሚ የአሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያሰጠውን "ጎልድ ካርድ" አስጀመሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ5 ሚሊዮን ዶላር ቋሚ የአሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ ለሚያሰጠው "ጎልድ ካርድ" ፕሮግራም ማመልከቻዎችን መቀበል መጀመሩን አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ አመልካቾች "ትራምፕ ካርድ" ወይም "ጎልድ ካርድ" ለተሰኘው ፕሮግራም ፍላጎታቸውን የሚያስመዘግቡበትን ድረ-ገጽ ይፋ አድርገዋል።

ድረገጹም TrumpCard.gov እንደሚሰኝና የተጠባባቂዎች ዝርዝር ምዝገባ መጀመሩንም ገልጸዋል።

ትራምፕ ትሩዝ በተሰኘው ሶሻል ሚዲያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት "በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየደወሉ 'በዓለም ላይ ወደር ወደሌላት ታላቅ ሀገርና ገበያ ለመግባት የሚያስችለውን ውብ መንገድ እንዴት ማግኘት እንችላለን?' እያሉ ይጠይቃሉ" ብለዋል።

ትራምፕ ባለፈው የካቲት ወር አስተዳደራቸው ለባለሃብት አመልካቾች የመኖሪያና የሥራ መብቶችን የሚያገኙበትን እንዲሁም ዜግነት ለማግኘት መንገድ የሚከፍተውን "ጎልደን ካርድ" የተሰኘ ፕሮግራም እንደሚያቀርብ ተናግረው ነበር።

"በዚህ መንገድ የሚመጡትን ባለሃብቶች ስኬታማ ይሆናሉ፤ ብዙ ገንዘብ በማውጣትም ብዙ ግብር ይከፍላሉ፤ ለብዙ ሰዎችም የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ" ሲሉ በወቅቱ ተናግረዋል።

የትራምፕ አስተዳደር ባለስልጣናት አዲሱ ፕሮግራም በአሜሪካ ቢያንስ 1.05 ሚሊዮን ዶላር ወይም በኢኮኖሚ በተጎዱ አካባቢዎች 800 ሺህ ዶላር ኢንቨስት ለሚያደርጉ ስደተኞች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያሰጠውን የኢቢ-5 (EB-5) የኢንቨስተር ቪዛ ፕሮግራምን ሊተካ እንደሚችል ጠቁመዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
242 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ

242 ሰዎችን ከአሕመዳባድ አሳፍሮ ወደ ለንደን በመብረር ላይ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ተከሰከሰ፡፡

ቦይንግ 787- 8 የሚል ስያሜ ያለው አውሮፕላኑ በምዕራብ ሕንድ አሕመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ ምድር እንደለቀቀ በቅጽበት መከስከሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በአደጋው አውሮፕላኑ በእሳት ተያይዞ ሲቃጠል የሚያሳዩ ምስሎች የወጡ ሲሆን ÷ እስካሁን የደረሰውን ጉዳት በሚመለከት የወጣ ዝርዝር መረጃ አለመኖሩ ተመላክቷል፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎥ቪዲዮ
ከ230 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ሲከሰከስ
በሕንዱ የአውሮፕላን አደጋ እስካሁን የ204 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል፡- የሀገሪቱ ፖሊስ

በሕንድ 242 መንገደኞችን አሳፍሮ ወደ ለንደን ሲበር በተከሰከሰው የአውሮፕላን አደጋ እስካሁን የ204 ሰዎች አስክሬን መገኘቱን የሀገሪቱ ፖሊስ ገልጿል፡፡

የተገኙት ሁሉም አስክሬኖች በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች አልያም አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ስፍራ ምድር ላይ የነበሩ ሰዎች ስለመሆኑ አለመታወቁን ቢቢሲ የሀገሪቱን መንግስት ፖሊስ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ከሕንድ አህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ለንደን በመብረር ላይ የነበረው ቦይንግ 787- 8 ድሪምላይነር አውሮፕላን፣ ከመሬት በተነሳ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ በመከስከሱ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት የነብስ አድን ሰራተኞች በስፍራው ተሰማርተዋል፡፡

በዚህም የሕክምና እና የሰብዓዊ ድጋፍ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሀገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን አስታውቋል፡፡የደረሰው አደጋ አስከፊ በመሆኑ የተሳፋሪዎች በሕይወት የመገኘት እድል አነስተኛ መሆኑን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን እየዘገቡ ነው፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
የሙሉጌታ ከበደ የቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ

ከምንጊዜም ምርጥ ኢትዮጵያውያን የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሙሉጌታ ከበደ ቀብር ሥነሥርዓት ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።

ዛሬ ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር ከተደረገ በኋላ ቤተሰቦቹ፣ የእግር ኳስ አፍቃሪያን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና የክለብ ተወካዮች በተገኙበት ነው ሥርዓተ ቀብሩ የተፈጸመው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮከብና የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሙሉጌታ ከበደ ባጋጠመው ህመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡

ሙሉጌታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ለበርካታ ዓመታት በድንቅ ብቃት ተጫውቶ አሳልፏል፡፡በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ በነበረው ቆይታ አምበል ሆኖም መጫወት የቻለ ድንቅ ተጫዋች ነበር።


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
አንድ ሰው ተርፏል, 290 ሰወች ሙተዋል!!

ከህንድ አውሮፕላን አደጋ የተረፈው ግለሰብ

ከህንድ የአህመዳባድ አውሮፕላን አደጋ አንድ ሰው በህይወት ተገኝቷል! ፖሊስ መጀመሪያ ላይ ማንም አልተረፈም ቢልም፣

አሁን ይህን ተአምራዊ መትረፍ አረጋግጧል። ከተረፉት አንዱ እንግሊዛዊ ሲሆን፣ ከመስኮት ዘሎ ህይወቱን ማትረፉ ተዘግቧል።

የአይን እማኝ ምስክርነት: "አውሮፕላኑ ከመሬት ከተነሳ 30 ሰከንዶች በኋላ ከባድ ድምጽ ተሰማ፤ ከዚያም ተከሰከሰ፤ ሁሉም ነገር በከፍተኛ ፍጥነት ነው የሆነው" ሲል የተረፈው እንግሊዛዊ ገልጿል።

የሟቾች ቁጥር: እስካሁን 290 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል፣ ከእነዚህም ውስጥ 204 አስከሬኖች ተገኝተዋል።

አውሮፕላኑ ሲከሰከስ በመሬት ላይ የነበሩ ሰዎችም አደጋው እንደደረሰባቸው ተጠቁሟል።

* የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች

* 169 ህንዳውያን፣
* 53 እንግሊዛውያን፣
* 7 ፖርቱጋላውያን እና 1
* ካናዳዊን ያካተቱ ነበሩ።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በሀኪሞች ማረፊያ ቤት ላይ ሲሆን፣ አንድ ልጅ ከሁለተኛ ፎቅ በመዝለል እንደተረፈ እናቱ መስክረዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምላሽ: ማርኮ ሩቢዮ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ ልባቸው መሰበሩን ገልጸው፣ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
#Mpox በሽታ

በአማራ ክልል በሁለት ሰዎች ላይ የኤም ፖክስ (Mpox) ቫይረስ መገኘቱን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኤም ፓክስ (Mpox) በሽታ የተያዙ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን ገልፀዋል።

በባህር ዳርና በመተማ ከተሞች በተገኙት ሁለቱ ሰዎች በተወሰደው ናሙና በኤም ፖክስ (Mpox) መረጋገጡን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ተገቢውን ህክምና እየተሰጣቸው መሆኑን አክለው ገልፀዋል።

የኤም ፖክስ ( Mpox) ቫይረስ በቫይረስ የሚተላለፍ በሽታ ነው።

መተላለፊያ መንገዶቹም ፦
- የቅርብ ንክኪ፣
- በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የሚኖር የእጅ መነካካት፣
- በቫይረሱ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸው ቁሳቁሶችን መጠቀም እና የፊት ለፊት የትንፋሽ ግንኙነት ናቸው።

የኤም ፓክስ በሽታ ምልክቶቹ ፦

° ከፍተኛ ትኩሳት፣
° ራስ ምታት፣
° የጀርባ ሕመም፣
° የሰውነት ዕጢ እብጠቶች፣
° ለመተንፈስ መቸገር፣
° በሰውነት ክፍል ጎልተው የሚታዩ ሽፍታዎች ሲሆን ምልክቶችም ህመምተኛው በቫይረሱ ከተያዘ ከ5 እስከ 21 ቀናቶች ውስጥ የሚታዩ ናቸው።

መከላከያ መንገዶች ፦

° በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነቶችን  መገደብ ፣
° እጅን በሳሙና መታጠብ፣
° በበሽታ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በጋራ አለመጠቀም።

አቶ በላይ በዛብህ ለህብረተሰቡ ባስተላለፉት መልዕክት " የኤም ፓክስ በሽታ ተገቢው ህክምና ከተደረገ በቶሎ የሚድን በሽታ ሲሆን የግል ንፅህናን በመጠበቅና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ በሽታውን መከላከል ይቻላል " ብለዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ጥንቃቄ❗️

በኢትዮጵያ የተገኘው የኤምፖክስ ቫይረስ ዝርያ "ከፍተኛ የሞት መጠን" እና "ሥርጭት" ያለው መሆኑ ተገለጸ

ከአንድ ወር በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው የኤምፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) ቫይረስ ዝርያ "ከፍተኛ የሞት መጠን" የሚያስከትል እና በከፍተኛ መጠን የሚሠራጭ እንደሆነ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቁ።

ከሁለት ሳምንት በፊት በበሽታው ሕይወቱ ያለፈው አንድ ወር እድሜ ያለው ሕጻን እንደሆነም ተቋማቱ ገልጸዋል። የጤና ሚኒስቴር እና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይህንን ያስታወቁት ትናንት ረቡዕ ሰኔ 4/2017 ዓ.ም. ምሽት ባወጡት 'ወቅታዊ ማብራሪያ' ነው።

ግንቦት 16 ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የተረጋገጠው ኤምፖክስ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 18 ሰዎችን መያዙን የተቋማቱ መረጃ ያመለክታል። በበሽታው ከተያዙት ሰዎች መካከል አምስቱ "ሙሉ ለሙሉ" ማገገማቸውን መግለጫው ያስረዳል።

የኤም ፖክስ ( Mpox) መተላለፊያ መንገዶቹም ፦

- የቅርብ ንክኪ፣
- በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የሚኖር የእጅ መነካካት፣
- በቫይረሱ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸው ቁሳቁሶችን መጠቀም እና የፊት ለፊት የትንፋሽ ግንኙነት ናቸው።

የኤም ፓክስ በሽታ ምልክቶቹ ፦

° ከፍተኛ ትኩሳት፣
° ራስ ምታት፣
° የጀርባ ሕመም፣
° የሰውነት ዕጢ እብጠቶች፣
° ለመተንፈስ መቸገር፣
° በሰውነት ክፍል ጎልተው የሚታዩ ሽፍታዎች ሲሆን ምልክቶችም ህመምተኛው በቫይረሱ ከተያዘ ከ5 እስከ 21 ቀናቶች ውስጥ የሚታዩ ናቸው።

መከላከያ መንገዶች ፦

° በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነቶችን  መገደብ ፣
° እጅን በሳሙና መታጠብ፣
° በበሽታ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በጋራ አለመጠቀም።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
እስራኤል በመላው ዓለም የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ዘጋች
**

እስራኤል በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ ኤምባሲዎቿንና የቆንስላ ፅህፈት ቤቶቿን በጊዜያዊነት ዘግታለች።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ተለዋጭ መልእክት እስኪሰጥ ድረስ በመላው ዓለም የሚገኙ የእስራኤል ኤምባሲዎችና የቆንስላ ፅ/ቤቶች ተዘግተው ይቆያሉ ተብሏል፡፡

በውጭ ሀገራት የሚገኙ እስራኤላውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ማሳሰቡን ዘገባው አክሏል።

የእስራኤል ጦር በኢራን ላይ በፈፀመው የአየር ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የኒውክሌር ጣቢያዎች እና ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታቱ ተነግሯል፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
2025/06/28 15:58:48
Back to Top
HTML Embed Code: