በሕንዱ የአውሮፕላን አደጋ እስካሁን የ204 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል፡- የሀገሪቱ ፖሊስ
በሕንድ 242 መንገደኞችን አሳፍሮ ወደ ለንደን ሲበር በተከሰከሰው የአውሮፕላን አደጋ እስካሁን የ204 ሰዎች አስክሬን መገኘቱን የሀገሪቱ ፖሊስ ገልጿል፡፡
የተገኙት ሁሉም አስክሬኖች በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች አልያም አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ስፍራ ምድር ላይ የነበሩ ሰዎች ስለመሆኑ አለመታወቁን ቢቢሲ የሀገሪቱን መንግስት ፖሊስ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ከሕንድ አህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ለንደን በመብረር ላይ የነበረው ቦይንግ 787- 8 ድሪምላይነር አውሮፕላን፣ ከመሬት በተነሳ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ በመከስከሱ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት የነብስ አድን ሰራተኞች በስፍራው ተሰማርተዋል፡፡
በዚህም የሕክምና እና የሰብዓዊ ድጋፍ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሀገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን አስታውቋል፡፡የደረሰው አደጋ አስከፊ በመሆኑ የተሳፋሪዎች በሕይወት የመገኘት እድል አነስተኛ መሆኑን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን እየዘገቡ ነው፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ

❤25😱7🤔6👏1
የሙሉጌታ ከበደ የቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ
ከምንጊዜም ምርጥ ኢትዮጵያውያን የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሙሉጌታ ከበደ ቀብር ሥነሥርዓት ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።
ዛሬ ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር ከተደረገ በኋላ ቤተሰቦቹ፣ የእግር ኳስ አፍቃሪያን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና የክለብ ተወካዮች በተገኙበት ነው ሥርዓተ ቀብሩ የተፈጸመው።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮከብና የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሙሉጌታ ከበደ ባጋጠመው ህመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡
ሙሉጌታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ለበርካታ ዓመታት በድንቅ ብቃት ተጫውቶ አሳልፏል፡፡በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ በነበረው ቆይታ አምበል ሆኖም መጫወት የቻለ ድንቅ ተጫዋች ነበር።

❤29😭24👍5👏1
አንድ ሰው ተርፏል, 290 ሰወች ሙተዋል!!
ከህንድ አውሮፕላን አደጋ የተረፈው ግለሰብ
ከህንድ የአህመዳባድ አውሮፕላን አደጋ አንድ ሰው በህይወት ተገኝቷል! ፖሊስ መጀመሪያ ላይ ማንም አልተረፈም ቢልም፣
አሁን ይህን ተአምራዊ መትረፍ አረጋግጧል። ከተረፉት አንዱ እንግሊዛዊ ሲሆን፣ ከመስኮት ዘሎ ህይወቱን ማትረፉ ተዘግቧል።
የአይን እማኝ ምስክርነት: "አውሮፕላኑ ከመሬት ከተነሳ 30 ሰከንዶች በኋላ ከባድ ድምጽ ተሰማ፤ ከዚያም ተከሰከሰ፤ ሁሉም ነገር በከፍተኛ ፍጥነት ነው የሆነው" ሲል የተረፈው እንግሊዛዊ ገልጿል።
የሟቾች ቁጥር: እስካሁን 290 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል፣ ከእነዚህም ውስጥ 204 አስከሬኖች ተገኝተዋል።
አውሮፕላኑ ሲከሰከስ በመሬት ላይ የነበሩ ሰዎችም አደጋው እንደደረሰባቸው ተጠቁሟል።
* የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች
* 169 ህንዳውያን፣
* 53 እንግሊዛውያን፣
* 7 ፖርቱጋላውያን እና 1
* ካናዳዊን ያካተቱ ነበሩ።
አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በሀኪሞች ማረፊያ ቤት ላይ ሲሆን፣ አንድ ልጅ ከሁለተኛ ፎቅ በመዝለል እንደተረፈ እናቱ መስክረዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምላሽ: ማርኮ ሩቢዮ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ ልባቸው መሰበሩን ገልጸው፣ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

❤49😢14👍4🥰3🤔1
#Mpox በሽታ
በአማራ ክልል በሁለት ሰዎች ላይ የኤም ፖክስ (Mpox) ቫይረስ መገኘቱን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኤም ፓክስ (Mpox) በሽታ የተያዙ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን ገልፀዋል።
በባህር ዳርና በመተማ ከተሞች በተገኙት ሁለቱ ሰዎች በተወሰደው ናሙና በኤም ፖክስ (Mpox) መረጋገጡን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ተገቢውን ህክምና እየተሰጣቸው መሆኑን አክለው ገልፀዋል።
የኤም ፖክስ ( Mpox) ቫይረስ በቫይረስ የሚተላለፍ በሽታ ነው።
መተላለፊያ መንገዶቹም ፦
- የቅርብ ንክኪ፣
- በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የሚኖር የእጅ መነካካት፣
- በቫይረሱ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸው ቁሳቁሶችን መጠቀም እና የፊት ለፊት የትንፋሽ ግንኙነት ናቸው።
የኤም ፓክስ በሽታ ምልክቶቹ ፦
° ከፍተኛ ትኩሳት፣
° ራስ ምታት፣
° የጀርባ ሕመም፣
° የሰውነት ዕጢ እብጠቶች፣
° ለመተንፈስ መቸገር፣
° በሰውነት ክፍል ጎልተው የሚታዩ ሽፍታዎች ሲሆን ምልክቶችም ህመምተኛው በቫይረሱ ከተያዘ ከ5 እስከ 21 ቀናቶች ውስጥ የሚታዩ ናቸው።
መከላከያ መንገዶች ፦
° በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነቶችን መገደብ ፣
° እጅን በሳሙና መታጠብ፣
° በበሽታ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በጋራ አለመጠቀም።
አቶ በላይ በዛብህ ለህብረተሰቡ ባስተላለፉት መልዕክት " የኤም ፓክስ በሽታ ተገቢው ህክምና ከተደረገ በቶሎ የሚድን በሽታ ሲሆን የግል ንፅህናን በመጠበቅና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ በሽታውን መከላከል ይቻላል " ብለዋል።

❤50👍4
ጥንቃቄ❗️
በኢትዮጵያ የተገኘው የኤምፖክስ ቫይረስ ዝርያ "ከፍተኛ የሞት መጠን" እና "ሥርጭት" ያለው መሆኑ ተገለጸ
ከአንድ ወር በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው የኤምፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) ቫይረስ ዝርያ "ከፍተኛ የሞት መጠን" የሚያስከትል እና በከፍተኛ መጠን የሚሠራጭ እንደሆነ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቁ።
ከሁለት ሳምንት በፊት በበሽታው ሕይወቱ ያለፈው አንድ ወር እድሜ ያለው ሕጻን እንደሆነም ተቋማቱ ገልጸዋል። የጤና ሚኒስቴር እና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይህንን ያስታወቁት ትናንት ረቡዕ ሰኔ 4/2017 ዓ.ም. ምሽት ባወጡት 'ወቅታዊ ማብራሪያ' ነው።
ግንቦት 16 ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የተረጋገጠው ኤምፖክስ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 18 ሰዎችን መያዙን የተቋማቱ መረጃ ያመለክታል። በበሽታው ከተያዙት ሰዎች መካከል አምስቱ "ሙሉ ለሙሉ" ማገገማቸውን መግለጫው ያስረዳል።
የኤም ፖክስ ( Mpox) መተላለፊያ መንገዶቹም ፦

❤82👍23😱5🤯2🤔1
እስራኤል በመላው ዓለም የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ዘጋች
**
እስራኤል በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ ኤምባሲዎቿንና የቆንስላ ፅህፈት ቤቶቿን በጊዜያዊነት ዘግታለች።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ተለዋጭ መልእክት እስኪሰጥ ድረስ በመላው ዓለም የሚገኙ የእስራኤል ኤምባሲዎችና የቆንስላ ፅ/ቤቶች ተዘግተው ይቆያሉ ተብሏል፡፡
በውጭ ሀገራት የሚገኙ እስራኤላውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ማሳሰቡን ዘገባው አክሏል።
የእስራኤል ጦር በኢራን ላይ በፈፀመው የአየር ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የኒውክሌር ጣቢያዎች እና ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታቱ ተነግሯል፡፡

❤68👍51😱7🤔6🥰5
የኢራን የሚሳኤል ጥቃት በእስራኤል መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመት ማድረሱ ተገለፀ
*****
ኢራን አርብ ዕለት በሰሜናዊና በማዕከላዊ እስራኤል ላይ የፈፀመችው ከባድ የሚሳኤል ጥቃት በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመት ማድረሱ ተገልጿል፡፡
የእስራኤል ወታደራዊ እርምጃ ተከትሎ ኢራን በእስራኤል ከተሞች ላይ በሁለት ዙር ከ150 በላይ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል መተኮሷ ተዘግቧል፡፡
የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት፤ በጥቃቱ ቢያንስ 10 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል፡፡
በጥቃቱ ከ100 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ቢቢሲ የእስራኤል የአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃንም ጠቅሶ ዘግቧል።
ስካይ ኒውስ የኢራንን ወታደራዊ ምንጮች ዋቢ በማድረግ እንደዘገበውም፤ ኢራን በፈፀመችው ጥቃት እያንዳንዳቸው 80 ሚሊዮን የሚያወጡ የእስራኤል ኤፍ35 ተዋጊ ጄቶችን መትታ መጣሏን ገልጻለች፡፡
እስራኤል በበኩሏ በፈፀመችው ጥቃት በቴህራን የነዳጅ ማከማቻ መጋዘን ላይ ውድመት ማድረሷን አስታውቃለች፡፡
እስራኤል ኢራንን ለመምታት ከተጠቀመችባቸው 100 የጦር ጄቶች መካከል እጅግ ዘመናዊ የሆኑት አዲር የሚል ስያሜ የተሰጣቸው እነዚህ ኤፍ35 ጄቶች እንደሚገኙበት ተነግሯል፡፡
የጦር አውሮፕላኖቹን ወደ ግዳጅ ለማሰማራት በሰዓት ለያንዳንዳቸው ከ44 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግም ነው የተገለፀው።

❤83👎8🤔2
የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና
(25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም)
💡ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 7-18 ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ ነው።
💡 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
💡 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል
💡 ስልጠናው ጤናማ የ ስናክ ጊዜ ያካታል
ፓኬጁ የሚያካትተው:
• Basic Computer skill
• Computer Programming
• Visual art and painting
• Language (chosen)
• Abacus and Math tips
የስልጠናው መጨረሻ ላይ
1.ፕሮጀክታቸውን ያቀርባሉ
2. ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል
ይደውሉ
☎️
0989747878
0799331774
በመራህያን የወደፊት ብሩህ ተስፋዎን የሚዘሩ ክህሎቶችን ይማራሉ !!
📍ሃያ ሁለት ፣ ከጐላጐል ወደ ቦሌ ሚወስደው ከ Hanan K Plaza አጠገብ ቢጫ ፎቅ ግራውንድ ፍሎር 10B
ለበለጠ መረጃ፦ @merahyan

❤25
ኢራናውያን ከወታደራዊ ተቋማት አካባቢ እንዲርቁ እስራኤል አሳሰበች
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ኢራናውያን ከወታደራዊ ተቋማት አካባቢ እንዲርቁ አሳስቧል፡፡
የኢስራኤል ጦር የጥቃት ኢላማ የተደረገባቸው እና የኢራን የኒውክሌር ማበልጸጊያ ፕሮግራም የሚካሄድባቸው ማእከሎች አካባቢ የሚኖሩ የቴሄራን ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ነው ያሳሰበው፡፡
ኢራን የኒውክሌር ማበልጸጊያ በምታካሂድበት ማእከል ላይ እስራኤል ጥቃት ልትፈጽም ስለምትችል የቴሄራን ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር እስራኤል ካትዝ ማሳሰባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንዲሁም ሚኒስትሩ በወታደራዊ የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎች እና በአካባቢው ባሉ የጦር ካምፖች የሚገኙ ሰዎች ስፍራውን ለቅቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ አቅርበዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሩ የቴሄራን ነዋሪዎች ከወታደራዊ ተቋማት አካባቢዎች እንዲወጡ የሰጡት ማሳሰቢያ በኢራን ላይ ጫና ለመፍጠር ያለመ ሊሆን እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

❤108😁9🤯4👏3👍1
የቴልአቪቭ እና የሃይፋ ጥቃት ቴህራንን ዋጋ ያስከፍላታል፦ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር
ኢራን በእስራኤል ቴልአቪቭ እና በወደብ ከተማዋ ሃይፋ በፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት 8 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ተጎድተዋል።
በጥቃቱ የመኖሪያ መንደሮች እና ህንፃዎችም መውደማቸው ተገልጿል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ቴህራን በቴልአቪቭ እና ሃይፋ በፈፀመቻቸው ጥቃቶች ዋጋ ትከፍላለች ብሏል።
ኢራን ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ እስራኤል ላይ በፈፀመችው የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት 23 ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
በእስራኤል የወደብ ከተማ ሃይፋ ወደብ አካባቢ የእሳት ቃጠሎ ሲታይ እንደነበርም ሮይተርስ ፅፏል።
የቴህራን የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶች በቴልአቪቭ፣ እየሩሳሌም እና ሃይፋ የመኖሪያ መንደሮችን አውድመዋል።
ይህ ውድመት ቴህራንን ዋጋ ያስከፍላታል ስትል እስራኤል ዝታለች። በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ኢራናውያን ቁጥር ደግሞ 224 መድረሱን የኢራን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

❤68👎6🙏4👍2
እስራኤል “የቴህራንን የአየር ክልል በሙሉ” መቆጣጠሯን ገለፀች!!
የእስራኤል እና የኢራን ጥቃት በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት እስራኤል የቴህራንን የአየር ክልል መቆጣጠሯን አስታወቀች።
የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ እስራኤል “ የቴህራንን አየር ክልል ሙሉ በሙሉ መቆጣጣር ችላለች” ሲሉ ተናግረዋል። ብርጋዴር ጄኔራል ኤፊ ዴፍሪን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ላይ “የኢራን አንድ ሦስተኛ የምድር ለምድር የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን አውድመናል” ሲሉ ተናግረዋል።
የእስራኤል ጦር ከ120 በላይ የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን ገልጿል።እስራኤል አርብ ዕለት ጥቃት መሰንዘር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ኢራን ከያዘችው አጠቃላይ ማስወንጨፍያዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛውን ማውደሟን ገልጻለች።
የአየር ኃይሉ ትናንት ምሽት ብቻ ከ20 በላይ ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን የገለፁት ቃል አቀባዩ፣ “ከደቂቃዎች በፊት” ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ለማስወንጨፍ ጥቅም ላይ ውለው እንደነበር ዴፍሪን ተናግረዋል።እስራኤል በማዕከላዊ ኢራን ኢስፋሃን ውስጥ ወደ 100 የሚጠጉ ወታደራዊ ዒላማዎችን ላይ ጥቃት ለማድረስ 50 የሚጠጉ ተዋጊ ጄቶችን ማሰማራቷን ተናግረዋል። በዚህ ጥቃትም የሚሳኤል ማከማቻ ስፍራዎችን፣ ማስወንጨፊያዎችን እና የማዘዣ ማዕከሎችን አውድማለች ብለዋል።

❤92👍17👎8😁8🤯4🤔3👏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስራኤል የኢራንን የመንግስት ቴሌቪዥን ዋና መስሪያ ቤት በቀጥታ ስርጭት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተዘግቧል።
የኢራን ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ በሚሳኤል ተመቷል፡፡
የእስራኤል ሀይሎች በዛሬው እለት በፈፀሙት ጥቃት የኢስላሚክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኢራን ኒውስ ኔትወርክ(ኢሪን) ዋና ፅህፈት ቤት ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በዚህም በቀጥታ ስርጭት ላይ የነበረው የቴሌቪዥን ጣቢያው ተቋርጧል፡፡
ይህ ጥቃት የደረሰው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኢል ካትዝ ‹‹የኢራን የፕሮፖጋንዳና አፈቀላጤ መሳሪያዎች እንዲጠፉ ይደረጋሉ›› ካሉ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ነው፡፡ የኢራን ሚዲያዎች እንደዘገቡት ይህ ጥቃት የተፈፀመው ዜና አቅራቢዋ በእስራኤል ላይ ትችት እያቀረበች እያለ ነበር፡፡
የቴሌቪዥን ስቱዲዮው በጥቃቱ ተመቶ ግድግዳው ሲፈራርስ በቀጥታ ስርጭት የታየ ሲሆን አቅራቢዋም ወዲያውኑ ከመቀመጫዋ ተነስታ ከአካባቢው ወጥታ ሄዳለች፡፡
ቪዲዮ፦ የማህበራዊ ትስስር ገጾች

❤42😁34👍21👎10😱2👏1🤔1

❤29