የመስማት ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች በመለየት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
የመስማት አቅም መለካት የሚያስችል የኦዲዮ ሜትሪ /Audiometry/ መሳሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
------------------------------------------------------
(ሰኔ 16/2017 ዓ.ም) የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራትና ማሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሐንስ ወጋሶ (ዶ/ር) በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት የመስማት ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች በመለየት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
ጉዳታቸውና ችግራቸው ሳይለይ ትምህርት ቤት ውስጥ እንደ ሰነፍ የሚቆጠሩ ተማሪዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ዩሐንስ ትምህርት ቤት እያሉ በመስማት ችግር የሚፈለገውን ክህሎትና እውቀት ያልጨበጡ ተማሪዎች ለመደገፍ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Ehnc5LdEw/

በሐረሪ ክልል የትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት በዲስትሪክት ደረጃ ሲካሄድ የነበረው የ2017 የት/ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድር ተጠናቀቀ።
----------------------------------------------
(ሰኔ 16/2017 ዓ.ም) በ14 የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መካከል ከሰኔ ሰባት ጀምሮ በድምቀት ሲካሄድ የነበረው የ2017 ስፖርት ሊግ ውድድር ማጠቃለያውን አግኝቷል።
በቅርጫት ኳስና ቮሊ ቦል የፍፃሜ ጨዋታ የተደረገ ሲሆን በቅርጫት ኳስ አው አብዳል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአባድር አቻውን 57 ለ 52 በማሸነፍ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
በቮሊቦል ፍፃሜ ጨዋታ አባድርና መዕሪፍ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባደረጉት የዋንጫ ጨዋታ መዕሪፍ 2 ለ 0 በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችሏል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1B2nsZMiAk/

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገር-በቀል እውቀትን በመሰነድና በማበልጸግ ለማህበረሰብ ጥቅም ማዋል እንደሚጠበቅባቸው ተመላከተ፤ በሀገር-በቀል እውቀት ዙሪያ አውደጥናት ተካሂዷል።
--------------------------------------------------
(ሰኔ 18/2017 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተ/መሪ ስራ አስፈጻሚ ሠራዊት ሃንዲሶ(ዶ/ር) በአውደ ጥናቱ ላይ እንደገለጹት አገር-በቀል እውቀት ለተሻለ አገር ግንባታና ለማህበረሰብ እድገት እንዲውል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገር-በቀል እውቀትን በመለየት፣መሰነድ፣ በየዘርፉ ማደራጀት፣ መመርመር፣ ማወቅ፣ መረዳት እና ማበልጸግ እንደሚገባቸውም ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር አገር-በቀል እውቀትን በአደረጃጀት ፣ በአሰራርና በግብዓት በመደገፍ ዘርፉ ለማህበረሰብ ልማትና ለአገር እድገት ጥቅም ላይ እንዲውል እየሰራ መሆኑን መሪ ስራ አስፈጻሚው አመልክተዋል።
የማህበረሰብ ጉድኝት እና አገር በቀል እውቀት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላም አለሙ በበኩላቸው ሀገር-በቀል ዕውቀት፣ ለአከባቢ ጥበቃና ለዘላቂ ልማት ግቦች መሳካት ያለው አስተዋፅዖ እየጎላ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫም ማግኘት ትችላላችሁ፤
https://www.facebook.com/share/p/1DDcgZ1Bzw/

አገር አቀፍ የቅድመ ልጅነት ዕድገትና ትምህርት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
------------------------------------------------
(ሰኔ 17/2017 ዓ.ም) በንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ባለፉት ሁለት አመታት በመንግስትና በማህበረሰቡ በተሰሩ ስራዎች የቅድመ አንደኛ ትምህርትን በማስፋፋትና ተደራሽ በማድረግ ረገድ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑ ተገልጿል።
"ልጆቻችን ብሩህ ነገን እንዲፈጥሩ መሠረቱን ዛሬ እንጣል " በሚል በተከናወነው መርሃ ግብር ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የሌሎች ባለድርሻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት የቅድመ ልጅነት እድገትና ትምህርት ላይ የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ሊሠራበት የሚገባው ጉዳይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን አሁን ላይ ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የልማት አጋሮች ጋር በተፈጠረው ቅንጅታዊ አሰራር አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት የትምህርት ጥራትን በማጐልበት የሀገርን ብልጽልግና በማረጋገጥና ዜጎች ከሚመዘገበው ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ትምህርት ቁልፍ ሚና ያለው መሆኑን በመግለጽ የቅድመ ልጅነት እድገትና ትምህርት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1Fn8WFGMfh

ኦስትሪያ እና ኢትዮጵያ በከፍተኛ ትምህርቱ ዘርፍ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን ውይይት አካሄዱ።
-------------------------------------------
(ሰኔ 18/2017 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በኦስትሪያ ምክትል የፋይናንስ ሚኒስትር ‘H.E. Andreas REICHHARDT’ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚሁ ወቅት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የትምህርት ጥራትና ብቃትን ለማረጋገጥ እየተተገበሩ ያሉ ሪፎርሞችን ለልዑካን ቡድኑ አብራርተውላቸዋል።
በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተልዕኮና ትኩረት መስክ በመለየት በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተው በዘርፉ የበለጠ ውጤታማ ለመሆን በትብብር የሚሰሩ ተግባራት መኖራቸውንም አብራርተዋል።
የኦስትሪያ ምክትል የፋይናን ሚኒስትር H.E. Andreas REICHHARDT በበኩላቸው ኦስትሪያና ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ የቆየ ትብብር እንደነበራቸው አንስተው ይህንን ትብብር የበለጠ አጠናክረው መቀጠል እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/16e9wjFp2b/