Telegram Web Link
ዩኒቨርሲቲዎች የተሠጣቸውን ተልዕኮ በሚገባ ለይተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ፤

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቦንጋ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል።
-------------------------------------------

(ሰኔ 24/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች አንድ ጊዜ ከተከፈቱ ተጠያቂነት የለም ማለት አይደለም፦ በተሠጠው ተልዕኮ መሠረት ካልሰሩ የተጠያቂነት ሥርዓት ሊዘረጋ ይገባል ብለዋል።

በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች በእውነትና እውቀት ለሀገር የሚጠቅም ውይይት የሚደረግባቸው፣ ብቃት ያላቸው የሰው ሃይል ማፍራት የሚችሉ ትክክለኛ ዩኒቨርሳል የሆነ አቋም ሊኖራቸው ይገባል ለዚህም ትኩረት ተሠጥቶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስት ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች አለም አቀፍ እውቀት የሚገበይባቸው ተቋማት በመሆናቸው ተቋማዊ አሰራርን መዘርጋት ተገቢ ነው ለዚህም የዩኒቨርስቲ አመራር ምደባ በእውቀትና በአለም አቀፍ ውድድሮች ሊሆን ይገባል ያሉ ሲሆን

እንደ ሀገር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚሰራው ሥራ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/19QmuzJJF7/
የበይነ መረብ ፈተና ተማሪዎች በራስ መተማመንን አዳብረው ፈተና እንዲሰሩ እድል እንደሚሰጥ ተጠቆመ፡
ከ299ሺ የሚበልጡ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡
-------------------//-----------------------------
የትምህርት ሚኒስትር ደኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በአዲስ አበባ  በበይነ መረብ የሚፈተኑ የማህበራዊ  ሳይንስ ተማሪዎችን ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት እንደገለጹት የበይነ-መረብ ፈተና ተማሪዎች በራሳቸው ተማምነው ባወቁትና በተዘጋጁበት አግባብ ፈተና መስራት እንዲችሉ እድል የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

የበይነ መረብ ፈተና ተማሪዎች በአቅረቢያቸው ሆነው ከቤታቸው እየተመላለሱ እንዲፈተኑ  እድል እንደሚፈጥር የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ደኤታዋ በፈተና ጣቢያዎች ባደረጉት ምልከታም ፈተናው በተሻለ ሁኔታ እየተካሄደና ተማሪዎችም በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን እየወሰዱ መሆናቸውን ለመታዘብ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

አክለውም የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ተጠናቆ የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና መጀመሩን የገለጹት ወ/ሮ አየለች በቀጣይ ያሉ ፈተናዎችንም ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲፈተኑና መልካም እድልም እንዲገጥማቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ / ዶ/ር/ በበኩላቸው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ.ም በሚሰጠው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከ299 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን በወረቀትና በበይነ መረብ እንደሚወስዱ ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የ2017 የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና 608ሺ በላይ ተማሪዎች በመላ አገሪቱ ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንም ዋና ይሬክተሩ አስታውሰዋል፡፡
በአገሪቱ ተመጣጣኝና ፍትሃዊ የትምህርት ዘርፍ ልማትን ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፡፡
የትምህርት ቤቶችን ሥርጭት የሚያሳይ የዲጂታል ካርታ የትምህርት ሚኒስትሩ በተገኙበት ይፋ ሆኗል።
---------------------------------//---------------------------------------------------
(ሐምሌ 03/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በሀገሪቱ ተመጣጣኝ የሆነ የትምህርት ዘርፍ ልማትን ለማምጣት ትምህርት ቤቶች ግልጽና ትክክለኛ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ እንዲገነቡ የሚያስችል ዲጅታል የትምህርት ቤቶች ስርጭት ካርታ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት በነበረው አሰራር የትምህርት ቤቶች ግንባታ ምርጫ የሚወሰነው በገለልተኝነትና በበቂ መረጃ ሳይሆን በዘር ፣ በትውወቅና ፖለቲካዊ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ እንደነበረም ፕሮፌሰር ብርሃኑ አስገንዝበዋል፡፡

በመሆኑም በአዲሱ ስርዓት ማንኛውም በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶችን የመገንባት ፍላጎት ያለው ሰውም ሆነ ለጋሽ ድርጅት የትኛውንም የመንግስት ባለስልጣን ወይም ተጽእኖ ፈጣሪ መጠየቅ ሳያስፈልገው በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ ትምህረት ቤቶችችን መገንባት እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

አክለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የትምህርት እድል ማግኘት እንዳለበት አንስተው ለሁሉም ዜጎች ትምህርትን በፍትሃዊነት ለማድረሰ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ሙሉ ዜናውን ለማግኘት https://web.facebook.com/share/p/1F5p3r4wEB/
ማስታወቂያ
ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርቱ ዘርፍ ያላትን ትብብር አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ተገለጸ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር Ambassador Monday የተመራ የልዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
------------------------------------//-----------------------------------
(ትምህርት ሚኒስቴር/ ሐምሌ 04/2017 ዓ.ም)በዚሁ ጊዜ ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር የቆየ ግንኙነት በተለይም በትምህርቱ ዘርፉ ጠንካራ ትብብር እንደነበራት ጠቅሰው አሁን ኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ትኩረት በመስጠት እየወሰደቻቸው ያሉ የሪፎርም እርምጃዎችን አብራርተዋል።

የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር Ambassador Monday በበኩላቸው ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም ጊዜ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት እንደነበራት አንስተው ይህንን ታሪካዊ ግንኙነት ሀገራቸው የበለጠ አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

አክለውም በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ የትምህርት እድል አግኝተው ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል 200 የሚሆኑት በሀገራቸው መንግስት በተለያዩ ቦታዎች ተቀጥረው አገልግሎት እየሰጡ በመሆኑ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ሁለቱ አካላት በነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያ ነጻ የትምህርት እድል የምትሰጣቸው ደቡብ ሱዳናውያንን በሚመለከት፣ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርስቲ የሚደረግ ትብብር፣ በጋራ የሚሰሩ ጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲሁም ለደቡብ ሱዳን የትምህርት ሚኒስቴር እና ለከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ግንባታ ሥልጠናና ድጋፍ በሚደረግባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ሙሉ ዜናውን ለማግኘት https://web.facebook.com/share/p/1ZbXuAZULS/
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ ከሚገኘውን የአለም ባንክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርኡ ዌንድሊን ክብዌ ከተመራ ቡድን ጋር ውይይት አካሄዱ።
-----------------------//---------------------
(ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ በትምህርት ዘርፉ በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚሰሩ እና በቀጣይ በሚኖሩ ግንኙነቶች ዙሪያ ከኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሩ ጋር ተወያይተዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም የትምህርት ተደራሽነት ለማስፋፋት በሰፊው ቢሰራም ከፍተኛ የጥራት ችግር የነበረበት መሆኑን በመጥቀስ ይህንን ለመለወጥ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ዘርፈ ብዙ የትምህርት ዘርፍ ሪፎርሞች ለዳይሬክተሩ አብራርተውላቸዋል።

በተለይም ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት እና ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው እነዚህ ከትምህርት ጥራት ጋር የተያያዙ ሪፎርሞችን ተግባራዊ ለማድረግ ከሚረዱ የትምህርት ልማት አጋር ድርጅቶች ጎን ለጎን የአለም ባንክ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

የዓለም ባንክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርኡ ዌንድሊን ክብዌ በበኩላቸው ትምህርት የዓለም ባንክ የቅድሚያ ትኩረት ጉዳዩ መሆኑን በመጥቀስ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉን ለመቀየርና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚሰራውን ሥራ በአድናቆት እንደሚመለከቱት ገልጸዋል።

አክለውም በቅርቡ በሚዘጋጀው የ5 ዓመት እና የ10 ዓመት የኢትዮጵያ እና የአለም ባንክ የትብብር ስትራቴጂ ላይ በተለይም የትምህርት ዘርፉን በሚመለከት ክቡር ሚኒስትሩ እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።
2025/07/13 14:09:07
Back to Top
HTML Embed Code: