Telegram Web Link
በመጀመሪያ ኸሚስ ምሽት ሊለቀቅ የነበረው የ ፉአድ ሸምሱ ሠላሜ የተሰኘ ስራ ባለመለቀቁ ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን። በተለያዩ Pre-Production እና Post-Production ስራዎች ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች አስፈላጊ መሆኑን ተረድተን ቆንጆ ስራ ወደናንተ ለማቅረብ ስንል ማራዘማችን ግድ ነበር። አሁን ግን ጥበቃው አብቅቷል። ማክሰኞ ማታ በ አል-ፋሩቅ መልቲሚድያ ፕሮዳክሽን ዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል። ሰብስክራይብ ካላደረጉ ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ሆነው ማክሰኞንና ሠላሜን ይጠባበቁ።🌝🌝
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በእንስሳት ስም የተሰየሙ አምስት የቁርዓን ምዕራፎች 🌙

#ramadan #quranverse #menzuma #ayatulkursi #quran #islamicquotes
ሠላሜ
#ramadan17 #battleofbadr
በዛሬው እለት ነበር በአስራ ሰባተኛው ረመዳን ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በዳዕዋቸው ያደረሱባቸው የዲኑም የእሳቸውንም ጠላቶች ገጥመው ድል ያደረጉት።

የበድር ጦርነት በታላቁ በረመዳን ወር በ624 (ዓ.ም)  የተካሄደ ጉልህ እና አስገራሚ ጦርነት ነው። በታላቁ ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም መሪነት በመዲና ሙስሊም ማህበረሰብ እና በመካ የቁረይሽ ጎሳ መካከል የተካሄደው ይህ ጦርነት በእስልምና ታሪክ ውስጥ ወሳኝ ቦታን ይወስዳል ።

ሙስሊሞችን ለማጥፋት እያደገ የመጣውን ተፅዕኖ ለመቅረፍ ሞከሩ ምንም እንኳ ቁጥራቸው ከነሱ አንፃር እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ይህ የቁጥር ማነስ ሳይበግራቸው በነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እየተመሩ ውጊያቸውን ጀመሩ።

በድር በጣም ብዙ ነገር የታየበት፤ አላህ ለነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የገባላቸውን ቃል የሞላበት ነው። ይህ ጦርነት ፉርቃን ተብሎ ተሰይሟል። ፉርቃን መለየት ማለት ሲሆን ምክናያቱ ደግሞ በዚያ ቀን አላህ እውነትን ከውሸት ስለለየ ነው።  በዚህ እለት ምዕመናን ታላቅ ድል ተሰጣቸው በተቃራኒዉ ደግሞ እያደገ የመጣውን እስልምና የማጥፋት ስራ ተስፋን ያጨለመበት ቀን ነው።

በበድር ከተደረጉ በርካታ ተዓምራት መካከል አንዱ ሁለቱ ቡድኖች በጣም እየተቀራረቡ በመጡ ቁጥር በዚያ ቅፅበት አላህ ከሃዲዎችን በሙስሊሞች አይን ጥቂት ማስመሰሉ አንድ ተዐምር ነው። ስለዚህም ቁረይሾች ሙስሊሞችን ሲያዩ እና ሲታዩ በጣም ጥቂት ሲሆኑ ሳቅ ብለው
[غر هؤلاء دينهم ] (ሰዎች በሃይማኖታቸው ተታልለዋል ብለው አሾፍ።  አቡ ቀታዳህ እንዳለው አቡ ጀህል ነቢያችንን እና ሰሀባዎቹን ባየ ጊዜ '" በአላህ እምላለሁ ከዚህ ቀን በኋላ አላህን አያመልኩም '" እንዳለ ተናግሯል ።

ምንም እንኳ በቁጥር የማይመጣጠኑ እና የማይገናኙ ቢሆንም የአላህ መልዕክተኛም ሆነ ሰሀባዎች እምነታቸው በቁጥር ሳይሆን በአላህ ነበርና  ለሊቱን በሙሉ "ያሐዩ ያቀዩም " እያሉ አላህን እየተማፀኑ ያደሩት። አላህም 3000 መላዒካ እርዳታውን ልኮ የነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምን የበላይነት ያሳየበት ትልቅ የድል ቀን ነበር በመጨረሻም ይህን ለማመን የሚከብድ ጦርነት በአላህ እገዛና ተዓምር በድል አጠናቀው ተመለሱ።

#ramadan #battleofbadr17ramadan #battleofbadr٣١٣ #amharicneshida #menzuma #neshida #neshida❤️❤️
2025/07/05 21:58:19
Back to Top
HTML Embed Code: